ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
2 268
المشتركون
+1324 ساعات
+947 أيام
+33730 أيام
أرشيف المشاركات
#ተመራቂዎች_እንኳን_ደስ_አላችሁ!! አቶ ታደለ አሰፋ የኮሌጁ ዲን ውድ የ2018 ዓ.ም የኮሌጃችን ተመራቂዎች በመጀመሪያ በምስራቅ ኢትዮጵያ ቀዳሚውና ብቸኛው የመንግስት ተቋም በመሆን በISO ሰርተፊኬ
+1
#ተመራቂዎች_እንኳን_ደስ_አላችሁ!! አቶ ታደለ አሰፋ የኮሌጁ ዲን ውድ የ2018 ዓ.ም የኮሌጃችን ተመራቂዎች በመጀመሪያ በምስራቅ ኢትዮጵያ ቀዳሚውና ብቸኛው የመንግስት ተቋም በመሆን በISO ሰርተፊኬት ጥራቱ በተረጋገጠና ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው ኮሌጃችን ሰልጥናችሁ ለዚህ ታላቅ የምረቃ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በተለያዩ የሙያ መስኮች በቀን እና በማታ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ከ858 በላይ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንዲሁም በዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 18 ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 876 ሰልጣኝ ተማሪዎችን የአስተዳደሩ የስራና ክህሎት ቢሮ በነገው እለት በ07/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 በኮንጎ ሜዳ ወጣቶች አካዳሚ አዳራሽ በሚያዘጋጀው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በደማቅ ሁኔታ የሚያስመርቅ መሆኑን እየገለፅን ኮሌጁ ለተመራቂዎችና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ልዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ምዝገባ መቼ ነው?...ማንኛውም የ12ኛ ክፍል አጠናቃቂ ከጥቅምት 6-20 ድረስ በአስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መመዝገብ የሚችል ይሆናል፡፡

#ዜና /በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም የተመራ ልኡካን ቡድን የኢትዮ-ጣሊያን ኮሌጅን የሥልጠና ክፍሎች ጎበኘ በአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም የተመራ ልኡክ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት የተግባር ክህሎት ሥልጠና የሚሰጥባቸውን የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። ኮሌጁ በሥሩ በሚገኙ ዘጠኝ የትምህርት ክፍሎች አማካኝነት በድሬዳዋ አስተዳደር ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃት ላይ ለሚገኘው ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በክህሎት የዳበረና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት የበኩሉን ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት ኮሌጁ ለአስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖ የተመለከቱ ሲሆን፣ ተቋሙ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ያለውን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል። አስተዳደሩ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን የጠቆሙት ከንቲባው በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ወጣቶች የንድፈ-ሀሳብ ዕውቀታቸውን ከተግባር ልምምድ ጋር በማዋሃድ በቀጥታ ወደ ሥራው ዓለም እንዲገቡና የራሳቸውን የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥትም ለተቋሙ ማጠናከሪያና ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

photo content
+9

በድሬዳዋ እስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በኮሌጁ ጉብኝት አካሄዱ:: #EIPC ጥቅምት 04. 2019 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ ከተቋሙ ማኔጅመንትና የፑል አመራር አባላት ጋር የስራ ትውውቅ ያካሄዱ ሲሆን የኮሌጁ አመራሮችም ለአዲሱ የቢሮ ሀላፊ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል:: በመድረኩ በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት የኮሌጁ ነባራዊ ሁኔታን ጨምሮ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በተመለከት ለቢሮ ሀላፊው ሰፊ ገለፆ የተደረገ ሲሆን በኮሌጁ የተመዘገቡ ውጤቶችን እንዲሁም የተቋሙ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ተመላክተዋል:: በተጨማሪም ዶ/ር ፍቃዱ በኮሌጁ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ወርክሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በመጨረሻም ለኮሌጁ አመራሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ቆይታቸውን አጠናቀዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከበረ:: #EIPC ጥቅምት 02. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ሰልጣኝ ተማሪዎች
+9
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከበረ:: #EIPC ጥቅምት 02. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ሰልጣኝ ተማሪዎች ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነትታችን" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ እክብረዋል:: በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው እንደገለፁት ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር የሉዓላዊነትና የነፃነት ምልክትና መሆኑን ገልፀው ይህን ቀን ስናከብር እውነተኛ የሀገር ፍቅር መገለጫ በሆነው በተሰማራንበት በየትኛውም ዘርፍ በጀግንነት ለማገልገል ለራሳችን ቃል በመግባት ሊሆንም ይገባል ብለዋል:: "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነትታችን" ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

photo content

ያለን ውስን ቦታ በመሆኑ ፈጥነው ይመገቡ!!
ያለን ውስን ቦታ በመሆኑ ፈጥነው ይመገቡ!!

photo content

የ2018/19 የድሬደዋ ተቋማት እግር ኳስ ውድድር የምድብ ሐ ጨዋታ ኢትዮ-ጣሊያን ከ ወጋገን ባንክ 🔆የምድብ አራተኛ ጨዋታ 🗓️ እሁድ መስከረም 24/2019 ዓ.ም ⏰ ጠዋት 3:30 ሰዓት 🏟 ምድ
የ2018/19 የድሬደዋ ተቋማት እግር ኳስ ውድድር የምድብ ሐ ጨዋታ ኢትዮ-ጣሊያን ከ ወጋገን ባንክ 🔆የምድብ አራተኛ ጨዋታ 🗓️ እሁድ መስከረም 24/2019 ዓ.ም ⏰  ጠዋት 3:30 ሰዓት 🏟 ምድር ባቡር ሜዳ

መልካም ዜና ለድሬዳዋ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች!!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በርካታ የከተማችንን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ለ
መልካም ዜና ለድሬዳዋ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች!!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በርካታ የከተማችንን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ አስቧል። በዚህም መስፈርቱን የሚያሟሉ 1ኛ. ዕድሜ፡- ከ18 እስከ 29 2ኛ. የትምህርት ደረጃ ፡-12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በታች 3ኛ. ፋይዳ ፣ የቀበሌ መታወቂያ እና የንግድ ባንክ አካውንት ማቅረብ የሚችሉ 4ኛ. ምንም አይነት ስራ የሌላቸው 5ኛ. በፕሮጀክቱ አሰራር ለመመራት ፍቃደኛ የሆኑ ከመስከረም 20-28/2019 ዓ.ም በወረዳ/ቀበሌ ሥራ ማዕከላት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

#ዜና_ሹመት!!! ዶ/ር ፍቃዱ በየነ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን!!!
#ዜና_ሹመት!!! ዶ/ር ፍቃዱ በየነ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን!!!

የአቶ ሮቤል ጌታቸው የምስጋና መልዕክት ውድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበረሰብ፣ በቢሮው ኃላፊነት ቆይታዬ አብራችሁኝ ለሠራችሁ፣ ለደገፋችሁኝና ለተቋሙ ውጤት ያደረጋችሁትን ያላሰለሰ ጥ
የአቶ ሮቤል ጌታቸው የምስጋና መልዕክት ውድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበረሰብ፣ በቢሮው ኃላፊነት ቆይታዬ አብራችሁኝ ለሠራችሁ፣ ለደገፋችሁኝና ለተቋሙ ውጤት ያደረጋችሁትን ያላሰለሰ ጥረት በልቤ እያደረግሁ ከፍተኛ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የተመዘገቡት ውጤቶች የአንድ ሰው ሳይሆኑ፣ የጋራ ትጋታችን፣ ትብብራችንና የሥራ ባህላችን ውጤት ናቸው። በተለይም በተቋሙ ውስጥ የሚታየው የለውጥ መንፈስ በሁላችሁም ተሳትፎ የተገነባ ነው። የቢሮ ኃላፊነቴን ለማስረከብና ቀጣይ ፓርቲዬ በሚሰጠኝ የስራ መደብ ለመስራት በተዘጋጀሁበት በዚህ ወቅት፣ ለሁላችሁም ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በቀጣይም የጀመራችሁትን ሥራ በተሻለ ትጋትና በተቋማዊ ትብብር እንድታስቀጥሉ አደራ እላለሁ። ከልብ አመሰግናለሁ።

በክህሎት የተገነባ የተሻለ ነገን ምርጫዎ ያድርጉ!
በክህሎት የተገነባ የተሻለ ነገን ምርጫዎ ያድርጉ!

photo content

photo content
+5

photo content
+9