ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

GONDAR POLYTECHNIC COLLEGE / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ /

GONDAR POLYTECHNIC COLLEGE / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ /

الذهاب إلى القناة على Telegram

Education & Training £ Technology & Extension Service/

إظهار المزيد
1 403
المشتركون
+224 ساعات
+67 أيام
+6130 أيام
أرشيف المشاركات
ደሴ አራጋው አካውንቱ ከቁጥጥር ውጭ ስለሆነ በእሱ የሚላኩ መረጃወች የራሱ አለመሆናቸው እውቅናው ኖሯችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ።

ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝተው የኮሌጁን የስልጠና መስጫ ወርክሾፖች ጎበኙ። የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊዎች እና የአብክመ ፕሬዚዳንት የደሊቨሪ ዩኒት አማካሪ
+6
ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝተው የኮሌጁን የስልጠና መስጫ ወርክሾፖች ጎበኙ። የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊዎች እና የአብክመ ፕሬዚዳንት የደሊቨሪ ዩኒት አማካሪ እንዲሁም የጎንደር ከተማ አመራሮች በኮሌጁ ተገኝተው የአውቶሞቲቭ ፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እና እንዲሁም የዲጅታል አድሬሲንግ ፕሌት ፕሮዳክሽን ዘመናዊ ስማርት ሲቲ የቤት ቁጥር ስራን እና የማስታዋቂያ ስራዎችን ማምረቻ ወርክ ሾፕ ጎብኝት አካሄዱ።

የኮሌጆችን ሴፍቲኔት የተመደባችሁ አሰልጣኞች በሙሉ => ወርሃዊ ሪፖርት የመጨረሻውን የመላከያ ቀን እንዳይረሳ ? ዛሬ በደረሰኝ መረጃ መሠረት ሪፖርት የላኩ => እሸት ብርሃኔ ፋሲካው አብዶም ታደለ መልካም እና አድኖ ካሳ እስከ 11;00 ሰአት 2019 ሪፖርት ያላኩ ናቸው => ሪፖርቱን ያላካችሁ አሠልጣኞች እና ኢንስትራክተሮች ሀላፊነት የምትወስዱ መሆኑን በጥብቅ አሳስባለሁ !

የቴክኖሎጂ_ሽግግር_የደረጃ_ዕድገት_መስፈረት_የገምጋሚና_አጽዳቂኮሚቴ_አጽዳቂ.pdf18.76 MB

አዲሱ የቴክኖሎጅ አፅዳቂ ኮሚቴ ሁሉም ሊያነበዉ የሚገባ ሰነድ

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አራተኛውን ዙር የ«ብቃት» የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከጎንደር ከተማ ስራና ስልጠና መምሪያ ጋር በመቀናጀት ለ247
+9
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አራተኛውን ዙር የ«ብቃት» የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከጎንደር ከተማ ስራና ስልጠና መምሪያ ጋር በመቀናጀት ለ2471 ለሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶች የ«ብቃት» የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል። በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት መምሪያ መ/ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉ ደሳለኝ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ለበርካታ ወጣቶች ተጠቃሚነት መረጋገጥ ዋነኛ አነሳሽ ሞተር የሆነ ትልቅ የለውጥ ፕሮጀክት ሲሆን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችም በአመለካከት ተቀይረው እና በክህሎት ታንጸው የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተገንዝበን ሰልጣኞች በቆይታቸው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የሚጠበቀውን እውቀትና  ክህሎት ይዘው እንዲወጡ ትኩረት ሰጠን ልንሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ም/ዲን የሆኑት አቶ አደራጀው ወልዴ በበኩላቸው ኮሌጃችን በብቃት" ወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ተግባራዊ በማድረግ ከዚህ ቀደም  በተለያዩ ዙሮች  ወጣቶች ተገቢውን የአመለካከት ፣የህይወት ክህሎት እና የስራ ፈጠራ እና ደንበኛ አያያዝ ስልጠናን መስጠት እንደቻልን ገልፀው፤   አሁንም ይህ ስልጠና በተገቢው መንገድ ለወጣቶች መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ሰላም የብቃት ለወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት አሰልጣኝ መምህራን ነገ ለስልጠና ስትመጡ አለባበስና የደረት ባጅ መያዛችሁን እንዳትረሱ። ሰላም አዳር

ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እና 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በ1ኛ ሩብ አመት
+9
ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እና 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ከኮሌጁ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል ። በመድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተገኙት የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮነን ኮሌጃችን ባለፈው በጀት አመት በእቅድ ከያዝናቸው ተግባሮቻችን መካከል መፈፀም የቻልነው እና ውጤታማ የሆንባቸው ስራዎች ሰፊው ሽፋን የሚይዙ ይሁን እንጂ በቀጣይ ትኩረትን የሚሹ እና የተሻለ አፈፃፀም ልናስመዘግባቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ ጠቁመዋል። የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተቀናጀ አሠራር፣ ተሳትፎና በቁርጠኝነት ወደ ተግባር በመቀየር የኮሌጁን የሥራ አፈጻጸም የበለጠ ለማሻሻል የሁሉም ሠራተኞች የጋራ ርብርብ ወሳኝ እንደሆነ አሳስበዋል። የኮሌጁ አጠቃላይ የ2019 በጀት ዓመት አመት እቅድ እና 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም በኮሌጁ ም/ዲን አቶ አደራጀው ወልዱ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧቸው መድረኩም በስኬት ተጠናቋል።

ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እና 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ከኮሌጁ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል ። በመድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተገኙት የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮነን ኮሌጃችን ባለፈው በጀት አመት በእቅድ ከያዝናቸው ተግባሮቻችን መካከል መፈፀም የቻልነው እና ውጤታማ የሆንባቸው ስራዎች ሰፊው ሽፋን የሚይዙ ይሁን እንጂ በቀጣይ ትኩረትን የሚሹ እና የተሻለ አፈፃፀም ልናስመዘግባቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ ጠቁመዋል። የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተቀናጀ አሠራር፣ ተሳትፎና በቁርጠኝነት ወደ ተግባር በመቀየር የኮሌጁን የሥራ አፈጻጸም የበለጠ ለማሻሻል የሁሉም ሠራተኞች የጋራ ርብርብ ወሳኝ እንደሆነ አሳስበዋል። የኮሌጁ አጠቃላይ የ2019 በጀት ዓመት አመት እቅድ እና 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም በኮሌጁ ም/ዲን አቶ አደራጀው ወልዱ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧቸው መድረኩም በስኬት ተጠናቋል።

ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እና 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም መድረክ አከናወነ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በ1ኛ ሩብ አመት
+7
ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ  እና 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም መድረክ አከናወነ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ከኮሌጁ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር የምክክር መድረክ አከናውኗል። በመድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተገኙት የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ተስፋሁን መኮነን መድረኩን ሲያስጀምሩ ኮሌጃችን ባለፈው በጀት አመት በእቅድ ከያዝናቸው ተግባሮቻችን መካከል መፈፀም የቻልነው እና ውጤታማ  የሆንባቸው ስራዎች ሰፊው ሽፋን የሚይዙ ይሁን እንጂ በቀጣይ ትኩረትን የሚሹ እና የተሻለ አፈፃፀም ልናስመዘግባቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ ጠቁመዋል።  አያይዘውም የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በተቀናጀ አሠራር፣ ተሳትፎና በቁርጠኝነት ወደ ተግባር በመቀየር የኮሌጁን የሥራ አፈጻጸም የበለጠ ለማሻሻል የሁሉም ሠራተኞች የጋራ ርብርብ ወሳኝ እንደሆነ አሳስበዋል። በመድረኩም የኮሌጁ አጠቃላይ የ2019 በጀት ዓመት አመት እቅድ እና 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም በኮሌጁ ም/ዲን በሆኑት አቶ አደራጀው ወልዱ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧቸው መድረኩም በስኬት ተጠናቋል።

Post this link https://forms.gle/q9CQw9zsyy46cFvT8 to a telegram pages, promote ...

Register For Digital Amhara Training

የብቃት የወጣቶች ፕሮጀክት የመምህራን ምደባ ስለማሳወቅ => ከዚህ በላይ ስማችሁ የተዘረዘረ የኮሌጆችን ኢንስትራክተሮች የህይወት ክህሎት ስልጠና ለመስጠት የተመደባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ስልጠናው በ1
+3
የብቃት የወጣቶች ፕሮጀክት የመምህራን ምደባ ስለማሳወቅ => ከዚህ በላይ ስማችሁ የተዘረዘረ የኮሌጆችን ኢንስትራክተሮች የህይወት ክህሎት ስልጠና ለመስጠት የተመደባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ስልጠናው በ1 ዙር የሚጠናቀቅ ስለሆነ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎችን የኮሌጁ ትምህርትና ስልጣና ቢሮ በመገኘት እንድትወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን ። ኮሌጁ !

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራና ተግባር ትምህርት ስልጠናን በትብብር ለማካሄድ ከጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። "በትብብር እውቀትንና ክህሎትን ያጣመሩ መምህራን
+8
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራና ተግባር  ትምህርት ስልጠናን በትብብር ለማካሄድ ከጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። "በትብብር እውቀትንና ክህሎትን ያጣመሩ መምህራንን እናፈራለን" በሚል መሪ ቃል የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራና ክህሎት (የስራና ተግባር)  ትምህርት እጩ መምህራንን በዲግሪ ደረጃ በትብብር  ለማሰልጠን ከጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። የጎንደር  መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ሻንበል ፀሃይ የመግባቢያ ሰነዱ ዋነኛ አላማ የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅና የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀብታቸውንና ልምዳቸውን በማቀናጀትና በትብብር  በመስራት በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስርዓተ ትምህርት ውስጥ የተካተተውን የስራና ክህሎት (የስራና ተግባር)  ትምህርት በብቃት የሚያስተምሩ ሁለገብ እጩ መምህራንን በዲግሪ ደረጃ አሰልጥነው በማስመረቅ ወደስራ ማሰማራት ነው ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ተስፋሁን መኮነን በበኩላቸው በሀገራችን እየተተገበረ በሚገኘው አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ የሙያ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ በትምህርት ቤቶች መሰጠት እንዳለበት በግልፅ ተቀምጧል። ለዚህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚኖራቸው ድርሻ ከፍ ያለ ነው። ስለሆነም ኮሌጃችን ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር በቅንጅት የስራና ክህሎት (ስራና ተግባር)  ትምህርት እጩ መምህራንን በዲግሪ ደረጃ በማሰልጠን እውቀት፣ ክህሎትና ሙያዊ ስነምግባር የተላበሰ ዜጋን በማፍራት በኩል ዝግጁ ነን ብለዋል። አያይዘውም  ከዚህ ቀደም የነበረነን መልካም  የሆነ የሁለትዮሽ ግንኙነት በዛሬው እለት የተፈራረምነው የመግባቢያ ሰነድ ውጤታማ እና የታለመለትን ግብ መሳካት ትልቅ ጉልበት ይሰጠናል ብለዋል።

የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል። እርስዎም የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት በኮሌጁ ዋናው ግቢ በመገኘት መመዝገብ
የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል። እርስዎም የምዝገባ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት በኮሌጁ ዋናው ግቢ በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስንገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማናል!!! ዘመኑ የሙያና የቴክኖሎጂ ስለሆነ ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ!!!!