Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
2 332
المشتركون
+1524 ساعات
+917 أيام
+37830 أيام
أرشيف المشاركات
4ኛው ሀገር ዓቀፍ ክህሎት ቴክኖሎጂ እና ጥናትና ምርምር ውድድር ዛሬ በዲጂታል ተወዳዳሪነት ቀን የተለያዩ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው።
የድሬዳዋ አስተዳደርም በአሰልጣኝ በሰልጣኝ እና በኢንተርፕራይዞች ተወክሎ ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ በመወዳደር ላይ ይገኛሉ።
ከሚካሄዱ ውድድሮች ጎን ለጎን የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽኖች እና ባዛር በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ግቢ እየተካሄደ ይገኛል።
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች"
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መነሻ አድርገው የሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎች የሚስተዋለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት መቅረፍ እንደሚያስችሉ ተገለፀ::
ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት በኢንዱስትሪው የሙያ ፍላጎትን አስመልክቶ በተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ::
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት "በቀጣይ እንደ ተቋም በሚኖረን ትግበራና ፕሮጀክቱም ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንደኛው የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ምንነትን ተገንዝቦ ስልጠናዎችን በዛ አግባብ መስጠት በመሆኑ ይህን የፍላጎት ደሰሳ እዲዘጋጅ እድርገናል" ያሉ ሲሆን አክለውም በቀጣይ እንደ ተቋም በምናዘጋጀው የ10 አመት እስራቴጂክ እቅድ ላይ መሰል ጥናቶች እንደ ግብዓት የምናካትት ይሆናልም ብለዋል::
በኢንዱስትሪዎች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ከተደረገባቸው ነጥቦች አንፃር የተገኙ ውጤቶች፣ የተለዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ ለመሙላት በሚያችል መልኩ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ መዘጋጀቱን የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም ይህን ጥናት እንደ መነሻ መሆኑን እና በቀጣይም የትኩረት ማዕከል በሆኑት ዘርፎች ላይ በልዩነትና በጥልቀት መሰል ጥናቶችን በማካሄድ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን በእቅድ መያዙን ገልፀው በዚህ የፍላጎት ዳሰሳ ላይ ለተሳተፉ በሙሉ በኮሌጁ ስም ላቅ ያለ ምስጋናም አቅርበዋል::
በእለቱ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ሰነድ በአሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ እና እሰልጣኝ መ/ር ነዋይ ይልማ አማካኝነት በመድረኩ ተሳታፊ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ካላቸው የትምህርት ዝግጅት አንስቶ ከሚሰሩት ስራ አኳያ ያላቸው ተዛማችነት በዝርዝር የዳሰሰ ሲሆን በርካታ መሰል የተለዩ ክፍተቶችም በቀረበው ሰነድ ላይ ተመላክተዋል::
በመድረኩ በቀረበው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን መነሻ በምድረግም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለሰነዱ ተጨማሪ ግብአቶችም የተገኙበት መድረክ ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
በስራና ክህሎት ቢሮ ደረጃ በተዘጋጀው የእውቅና መርሃ-ግብር ላይ ተጨማሪ ምስሎች📸📸
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
ለ4ኛው አገር ዓቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ ስራዎች እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሮች በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለተሳተፉና ላለፉ ተወዳዳሪዎች የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራ ክህሎት ቢሮ የውድድርና የተነሳሽነት ስሜትን በመፍጠር በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማቱ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን እና አሰልጣኞችን ባለሙያዎችን ለማፍራት በማለም የ2017 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ ስራዎች እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሮች ማካሄዱ ይታወሳል፤
በዛሬው ዕለት በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ፕሮግራም ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደገለጹት፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት በዋናነት በአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር በሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በተለይም ከኢንዱስተሪዎችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን የላቀ ሚና ለማጎልበት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ እና በዚህም አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑንና ይህም መርሃግብር አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከተጣለበት ከፍተኛ ኃላፊነት አንዱ በሙያ ክህሎቱ የበለጸገ የሰው ሀይል ማፍራትና ቴክኖሎጂን የመቅዳት፣ የማሻሻል እና የማሸጋገር ስራ ዋነኛው መሆኑን ገልጸው፡፡ በሙያ ክህሎታቸው የበቁ ቴክኖሎጂስቶችና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ለሚሰሩ አሰልጣኞች፤ ሰልጣኞች፤ ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እንዲሁም ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች ውድድሮችን በማዘጋጀት ማትጋቱ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት ቢሮው ይህን ኃላፊነት በመውሰድ ውድድሮችን በማዘጋጀት ዕውቅናና ሽልማት መርሃግብር ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ መርሃ ግብር በሁሉም ውድድሮች ለተሳተፉና ውጤት ላስመዘገቡ የሰርተፍኬትና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በቀጣይ ድሬዳዋን ወክለው በፌደራል ደረጃ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ

የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራር አባላትን የያዘ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ እያሳየ በሚገኘው ከፍተኛ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ኮሌጆች ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማችን እየመጡ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለትም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋማችን የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አድርጏል::
ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የአፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ የለውጥ ስራዎችም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረገው ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች መደነቃቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ በአጭር ጊዜ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ሞዴል ተደርጎ መወሰድ የሚችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሀሳባቸውን ገልፀዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኟቸውን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡበት ኮሌጅ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
የስራ ማስታወቂያ ለድሬዳዋ ነዋሪዎች በሙሉ
የኢትዮጲያ አየር መንገድ አዲስ የስራ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን በኤሌክትሮኒክስ በሜካኒካል ፣ በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች የተመረቁትን ለመቅጠር ይፈልጋል ።
በመሆኑም እድሜያቸው ከ 18 እስከ 25 እንዲሁም ቁመት ሜትር ከ ስልሳ የሆናቹ ከሚያዚያ 20 አንስቶ እስከ ሚያዚያ 24 2017 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይኖርባቸዋል ።
አስታውሱ የምዝገባው ቀን አጭር ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ !
+1
#እንኳን_አደረሳችሁ!!
በቅድሚያ ለኮሌጃችን ማህበረሰብ እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እንዲሁም የመተሳሰብ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቴን አገልፆለሁ፡፡
#መልካም_የፋሲካ_በዓል!!
አቶ ታደለ አሰፋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ ዲን