የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
إظهار المزيد2 755
المشتركون
-124 ساعات
+57 أيام
+4130 أيام
أرشيف المشاركات
ተቀጸል ጽጌ/አጼ- መስቀል/
'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል። በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው። በወቅቱ ንጉሡ፣ ሠራዊቱ፣ ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር ያድኅነነ እምጸር።" "መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል።" እያለ ይዘምር ነበር።
የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር። ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል።
''በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ'' ሮሜ 12፥2
በመ/ር ዲ/ን ዳንኤል ታደለ
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ሊቀ ነቢያት ሙሴ
መስከረም ስምንት በዚህች ቀን የእግዚአብሔር ሰው የሆነ የዋህ ቅን ጻድቅ የነቢያት አለቃ የሙሴ ዕረፍቱ ነው። ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው።
ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም። እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና። በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው።
አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊውም ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው። በማግሥቱ ደግሞ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ። አንዱ ዐመፀኛም ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን አለው።
ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቍጥቋጦ ውስጥም እሳት እየነደደ ራእይን አየ። አይቶ ሊረዳ በቀረብ ጊዜ ጳጦስ በተባለ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገረው። ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲአወጣቸው አዘዘው።
ከዚህን በኋላ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ በግብጻውያን ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን አመጣ። መጀመሪያው የወንዙን ውኃ ደም ማድረግ የመጨረሻው የግብጻውያንን የበኵር ልጅ መግደል ነው።
ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርዖንና በሠራዊት ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው።
ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር።
እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስለርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል። እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላልክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርዘኝ አለው።
ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ ሸፈነ ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሀን ፊቱ በራ።
መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንደጠበቃቸው እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን ለኢያሱ አስረክብ ብሎ አዘዘው።
ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝቡንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስትም እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠለት። ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በተራራ ውስጥ አረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ። የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ።
በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጥላችው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ይሁዳ በጻፈው መጽሐፉ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው የእስራኤል ልጆችም አርባ ቀን አለቀሱለት።
የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ረድኤት አይለየን።
+8
በዛሬው ዕለት መስከረም 04/2018 ዓ.ም የተጠራው የሰንበት ትምህርት ቤታችን የጠቅላላ ጉባኤ ተከናወነ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+8
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሰዎ መርሐ ግብር ተከናወነ።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የምሥራቅ ደቡብ ትግራይ እና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ልዩ ልዩ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ እና ሰንበት ተማሪዎች ተገኝተዋል።
© Eotc
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼 ✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼 ✨🌼✨🌼
"ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ" (መዝ ፷፬ ፥ ፲፩)
እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ!!
በጊዜ ሥጦታ ቀናት ተፈጥራዊ ዑደትን ተከትለውና ወራትን ተክተው ዘመንን ይፈጥራሉ፤ የዘመናት ለውጥም አዲስ ዓመትን ይተካሉ፤ ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ሆነ፤ እኛም ለአዲሱ ዓመት ዘመነ ማርቆስ እንደ ቸርነቱ ደረስን፡፡
በዝናብ አብቅሎ፣ በፀሐይ አብስሎ ፍጥረቱን የሚመግብ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ልናቅድ ይገባናል፤ ለምድራዊ ኑሯችን የምንተገብራቸውን እንደምናቅደው ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችንም ልናስብ ይገባል፤ የዘመናት ጌታ ብርሃንና ጨለማን፣ በጋና ክረምትን የሚያፈራርቅ ዘመንን፣ በዘመን የሚተካ የሠራዊት ጌታ የእስራኤል ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ዘመነ ማቴዎስን _አሻግሮ ለዘመነ ማርቆስ አድርሶናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን! ዝናመ ምሕረቱን፣ ጠለ በረከቱን ለምድር ለግሶ፣ አለስልሶ ባዶነቷን በሰብል፣ በልምላሜ፣ በጽጌአት ውበት አስጊጦ፣ እክለ በረከቱን ለእኛ የሚያድል ፈጣሪ ዘመኑን የፍቅር፣ የሰላም፣ የምሕረት ዘመን ያድርግልን! የተሰጠንን ዘመን መልካም ልንሠራበት ይገባል! በስንፍና ያሳለፍነው ጊዜ ይብቃን! በአዲስ ዘመን በአዲስ ዕቅድ፣ በአዲስ መንፈስ ለሥራ እንነሣ! ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ እንዲህ ይለናልና ‹‹የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም፣ በስካርም፣ በዘፈንም፣ ያለ ልክም በመጠጣት፣ ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና፡፡››
የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤታችን በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ እያለ፤ አዲሱ ዓመት መልካም ሥራ የምንሰራበት፣ በኀጢአት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ ታጥቦ ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ የምንበቃበት፣ በመልካም ተግባር የሚታደስበት እና ለስጋ ብቻ ሳይሆን ለነፍሳችንም የምንሰራበት እንዲሆን እንዲሁም አዲሱ ዓመት በሃይማኖት የምንፀናበት፣ በፍቅርና በመረዳዳት የምንኖርበት፣አንድነታችን የሚጠነክርበት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የምትሆንበት እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን፡፡
የዘመናት ጌታ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን!!!
መልካም አዲስ ዓመት!!
2018 ዓ.ም
የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
