cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አቡ-አብዲላህ ሙባረክ ሐቢብ

★ይህ ቻናል የሚያጠነጥነው በአለህ ፍቃድ የተለያዩ የዲን እውቀቶችን ለእናንተ በማድረስ ይሆናል ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት ወይንም ዐቂዳ ማለት፣ ቁርኣንና ሀዲስን በ(ሠለፎች) ቀደምቶች ግንዛቤ ላይ በተመሰረተ መልኩ ከሆነ ብቻ ነው። ✍ ከወንድማችሁ ሙባረክ ሐቢብ https://t.me/Ibnu_hebib ለአስታየታችሁ እና ለምክራችሁ☞ https://t.me/Mubarekhebib

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
198
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በቁርኣን ላይ ያሉ የጂሃድ አንቀፆች ግን የተለያዩ ገደቦች እንዳሏቸው ሙስሊሞች ሁሉ ስለሚረዱ በአንድም አጋጣሚ አንድም በኢስላማዊ መንግስት የሚመራ ጦር ህዝቦችን በጅምላ ጭፍጨፋ አጥፍቶ አያውቅም! በየትኛው የኢስላም ማህደር ላይ ነው ጭራሽ የማይዋጉ ወንዶች፣ ሴቶች፣ አዛውንት፣ ህፃናት፣ እንስሳት የተገደሉት?! በየትኛው መዝገብ ላይ ሰፍሯል?! መቼም ይህን ሁሉ የዘረዘርኩት “ሁሉም ክርስቲያኖች ደመኞች ናቸው!” ብዬ አስቤ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፤ እምነቱም በራሱ በቀጥታ ሽብርን የሚያበረታታ ላይሆን ይችላል። ታዲያ እናንተ አጃችሁን ወደ ቁርኣን የቀሰራችሁ ክርስቲያን ግለሰቦች ሆይ! ለነዚያ አንቀፆቻችሁ ማብራሪያ ካላችሁ እኛ ደግሞ ስለምትመዟቸው ቁርኣናዊ አንቀጾቻችን የተሻለና ይበልጥ የተቃና ማብራሪያ እንዳለን ማወቅ ተሳናችሁን?! - አሁን ደግሞ የላይኞቹን አንቀፆች ከሚከተሉት ኢስላማዊ የጦርነት ህጎች ጋር አነፃፅሩልኝ! * የኛ ኢስላም ፦ የሙስሊሙን ህልውና ለመፋቅ ሰይፋቸውን ከመዘዙ ጠላቶች ጋር በሚደረግ የጦር ሜዳ ፍልሚያ ላይ እንኳ ወሰን ማለፍን የሚከለክል ነው! አላህ እንዲህ ብሏል፦ وَقَٰتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ يُقَٰتِلُونَكُمۡ وَلَا تَعۡتَدُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِينَ = {እነዚያ የሚጋደሏችሁን በአላህ መንገድ ላይ ተጋደሏቸው፤ ወሰንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።} [አል-በቀረህ 2 : 190] አዎን! “ለሚጋደሏችሁ አንገታችሁን ስጡ!” አልተባልንም! ግን ራስን በመከላከል ሂደትም ቢሆን የትኛውንም የፍትህና የሰብዓዊነት ወሰን ማለፍን ተከልክለናል! -› “ወሰንም አትለፉ!” የሚለውን የአንቀፁን መልዕክት ታዋቂው የመልዕከተኛው ባልደረባ ዐብዱ’ላህ ኢብኑ ዐብ-ባስ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፦ يقول: لا تقتلوا النساء ولا الصِّبيان ولا الشيخ الكبير وَلا منْ ألقى إليكم السَّلَمَ وكفَّ يَده، فإن فَعلتم هذا فقد اعتديتم. «”ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አዛውንትን፣ እርቅን ወደናንተ ያቀረበንና እጁን የሰበሰበንም አትግደሉ! ይህን ካደረጋችሁ ወሰን አልፋችኋል!” ማለቱ ነው!» [አጥ-ጠበሪ - “ጃሚዑ’ል-በያን..” (“ተፍሲሩ’ጥ-ጠበሪ”) (3/563)፣ ኢብኑ አቢ ሓቲም - “አት-ተፍሲር” ( 1/325) ቁጥር 1721] ያስተውሉ! ይህ ሁሉ ገደብ በጦርነት ላይ ነው። * እንዲሁም ነብያችን ዘማቾችን ለውጊያ በሚልኩበት አጋጣሚ ዘወትር ከሚመክሯቸው ምክሮች መካከል፦ وَلَا تَغْدِرُوا وَلَا تَمْثُلُوا وَلَا تَقْتُلُوا وَلِيدًا... -› «ቃል ኪዳን አታፍርሱ፤ ሬሳንም አትቆራርጡ፤ ህፃንም አትግደሉ..» የሚል አደራ ይገኝበታል። [ሙስሊም የዘገቡትና ቡረይደህ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው፤ ሰሒሑ ሙስሊም - ቁጥር (1731)] * እንዲሁም ዐብዱ’ላህ ኢብኑ ዑመር የሚከተለውን አስተላልፈዋል፦ عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بن عمر: أَنَّ امْرَأَةً، وُجِدَتْ فِي بَعْضِ مَغَازِي رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مَقْتُولَةً، فَأَنْكَرَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَتْلَ النِّسَاءِ وَالصِّبْيَانِ -› «በመልዕክተኛው አንድ ዘመቻ ላይ አንዲት የተገደለች ሴት ተገኘች፤ እርሳቸውም ሴቶችንና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።» [አል-ቡኻሪይ - ቁጥር (3014) ፤ ሙስሊም - ቁጥር (1744)] * አል-ኢማም ኢብኑ ዐብዲ’ል-በር ይህንን ዘገባ ባብራሩበት አጋጣሚ እንዲህ ብለዋል፦ وَأَجْمَعَ الْعُلَمَاءُ عَلَى الْقَوْلِ بِجُمْلَةِ هَذَا الْحَدِيثِ وَلَا يَجُوزُ عِنْدَهُمْ قَتْلُ نِسَاءِ الْحَرْبِيِّينَ وَلَا أَطْفَالِهِمْ «የኢስላም ሊቃውንት የዚህን ሐዲሥ ጥቅል መልዕክት በመቀበል ላይ ተስማምተዋል፦ እናም እነርሱ ዘንድ የተዋጊ ጠላቶችን ሴቶችና ህፃናትን መግደል አይፈቀድም..» [ኢብኑ ዐድቢ’ል0በር - “አት-ተምሂድ” (16/138)] በተመሳሳይ መልኩ አል-ኢማም አን-ነወዊ እንዲህ ብለዋል፦ أَجْمَعَ الْعُلَمَاءُ عَلَى الْعَمَلِ بِهَذَا الْحَدِيثِ وَتَحْرِيمِ قَتْلِ النِّسَاءِ وَالصِّبْيَانِ إِذَا لَمْ يُقَاتِلُوا... « ይህ ሐዲሥ የሚተገበር ስለመሆኑና ሴቶችና ህፃናትም እስካልተጋደሉ ድረስ እነርሱን መግደል እርም ስለመሆኑ ሊቃውንት ተስማምተዋል..» [አን-ነወዊ - “ሸርሑ ሰሒሂ ሙስሊም” (12/48)] * እንዲሁም አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዳስተላለፉት ነብያችን እንዲህ ብለዋል፦ " انْطَلِقُوا بِاسْمِ اللَّهِ وَبِاللَّهِ وَعَلَى مِلَّةِ رَسُولِ اللَّهِ، وَلَا تَقْتُلُوا شَيْخًا فَانِيًا وَلَا طِفْلًا وَلَا صَغِيرًا وَلَا امْرَأَةً .. " -› «በአላህ ስም፣ በአላህ ታግዛችሁ በመልዕክተኛው መንገድ ላይ ጉዞ ጀምሩ፤ ያረጀ ሽማግሌን፣ ህፃንን፣ (ያልደረሰ) ልጅንና ሴትን አትግደሉ! ..» [አቡ ዳዉድ - ቁጥር (2614)] * እንዲሁም ረባሕ ኢብኑ አር-ረቢዕ ባስተላለፉት ዘገባ ደግሞ ነብያችን እንዲህም ብለዋል፦ لَا تَقْتُلُوا ذُرِّيَّةً، وَلَا عَسِيفًا -› «..ልጆችንና ተቀጣሪ ሰራተኛን አትግደሉ!» [አሕመድ - ቁጥር (15992) ፤ አቡ ዳዉድ (2669)] * እንዲሁም ከመልዕክተኛው ህልፈት በኋላ የመጀመሪያው የሙስሊሞች መሪ የሆኑት ታላቁ ኸሊፋ አቡ በክር አስ-ሲድ-ዲቅ በአንድ አጋጣሚ የዚድ ኢብኑ አቢ ሱፍያንን ለዘመቻ ሲልኩት እንደሚከተው እንደመከሩት ተዘግቧል፦ ".. وَإِنِّي مُوصِيكَ بِعَشْرٍ: لَا تَقْتُلَنَّ امْرَأَةً، وَلَا صَبِيًّا، وَلَا كَبِيرًا هَرِمًا، وَلَا تَقْطَعَنَّ شَجَرًا مُثْمِرًا، وَلَا تُخَرِّبَنَّ عَامِرًا، وَلَا تَعْقِرَنَّ شَاةً، وَلَا بَعِيرًا إِلَّا لِمَأْكَلَةٍ، وَلَا تَحْرِقَنَّ نخلا، وَلَا تُغَرِّقَنَّهُ، وَلَا تَغْلُلْ، وَلَا تَجْبُنْ " -› «..አስር ነገሮችን አደራ እልሃለሁ፦ ሴትን፣ ህፃንንም፣ ያረጀ ሽማግሌንም እንዳትገድል፤ የሚያፈራ ዛፍን እንዳትቆርጥ፤ ግንባታዎችን እንዳታፈራርስ፤ በግን፣ ፍየልንና ግመልን በአግባቡ ለመብላት ካልሆነ በቀር እንዳታቆስል፤ የተምር ዘንባባን (አንዳንድ መዛግብት ላይ፦ የንብ ቀፎን..) እንዳታቃጥል፤ በውሃም እንዳታሰምጠው፤ የምርኮ ንብረትንም ሳይከፋፈል እንዳትወስድ፤ እንዳትፈራም!» [አል-ኢማም ማሊክ - በ“አል-ሙወጥ-ጠእ” ቁጥር (1627) ላይ ከየሕያ ኢብን ሰዒድ አስተላልፈውታል፤ የዘገባው ሰነድ የተቋረጠ ቢሆንም በሌሎች ደጋፊ ምክንያቶች ይጠናከራል።]
إظهار الكل...
«የአማሌቅንም ንጉስ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች፥ ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፏቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት። የእግዚአብሔርም ቃል፦ ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገስሁት ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ።..» 2- « እግዚአብሔርም፦ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር፤ አለኝ። ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ። አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን። በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንም ሕፃናቶችንም አጠፋን፤ አንዳችም አላስቀረንም!» [ኦሪት ዘዳግም ምዕ. 2:31-34] 3- «ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም።ነገር ግን ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኵሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት እንዳትሠሩ፥ አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጢያዊውን አሞራዊውንም ከነዓናዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈጽመህ ታጠፋቸዋለህ። » [ኦሪት ዘዳግም ምዕ. 20፡ 16-18] 4- « በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ። » [መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:21] 5- «እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው። እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ ፡‐ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ። እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ፤ ውጡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።» [ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 9:4-7] 6- «የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ታናሽ ወይም ታላቅ፣ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ይገደል ዘንድ ማሉ።» [መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 15:13] 7- «አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ! ስለተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው። ሕፃናቶችሽን ይዞ በአለት ላይ የሚፈጠፍጣቸውየተመሰገነ ነው።» [መዝሙር ዳዊት 137:8-9] 8- «ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና በደልዋን ትሸከማለች፤ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ሕፃኖቻቸውም ይፈጠፈጣሉ፥ እርጕዞቻቸውም ይቀደዳሉ።» [ትንቢተ ሆሴዕ 13:16] 9- « እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ። » [መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7:15] ጥቅሶቹን ያሰፈርኩት አንዳንዶች ቁርኣን አግባብ የሌለው ግድያን እንደሚያነሳሳ ሲሞግቱ እነርሱ የሚያምኑበት “መፅሐፍ ቅዱስ” ደግሞ ከማነሳሳት አልፎ ሙሉ የጅምላ ጭፍጨፋን የሚያፀድቅ እንደሚሆን ለማሳየት ብቻ ነው። -› የስነ ታሪክና ሀይማኖቶች ጥናት ተመራማሪ የሆነው አሜሪካዊው ዝነኛ ፕሮፌሰር ፊሊፕ ጄንኪንስ (Philip Jenkins) እ. ኤ. አ. በ March 8, 2009 “Dark Passages” በሚል አርዕስት ስር ባስነበበው መጣጥፍ ላይ የሚከተለውን ምስክርነት ይሰጣል፦ “..In fact, the Bible overflows with "texts of terror," to borrow a phrase coined by the American theologian Phyllis Trible. The Bible contains far more verses praising or urging bloodshed than does the Koran, and biblical violence is often far more extreme, and marked by more indiscriminate savagery. The Koran often urges believers to fight, yet it also commands that enemies be shown mercy when they surrender. Some frightful portions of the Bible, by contrast, go much further in ordering the total extermination of enemies, of whole families and races - of men, women, and children, and even their livestock, with no quarter granted…” ትርጉሙም፦ «በተጨባጭ መፅሐፍ ቅዱስ - በአሜሪካዊቷ የመንፈሳዊ ጥናቶች ምሁር ፊሊስ ትሪብል የተከሸነ ሀረግን ለመዋስ ያህል- “በሽብር ጥቅሶች” የተጥለቀለቀ ነው! መፅሐፍ ቅዱስ ቁርኣን ከሚያካትታቸው (የግድያ አንቀፆች) እጅጉን የበዙ ደም ማፍሰስን የሚያወድሱ፣ አሊያም የሚያነሳሱ አንቀፆችን ያካተተ ሲሆን መፅሐፍ ቅዱሳዊው ደመኝነት ባብዛኛው እጅግ የከፋ ፅንፈኝነት ያለውና ይበልጡኑ በጅምላ ጭፍጨፋ የሚገለፅ ነው። ቁርኣን በብዙ አጋጣሚዎች አማኞችን ወደ ትግል ይገፋፋል፤ ከመሆኑም ጋር ጠላቶች ሲማረኩ አዘኔታ እንዲቸሩ ያዛል። በአንፃሩ ግን አንዳንድ አስፈሪ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጠላትን፣ ከነሙሉ ቤተሰቦችና ዘሮች፣ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ ከብቶቻቸውን እንኳ ሳይቀር ያለምንም መፈናፈኛ በጅምላ በማጥፋት ረገድ እጅግ ርቀው ይሄዳሉ።..» ሙሉ መጣጥፉን እዚህ ያገኙታል፦ http://www.boston.com/bostonglobe/ideas/articles/2009/03/08/dark_passages/?page=full ፕሮፌሰር ፊሊፕ ጀንኪንስ በ2010 ከ National Public Radio ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ይህን እምነቱን አጽንቷል። በ 2011 ባሳተመው “Laying Down The Sword: Why We Can't Ignore The Bible's Violent Verses” በተሰኘው መጽሀፉ ደግሞ ይህንን ድምዳሜውን በሰፊው አብራርቷል። ይህ ምሁር ክርስቲያን እንጂ ሙስሊም አይደለም። (ስለግለሰቡ ማንነት የሚከተለው የዊኪፒዲያ ሊንክ ላይ ማንበብ ይችላሉ፦ http://en.wikipedia.org/wiki/Philip_Jenkins ) * አንዳንዶች “እነዚህ ያለፉ ታሪካዊ ክስተቶች ናቸው፤ ቁርኣን ላይ ያሉት ግን ለአማኞች የተላለፉ መመሪያዎች ናቸው!” ይሉ ይሆናል። ይህ ሙግት ግን ነገሩን ያብሰዋል፤ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የመፅሐፍ ቅዱስ አንቀፆች ላይ እንደምናስተውለው ጭፍጨፋዎቹ በአምላክ የታዘዙና በነብያት የተፈፀሙ ናቸው! ያልሆኑትም ያለ አንዳች ተቃውሞ ፀድቀዋል፤ ስለዚህ ተፈፃሚነታቸው ገደብ ስለሌለው በቀጥታ በተጨባጩ ዓለም ላይ ተተግብረዋል!
إظهار الكل...
Philip Jenkins

British historian

አል-ኢማም አል-አውዛዒይ ይህን አስመልክቶ የሚከተለውን ብለዋል፦ وَنَهَى أَبُو بَكْرٍ الصِّدِّيقُ [يزيدَ] أَنْ يَقْطَعَ شَجَرًا مُثْمِرًا، أَوْ يُخَرِّبَ عَامِرًا، وَعَمِلَ بِذَلِكَ الْمُسْلِمُونَ بَعْدَهُ -› «አቡ በክር አስ-ሲድ-ዲቅ የሚያፈራ ዛፍን እንዳይቆርጥና መኖሪያ ግንባታን እንዳያፈራርስ [የዚድን] ከልክለዋል፤ ሙስሊሞችም ከርሳቸው በኋላ ይህንን (መመሪያ) ተግብረዋል።» [ሱነኑ’ት-ቲርሚዚይ - አብዋቡ’ስ-ሲየር - ከቁጥር 1552 ቀጥሎ የሰፈረ ነው።] * እንዲሁም ለምርኮኞች ማዘንና በጎ መዋል የጀነት ወራሾች መገለጫ ሆኖ ተወስቷል፦ قَالَ تَعَالَى: {وَيُطْعِمُونَ الطَّعَامَ عَلَى حُبِّهِ مِسْكِينًا وَيَتِيمًا وَأَسِيرًا} {ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ድሃን፣ የቲምንና ምርኮኛን ያበላሉ።} [አል-ኢንሳን 8] ኢብኑ ዐብ-ባስ ይህን አንቀፅ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ كَانَ أُسَرَاؤُهُمْ يَوْمَئِذٍ مُشْرِكِينَ. «የዛኔ ምርኮኞቻቸው አጋሪያን ነበሩ።» [“ተፍሲር ኢብኒ ከሢር” (8/288)] ኢብኑ ከሢር አያይዘው እንዲህ ይላሉ፦ وَيَشْهَدُ لِهَذَا أن رسول الله صلى الله عليه وسلم أَمَرَ أَصْحَابَهُ يَوْمَ بَدْرٍ أَنْ يُكْرِمُوا الْأُسَارَى، فَكَانُوا يُقَدِّمُونَهُمْ عَلَى أَنْفُسِهِمْ عِنْدَ الْغَدَاءِ، «ለዚህ (ትርጓሜ) የሚመሰክረው መልዕክተኛው በበድር ዘመቻ ወቅት ምርኮኞችን እንዲንከባከቡ ሰሓቦቻችውን ማዘዛቸው ነው፤ እነርሱም በምግብ ወቅት ከራሳቸው ያስቀድሟቸው ነበር!» አቡ ዑዘይር ኢብኑ ዑመይር ኢስላምን ሳይቀበል በፊት ስላጋጠመው ተያያዥ ጉዳይ እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦ كُنْتُ فِي الأُسَارَى يَوْمَ بَدْرٍ، فقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم: " اسْتَوْصُوا بِالأُسَارَى خَيْرًا ". وَكُنْتُ فِي نَفَرٍ مِنَ الأَنْصَارِ، وَكَانُوا إِذَا قَدَّمُوا غَدَاءَهُمْ وَعَشَاءَهُمْ أَكَلُوا التَّمْرَ وَأَطْعَمُونِي الْخُبْزَ بِوَصِيَّةِ رَسُولِ اللَّهِ إِيَّاهُمْ. -› «በበድር ጦርነት ከተማረኩት መካከል ነበርኩ፤ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ “ለምርኮኞች መልካም የመዋልን አደራ ጠብቁ!” እኔም ከአንሷር ጭፍራዎች ጋር ነበርኩ፤ ቁርሳቸውንና እራታቸውን ባቀረቡ ጊዜ በመልዕክተኛው አደራ የተነሳ እነርሱ ቴምር በልተው እኔን ዳቦ ያበሉኝ ነበር!» [አጥ-ጦበራኒ በሁለቱ ሙዕጀሞች ዘግበውታል፦ “መጅመዑ’ዝ-ዘዋኢድ” ቁጥር 10007 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም “ሲረቱ ኢብኒ ሂሻም” (1/645) ይመልከቱ።] -› ታዲያ ይህ ሁሉ ገደብና ፍትህ በጦርነት ዘመቻ ላይ ከሆነ ጭራሽ በሰላሙ አለም ደግሞ ወሰን የመተላለፍ ክልከላው እጅግ የበረታና የፀና መሆኑ አያጠራጥርም። አዎን! ይህ ነው የኛ ኢስላም! وَالسَّلَامُ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَى أبو حُنيف إلياس أحمد
إظهار الكل...
ሲያመላክት እንዲህ ይላል፦ كَيْفَ وَإِنْ يَظْهَرُوا عَلَيْكُمْ لَا يَرْقُبُوا فِيكُمْ إِلًّا وَلَا ذِمَّةً -› {በናንተ ላይ ቢያይሉ ስለናንተ አምላክንም (ወይም “ዝምድናንም”) ሆነ ቃልኪዳንን (ወይም “ከለላን”) የማይጠብቁ ሆነው ሳለ እንዴት (ቃልኪዳን ይኖራቸዋል)?} [አት-ተውባህ 8] በአንቀፅ 13 ላይም እንዲህ ይላል፦ ألَا تُقَاتِلُونَ قَوْمًا نَكَثُوا أَيْمَانَهُمْ وَهَمُّوا بِإِخْرَاجِ الرَّسُولِ وَهُمْ بَدَءُوكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ -› {መሃላዎቻቸውን ያፈረሱትንና መልእክተኛውን ለማስወጣት የፈለጉትን ህዝቦች እነርሱ መጀመሪያ ላይ (መዋጋት) የጀመሯችሁ ሆነው ሳለ አትጋደሏቸውምን?..} [አት-ተውባህ 13] የጦር ትንኮሳውን የጀመሩት ከሃዲያኑ ራሳቸው መሆናቸው እንደተወሳ ያስተውሉ! እናም በጥቅሉ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት አንቀፅ ቁጥር 5ን ቆንጥሮ “ቁርኣን ሙስሊም ያልሆነ ሁሉ እንዲገደል ያዛል” ሲሉ መሞገት በጣሊያን ወረራ ጊዜ “ጣሊያኖችን ተዋጉ፤ስታገኟቸውም ግደሏቸው!..» በሚል ቃል የተላለፉ የጦር ትእዛዞችን ኢትዮጵያውያን ጣሊያኖችን ጣሊያናውያን በመሆናቸው ብቻ ሁሌም የሚገድሉ ዘረኞች እንደሆኑ ለመሞገት በማስረጃነት እንደማቅረብ ነው! * ሆኖም በዚሁ ርዕስ ላይ ከላይ ከተብራራው አንቀፅ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ አለ፤ ቁጥር 5 ላይ {ተፀፅተው ከተመለሱ፣ ሰላትንም ካዘወተሩ፣ ዘካትንም ከሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው..} ሲል ኢስላምን ካልተቀበሉ መገደላቸው ብይኑ ከእምነታቸው ጋር እንጂ ቃልኪዳን ከማፍረሳቸው ጋር እንድማይያያዝ አያስገነዝብም ወይ? መልሱም፦ “አያስገነዝብም” ነው! ምክንያቱም ተፀፅተው መመለሳቸውና ኢስላምን መቀበላቸው በበፊቱ ጥፋታቸው የተነሳ የተበየነባቸውን ቅጣት የሚያስምር እድል እንጂ ሌላ አይደለም። ይህንን በምሳሌ እናብራራው፦ አንድ በስርቆት ወንጀል ምክንያት የ5 አመት እስራት የተፈረደበት ግለሰብ ለረጅም ጊዜ ከተጠናወተው የሲጃራና የመጠጥ ሱስ ሙሉ በሙሉ ከተላቀቀ እስራቱ እንደሚሻርለት ቢነገረው እስራቱ የተፈረደበት በሱሰኝነቱ ምክንያት ነው ማለት አይደለም! ከሱሱ መላቀቁ ግን በስርቆቱ ምክንያት የተፈረደበትን ቅጣት ሊያስቀርለት የሚችል አበራታች እድል ነው። በአንቀፁም ላይ አጋሪያኑ ሞት የተፈረደባቸው ቃልኪዳን በማፍረሳቸውና ሙስሊሞችን በመውጋታቸው እንጂ ሙስሊም ባለመሆናቸው ብቻ አይደለም፤ ፍርዱ ቃል ኪዳናቸውን ያከበሩትን አይመለከትምና! ከጥፋታቸው ታቅበው ኢስላምን ከተቀበሉ ግን ቅጣቱን የሚያስምር እድል ያገኛሉ ማለት ነው። ያስተውሉ! ስለሆነም ሙስሊሞች እስከዛሬ ሙስሊም ያልሆነን ሁሉ የመግደል ግዴታ እንዳለባቸው ከአንቀፁ ወይም ከሌሎች የሀይማኖቱ መመሪያዎች ተገንዝበው አያውቁም! ይህ ከዚህ ውጭ ያሉ የቁርኣን ወይም የሐዲሥ ጥቅሶች መሰል ማብራሪያ እንዳላቸው የሚጠቁም ምሳሌ ይሁን። ሸይኹ’ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ እንዲህ ይላሉ፦ وَقَوْلُ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: {أُمِرْت أَنْ أُقَاتِلَ النَّاسَ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ؛ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ} مُرَادُهُ قِتَالُ الْمُحَارِبِينَ الَّذِينَ أَذِنَ اللَّهُ فِي قِتَالِهِمْ، لَمْ يُرِدْ قِتَالَ الْمُعَاهَدِينَ الَّذِينَ أَمَرَ اللَّهُ بِوَفَاءِ عَهْدِهِمْ. - « “ሰዎች ከአላህ በቀር (እውነተኛ) አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ፣ እንዲሁም ሰላትንም እስኪያዘወትሩና ዘካትንም እስኪሰጡ ደረስ እንድጋደላቸው ታዝዣለሁ” በሚለው የነብዩ ንግግር ላይ ፍላጎታቸው እነዚያ ሊጋደሏቸው አላህ የፈቀደ የሆኑት ተዋጊ ጠላቶችን ነው፤ ቃላቸው እንዲሞላ አላህ ያዘዘ የሆኑትን ቃል ኪዳነኞችን ፈልገው አይደለም..» [መጅሙዑ’ል-ፈታዋ (19/20)] * አዎን! ሙስሊሞች የሚከተለውን የአላህ መልዕክተኛ ንግግር ያከብራሉ፦ «مَنْ قَتَلَ مُعَاهَدًا لَمْ يَرحْ رَائِحَةَ الجَنَّةِ، وَإِنَّ رِيحَهَا تُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ أَرْبَعِينَ عَامًا» -› «(የሰላም) ቃል ኪዳን የተገባለትን የገደለ የጀነትን ሽታ እንኳ አያሸትም፤ የርሷ ሽታ የአርባ አመታት የጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል!» [አል-ቡኻሪይ በቁጥር 3166 ከአብዱ’ላህ ኢብኑ ዐምር ዘግበውታል።] ይህ ሙስሊም ያልሆኑ የሰላም ቃልኪዳን ባለቤቶችን መግደልን የሚያወግዝ ቃል ነው። የዘመናችን የኢስላም ሊቃውንት “የቃልኪዳን ባለቤቶች” የሚለው ገለፃ በሙስሊሞች አስተዳደር ስር የሚኖሩ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን፣ ህጋዊ ቪዛ ይዘው ወደ ሙስሊሞች አገራት የገቡትንና ሌሎች ባለ ቃልኪዳኖችን ሁሉ እንደሚያካትት ያስረዳሉ። እንዲያውም በተለያዩ ጥፋቶች የተነሳ ሞት የተገባው ውስን ግለሰብ ቢኖር እንኳ የፍርዱ ተፈፃሚነት በግለሰቦች ወይም በጭፍራዎች እጅ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። አዎን! ኢስላም መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ የህይወት መንገድ በመሆኑ በተለያዩ ጥፋቶች ላይ የራሱን ቅጣቶች ይበይናል። እነዚህ ብይኖች ተግባራዊ የሚሆኑት ግን በመንግስት ደረጃ ነው፤ ይህም ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውና ቅጣቱ እንዳይተገበር የሚያግዱ ምክንያቶች መወገዳቸው በፍርድ ቤት ከተጣራ በኋላ እንጂ በዘፈቀደ አይደለም! ይህ በአለማዊ ህገ-መንግስታት ላይም የፀደቀ ነው፤ አንድ ወንጀለኛ በሌለበት የሞት ፍርድ ቢወሰንበት የተደበቀበትን ቦታ ያወቀ ግለሰብ ምናልባት ለፖሊስ ይጠቁም ይሆናል እንጂ ፍርዱን ለመተግበር ራሱ ቢገድለው እርሱ ራሱ በነፍሰ ገዳይነት እንደሚከሰስ ግልጽ ነው! ጭራሽ ያለተፈረደበትን መግደል ደግሞ የከፋ ነው። እንዲህ አይነቱ ሂደት ስርዓት አልበኝነትን ያወርሳልና! ኢስላም ደግሞ ከሌሎች ይበልጥ ስርዓት አልበኝነትን እንደሚዋጋ ህግጋቱ ሁሉ ይመሰክራሉ! - - - * ታዲያ በኢስላም ከተለያዩ መስፈርቶችና ሂደቶች በኋላ በመንግስት ደረጃ የሚታወጅ ጦርነት ላይ ራሱ ሊከበሩ የሚገቡ የፍትህ ወሰኖች አሉ። ይህንን ከማውሳታችን በፊት ግን ስለ ኢስላም “ደመኝነት” ዘወትር ለሚለፍፉ አንዳንድ ፀሃፊዎች ለንፅፅር ያህል ከብሉይ ኪዳን የሚገኙ አንዳንድ ጥቅሶችን ላስታውስ እወዳለሁ! 1- «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ። አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፣ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፣ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ህጻኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።» [መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15:2-3] የሚደንቀው እንደታዘዙት ህዝቡን ሁሉ ካጠፉ በኋላ ለንጉሱ፣ ለአንዳንድ የቤት እንስሶችና መልካም ንብረቶች በመራራታቸው ትዕዛዙን እንዳልፈፀሙ ተቆጥሮ ከንግስና ተወግደዋል። ከአንቀፅ 8 እስከ 11 እንደሚከተለው ይነበባል፦
إظهار الكل...
* ይህ ነው የኛ ኢስላም! * በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ================= ስለ አንድ ሀይማኖት እውነተኛ ይዘት ለመረዳት ወደ ትክክለኛ መዛግብቱና ምንጮቹ መመለስ አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። ይህ ሲሆን ግን መመሪያዎቹንና አንቀፆቹን በቁንፅል እይታና በጥራዝ ነጠቅ መዘዛ እየገመገሙ ለፍርድ መቻኮል ታላቅ ስህተትን ያወርሳል፤ ለበደልም ያበቃል። የእምነቱን ሁለንተናዊ ይዘትና አስተምህሮት መገንዘብ የሚቻለው አናቅፁን በታትኖ ሳይሆን ሰብስቦ፣ አራርቆም ሳይሆን አቀራርቦ ነውና። በአንድ ቦታ ያልተብራራው በሌላ ቦታ ይብራራል፤ እዚህ ጋር ያልተገደበውም እዚያ ጋር ሊገደብ ወይም መስፈርቱ ሊገለፅ ይችላል። ከዚህም ጋር ቃሉ የተነገረበትን አገባብና አኳያ ማስተዋል የግድ ነው። በጥናት ሂደት ላይም በአሻሚ ገለፃዎች ላይ ከመንጠልጠል ይልቅ ወደ ግልፅ መመሪያዎች መመለስ ይገባል። ይህን መተግበር የአንድ ዘርፍ ምሁራን ከሰርጎ ገቦች ከሚለዩባቸው ነጥቦች አንዱ ነው። ይህን እንደመግቢያ ከተረዳን ዘንድ ወደ አንድ ሁነኛ ምሳሌ እንሸጋገር፦ ሙስሊሞች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በሚኗኗሩበት ሂደት ሊከተሉት ስለሚገባቸው አጠቃላይ ስርዓት ኢስላም ያሰፈረውን ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው በጦረኛ ጠላቶች ላይ ውጊያ በታወጀባቸው አንቀፆች በኩል አይደለም። እነዚህ በውስን የጦርነት ሂደት ላይ ብቻ ሊተገበሩ የሚችሉና በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች የተከበቡ ህግጋት እንጂ የሁልጊዜ ደንቦች አይደሉም። -› ይህንን ከሚያብራሩት አንቀፆች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦ لَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ أَنْ تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ * إِنَّمَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قَاتَلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ وَظَاهَرُوا عَلَى إِخْرَاجِكُمْ أَنْ تَوَلَّوْهُمْ = {ለእነዚያ በሀይማኖታችሁ ላልተጋደሏችሁና ከአገራችሁ ላላስወጧችሁ በጎ ብታደርጉና ፍትህን ብትውሉ አላህ አይከለክላችሁም፤ አላህ ፍትኸኞችን ይወዳልና። አላህ የሚከለክላችሁ እነዚያ በሀይማኖታችሁ (የተነሳ) የተጋደሏችሁንና ከአገራችሁ ያስወጧችሁን እናንተን በማስወጣትም ላይ ያገዙትን እንዳትወዳጇቸው ነው።} [አል-ሙምተሒነህ 60 ፡ 8-9] ይህ ሌሎችን ሙስሊም ስላልሆኑ ብቻ መግደል እንደማይቻል ያሳያል፤ በየትኛውም የታሪክ ማህደር ሙስሊሞች ሌሎችን ኢስላምን ስላልተቀበሉ ብቻ ገድለው አያውቁም። በኢስላማዊ አስተዳደር ውስጥ ለምዕተ አመታት የኖሩት ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ተገድደው ኢስላምን እንዳልተቀበሉ ተጨባጩ አለም ይመሰክራል። ይህም ማለት የግዛቱ መተዳደሪያ ህግ ቁርኣናዊ ሆኖ ሳለ መብታቸው በጥቅሉ ተጠብቆ ነበር ማለት ነው። አደራ! እንደነ isis ያሉትን ቡድኖች እዚህ ርዕስ ላይ ማስገባት ራሱ ስህተት ነው! እነርሱ ከማንም ይልቅ የገደሉት ሙስሊሞችን ነውና! በዚህ ላይ ደግሞ ስለማንነታቸው የምንለው፦ ውስጡን ውስጠ-አዋቂ ይወቀው፤ ነው! በዚህ ላይ ክርስትናን ጨምሮ በተለያዩ እምነቶች ውስጥ ያለአግባብ የተሰገሰጉ የጥፋትና የሽብር ቡድኖች ሁሌም ነበሩ፤ አሉም። * ይህ እውነታው ሆኖ ሳለ ጥቂት ግለሰቦች በኢስላም ስም ለሚፈፀም የደም መፍሰስ ሁሉ ክቡሩን ቁርኣን ተጠያቂ ያደርጋሉ፤ ወይም ሀማኖቱን ራሱ ይኮንናሉ። ይህንን የሚያናፍሱት አብዛኛዎቹ ሙግተኞች መረጃዎችን ከላይ በጠቆምነው መልኩ ለማገናዘብ ብቃቱ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱም የላቸውም! በዚህ ረገድ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሚመዟቸው አንቀፆች መካከል ዋነኛው በሱረቱ’-ት-ተውባህ (9ኛው ምዕራፍ) ቁጥር 5 ላይ የሚገኘው አንቀፅ ነው፤ እንደሚከተለው ይነበባል፦ فإذَا انسَلَخَ الْأَشْهُرُ الْحُرُمُ فَاقْتُلُوا الْمُشْرِكِينَ حَيْثُ وَجَدتُّمُوهُمْ وَخُذُوهُمْ وَاحْصُرُوهُمْ وَاقْعُدُوا لَهُمْ كُلَّ مَرْصَدٍ ۚ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَخَلُّوا سَبِيلَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّـهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ -› {የተከበሩት ወራት ባበቁ ጊዜ አጋሪዎቹን ባገኛችኋቸው ቦታ ግደሏቸው፤ ያዟቸውም፤ ክበቧቸውም፤ በመጠባበቂያ ስፍራዎች ሁሉ ተቀመጡላቸው፤ ተፀፅተው ከተመለሱ፣ ሰላትንም ካዘወተሩ፣ ዘካትንም ከሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፤ አላህ እጅግ መሃሪ፣ አዛኝ ነውና!} [አት-ተውባህ 5] ብዙዎች ይህን አንቀጽ ኢስላም ተከታዮቹን በሌሎች ላይ እንደሚያነሳሳና ፅንፈኝነትንም እንደሚሰብክ ለመሞገት ይጠቅሱታል። ይህ እሳቤ ስህተት መሆኑ እንደሚከተለው ባጭሩ ይብራራል፦ አንቀፁ በውስን ታሪካዊ ሂደት መሃል የሚገጥም እንጂ የሁልጊዜ መርሆን የሚያስተላልፍ አይደለም። በስምንተኛው አመተ-ሂጅራ የአላህ ነብይ የተሰደዱበትን የትውልድ አገራቸውን መካ መልሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ እዚያ የነበሩ ከፊል ጣኦት አምላኪያንን አስመልክቶ የተላለፈ መመሪያ ነው። የመካ ጣኦት አምላኪያን ሁለት አይነት ነበሩ፤ ከፊሎቹ ከመልእክተኛው ጋር የፈፀሙትን የሰላም ስምምነት ጠብቀው ያቆዩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ቃልኪዳናቸውን አፍርሰው ሙስሊሞችንና ሌሎች በስምምነቱ ላይ የተሳተፉ ወገኖችን የተዋጉ ነበሩ። ቃልኪዳናቸውን ያከበሩትን አስመልክቶ በዚያው ምእራፍ ላይ የሰላም ስምምነቱ እንዲጠበቅላቸው በአፅኖት ያዛል፦ ከላይ ከጠቀስነው አንቀፅ በፊት ባለው አንቀፅ (በቁጥር 4) ላይ እንዲህ ይላል፦ إِلَّا الَّذِينَ عَاهَدْتُمْ مِنَ الْمُشْرِكِينَ ثُمَّ لَمْ يَنْقُصُوكُمْ شَيْئًا وَلَمْ يُظَاهِرُوا عَلَيْكُمْ أَحَدًا فَأَتِمُّوا إِلَيْهِمْ عَهْدَهُمْ إِلَى مُدَّتِهِمْ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ -› {ከአጋሪዎቹ ቃል የተጋባችኋቸውና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ፣ በናንተም ላይ አንድንም ያላገዙ ከሆኑት በስተቀር፤ ቃል ኪዳናቸውን እስከጊዜያቸው (መጨረሻ) ድረስ ሙሉላቸው፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።} [አት-ተውባህ 4] በአንቀፅ 7 ላይም እንዲህ ይላል፦ فَمَا اسْتَقَامُوا لَكُمْ فَاسْتَقِيمُوا لَهُمْ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ -› {..(በቃል ኪዳናቸው) እስከፀኑ ድረስ ፅኑላቸው፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።} [አት-ተውባህ 7] ሆኖም ቃል ኪዳናቸውን ያፈረሱትን በተመለከተ ግን የተከበሩት ወራት ሲገባደዱ ጦርነት ታወጀባቸው፤ ይህም የሆነው እንዲሁ ጣኦት አምላኪያን ስለነበሩ ብቻ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፤ ቃላቸውን የጠበቁት ጣኦታውያን ላይ ጦር አልተመዘዝምና! ነገር ግን ከዚያ በፊት በመካ ሙስሊሞችን ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ ሲያሰቃዩ፣ ሲዘርፉና ሲገድሉ የነበሩ፣ መልዕክተኛውንና ባልደረቦቻቸውን ከትውልድ አገራቸው ያፈናቀሉ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ነብዩን ለመግደል የሞከሩ፣ ሙስሊሞች ወደ ተሰደዱበት አገር ድረስ በተደጋጋሚ ጦር ሰብቀው በመዝመት ሊያጠፏቸው የጣሩ፣ ቃል ኪዳናቸውንም ያፈረሱና ለማፍረስም ወደኋላ የማይሉ ከዳተኞች ነበሩ። ይህንን እውነታ አንቀፅ ቁጥር 8 ላይ
إظهار الكل...
00:24
Video unavailableShow in Telegram
ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች! = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
500 ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ ======================= ሊቀንሱን ሲሞክሩ እንበዛለን ማለት እንዲህ ነው። የእስልምናን ጉዞ ለመግታት መሞከር የጸሐይን ጮራ በእጅ ለመሸፈን እንደመሞከር ነው። በአላህ ፈቃድ ዛሬ እሁድ ግንቦት 27/2015 ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ በተደረገ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞ 500 ሰዎች፤ ነሲሓ ቲቪ ላይ በጥዑም ዳዕዋዎቹ በምናውቀው በተወዳጁ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ እጅ ኢስላምን ተቀብለዋል። አላህ ፅናትና ጥንካሬን እንዲለግሳቸው እንለምነዋለን። አል- ሐምዱሊላህ! አላሁ አክበር። በተለይ በዚህ የሃገራችን ክፍል ዳዕዋ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
إظهار الكل...
ያሳዝናል፤ ያሳፍራል‼ =============== ✍ "ጀግኖቹ" የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች፤ በተመረጡ ህንፃዎች ላይ ስናይፐር ካጠመዱ በኋላ በአንዋር መስጅድ የነበሩ ሰጋጆች ሃገር ሰላም ብለው ሲወጡ ረፈረፏቸው። የሱንና ሶላት ጀምሮ ያልጨረሰ አለ፣ ከፈርዱ ሶላት ረከዓህ አምልጦት ለማሟላት የቆመ አለ፣ በጣም ያረፈደና የሚመጣም አለ፣ …ሆኖም ግን ቀድመው አስበውበት፣ ለቀናት ተመካክረውበትና ተዘጋጅተውበት የመጡበት ጉዳይ ስለነበር ደቂቃዎችን እንኳ መታገስ ሳይችሉ ካኪና ሙሶላ የያዞ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ የጥይት እሩምታ አርከፈከፉባቸው። እንደተዘጋጁበት ብናውቅም፤ በተደጋጋሚ ህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ የለም ስላልነው ካልተቃወመ ምንም አያደርጉትም ብለን አስበን እንጂ፤ ቢቃወምም ባይቃወምም እንደሚገድሉት ብናውቅ ኖሮ አንዋር መስጅድ አትሂዱ እንላቸው ነበር። || t.me/MuradTadesse
إظهار الكل...
የፖሊስ ሀይሎች በታቀደ እና በተጠና መልኩ ሆን ተብሎ ዝግጅት ተደርጎበት በንጽኋን ላይ ፍጅት ፈጽመዋል ማስረጃውን እነሆ :- ================================= በትላትናው ዕለት በአንዋር መስጅድ ንጽኋን ላይ ሆን ተብሎ በታቀደ መልኩ የተፈጸመው የሽብር ተግባር መጀመሪያውኑ ታቅዶበት ፣በቂ ዝግጅት ተደርጎበት የተፈጸመ ተግባር ነው ። ይህንን ተግባር ለመፈጸም በመጀመሪያ ደረጃ አልሞ ተኳሾች የሚቆሙባቸው ህንጻዎች በእለተ ጁምዓ የታቀደው የሽብር ተግባር እስኪፈጸም ድረስ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው ። ለአብነት ያህል ተወከል ህንጻ አክሲዮን ማህበር እና ድር ተራ አክሲዮን ማህበራት በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ዝግ እንደ ሚሆኑ አስታወቁ ። የህንጻዎቹን አናት በመጠቀም ለታሰበው የሽብር ተግባር ዝግጁ ሆኑ ማለት ነው ። ይህንን የሽብር ተግባር ዝግጅት የተረዳው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምንም አይነት ተቃውሞ የማይደረግ መሆኑ ተገለጸ ። ነገር ግን የሽብር ተግባሩ ከመጀመሪያው የታቀደበት ነበር እና በንጽኋን ላይ የፍጅት ተግባር ተፈጸመ ። እውነታው ይኼው ነው መታወቅ ያለበት ነገር ግን በንደዚህ አይነት የሽብር ተግባር ፈጽሞ ሀገር ማረጋጋት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ። (አብዱረሂም አህመድ)
إظهار الكل...
ሁላችንም በያለንበት በዱዓ በኢስትግፋር እንበርታ
إظهار الكل...