ar
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

الذهاب إلى القناة على Telegram

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 454 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 042 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 328 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 454 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 550، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 26، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 37.47‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.23‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 412 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 477 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

وصف القناة غير متوفر.

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

14 454
المشتركون
+2624 ساعات
+1347 أيام
+55030 أيام
أرشيف المشاركات
"በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።" 2ጢሞ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube
"በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።" 2ጢሞ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!  "ልጅን በሚኼድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከርሱ ፈቀቅ አይልም።" {ምሳሌ 22፥6}     በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ በ2015 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን  ተከታትለው  ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ  #የ4ኛ , #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል #ከ4500 በላይ ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር !!! #ጥቅምት_4_2016_ዓ_ም  #ከቀኑ_7_00_ሰዓት_ጀምሮ  #በደብረ_ምጥማቅ_ሰዓሊተ_ምህረት_ቅድስት_ማርያም_እና_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_ካቴድራል        #በዕለቱ_የሚኖሩ_ሌሎች_መርሐግብሮች 👇 👉 በ2015 ዓ.ም በክረምት መርሐግብር  በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የተማሩ የተተኪ መምህራን ምርቃት ፤ 👉  በተጨማሪም የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች ተሰናድተዋል። #በመርሐግብሩ_ላይ 👇 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት  የየክፍሉ ኃላፊዎች ፤ የደብራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ባለስልጣኖች ፤ የየሰንበት  ት/ቤቱ አባላቶች እንዲሁም ምዕመናን/ት ይገኛሉ። እርስዎም በዚህ ልዩ መርሐግብር ላይ ጥቅምት 4/2016 ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል ተገኝተው የመርሐግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!!  #ኑ_ተማሪዎቻችን_በጋራ_እንመርቅ!!!           #የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔

የተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር በ2016ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀውንና በሁሉም አህጉረ ስብከት በትግበራ ላይ ባለው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በ2015 ዓ.ም የ12ኛ
የተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር በ2016ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀውንና በሁሉም አህጉረ ስብከት በትግበራ ላይ ባለው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ጥቅምት 3 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ  በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል። እርሶም በእለቱ ተገኝተው የጉባኤው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት ሁሉ አቀፍ ትሥሥርን በሚመለከት ከሊቃውንት፣ ከባለሙያዎች፣ ከሰ/ት/ቤት መ/ራን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ። መስከረም 27/01/2015 ዓ.ም (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጀውን  ሥርዓተ ትምህርት አስመልክቶ  አንጋፋ መምህራን ፣ የሥርዓተ ትምህርት ባለሞያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ምክክር በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተካሂዷል። በምክክሩ ላይም የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አባላት ፣ የማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሳኤ ፣ የሊቃውንት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለ ፣  ከአንጋፋ የሰንበት ት/ቤት አገልጋይ መምህራን መካከል መልአከ ሰላም መምህር ታዬ አብርሃም ፣ መምህር ያረጋል አበጋዝን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው መምህራንና የሥርዓተ ትምህርት ባለሞያዎች ተገኝተዋል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ምክትል ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ ምስጋና ሥርዓተ ትምህቱን በሚመለከት ገለጻ ካደረጉ በኋላ ሥርዓተ ትምህርቱ ከሁሉም የቤተ ክርስቲያን የትምህርት ተቋማት ጋር የሚኖረውን መስተጋብር መነሻ አቅርበዋል። በመቀጠልም ሁለተኛውን የመነሻ ሐሳብ ከመደበኛ የአስኳላ ትምህርት አንጻር ሥርዓተ ትምህርቱ ሊያያቸው የሚገባውን ሐሳቦች ፣ ጥሩ እድሎችና ተግዳሮቶች በዶ/ር ወርቁ ቀርቧል። በ2016 የሙከራ ትግበራ የሚጀምረው የቅድመ መደበኛ (ዕድሜያቸው ከአራት እስከ ስድስት) ላሉ ሕፃናት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ዲ.ን ሚኪያስ ግዛቸው በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሥርዓተ ትምህርት ፕሮጀክት አስተባባሪ ገለጻ አድርገዋል። ለምክክሩ የተዘጋጀውን ሦስተኛ መነሻ ሐሳብ ሥርዓተ ትምህርቱ ከተጓዳኝ ወቅታዊ ጉዳዮችና ክስተቶች አንጻር እንዴት ሊቃኝ እንደሚገባ በቀሲስ ሱራፌል ቀርቧል። የቀረቡትን መነሻ መሠረት በማድረግም ተሳታፊዎች ያላቸውን ሐሳብንና ልምዶች በሰፊው አጋርተዋል። በመጨረሻም ተተኪውን ትውልድ ለማፍራት ዘመኑን የዋጀ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የተሟላ ሁሉ አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሥርዓተ ትምህርት ከቅድመ መደበኛ ሕፃናት ፬ ዓመት ራሱን የቻለ ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት ፣ ዝግጅት ላይ ያለውን ከ፩ኛ ፲፪ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርት ማጠናቀቅ እና ከ፲፪ኛ ክፍል በኋላ ወደ ቀጣይ ተቋማት የትምህርትና የአገልግሎት ስምሪት አጠቃላይ ማኅቀፍ ላይ ከሊቃውንት፣ ባለሙያዎች፣ ሰ/ት/ቤት መ/ራንና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክርና በየዘርፉ ጥናት እየተጠና  በተደራጀ መልኩ ዝግጅትና ትግበራው ላይ በስፋት እንደሚሳተፉ በመግለጽ ቀጣይ መርሐ ግብሮች ተይዘው ምክክሩ ተፈጽሟል። ( የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

እንኳን ለዘመነ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ! ( የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www
እንኳን ለዘመነ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ! ( የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ  በሻሸመኔ ከተማ ሥልጠና ተሰጠ። መስከረም 24/01/2016 ዓ.ም (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ዙሪያ ከሚገኙ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ አባላት ሥልጠና ተሰጠ። በሻሸመኔ ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሕብረት አዘጋጅነት የሥርዓተ ትምህርት አስፈላጊነት እና የሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ዙርያ ሰፊ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ሥልጠናውን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ. ም ያዘጋጀውን የክረምት የአሠልጣኞች ሥልጠናን  በተሳተፉ መምህራን አማካኝነት  ✝️  በዲ/ን ሳሙኤል  (ሠምረ) ✝️በመ/ር ረድኤት  ተክሉ መስከረም 20 እሁድ ከጠዋቱ  3:30 እስከ 7:30 ተሰጥቷል። በነበረው የሥልጠና ሰዓት ሰንበት ትምህርት ቤቶች እስካሁን ያለፍንበትን ያልተቀናጀ እና ወጥነት የጎደለው የሥርዓተ ትምህርት ጊዜ በመገምገም በሚቀጥለው ለምንተገብረው የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ባዘጋጀውና በሁሉም ሀገረ ስብከቶች እየተተገበረ ባለው ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ በሀገረ ስብከቱ እንዴትና በምን አይነት መልኩ መተግበር እንዳለበት ሰፊ ውይይት በማድረግ የ2016ዓ.ም የትግበራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል። ( የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

photo_2023-10-04_21-34-44.jpg1.19 KB

photo_2023-10-04_21-34-08.jpg1.40 KB

photo_2023-10-04_21-34-04.jpg1.66 KB