Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
2 370
المشتركون
+1124 ساعات
+997 أيام
+37430 أيام
أرشيف المشاركات
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ፥ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሠልጣኝ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በጋራ በመሆን አስመረቁ።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሃርቢ ቡህ እንደገለጹት የአንድ አገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት የሚወሰነው በትምህርት የሰለጠነ የሰው ሃይል የዳበረ እውቀትና ክህሎት ባላቸው ዜጓቿ በመሆኑ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ምክትል ከንቲባው አክለውም ድሬዳዋ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ያልተቆጠበ ተሣትፎ ቀዳሚውን ድርሻ የሚይዝ ብለዋል።
በዚህ የምርቃት ስነ -ስርአት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሃርቢ ቡህ፣ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የሁለቱም ኮሌጆች ዲኖችና ም/ዲኖች እንዲሁም መምህራን እና ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሠቦች ተገኝተዋል ።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ከኢትዮ ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ ተማሪ ኤርሚያስ ከፍያለው 3.95 በማምጣት አጠቃላይ የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ከድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ ጋርመንት ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆኑት ሲሳይ ዘውዱ እና በእምነት ጠብቀው 3.91 እኩል ነጥብ በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ሀምሌ 6/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+1
የሥራ ማስታወቂያ
****
Ethiopian Airlines
መረጃውን ሼር በማድረግ ለወጣቶቻችን ተደራሽ እናድርግ!!
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ምሩቃን በሙሉ
****
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚቢሽን(Job Fair)" የፊታችን አርብ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ የሚካሄድ ይሆናል።
በዚህም ስራ ፈላጊ ምሩቃን የተለያዩ ድርጅቶች በቅጥር ሥራ የምታገኙበትን ሁኔታ ሊያመቻቹ እናንተን ስለሚጠብቁ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በመያዝና በአካል በመገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የድሬዳዋ አስተዳደር
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች "ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አደረጉ።
በመድረኩም ከተረጂነት ለመላቀቅና በምግብ እራስን ለመቻል አገራዊ መግባባትን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተረጂነት ተጨባጭ ለውጥ ባለመመዝገቡ የዜጎችን አመለካከት በመቀየር፣ አቅምን በማቀናጀትና እንዲሁም የዘርፉን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት የሥራ ዕድል ፈጠራን ማጠናከር እንደሚገባም በሰነዱ ቀርቧል።
ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ያደጉበት ሲሆን አገራዊ እሳቤውና አቅጣጫውን እንደ አስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጠውም አስተያየታቸውን ሰተዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ከደቡብ ኮርያ የመጣ የቮለንተር ቡድን በኮሌጁ ሙያዊ ልምድ ልውውጥ አካሄደ::
ቡድኑ ከWitness of christ Church ጋር በመተባበር በሚያደርገው ድጋፍ አማካኝነት በኮሌጁ ተገኝቶ ልምድ ልውውጥ ያደረ ሲሆን በዚህም ከኮሌጁ ጋር በትብብር ለመስራት በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ከኮሌጁ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል::
በተጨማሪም የቮለንተር ቡድኑ በWitness of christ Church አጫጭር ስልጠና ተማሪዎች አማካኝነት በኮሌጁ የተሰሩ ስራዎችን የተመለከቱ ሲሆን የኮሌጁን የት/ትና ስልጠና ወርክ ሾፖችንም ተዘዋዉረው ተመልክተዋል::
ይህ ከደቡብ ኮርያ የመጣው ቡድን በውስጡ ከተለያዩ ቴክኒካል ሞያዎች የተወጣጡ ባለሙያዎችን ያቀፈ ሲሆን በቀጣይ ከሙያዊ ድጋፍ ጀምሮ ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ቆይታም አድርገዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሰኔ 20/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፑል አመራር አባላት ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ሜንስትሪምንግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከጤና ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት የአስተዳደሩን ወቅታዊ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ሁኔታ ግንዛቤ ለመስጠት የሚረዳ እንዲሁም በተቋሙ የኤድስ ፈንድ ለማስጀመር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለኮሌጁ ፑል አመራር አባላት አካሂዷል።
በመድረኩ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት መንስኤም ሆነ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ዘርፈ-ብዙ ከመሆኑ አንፃር ቫይረሱን ለመከላከልና ኤድስ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች የመቀነሱና የመከላከሉ ሥራ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ የኮሌጁ ማህበረሰብም የበኩሉን መውጣት እንደሚገባው በመድረኩ ተግልፇል::
በቀጣይም ስለ ኤድስ ፈንድ ለኮሌጁ ማህበረሰብ በቂ ግንዛቤን በመፍጠር የኤድስ ፈንድ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ከኤድስ ፈንድ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሥራዎች በቶሎ እንዲከናወኑ የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንዲሰጡም በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሰኔ 12/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስር እየተተገበረ የሚገኘው የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕሮጀክት በ 2016 ዓ.ም የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ ልምዶችን የሚያሳይ ሪፖርት ለባለ ድርሻ አካላት አቀረበ::
የፕሮጀቱ አመታዊ ሪፖርት በፕሮጀክቱ ማናጀር አማካኝነት ለመድረኩ የቀረበ ሲሆን በዚህም የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕሮጀክት በዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ፕሮጀክቱ ያስገኛቸው ጥሩ ልምዶችን ጨምሮ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም ጠቅለል ተደርገው ቀርበውበታል::
በተጨማሪም በመድረኩ የቀረበው አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በSolar Pv installation and maintenance እያሰለጠናቸው የሚገኙ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ሰልጥኞቹ የስራ ላይ ልምድ የሚያገኙበትን እድል በማመቻቸቱ ረግድ የተሰሩ ስራዎች በመድረኩ ቀርበዋል::
በዚህም ሰልጣኞች ስራ እየሰሩ ልምድ የሚያዳብሩበን መንገድ ከጤና ቢሮ፣ከትምህርት ቢሮ እና ከኢነርጂ ቢሮ ጋር በመነጋገር የገጠር ሶላር ስራ ላይ የጥገና ስራ እንዲሰሩ መንገድ የተመቻችላቸው ሲሆን ከፊልድ ስራ ሲመለሱ የብቃት ምዘና(COC) በመውሰድ ወደ ስራው ዓለም እንደሚሰማሩ ይጠበቃል::
በፕሮጀክቱ እቅድ መሰረት 40% በቅጥር 60% ደግሞ የራስ ስራ በመፍጠር ወደ ስራ ይሰማራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም ይሆን ዘንድ ከፐብሊክ ሰርቪስ በተላከ ባለሞያ አማክኝነት በተደረገው ገለፃ መሰረት እንደ አገርም አዲስ የሆነውን የሶላር ባለሙያ JOB BOX በማዘጋጀት የመጀመሪያ ድራፍት ዶክመንት በዛሬው እለት ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ የተተቸ ሲሆን በቀጣይም በተሰጠው ግብረ መልስ መሰረት ማስተካከያ ተደርጎበት እንደሚፀድቅ ተገልፇል::
በመጨረሻም በቀጣይ ለሚገቡት ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች የምልመላ መስፈርት ላይ በመድረኩ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግና መስፈርቱንም በማሻሻል መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ሰኔ 9/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
እንኳን አደረሳችሁ!!
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛ ዓመት ሂጂራ የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል::☪️
#ኢድ_ሙባረክ
