ar
Feedback
Abu Menal || አቡ መናል

Abu Menal || አቡ መናል

الذهاب إلى القناة على Telegram
1 460
المشتركون
+124 ساعات
+577 أيام
+80730 أيام
أرشيف المشاركات
በጣም ትገርማለህ ! ....ቀንህ ለሌላ ነገር ሲሆን ይሰፋልህ እና ለቁርአን ሲሆን ይጠብብሀል ... لقائله Abu Menal || አቡ መናል

🔖እኛ ምስኪን ህዝቦች ነን፤ የአላህ መሸፈን ባይኖር ኖሮ እንዋረድ ነበር...🔖 የአላህ ታላቅ የቸርነትና የረህመት ባህሪ ከሆኑት መካከል አንዱ" አ'ሲቲ'ር "ወይም የሰው ልጅን ነውር፣ ስህተትና ድክመት መሸፈኑ ነው። በየቀኑ በግልጽም ሆነ በድብቅ የምንሰራቸውን እጅግ የቀዙ ወንጀሎች አላህ በሰዎች ፊት ቢገልጣቸው ኖሮ ማህበራዊ ህይወታችን ይናጋ ፣ አንዱ ከሌላው ጋር መኖሩ ይቅርና ፊቱን ለመተያየት እንኳን ያፍር ነበር። ነገር ግን አላህ በፍጹም ቸርነቱና በትዕግስቱ ነውራችንን ከሰው አይኖች ሰውሮ ክብራችንን ይጠብቅልናል። ​ይህ የአላህ ሲትር ዋና ዓላማው በደላችንን ደብቀን ሳሊህ መስለን እንድንታይ ወይም በሰዎች ላይ እንድንኩራራ ሳይሆን፡ ወደ እርሱ ተመልሰን እውነተኛ ተውበት እንድናደርግ ዕድል መስጠት ነው። አላህ የሰራነውን ጥፋት ወዲያውኑ ይፋ በማድረግ አዋርዶ ተስፋ እንዳንቆርጥ ያደርገናል፤ በሩ ሳይዘጋና በህይወት እያለን እንድንማጸነውና እንድንታረም ጊዜ ይሰጠናል። ነቢም 🤍 አላህ የባሪያዎቹን ወንጀል መሸፈንን የሚወድ መሆኑን አስተምረውናል። ​ይህንን ታላቅ ጸጋ ያገኘ ሰው በበኩሉ አላህን የማመስገንና የሰዎችንም ነውር የመሸፈን ግዴታ አለበት። ሰይዳችን 🤍 🔖የሙስሊምን ጉድለት የሸፈነ አላህ በቂያማ ቀን ጉድለቱን ይሸፍንለታል🔖 እንዳሉት፡ የእኛን ነውር አላህ እንዲሸፍንልን የሌሎችን ነውር ከመከታተልና ከማውራት መቆጠብ አለብን። በተጨማሪም አላህ በቸርነቱ የሸፈነልንን ወንጀል ለሰዎች በማውራት 🔖ሙጃሃራ🔖 የገባንበትን የመሸፈን ጥላ በገዛ እጃችን ማወልቅ አይገባንም ። ✈️ @AbuMenal

ወንድም ሳላህን (ማሂር ) አግንቼዋለው ፤ ሹክረን ልጆች ...

ንፅፅር ላይ የምትሞክሩ ወንድሞች እፈልጋችኋለው @abu_menal ላይ ፃፉልኝ ። አንድ ክሪስቲያን ጥያቄዎች አሉት ፤ በአላህ ፍቃድ የመስለም ተስፋ አለው ።

▫️ሸይኽ ሳሊህ ❤️ ሲንዲ እንዲህ አሉ.. 🔖ወደ ጠማማ ሰዎች ድህረ ገጾች አትግቡ፤ የአጠራጣሪ ሰዎችን አካውንቶችም አትከተሉ። የተዛቡና የተሳሳቱ ሰዎችን መጻሕፍት አታንብቡ፤ እንዲሁም የተተዉና የተሸነፉ ሰዎችን ቪዲዮዎች አትመልከቱ። የአጥፊዎችን ቻናሎችና ጣቢያዎች ከመከታተል ተቆጠቡ። ተላላለፊ በሽታ ካለበት ሰውን ልክ እንደ አንበሳ የምትሸሹ ከሆነ ፣ ታዲያ የልብ፣ የአእምሮ እና የሃይማኖት በሽታ ካለበት ሰው እንዴት አትሸሹም? አላህ ይጠብቅህና ዕወቅ፤  የሹብሃ ፍንጣቂ ወደ ቀልብ ከገባች  ቀልብን ሙሉ በሙሉ አቃጥላ ልታጠፋው ትችላለች። በመሆኑም በነጻነት እና በክፍትነት  ስም የሚደረጉ ጥሪዎች ወይም የማወቅ ጉጉት ስሜት አያታሉህ ። ነቢ 🤍 በሁለቱ ሰሂህ መጻሕፍት እንደተወራው እንዲህ ብለዋል፦ 🔖ከእርሱ (ከቁርኣን) አሻሚ የሆኑትን ነገሮች የሚከተሉትን ሰዎች ባያችሁ ጊዜ፣ እነዚያ አላህ የጠራቸው (የገለጻቸው) ሰዎች ናቸው፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው።🔖

Repost from HADIISA📚

ጀዛኩሙላሁ ኸይራ ልጆች

▫️ጀምረናል

ይሰማል?

⏰️ 3:00 ሲል ደርሳችንን እንጀምራለን ከታች ባለው ሊንክ ግቡ ⬇ https://t.me/AbuMenal?livestream=69c5959f8b97ecace6

3:00 ደርሳችንን እንጀምራለን

▫️ዛሬ ከምሽቱ 3:00 የምንጀምረውን ኪታብ ያዘጋጁት ሸይኽ ማናቸው ለሚለው ጥያቄ ..ጥሩ. ምላሽ የሚሰጥ ፅሁፍ ነው ። ይነበብ ።

🔖ሸይኽ ሙሀመድ አህመድ ኡመር (ሸህ ባሲጢ) ከግማሽ ክፈለ ዘመን በላይ በመማር ማስተማር የተጉ ድንቅ አሊም ዑለሞቻችን ሲዘከሩ... የአንድ ሰዉ ስም ከተጠራ ለኢትዪጵያ ሙስሊም ከፍተኛ አስተዎጾ ማበርከታቸዉ ብዙ ባይነገርም ብዙዎች ግን "ተምሬባቸዋለው" ይላሉ። እኚህ ሰዉ ተዉሂድን በማስተማር ለአስርት አመታት ታግለዋል። ሚሊየኖች የሚታደሙበት የመረጃ መረቦችና የሀርድ ኮፒ ሲዲዎች ሳይኖሩ በፊት፤ ከደሴው አረብ ገንዳ እስከ አንዋርና ሀሺም መስጂዶች ለረጅም አመታት በሰጧቸዉ የተዉሂድ፣ የሀዲስና የተፍሲር ትምህርቶች ለብዙ ኢትዬጵያውያን ሙስሊሞች መድረስ የቻሉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ባለውለታ ናቸው። ለመሆኑ እኚህ ሸይኽ  ማናቸዉ??? ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ ይባላሉ። 👉 *ዉልደት* ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ  በወሎ ከተማ ምዕራብ ደሴ የባሲጥ እጅ መንደር በ1938 እ•ኢ•አ በ1945 እ•ኤ•አ ከተከበረ ሙስሊም ቤተሰብ ተወለዱ። የአባታቸዉ  ስም አህመድ ዑመር  የእናታቸዉ ስም ዘይነቡ ሽፋ ይባላል። የሸይኽ አልባሲጢይ አባት አህመድ ዑመር የዘመነ መሳፍንት ባላባት ናቸው። እናታቸው  ዘይነቡ  ሽፋ የሸይኽ  ልጅ  ናቸው። 👉 *የ22 ዓመታት የትምህርት ጉዞ* ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ የልጅነታቸውን ጊዜ በጥሩ ኢስላማዊ  አስተዳደግ ያሳለፋት። ገና  በልጅነታቸው  በባሲጥ የጁ መንደር ውስጥ ቁርዐንና ሌሎች ተዛማጅ የሸሪዐ ትምህርቶችን ቀስመዋል። በጨቅላነታቸዉ ቁርዐንን ከእናታቸዉ ዘመድ ከሸኽ አሊ ቡሩ ቀሩ። √ ለ9 አመታት በለገሂዳ መንደር ሸይህ አሊ አደም ዘንድ የፊቅህ እውቀትን አዳርሰው ቀስመዋል። እኚህ ሸይኽ የታዋቂዉ የመካ አሊም ሸይኽ ሙሀመድ አሊ አደም አል–ወሎዊ  አባት ናቸው። √ በመቀጠል ወደ ቃሉ ወረዳ አጋምሳ መንደር ሸህ ተማም ዘንድ በመሄድ ለ 6 አመታት ነህውና ሰርፍ ተምረዋል። √ ከቃሉ ሳይወጡ በቦሩ መንደር ሀጅ ቡሰይር ዘንድ ለአንድ አመት ተኩል ተፍሲር ቀርተዋል። √ ወቅቱ ታላቁ አሊም አል ሐጅ   ራፊዕ ወደ ከረጅም አመታት ቆይታ በኃላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ማስተማር የጀመሩበት ወቅት ስለነበር ቀጣጤ መንደር በመዘዋወር ለሁለት አመታት ቡኻሪና ሙስሊምን ቀርተውባቸዋል። ከሸይኹ ጋር የነበራቸው ቆይታ ይህ ብቻ አልነበረም። ሸይኹ የኃላ ኃላ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡም ተከትለው በመምጣት ለተከታታይ ሶስት አመታት ከኩቱቡ ሲታ ያልተማሯቸውን አራቱን ሱነኖች አንጥረው ቀርተዋል። በጥቅሉ ወደ ዳዕዋ መንደር ሳይገቡ  ለ22 አመታት የሸሪዕ ዕውቀትን ቀስመዋል። 👉🏻 *የታላላቅ ኡለማዎች ማእድ* ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ  ወደ  አዲስ አበባ  በመምጣት የከተማ ዳዕዋና የመማር ማስተማር ህይወትን  አሀዱ ብለዉ የጀመሩት በ1970ዎቹ እ•ኢ•አ  ነው። በአዲስ አበባ ከሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀቢብ ዘንድ ብዙ የተማሩ ሲሆን ሀዲስን በተመለከተም ከሸይኽ ሙሀመድ ራፊዕ ብዙ ተምረዋል። ከታላላቅ ኡለማዎች በቀሰሙት ጥልቅ እውቀት ለማስተማር የብቃት ማረጋገጫ ኢጃዛ የተሰጣቸው ኢጃዛ በእጃቸው ይገኛል። ከዚህም መካከል የሀዲስ ሊቁ አል ሐጅ ራፊዕ እና የሸይኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ ኢጃዛ ይገኙበታል። ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በሸይኾቻቸው ዘንድ ተወዳጅና ተመራጭ ነበሩ። ሀጅ ራፊእ በታላቁ አንዋር  መስጂድ በራሳቸው ቦታ ላይ ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ተፍሲር እንዲያስቀሩ አድርገዋቸው ነበር። እንደዚሁ ሀጂ ሳኒንን ተክተው በአንዋር ትልቁ መስጂድ ውስጥ የተፍሲር ትምህርት መስጠታቸው ይታወሳል። ከዘመናችን ታላቅ አሊም ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ኢብኑ ባዝ ጋር ጥሩ ወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን፤ ሸይኹ ለዳእዋ እንዳበረታቷቸው እና የኢልም ብቃት ፈተናዎችን ካለፉ በኃላ ብዙ መልካም ውለታዎችን እንደዋሉላቸው ይጠቅሳሉ። ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በዘመናችን የፊቅህ ፈርጥ  የሆኑትን ሸይኽ  ኢብን  ዑሰይሚን ብዙ የሚያደንቁና በእጅጉ የሚወዱ ከመሆናቸው ባሻገር ከኪታቦቻቸውም ብዙ ተምረዋል።  የአላህ ፍቃድ ሆኖም በመካ ለአስር ቀናት የቆየ የኢልም ኮርስ ታድመዋል። ያዩትን የሸይኽ ኡሰይሚን ትህትና፣ ጥልቅ እውቀትና ግርማ ሞገስ ሲያወጉ በሰፊው ነው። 👉🏻 *ረጅሙ የዳዕዋና የማስተማር ስራ* ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ በአዲስ  አበባ  ከተማ ከ38 አመታት በመማር ማስተማር እና በዳዕዋ  ላይ  የታገሉ፤ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሙስሊሙን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቅ አሊም ናቸው። ባለፉት ሶስት አስርት አመታት የሸኹ የተፍሲር ደርሶች ብዙ መስጂዶችን ያስዋቡ ነበሩ። በተለይም አንዋር፣ ሀሽም እና አባቦራ መስጂዶች በሸይኹ የኢልም መሽሊሶች የደመቁ ሆነው ቆይተዋል። ሸይኽ መሀመድ አህመድ ዑመር አልባሲጢይ ሀቅን ለመናገር ባላቸው ጀግንነት ጥንካሬና ለኢስላም የመቆርቆር ስሜት ይታወቃሉ። ኑር መስጂድ አጠገብ በነበረው ፈትህ መስጂድ ለ22 አመታት ያስተማሩ ሲሆን ከመድረኮቻቸው በአላህ ፍቃድ አያሌ ተማሪዎችን አፍርተዋል። ብዙዎችም የሳቸውን  ፈለግ በመከተል በኢልምና በዳዕዋ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በቅርቡ በአሜሪካ አትላንታና ዲሲ የነበራቸው የዳእዋ ቆይታ ፍሬያማ የነበረ ሲሆን በሳውዲም በተለያዩ አጋጣሚዎች የዳእዋ ስራዎች ላይ ተሳትፈዋል። 👉🏻 *የሸይኹ ድርሳናት* ሸይኽ አልባሲጢይ በአረብኛ አያሌ መፅሀፍትን የደረሱ ሲሆን በተለይም በቅርቡ ጠንካራ ጥናቶችና ጠቃሚ መልእክቶችን ለንባብ አብቅተዋል። ከነዚህም መካከል፤ 1) ኑሩሸምዓህ ፊ መሳኢሊ የውሚል ጁምዓህ 2) ተፍሲሩ ጁዝ ዓምመ 3) ሪሳለቱን ፊል ኢማኒ ቢላህ 4) መዛየል ኢስላም 5) አል መርአቱ ፊል ኢስላም እና ሌሎችም ይገኙበታል። *ህልፈታቸው* ሸህ ባሲጥ በደረሰባቸው የጤና መታወክ ህንድ ሀገር የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ቅዳሜ ነሐሴ 12/2010 ዓ.ል ህይወታቸው አልፏል። የቀብር ስነስርአታቸው ዛሬ እሁድ ነሀሴ 13/2010 በኮልፌ መካነ መቃብር ይፈፀማል። ለቤተሰባቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እና ለወዳጆቻቸው በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን። አላህ ይማራቸው፣ ስራቸውን ይቀበላቸው፣ ትተውት ያለፉትን የእውቀት አሻራ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጠቃሚ ያደርግላቸው... አሚን!! 🔖 ▫️CC : ሸይኹ 🔳 ወደ አኺራ በሄዱ ጊዜ በተማሪዎቻቸው እና/ወዳጆቻቸው የተዘጋየ ፅሁፍ ነው

ከሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት በፈገግታና በትህትና ሲታጀብ ውብ ይሆናል። መልካም ስነ-ባህሪን መላበስ በጣም ትልቅ አጅር ያለው ስራ ነው ። ለሰዎች ይቅር ባይ መሆንና በውስጥ ቂም አለመያዝ ለአእምሮ ትልቅ እረፍት የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ አላህ ይቅር እንዲለን ምክንያት ይሆናል ። ከዚህ በተጨማሪ መልካም ስነ ባህሪ የሰዎችን ቀልብ ለመማረክና የኢስላምን ውበት ለማሳየት ትልቁ መንገድ እና የዳእዋ ወሳኙ ክፍልም ነው ። Abu Menal || አቡ መናል

ምላስና አይን በጥንቃቄ ካልተያዙ ወደ ጥፋት የሚመሩ አደገኛ የሰውነት ክፍሎቻችን ናቸው ። ምላስን ከሐሜት፣ ከውሸትና ከስድብ መጠበቅ፣ አይንን ደግሞ አላህ ከከለከላቸው ነገሮች መስበር የቀልብ ጥንካሬን ይሰጣል። በምላስም መልካም ነገርን መናገር ወይም ዝምታን መምረጥ ትልቅ ኢስላማዊ እሴት ነው። የሰው ልጅ አብዛኛውን ጊዜ ወደ ስህተት የሚወድቀው በሀራም ንግግሩና ባልተገቡ እይታዎቹ ምክንያት ስለሆነ፣ እነዚህን የሰውነት ክፍሎቻችንን በአላህ ታዛዥነት ላይ ብቻ በመጠቀም ቀልብን ከጨለማ መጠበቅ ይኖርብናል ። Abu Menal || አቡ መናል

ሼር አድርጉት ልጆች ...የፊታችን እሁድ ነው የምንጀምረው

🫥 የደርስ ማስታወቂያ ! 🔎 ቀጣይ የሚጀመረው ዐቂዳ ኪታብ ነው ➖የኪታቡ ስም   🏷️ሪሳለቱን ፊል ኢማኒ ቢላህ🏷️ ➖አዘጋጅ  :   የተከበሩ ሸይኽ መሐመድ ዑመር ባሲጢ  🔳 🫥ደርሱ ዘወትር ጁምዐ እና እሁድ ከምሽቱ 3:00-3:30 የሚሰጥ ሲሆን ፤ የፊታችን እሁድ መስከረም 10 : 2019 እ.ኢ.አ  ይጀመራል 🤍 የኪታቡን 📄 ለማግኘት ይንኩት ትምህርቱ የሚሰጥበት ቻናል ⬇ ▫️ t.me/AbuMenal

رسالةٌ_في_الإيمانِ_بالله_تعالى_للشيخ_الباسطي_.pdf4.25 KB

አልሐምዱሊላህ ▫️ሸይኹል ኢስላም አቡ ዑስማን አ'ሳቡኒ 🔳 ያዘጋጁት " ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሀቡል ሀዲስ ኪታብ ተቀርቶ ተጠናቋል ። ☝️ ➖በቀጣይ አል ሀፊዝ አል ኢስማዒሊ 🔳 ያዘጋጁት " ኢዕቲቃዱ አህሊሱና " የተሰኘው ኪታብ ይጀመራል 🤍 PDF⬇ https://t.me/IbnulQeyyimMedresa/258 ▫️12 የዐቂዳ ኪታቦችን እየታረመላችሁ ለመማር @aqidaders ላይ ተመዝገቡ ።