ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
إظهار المزيد603
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-1630 أيام
أرشيف المشاركات
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፳፱ 29 ቀን
✝ እንኳን #ጌታችን_አምላካች_መድኀኒታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል ተገልጦ በደሃ ሰው ተመስሎ ከማኅበረ ዴጔ ጋር በመካከላቸውም ተገኝቶ የጽዋ ማኅበር እየጠጣ ተራው ደርሶ ተዓምር አድርጎ አምላክነቱ ለገለጠበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ የስሟ ትርጓሜ መጻተኛ ለሆነ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ በራእይ ለተገለጠላትና ከከበሩ ነገሥታት ወገን ለሆነችው ዓለምን ንቃ በመመንኰስ በምትተኛ ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ እየተኛችና ጥሬ ባቄላን ብቻ እየተመገበች በታላቅ ተጋድሎ ለኖረችው ለከበረች #ቅድስት_አክሳኒ ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ ተጋዳይ ለሆነ በበረሃ ውስጥ የሞተ ሰው ራስ ቅል አግኝተው የራስ ቅሉን ላነጋገሩና ሥራውን መርምረው ለተረዱ በኋላም አማልደውት ምሕረትን ላሰጡት #አባ_እስጢፍኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከድንግል እመቤታችን ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከተወለደበት #ከልደቱ_በዓለ_ወልድ_ወራዊ መታሰቢያ፣ ከመስተጋድል ከከበረ #ሰማዕት_ከሰርያኮስ ከመታሰቢያው፣
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል !
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።
ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ " ብለዋል።
ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ብፅዕነታቸው " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል።
ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል።
ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል።
ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጀል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።
ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፳፰ (28) ቀን።
✝ እንኳን #ለአምላካች_ለቅዱስ_አማኑኤል ተአምራት አድርጎ አምስት እንጀራንና ሁለት ዓሣን አበርክቶ ሕፃናትና ሴቶች ሳይቆጠሩ አምስት ሺህ (አምስት የገብያ ሕዝብ ለመገበበት (ላጠገበበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ኪራኮስ ከሚባል አገር ስሟ አክሮስያ የምትባል ለመበለት ልጅ ሰባት ጊዜ ታላላቅ አሠቃቂ መከራዎችን በመቀበል ሰማዕትነቱን ለፈጸመው ለከበረ #ለቅዱስ_ቀሌምንጦስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ፍዩም ከሚባል ሀገር ለሆነ ሰይጣን ይዞ በራሱ ጠጉር አሥሮ ለቀጣው ለከበረ መነኰስ #ለአባ_አካውህ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና፣ ለከበረ ለአይሁዳዊ ለማኅው ልጅ እመቤታችን ከእሳት ውስጥ አውጥታ ላዳነችው በዕረፍቱም ጊዜ "በሦስተኛው ቀን በሦስት ሰዓት ወደኔ ትመጣለህና ደስ ይበልህ" ላለችው #ለቅዱስ_ዮሴፍ ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_አባ_አካውህ_ማኅበር ከስምንት መቶ ሰማዕታት፣ ከአባቶቻችን #ከቅዱሳን_አብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ፣ #ከሠልስቱ_ደቂቅና_ከታቤላ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፳፯ (27) ቀን።
✝ እንኳን #ሳፍራ_ለሚባል_ለመልአክ_ለቅዱስ_ሱርያል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ በሞት ፋንታ ለተሰውረው #ለነቢዩ_ቅዱስ_ኄኖክ ለዕርገቱ መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ሐዋርያ #ለቅዱስ_ጢሞቴዎስ ከኤፌሶን አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ለሥጋው ፍልሰት በዓል፣ ከግብጽ ደቡብ ከታችኛዪቱ ምስር አውራጃ በብኑዲ ከምትባል መንደር ለሆነ ለከበረ #ቅዱስ_ሰራብዮን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ከታናሽነቱ ድንግል ለሆነ እግዚአብሔርን ለሚወድ ለድኆችና ለችግረኞች ለሚመጸውት ይህንንም ዓለም ንቆ ለተወ በእሳት ተቃጥሎ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለከበረ #ቅዱስ_ቢፋሞን ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቸሩ_መድኃኔዓለም_ከስቅለቱ ከወራዊ መታሰቢያ፣ #ከሰማዕታት_ትውፍሎን_ከዮስና_ከሰርኒስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ በዚች ቀን #ሳፍራ_የሚባል_የመልአክ_ሱርያል በዓል ነው እርሱም #ከነቢይ_እዝራ ጋር የኖረ የተሠወረ ምሥጢርንም የገለጠለት ነው እርሱም ስለ ሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር የሚለምን ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሱርያል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️
በጉጉት የምንጠብቀው ታላቁ የምስጋና መርሀግብራችን የፊታችን እሑድ እናከብራለን ሁላችሁም የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ : አለን!!!
በእለቱ ሁላችንም ጥምቀትን በክብር አሳልፎ ለዚህች ቀን ያደረሰንን አምላካችን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዝግጁ ሆነን እንገኝ።
ፈጣሪያችን ለዚህች ቀን ያድርሰን አሜን!!!
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በዛሬው ዕለት በደብራችን በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ከሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር📸 በጥቂቱ ይህን ይመስላል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፳፭ (25) ቀን።
✝ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ለሮም ንጉሥ ልጅ ለከበረ #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ስብስትያኖስ ምስክርነቱ ለፈጸመበት ለዕረፍቱ በዓልና አስቀድሞ ቀራጭ ለነበነ ራሱን ለሸጠው በገድል ለተጸመደ ለኖረ ለከበረ #ቅዱስ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት #ቅዱስ_አስኪላ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ስብስትያኖስ፦ ይህም የቅዱስ የሮሜ ንጉሥ ልጅ ነው። እርሱንም ወላጆቹ በተግሣጽና እግዚአብሔርን በመፍራት የአሳደጉት ነው። አባቱም ከሞቱ በኋላ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ ይህንንም ቅዱስ አገረ ገዥነት ሾሙት እንደ አባቱም እጅግ አከበሩት። እርሱሜ በጥበብና በማስተዋል ይጓዝ ነበር በሽተኞችን ሁሉ የዕውራንንም ዐይኖች በጸሎቱ ከፈተ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
#C_25
ጥር ሃያ አምስት በዚህች ዕለት ሰማዕቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን የረዳበት ዕለት ነው፡፡ በገድል የተጸመደ የከበረ #ቅዱስ_ጴጥሮስ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ስብስትያኖስ ምስክር ሁኖ ሞተ።
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ
ጥር ሃያ አምስት በዚህች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን የገደለው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት። አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
የመርካቶ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ - የአባታችን የጻድቁ ተክለሃይማኖት ስባረ ዐጽም ክብረ በዓል እና የቤተ መቅደሱ እድሳት ምርቃት !!!
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ ጥር ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (ለስብተ አፅማቸው) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ለሚታወቁት ለአቡነ እጨጌ መርሐ ተክርስቶስ (ዘሸዋ) ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስብረተ አፅም፦ "...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
🕐🕑🕒🕓🕔🕕🕖🕗🕘🕙🕚🕛🕜
ሰላም ዉድ የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች
፦፦፦እንደሚታወቀው ሁል ጊዜ በየአመቱ አምላካችንን ያሳለፍነውን አመት በሰላም እንድናልፍ ስለረዳን የምስጋና መርሀግብር እናዘጋጃለን።
በመርሀግብሩ ላይም ስዕለት እንሳላለን :
ባሳለፍነው አመት ከተሳልናቸው ስዕለቶች ላይ እንድናስታውስ ይህንን መዝገብ አዘጋጅተንላችኋል እየከፈታችሁ ተመልከቱት።
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፫ (23) ቀን።
✝ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ (በመንፈስ ልጁ) ለሆነው ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ለዕረፍት በዓልና ለጻድቁ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ሰማዕታት ከቅዱሳን ጌርሎስና አትናቴዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ "ሰላም ለቴዎዶስዮስ ንጉሥ ዘፈጸመ መንግሥቶ በሕገ ቈስጠንጢኖስ ዘኮኖሙ ለክርስቲያን ዐምደ ዘኢይጸንን፤ በመዋዕሊሁ ዘተከሥተ መድፍን"። ትርጉም፦ በርሱ ዘመን የተሰወረው ወርቅ የተገለጠ፤ ለክርስቲያን የማያዘነብል (የማያጋድል) ምሰሶ የኾናቸው መንግሥቱንም በቈስጠንጢኖስ ሕግ የፈጸመ ለኾነ ለንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፪ (22) ቀን።
✝ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ዑራኤል ለሢመቱ (ለተሾመበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል፡- ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡
✝ በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ "አጋእዝት" ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ "ኪሩቤል" ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ወርሃዊ አስተዋፅኦ ያልከፈላችሁ እና ልብሰ ስብሐት ያልመለሳችሁ አጥባችሁ እስከ ቅጣቱ ይዛችሁ እንድትመጡ ንብረት ክፍሉ ያሳስባል።
🌹 አስተርእዮ ማርያም 🌹
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"
#ሞት ለሚሞት ይገባል
የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል "
በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡
እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምንልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን አሜን !!!
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፩ 21 ቀን።
✝ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለዕረፍቷ በዓል (ለአስተርእዮ ማርያም)፣ ለኑሲስ ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ለከበረ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍት በዓልና ለሮሜ አገር ንጉሥ ለዘይኑን ልጅ ለከበረች ለቅድስት ኢላርያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እመቤታችንንም ከመጥቁ ዮሐንስ ጋር በደብረ ማሕው ከተገለጠችበት፣ ከነቢዩ ከቅዱስ ኤርምያስ፣ ከዮሐንስና ከአባ እስክንድር፣ በዋሻ ከቅዱስ ኒቆላዎስና ከኤጲስቆጶስ ከአባ ፊቅጦር ከሁሉም ከመታሰቢያቸው፣ በናፍቁ ንጉሥ በመርቅያን ዘመን በሰማዕትነት ከዐረፉ ከቅዱሳን ጳውሎስና ከቀሲስ ሲላስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ የዕለቱ አንገርጋ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተዓቊረ እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ ዘድንግል መናሥግተ እያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዮ"።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
