ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

الذهاب إلى القناة على Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
908
المشتركون
-324 ساعات
-157 أيام
+4830 أيام
أرشيف المشاركات
🔰 « أهل السنة لا يحكمون لأحد بجنة ولا نار »
🎙️ لفضيلة الشيخ أ.د. صالح بن عبدالعزيز السندي (حفظه الله تعالى ورعاه)
رابط دروس شرح العقيدة الطحاوية : https://youtube.com/playlist?list=PLVw9FtCy781ZSgNnw5hJm1QkniE2k6Jx8&si=G_9F_YHlqaUcScQG

ምክንያቱ ባይገባንም፣ በአካል ሳናያቸውና በቅርበት ሳናውቃቸው እንዲሁ ነፍሳችን አጥብቃ የምትወዳቸው ሰዎች አሉ። ልባችን ከእነሱ ጋር ይመታል፤ መንፈሳችን አብሯቸው ይጓዛል፤ ዐይናችን ሊያያቸው፣ አካላችንም አጠገባቸው ሊሆን በብርቱ ይናፍቃል። አላህ ሁሌም ከምትወዱት ጋር አብሮ ያኑራችሁ!

🇸🇦🇸🇦🇪🇹ቁጣን (በቀልን) መተዉ ያለው ትሩፋት! 🌿🌿 ረሱል (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن كَظَمَ غيظًا وهو قادرٌ على أن يَنْفِذَه دعاه اللهُ عزَّ وجلَّ على رؤوسِ الخلائقِ يومَ القيامةِ حتى يُخَيِّرُه اللهُ مِن الحُورِ ما شاءَ.﴾ “ቁጣውን ለመወጣት (ለመበቀል) አቅም እያለው ቁጣውን የዋጠ ሰው፤ አላህ (አዘወጀል) በቂያማ እለት በሕዝቦች ሁሉ ፊት ይጠራዋል፤ ከሁር አል-አይን (ከጀነት ሴቶች) ያሻውን መርጦ እንዲያገባ ምርጫ ይሰጠዋል።” ✅ አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 4777 Join https://t.me/Tewhid_and_Sunah https://t.me/TewhidAnd_Sunah

Repost from N/a
​✨ ከስራ ደክሞዎት ቤት ሲገቡ የሚያስተንፍሱበት ምርጥ መፍትሔ! 💆‍♂️💆‍♀️ ​የአንገት፣ የጀርባ ወይም የወገብ ህመም እና ድካም ተሰምቶዎታል? ይህንን ዘመናዊ የአንገት እና የሰውነት ማሳጀር (Neck & Body Massager) በመጠቀም ድካምዎን በአጭር ጊዜ ያስወግዱ! ​🔥 ማሽኑን ልዩ የሚያደርጉት ባህሪያት፡ ✅ የሙቀት ኤፌክት (Heat Function): ከማሳጁ ጋር ተያይዞ በሚሰጠው ሙቀት የደም ዝውውርን ያፋጥናል፣ የጡንቻ መወጠርን ያዝናናል። ✅ ብዙ አገልግሎት (Multi-functional): ለአንገት፣ ለወገብ፣ ለእግር እና ለሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚሆን። ✅ በቻርጅ የሚሰራ (Rechargeable): በቻርጅ የሚሰራ በመሆኑ የትም ቦታ ይዘውት ለመንቀሳቀስ ይመቻል። ✅ ለመጠቀም በጣም ቀላልና ምቹ! ​💡 ለሁሉም የቤተሰብ አባል አስፈላጊ የሆነ ምርጥ እቃ! ​🚚 ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ/በፍጥነት እናደርሳለን! ​👉 ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡ 📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ] ➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy] ​📍 አድራሻ፡ [ወሎ ኮምቦልቻ/ደሴ] ​✨ በፍጥነት ይዘዙ፣ ህመምዎን ያቅልሉ! ✨ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ! 🔗 የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦ https://t.me/Al_Faiz_online_shopping ​ 🔏 የቴሌግራም ግሩፓችንን ሊንክ https://t.me/Al_aaayaa

Repost from Abu Hayder Aliy
ለዚች አጭር ጊዜ ለዚች ከንቱ ዓለም ዕድሜአችን ቢበዛ ላንኖር ዘላለም በድንገት ተጠርተን ላይቀር መሄዳችን ጥሩና ደግ ይሁን ምንግዜም ስራችን !! አዎ ስራችንም ባህሪያችንም መልካም ብቻ መሆን አለበት
+3
ለዚች አጭር ጊዜ ለዚች ከንቱ ዓለም ዕድሜአችን ቢበዛ ላንኖር ዘላለም በድንገት ተጠርተን ላይቀር መሄዳችን ጥሩና ደግ ይሁን ምንግዜም ስራችን !! አዎ ስራችንም ባህሪያችንም መልካም ብቻ መሆን አለበት መልካም ስነ-መግባርና መልካም ስራ በዱንያም በአኼራም ከፍ ያደርገናል። ካልሆነ ግን መጥፎ ባህሪና መጥፎ ስራ በዱንያም በአኼራም የበታች ያደርገናል። ስለዚህ መጥፎ ባህሪና መጥፎ ስራ እንዳይኖርብን ሁሌም እራሳችንን እንፈትሽ  ትንሽም ቢሆን ካለብን ከወዲሁ በመልካም እናስተካክለዉ ።            መልካምነት ለራስ ነዉ ✅ https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

እንደ ወርቅ ዉድ መሆን ከፈለግሽ/ህ እንደ ድንጋይ በየቦታዉ አትገኚ/ኝ

قال الإمام بن القيم رحمه الله أغبى الناس من ضل في أخر سفره وفد قارب المنزل ከሰዎች ይበልጥ ሞኝ ማለት (ጉዞ ወቶ) በጉዞዉ መጨረሻ ላይ ወደ መዳረሻዉ ከቀረበ በኋላ መንገድ የሳተ ግለሰብ ነዉ :: አል ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉ الفوائد ١٠٧ አሏህ የመንገዳችንን መጨረሻ ያሳምረዉ

Repost from N/a
ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ ማስታወቂያዎችን በአንድ ቻናል ላይ በነጻ ማስተዋወቅ እንዲሁም ስራ ለማግኘት ከፈለጉ Halal Jobsን ይቀላቀሉ!👇
ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ ማስታወቂያዎችን በአንድ ቻናል ላይ በነጻ ማስተዋወቅ እንዲሁም ስራ ለማግኘት ከፈለጉ Halal Jobsን ይቀላቀሉ!👇

ሰውን በእውነት ለማወቅ ከፈለግክ፣ አብረኸው ተጓዝ፤ ጉዞ እውነተኛ ባህሪውን ያሳያል። አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

ዐብዱረሕማን አልአውዛዒይ (157 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:- اصْبر نفسك على السُّنَّة، وقفْ حيثُ وقفَ القوم، وقُلْ بما قالوا، وكفّ عمَّا كفّوا
ዐብዱረሕማን አልአውዛዒይ (157 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:- اصْبر نفسك على السُّنَّة، وقفْ حيثُ وقفَ القوم، وقُلْ بما قالوا، وكفّ عمَّا كفّوا عنه، واسْلك سبيل سلفك الصَّالح، فإنَّهُ يسعك ما وسعهم “እራስህን በሱና ላይ አፅና፡፡ ሰዎቹ (ሶሐቦቹ) ከቆሙበት ቁም፡፡ እነሱ ያሉትን በል፡፡ ከታቀቡት ታቀብ፡፡ የመልካም ቀደምቶችህን መንገድ ተከተል፡፡ ለነሱ የበቃቸው ይበቃሀልና!” = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የድሮ ስርዓት ናፋቂው የከላላ ከተማ ከንቲባው ህገ ወጥ እስርና ወከባ! የከላላ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ ጥላሁን የክርስትና እምነት ተከታይ ናቸው። ከላላ በአብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ያለበት ከተማ ቢሆንም የህዝበ ክርስቲያኑ መብት ተከብሮ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በተቃራኒው በሙስሊሙ ማህበረሰብ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የኢስላማዊ ዳዕዋ ይዘትን ጭምር ካልወሰንኩና ለምን ዳዕዋ ታደርጋለህ በሚል  ከንቲባው የመጅሊስ አባል የሆነውን ወንድም ኢዘዲን ሻፊን አስሮና አስፈራርቶ ከለቀቀው በኋላ በድጋሜ ሌሎት 5:00 አፍነው ለመውሰድና ለመግደል ሙከራ ቢያደርጉም አልሳካላቸው ሲል የከለላ ከተማ መጅሊስ ም/ኃላፊ የሆነውን ሸህ ሙሀባ ሰኢድን አስረውት የወገኛሉ። የከተማው ከንቲባ ይህንን ኢህገመንግስታዊ፣ አሳፋሪና ህዝብን የሚያቃቅር ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ሸህ ሙሀባ ሰኢድን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቁት እንጠይቃለን! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትም በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አመራር ጋር በመነጋገር መሠል ድርጊቶችን እንዲቃወምና የወንድማችንን መብትና የመጅሊስ ክብር እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን። ከከላላ ሙስሊሞች

ስለ ጀርህ ወተዕዲል ኡለሞች ምን አሉ‼️ ======================= [ ለዚህ ነገር አቅሜ ስለማይፈቅድ የኡለሞችን ንግግር ብቻ ነው የማስቀምጠው] በዚህ ፅሁፍ ኢንሻ አላህ ስለ ጀርህ ወተዕዲል ኡለሞች ምን እንዳሉ እያንዳንዱን እያነሳሁ ለማሳየት እሞክራለሁ። በአላህ ፍቃድ!። እኔ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለስሜቴ የገጠመልኝን ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኡለሞች ያሉትን ለማንሳት ሙከራ አድርጌያለሁ። የኡለሞቹን ንግግር ከታች ባስቀመጥኩት የ"YouTube" ሊንክ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ። ቪዲዮን ለመላክ ሞክሬ ነበር ነገር ግን እምቢ ስላለኝ ትቼው በሊንክ አስቀምጬዋለሁ። አረቢኛውን እየፈጠንኩ ስለፃፍኩት አንዳንድ የቃላት ስህተት ሊኖረው ይችላልና አትውቀሱኝ። ይሄው እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፦ ١. علم الجرح والتعديل العلامة صالح بن عبدالله الفوزان حفظه الله التأصيل العلمي عند السلف الصالح محاضرة https://youtu.be/zml7VmSdYZ8 ٢. من يتكلمون في الدعاة بحجة الجرح والتعديل- العلامة صالح الفوزان حفظه الله https://youtu.be/aqarKB25HlE ٣. قاعدة الجرح والتعديل- العلامة صالح الفوزان حفظه الله في شرح كتاب تفسير القران الكريم https://youtu.be/MRylYH6Qh6E ٤. حكم الجرح والتعديل في هذا العصر للشيخ ابن عثيمين رحمه الله هل سنة الجرح والتعديل ماتت؟ وما حكم الرد على المخالف؟ https://youtu.be/v0SS5PQqHIg ٥. موقفنا من إختلاف العلماء في الجرح والتعديل؟؟ "إذا اختلف بعض من الدعاة في تجريح شخص أو تعديله؛ يعني: بعض الدعاة عدل والبعض الآخر جرح، هل يلزم من ذالك تجريح من عدل؟ جواب الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله https://youtu.be/HjvrEDC7FnI ٦. وصية الشيخ الألباني لطلبة العلم أن لا يضيعو أوقاتهم في نقد بعضهم بعضا فلان كذا وفلان كذا !!! كلام قمة الروعة رحمك الله يا شيخنا الألباني وجمعنا بك في الفردوس الأعلى https://youtu.be/yyocixKbAfw ٧. غلو بعض الطلاب والشباب في الجرح والتعديل وتحذير - للشيخ الوالد فلاح بن إسماعيل مندكار - رحمه الله تعالى https://youtu.be/PQIneXOyqXE ٨. مسألة مهمة في الجرح والتعديل- الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله تعالى https://youtu.be/KwPQHHlEtGg ٩. سؤال: إذا اختلف العلماء في جرح شخص أو تعديله ماذا يفعل المقلدون؟ جواب الشيخ عبدالمحسن العباد حفظه الله https://youtu.be/7fpKz3QNfbo ١٠. بيان ضوابط الجرح والتعديل ودفاع عن العلامة محمد بن هادي للشيخ محمد بازمول حفظهم الله https://youtu.be/r7GMY1e3zN0 ١١. هل صحيح أن علم الجرح والتعديل انتهى وأن هذا الباب قفل؟ الشيخ أحمد بازمول حفظه الله https://youtu.be/trRHE12RcEw ١٢. نصيحة مهمة حول الجرح والتعديل و ردود السلفيين بعضهم لبعض! الشيخ صالح السحيمي حفظه الله تعالى https://youtu.be/tOkmCSswPNs ١٣. فتاوى الوالد الشيخ عبدالمحسن العباد حفظه الله تعالى عن الجرح والتعديل https://youtu.be/yeSNHJ4rr50 ١٤. حكم الجرح والتعديل للدعاة وطلبة العلم عن طريق وسائل التواصل الإجتماعي؟ لفضيلة الشيخ عبدالعزيز آل الشيخ حفظه الله https://youtu.be/ytIEENpyhwo ١٥. حكم التقليد في الجرح والتعديل - الشيخ عبدالعزيز الريس حفظه الله https://youtu.be/15cqC3dXXkE ١٦. منهج الجرح والتعديل للشيخ مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله تعالى https://youtu.be/Yvfe_zfPmqs ١٧. سؤال مهم جدا عن الجرح والتعديل- العلامة عبدالعزيز بن باز رحمه الله تعالى https://youtu.be/vursG6tSpXY ١٨. فتنة الجرح والتجريح للرد على من صار شغلهم الشاغل الطعن في الدعاة والعلماء واصطياد زلاتهم -العلامة المحدث محمد ناصر الدين الألباني -رحمه الله تعالى https://youtu.be/k9j4I8MULcU ١٩. إذا كان الرد من باب الجرح والتعديل فهو واجب شرعي - الشيخ العلامة محمد امان الجامي https://youtu.be/wguAUPfkDjQ ٢٠. حقيقه الجرح والتعديل لفضيلة الشيخ المحدث صالح اللحيدان حفظه الله تعالى https://youtu.be/l8dyoqKWlDw ٢١. شهر بن حوشب وبيان حاله علماء الجرح والتعديل- للعلامة محمد بن آدم الإتيوبي رحمه الله تعالى https://youtu.be/fAXaFCer7p4 ٢٢. كلام مهم جدا.....الفرق بين الجرح والتعديل والغيبة الشيخ محمد سعيد رسلان حفظه الله تعالى https://youtu.be/t9wnGgyxb9w الدرس تعارض الجرح والتعديل https://youtu.be/c_PVcUD373E ~~~~~ ይህን ፅሁፍ "ለዛ ሰፈር ሰዎች አድርሱ" ምናምን አልልም። ብቻ ዋናው የኡለሞችን ሀሳብ መሠረት እያደረግን በዛ ብንጓዝ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ወሏሁ አእለም! ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ https://t.me/Daru_Sunnah https://t.me/Daru_Sunnah

🔊 الدروس الصوتية 🔊 ▪️دروس الحديث 1. شرح رسالة أبي داود إلى أهل مكة في وصف سننه 2. شرح بلوغ المرام 3. شرح كتاب الصيام من اللؤلؤ والمرجان فيما اتفق عليه الشيخان 4. شرح الأربعين النووية وتتمة ابن رجب 5. شرح ألفية السيوطي في علم الحديث 6. شرح عمدة الأحكام من كلام خير الأنام 7. شرح سنن ابن ماجه 8. شرح سنن الترمذي 9. شرح سنن النسائي 10. شرح سنن أبي داود 11. شرح صحيح مسلم 12. شرح صحيح البخاري (الجديد 1431ه‍ـ-1441ه‍ـ): 13. شرح موطأ الإمام مالك ▪️دروس الفقه 14. شرح شروط الصلاة وأركانها وواجباتها 15. الإختيارات الفقهية من فتاوى الشيخ عبد العزيز بن باز: -أ- كتاب الزكاة -ب- كتاب الصيام 16. شرح كتاب آداب المشي إلى الصلاة 17. تبصير الناسك بأحكام المناسك - عام 1429هـ ▪️دروس العقيدة 18. شرح الصدور بتحريم رفع القبور 19. شرح مقدمة رسالة القيرواني 20. شرح كتاب تطهير الاعتقاد من أدران الإلحاد ▪️محاضرات عامة 21. المحاضرات العلمية والتوجيهات المنهجية ا〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 إذا واجهتك أي صعوبات في الصوتيات تفضل بزيارة هذه الصفحة: اضغط هنا ا〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

Repost from ፈዋኢድ
አህባሾች ኢብኑ ተይሚያን ከሚከሱበት ነጥብ አንዱ ጀሀነም(ጀነት አላልኩም) ትጠፋለች ብሏል ሚለው ነው። ኢብኑ ተይሚያ በፈታዋቸውና በሌሎችም ኪታቦቻቸው ጀሀነም እንደማትጠፋ በግልፅ ያስቀምጣሉ። አህባሾቹ ክሳቸውን ከሚወስዱባቸው ኪታብ መካከል ቀጣይ ከታች ያለችው ሪሳላ ነች። ሚገርመው በኪታቡ ኢብኑ ተይሚያ ጀሀነም ትጠፋለች ሚለው ቀውልን ነው ረድ ያደረጉበት። በመፅሀፋ በተወሰነው ክፍል የዚህን ቀውል ባለቤቶች መረጃ ስለዘረዘሩ ብቻ የእሳቸውም ቀውል ነው ብለው እንደመረጃ ያመጣሉ። (በምን እንክሰሳቸው ነው እንግዲህ 😆😆) ከሰለፎችስ ይህ ቀውል አልተገኘም? ቢድዐ ነው? ሚለውን መመልከት ይቻላል። በተጨማሪ መስዐላው በሸርህ ጠሀዊያ በጥሩ ሁኔታ ተብራርቷል። እንድታነቧት እጋብዛለው። ከስር ዳውንሎድ ማድረግ ትችላላችሁ https://t.me/fewaidabdurazaq/10

አዎ እንቁጣጣሽ በዓላችን አይደለም! ~ እንደ ሙስሊም እንቁጣጣሽን ማክበር አይፈቀድም። ይሄ አጉል ማክረር ጋር የሚገናኝ ነገር አይደለም። አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ግን ማክበር ያለብንንና የሌለብንን በዓላት ሊመርጡልን ይፈልጋሉ። አክራሪነት ማለት በሌሎች እምነት ውስጥ ዘው ብሎ በመግባት የእምነታችሁን ህግጋት ካላሰመርንላችሁ፣ እኛን ካልመሰላችሁ ማለት ነው። አንዳንዶቹ ሳዑዲ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ያከበረችበት ነው እያሉ ፎቶ ይቀበላሉ። ማስረጃ ማቅረባቸው ነው በነሱ ቤት። ሸሪዐዊ ህግጋትን የምንወስደው ከቁርኣንና ሐዲሥ እንጂ ከሳዑዲም ይሁን ከሌላ ሃገር አሰራር፣ ወግና ልማድ አይደለም። የመውሊድም ጊዜ በያመቱ ተመሳሳይ ከሸረሪት ድር የደከሙ "ማስረጃዎችን" የሚለቃቅሙ አሉ። የሆነ ጊዜ መካ ካለው አብራጀ ሳ0ህ ላይ የረቢዕን መግባት ተከትሎ መብራት ለቀዋል መውሊድን ማክበር ጀመሩ ይላሉ። የሆነ ጊዜ እለቱን በካላንደር ዝግ እንደሆነ አሳወቁ ይላሉ። የሆነ ጊዜ ከዓመታዊ የዲን ትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲራ የሚመለከተው ክፍል በረቢዕ ወር ላይ መደልደሉ መውሊድን ማክበር መጀመራቸውን ያሳያል ይላሉ። ወደፊትም የሆነ መንጠላጠያ መፈለጋቸው አይቀርም። ከዚህ ሁሉ መንጠላጠያ ፍለጋ ኋላ ያለ አንድ ብልሹ እምነት አለ። በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሳዑዲን መንግስት ነው የሚከተሉት የሚል እምነት አላቸው። ይሄ ራሳቸው ጮኸው ራሳቸው ያመኑት ባዶ ሙግት ነው። አንዳንዶቹ በግልፅ በመምጣት "እናንተ ዘንድ የሳዑዲ መንግስት ሐላል ያለውን ሐላል፣ ሐራም ያደረገውን ደግሞ ሐራም ታደርጋላችሁ" የሚል የለየለት ቅጥፈት ያራግባሉ። ይህንን ውሸት ደጋግመው በማስተጋባታቸው የተነሳ አንዳንድ የዋሆች እውነት እስከሚመስላቸው ደርሰዋል። ለማንኛውም መመሪያችን ቁርኣንና ሐዲሥ ብቻ ነው። የሳዑዲ መንግስት ሐላል ያለውን ሐላል፣ ሐራም ያደረገውን ደግሞ ሐራም አድርጎ የሚያምን አንድ ሙስሊም የለም። አንድ እንኳ! ሲጀመር በዚህ መልኩ እያመኑ ሙስሊም መሆን አይቻልም። እንኳን የሳዑዲ መንግስት፣ የሳዑዲ ዑለማኦች እራሱ የሐላል ሐራም መወሰኛ አይደሉም። በዚህ መልኩ የሚያምን ሰው ሙስሊም ሊሆን አይችልም። ወደተነሳሁበት ነጥብ ስመለስ በኢስላም የሌሎች እምነት በዓላትን ማክበር ቀርቶ "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት አይፈቀድም። ይሄ ኢጅማዕ ያለበት ጉዳይ ነው። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ وأما التهنئة بشعائر الكفر المختصة به فحرام بالاتفاق، مثل أن يهنئهم بأعيادهم وصومهم، فيقول: عيد مبارك عليك، أو تهنأ بهذا العيد ونحوه، فهذا إن سلم قائله من الكفر فهو من المحرمات، وهو بمنزلة أن يهنئه بسجوده للصليب، بل ذلك أعظم إثمًا عند الله، وأشد مقتًا من التهنئة بشرب الخمر وقتل النفس وارتكاب الفرج الحرام ونحوه " የበክህ ^ደት (ኩ^ፍር) ሃይማኖታዊ መገለጫዎችን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ ማለት በዑለማኦች ሙሉ ስምምነት ሐራም ነው። ይኸውም በበዓሎቻቸውና በጾማቸው ወቅት እንኳን አደረሳችሁ በማለት፤ ለምሳሌ፦ 'መልካም በዓል ይሁንልህ' ወይም 'በዚህ በዓል ደስ ይበልህ' እና የመሳሰሉትን አባባሎች በመጠቀም ነው። ይህን ያለው ሰው ራሱ ከኩ ^ፍር ቢተርፍ እንኳ፣ ድርጊቱ ከሐራም ነገሮች አንዱ ነው። ይህም ልክ ለመስቀል ሲሰግድ 'እንኳን ሰገድክ' ብሎ ደስታውን እንደመግለጽ ያህል ነው። እንዲያውም ይህ በአላህ ዘንድ አልኮል መጠጥ በመጠጣት፣ ነፍስ በማጥፋት እና ዝሙት በመፈጸም እንኳን ደስ አለህ ከማለት የከበደ ወንጀልና የከፋ ቁጣን የሚያስከትል ነው።" [አሕካሙ አህሊ ዚመህ፡ 1/205] (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

✅ ቁጣን (በቀልን) መተዉ ያለው ትሩፋት! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن كَظَمَ غيظًا وهو قادرٌ على أن يَنْفِذَه دعاه اللهُ عزَّ وجلَّ على رؤوسِ ا
✅ ቁጣን (በቀልን) መተዉ ያለው ትሩፋት! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن كَظَمَ غيظًا وهو قادرٌ على أن يَنْفِذَه دعاه اللهُ عزَّ وجلَّ على رؤوسِ الخلائقِ يومَ القيامةِ حتى يُخَيِّرُه اللهُ مِن الحُورِ ما شاءَ.﴾ “ቁጣውን ለመወጣት (ለመበቀል) አቅም እያለው ቁጣውን የዋጠ ሰው፤ አላህ (🤍) በቂያማ እለት በሕዝቦች ሁሉ ፊት ይጠራዋል፤ ከሁር አል-አይን (ከጀነት ሴቶች) ያሻውን መርጦ እንዲያገባ ምርጫ ይሰጠዋል።” 📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 4777 🟧🟧🟧🟧🟧🟧🟧 🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

አልተፈታም ህልሜ /=====================/ አንደበቴ አፍታቶ ሲሳነው መናገር፡ ጊዜው ተራመደ ሳልሰራ ቁም ነገር፡ ጎዳናው ጠፋብኝ ካደባባይ ቆሜ፡ ዲብቅ ሚስጥር ሆኖ ሳይፈታ ህልሜ፡ ኑሮ ትርጉም ሲያጣ ሲሆን እንቆቅልሽ፡ አነባሁ አምርሬ ህይወት አዘንኩብሽ፡ ሳልኖር እየኖርኩኝ ሳያመኝ ታምሜ፡ አለሁ እስከ ዛሬ አልተፈታም ህልሜ፡ _ ውስጤ እየተከፋ አንጀቴ እያረረ፡ ለሰወች እያልኩኝ የግል ሀሳቤ እየተቀየረ፡ እንደ እኔ አስተሳሰብ ህይወት መች ተኖረ፡ በበቂ ምክንያት ችግር ሆኖ ይፋ፡ እኔ እያለቀስኩኝ ሰው እንዳይከፋ፡ በሀሳብ ማዕበል ውስጤ እየተገፋ፡ የነገን እያሰብኩ አለሁኝ በተስፋ፡ ሀሳቤ ነበረ እምነቴን ማስፋፋት፡ ጀግና ወጣት መሆን ጥንቁቅ ከኹኀራፋት፡ በፍቅር ለመኖር የፍቅር ሰው ሆኘ፡ አዕምሮየ አስቦ ልቤ እንደተመኘ፡ ሆነብኝ በዐክሱ ዛሬ ምን ተገኘ፡ ተስፋ አልቆርጥም ዛሬም ምኞቴ ይሳካል፡ የዛሬው መከፋት በደስታ ይተካል፡ ውስጠቴ ንፁህ ነው እያልኩ አስባለሁ፡ አላህ እስከሚሻ በተስፋ እኖራለሁ፡ ተውሒዲ ሱናን ይዠ ምን ያስጨንቀኛል፡ የውስጥ ስሜቴ አይዞህ ይለኛል፡ ጓደኛ ቢጠፋም ውስጤ ያፅናናኛል፡   ውስጤ ይመክረኛል፡  እንዲህም ይለኛል፡ የትናንት ወዳጂህ ዛሬ ቢሆን ባዳ፡ በየ ደረሰበት ስላንተ መጥፎነት ወሬውን ቢነዳ፡ ቆም ብለህ አስብ አሰታውስ ያላህን ቃል፡ በእምነትህ ጠንክር ሀዘንህ ይርቃል፡ ትክክል ነህ በነገር መወጋት ያማል! ያስጨንቃል ልብንም ያደማል! ግን ከወሬኞች በላይ አንተ ራዕይ አለህ፡ እነርሱ ሲያወሩ አንተ ተለይተህ፡ ለአላማህ ስራ የተግባር ሰው ሆነህ፡ የነገረኞች ቃል እንደ እሬት ቢመርም፡ ለሚጮኸው ሁሉ አይወረወርም፡ ዛሬ ያስተከዘህ ነገ ላይ ይፈካል፡ አብሽር አትጨነቅ ምኞትህ ይሳካል፡  ኢንሻ አላህ አብሽር ጠንከር በል ራስህን አፅናና፡ ከጌታህ በስተቀር ባይተዋር ነህና፡ ሰው ያለውን ይበል በተውሒዲህ ፅና፡ የልቤ ትርታ ይህንን ሲመክረኝ፡ እኔም ተረጋጋሁ ውስጤንም ደስ አለኝ፡ ትልቅ ተሰፋን ጫንኩኝ ከሀዘን ርቄ፡ በወደፊት እቅድ ደስታየን ናፍቄ፡ ህልሜ እውን ይሆናል ቆርጨ ወሰንኩኝ፡ አዛኙን ጌታየን እየተማፀንኩኝ፡ ነገር ግን ዛሬ ላይ! በወደፊት ህልሜ እጂጉን ብደሳም፡ በአላህ ተወክየ እንደሚስተካከል ወስኘ ብነሳም፡ ፈተናወች በዝተው ብተኛም ታምሜ፡ በችግሬ ጊዜ ቢርቀኝ ወንድሜ፡ ተስፋ አልቆርጥም እንጂ አሁን ባለሁበት  አልተፈታም ህልሜ፡ 17- 07- 2011 አ.ል (ኑረዲን  አል_አረቢ)

♦️♦️♦️እህቶች በግዜ አግቡና ወለዱ አላህ መልካሙን ባል ይውፍቃችሁ በታሪኩ ተማሩ 📌‏قال الشيخ أحمد بن يحيى النجمي رَحِمهُ الله : فَالْمَرأَة مَهْمَا حَصَلَ لَهَا مِن شَهَادَاتِ ، فَإِنَّ الْحَيَاة لا تطيب لَهَا إلا بالبنين والبنات ، ولقد سمعت أَنَّ امرأة دَرَسَتْ وتَدَرَّجَتْ فِي الشَّهَادَاتِ حَتَّى أخذت أعلاها ، وفي النهاية قالت : خُذُوا شَهَادَاتِي كُلها ، وأعطوني طفلاً ألاعبه . ولقد خلق الله النساء ليكُنَّ أُمَّهَاتِ مُرَبَيِات وحاضنات ماهرات ، فَإِذَا خَرَجَت عن هذه الوظيفة وتركتها ؛ ندمت بعد ذلك ، وحنت إليها بعد أن ذَهَبَ الزَّمَن وبَلِيَ الشباب ، فالله الْمُسْتَعَان. ሴት ምንም ያህል ትምህርት ብትማርና ብዙ የትምህርት ዲግሪዎችን ብታገኝም፣ ሕይወቷ ያለ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ሙሉ በሙሉ ደስተኛ አይሆንም። አንዲት ሴት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምራ በትምህርት ደረጃዎች ሁሉ እየተማረች እስከ ከፍተኛው የትምህርት ድረስ እንደደረሰች ሰምቻለሁ። በመጨረሻም እንዲህ አለች፦ “ሁሉንም የትምህርት ዲግሪዎቼን ውሰዱ፤ እኔ ግን የማጫውተውና የምንከባከበው አንድ ሕፃን ስጡኝ።” አላህ ሴቶችን እናቶች፣ ልጆቻቸውን በመልካም ሥነ-ምግባር የሚያሳድጉ አስተማሪዎችና ብቁ አሳዳጊዎች እንዲሆኑ ፈጥሯቸዋል። ስለዚህ ሴት ከዚህ የእናትነትና የልጆችን የማሳደግ ተፈጥሯዊ ሚናዋ ብትወጣና ብትተወው፣ በኋላ ትጸጸታለች። ጊዜው ካለፈ፣ ወጣትነቷም ካለቀ በኋላ ወደዚያ ሚና ትናፍቃለች። አላህ ረዳታችን ይሁን። 📚 تأسيس الأحكام (ج ٢ ص ٣١٢). አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

ይቅርታ! ሰዎች ሲበድሉን፣ ይቅርታ ሲጠይቁን «ለምን ወዲያው ይቅር አልኳቸው?» እያልን ራሳችንን እንወቅሳለን። ጤናማና ሰብአዊ ስሜት ያለው አእምሮ እንኳ ሳይቀር የጥፋተኛውን ይቅርታ ወዲያውኑ መቀበል አቅቶት ሲቸገር ይስተዋላል። ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት የጥፋቱ ስሜት ከቃሉ ይልቅ በውስጣችን ጥሎት ያለፈው ቁስል ከባድ ስለሆነ ነው። የጥፋቱ ስሜት ውስጣችንን እንዲህ ይጎዳዋል፦ መተማመን ሲሰበር በሰዎች ግንኙነት ውስጥ ዋጋው ከፍተኛው ነገር መተማመን ነው። አንድ ሰው ሲበድለን፣ የጥፋቱ ክብደት ብቻ ሳይሆን ያመነበትና የተመካበት ልባችን መክዳቱ ዋነኛው ጉዳት ነው። ይቅርታ መጠየቅ የጠፋውን ነገር በቅጽበት መልሶ መገንባት አይችልም። መተማመን እንደ አበባ ቡቃያ ነው፤ ጊዜ፣ እንክብካቤ እና ታጋሽነት ይፈልጋል። የተፈጠረው ክፍተት እና ድካም እያንዳንዱ ስህተት እና በደል በሰው ልብ ላይ የስነ-ልቦና ድካም ይፈጥራል። «ለምን እንዲህ አደረገ?» የሚለው ጥያቄ፣ ያሳለፍነው መመረር እና ውስጣዊ ጭንቀት አእምሯችንን ያደክሙታል። ይቅርታን ለማድረግ ሲሞከር እንኳን ውስጣችን ዝግጁ የሚሆነው ያ የደረሰን ድካም ሲቀልና አዕምሯችን እረፍት ሲያገኝ ነው። ጊዜን የሚጠይቅ የፈውስ ሂደት ቁስል ሲነካ ወዲያው እንደማይድን ሁሉ፣ የልብ ስብራትም የራሱ የሆነ የፈውስ ጊዜ አለው። ይቅርታ የሚጠይቅ አካል «ይቅርታ አድርግልኝ» ሲል፣ የተበዳዩ አካል ውስጣዊ ሰላም ግን ወዲያውኑ ሊመለስለት አይችልም፤ ልቡ የደረሰበትን ጉዳት አብጥሮ ለማየትና ያንን ስሜት ለማስተናገድ ጊዜ ይሻል። ይህ ሁሉ ሆኖ፣ ይቅርታ ማድረግ የደካሞች ሳይሆን የጠንካሮች መለያ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ያንን ይቅርታ ከመቀበል በፊት ውስጣችንን ማዳመጥ ቅንጦት ሳይሆን የግድ የሚል ፍላጎት ነው። ቁስሉ ሳይደርቅና ውስጣችን ሳይረጋጋ የሚሰጥ ይቅርታ ባዶ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም፣ ይቅርታችሁን ከመቀበል በመዘግየታችን እንዳያማችሁ—እራሳችንን እስከምናስታግስ እንጂ ይቅርታችሁን ሳንቀበል አንቀርም። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida