ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
318
المشتركون
-424 ساعات
-77 أيام
+5430 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from ስለ ቀልባችን
የሀራም ፍቅር መነሻው «ስሜት»፣ መድረሻው ደግሞ «ክህደት» ነው።
የአንዳንዱ ወንድ ውሸታም ናፍቆት ኒቃብሽን አስገልጦ የተሸፈነውን እስኪያይ ድረስ ብቻ ነው፤ በሀራም መንገድ ፊትሽን አይቶ ጉጉቱ
ሲበርድ ግን «ይህች ናት እንዴ?» ብሎ ድራሹ ይጠፋል።
እህቴ ሆይ! በሀራም መንገድ ኒቃብሽን የሚያስወልቅሽ ሰው የፈለገው የተከለከለውን ስሜቱን እንጂ አንቺን አይደለም። ውበትሽም ሆነ ክብርሽ የሚገባው በኒካህ ለሚያከብርሽ ለሀላልሽ ብቻ ነው!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
ይልቁን አሁንም በድጋሜ ሳይመሽ ወደ አላህ ልትመለሱ ይገባል።አላህን ልትፈሩ ስሜትን ከመከተልና ከአጉል ኩራትና መኮፈስ እራሳችሁን ልታቅቡ ይገባቹሃል ። በመጨረሻም ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር እና ኡስታዝ ኸዲር አሕመድ ከጥንት እስከዛሬ እናንተን በዉይይት ፣ በፁህፍ እና ተከታታይ እርምቶችን በመስጠት መክረችኋል እና ኩራታችሁን ወዲያ አዉልቃችሁ ጣሉና ምክሩን ተቀበሉ። ኩራት ለኢብሊስም አልበጀ!
ክፍል ሁለት፦
‼️ من الذى جاء بمنهج جديد ؟ وبدل ما كان عليه
⭕️ አዲስን መንሃጅ በማምጣት ድሮ የነበረበትን የቀየረውና የተከረበተው ማነው ?
ከላይ በክፍል አንድ ለማውሳት እንደተሞከረው ከአመታት በፊት ከስድስት ሰዓት በላይ የወሰደ ዉይይት ተደርጎ ነበር። ይህ ዉይይት በዉስጡ አሁን ላለው ዉዢንብር መፍትሄ ስላለዉና ማን ከነበረበትን አቋም እንደተከረበተ ማወቅ ስለሚያስችል ስለ ዉይይቱ በአላህ እገዛ የተወሰነ እንበል።
የዉይይቱ አላማ ፦ 👉 በሰለፍዮች መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት መፍታት፦
የዉይይቱ ተሳታፊዎች፦
1) ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ ያሲን
2) ኡስታዝ በሕሩ ተካ
3) ኡዝታዝ ዓሊ ሑሰይን
4) ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን
5) ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
6) ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
7) ኡስታዝ ሳዳት ከማል
8) ኡስታዝ ፉኣድ ሙሐመድ
አወያይና ሽማግሌዎች ከባህር ዳር፦
9) ሸይኽ ሐሠን ገላዉ
10) ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መሻይኾች እና ኡስታዞች ዉይይቱን ሳዳምጥ መኖራቸዉን የተገነዘብኩት ሲሆን ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ።
አለመግባባት ከተፈጠረባቸዉ ነጥቦች ዉስጥ ዋነኛው የሚከተለዉ ነው ፦
ከአንድ እስከ አራት የተጠቀሱት ኡስታዞች "የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ዋና ዋናዎቹ ሙብተዲዖች ናቸዉ" የሚል ብይን ሲሰጡ ከ አምስት እስከ ስምንት የተወሱት ደግሞ "ሙብተዲዖች አንልም ነገር ግን ስህተታቸዉን በማስረጃ እናጋልጣለን" ይላሉ።
👉 ዋናው የልዩነት አጀንዳ እነ ዓብዱል ሐሚድ የመርከዙን ሰወች መበደዓቸውና እነ ኢብኑ ሙነወር አለመበደዓቸው ሳይሆን። እነ ዓብዱል ሐሚድ በሰጡት ብይን እነ ኢብኑ ሙነወርን እኛ እንዳልነው በሉ በማለት "ኢልዛም" ማድረግ ይችላሉን? ወይስ ይህ የተብዲዕ ብይን "ኢጅቲሃዲይ" ( ጥረትን የሚያስተናግድ ) ነው?
ለዚህ ወሳኝ ጥያቄና የልዩነት ነጥብ የጋራ ድምዳሚያቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"ከፊላችን የመርከዙን ሰዎች ሙብተዲዖች ናቸው ብንል ከፊላችን ደግሞ አይደሉም ብንል በመካከላችን የመንሃጅ ልዩነት አያመጣም። ምክኒያቱም ይህ አጀንዳ ኢጅቲሃድን የሚያስተናግድ ነውና" የሚል ነበር።
በተለይ በተለይ አወያይ የነበሩት 👉ሸይኽ ሐሰን ገላው መስዓላው ኢጅቲሃዲይ እንደሆነ ከሰለፎች ምሳሌን እያጣቀሱ ደጋግመውና አስረግጠው ይናገራሉ።
ለዚህም ትልቁ ማሳያ እና ማስረጃ የዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ መጨረሻ እንዲናገር እድል የተሰጠው ኡስታዝ ዓሊ ሑሴን የተናገረው የመደምደሚያ ሃሳብ ነው ይህንንም ንግግር የተናገረው ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር እንዲህ ብሎ ከተናገረ በኋላ ነበር፦
" በመጀመሪያ አላህ ከልፋታቹህ በላይ ይመንዳቹህ" ብሎ ለዉይይቱ ለመጡት ሰዎች ዱዓ ካደረገ በኋላ " 👉 ከአሁን በፊት ወደ ነበርንበት እንድንመለስ ከሚያግዙን ዉስጥ ስንወጣ የሚጠብቁን ሰዎች የት ደረሳቹህ ብለው ስለሚጠይቁን ለነሱ ምን ማለት እንዳለብን ማውራቱ ወሳኝ ነው.....
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አውርቶ ከጨረሰ በኋላ "ዓሊ እጁን እያወጣ ነው እድል ስጠው ይላል" ። ኡስታዝ ዓሊ ሑሴንም የዉይይቱ የመጨረሻ ሃሳብ ሰጭ ሲሆን እንዲህ ይላል ፦
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴 ቃል በቃል ነው የሰፈረው
[[ ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም እኔ ሐቂቃ ዉጭ ያለውን ጉዳይ ማስተካከል ያስፈልጋል የሁላችንም አስተዋፅኦ ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ። ምንድን ነው አሁንም የደዕዋዉ ሂደት ላይ ስንሄድ ቅድም አዲስ አደረክ እንዳትሉኝ እንጂ ! እኛ ጋ የሆነ አቋም አለ እነሱ ዘንድ የሆነ አቋም አለ። ያ አቋም ኢጅቲሃዲይ ነው ብለን አምነንበታል ።
እኛ ለምናደርገው አካሄድ ተደኹል መሆን (ጣልቃ መግባት) የለባቸዉም እነሱ በሚሄዱትም ተደኹል መሆን የለብንም ። ይህ በእናንተ እዚህጋ ባለው ወንድሞች የተስማማነው ነው ። ስለዚህ አሁን እንደ ጥያቄም ስንጠየቅ እኔ በራሴ ልለዉ የማስበው እነዚህ ሰዎች እንዴት ነው ? እናንተ ሙብተዲዖች ናቸው ስትሉ እነሱ አይደሉም የሚሉ ሰዎች ምናምን የሚለው ነገር ከተነሳ እኛ የነሱን አይመለከተንም እነሱ በዚህ ጉዳይ ላይ -ከመንሃጅ አስወጡ አላስወጡ - በዚህ ጉዳይ ላይ እንድትጠይቁን አንፈልግም ]]
ሸይኽ ሐሰን ገላዉ በመካከል በመግባት (( መስኣላው ኢጅቲሃዲያ ነው በሉ )) ይላሉ።
ዓሊ ሑሴንም እንዲህ ሲል ይቀጥላል ፦ [[ እኛ የራሳችን አቋም አለን። ከማስረጃ ከፈለክ ከኔጋ አውራ። ኢልያስ ሙብተዲዕ ነው ፤ ከመንሃጅ ወጡ አልወጡም ? ከኔጋ በመረጃ አውራ ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ኢብኑ ሙነወርን የሚመለከት ፉኣድን የሚመለከት ከሆነ ከእራሱ ጋ ሂድና አውራ።
ስለዚህ አሁን ሙኻለፋዉ ላይ ተስማምተናል እነእርሱ (የመርከዙ ሰዎች) የተለያዩ ሙኻለፋ እንዳለባቸው ሁላችንም እናምናለን ]]
ኢብኑ ሙነወር በመካከል እንዲህ ሲል ተናገረ (( ይህን ነጥብ የሚያጠናክር መጥቶ ጠየቀኝ አንድ ልጅ ተብዲዕ እያደረጉ ነው ሌሎች ለምን አታስቆሟቸውም? እናንተ ተብዲዕ ታደርጋላቹህ ወይ? አለኝ ። ከኛ ያየኸው ነገር አለ ወይ? አልኩት። እሽ የሚያደርጉትን ለምን አታስቆሙም አለኝ ። አናስቆምም ልክ ሊሆኑ ይችላሉ አልኩት .....))
ዓሊ እንዲህ ሲል ይቀጥላል ፦ [[ ስለዚህ አሁን በሆነው ነገር ምንድን ነው እኛና እነሱ (እነ ኢብኑ ሙነወር) አንድ ነን በነእርሱ (የመርከዙ ሰዎች) ላይ ረድ በማድረግ። እነእርሱን (የመርከዙን ሰዎች) ከመንሃጅ በማስወጣትና ሙብተዲዕ በማለት በአካሄድ ልንለያይ እንችላለን ። ግን ደዕዋው አንድ ላይ ነው ምናስኬደው ። በረድ ላይ አንድ ነን ፤ ተሕዚር በማድረግ ላይ አንድ ነን ስለዚህ በመካከላችን ልዩነት የለም የሚለውን ነገር በግልፅ እናወራለን .....አሁን በመካከል የነበረው ግርዶሽ ፈርሷል አልሐምዱሊላህ ......]]
የዓሊ ንግግር በዚህ አለቀ። ሙሉ ቅጂው ከፈለግን ያሳለፍነው የኡስታዝ ዓሊ ሁሴን ንግግር 5:43 አምስት ሰዓት ከአርባ ሶስተኛው ደቂቃ ላይ እናገኘዋለን። የተከበራችሁ ውድ ሀቅ ፈላጊ ሰለፊይ ወንድም እህቶች ሆይ!፦ እንግዲህ ይህን ድምዳሜ እያሰፈረ ያለው ዛሬ "መስዓላው ኢጅቲሃዲይይይ አይደለምምም" እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሚናገሩት ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ፊት ነበር። ታዲያ የዛኔ ለምን ዝም አሉ? የዛኔ ኢጅቲሃዲይ የነበረው ዛሬ እንዴት አይደለም ይባላል? ነው ወይስ የዛኔ በመንሃጅ ሰለፍ ጃሂሎችና እነርሱም #ሙመይዖች ነበሩ? እና አሁን ከ5/6 አመት ወዲህ ነው አለመሆኑ የተገለጠላቸው እንበል? ነው ወይስ የዛኔም ኢብኑ ሙነወር እና ፉኣድ በዛ መልኩ አጥበቀውና አጠንክረው "#ኢልዛም አለ የምትሉ ከሆነ በማስረጃ እዚሁ እናውራበት" ሲሏቸው "አላልንም ፤ አንልም" ሲሉ የነበሩት ሐቁን እያወቁ ደብቀው ነበር ዉሸት እያወሩ የነበሩት በውሸትም የተስማሙት እንበል?
👉ነገሩን ከወገንተኝነት ፀድቶ ለተመለከተው ሰው እነ ዓብዱል ሐሚድና ከሱም ጋር ያሉት በመንሃጅ ስም የ "ካፈርኩ አይመልሰኝ"ን ጉዞ ነው የተናነቁት ። አንዴ ሙብተዲዕ ብለናል ብለናል በቃ!
👉 ከዳተኛው እና አጭበርባሪው የለተሞ መንጋ፡
{{ وَقُلْ جَاءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَاطِلُ إِنَّ ٱلْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا }} الإسراء ٨١
[[ በልም "እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና ]] ኢስራእ 81
" النصحُ السديدُ لِمن نَحَا نحوَ ما نحا إليه عبدُ الحميد "
"የተስተካከለ ምክር ዓብዱል ሐሚድ ያዘነበለበትን አቅጣጫ መሄድ ላሰቡ ሰዎች"
ክፍል አንድ፦
"الخيانة بئست البطانة"
📌 "ከዳተኝነት"
ከዳተኝነት እንደሚታወቀው ሙስሊሞች ይቅርና ከሃዲያኖች የሚፀየፉት ቆሻሻ ተግባር ነው። ይሁን እንጂ አሁን አሁን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ እራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉና ለሱና ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አካሎች ላይ እንመለከተዋለን።
ይህን ስንል በማስረጃ ነዉ። ከአመታት በፊት ማለትም እነ ዓብዱል ሐሚድ እነ ኢብኑ ሙነወርን "ሙብተዲዕ" ብለው ብይን ከመስጠታቸዉ በፊት ከነ ኢብኑ ሙነወር ጋር ከስድስት ሰዓት በላይ የወሰደ "ጀልሰህ" (መቀማመጥ) አድርገው ነበር።
በዚህም "ጀልሰህ" የተለያዩ ርዕሶች ተነስተዋል። እናም ዉይይቱ ከተጀመረ በኋላ ከቤቱ የዉይይት ስርዓት አልታይ ሲልና ጫጫታ ፣ አለመሰማማት እና አንዱ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላኛው ጣልቃ እየገባ የዉይይት አደብ አልሰፍን ሲል ድምፃቸዉ እየተቀዳ ስለነበር ይህ ነገር ሪከርድ ተደርጎ ለህዝብ መዉጣቱ አስነዋሪ ስለሆነ ባይደረግ የሚል ሃሳብ ከከፊል ወንድሞች ተነሳ ከዚያም በዚህ የተነሳ (ሪከርድ መደረግ አለበት እና የለበትም በሚል) ለረዢም ሰዓት ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻ ድምፁ መቀዳት እንደሌለበትና የተቀዳዉንም በመሰረዝ ተስማምተው ዉይይቱን ቀጠሉ።
👉 አሳዛኙ ነገር ግን ከነ ኢብኑ ሙነወር በኩል የነበሩት ሰዎች ሀሉም ሪከርደሩን ቢዘጉም ከነ ዓብዱል ሐሚድ በኩል የነበሩ ሰዎች ግን የገቡትን ቃል በማፍረስ ድምፁን ቀድተው ይዘው ወጡ። ከትንሽ ጊዜ በኋላም "ከኛ ጋር የተቀዳ ድምፅ አለ" እያሉ ብቅ አሉ። ይህ ከዳተኝነት እንኳን ከሱና ኡስታዝና ሸይኽ ተብየ ይቅርና ከተራ ሙስሊም የማይጠበቅ የሙናፊቅ ተግባር ነው።
👉 እነዚህ ሰዎች ለኛ ማስረጃ የሚሆንበት ቀን ይኖራል ብለዉ ሪከርድ ቢያደርጉቱም አላሁ ተባረከ ወተዓላ ግን ነገሩን ገለበጠባቸውና ማስረጃዉ ለእነርሱ ሳይሆን በነእርሱ ላይ ሆነባቸው።
ለዚህም ትልቁ ማሳያ የዉይይታቸው ማጠቃለያና ጭብጥ ሃሰብ እንዲህ የሚል መሆኑ ነዉ።
"የኢብኑ መስዑድ መርከዝ ሰዎችን በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ ቢኖረንም መበታተን ፣ መለያየትና ከፊላችን ከፊላችንን #ሙብተዲዕ ማለት አይገባም።''
እንግዲህ ይህን የተስማሙበትን ቃል ያፈረሱና የነበሩበትን አቋም የቀየሩት እነ ዓብደል ሐሚድ ወይስ እነ ኢብኑ ሙነወር??? መልሱን ለአንባቢ እንተወው። ይህ "ከዳተኝነት" እንግዲህ ከነዚህ ሰዎች ከተገኙ ከባባድ እና ቀደም ካሉ ጥፋቶች ዉስጥ አንዱ ነው።
Repost from የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ
▣ በድብቅ የተቀዳው የድምፅ ፋይል ሙሉውን
⌚️ 6:08:38 ሰዓት
📌 ለእውነት ፈላጊዎች ይቺ ፋይል በቂ መረጃና ማስረጃ ናት!
➩ አድምጣችሁ ፍረዱ ማን እንደተቀየረ
➩ ለተሚዮች የኡስታዞቻችሁ ውሸት ተገንዘቡ በምን እንደተስማሙ አድምጡ
- እንደ መርከዙ ሰዎች ያሉ ሰዎች ላይ መለያየት ኢጅቲሓዲይ ነው
- የመርከዙ ሰዎች ተብዲዕ ማድረግ አለማድረግ ሊያጣላን አይገባም
◍ O Altemiyun Listen the lies of your Teachers
https://t.me/Menhaje_Selef/21
https://t.me/Menhaje_Selef/
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የዐቂዳ መሰረታዊ እውቀትን የማስጨበጥ ፕሮግራም
~
ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በ الجمعية العلمية السعودية لعلوم العقيدة والأديان والفرق والمذاهب ነው። ማህበሩ በመሰረታዊ የዐቂዳ ትምህርቶች እና የተለያዩ አፈንጋጭ አመለካከቶች ላይ ጥናት በማካሄድ ላይ የተሰማራ የሳዑዲ ድርጅት ነው። ሸይኽ ሷሊሕ ሲንዲ የዚህ ማህበር ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አባል ናቸው።
የምትችሉ ብተመዘገቡ ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ።
ለአንድ ዓመት የሚቆይ የዓቂዳ ትምህርት ነው።
በማሰራጨት የኸይር ሰበብ ሁኑ ባረከላሁ ፊኩም።
ስለ ድግምት (ሲህር )የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ ➋➋ አከባቢ ሙሓደራወች
በተለይ ቋግሜን ሲህር መተት የሚሰራበት ነው በሀገራችን እና ጠተንቀቁ ራቁ ከዚህ ከባድ ወንጀል ከማስራትም ከመስራትምድግምት እና አደገኝነቱ ድግምት እና አህባሽ በሞባይል ጥንቆላ ድግምት ብይኑ እና ቅጣቱ ስለ ሲህር ድግምት እከፋ መጥቶል በከተማ በገጠር ከሲህር መጠንቀቅ ትዳር እዳትይዝ /እዳይዝ የሚደረግ ሲህር ሲህር ምንድነው ሲህር የሚሰራ ሰው መዘዙ ድግምት የሚሰራ ሰው ቅጣቱ የድግምት መድሀኒት የድግምተኝ ሰው መለያዎች ስለ ድግምት ጥያቄዎች አሲቂኙ ጠንቆይ አርባ ያሲን መቅራት ስለ ድግምት እና ጠንቆይ የሲህር አደጋዎች ወደ ጠንቆይ መሂድ ቃልቻ እና ጠንቆይ ጠንቆይ የሚፈራ ሰው ደፋር ጠንቋዮች
Repost from الّدَاء و الّدَوَاء 📖
شـــــ« كتاب »ــــــرح
الــداء و الـــــدواء
الــــــــــــ[ الاول ]ـــــــدرس
فضيلة الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله
⿻ ︙@alsaa9 📖
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ያ ወዱድ!...
ስሞችህን ልጥራ - ደግሜ ደግሜ
ኢላሂ!... ልበልህ - ሁሌ ደጋግሜ
ያረሂም! ልበልክ - ሁሌም እንዳቅሜ
ፈውስ እንዲሆነኝ - ላልሻረው ህመሜ
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«ኢኽዋን ማለት ይህ ነው ።»
የሱዳን ምድር ፈርጥ የካርቱም ድምቀት ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂሪ ሀፊዞሁሏህ ስሟቸው ይህን ጀግና
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
«አሁን የመጡት መሪያችን (ዶር አብይ አሕመድ ዓሊ) የአባታቸውና የአያታቸው ስም የእኛ እምነት ስለማይመስል ከተመረጡ ጀምሮ እንቅልፍ አልወሰደንም»
የአፓርታይዷ ቄስ የኢትዮጵያን መሪ ስሙ ከሱ ስም ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት፣ መለየት የለበትም ብሎ ያምናል😎
ለማንኛውም ከእነዚህ ጋር ነው እየኖርን ያለነው። እነዚህ በሙስሊሙ ላይ በአከባቢያቸው እየፈጸሙት ያለ ግፍ መፈጠርን ያስጠላል።
መረጃው ከ ትግራይ ሙስሊም ሚድያ ገፅ የተወሰደ ነው።
ህወሓትም ቢሆን ከዚህ የተሻለ አመለካከት የለውም። በፌዴራል መንግስት ተገፍቻለሁ እያለ ዞሮ የክልሉን ሙስሊሞች በሃይማኖታቸው ሰበብ በያይነቱ የግፍ አይነት ያወርድባቸዋል። አቅሙ በቀለለበት በዚህ ጊዜ በደል ከመፈፀም ያልተመለሰ ድርጅት ያለ ተቀናቃኝ አገር ቢቆጣጠር ክፋቱ ከዚህም የባሰ ነው የሚሆነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
👁👁👁👁አስደሳች ዜና
የአወሊያ የጤና ማዕከል መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ካደረገው የአል - በስር ኢንተርናሽናል ፍውንዴሽን ጋር በመተባበር ነፃ የሆነ የአይን ሞራ ገፋፋ ህክምና ከ መስከረም 4 እስከ 7/ 2019 አ.ል ይሰጣል።
👉በመሆኑም ከጳግሜ አንድ ጀምሮ ዊንጌት ተሻግሬ በሚገኘው የአወሊያ ጤና ጣብያ መጥተው መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስንገልፃላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
👉ለበለጠ መረጃ
+251911599329
+251912410372
👉ይደውሉ
እባክዎ መረጃውን share ያድርጉ
Telegram
ይህች ሰብብ ልትሆን ትችላለች ቁርዓን ለመቅራት የተቸገሩ ካሉ ከዉጪ የመጡ የአይን ሀኪሞቾ በነፃ ... ሼር አድርጉላቸው
@cataract2026
በሕይወት መንገዳችን ላይ ከምናገኛቸው ሰዎች ጋር የምንመሰርተው ግንኙነት ልክ እንደ እሳት ነው።በጣም ከቀረብነው ያቃጥለናል።በጣም ከተራራቅን ደግሞ ብርዱ ይበርደል።በሰዎች መካከል የሚኖር ጤናማ ርቀት የፍቅር ማነስ ሳይሆን የትስስር መኖሪያና የዘላቂነት ሚስጥር ነው።
ብዙዎቻችን በፍቅር ወይም በጓደኝነት ስም በሰው ላይ እንጣበቃለን። ያለ እሱ/እሷ መኖር የማንችል ያህል መሄጃና መድረሻችንን በእነሱ መዳፍ ላይ እናስቀምጣለን። ነገር ግን ሰውን ከልክ በላይ ስንቀርበው አክብሮቱንና ግርማውን ያጣል።
ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ከፍ ካለ የክብር ዙፋናችን ላይ አውርደው ሲጥሉንና ሲያዋርዱን የምንደነግጠውም ለዚህ ነው። ያኔ «እኔው ነኝ ያበዛሁት፣ የቀበጥኩት፣ ራሴን አሳልፌ የሰጠሁት…» ብሎ በቁጭት ከመቃጠል ቀድሞ ርቀትንና ወሰንን ማወቅ አስተዋይነት ነው።
ሰውን ስትወድ ሰው መሆኑን አትርሳ። ሰው ደካማ ነው።ተለዋዋጭ ነው። ዛሬ ያከበረህን ነገ ሊረሳው ይችላል።
ስለዚህ ውደታህን በልክ አድርግ።
አቅምህን እና ሙሉ ልብህን ሙሉ በሙሉ በሰው ላይ አታፍስስ። ለራስህ የሚሆን ስሜትና ክብር አስቀር።መጠነኛ ክፍተት ተው።በሁለት ዛፎች መካከል ክፍተት ሲኖር ሁለቱም አየርና ፀሐይ አግኝተው እንደሚያድጉ ሁሉ፣ በጓደኝነት መካከልም ያለ ክፍተት ግንኙነቱ መተንፈስ አይችልም።
ራስህን አትጣል። ሰው እንድወድህ ብለህ ማንነትህንና ክብርህን አታጣጣል። ርቀትህን መጠበቅ ማለት ሰዎችን መጥላት ወይም መሸሽ አይደለም።ይልቁንም ሰዎችን በነበሩበት ቦታ አክብሮ የማስቀመጥና የራስንም ስሜታዊ ደህንነት የመጠበቅ ጥበብ እንጂ። ውደታህ ሚዛናዊ፣ ትስስርህ ደግሞ የጠጠረ ይሁን።
የተወሰደ
Repost from N/a
ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ
ማስታወቂያዎችን በአንድ ቻናል ላይ በነጻ
ማስተዋወቅ እንዲሁም ስራ ለማግኘት ከፈለጉ
Halal Jobsን ይቀላቀሉ!👇
Repost from []ትዳር የአማኞች ምሽግ[]
🌸 የሴት ልጅ አንደበት 🌸
እህቴ ሆይ፣ አንደበትሽ ትንሽ አካል ቢሆንም በአላህ ዘንድ ያለው ሀላፊነት ግን ትልቅ ነው
በአንድ ቃል ሰውን ልታስደስቺ ትችያለሽ በአንድ ቃልም ልብን ልትሰብሪ ትችያለሽ።
قال الله تعالى:
﴿مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ﴾
“ሰው ማንኛውንም ቃል ሲናገር ከእርሱ ጋር የሚመዘግበው ጠባቂ አለ።”
[ሱረቱ ቃፍ፡ 18]
🌷ከሐሜት ተጠንቀቂ
አላህ በቁርአን እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَا يَغْتَبْ بَعْضُكُمْ بَعْضًا﴾
“አንዳችሁ ሌላውን አትማሙ።”
[ሱረቱል ሑጁራት፡ 12]
እህቴ፣ በሌለችበት ስለ አንዲት እህትሽ የምትናገሪው ነገር እሷ ብትሰማው የምትጠላው ከሆነ ይህን ንግግር አቁሚ።
🌸መልካም ቃል ተናገሪ
رسول الله ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مَن كانَ يُؤمِنُ باللهِ واليومِ الآخِرِ فليَقُلْ خيرًا أو ليَصمُتْ»
“በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምን ሰው መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል።”
[ቡኻሪና ሙስሊም]
💎 እህቴ ሆይ፦
• ከሐሜት አንደበትሽን ጠብቂ።
• ከሐሰት ንግግር ራቂ።
• ሰውን በቃልሽ አትጉጂ።
• ቁጣ ላይ ሆነሽ ከመናገር ተቆጠቢ።
• መልካም ቃልን ልማድሽ አድርጊ።
• ዝምታሽ ከክፉ ንግግር የተሻለ ከሆነ ዝም በይ።
🌿 አስታውሺ፦
አንደበትሽ የምትናገሪውን ሁሉ የሚመዘግብ አለ ስለዚህ ከመናገርሽ በፊት “ይህ ቃል አላህን ያስደስተዋል?” ብለሽ ራስሽን ጠይቂ።
አላህ ሆይ! አንደበታችንን ከሐሜት ከሐሰትና ከክፉ ንግግር ጠብቀን መልካም ነገር የምንናገር ባሮችህ አድርገን። آمين
ተው በሉት ሙስሊሙን!
~~~
ተው በሉት ሙስሊሙን አቅጣጫውን ሳተ፤
ጳጉሜ ናት እያለ መተቱን አተተ፤
ጳጉሜ በረካ ናት ሲልም ወተወተ፤
በጠንቋይ በሰይጣን መረብ ተጎተተ፤
ቁርአንን የሚያህል መመሪያ እንደሌው፤
ሐድስን የሚያህል መመሪያ እንደሌለው፤
ነቢዩን የሚያህል ነብይ እንደሌለው፤
ሙስሊሞች ሲጀመር ጳጉሜን አያውቋትም፤
በሸሪዓችን ውስጥ ማስረጃ የላትም
ማስረጃውን ያምጣ ጳጉሜ ያላት ማነው፤
በቁርአን አመቱ አስራ ሁለት ወር ነው፤
ደግሞ ከዚህ በላይ ልቤን የሚያደማው፤
ጳጉሜ የዱዓ ቀን ብለው ሲዋሹ ነው፤
የሀገሬ ቃልቻ ተው አላህን ፍራ፤
ዱዓ እያልክ አትዙር ወጣ ብለህ ስራ፤
ዑለማኦች ቢናገሩ ጃሂሎች ቢሰሙ፤
ጳጉሜ የመጣችው ከነቄስ ቀለሙ፤
ህዝባችን ተገሰፅ እረ ተው አስተንትን
ሙስሊም አያውቀውም ቅዱስ ዮሀንስን፤
አምስት ቀን ሆኖ በወር የሚጠራ፤
ጳጉሜ እየተባለ ሁሌም የሚወራ፤
በሐበሻ ምድር በእውነተኞች አለም፤
የወራት ድቃላ ጳጉሜ የሚባል የለም፤
ድሮም አቋሜ ነው ዛሬም ደጋግሜ፤
እኛ ሙስሊሞች ነን ወር የለንም ጳጉሜ፤
እዛ ጥግ ላይ ይሰማል ስማ በደንብ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ።
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«መንሐጀን አትንኩብኝ እኔን እንደፈለጋችሁ»
♦️.......ሰለፍያ......♦️
በጠላቶች ብዛት ከቶ እማትሰበር፡
ከአሏህ መታረቂያ ያላት ግሩም ድንበር፡
የቅዱሳን እምነት የሰማይ መግቢያ በር፡
ከትናንት እስካሁን የማትጠልቅ ጀንበር፡
......ሰለፍያ.....
ጥመት በሙሉ ደቆ በስርሽ ይሁንሽ ብናኝ፡
ዝናሽ አፅናፉን ያዳርስ ስምሽ በአለም ይናኝ፡
እኔም በአንች ልታወቅ ስሞትም ጀነትን ይቅናኝ፡
.....ሰለፍያ.....
አንች ነሽ የኔ ማንነት ስምሽ ነው የኔ ሰላሜ፡
የወንድነቴ መለኪያ የውስጤ ውብ ልምላሜ፡
ማንም በስሜት ጡዞ አይናገሩሽ አለሜ፡
አንች ነሽ የስንኘ ጫፍ አንች ነሽ ጌጥም ቀለሜ፡
..ሰለፍያ.....
ፍኪልኝ ልዩ መንሀጄ
አድምቂኝ በፍቅርሽ ጠረን፡
በህግሽ ተቆጣጠሪኝ
ፈር ለቅቄ እንዳልሔድ ምረን፡
ሰምና ወርቅ ነን እኛ
መግለጫ ቃላት ያጠረን፡
አንችን እንድከተልሽ
አሏህ ነው ያስተሳሰረን፡
.....ሰለፍያ.....!!
ድመቂ ነግሰሽ በምሽት ሆነሽ እንደ ጨረቃ፡
በቀን እንደ ፀሀይ ፍኪ የለሽም አንች ፈረቃ፡
ማን አለ አንጀት የሚያርስ እንደ አንች የሚያጠረቃ፡
ምርጥ ነው በአንች የሚመረጥ ከሰዎች ቀድሞ የነቃ፡
ፍቅር ትግስት የሆንሽኝ መንሐጄ አንች ነሽ በቃ‼️
.....ሰለፍያ....
ከፍ በይ ለዘላለሙ ክበሪ በልቤ ዙፋን፡
ፅኑ ነን ታላቅ አለቶች፤
ማዕበል ደፍሮ እማይገፋን፡
ወላሒ በአንች ከፀናን፤
መቼም ነው ውሉ እማይጠፋን፡
ከጥመት ከሽርክ ጋራ፤
ምን አለን ከቶ እሚያጋፋን⁉️
ልጆችሽ በአንች ላይ ቆመን፤
ማንም ላይ በደል አንሰራም፡
ግን ደግሞ ልንገርሽ፤
አንችን ከመጡብን
መልስ አለን ሰዎች አንፈራም፡
ለሚዲያ ጯሒ ለፌስ-ቡክ አርበኛ፡
ለፌክ ባለሙያ ለቲክቶክ ግንበኛ፡
ታብ ታብ አርጉ እያለ ሲያላዝን ለሚውል፡
እውቅና ለበላው ለዛ እማያስተውል፡
ለቁጥብያ ሙሪድ ለበናዕይ አሽከር፡
ሱሩርይ ሆኖ ጠሞ ሲከራከር፡
ቁርዓንና ሀዲስ በጥርሳችን ነክሰን፡
መልካሙን አረዳድ ከሰለፎች ጠቅሰን፡
ውብ መንሀጃችንን ሀሰዝቡ ላይ አንግሰን፡
ውድ ነፍሳችንን ለሐቅሽ ለግሰን፡
ላንች ክብር መኖር ይህ ነው አላማችን፡
አብረቅራቂ ሰንደቅ ከፍ በይ አርማችን፡
አንፈልግም ኢኽዋን የኮተት ገለባ፡
አንጠጋም ሱፍይ ለጫታም ገሪባ፡
ሱና ነው ሐቃችን ጀነት እስክንገባ፡
ስለሆነም ባንች አንደራደርም፡
ካንች ውጭ ሌላ መስመር አናሰምርም፡
በአንች ላይ እንፅና ሌት ቀን ሳንሳቀቅ፡
ባንድራሽን ይዘን ዱንያን እንላቀቅ፡
እንደ ጥመት ሙሪድ የለንም ኮፍያ፡
አቂዳ ሱና ነው ደዕዋ ሰለፍያ፡
....በኑረዲን አል-አረብ..✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
ኢላሂ!
የልቤን ክጃሎት የቀን ከለት ህልሜን፣
ጌታዬ ታውቃለህ ሀሳብ ሰመመኔን፣
ቀን በሀሳብ ጨርሶ መንገድ የሚያስተኝ፣
ሌት በትዝታ አሻግሮ እንቅልፍ የሚነሳኝ፣
ሳልነግርህ ታውቃለህ ጌታዬ ጀሊሉ፣
የልቤን ታውቃለህ የውስጤን በሙሉ፣
አይኔ በእንባ ጎርፍ ለምን እንደራሰ፣
ልቤ በደም ጭቃ እንደተላወሰ፣
ነጋሪ ሳያሻህ ህመሜን ታውቃለህ፣
ሱጁድ ተደፍቼ አንተን ስለምንህ፣
እንባዬ ቢደርቀም ብጎዳም በናፍቆት፣
መቻሉ ቢያቅተኝ የልቤን ስብራት፣
ኢላሂ እላለሁ ያረቢ እላለሁ፣
አሳካልኝ ብዬ - እለምንኃለሁ፣
የልቤን የውስጤን ስነግርህ ሳነባ፣
አሳካልኝ ብዬ ሁሌ ነጋ ጠባ፣
የለመንኩህ ጀሊል ድካሜ በዝቶ ነው፣
አቅሙ እንደሌለኝ ስለተረዳውት ነው፣
አንተ በእዝነትህ
ሁን በሚለው ቃልህ፣
እስክትፈርደው ድረስ ሁሌም ልለምንህ!
አብዱ ረህማን አማን
