cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

The Home of all የሁሉም ቤት

Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day * Motivate for free * learn for free * earn more for free Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0 ══════❁✿❁═════════

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
16 013
المشتركون
+4624 ساعات
-517 أيام
+7730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailable
እየተጠነቀቅን ወገን😂 ለተጨማሪ ሜሞች 👇 @funny_coment ይቀላቀሉ
إظهار الكل...
🤣 9👍 2 1
የትኛው ቻነል መቀላቀል ይፈልጋሉ
إظهار الكل...
😂አስቂኝ ቻነል😂
የ crypto ቻነል
ስለ online ስራ የሚያስተምር
ሁሉም በአንድላይ
ከቴሌግራም ምርጥ ምርጥ የሆኑ ቻነሎች ንገረን ባላችሁኝ መሰረት ዛሬ ምርጥ ምርጦቹን እንሆ ጋበዝኳችሁ ተሎ ሳላጠፋው ተቀላቀሉ
إظهار الكل...
ምርጦች ብቻ
5 ምርጥ
top 3 ምርጥ
++ሁሉም በአንድላይ++
​​❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥                                      ክፍል 1⃣4⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅        ✍ ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።በዛ ላይ እኔም ስልኬ ጠፍቷል እንደ በፊቱ አናወራም፤አሁን ገና ርቀታችን እየተሠማኝ መጣ።ሮቢን እንደ በፊቱ ባላገኘውና ባላወራውም ለሡ ያለኝ ፍቅር ቅንጣት እንኳን አልቀነሠም ነበር፤እንዲያውም ከነሠፍቆቱ ጋ ተደምሮ ፍቅሩ እጅግ በረታብኝ።ከ9 ወደ 10ኛ ክፍል ያለፍኩት ያው እንደተለመደው በደረጃ ቢሆንም የዘንድሮ ግን ያሳስባል፤ጥር ወር ውስጥ የ1st semester final exam ስለነበር ለማጥናት ብሞክርም አልቻልኩም፤ሀሣቤ ሁሉ ሮቢ ሆኗል።አሁንማ በስልክ እንኳን ካወራን 1 ሳምንት ከ3ቀን ሆኖናል።ጥር 14/2010አ.ም ማክሰኞ ቀን ከጊዜ በኀላ እንዳመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ክፍል ውስጥ ቆዝሜ ተቀምጬ አንድ ጓደኛዬ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠችና<ኧረ ምንሼ ርብቂ ሮቢ ሚሠራው ስራ ምንም አይነፋም fb ላይ ሚለቃቸው ፎቶዎች እና ሚሠጣቸው comment አንቺን ሲያፈቅርሽ ከነበረው ሮቢ አይጠበቅም>አለችኝ።ለራሴ ግራ ገብቶኝ ብቻዬን እያወራው መሄድ ነው የቀረኝ እሧ እንደዛ ብላኝ አዞረችብኝ።ግን ለሮቢ ያለኝ እምነት እንዲህ በቀላሉ ሚበገር ስላልነበር<በሮቢ account ሌላ ሠው እየተጠቀመ ይሆናል አልኳት፤እሺ እራስሽ አይተሽ ፍረጂ ብላ ከእናቱ ጋ ሆኖ የለቀቀው ፎቶ ላይ የተሠጠውን comment አሳየችኝ።ልጅቷ እኛ ት/ቤት ናት ስለኛ ግንኙነትም በደንብ ነው ምታውቀው የሠጠችው comment የኔ ብቻ ነበር ሚለው የድንጋጤና የፌዝ ሣቅ እየሣኩኝ ወዲያው እሡ መልሶ የሠጣትን ለማየት ከፈትኩት።የሡ ብሶ ቁጭ ፍቅሬ እናቴ ህይወቴ ነበር ሚለው ስልኩን ለቅቄው እየተንቀጠቀጥኩ<አይ አይ ውሸት ነው እሡ አይደለም> እያልኩ ጮክ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ።በዚ ጊዜ አጠገቤ ተቀምጣ ዞራ ስታወራ የነበረችው የልብ ጓደኛዬ የነገረችኝ ልጅ ላይ እንዴት ከፈተና በፊት ትነግሪያታለሽ እያለች ጮኸችባት።ስለዚህ እውነት እያልኩ ለራሴ የተቀመጥኩበት ወንበር ላይ ተቀምጬ መንሠቅሠቅ ጀመርኩ።<በቃ ርብቂ ማወቅሽ ካልቀረ ሁሉንም እነግርሻለው>አለችኝ ጓደኛዬ እኔም እጇን ጥብቅ አድርጌ ይዣት እያለቀስኩ<ውሸት እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ>አልኳት በሚለማመጥ ድምፅ በሠአቱ የነበረን free period አልቆ አስተማሪ እየገባ ስለነበር አሟት ነው ብላ ከክፍል ይዛኝ ወጣች።ግቢ ውስጥ ምሳ ለመብላት ምንጠቀምበት ቦታ ሄድንና ተቀመጥን።ምትነግረኝ ነገር ሮቢን እንደሚያሣጣኝ ስለማውቅ ንገሪኝ ብዬ መጠየቅ ፈራው።ለብዙ ደቂቃዎች ከኔ ለቅሶ ውጪ ሌላ ድምፅ ሳይሰማ ከቆየ በኀላ በረጅሙ ተንፍሣ መናገር ጀመረች።<ርብቂዬ ብዙ ጊዜ ሆኖታል፤ቢያንስ ወር ከምናምን ግን አንቺ ሮቢን ከምታፈቅሪው ይልቅ ሁሌ ምትነግሪን እንደምታምኚው ነው ስለዚህ ሁላችንም ልንነገርሽ አልደፈርንም>በመሀል አቋርጫት አሁንም ቢሆን አምነዋለው ምትሉትን አላምንም አልኳት።ባታምኚኝም ልነግርሽ ይገባል ብላ ንግግሯን ቀጠለች።<የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር> አለችኝ። ✎ ክፍል አስራ አምስት (15) ይቀጥላል...  ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨  @yehulum_bet Share➨  @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂   ✽┉┉‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉
إظهار الكل...
👍 8
#Morning_Motivation! የተሰጠን ዛሬ ነው፡፡ ማናችንም ስለነገ እርግጠኞች አይደለንም ስለዚህም እቅዳችንን ለማሳካት ከዛሬ በጣም ቅርብ ከሆነው ከአሁን የተሻለ ጊዜ የለም፡፡ ህልምህን ለማሳካት ጊዜው አሁን ነው። ነገን አትጠብቅ። ሁላችንም ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ አናውቅም፤ ግን ሁላችንም ያን ነገ እንጠብቃለን፤ ከእስከ ዛሬው የተሻለ ነገ ይሆናል ብለን እናምናለን። ለሁሉም ጊዜ አለው ስለዚህ የዛሬዋን በድል እና በደስታ ተወጡ፣ የሚያስደስታቹን ነገር አርጉ፣ ኑሩት። የዛሬን ስትኖሩት ነው የወደፊቱን ምታዩት፣ አምና ምትሉት፣ ስኬታቹጋ ምደርሱት የዛሬን አመስግናቹ፣ ደስተኛ ሆናቹ ስትኖሩት ነው። በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!
إظهار الكل...
🥰 7👍 3💯 1
​​•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥                                      ክፍል 1⃣3⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅            ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።የቀረው ቦታ ላይ የፍቅር ጥቅሶች በመፃፍ፣የተለያዩ ስዕሎችን በመሣል እና ለየት ያሉ ፅሁፎችን በመፃፍ ደብተሩን በደምብ ካስዋብኩት በኀላ ከጀርባው የቀረው ቦታ ላይ ከተዋወቅን ጀምሮ ያሣለፍነውን የማይረሣ ጊዜ ፅፌ ካሠብኩት ቀን ቀድሜ ጨረስኩ።ምንም እንኳን ከነ ሮቢ ቤት ብንወጣም አንድ ቀን እንኳን ርቀታችን እንዲሠማኝ አያረግም ነበር፤በቻለው ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ያገኘኛል።በስልክ ምናወራበት ሠአትም በጣም ብዙ ስለሆነ ሁለታችንም አብረነሸ ያለን ያህል ነበር ሚሠማን ግን ከኔና ከሡ ችግር ፍቅር የያዘው ይመስል ሁሌ አብሮን ነው።ጥቅምት ወር መጨረሻ አከባቢ እኔ ስልኬን ት/ቤት ተሠረኩኝ፤ያው ስልኬ ለኔ ስልክ ብቻ አልነበረችም ሮቢ አጠገቤ እንዳለ እንዳስብ ምታረግ ትልቅ ሀይልም ነበራት።ነገር ግን እናቴ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ በሷ ስልክ መደዋወል ጀመርን፤መቼም ከምንም ይሻላል።ህዳር 4 የሮቢ ልደት ነበር፤ምንም እንኳን ስልክ ባይኖረኝም ከሁሉም ሠው ቀድሜ ሮቢዬን መልካም ልደት የምልበት እድል አላጣሁም ነበር።የልደቱ ቀን እኔ ከቤት መውጣት ስላልቻልኩ እሡ እቤት መጥቶ ተገናኝተን በዛውም ያዘጋጀሁለትን ስጦታ ሠጥቼው ብቻውን እንዲያየው ነገርኩት።ሮቢ ስጦታውን እንዳየው ደውሎልኝ ብዙ አወራን፤በጣም ደስ ብሎት ነበር እኔም የሡ ደስታ ተጋብቶብኝ ደስተኞች ሆንን።ሰከንድ ሰከንድን፤ደቂቃ ደቂቃን፤ሠአት ሠአትን፤ቀናት ቀናትን እየተኩ ህዳር 15 ቀን ፍቅር ከጀመርን 9ወር ከ10 ቀን በኀላ ቀለበት አደረገልኝ።በጣም የተለየ ስሜት ነበር የተሠማኝ እንዴት ብዬ ላስረዳቹ በቃ ያላያችሁ ስታዩት ያያችሁ ደሞ የተሠማችሁን አስታውሣቹ ትንሽ ከገባቹም ተረዱኝ።ቀኑን ሙሉ ማታም ቁጭ ብዬ ቀለበቴን ሣየው አደርኩኝ።ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ። ✎ ክፍል አስራ አራት (14) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ። ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨  @yehulum_bet Share➨  @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂   ✽┉┉‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉
إظهار الكل...
👍 10 3
​​​​•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦              🌹የፍቅር ንቅሣት♥                                      ክፍል 1⃣2⃣ ✅በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✅      የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው፤የኔና የሮቢ እናት ተጣሉ።ሮቢ ነገሩ ስላስጨነቀው ሁሉቱን ለማስታረቅ የአስትን እናት ሊያመጣት ወደ አሠላ ሄደ።ሮቢ ስልኩ ተበላሽቶበት ስለነበር እሡ በሌላ ሠዉ ስልክ ሲደዉልልኝ ብቻ ነበር ማገኘው፤እናቴም ቤቱን ለመልቀቅ አስባ ለጊዜው እዛው ሠፈር አገኘች።ለሮቢ እንኳን ነግሬው እንዲያስቆማት ማድረግ አልቻልኩም ነበር ምክንያቱም ሮቢ አልደወለልኝም፤ሮቢ አርፍዶ ነበር ቤቱን ለቀን አዲሡ ቤት እቃውን አስገብተን ስንጨርስ ደወለልኝ።ሮቢ በጣም ባይናፍቀኝ ኖሮ ቀዛ ሠአት ባላወራው ደስ ይለኝ ነበር፤አነሳሁና አዋራሁት በጣም ቅዝቅዝ ብዬበት ስለነበር ምን እንደሆንኩ ሲጠይቀኝ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ሮቢ ምንም አላለኝም ሣወራም አይመልስልኝም በጣም ጨነቀኝ ስሙን ደጋግሜ ብጠራውም መልስ የለም ከብዙ ዝምታዎች በኀላ ያለ ምንም መልስ ስልኩ ተዘጋ።ሮቢ በጣም ሲከፋው ምንም አይናገርም ዝምታን ነው ሚመርጠው፤ምንም አያጠያይቅም አሁን ሮቢ በጣም ከፍቶታል።እኔም ሀዘኔን ዋጥ አድርጌ እሡን እንዳላፅናናው እንኳን እንደ ሌላው ጊዜ አብረን አይደለንም ሌላው ቢቀር እንኳን ስልኩ አይሠራም።ሮቢ በነጋታው ከተረጋጋ በኀላ ደወለልኝ እዛ ምንም እንደማይሠራ እና ቶሎ እንደሚመጣ እቤትም መጥቶ እንደምንገናኝ ነገረኝ።ሮቢ በነገረኝ ቀን እቤት መጣ።ሮቢዬን ከ3 ቀን ናፍቆት በኀላ አገኘሁት፤ሁሉንም ሠላም ብሏቸው እኔ ጋ ሲደርስ ተያየን እና ተቃቀፍን።እስኪሄድ ድረስ አቅፎኝ ቁጭ አልን፤ማም እያየችን ትገረማለች ምንም ብንፈተን ፍቅራችን ይበረታል እንጂ ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር።ከሮቢ ጋ በዚህ መንገድ እሡ እቤት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከነ ሮቢ ቤት ነሀሴ 21/2010አ.ም ነበር የወጣነው፤ማም የተሻለ ቤት ስታገኝ ነሀሴ 28/2010አ.ም ጭራሽ ሠፈሩን ለቀን ወደ ሌላ ሠፈር ገባን።የገባን ቀን ለሮቢ በምልክት እየነገርኩት መጣ።ሮቢ አዲስ የተከራየንበት ቤት ሁሌ ይመጣል፤ቢያንስ አሁንም ሮቢዬን አገኘዋለው ለኔ ይሄ በቂ ነበር።እንግዲህ በዚህ ሁኔታ 2011 መጣው መጣው ተቀበሉኝ ማለት ጀመረ።መስከረም 1/2011አ.ም ሮቢዬ ወደ ከሠአት እቤት መጥቶ አብረን በአሉን ደስ ብሎን አሣለፍን።ለ10ኛ ክፍል ሁለታችንም መዘጋጀት ጀመርን፤ት/ትም ተጀምሮ እንደ በፊታችን ት/ቤት መገናኘት ጀመርን ቅዳሜ ቅዳሜ ደግሞ ሮቢ እቤት እየመጣ አብረን እንውል ነበር።የሮቢ ልደት ህዳር ወር ላይ ስለነበር እኔ ልሠጠው ያሠብኩት ስጦታ ደሞ ጊዜ ስለሚፈልግ ስልኬ ያሉትን ፎቶዋችንን ቶሎ በማሳጠብ ጀመርኩኝ።ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው። ✎ ክፍል አስራ ሶስት (13) ይቀጥላል...  ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨  @yehulum_bet Share➨  @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂   ✽┉┉‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉
إظهار الكل...
👍 12 3
Photo unavailable
👍 17👏 1
Photo unavailable
إظهار الكل...
🤣 10😁 1