ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多603
订阅者
-324 小时
-87 天
-1730 天
帖子存档
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በዛሬው ዕለት በደብራችን በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል ከሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር📸 በጥቂቱ ይህን ይመስላል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፳፭ (25) ቀን።
✝ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ለሮም ንጉሥ ልጅ ለከበረ #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ስብስትያኖስ ምስክርነቱ ለፈጸመበት ለዕረፍቱ በዓልና አስቀድሞ ቀራጭ ለነበነ ራሱን ለሸጠው በገድል ለተጸመደ ለኖረ ለከበረ #ቅዱስ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት #ቅዱስ_አስኪላ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ስብስትያኖስ፦ ይህም የቅዱስ የሮሜ ንጉሥ ልጅ ነው። እርሱንም ወላጆቹ በተግሣጽና እግዚአብሔርን በመፍራት የአሳደጉት ነው። አባቱም ከሞቱ በኋላ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ ይህንንም ቅዱስ አገረ ገዥነት ሾሙት እንደ አባቱም እጅግ አከበሩት። እርሱሜ በጥበብና በማስተዋል ይጓዝ ነበር በሽተኞችን ሁሉ የዕውራንንም ዐይኖች በጸሎቱ ከፈተ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
#C_25
ጥር ሃያ አምስት በዚህች ዕለት ሰማዕቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን የረዳበት ዕለት ነው፡፡ በገድል የተጸመደ የከበረ #ቅዱስ_ጴጥሮስ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ስብስትያኖስ ምስክር ሁኖ ሞተ።
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ
ጥር ሃያ አምስት በዚህች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን የገደለው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት። አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
የመርካቶ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ - የአባታችን የጻድቁ ተክለሃይማኖት ስባረ ዐጽም ክብረ በዓል እና የቤተ መቅደሱ እድሳት ምርቃት !!!
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ ጥር ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (ለስብተ አፅማቸው) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ለሚታወቁት ለአቡነ እጨጌ መርሐ ተክርስቶስ (ዘሸዋ) ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስብረተ አፅም፦ "...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
🕐🕑🕒🕓🕔🕕🕖🕗🕘🕙🕚🕛🕜
ሰላም ዉድ የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች
፦፦፦እንደሚታወቀው ሁል ጊዜ በየአመቱ አምላካችንን ያሳለፍነውን አመት በሰላም እንድናልፍ ስለረዳን የምስጋና መርሀግብር እናዘጋጃለን።
በመርሀግብሩ ላይም ስዕለት እንሳላለን :
ባሳለፍነው አመት ከተሳልናቸው ስዕለቶች ላይ እንድናስታውስ ይህንን መዝገብ አዘጋጅተንላችኋል እየከፈታችሁ ተመልከቱት።
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፫ (23) ቀን።
✝ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ (በመንፈስ ልጁ) ለሆነው ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ለዕረፍት በዓልና ለጻድቁ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ሰማዕታት ከቅዱሳን ጌርሎስና አትናቴዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ "ሰላም ለቴዎዶስዮስ ንጉሥ ዘፈጸመ መንግሥቶ በሕገ ቈስጠንጢኖስ ዘኮኖሙ ለክርስቲያን ዐምደ ዘኢይጸንን፤ በመዋዕሊሁ ዘተከሥተ መድፍን"። ትርጉም፦ በርሱ ዘመን የተሰወረው ወርቅ የተገለጠ፤ ለክርስቲያን የማያዘነብል (የማያጋድል) ምሰሶ የኾናቸው መንግሥቱንም በቈስጠንጢኖስ ሕግ የፈጸመ ለኾነ ለንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፪ (22) ቀን።
✝ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ዑራኤል ለሢመቱ (ለተሾመበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል፡- ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡
✝ በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ "አጋእዝት" ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ "ኪሩቤል" ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ወርሃዊ አስተዋፅኦ ያልከፈላችሁ እና ልብሰ ስብሐት ያልመለሳችሁ አጥባችሁ እስከ ቅጣቱ ይዛችሁ እንድትመጡ ንብረት ክፍሉ ያሳስባል።
🌹 አስተርእዮ ማርያም 🌹
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"
#ሞት ለሚሞት ይገባል
የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል "
በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡
እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምንልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን አሜን !!!
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳፩ 21 ቀን።
✝ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለዕረፍቷ በዓል (ለአስተርእዮ ማርያም)፣ ለኑሲስ ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ለከበረ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍት በዓልና ለሮሜ አገር ንጉሥ ለዘይኑን ልጅ ለከበረች ለቅድስት ኢላርያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እመቤታችንንም ከመጥቁ ዮሐንስ ጋር በደብረ ማሕው ከተገለጠችበት፣ ከነቢዩ ከቅዱስ ኤርምያስ፣ ከዮሐንስና ከአባ እስክንድር፣ በዋሻ ከቅዱስ ኒቆላዎስና ከኤጲስቆጶስ ከአባ ፊቅጦር ከሁሉም ከመታሰቢያቸው፣ በናፍቁ ንጉሥ በመርቅያን ዘመን በሰማዕትነት ከዐረፉ ከቅዱሳን ጳውሎስና ከቀሲስ ሲላስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ የዕለቱ አንገርጋ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተዓቊረ እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ ዘድንግል መናሥግተ እያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዮ"።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ ጥር ፳ (20) ቀን።
✝ እንኳን ጌታችን ወንጌልን ይሰብኩ ዘንድ በሽተኞችንም ይፈውሱ ዘንድ መርጦ ወደ ዓለም ከላካቸው ቁጥሩ ከሰብዓ ሁለቱ አርድእትና ከሰባቱ ዲያቆናት ለሆነ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊው ደቀ መዝሙር ለሐዋርያው ለቅዱስ አብሮኮሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ልጁን በስምህ የሚሰይመውን ሁሉ እኔ እባርከዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ለገባለት በግብጽ አገር እልፈንት ከሚባል ከተማ ለከበረ ቀሲስ ለቅዱስ አክሎግ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለታላቁ ሰማዕት ለመምህናም ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበትና ተአምራቱ ለተገለጠበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሕኑ ከመታሰቢያው፣ ከወንጌሉ ዘወርቅ ከቅዱስ ዮሐንስም ቤተ ክርስቲያኑ ከከበረችበትና ሥጋው ወደ ሮሜ ከፈለሰችበት፣ ከአባ ኖኅ፣ ከአባ ስልዎኖስና ከአባ አብድዩ ከመታሰቢያቸው ረድኤት በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፱ (19) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ ካመነኰሷቸው ከሳባቱ ከዋክብት አንዱ ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አፍቅረነ_እግዚእ_ዘጉጉቤን ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #አቡነ_አፍቅረነ_እግዚእ_ዘጉጉቤን፦ እኚህ ጻድቅ እጅግ ከከበሩት ከሳባቱ ከዋክብት የአገራችንን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ትውልዳቸው ትግራይ አክሱም ሲሆን አባታቸው ገብረ ኢየሱስ እናታቸው አፎምያ የተባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ልደታቸው ሐምሌ19 ሲሆን ዕረፍታቸዉ ጥር19 ቀን ነዉ። በገዳማዊ ሕይወታቸዉ በእጅጉ ይታወቃሉ። በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመን የነበሩ ሲሆን ደራሲና ፈላስፋም ናቸው። ጻድቁ ደራ ፎገራ ውስጥ ባለ አራት ዓምድ አስደናቂ ገድል አላቸው። ደራ ፎገራ ተነስተው በጣና አድርገው ፈላሾችንና ቅማንቶችን በሚገባ በማስተማርና በማጥመቅ ብዙ ሐዋርያው አገልግሎት ፈጽመዋል፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፰ (18) ቀን።
✝ እንኳን #ለፀሓየ_ልዳ_ለኮከበ_ፋርስ ለሰማዕታት አለቃ #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ (ለዝርወተ ዐፅሙ) ዐፅሙ ተቃጠጥሎ ተደቁሶ በይድራስ ተራራ በነፋስ ከተበተነ በኋላ ከሞት ለተነሳበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና በገድል ለተጸመደ ለከበረ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ_መምህሩ ቁጥሩ ከሠለስቱ ምዕት ለሆነ ለአገረ ንጺቢን ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ያዕቆብ_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአራት ቀኖች በኋላ ጌታች ከመቃብር ያነሳ #ከአልዓዛር_እኅቶች_ከቅድስት_ማርያምና #ከቅድስት_ማርታ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዝርወተ_አፅሙ፦ በዚች ቀን ሰባ ነገሥታት ማሰቃየት በሰለቻቸው ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አውጥተው ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት ንጉሥ ዱድያኖስ አዘዘ፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፯ (17) ቀን።
✝ እንኳን #ለለውንድዮስ_ለሮም__ንጉሥ_ልጅ ለሆኑ ለከበሩና ለተመሰገኑ ወድማማቾች #ለቅዱስ_ዱማቴዎስ ለዕረፍት በዓልና #ለቅዱስ_መክሲሞስ ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ከእነዚህ ሁለት ወድማማቾች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_መክሲሞስና_አባ_ዱማቴዎስ፦ እነዚህም ቅዱሳን ለሮም ንጉሥ ለለውንድዮስ ልጆቹ ናቸው። ይህም ንጉሥ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔር የሚፈራ በእውነትም የቀና ፍርድን የሚፈርድ ነበር ስለዚህም እሊህን ሁለት ቅዱሳን እግዚአብሔር ሰጠው እነርሱም ከታናሽነታቸው ጀምሮ በንጽሕና እንደ እግዚአብሔር መላእክት ሆኑ።
✝ ትሕትናን ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጋቸው የሚጾሙና የሚጸልዩ በቀንና በሌሊትም የብሉይና የሐዲስ መጽሐፍቶችን የሚያነቡ ሆኑ። ከዚህም በኋላ ይህ ዓለም ይተውት ዘንድ የመላእክት ልብስ ይለብሱ ዘንድ እርሷም የከበረች የምንኵስና ልብስ ናት ከዚያም ሀሳብ መጣባቸው ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ አስራ ስምንት አባቶች ወደ ተሰበሰቡባት ወደ ኒቂያ ሔደው ይጸልዩ ዘንድ እንዲያሰናብታቸው ለአባታቸው ምክንያት አቀረቡ። ይህንም ከእርሷቸው በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው። ከብዙ አገልጋዮችና ከብዙ ሠራዊት ጋር አሰናበታቸው ከኒቅያ አገርም በደረሱ ጊዜ ከከበረ ቦታ በረከትን ተቀበሉ ሠራዊቱንም ወደ ንጉሥ አባታቸው ጌታችን ንጉሥ ሆይ "እኛ ከዚህ ጥቂት ቀን መቆየት እንሻለን" የሚል ጽሑፍ ጋር ጽፈው ላኩ።
✝ ከዚህም በኋላ ለአንድ ጻድቅ መነኰስ ኀባቸውን ገለጡ እንዲህም አሉት "ከአንተ ዘንድ የምንኵስናን ልብስ እንድንለብስ እንሻለን" እርሱም "እኔ ከንጉሥ አባታችን የተነሣ እፈራለሁ ነገር ግን ወደ ሶርያ ሒዱ ስሙ አጋብዮስ የሚባል ከዚያ ሃይማኖቱ የቀና ካህን ደግ መነኰስ አለ" አላቸው ይህንንም ሲላቸው ምክሩን ተቀብለው ወደ ሶርያ ተጒዘው ወደ ቅዱስ አባ አጋብዮስ ደርሰው ኀሳባቸውን ገለጡለት እርሱም ተቀብሎ የምንኵስና ልብስን አለበሳቸው እስከሚአርፍበት ቀን ከእርሱ ዘንድ ኖሩ። ከዕረፍቱም አስቀድሞ ያየውን ራእይ ነገራቸው ታላቁ አባ መቃርስ ወደርሱ እንደመጣና "ልጆችህ መክሲሞስና ዱማቴዎስ ለኔ ልጆቼ ይሁኑኝ ዘንድ ወደ እኔ ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመጡ ከመሞቴ በፊት እዘዛቸው" አለው። ዳግመኛም እንዲህ አላቸው ልጆቹ "እኔ ይህን ሰው አባ መቃርስን በሥጋው አየው ዘንድ እመኝ ነበር እነሆ በመንፈስ አየሁት እናንተም ከሞትኩ በኋላ ወደርሱ ሒዱ"።
✝ ከዐረፈም በኋላ አልሔዱም በዚያ በሶርያ አገር ኖሩ እንጂ እግዚአብሔር ሀብተ ፈውስ ሰጥቷቸው በሽተኞችን የሚፈውሱ ሆነ ወሬያቸውም በአገሮች ሁሉ ተሰማ በባሕርና በየብስ ከሚነግዱ ነጋድያንም የመርከብ መዛነቢያዎችን መሥራት ተምረው ከድካም ወጋቸው በጥቂቱ የሚመገቡና የተረፈውን ለድኆችና ለችግረኞች የሚሰጡ ሆኑ። እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ከሚሠራቸው ድንቆች ተአምራቶች የተነሣ የቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስን ስም መናፍስት ርኵሳን በማሰሚ ጊዜ ከሰዎች ወጥተው ይሸሻሉ ሰዎችም ያን ጊዜ በጌታ ኃይል ይድናሉ ጤነኞችም ይሆናሉ። እጅግ ታላቅ የሆነ በጐዳና አጠገብ የሚኖር ከይሲ ነበር ብዙዎች ሰዎችንም አጥፍቷል የአገር ሰዎችም ወደ ከበሩ መክሲሞስና ዱማቴዎስ መጥተው ከዚያ ከይሲ ያድኗቸው ዘንድ ለመኗቸው አባ መክሲሞስም ክርታስ አንሥቶ እንዲህ ብሎ ጻፈ "የብፁዕ መቃርዮስ አምላክ በሆነ መንፈስ ቅዱስንም በለበሰ በአባታችን በአጋብዮስ አምላክ ሕያው እግዚአብሔር አካላዊ ቃል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደብዳቤ ከዋሻህ ደጅ ሲደርስ አንተ ወጥተህ ሙት የሰማይ ወፎችም ይብሉህ"።
✝ አንድ ሰውም ያቺን ደብዳቤ ተቀብሎ ሔደ በዚያም የዘንዶ ዋሻ ደጃፍ አኖራት በዚያንም ጊዜ ዘንዶው ወጥቶ ሞተ የሰማይ ወፎችም በሉት ሕዝቦችም ሁሉ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርም።እግዚአብሔርም በእነዚህ ሁለት ቅዱሳን እጆች ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፡፡ በአንዲትም ዕለት ከአባታቸው መኳንንቶች አንዱ ወደ ባሕር ዳርቻ ደረሰ፡፡ ከመርከቦችም በአንደኛው መርከብ ላይ መክሲሞስና ዱማቴዎስ የሚል ጽሑፍ ባየ ጊዜ የመርከቡን ሹም የጠቀው፡፡ የመርከቡ ሹምም "ማዕበል በተነሣ ጊዜ በጸሎታቸው ከመስጠም እግዚአብሔር እንዲያድነኝ የእነዚህን ሁለት ወንድማማቾች ቅዱሳን ስማቸውን በመርከቤ ላይ ጻፍኩ" አለው፡፡ መኰንኑም "መልካቸው ምን ይመስላል?" አለው፡፡ እርሱም የመልካቸውን ነገር ነገረው፡፡ መኮንኑም የንጉሡ ልጆች መሆናቸውን ዐውቆ ያንን ነጋዴ ወደ ንጉሡ ዘንድ ወሰደው፡፡ ንጉሡም የሁለቱን ቅዱሳን ነገር ነጋዴውን የጠቀው፡፡ እርሱም ስለ ቅዱሳኑ የሚያውቀውን ሁሉ የመልካቸውንም ነገር ነገረው፡፡ ንጉሡም ልጆቹ እንደሆኑ ተረዳ፡፡
✝ ከዚህም በኋላ እናታቸውንና እኅታቸውን ወደ ልጆቹ ዘንድ ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከ፡፡ ደርሰው ባዩአቸውም ጊዜ ጮኸው አለቀሱ፡፡ እናታቸውም ቅዱሳኑን ወደ አባታቸው ዘንድ እንዲሄዱ ለመነቻቸው፡፡ ቅዱሳኑም "ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ሰጥተናልና ይህን ማድረግ አይቻለንም" አሏት፡፡ "ነገር ግን ወደ ቤተ መንግሥትሽ ተመለሺና ሂጂ፣ አንቺንም አባታችንንም እግዚአብሔር ከመከራ ሁሉ እንዲጠብቃችሁ እንጸልያለን" ብለው አረጋጓትና ሸኟት፡፡ እርሷም ወደ ንጉሡ ባሏ በደረሰች ጊዜ የሆነውን ነገረችው፡፡ እርሱም ለሚስቱና ለባለሟሎቹ ሁሉ "በዓለም ውስጥ ያለ ክብር ሁሉ እንደ ሕልም ኃላፊ ጠፊ ነውና ልጆቼ ግን የማያልፈውን መንግሥት መርጠዋልና ለእግዚአብሔር ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮቹ ይሆኑ ዘንድ እንተዋቸው፣ በጸሎታቸውም እኛን ይጠብቁናል" አላቸው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፭ (15) ቀን።
✝ እንኳን #ለከበረ_ሕፃን በሦስት ዓመቱ ተጋድሎውን ለፈጸመ #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ለዕረፍቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ማኅበር_ለዐሥራ_አንድ_ሽህ_አራት_ሰዎች_ሰማዕትነት ለተበቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለሐናንያ ልጅ ለዕውተኛ ነቢይ #ለቅዱስ_አብድዩ ለዕረፍት በዓል። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሶርያ አገር ያሉ የክርስቲያን ወገኖች #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ የዕረፍቱን መታሰቢያ በዓል ከመያከብሩት፣ #ከጴጥሮስ_ከሶፍያ_ከአድምራና_ከይስሐቅ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝# ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ፦ በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ። ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮሜ ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በአገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች። ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው። ይቺንም ቅድስት ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት።
✝ መኰንኑም "ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው አገርሽስ ወዴት ነው" አላት። የከበረች ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት "የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ" አለችው። መኰንኑም "በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን" አላት "አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ" የከበረች ኢየሉጣም አለችው "ለረከሱ አማልክት እኔ አልሠዋም" አለችው መኰንኑም "ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት እርሷም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው" አለችው። መኰንኑም "ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው" ብላ መለሰችለት። መኰንኑም "ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳያመጡ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "ዕውነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ አገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይነገረን" አለችው።
✝ ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የአገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን "የስንት ዓመት ልጅ ነው" ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም "ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው" አሏቸው። ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየ ጊዜ "ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል" አለው። ሕፃኑም "እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን "ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን" አለው። ሕፃኑም "ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ" አለው።
✝ መኰንኑም "ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ "ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም "ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ" አለው የከበረ ሕፃንም "ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው" በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን "እሺ በለኝና እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ" አለው። ሕፃኑም "የሰይጣ መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ" አለው። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲግፉት አዘዘ። የከበረች ኢየሉጣሜ የልጅዋን ትዕግሥት በአየች ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነችው።
✝ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ። የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ ሕፃኑ "ትእዛዝህ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ" ብሎ ጮኸ። ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት ጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፋ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም "ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው" አለ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
