የስንኝ ቋጠሮ
الذهاب إلى القناة على Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
إظهار المزيد2 046
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
2 046
በውስጥ መስመር የተላከ ግጥም
በ Jerry
🌧በዝናብ ስትቀጥረኝ🌧
🌧በዛ በክረምቱ ዝናብ በሚበዛው
🌧አዋራውም ቦክቶ ጭቃ በሚሆነው
🌧መብረቅ እንደልቡ እንዳሻው በሚጮኀው
🌧ነይ ስትል በዝናብ ጊዜውን ጠብቀህ
🌧መች መሰለኝ እኔ እንዳላየው እንባህ
🌧ለካስ ውስጥህ ጠቁሮል ለካ ውስጥህ ቆስሎል
🌧እኔን በማጣትህ አዝነሀል አሞሀል
🌧ሀዘንህን አይቼ ጤና እንደማይኖረ ኝ
🌧ይሄን ስለምታውቅ በዝናብ ቀጠርከኝ
🌧በሁለቱ ጉንጮችህ የሚፈሰው እንባ ዝናብ እንዲመስለኝ
🌧ለካ እንዳላየው ነው እንባህን በአይኔ
🌧ዶፍ ዝናብ ሲዘንብ የምጠራኝ ያኔ
ገጣሚ እየሩሳሌም አሰፋ
@gitmv
@gitmv
@gitmv
2 046
Group:
መሳም ያሣሣተው የስተ-ቀኙ ፊቴ
ቡጢ አበልዞታል ቀጥቅጦኝ ጠላቴ
ሸክም ያልታከተው ድንድኑ ትከሻ
ዛሬ ቁልቁል ዘምሟል የለውም መካሻ
ስንት ጉድ ያዘለው ጀርባዬ ቢጎብጥ
ጫንበት ይላሉ ጭራሹን እስኪላጥ
ዳገት ሽቅብ ወጥቶ ቢዝልም ጉልበቴ
ጎመን መደለሌን መች አይተው በህይወቴ
መዳፌ ሻክሮ ከአለት ቢጠጥር
ደልቶኝ መሠላቸው ሌላ ጉድ ስፈጥር
ጫማዬን ሣይለኩ በእኔ እግር ገብተው
ሠፍቶት ነው ይላሉ በማያገባቸው
ልኩም ነው ይላሉ ጭራሽ ሣይነካቸው
በጫማዬ ልኬት ህይወት በሠፋችው
ጠቦ እንደምሠቃይ ማን በነገራቸው
ፀባዖት
@gitmv
@gitmv
@gitmv
2 046
የፈላስፎች ንግግር
~~~~~~
ሀብታም ይደኸያል ሀኪምም ይሞታል፣
ጎበዝ ይሸነፋል ብልህ ይሳሳታል፣
የበራውም ጠፍቶ የሠሩት ይፈርሳል፣
የቆመውም ወድቆ የሳቀ ያለቅሳል።
ፍሬ መሬት ወድቆ ከዋለ ካደረ፣
ሰው ገንዘብ አግኝቶ መክበር ከጀመረ።
የመጣ ነውና ቀድሞውን ከጥንት፣
ሁለቱም አይድኑም ከመበላሸት።
የሰዎችን ፀባይ የተመራመረ፣
አንድ ፈላስፋ ሊቅ እንዲህ ተናገረ።
በጣም በማስተዋል ከላይ እስከ ታች፣
ስመለከታቸው የሰውን ልጆች።
እያጣሁባቸው ግብሩ እሚመሰገን፣
እንቃቸው ጀመር እጅግ ያለመጠን።
የደንቆሮ መንፈስ ምንኛ ታደለ፣
ብልጥነት አላጣም ጅል እየመሰለ።
እንኳን መፅሀፍ ማንበብ ፊደል ሳያጠና፣
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና።
የሊቅ ሰው መከራ የብልኅ አባዜ፣
ሲጨነቅ መኖር ነው ባሳብ በትካዜ።
አቶ ዐሳበ ቢስ ይተኛል ዝም ብሎ፣
ከትራሱ ጋራ ዐሳቡን ጠቅሎ።
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
........
~~~~~~~~~
@gitmv @gitmv @gitmv @gitmv
@gitmv
@gitmv
@gitmv
@gitmv
2 046
እንደ ክረምት ዝናብ ፣ችግሬ ይረግፋል
ምስኪን ትከሻዬ ፣እሱን ይቀበላል
ሰዎቹም ይላሉ ፣እንዴት ቻለው እሱ
ሁሌም ብልጭ ይላል ፣ አይከደን ጥርሱ
የተበደለ ሰው፣ ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት፣ ፈገግታ ነው መልሱ
ይስማዕከ ወርቁ
