قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
الذهاب إلى القناة على Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
914
المشتركون
-324 ساعات
-177 أيام
+5330 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from አህመድ ፈንታቢል
💡እውቀት የሌለው አካል ያለ እውቀት ሺርክ ቢሰራ ስራው ሽርክ ነው ሰውየው ግን በጅህልናው ዑዝር ይሰጠዋል ይላሉ ሸይኽ ፈውዛን
Repost from قناة أبو عمران الخميسي لنشر السنة والتوحيد
بسم الله الرحمن الرحيم
ታላቅ የትምህርት ብስራት ከ«ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ!
እውቀት የልብ ብርሃን፣ የሕይወት መመሪያ ነው። የዲንዎን እውቀት በጥራትና በስርዓት ለመቅሰም ካለዎት ፍላጎት በመነሳት «ኢብኑ ዐብባስ» የኦንላይን መድረሳ አዲስ ትምህርት ይዞላችሁ ቀርቧል።
📌 የኮርሱ ዝርዝር መረጃ፦
➠ የሚቀራው ኪታብ፦ «መሳኢሉል ጃሂልያ» (مسائل الجاهلية) — በሸይኽ ሙሐመድ ብን ዐብደልወሃብ (ረሒመሁልላህ)
◈ አስተማሪ፦ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል-ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ
📲 የምዝገባ አድራሻዎች እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦
🔹 ለወንዶች፦
👉 @Hussein_cod018
👉 @Yufa4
በሴቶች ለመመዝገብ እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦
🔹 ለሴቶች፦
👉 @bint_Adem15
👉 @Riiche1
📖 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!»
💡 ቦታ ሳይሞላ በፍጥነት ይመዝገቡ፤ ለሌሎችም በማጋራት የእውቀት ጥሪውን ያድርሱ!
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
📢 ለአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአካባቢው ላሉ ሁሉ የምሥራች!
ኢንሻ አላህ፣ በሚከተለው መርሃ ግብር ትምህርቶችን እንጀምራለን።
📚 ከዙህር ሰላት በኋላ፦
የዕውቀት ፈላጊ ተማሪ መሠረታዊ መጻሕፍት – የመጀመሪያ ደረጃ
በዚህ ደረጃ የሚከተሉት መጻሕፍት ይማራሉ፦
• አል-ኡሱሉ አስ-ሰላሳህ ወአዲላቱሃ — الأصول الثلاثة وأدلتها
• አል-ቀዋዒዱ አል-አርበዓ — القواعد الأربع
• ነዋቂዱል ኢስላም — نواقض الإسلام
• አል-አርበዒን አን-ነወዊያ — الأربعون النووية
📖 ከመግሪብ ሰላት በኋላ፦
• ኪፋያቱል ሙተዓቢድ — كفاية المتعبد
• የነቢዩ ﷺ ሕይወትና ታሪክ — سيرة الرسول ﷺ
📍 ቦታ፦ መስጂድ ኸዲጃ — ቡሊ — አዳማ
📅 ቀናት፦ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ
🗓 የመጀመሪያ ቀን፦ ቅዳሜ፣ ረቢኡል አኺር 15/1447 ሂጅሪ, (መስከረም 30,2019),
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
🌿 ሁላችሁም በደህና መጡ! አላህ በዕውቀት እንዲጠቅመን፣ ከእርሱም ዘንድ ቅንነትንና ጽናትን እንዲሰጠን እንለምነዋለን።
📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/AbumuslimAlarsi
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
💗 የተከበራችሁ እህቶች በየትኛውም ዩንቨርሲቲ የምትገኙ የሙስሊም ሴት ዓሚሮች ሁላችሁንም የምንፈልጋችሁ ስለሆነ ባረከላሁ ፊኩነ ከዚህ በታች ባለው ዩዘር ኔም አናግሩን።
💗 የቻናል እና የግሩፕ ባለቤቶች ሸርርር በማድረግ ተባበሩን ባረከላሁ ፊኩም።
👇👇👇
@umureyan_33
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
መንገዱ ቢርቅም #የመን አድርሱልኝ አደራ
#መርከዘልፈዩሽ!!
-------------------------------
ትንኝ ምንም ቢሮጥ መንገድ ላይ ቢያመሽም፡
ከጩጯን አንደበት ቅጥፈት ቢቀረሽም፡
መሰላቸው እንጂ ሰው አይረበሽም፡
ሀሸራት ተፈርቶ ከአላማ አይሸሽም፡
በባጉንቸር ዝላይ ውቅያኖስ አይጓሽም፡
የሚዳቆወች ድምፅ ተራራ አይረብሽም፡
የአይጦች ድንፋታ ከድመት አያልፍም፡
ውሀ ከተረጨ አመድ ይሆናል ፍም፡
#የመንፈዩሽ_!!
ብዙ ጀግና አፍርቷል የየመን ማህፀን፡
ተውሒድና ሱናን ሀቅን የሚማፀን፡
ሽርክና ቢዲዐን ሌት ቀን የሚዋጋ፡
በገንዘብ በነፍሱ የሚከፍል ዋጋ፡
ሱናን ለማስረዳት የሚል ከላይ ከታች፡
ሀቅን የሚጠብቅ ከፈጣሪ በታች፡
#የመን____!!
የታሪክ ሀገር ነው የጀግና መፍለቂያ፡
የኢስላም አርማ ነው ግሩም መታወቂያ፡
ለደነዘዘ ሰው ቆንጆ ማነቃቂያ፡
መርከዝ እየሰራ ኪታብ የሚሰድር፡
ሀቅን ከማንም ጋር የማያወዳድር፡
የሊቆች ሀገር ነው ይህ የየመን ምድር፡
#የመን___!!
ከነብያት ዘመን ከድሮ ጀምሮ፡
አለ በየመን ውስጥ ታሪክ ተከምሮ፡
እስከ ዛሬ ድረስ ተነግሮ አላለቀም፡
ጦርነት ቢኖርም #ታሪኳ አልደቀቀም፡
አጂግ በጣም ብዙ ፈተና ቢኖርም፡
የየመን ዑለማዕ ክንዱ አይሰበርም፡
በተውሒድ በሱና በሒፍዝ ጠንክሯል፡
ኢስላም በሽምደዳ አዕምሮው ላይ ሰፍሯል፡
#የመን....!!
ምንም ቢፈጠርም ፊትናን አቀጣጣይ፡
ለትውልድ መድረስ አይችልም ለቀጣይ፡
ብዙ ነገር መጥቶ እንዳልነበር ከስሟል፡
የየመን ዑለማዕ በተጠንቀቅ ቆሟል፡
በእምነቱ ለመጣ ማንንም አይሰማም፡
በእውቀትም በተግባር የመን አይታማማም፡
የየመኖች ምድር ጀግና በቅሎበታል፡
ገና ብዙ ኸይራት ይፈፀምበታል፡
የየመን ዑለሞች እውቀት እየሰጡ፡
▸#ፊትና__ናፋቂወች_እየተዳመጡ፡
ተውሒድና ሱና ኸይሩ ይቀጥላል፡
የፊትናው ናፋቂ ገና ይቃጠላል፡
በተአሱብ ሰክሮ እስበሱ ይባላል፡
የመን ጀግኖቹ ጋር ታሪኩን ያድሳል፡
ገና ብዙ ጀግና አርበኛ ይነሳል፡
ሱናው እያበበ ቢዲዐው ይከሳል፡
#ኢንሻ_አሏህ_!!
የመን ላይ ሔዳችሁ የምትበጠብጡ፡
ነገር ከዚያ ከዚህ የምታሯሩጡ፡
ወይ ስርዐት አረጉ አልያ ደግሞ ውጡ፡
ከሀበሻ ድረስ ሀገር አቋርጣችሁ፡
ከታሪኳ ቦታ #የመን ላይ ሔዳችሁ፡
ፊትና ስትፈጥሩ አለማፈራችሁ⁉️
#ለማንኛውምግን_
ከፍ ያለች ሀገር ነች በታሪኳ የመን፡
አላት ብዙ ጀግና ለአሏህ የሚታመን፡
ከትላንት እስካሁን የመን ባዶ አልሆነም፡
የመን በእውቀት እንጂ በሽርክ አልገነነም፡
መጥፎወች ቢኖሩም ይፀዳሉ ገና፡
ድጋሜ ያፈራል ተውሒድና ሱና፡
በሶሀቦች ፈለግ በእውነተኞች ፋና፡
ይህን የሚሰሩ#የመን አሏት ልጆች፡
በቁርዐን በሀዲስ በእውነት ፈራጆች፡
#የመን_!!
እንኳንስ ዛሬና መረጃው ተዳርሶ፡
ብዙ የሽርክ ቋት እየጠፋ ፈርሶ፡
አለም ጫፍ እስከጫፍ ተውሒዱ ተዳርሶ፡
የየመኑ አሊም ጫካውን መንጥሮ፡
በአሏህ ተወክሎ ትንሽ ስንቅ ቋጥሮ፡
ደማጅን መስርቷል ሀቅን አስተምሮ፡
በተውሒድ በሱና ሽርክን አሶግዶ፡
ጥመት ኹራፋትን በሀቅ ገርምዶ፡
አልሀምዱ ሊላሒ ምድሪቷ ጀግና አላት፡
ለተውሒድ ለሱና ህይወቱን ገብሮ የሚታገልላት፡
👉#እስኪ__አስቡት‼️
ደማጂን ሸይኽ ሙቅቢል እንደመነጠሩት፡
ያኔ በምን መልኩ እንዳስተዳደሩት፡
#የህያ ፋትና ፈጥሮ እስኪያፈርሰው ድረስ፡
ደማጅ ግሩም ነበረ ውብ የሱና ፈረስ፡
ሜዳ ነበር ደማጅ የተውሒድ የሱና፡
#አበላሸው እንጂ#ሀጁሪ መጣና፡
ምንም በዚያ ፊትና ብዙ ግፍ ቢሰራም፡
ኪሳራ ቢያደርሱም የስሜት ሰካራም፡
#ሙቅቢል የለኮሱት አልጠፋም ችቧቸው፡
አለ ዛሬም ድረስ ውብ ነው ታሪካቸው፡
ፊትና ቢፈራገጥ ምን ከዚያ ከዚህ ቢል፡
የቆሸሸ ውሀ እንደያዘ ዘንቢል፡
በአሏህ ታግዞ መስርቶታል ሙቅቢል፡
ወደ ባለቤቱ አሁን ተመልሷል፡
ጨርሶ ባይጠፋም ፊትናውም ፈራርሷል፡
ይቀጥላል ገና ድጋሜ ታድሷል፡
👉#እናም_ወዳጀ_ሆይ__!!
የታላቁ አሊም የሙቅቢል ተማሪ፡
የተውሒድ የሱና የኢስላም ዘማሪ፡
የዚያ የጀግና#ሸይኽ የሙቅቢል ደረሳ፡
ፊውሽን ቆርቁረው#የአደኑ አንበሳ፡
ሽርክና ቢዲ ን ሲያሳዩት ሀበሳ፡
ጥመት ኹራፋቱን በመረጃ ገርፈው፡
ሞት አይቀርምና እርሳቸውም አርፈው፡
ሌሎች ተተክተው ዛሬም ድረስ አሉ፡
ተውሒድና ሱናን በደስታ እየበሉ፡
ሀቅን እንደ ምግብ እየተመገቡ፡
ኢስላምን ለመጥቀም ሱና እንዳነገቡ፡
ለጠላቶቻቸው ሆነው የግር እሳት፡
ሁሌም ለሚለፋ ሰውን ለማሳሳት፡
ፊትናን ለሚናፍቅ ሆነውት ትኩሳት፡
አሉ ዛሬም ድረስ ሀቅን ባለመርሳት፡
ሁሉንም ቻል አርገው ለሱና እንደቆሙ፡
ለደረሶቻቸው የኢልምን ጎዳና ሁሌ እየጠቆሙ፡
------------------------------------------------
......#አወና.......
ያንን ግሩም መርከዝ ቦታው ላይ የሰሩት፡
መርከዘል-ፈዩሽን እንድህ ያሳመሩት፡
አብደረህማን ናቸው የአደኑ ነብር፡
በሀቅ ፈላጊ በጀግኖች ትብብር፡
ከዛን ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ፡
አለ ለህዝባችን#ኢልማቸው ሲዳረስ፡
መርከዙን#ጌታ እንጂ ሰው አይችልም ማፍረስ፡
ይህንን ራዕይ በቅድሚያ ያሰቡት፡
በትኩረት በጥልቀት ቆርጠው ያነገቡት፡
#የአደኑ__አንበሳ ናቸው የገነቡት፡
እውቀት እንድቀስም ወጣቱን የሳቡት፡
#ፈዩሽ____
ቁርአንና ሀዲስ ተውሒድና ሱናን ያስተምሩበታል፡
ዒልሙ ከሸይኽ ሙቅቢል ተመስክሮለታል፡
የጥመትን ቡድን በደሊል ይማታል፡
ሱናን ከመጠበቅ መች ስራ ይፈታል፡
ብዙ ኸይር ስራ ይፈፀምበታል፡
የሀቅ ዘበኛ ተተኪ ያመርታል፡
#መርከዘል--#ፈዩሽ___!!
ጠላት ቢኖሩትም ጥቁር እንደ ከሰል፡
ሀሰድ ምቀኝነት ተንኮል በማውሰልሰል፡
ውሸትና ቅጥፈት ሁሌ በማማሰል፡
ቀሩ እንደከሰሩ አያውቁትም መሰል!!
ተመስርቷልና በእሳት ተፈትኖ፡
መርከዛችን ደምቋል ጠላቱን በትኖ፡
የመርከዙን ውብ ስም በመጥፎ ለማንሳት፡
እውቀት እንዳይፈልግ ህዝቡን ለማሳሳት፡
በስሜት ተነስተው ብዙ ግፍ ቢሰሩም፡
የሌለ ቢቀጥፉ ምንም ቢናገሩም፡
ለዚህ ታላቅ መርከዝ ምንም አልፈጠሩም፡
#ፈዩሽ.....!!
ይህ መርከዝ የማን ነው ብለው ሳይጠይቁ፡
ዘለው እየገቡ ቀሩ እየደቀቁ፡
ለማይጥሱት አጥር እየነቀነቁ፡
ከሰሙ ጠቅላላ ዳግም ላይነሱ፡
ተመናምነው ጠፉ እየተቀነሱ፡
ምን ከፊትና ሰው ሴራ ቢጠነሰስ፡
በውሸት በቅጥፈት መርከዙ ቢከሰስ፡
መርከዙ ልምዱ ነው ባጢልን መከስከስ፡
በነጋ በመሸ ተንኮል ቢቀምሩም፡
በፅኑው መርከዝ ላይ ምንም አልፈጠሩም፡
ከወዳ ከወድህ#ሙፍቲኖች ቢዘሉም፡
ፈዩሾች በተንኮል የሚጠፉ አይደሉም፡
በውሸት ትረካ ይጠፋል መስሏቸው፡
#ፈዩሽ እየፀና አልወድቅም አላቸው፡
ረግጧቸው ዘምቷል እንኳን ሊሰማቸው፡
ትርጉም አልባ ሆኖ ቀረ ልፋታቸው፡
የሱና ጠላቶች ወይ ማሳዘናቸው‼️
-------------------------------------------
ምላስን በመሳል በማሾል ከሲኪን፡
ምኞትን ማሳካት አይቻልም ሚስኪን፡
በእውቀት ጠንክሩ ቢጠቅማችሁ ላኪን፡
ይህን ትልቅ መርከዝ ጠማሞች ቢገፉት፡
ለርሱ ገቢ ሆኖ የበለጠ አሰፉት፡
የወደደ ይውደድ የከፋውም ይክፋው፡
መርከዘል__ፈዩሽን፤
ከጌታችን ውጭማንም አያጠፋው፡
👉 ይልቅ ፅና! ጠላቶችህ የፀናህ ሆነህ ማየት ነው የሚያስፈራቸው።
ይልቅ ፅና! ጠላቶችህ የፀናህ ሆነህ ማየት ነው የሚያስፈራቸው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በሑዘይፋ መስጂድ ሲቀርብ የነበረው የመንሀጁ ሳሊኪን ኪታብ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱ ሊላህ። በቀጣይ የምንጀምረው - ኪታቡ ገበያ ላይ የሚገኝ ከሆነ - የኢብኑ ተይሚያን አልሐመዊያህ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ። ኪታቡ ካልተገኘ የምንጀምረውን ኪታብ አሳውቃለሁ፣ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ግጥም ለኢትዮ ኮከቦች በኡስታዝ አቡ ሓሳን ሓፊዘሁሏህ ኡስታዞቻችንም አሏህ ይጠብቃቸው ያረብ
http://t.me/UmuAbdurhamn
Repost from Abu useymin (Mohammed Ali)
ኢብራሂም ኢብኑ አድሃም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"ከሰዎች ጋር ምን አገባኝ!!
በእናቴ ሆድ ውስጥ ብቻዬን ነበርኩ፤
ወደዚች ዓለም የወጣሁት ብቻዬን ነው፤
የምሞተውም ብቻዬን ነው፤
ወደ ቀብሬ የምገባው ብቻዬን ነው፤
የምጠየቀው ብቻዬን ነው፤
ከመቃብሬ የምቀሰቀሰው ብቻዬን ነው፤
የምተሳሰበውም ብቻዬን ነው፤
ጀነት ብገባ ብቻዬን እገባለሁ፤
እሳት ብገባም ብቻዬን እገባለሁ፤
በእነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ውስጥ ማንም አይጠቅመኝም።
ታዲያ ከሰዎች ጋር ምን አገባኝ!!"
— ኢቃዙል ሂመም፣ በኢብኑ አጂባ [1/176]
በነገራቹህ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ለመፃፍ አስብና እትወዋለሁ። የተውኩትም ኸይርን ያሰቡ በርካታ የቻናል፣ የግሩፕና የ"ዋቭ" ባለቤቶች ፅሁፌን በመልካም ሳይረዱት ይቀሩና አንድም ቅር እንዳይሰኙብኝ ሲቀጥል ደግሞ ሰዎችን ከኸይር ማሰናከል እንዳይሆን በሚል ስጋት ነበር።
የቻናል ማሳደጊያ ተብለው በሚለቀቁ ማስታወቂያና ጥያቄና መልስ ምክኒያት እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ከምንወዳቸው የሱና ወንድሞች ቻናል ለመውጣት ተገደናል። ምክኒያቱም የቴሌግራም ተጠቃሚ የሚፈልገው ከሁሉም የተለያዩ ቻናሎች የተለያዩ ቁምነገሮችን መውሰድ እንጅ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ቻናሎች ተመሳሳይ ማስታወቂያና ጥያቄና መልስ ማንበብ አይደለም።
ለማንኛውም ወንድሜ አቡ ሱፍያን ጀዛከላሁ ኸይራ
= t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
እውነቱን ለመናገር፣ በአሁኑ ወቅት በንቃት የምከታተላቸው የቴሌግራም ቻናሎች ከአምስት እንኳ አይበልጡም። ቴሌግራም እንደ ቀድሞው ማራኪነቱ ቀርቶ እጅግ አሰልቺ መድረክ እየሆነ መጥቷል።
በተለይ "ዋቭ" በሚል ሰበብ የሚለጠፉት የቻናል ማሳደጊያ ማስታወቂያዎች ቻናሎችን ከመረጃና ዕውቀት ማዕከልነት ይልቅ ወደ አደባባይ ልመና ቀይረዋቸዋል። በዚያ ላይ አስር አድሚን ተሹሞበት፣ እንደ ሰፈር ስብሰባ እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን እየረጨ የሚወጣበት የተዘበራረቀ ጓዳ ሆነዋል።
ሐቂቃ ኢኽላስ እና የሚጨበጥ ጠቃሚ ይዘት ያለው ሰው እንዲህ ዓይነት የቁጥር ብዛት አያስጨንቀውም። ያለ ምንም ማስታወቂያ በይዘታቸው ጥንካሬ ብቻ ከዜሮ ተነስተው በአስር እና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈሩ ብዙዎች አሉ።
ቻናል ማስተዳደር ቀላል ነገር ሳይሆን ትልቅ አማናና ኃላፊነት ነው። የቁጥር መብዛት ሳይሆን ተከታዮቻችሁን ማክበር እና ለነሱ
የሚመጥን ጥራት ያለው ነገር ማቅረብ ይቅደም።ይዘታችሁ ይመስክርላችሁ፤ ተከታይ በራሱ ይመጣል!
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from ስለ ዲናችን
ስለ ሽርክ የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ ➍❹አከባቢ ሙሓደራወች❶ ሽርክ ታላቁ በደል ❷ከሽርክ ለመውጣት ❸የቀብር አምልኮ ❹ሽርክ ሲፈርስ ❺ሽርክ ላይ መዳረሻ ምክናያቶች ❻ለምን ሽርክ ይፈፀማል ❼ሸይኽ ኑሩ ሁሴን እና ሽርክ ➑በዱአ ስም የሚሰራ ሽርክ ❾ የሽርክአስከፊነት ➓ትንሹ ሽርክ ❶❶ሽርክ እና ተያያዥ ነገሮች ❶❷ሽርክ ምንድነው ❶❸የአብሬት ሽርክ ❶❹መጠበቅ በአላህ ብቻ ነው ❶❺የሽርክ አደገኛነት ❶❻ወሎ ላይ ሽርክ በየአይነቱ ❶❼ስለሽርክ ❶➑ሽርክ ❶❾ሽርክ ከወንጀለኞች ሁሉ የከፋ ነው ❷0የሽርክ አደጋ ❷❶ከሽርክ ነፃ መውጫ መንገዱ ❷❷አብሬት እና ሽርክ ❷❸ሽርክ ሸይኽ አወል ❷❹ሽርክ እና ማህበረሰባችን ❷❺ከአላህ ውጭ ማረድ ሽርክ ነው ❷❻በገድ ማመን ሽርክ ነው ❷❼ሽርክ ሲኮታኮት ❷➑ትንሹ ሽርክ ዩዩልኝ እና ይስሙልኝ ❷❾አላህ ሽርክን አይምርም ❸0የሽርክ ሰወች ቅጥፈት ❸❶ርዕሱ አይቀርም ❸❷ደገር እና ሽርክ ❸❸የሽርክ አስከፊነት ❸❹ስለ ሽርክ እና ንፍቅና ❸❺ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው ❸❻ሽርክ እና ውደታ ❸❼በመታዘዝ የሚመጣ ሽርክ ❸➑ግጥም ስለ ሽርክ ❸❾ሽርክን ኑዛዜ ❹0የሽርክ ተግባር ❹❶የሽርክ ጠበቃ አትሁን ❹❷መጠንቆል ሽርክ ነው ❹❸የአህባሽ ቲቪ እና ሽርክ ❹❹ሽርክን ተጠንቀቁ
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
የሀበሻ ዑለማወች ''ከዋክብቶቻችን''
በግጥም ሲታወሱ ኢንሻ አሏህ....
➊ሸይኽ ሙመድ አሊ አደም አል-ወሎውይ
► ''የሀበሻው ጀንበር''
❷ ሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚ አል-ሀረሪይ
► ''የተውሒዱ ሞተር''
❸ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አል-ሐረሪይ
► ''የቋንቋው መሀንድስ''
❹ ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ አል-ወሎውይ
►የሒዝብዮች መብረቅ
➎ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን አደም
► ''የአዲስ አበባው ፈርጥ''
❻ ሸይኽ ሙሳ አልቀጧኒ አል-አፈሪይ
► ''የአፋሩ አንበሳ''
➐ሸይኽ ከማል አፍሬ (አነህዊይ)ቻግኒ
► ''የቻግኒው አርበኛ''
❽ሸይኽ አወል አህመድ አል-ከሚሲይ
► ''የከሚሴው ኮከብ''
❾ማጠቃለያ ብዙ አርበኞች አሉን
► ''የቲም አይደለንም''
ሰአቱን ጠብቆ ይለቀቃል ኢንሻ አሏህ
✍️በኑረዲን አል አረቢ .......
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
የኡስታዝ አቡ ሙስሊም ደርሶች፦
01. ኹዝ ዐቂደተክ
02. ፊቅሁ ሲያም
03. መውዒዞቱ ኒሳእ
04. ሠላሠቱል ኡሱል
05. አርበዑነ ነወዊያ
06. አነሕውል ዋዲሕ
07. ነዋቂዱል ኢስላም
08. አዳቡል መሽይ ኢለ ሶላት
09. ረካኢዙ ተርቢየቲል አውላድ
10. ላሚየቱ ብኒ ተይሚያ
11. ሓኢየቱ ብኒ አቢ ዳውድ
12. ሉዙሙ መንሀጂ ሰለፍ
13. ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና
14. ኡሱሉ ሱና ሊልሑመይዲ
15. አልቀዋዒዱል አርበዕ
16. ኡሱሉ ሱንና
17. ውድ የሆኑ ምክሮች ለሙስሊሟ ሴት
19. ዋጂቡና ነሕው ማ አመረነሏሁ ቢህ
20. ሙኽተሶሩን ፊ አሕካሚ ሲያም
21. ተክሪሙል ኢስላሚ ሊልመርአ
22. ረመዳንን እንዴት እንቀበል?
23. መንዙመቱል በይቁኒያ
24. አልዐቂደቱ ሶሒሓህ ወማ ዩዷዱሃ
25. የሴቶች ስህተቶች በረመዳን
26. ሚን ኡሱሊ ዐቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀማዐ
27. መንሀጁ ሰለፊ ሷሊሕ
28. ቀዋዒዱን ሀማ ፊል አስማኢ ወሲፋ
29. ሑቁቁን ደዐት ኢለይሃል ፊጥረቱ
30. አዳቡል ሙዓሊም ወል ሙተዐሊም
31. አልመፋቲሑል ዐሸራ
32. አስባቡ ሰዐደቲል ኡስራ
33. አሠባት ዐለል መንሀጅ
34. አምኑል ቢላድ
35. ኹዝ ዐቂደተክ
36. ኡሱሉ ሲታ
37. ነሲሓቲ ሊአህሊ ሱና
38. ተንቢሃቱን ሙሂማ
39. ፉሱሉን ፊ ሲያም
40. አልወሲየቱ ሱጝራ
41. ፊቅሁ ኒካሕ
42. ሹሩጡ ሶላት
43. ዐቂደቱ ራዚየይን
44. አረካኢዙል ዐሽር
45. ተውጂሀት ሊል ፈታት
46. ሲፋቱ ዘውጀቲ ሷሊሓ
47. አተዕሲሉ ፊ ጦለቢል ዒልም
48. ሸርሑ ሐዲሢ ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ
49. መንሀጁን የውሚዩን ሊጧሊቢል ዒልም
50. አልሙዒን ሊተውዲሒ መዐኒ አሠሪ ብኒ ሲሪን
51. ከሊመቱ ተውሒድ ላኢላሃ ኢለላህ
ጥቂት ስለ ኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሐሰን አል አርሲ
ኡስታዝ ዑመር ሐሰን አቡ ሙስሊም ከ16 አመት በፊት የኡሙል ቁራ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እድል (scholarship) በማግኘቱ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሲከታተለው የነበረውን አካዳሚ ትምህርት በመተው ወደ መካ አቀና። የመጀመሪያ ዲግሪውን በመካ ከተማ ከሚገኘው የኡሙል ቁራ ዩኒቨርሲቲ በ
الكتاب والسنة مع الإعداد التربوي
አጠናቋል። የተማረባቸው ዑለማዎችን ለምሳሌ ያክል እንጥቀስ
① ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
② ሸይኽ ዐብዱረሕማን አልዐጅላን፣
③ ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም አልወሎዊ፣
④ ታዋቂው ሙሐዲሥ ሸይኽ ወሲዩላህ ኢብኑ ሙሐመድ አልዐባስ
⑤ ሸይኽ የሕያ ኢብኑ ዑሥማን (ከሸይኽ ሙቅቢል ሸይኾች ውስጥ ናቸው)፣
⑥ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል፣
⑦ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል
ከነዚህም በተጨማሪ ወደ መካ በሚመጡበት ጊዜ ባገኛቸው አጋጣሚ የተማረባቸው ዑለማዎች አሉ። ለምሳሌ:–
⑧ ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን
⑨ ሸይኽ ሷሊሕ አልሉሐይዳን፣
(10) ሙፍቲ ዐብዱል ዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ፣
(11) ሸይኽ ፉኣድ ኢብኑ ሰዑድ አልዐምሪ፣
(12) ሸይኽ ዓዲል ኢብኑ መንሱር አልባሻ
(13) ሸይኽ አቡ ሁማም ሙሐመድ ኢብኑ ዐሊይ አልበይዷኒ እና ሌሎችም።
ከመካም ውጭ በተለያዩ ደውራዎች (አጫጭር ስልጠናዎች) ላይ በመካፈል ዒልም የቀሰመባቸው መሻይኾች ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ያክል፦
* ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አልመድኸሊ (ረሒመሁላህ)፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
• ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊ፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ረምዛን አልሃጂሪ፣
• ሸይኽ ዐብዱረሕማን ኢብን ሙሕዪዲን፣
• ሸይኽ ዐልይ ኢብኑ የሕያ አልሐዳዲ፣
• ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዐብዲል ወሃብ አልዐቂል፣
• ሸይኽ ኡሳማ አልዐምሪ እና ሌሎችም።
ኡስታዝ አቡ ሙስሊም ተባባሪና ፈጥኖ ሰው ጋር የሚግባባ ነው። ከሚማርባቸው መሻይኾች ዘንድ ያለው ቅርበት እና አመኔታ የሚያስቀና ነው።
አቡ ሙስሊም የሳዑዲ ኢስላማዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሚያሰማራቸው ዱዓት ጋር በመሆን በየዓመቱ ወደ መካ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች በማስተማር ይጠመዳል።
* ከሐጅ ውጪም የተለያዩ የማስተማር ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
* በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ውስጥም አስተምሯል። ትምህርቱን መከታተል ለመከታተል የሚከተለውን የቴሌግራም ቻናሉን Join ይበሉ።
🌐 t.me/AbumuslimAlarsi
🌹 ወንድ ልጅ ሲያፈቅር… እምነቱን ይሰጣል ይባላል፦
ወንድ ልጅ ሲያፈቅር ሞኝ ይሆናል ይላሉ…
እኔ ግን ፦ ሞኝ አይሆንም፤ ልቡን ለአንድ ሰው አደራ ይሰጣል ነው የምለው። 🫀
ወንድ ልጅ ላፈቀራት ሴት የሚሰጣት ትልቁ ስጦታ ገንዘብ አይደለም፤ በገንዘብ የሚገዙ ነገሮችም አይደሉም።
ትልቁ ስጦታ እምነቱ ነው፤ ልቡን የሚከፍትላት መሆኑ ነው።
ለዓመታት ማንንም ላያምን ይችላል፣
ራሱን ብቻ ተማምኖም ሊኖር ይችላል፣
ግን የገነባውን ጠንካራ ማንነት፣
ጥርጣሬውን፣ ጥንካሬውን፣ “ማንም አይጎዳኝም” የሚለውን ግድግዳ…የሆነ ማንነቱን ።አንድ ቀን ለአንዲት ሴት ብቻ ያፈርሰዋል።
በሌሎች ፊት ጠንካራ የሆነው ወንድ፣
በእሷ ፊት ግን ስስ ይሆናል።
ሌሎችን በጥርጣሬ የሚመለከተው ሰው፣
እሷን ግን በእምነት ይመለከታል።
ለሌሎች ልቡን የማይከፍተው፣
ለእሷ ግን የዓመታትን የተዘጋ በር ይከፍታል። 🫀
እና ይሄ ነው ፍቅር በአንድ ወንድ ላይ የሚያደርገው፤ ከባዱ ነገር
አንዴ ልቡ ካመነ፣ ምክንያት ሳይጠይቅ ያምናል።አንዴ ካፈቀረ፣ በምንም ነገር ላይ እንደማይሰጥ የጠበቀውን ልቡን ይሰጣል።
ነገር ግን እህቴ…
የተሰጠሽን እምነት እንደ መጫወቻ አትዪው። አንዳንድ ሴቶች ወንድ ከልቡ እንዳመናቸው ሲያውቁ፣ ያንን እምነት እንደ ድክመት ይቆጥሩታል። እሱ የነገራቸውን ሚስጥር ይጠቀሙበታል፤ የሰጣቸውን ፍቅር ያቃልሉታል፤ የሰጣቸውን እምነት ይሰብሩታል። ከዚያም አንድ ቀን በድንገት ይከዱታል።
ያኔ ግን የሚሰበረው ፍቅሩ ብቻ አይደለም…
“እንደገና ማንንም አላምንም” የሚለው የልብ ግድግዳ ይገነባል።
ስለዚህ ማወቅ ያለባችሁ የአንድ ሰው ልብ በእጃችሁ ከገባ፣ አደራ መሆኑን ነው።
እምነቱን ከሰጣችሁ፣ አደራ ነው።
ሚስጥሩን ከነገራችሁ፣ አደራ ነው።
ድክመቱን ካሳያችሁ፣ አደራ ነው።
ፍቅርም ቢሆን፣ እምነትም ቢሆን፣ ልብም ቢሆን… አደራ ነው።
🌹 ስለዚህ ወደ ልብሽ የገባውን ወንድ እንደ ዕድል ብቻ አትመልከቺው፤ እንደ አደራ ተመልከቺው። እሱ በፊትሽ ስስ ከሆነ፣ ድክመቱን ካሳየሽ፣ እንባውን ካሳየሽ፣ የልቡን ሚስጥር ካካፈለሽ…
ይህ ማለት ደካማ ስለሆነ አይደለም፤ አንቺን ከሌሎች በተለየ መልኩ ስላመነሽ ነው።
እውነተኛ ፍቅር ሰውን ማሸነፍ አይደለም፤
የሰጠንን ልብ እንዳንሰብር መጠንቀቅ ነው።እና አንድ ቀን ያ ሰው እንደገና ለመታመን ከተቸገረ፣ ምናልባት የሚያስቸግረው ፍቅር ሳይሆን…
አንድ ጊዜ በተሰጠ እምነት ላይ የደረሰበት ቁስል ነው። 🥀
ልቦችን እንደ አበባ እንያዛቸው…
ምክንያቱም አንድ ጊዜ ከተሰበሩ በኋላ እንደቀድሞ ለማበብ ጊዜ ይፈልጋሉ። 🌹
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from ስለ ዲናችን
ተውሂድ
የታላላቅ ዑለሞች ስብሰብ፡-
🎙ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ
🎙ሸይኽ ሷሊሕ አሉሐይዳን
🎙ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን
🎙ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ
🎙ሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሑመይድ
🎙ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ
🎙ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዑሠይሚን
ይደመጥ በጣም ወሳኝ ጣፋጭ ዳእዋ ነው ስማ ጥግ ላይ ያለኸው ተውሂድ ችላ የምትለው ኢኽዋን ሙፍሲድን እና መሰሎቹ🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/KedmiyaLetewhid9
