ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

الذهاب إلى القناة على Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
899
المشتركون
-124 ساعات
-177 أيام
+3530 أيام
أرشيف المشاركات
تفصيل حول العذر بالجهل شيخ و اقامة الحجة صالح ال الشيخ ዑዝር ቢል ጀህል እና ሁጃ ማቆምን በተመለከተ በሸይኽ ሳልህ አል ሸይኽ

⚠️እውነት የአረበ ሀገር ሴትን የሚያገባ ቤተሰቡ የረገመው ነውን?!! በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በአረብ ሀገር  የሚለፉና የሚደክሙ እህቶቻችንን በማንኳሰስ፣"አረብ ሀገር ያለች ሴትን ከማግባት 1000 ዓመት ያለ ሚስት መኖር ይሻላል" ወይም "የቤተሰብ እርግማን ያለበት ሰው ነው ሳውዲ የነበረችን ሴት የሚያገባው" የሚሉ አሳፋሪና የባለጌ ንግግሮችን እያየን ነው። ይህ ንግግር የሴቶቹን ማንነት ሳይሆን፣ እንዲህ የሚሉትን ወንዶች ማንነትና የሞራል ዝቅጠት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ⚠️ማወቅ ያለባችሁ... የአረብ ሀገር ሴት ማለት የኡማው ኩራትና የቤተሰብ ደጀን ናት! እነዚህ እህቶቻችን እኮ በለጋ ዕድሜያቸው የራሳቸውን ደስታ መስዋዕት አድርገው፣ በሰው ሀገር ብርድና ፀሐይ እየተገረፉ፣ የናፍቆትና የብቸኝነት ሰቀቀን እየበላቸው ቤተሰቦቻቸውን ከድህነት ያወጡ የቁም ጀግኖች ናቸው። ስንት እናትና አባት ዛሬ በገዛ ቤታቸው በክብር የሚያርፉት በእነዚህ እህቶች ላብ አይደለምን? ስንት ታናናሽ ወንድሞችና እህቶች ትምህርታቸውን ጨርሰው ለቁም ነገር የበቁት በእነሱ ድካም አይደለምን? ስንት ቤተሰቦች ከሽርክ አረንቋ ተላቀው የተውሒድን ብረሀን ያዩት በነሱ አይደለምን? የሚገርመው ደግሞ፤ ስልክ ተሞልቶለት፣ በልቶና ለብሶ፣ በሳውዲ ብር እየተንቀሳቀሰ መልሶ እነዚህኑ እህቶች የሚዘልፍ ወንድ ማየት የታላቅ "ውለታ ቢስነት" ጥግ ነው። የሳውዲን ብር እየበላህ፣ የሳውዲን እህት የምታጥላላው አንተ ነህ እንጂ "የተረገምከው"፤ እሷማ የጽናትና የጀግንነት ተምሳሌት ነች። ⚠️ የአረብ ሀገር ሴት በኸይር ስራ ላይ ቀዳሚ ነች! አዎን! የሰው ልጅ በመሆኗ ጎደሎ ሊኖርባት ይችላል። ነገር ግን ሐቁን እንነጋገር ከተባለ፤ በየትኛውም የኸይር ቦታ፣ መስጂዶች ሲገነቡ፣ ለተቸገሩት እርዳታ ሲሰበሰብ፣ ኡለሞችና መድረሳዎች ሲደገፉ ቀዳሚዎቹ እነዚህ በእንባና በላብ የቆጠቡት እህቶቻችን ናቸው። እነሱ ለዲናቸው ያላቸው ቀናኢነትና ለጋስነት ከብዙ "አውቃለሁ" ባይ ወንዶች ይበልጣል። እነሱ ልባቸው ለዲን፣ እጃቸው ደግሞ ለሰደቃ የተዘረጋ ንጹህ ነፍሳት ናቸው። እንዲህ ያለችውን ምርጥና ለጋስ ሴት በንቀት ዓይን መመልከት የእራስን ድንቁርና ማወጅ ነው። ⚠️ በጥቅሉ ስለ ሴት ልጅ ክብር ኢስላም ምን ይላል? የዓለማቱ እዝነት ነቢዩ መሐመድ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ሴቶችን በክብር እንድንይዝ፣ አደራቸውን እንድንጠብቅና ልባቸውን እንዳንሰብር በተደጋጋሚ አዘዋል። ሴት ልጅ አደራ ነች፤ አደራን የሚያከብር ደግሞ የከበረ ወንድ ብቻ ነው። ሴት ልጅን የሚያዋርድና ክብሯን በአደባባይ የሚገፍ ወንድ ወንድነቱ ጎደሎ ነው። እውነተኛ ወንድነት የሚለካው ሴት ልጅን በሚከፍሏት መስዋዕትነት በማድነቅና ለድካሟ እውቅና በመስጠት እንጂ፣ በቁስሏ ላይ ጨው በመነስነስ አይደለም። 🌹 ውድ የስደት ጮራዎች የሆናችሁ እህቶቻችን! በነዚህ ባለጌዎች ንግግር ልባችሁ አይሰበር። የእናንተን ዋጋ የሚያውቀው አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ነው። እናንተ ለቤተሰባችሁ በረካ፣ ለሀገራችሁ ኩራት ናችሁ። ዛሬ በናንተ ላይ የሚሳለቁት ወንዶች ነገ አቅጣጫ ሲጠፋቸው የሚፈልጉት የእናንተን የጽናት ጥላ እንደሆነ አትጠራጠሩ። ጽናታችሁ ይበልጥ ይጥነክር፣ ክብራችሁንም በአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ዘንድ ጠብቁ። ⚠️ሁሉም ወንድ ሊያውቅ የሚገባው  የተኛዋም ሴት አረብ ሀገር ሂዳ ለመስራት ያስገደዳት የኔ ያንተ የሁላችንም ወንዶች ደካማነት ነው እኛ ጠንክረን ሰርተን እነሱን ማስተዳደር መሰተር የቤተሰቦቻችንን ችግር መቅረፍ ብንችል ኖሮ እነዚህ ሴቶች ያልተፈቀደላቸውን ስደት ሂደው ባልሰሩ ለብዙ ፈተናዎችና ችግሮች ባልተዳረጉ ነበር ስንቱ አልጫ ወንድ ነው ሚስቱን ስደት ልኮ ተኝቶ ሲቅምና ሲበላ የሚዉለው በሷ ጉልበት ስንቱ ጨካኝ ቤተሰብ ነው ልጁ ወደ ሐገሯ ተመልሳ አግብታ ወልዳ የራሷን ኑሮ እንዳትመሰርት ይሄን ሳታደርጊ ይሄን ሳትሰሪ አትምጭ የሚሉ ስንት አረመኔ ወንድሞቼ አሉ በእምነት ቤት ስራልኝ ሀገሬ ስገባ መቋቋሚያ የሚሆነኝ ነገር አድርግልኝ ብላው ብሯን ቅርጥፍ አድርጎ በልቶ አላቅሽም የሚል  ስንቱ አልጫ ወንድ ነው ቤቱ ተቀምጦ የአረብ ሀገር ሴትን እየለመነ ኑሮውን የሚመራ ... እረ ብዙ አታሶሩኝ ለማንኛውም እነዚህ ሴቶች ስደት ለመሄዳቸው የአንድ አባት የአንድ ወንድም የአንድ አጎት የእንድ ባል የአንድ ልጅ ተጠያቂነት አለበት ይሄንን ሁላችንም ልናውቀው ይገባል። ..........ይቀጥላል?!! ያ አላህ! በሰው ሀገር የሚለፉትን እህቶቻችንን አንተ በያሉበት ጠብቅልን። ድካማቸውን ሐሰናት አድርገህ ጻፍላቸው። ለእነሱ የሚገባውን ክብርና ፍቅር የሚሰጥ፣ በሐቅ የሚወዳቸውና የሚንከባከባቸውን ሷሊሕ ትዳር ለግሳቸው። እነዚህን አቃላይ ወንዶችንም ልቦና ይስጣቸው፤ ካልሆነም ከእህቶቻችን መንገድ ያርቅልን። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

الشيخ محمد بن عبد الله الإمام هو أحد أبرز علماء ودعاة المنهج السلفي المعاصرين في اليمن. يُعرف بجهوده الكبيرة في التدريس والتأليف، وهو مؤسس ومدير "دار الحديث"في مدينة مَعْبَر (التابعة لمحافظة ذمار في اليمن). إليك أبرز المعلومات عن مسيرته العلمية والدعوية: نشأته وتعليمه፡ ١. بدأ طلب العلم في وقت مبكر، ويُعد من أبرز وأكبر تلامذة الشيخ المحدث مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله (مؤسس دار الحديث #بدماج ومجدد الدعوة السلفية في اليمن). رحل إلى الشيخ مقبل ولازمه لفترة طويلة، وأجازه الشيخ وأثنى عليه وعلى علمه وحرصه. دوره الدعوي (دار الحديث بمعبر) أسس الشيخ محمد الإمام مركزاً علمياً كبيراً في مدينة مَعْبَر عُرف بـ "دار الحديث". يُعد هذا المركز حالياً من أكبر المراكز العلمية في اليمن، حيث يقصده #آلاف الطلاب من داخل اليمن وخارجه لتعلم القرآن الكريم، والحديث النبوي، والعقيدة، والفقه، واللغة العربية. منهجه ومؤلفاته: المنهج: يُعرف الشيخ بتمسكه بالمنهج السلفي، ويركز في دعوته على طلب العلم الشرعي، والابتعاد عن الحزبية والسياسة، والاهتمام بتعليم العوام وتربية الطلاب على الكتاب والسنة بفهم السلف الصالح. كما عُرف بمواقفه الداعية للصلح وحقن الدماء في فترات النزاع. المؤلفات: له إنتاج علمي غزير جداً، حيث صنف عشرات الكتب والرسائل في مختلف العلوم الشرعية (كالعقيدة، والفقه، والحديث، والآداب، والردود العلمية).

ብቻ አላህ አይርሳህ! ስምህ በታሪክ መዝገብ ውስጥ መስፈር አለመስፈሩ አያስጨንቅህ። እሱ የስኬት መስፈርት አይደለም። አላህ መርጦ ከላካቸው ነብያት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው ስማቸው ለታሪክ የቀረው? ከጥቂትም በጣም ጥቂት! ጠቢቡ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَرُسُلًا لَمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ﴾. {ባንተ ላይ ያልተረክናቸውም መልእክተኞች (ልከናል።} [ኒሳእ፡ 164] ግን ታሪክ ባይዘክራቸው፣ ሰው ባያውቃቸውም #ሁሉ በእጁ ከሆነው ሃያል ጌታቸው ዘንድ የከበሩ ናቸው፣ ደረጃቸው ከፍ ያለ ነው። አብዛኞቻችን የምንዘናጋበት የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ስምህ በታሪክ መዝገብ ታወቀ አልታወቀ ምንም ነው ፤ ዋናው አላህ ዘንድ ከፍ በል።    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

🎚 :- ይህ አውዳሚ የተክፊ_…ይ ፊክራ በባዶ ሜዳ ይነፋፋሀል ድንቢጥ ሆነህ አሞራ ያደርገሀል በአጭሩ ቀድርህን ያሳጣሀል። 💬ከሚገርመው ነገር አንድ መርከብ ላይ ይሳፈሩና ቆየት ብለው እርስ በርስ
🎚 :- ይህ አውዳሚ የተክፊ_…ይ ፊክራ በባዶ ሜዳ ይነፋፋሀል ድንቢጥ ሆነህ አሞራ ያደርገሀል በአጭሩ ቀድርህን ያሳጣሀል። 💬ከሚገርመው ነገር አንድ መርከብ ላይ ይሳፈሩና ቆየት ብለው እርስ በርስ ይባላሉ አንዱ ከአንዱ የጠራሁ ነኝ ይላል…ይህ የታወቀ ባህሪያቸው መርሀላቸው ነው ። የሙሪዶቻቸው መታወር ታዲያ ምን ጉድ ነው??"'ንቃ ወዳጀ በጮኽ አደለም ። ➕"ጉዞው የተውሂድ ጥሪ ሳይሆን ባዶ ፉከራ፣ በታታኝ (አንድ የማያደርግ)፣ አውዳሚ፣ ገዳይ በሽታ…ነው" 🌐አላኩሊ ሀል ይህን ብልሹ አካሄዳቸውን ሰለፍዬች ባሉበት ሜዳ ላይ እንደልባቸው ሊጋልቡ ባለመቻላቸው ቀን እና ማታ ጦራቸውን ፤ጡዑናቶቻቸውን፣በር ዘግቶ ጩኸታቸውን ባአጠቃላይ ወደ ሰፍዬች ወደ ኡለማዎች ወደ ዱዐቶች ሲያዞሩት ታያቸዋለህ "ላ ተስተግሪብ ያ አኺ።🚫 اذا عرف السبب بطل العجب ✔ከነዚህም ድንቢጦች ዛሬ የሚታየው//የሚሰማው ይህ ነው:- ሙርጆኣ፣ ዐዚር፣ የሙሽ…_ክ የአህባሽ ጠበቃ፣ የአቂዳ ልፍስፍስ፣ በጅህሚያ በከራሚያ የነቀዙ፣ ከናንተ እነ እንትና በስንት ይሻላሉ፣ የሚል ማስረጃ ያልተደገፈ ጩኽት። የማታሸንፈው ጦርነት ውስጥ መግባት ትርፉ ሰራዊትን ማስጨረስ ነው። ተባዮች نسأل الله السلامة والعافية🤲 "የነሱ ፊክራ ተጋብቶብህ ከሆነ በጊዜ(በወቅቱ)'ሳያጠፋህ በፊት ከአዕምሮህ ላይ 🗑 ዲሌት' አዲርግ። https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1

የሺርክና የቢድዐ ጉዳዮች በብዙ አስተማሪዎች የማይደፈሩ ርእሶች ናቸው። ከዚህም የባሰው ግን የዘረኝነት ርእስ ነው። እንደ ሃገር በአራቱም ማእዘናት በዘረኝነት ብንታመስም ስለ ጉዳዩ ደፍሮ የሚያስተምረ
የሺርክና የቢድዐ ጉዳዮች በብዙ አስተማሪዎች የማይደፈሩ ርእሶች ናቸው። ከዚህም የባሰው ግን የዘረኝነት ርእስ ነው። እንደ ሃገር በአራቱም ማእዘናት በዘረኝነት ብንታመስም ስለ ጉዳዩ ደፍሮ የሚያስተምረው ግን ከጥቂትም ያነሰ ነው። ዘረኝነት የእልፎችን ህይወት ቀጥፏል። ሌሎች እልፎችን አፈናቅሏል። በውል የማይታወቁ ንብረቶችን አውድሟል። እምነታዊ ትስስራችንን በእጅጉ ሸርሽሯል። በዘረኝነት በዚህ ልክ ብንግጎዳም ሸይኹም ምሁሩም ፀጥ ብሏል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሁለት ነው። 1ኛ፦ እነሱ ራሳቸው የችግሩ ሰለባዎች መሆናቸው ነው። እንኳን ስለ ጉዳዩ ሊያነሱ በሌሎች ጠንከር ያለ ትምህርት ቢስሰጥ የማይጥማቸው ናቸው። ይሄ በተግባር የታየ አሳፋሪም፣ አሳዛኝም ሐቅ ነው። 2ኛው ምክንያት ደግሞ መንጋውን መፍራት ነው። በዘረኝነት ልክፍት የተበከለው መንጋ ርህራሄ የለውም። ስም ከማጉደፍ፣ በስድብ ከማጥረግረግ በላይ ህይወት ሊነጥቅ ይችላል። መስማት የሚሻው የሚያስፈልገውን ሳይሆን የሚፈልገውን ነው። የፖለቲካውም ይሁን የእምነት ቅኝቱ ይሄው ነው። ከዚህ ለወጣበት ምላሱም እጁም ጨካኝ ነው። በዚህ ስጋት የተነሳ መሬት ላይ በሚያዩት መሪር እውነታ ልባቸው ቢደማም ለችግሩ የሚመጥን ጥንካሬ ያለው ትምህርት ለመስጠት የማይደፍሩት ብዙ ናቸው። ግን እስከ መቼ በዚህ ሁኔታ መዝለቅ ይቻላል? ችግሩን ከመሰረቱ ካልተጋፈጥነው መጨረሻው ለሁሉም በጣም አስፈሪ ነው። አላህ ልብ ይስጠን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

مَنْ تَكَبَّرَ وَتَجَاوَزَ قَدْرَهُ فَتَنَهُ اللهُ، وَإِنَّ مِنَ النُّبْلِ أَنْ يَتَحَدَّثَ المَرْءُ بِمَا يُقَاسِمُ حَالَهُ وَيَعِيشَ بِقَدْرِهِ "رَحِمَ اللَّهُ امْرَأً عَرَفَ قَدْرَ نَفْسِهِ

🔹 "ጀምዒየቱ ጦሳ ማዶ" እነዚህ ጉዶች ሰለፊዮችን ከሱና ያስወጡበትን ጉዳይና ውስጥ ለውስጥ በድብቅ ሲያራምዱት የነበረውን በኸይር ስራ ማስተባባር ወይም "ጀምዕይነትን" "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም" ብለው ይሄው በግልፅ ባደባባይ ልመናውን ተያይዘውታል። ከዚህ በኋላ ማንም ሞርዶፋ ስለጀምዒያ የማውራት ሞራሉም ይሁን አቅሙ ያለው አይመስለኝም። ድጋሜ ግን ስለ ጀምዒያ እናወራለን ካሉ ከ"ጦሳ ማዶ" የሚለውን አውልቀው "ከህሊና ባዶ" የሚል ልብስ ነው መልበስ ያለባቸው። በኢሞ "ከህሊና ባዶ ደሴ" የሚል ግሩፕ ከፍተን አስተባብረን ቢሆን ልብሱን እናሰራላቸዋለን። አይመስላቹህም ጀማዓው!? 👌 መልዕክቴ አሁንም እውነት ያላቸው መስሏቹህ በነዚህ አጭበርባሪ ጉዶች የተሸወዳቹህ የተከበራቹህ ዲን ወዳድ ሱና ወዳድ ወንድም እህቶች እባካቹህ ከእንቅልፋቹህ ንቁ። ይሄው ትላንት ሲያወግዙት የነበረውንና ከሰለፊዮች ተገንጥለው ጎጆ የቀለሱበትን "ጀምዒይነት" ባደባባይ ፈፀሙትኮ። ምን ትጠብቃላቹህ ከዚህ በኋላ!? ለሌሎች የሚከለከል ለእነርሱ የሚፈቀድ ነገር አለ እንዴ በዲናችን!? = ✔️ የቴሌግራም ቻናል 😎 t.me/Abu_lmran_Alaseriy 😎 t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ቀብርን፣ ሲራጥን፣ ሒሳብን፣ ከአላህ ፊት መቆምን፣ እንዳጠቃላይ ኣኺራችንን ደጋግሞ ማስታወስ ያስፈልገናል። ከተቅዋ ለመራቃችን፣ ወንጀል ለመዳፈራችን፣ በደል ለማ ብዛታችን፣ ከአላህ ትእዛዝ ለመራቃችን
ቀብርን፣ ሲራጥን፣ ሒሳብን፣ ከአላህ ፊት መቆምን፣ እንዳጠቃላይ ኣኺራችንን ደጋግሞ ማስታወስ ያስፈልገናል። ከተቅዋ ለመራቃችን፣ ወንጀል ለመዳፈራችን፣ በደል ለማ ብዛታችን፣ ከአላህ ትእዛዝ ለመራቃችን ዋናው ሰበብ የየቂን ድክመት፣ በዱንያ ውጥንቅጥ ውስጥ መስመጣችን ነው። ህይወት ማለት የኣኺራ ህይወት ነው። { وَمَا هَـٰذِهِ ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا لَهۡوࣱ وَلَعِبࣱۚ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلۡـَٔاخِرَةَ لَهِیَ ٱلۡحَیَوَانُۚ لَوۡ كَانُوا۟ یَعۡلَمُونَ } "ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)።" [አልዐንከቡት: 64] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የሰው ልጅ በተፈጥሮው ያስደሰተውን ይረሳል ....የደግነት ውለታ ቢረሳም ደግ ሆነን ለመረሳት እንወስን... በመልክምነታችን ሰዎች ላያመሰግኑን ቢችሉ ወይም ውለታህን ላያስተውሱት ቢችሉም አትፍረድባቸው ሰዎች ከጠቀማቸዉ ይልቅ የተጠቀመባቸውን ፣በፍቅር ከተንከባከባቸው ይልቅ የበደላቸውን አይረሱም። ⭕️በህይወት ሳለን በሚዛን እንኑር አንዳንዱ ጋር ቸኩለን አንዳንዱ ጋ ፈጥነን ዋጋ አንክፈል። .....አንዳንዱ ጋር ጠግበን አንዳንዱ ጋ ትህትናችን በዝቶ እንዳያስገምተን። ....አንዳንዱ ጋር ጥያቄ አብዝተን አንዳንዱ ጋ ደግሞ ዝምታችን በዝቶ ፊት እንዳያስነሳን እንጠንቀቅ!! ⭕️አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አብዝተን አንዳንዱ ጋ ደግሞ ግዴለሾች ሆነን ሰው እንዳናስመርር....... #አንዳንዱ ጋር ጨዋነታችን በዝቶ አንዳንዱ ጋ ብልግናችን ጎልቶ ሰው እንዳንረብሽ ራሳችንን እንፈትሽ!! ⭕️አንዳንዱ ጋር አማኝነታችን ከልክ አልፎ አንዳንዱ ጋ አህዛባዊ ባህሪያችን አነጋጋሪ ሆኖ ሰው እንዳናወዛግብ .... አንዳንዱ ጋር ቸርነታችን አንዳንዱ ጋ ስስታችን ሰው አስገርሞ እንዳያስገምተን በማስተዋል እንኑር። ✅የሰው ልጅ በባህሪው ያሳቀውን ይረሳ ይሆናል እንጅ ያስለቀሰውን ግን በፍፁም አይረሳምና መጥፎ ሆነን ከምንታወስ ደግ ሆነን ሰው እንድረሳን ፈቃደኞች እንሁን እላለሁ!! ...N.....✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

«ነፃ መውጫ መንገዶች» ለሀዘን------ሶላት አለልህ። ለህመምህ ------ቁርዓን አለልህ። ለወንጀልህ -----ኢስቲغፋር አለልህ። ለእቅድህ------ዱዐዕ አለልህ። ላለፈህ ነገር ሁሉ ደግም ጀነት አ
«ነፃ መውጫ መንገዶች» ለሀዘን------ሶላት አለልህ። ለህመምህ ------ቁርዓን አለልህ። ለወንጀልህ -----ኢስቲغፋር አለልህ። ለእቅድህ------ዱዐዕ አለልህ። ላለፈህ ነገር ሁሉ ደግም ጀነት አለልህ። ....በተግባር ሞክሩት ፍቱን መድሀኒቶች ናቸው። t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

قَالَ رسول الله ﷺ : "مِنْ حُسْنِ إِسْلَامِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لَا يَعْنِيهِ"

ሰውን ባነጋገሩ፣ ባለባበሱ፣ በስራው፣ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታው፣ በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በትምህርት ደረጃው ፣ ... የተነሳ መናቅ አይገባም። ምናልባትም አላህ ዘንድ ያለው ደረጃ ከኛ የበለጠ ሊሆን ይችላል።
ሰውን ባነጋገሩ፣ ባለባበሱ፣ በስራው፣ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታው፣ በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በትምህርት ደረጃው ፣ ... የተነሳ መናቅ አይገባም። ምናልባትም አላህ ዘንድ ያለው ደረጃ ከኛ የበለጠ ሊሆን ይችላል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقۡنَـٰكُم مِّن ذَكَرࣲ وَأُنثَىٰ وَجَعَلۡنَـٰكُمۡ شُعُوبࣰا وَقَبَاۤىِٕلَ لِتَعَارَفُوۤا۟ۚ إِنَّ أَكۡرَمَكُمۡ عِندَ ٱللَّهِ أَتۡقَىٰكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِیمٌ خَبِیرࣱ } "እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው።" [አልሑጁራት፡ 13] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ግን እንደ ኢኽዋን ገራሚ ፍጡር አለን? ምን ይሄ ብቻ ሲነገራችሁ እንኳን ትንሽ አትታረሙም? አንዱ የኢኽዋን ኡስታዝ ብድግ ብሎ ሀገራችን እየመከረች ነው ምናምን ብሎ ደስታውን ይገልፃል፦ ምን አስደሰተህ? ሰወቹኮ የተሰበሰቡት የሸሪዓን ህግ ሊያፀድቁ አይደለም ሰው ሰራሽን ህግ ነው የሚያፀድቁት። ሌሎቹ ባዕድ የሆነች ሴት ጋር ከጎኗ እንደፓርላማ ቁጭ ብለው ለባቡል ኸይር ግንባታ ገቢ እያሰባሰቡ ትመለከታቸዋለህ። ለብቻችሁ ተፈቅዶላችሁ ነውዴ ከሴት ጋር መደባለቅ? ፎቶም አታብዙ ስለፎቶ የመጡትስ ሀድሶች? አንዱ እንኳን አልደረሳችሁምን? ኢንሻ አሏህ በድምፅ እመለሳለሁ https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

ኢላሂ...ፍጡራን ሁሉ ቢወዱኝም ሆነ ቢጠሉኝ ግድ የለኝም፤ የእኔ ትልቁ ጭንቀት በአንተ ዘንድ ያለኝ ስፍራ ብቻ ነው። ኢላሂ! ሰዎች ከሚያዩት ውጫዊ ማንነቴ ይልቅ በአንተና በእኔ መካከል ያለውን አሳምርልኝ!

አንዳድ ሙስሊሞች ወንጀለኛ የሆነን ሰዉ ያማሉ አንዳዶቹ ወንጀለኛ የሆነን ሰዉ ማማት ይቻላል አስከሚሉ ድረስ ያያሉ በዚህ ላይ ምክር ካላቹህ መልስ ሀሜት አይፈቀድም ሀሜት በሶስት ሁኔታ እንጅ አይፈቀድም 1ኛ, ስሞታ ስታቀርብ ምሳሌ እገሌ ሀቄን ወሰደብኝ ብለህ መናገር 2ኛ, ወንጀለኛ የሆነ ሰዉ ለሙስሊሞች መሪ ስርዓት እንድያስይዘዉ መናገር ምሳሌ እገሌ ሶላት በጀመዓ መስገድ ትቷል ወይም እገሌ አስካሪ መጠጥ ይጠጣል 3ኛ, በማማከር አንድ ሰዉ ልጁን ለምታቀዉ ሰዉ ሊድር ካማከርህ ያለበትን ነዉር ትናገራለህ ምሳሌ ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ጫት የሚቅም ሲጋራ የሚያጨስ ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ያለበትን ነዉ ትናገራለህ ጎደኛየ ነዉ ብለህ መደበቅ አይፈቀድም አንዳድ ወንዶች ጓደኛዉ የሆነችን ሴት ሊያገባ ሚስት ከመጋባታቸዉ በፊት መጥታ ጓደኛዉን ስትጠይቀዉ ስለ ጓደኛዉ ብዙ ነዉ እያወቀ ደብቆ ሷሊህ ደግ መልካም እያለ ይናገራሉ አሏህን ልንፈራ ይገባል ያለበትን ነዉር ሶላት የማይሰግድ ከሆነ አይሰግድም ጫት ሲጋራ የሚበላ ከሆነ ጫት ይበላል ብለህ መናገር አለብህ ይሄ ከምክር እንጅ ከሀሜት አይደለም 👇👇👇 https://t.me/HuzeyfaAhmed

خطبة الجمعة  عنوانه ( القدوة الصالحة) 🗒የጁሙአ ኹጥባ            ርእሱ መልካም አረአያ መልካ ተምሳሌት             في مسجد  الصفا بمدينة هرا                                                                 🕌  ሃራ መስጂደ ሶፋ                                           صفر 3     لِعَامِ. ١٤٤٨ه‍                                   🎤    በወንድም           አቡ ፈውዛን ልአአረባሊይ                   

أبو ذر القديم يرد على أبي ذر الجديد ወሳኝ ሙሀደራ በለተምዮች ላይ የተሰጠ ረድ وَشَهِدَ شَاهِدٌ مِنْ أَهْلِهَا በተረጋጋ መንፈስ ብታዳም ጡት ተጠቃሚዎች ትሆና ላችሁ!! https://t.me/Multeka_Selefiyin