ar
Feedback
Zeraf Books

Zeraf Books

الذهاب إلى القناة على Telegram

Your #1 Source For Ethiopian Books Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇩🇪🇬🇧🇰🇷🇮🇹~🌎 & Delivering Locally. Work Phone 📲 +251985333153 Inbox Your Inquiries To @Zerafb

إظهار المزيد
7 909
المشتركون
+124 ساعات
-137 أيام
-7330 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+5

photo content

photo content

photo content
+3

photo content
+2

photo content

photo content
+7

photo content
+8

የማስረዳት ሸክም (ሄኖክ ፋሲል) ከልጅነቴ ጀምሮ ለሀገራችን የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች ጥልቅ ፍቅር አለኝ።የምህንድስና ሙያዬ ያስተማረኝ ሥርዓታዊ አስተሳሰብና ትንተናዊ ክህሎት ደግሞ የፍልስፍናና የሥነ-ልቦና መጻሕፍትን በጥልቀት እንድመረምር ትልቅ እገዛ አድርጎልኛል።ማንኛውንም ጉዳይ ለመረዳትና ለመተንተን ሁልጊዜም አመክንዮአዊ መነጽርን መጠቀም እመርጣለሁ።ይህንን ዳሰሳ ያዘጋጀሁት የዳዊት በዛብህን “የማስረዳት ሸክም” የተሰኘው መጽሐፍ የሥነ-አመክንዮ እና የፍልስፍናን ውስብስብ ዓለም ከሙያዬ አንፃር እንዳስስበት ስላስገደደኝ ነዉ። መጽሐፉን የጻፉት ዳዊት በዛብህ ናቸው።ደራሲው በሕግና በፍልስፍና ዘርፍ የዳበረ እውቀት ያላቸውና የረጅም ጊዜ የጥናትና ምርምር ልምድ ያላቸው ናቸዉ። “ሙግት እና አመክንዮ” በሚለው የመጽሐፉ ንኡስ ርዕስ ላይ እንደተገለጸውም ዋነኛ ትኩረታቸው የሰው ልጅን የማመዛዘን ችሎታ ማጎልበት ላይ ነው። መጽሐፉ የረቀቁ ፍልስፍናዊ ሐሳቦችንና የሕግ ሥርዓቶችን የሚጠቅስና ውስብስብ የሆኑ የፍልስፍና መርሆችን ቀላል በሆነ አማርኛ በማብራራት ለሁሉም አንባቢዎች ተደራሽ ያደረገ ነዉ ፤ በሽፋኑ ላይ አትላስ የተባለው ግዙፍ ሰው ምድርን በጀርባው ተሸክሞ የሚያሳይ ምስል ያለዉ ሲሆን ይህ ምስል የመጽሐፉን ዋና ጭብጥ በሚገባ ይወክላል።መጽሐፉ 222 ገጾች ያሉትና በሰባት ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፈለ ነው ፤ የመረጃ ምንጮቹም የረጅም ጊዜ የፍልስፍና እና የሕግ ታሪኮች፣ እንዲሁም የታወቁ ምሁራን ንድፈ ሐሳቦች መሆናቸውን አስተውያለሁ። የመጽሐፉ ዋና ፍሬ ሐሳብ አመክንዮአዊ አስተሳሰብ ለግለሰብም ሆነ ለኅብረተሰብ ዕድገት ወሳኝ ነው የሚል ነው።"የማስረዳት ሸክም" የሚለውን ጽንሰ ሐሳብን በመተንተን፣ ማንኛውም ሐሳብ ወይም እምነት ምክንያታዊ በሆነ ማስረጃ እስካልተደገፈ ድረስ ክብደት እንደሌለው ደራሲው አሳይተዋል። ይህን መጽሐፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ካየናቸው ነገሮች ጋር ማያያዝ እችላለሁ።ነፃነት ከኃላፊነት ጋር ካልተያያዘ ነፃነት እንዳልሆነ አምኛለሁ።በቅርቡ በነፃነት ስላሳለፉት ህይወታቸውና ስለ ሱሳቸው በግልፅ ሲያወሩ የሰማናቸው ብላቴናዋ እና አዶናይ የነፃነትን አዲስ ገፅታ አሳይተውናል።ነፃነት ለሁሉም ሰው የሚገባ መሆኑን ሲያረጋግጡም፣ “የማስረዳት ሸክም” የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ከዚህ ሁኔታ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ተረዳሁ።የመናገር ነፃነት የራሳችንን ታሪክና ስብራት የማቅረብ መብት ይሰጠናል።ነገር ግን፣ ከዚህ ነፃነት ጋር አብሮ የሚመጣው ትልቅ ኃላፊነት አለ።የነፃነት ሸክም የውስጥ ቁስላችንን በኃላፊነት የማስተላለፍ ግዴታን ይጭናል።ይህንን የምንሸከመውም ለምንናገራቸው ነገሮች በምክንያትና በማስረጃ መልስ መስጠት ስንችል ነው። በአጠቃላይ፣ “የማስረዳት ሸክም” በዘመናዊው የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሥራ ነው።እኔ እንደ አንድ ኤሌክትሮኒክስ መሐንዲስ ይህንን መጽሐፍ በማንበቤ፣ አመክንዮአዊ አስተሳሰቤን ለሥራዬ ብቻ ሳይሆን ለግል ሕይወቴም እንዴት እንደምጠቀምበት ተምሬያለሁ።እውነተኛ ነፃነት በምክንያትና በኃላፊነት የሚመራ ሕይወት እንደሆነ በጥልቀት ተረድቻለሁ። Reviewer : Henok Fasil is an associate editor at Think Ethiopia)

photo content

ከሠርቶ አደሮች የመኖሪያ ሠፈር ከፍ ብሎ የሚገኘው ፋብሪካ ጡሩምባ፣ በጥቀርሻ እና በዘይት የተበከለውን ቆሻሻ አየር ሰንጥቆ ው! ው! ው! በማለት በየቀኑ ያጓራል፤ የጡሩንባውን ጥሪ በማክበርም፣ እንቅልፋቸውን ገና ጠግበው ያልጨረሱ እና ፊታቸውንም ያጨፈገጉ ሰዎች ግራጫማ ከሆኑት ትንንሽ ጎጆዎቻቸው ውስጥ በመውጣት ልክ እንደ ደነገጠ በረሮ ክው-ክው እያሉ በፍጥነት እርምጃ መንገዳቸውን ይዘው ይጓዛሉ። ብርዳማ በሆነው የማለዳ ጭለማ የእግረኛ መንገዳቸውን ይዘው እና በቆሻሻ ዘይት የተበከሉት ብዙ መብራቶች ብዥ-ብዥ በሚል ብርሃናቸው መንገዱን እያበሩላቸው ቀዝቃዛ አቀባበል ወደሚያደርግላቸው ወደ ፋብሪካው ትልቅ ድንጋይ ግንብ ቤት ያመራሉ። ጭቃው በእግራቸው ስር ጮቅ-ጮቅ ይላል። ገና ከእንቅልፉ የነቃ ሰው የሚያሰማው ጎርናና ድምፅ በማሰማት አየሩን በባለጌ ፀያፍ ስድቦች እንዲወረር ያደርጉታል። ከዚሁ ጋር በአንድነትም ሌሎች ድምፆች በማጀብ ይቀበሏቸዋል፦ እነዚህም የፋብሪካ ከባድ የጩኸት ድምፅ እና ትሽ-ትሽ! ትሽ-ትሽ! የሚል ድምፅ የሚያሰማው ተን ነው። የቀፈፋቸውና የተኮሳተሩ የሚመስሉት ረዣዥም የሆኑት እና የጠቆሩት የፋብሪካ ጪስ-ማውጫዎች ከስርቶ አደሮቹ መኖሪያ ሰፈር ከፍ ብለው እንደ ሞላላ ግንዲላ ተጀንነው ተገትረዋል። ምሽት ላይ ፀሀይቱ ዘቅዘቅ በማለት በየቤቶቹ መስኮቶች ቢጫማ የብርሃን ጨረሮቿን ስታነፀባርቅ ፋብሪካው ሰራተኞቹን ከድንጋያማ ሆድ-ዕቃው ውስጥ እንደብረት ዝቃጭ በመዘርገፍ ተፍቷቸው እንደ ገና የእግር መንገዱን ይያያዙታል። - መልካቸው ጥላሸት ተለቅልቆ ጠቁሮ፣ የተራበው ጥርሳቸው ግጥጥ ብሎ እና ከአካላቸው የሚወጣው ሙጫማ የሞተር ዘይት ሽታም አየሩን አውርዶት ወደየጎጇቸው የሚያመራውን የእግር መንገድ ይያያዙታል። እስከሚቀጥለው ቀን ድረስ ስራው ስላበቃ እና በየጎጇቸው ውስጥም እራት እና እረፍት የሚጠብቃቸው በመሆኑ ምክንያት ፊታቸው ፈካ ማለት ብቻ ሳይሆን ደስተኛም ይሆናሉ። የፋብሪካው ማሽኖች የሰርቶ- አደሮቹን ጉልበት የሚበቃውን ያህል እንደ ሎሚ ከመጠጡ በሗላ አሁን የእለት ስራው ጊዜ አክትሟል፤ አንዳችም ቀሪ ምልክት ሳይተው ዕለቱ ህይወትን ትቶ ነጉዶአል። (ማክሲም ጎርኪ እናት)

photo content

photo content
+3

ይኼ የኹሉም ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ነው። መነጠል፣ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት ፣ ዋስትና ማጣት፣ ግራ መጋባት፣ ሥጋት፣ የያዙትን መርሳት፣ ራስን መሳት፣ ጠላትን አለመለየት፣ ወዳጅ ላይ ማደባት፣ እ
ይኼ የኹሉም ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ነው። መነጠል፣ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት ፣ ዋስትና ማጣት፣ ግራ መጋባት፣ ሥጋት፣ የያዙትን መርሳት፣ ራስን መሳት፣ ጠላትን አለመለየት፣ ወዳጅ ላይ ማደባት፣ እርካታ ማጣት...

photo content
+9

photo content
+4

photo content
+4

photo content

photo content
+4

photo content
+2