📚 አዳም ረታ ™
الذهاب إلى القناة على Telegram
Quotes ✒️ | Reviews 📝 | Poetry 📖| Research | Literary Discourse A hub for readers and thinkers. 📚
إظهار المزيد3 741
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
3 741
Repost from Seblework Old Books Delivery ™📚
የታሪክ
የልቦለድ
መንፈሳዊ መጽሐፍ ት
እንገዛለን
ይደውሉልን ካሉበት መጥተን እንገዛለን
ስልክ ቁጥር ፦ 0946523397
@sebleold inbox 📚
3 741
የአዳም ረታ 'መዝሙረ ሄላም' በ Paper back ታትሟል።
:
@sebleworkbooks inbox order
ስልክ ቁጥር 0946523397 ይደውሉ 📚
ይዘዙን ክፍለ ሀገር ም ሆነ ከሀገር ውጭ የ Delivery እናደርጋለን ።
3 741
Repost from N/a
ኤልሻዳይ ትባላለች። (አስቸጋሪ ወዳጄ ናት)
"customize your own stickers!" ነው ሞቶ'ዋ እዘዟት እስቲ..
@ink_duoo
3 741
ያመሻሽ ስንኞች
(በእውቀቱ ስዩም)
በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ
እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤
ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ
ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤
እሳቴን አንድጄ
ጭራሮ ማግጄ
ሰታቴየን ጥጄ
ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ
እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤
በዕውቀቱ ስዩም
3 741
Repost from N/a
አዝማሪ ሀሰን አማኑ በአድዋ ጦርነት ወቅት ከአርባኞች ጀርባ ወኔ በመስጠት አዝማሪዎች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። አይነ ስውር ነበሩ።
በመሳፍንቱም፣ በነገሥታቱም እጅግ የታወቁ እና የተከበሩ አዝማሪ ነበሩ፡፡ በአድዋ ጦርነት ወቅት ጦር ሜዳ ድረስ በመሄድ በግጥም እየሸለሉ እና እየፎከሩ ጦረኞችን ሲያጀግኑ የነበሩ ሰው ነበሩ።
ውልደታቸው ከወሎ ነው። ስለእሳቸው ታሪክ የተጻፈ መጽሐፍ እስካሁን አላገኘሁም፤ ከግጥሞቻቸው በስተቀር። ሐሰን አማኑ በመሳፍንቱም፣ በነገሥታቱም እጅግ የታወቁ እና የተከበሩ አዝማሪ ነበሩ፡፡ በዋናነት የንጉሥ ሚካኤል አዝማሪ ቢሆኑም በዐጼ ዮሐንስም በዐጼ ምኒልክም ዘንድ እንዲሁ ተወዳጅ ነበሩ፡፡
"ሸዋ ነው ሲሉት፣ ዓድዋ የታየው፤
ሺናሻ መላሽ፣ ወንዱ አባ ዳኘው።
ወዳጁም ሣቀ፣ ጠላቱም ከሳ፤
ተንቀሳቀሰ ዳኘው ተነሣ፤
አራቱም አህጉር፣ ለሱ እጅ ነሣ።"
(ዝክረ ነገር፤ ገጽ 880)
በተመሣሣይ መልኩም፣ ከዓድዋ ጋር በተያያዘ ስለወሎው ንጉሥ ሚካኤልና ስለታላቁ ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራው) የሙገሳ ግጥሞች ተቀኝቷል። ስለንጉሥ ሚካኤል እንዲህ አሉ፦
"ማን በነገረው ለጣሊያን ደርሶ፤
ሚካኤል መጣ ረመጥ ለብሶ።"
(ዝክረ ነገር፤ ገጽ 883)
(መጪው "ሚካኤል" ሰውም መልአክም ነው። ሰው ሲሆን፣ ንጉሥ ሚካኤል ነው። መልአኩ ሚካኤል ሲሆን ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን አትጊና አጽኚም ነው።)
ስለፊታውራሪ ገበየሁ የተገጠሙት ሁለት መንቶዎች ግን በስፋት የሚታወቁ ናቸው። የነዚህም ገጣሚ ሐሰን አማኑ ነው።
"ታጭዶ ሲወቃ፣ ዐድዋ ላይ ገብስ፤
አናፋው ዘልቆ፣ (ጎራው) በመትረየስ።
ዐድዋ ሥላሴን፣ ጥሊያን አረከሰው፤
ገበየሁ በሞቴ፣ ግባና ቀድሰው።"
(ዝክረ ነገር፤ ገጽ 885)
____
ማጣቀሻ - ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፣ ዝክረ ነገር፣ አዲስ አበባ፣ 1962
3 741
Repost from N/a
ምንሽን - (በዕውቀት ሥዩም)
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፣ በወጣሁበት እንዳልቀር
ሀገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፣ ግና ምንድር ነው ማፍቀር?
እንዳስመሳይ አዝማሪ፣ ካልሸነገልኩሽ በቀር
ከተወለድሁ እስተዛሬ፣ ከጣትሽ መች ጎርሼ
ወተትሽን መች ቀምሼ
ወለላሽን መች ልሼ
ሲርበኝ
ጠኔ በቀኝ በግራ፣ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ
የት ነበር የንጀራሽ ሌማት?
ሾላ ስለቅም ተሻምቼ፣ ከሽመላ ከማማት
ኑሮየ ሁዳዴ ጦም፣ ፋሲካ አልባ ህማማት
እና ከድሎት አገር፣ የሲሳይ ዶፍ ከሚያወርደው
ምን ገፍቶኝ ነው በሞቴ? ወዳንቺ ምሰደደው
ምን ነክቶኝ ነው? ምንሽን ነው የምወደው?
እኔና ብጤዎቼ፣ እኛ ቅብዝብዝ ልጆችሽ
መስኮት በሩ ተዘግቶብን፣ ተበትነን በደጆችሽ
ይሄው ሶስት ሺ ዘበን፣ ወደ ሰማይ አንጋጠን
በንዝርት እግር ተንበርክከን፣ በቀይ እንባ ስንማጠን
የእለት እንጀራችንን ነፍጎ፣ የለት ገጀራችንን ሰጠን።
አሁንማ ለመከራሽ፣ ማን አለና የሚገደው
እሪታሽን እንደዘፈን፣ ያለም ጆሮ ለመደው
እና ምንሽ ነው ሚስበኝ? ምንሽን ነው የምወደው?
ዛሬም ሆነ ያለፈው
በላባ ብእርም ይሁን፣ በኪቦርድሽ የተፃፈው
ታሪክሽን ሳነበው፣ ደምና አመድ ነው የሞላው
መች ተነቅሎ ከወለልሽ፣ የሾህ ጉንጉን አሜኬላው
መች ተጥሶ ያውቃልና፣ የጭቆናሽ ዘመን ኬላው
ሥልጣን ፈልሶ ቢሸጋገር፣ ካንዱ ጭራቅ ወደ ሌላው።
እናም እንሆ!
ያለፈውን ዘመን ትቼ፣ የቀረኝን እያሰላሁ
የብርሃን ቅሪት ባጣ፣ አምፖሌን በተስፋ ሞላሁ
እንጀራየን እንደ ሀሰን* በዳበሳ እየበላሁ።
ከዚህ ሁዋላ አልልሽም፣ ወዴት አለ ያንቺ አለኝታ
ግን ምንሽ ነው ግን የሚስበኝ? ልማድ ይሆን ወይ ይሉኝታ?
እግሬን ከምድርሽ ጋራ፣ ምንድነው ያስተሳሰረው
ያገር ፍቅር አለኝ ብልስ፣ ምንሽን ነው የማፈቅረው?
_
*ሀሰን ተብሎ የተጠቀሰው (ሀሰን አማኑ የተባለው ዝነኛው አይነስውር የወሎ አዝማሪ ነው።)
3 741
Repost from N/a
“connaissais de face” a rough translation is “knowing someone by face”, as in, you’ve seen them plenty times, even interacted with them, but never got to actually exchange names. this song, by khruangbin, was meant to be in reference to a waitress from a coffee shop the band used to frequent and after many years, the waitress stopped working at that place and they all felt some sort of nostalgia for this connaissais de face and it took them down memory lane.
“it makes me think of that place”
what place? were they together? take me there.
3 741
ደነቀኝ መኖርሽ! (በድሉ ዋቅጅራ)
ጢሻ ስመነጥር፣ ስደለድል ጉድባ፤
አፀዴን ስቆፍር፣ ልተክል አበባ፤
መኖርሽ አይደንቅም::
ያበባ ችግኜ፣ እንዳትደርቅ በበጋ፤
ለወንዝ ቦይ ስቀድ፣ ጥላ ስዘረጋ፤
መኖርሽ አይደንቅም፡፡
እንቡጥ እያሻሸሁ፣ እንዳዲስ ነፍሰጡር
ያበባዬን መፍኪያ፣ ዕለቱን ስቆጥር፣
መኖርሽ አይደንቅም፡፡
ከአበባው ውበት፣ መልክሽ ተመሳስሎ፤
ከመአዛው ጋራ፣ ጠረንሽ ተጋብቶ፤
አንቺን ያዩ ንቦች፣ አበቦቹን ንቀው፤
አይንሽ ላይ፣
ጉንጭሽ ላይ፣
ከናፍሮችሽ ላይ፣ ሲያንዣብቡ ውለው፤
ክንፋቸው እየዛለ፣ እግርሽ ሥር ሲወድቁ፤
"አበስኩ ገበርኩ!" ስል፣ እያየሁ በሩቁ፡፡
መኖርሽ አይደንቅም::
ኖረሽ
ኖረሽ
ኖረሽ...
መአዛው ሲጠፋ፣ አበባው ሲደርቅ፤
ያበበ ፍለጋ፣ ንብ ከደጄ ሲርቅ፤
ያለ ለምለም ችግኝ፣
ያለ እንቡጥ ተስፋ፣
ያለ አበባ ፍካት፣
ደረቅ አፀዴ ውስጥ፣ እንደፈካሽ ሳገኝ፤
ከኖርሽው የበለጠ፣ መኖርሽ ደነቀኝ::
-------------
መስከረም፣ 2015፤ (አደይ እና ጥቀርሻ)
3 741
Repost from Seblework Old Books Delivery ™📚
“ሰው ትክክለኛውን ትምህርት ያገኘ እንደሆነ ለስላሳና እግዜርን የሚመስል ፍጡር ነው፤ ትምህርት ያላገኘ እንደሆነ ግን በምድር ላይ ካሉት አራዊት ሁሉ የከፋ ይሆናል።”
[ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ ]
[ ከእጓለ ገብረዮሐንስ 📚 ]
3 741
Repost from Tedossier
ዛሬ ነሐሴ 12፣ 2018 ዓ.ም. ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድሕን 90ኛ የልደት ቀኑ ነው፤ ይህንኑ በማሰብ የሕይወት ታሪኩ የተዘገበበትን “ምጥቀት በቅኔ አክናፍ” የተሰኘ መጽሐፍ የመረመርኩበትን የመጽሐፍ ዳሰሳ ጋብዣችኋለሁ::
3 741
የዱር አበባ ዝምታ
(የመንገደኛ አንባቢ ግብዣ)
ይህቺን ሰሞን “የዱር አበባ” መኾን የሚመኘውን የሞክሼዬን የቴዎድሮስ ካሳን ግጥሞች እየገረብኹ ነው፤ ስለወደድኳቸው። “የዱር አበባ” ቴዎድሮስ ካሳ ( Tewodros Kassa) በ2017 ዓ.ም. ያሳተማት፣ የግጥሞቹን ስብስብ የያዘች መጽሐፍ ናት። ቢሮ <-> ቤት ስመላለስ እያነበብኳት፣ አንዳንድ ነገሮች ገርመውኝ በእርሳስ ሳሰማምርባት ሰነበትኹ። እንዲያው ለግጥም ቀልብ ያለው ጎበዝ በጥልቀት ቢያነባቸውና ቢያመሳጥራቸው ብዬም እየተመኘኹ፣ ዐይኔ የገባውን ላካፍላችኹ።
“ሕይወት”፣ ቅዝቃዜ፣ ዝምታ፣ ሕማም ይበረታባቸዋል፤ እንደዋዛ ልብ እንዳልኩት “ሕይወት” የሚለው ቃል የሌላቸው ግጥሞች ሦስት አራት ቢሆኑ ነው። ሕማሞቹ ሳይወዱ በግድ የሚጋቡ፣ የተረሳ/የሻረ ቁስል ሳይቀር የሚነካኩ ናቸው። ስንኞቹ በዝምታ ማዜምን፣ በዝምታ መቀኘትን፣ በዝምታ መጮኽን የሚቃትቱ ናቸው። አስረጅ ይኾኑን ዘንድ እነዚህን ስንኞችና አንጓዎች እንያቸው፦
ጡንቻዬ ፈርጥሟል
ብቻ በሆንኩበት
ትንሽ ፈገግታና ብዙ ዝምታ ነው
ጥሩ ኑሮ ማለት። (“በሪ ጠፊ ፍቅር”)
***
አካልህን ጥለህ
ሁነው ለሌቱ ኩል፤
ግጥም መጻፍ ልመድ
፤ በዝምታህ በኩል። (“የሌሊት ሹክሹክታ”)
***
ደንሱ ምሽቱ ሳይጎህ፤
አንጎራጉሩ
ድምፅ ምን ያሻል!?
ልባችሁ ከልቤ ላይሻል፤
የዝምታን [እሩ---ቅ] መንገድ
አትጋፉት
ተዉት ይቅር፤… (“የአብሮነት መለከት”)
***
ምርጥ ግጥም ማለት
በሁለት ፍቅሮች መኃል ያለ ዝምታ ነው። (“እነኾ የሰው ልጅ…”)
እነዚህ መንገድ ለመንገድ ሳነብ ምልክት ያደረግሁባቸው #ዝምታ በቀጥታ የተጠቀሰባቸው ስንኞች ናቸው። መጽሐፏ ግን ቃሉ ሳይጠራ (implicitly) ዝምታ የተናፈቀባቸው ሌሎች አንጓዎችና ስንኞችም አሏት።
በስንኞች የተቀመሩ ርእሶቹ፣ ዐዳዲስ ምሰላዎቹ፣ የስሜት አያያዙ ለቴዲ መለዮዎቹ ይመስላሉ።
ግጥም ተንታኝ ከ“ማኮብኮቢያ”ው እስከ ማረፊያው ያሉትን ኅፅን በኅፅን አንብቦ እንዲተነትናቸው፤ ሊሪካል ግጥም አፍቃሪውም ስሜት በስሜት አዳምጦ እንዲደመምባቸው እጋብዛለሁ።
በርታ ሞክሼ!
©️Tewodros_Atlaw
3 741
ስብሃት:-
''የሚጥል በሽታ ነበረብኝ። የእኔ እንደ ዶስቶየቪሲኪ እያነሣ የሚያፈርጥ አይነት አይደለም። እኔ ላይ የደረሰብኝን ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ሌሊት እነሳና በኃይል! በኃይል እጮሃለሁ። ተነስቼ እሮጣለሁ። ይዘውኝ ያስተኙኛል።
ጡንቻዬ ደግሞ የዛን ጊዜ በጣም ጠንካራ ነው። ጠዋት ስነሣ በጣም ድክም ያደርገኛል። አንዳንዴም ጉንጬን እነክሳለሁ። አንዳንዴ ጧት ስነቃ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰከንዶች ማን እንደሆንኩና የት እንደሆንኩ አላውቅም። በዚህ በሽታ ምክንያት ልጅ ላለመውለድ ወስኜ ነበር።
ዘነበ ወላ : ''ለምን?''
ስብሃት : በምወልደው ልጅ ይተላለፋል የሚል እምነት ነበረኝ።
ዘነበ ወላ : ባለቤትህ በዚህ ተስማማች?''
ስብሃት : ምን አማራጭ አላት? የሚቸልኮትስ ቼርማን እንደ አባቷ ነበር። ኤውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት አራት ዋነኛ የንዲህ አይነት በሽታዎች እስፔሻሊስት አንዱ ከሆነው ሀኪም ጋር ሚስተር ዲክ ቀጠሮ ያዘልን።
''በሽታህ በዘር አይተላለፍም'' አለን ''ነገር ግን ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ኤፕሌፕቲክ ለመሆን ሦስት ከመቶ እድል አለው። ስለዚህ ምናልባት ያንተ ልጅ ኤፕሌፕቲክ ቢሆን፣ ሎተሪው ሦስት ከመቶው ደርሶት ነው እንጂ ካንተ ወርሶት አይደለም'' አለኝ። መድኃኒት አዘዘልኝ በቀን አንዴ ጊዜ የሚዋጡ።
''ለብላታ ደሬሳ ያመኛል ሳልላቸው ላማክራቸው ወሰንኩ። ይህ በሽታ በእኛ ሀገር <የባርያ በሽታ> ይባላል። አነሣሁና ጠየቅኳቸው። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደ ማርኮ ፖሎ ጉዞ ከአንድ ሰአት በላይ በባርያ በሽታ ትንታኔ ይዘውኝ ተጓዙ። በመጨረሻ መልሣቸው እኔ ሠርቼበት አላውቅም ሆነ። እንደኔው የሀገራችንን መድሃኒት የሚያውቅ ጓደኛዬ እገሌ እንደነገረኝ ብለው አንድ መድሃኒት ጠሩ። ተጠቀምኩባት። ብዙም ሳልቆይ ከበሽታዬ ዳንኩኝ። ኬኒኑን መዋጥ አቆምኩ። ከሃና ጋርም የመጀመሪያ ልጃችንን ያለምንም ስጋት ለመውሰድ ተስማማንን።
ዘነበ : መድሃኒቱን ብትነግረኝ
ስብሃት : ታስሬበታለሁ
ዘነበ : ለምን?
ስብሃት : ፖሊስ ተወው ብሎ
ዘነበ : በሕግ የተከለከለ ነው?
ስብሃት : ይላሉ
ዘነበ : ታዲያ አንተ በተፈጥሮህ ሕግ አክባሪ ሰው ነህ ለምን ሕገ ወጥነቱን መረጥከው?
ስብሃት : መድሐኒቴ ከሕመም ፈውሶኛል። ደስታንም ይፈጥርልኛል።
ዘነበ : መድሃኒቱን አልነገርኸኝም
ስብሃት : አንዳንዱ ሰው በሰው ሕይወት ውስጥ ገብቶ ይፈተፍታል።
ዘነበ : በምን?
ስብሃት : ደግሞ እኮ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ሲል ትሰማዋለህ
ዘነበ : አልገባኝም?
ስብሃት : ግን የእኔም በባሕሪዬ አደባባይ መሆን የጎዳኝ መሰለኝ
ዘነበ : አዎን እንደሀበሻ በአደባባይ ተከናንበህ ጨለማን ተገን አርገህ የልብህን መከወን
ስብሃት : እንደዛ ነው የሚደረግ፣ ሰው ምን ይለኛል እያልክ
ዘነበ : መድሃኒቱን ግን አልነገርከኝም
ስብሃት : አልነግርህም
ዘነበ : ለምን?
ስብሃት : ዘነበ አምንሃለሁ። አንተም ሌላ የምታምንም ወዳጅ አለ። ስለዚህ ትነግረውና ሳይታወቅ መድሐኒቱን ታረክሱብኛላችሁ።
(ማስታወሻ - ዘነበ ወላ)
3 741
‹‹በአንድ በኩል ስታስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ እኔ የትግራይ ሰው ነኝ፣ እኔ አማራ ነኝ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩም አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ በሴት አያቶቻችን በራፍ ላይ ማን እንዳለፈ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? የእኔን ጥሩ ኦሮሞነት እግዚአብሔር እና የሴት አያቶቼ ናቸው የሚያውቁት፡፡ የሁሉንም እንዲሁ፡፡››¹
«ወደድንም ጠላንም በመኖር ኪነጥበብ ተነካክተናል።»²
1 ሰሎሞን ደሬሳ
2 አዳም ረታ
