ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
319
المشتركون
-124 ساعات
-27 أيام
+5430 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኹጥባ በተቻለ መጠን፡
* ቃላቱ የተከሸነ፣
* መጠኑ የተመጠነ፣
* መልክቱ ወቅቱን ያማከለ፣
* አቀራረቡ ታዳሚውን ያልዘነጋ ቢሆን መልካም ነው።
ኸጢቦች ሆይ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ሰዎች ውጭ ላይ ከባድ የቀትር ፀሐይ ቃጠሎ ሲያንቃቃቸው ወይም ዝናብ ሲዘንብ እንኳ ርህራሄ ቢኖራችሁ መልካም ነው። ሰዎች እየተከፉ ዒባዳቸውን እንዲፈፅሙ አታድርጉ። "ከናንተ ውስጥ አስበርጋጊዎች አሉ" የሚለውን ሐዲሥ አስታውሱ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (41)
~
የብዙ ፈተናዎችና ብጥብጦች ሰበብ ሶብር ማጣት ነው። በሚገጥሟቸው ፈተናዎች ተበሳጭተው ወደ ሃይልና ብጥብጥ በመግባታቸው የተነሳ ስንቶች ህይወታቸውን አጥተዋል?! ስንቶች አካላቸው ጎድሏል?! ስንቶች ንብረታቸው ወድሟል?! ስንቶች ለረጅም የወህኒ ቆይታ ተዳርገዋል?! ስንቶች ቤተሰቦቻቸውን አጥተው የቁጭት እሳት እየለበለባቸው ነው?! ስንቶች አገራቸውን ጭምር አጥተዋል?! ስንቶች መስጂዳቸውን፣ ደዕዋቸውን፣ ዲናቸውን አጥተዋል?! በሶብር ማጣት ስንቶች ትዳራቸውን አጥተዋል?! ስንቶች የተሻለ ስራቸውን አጥተዋል?! ሶብር ማጣት ብዙ ነገር ነው የሚያሳጣው።
ብዙዎች ከሶብር የሚርቁት ወደ ዓላማቸው ለመድረስ ካላቸው ጉጉትና ችኮላ የተነሳ ነው። ነገር ግን የሚዘነጉት ነገር ሶብር በራሱ ወደ ዓላማ መቃረቢያ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ነው። በሶብራቸው ደካሞች ካለሙበት ደርሰዋል። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِینَ كَانُوا۟ یُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَـٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَـٰرِبَهَا ٱلَّتِی بَـٰرَكۡنَا فِیهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ بِمَا صَبَرُوا۟ۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ یَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُوا۟ یَعۡرِشُونَ }
"እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆቿንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው። የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስ ^ራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን።" [አልአዕራፍ፡ 137]
ፈተና ሲገጥመን ሶብር ላይ፣ ዱዓእ ላይ፣ ጥረት ላይ መበርታት ይገባል። ያኔ ፈተናው በአላህ ፈቃድ ይገፈፋል። ኸባብ ብኑል አረት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
شَكَونا إلى رَسولِ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم وهو مُتَوسِّدٌ بُردةً له في ظِلِّ الكَعبةِ، فقُلنا: ألا تَستَنصِرُ لنا، ألا تَدعو لَنا؟ فقال: قد كان مَن قَبلَكُم يُؤخَذُ الرَّجُلُ فيُحفَرُ له في الأرضِ، فيُجعَلُ فيها، فيُجاءُ بالمِنشارِ فيوضَعُ على رَأسِه فيُجعَلُ نِصفَينِ، ويُمشَطُ بأمشاطِ الحَديدِ ما دونَ لَحمِه وعَظمِه، فما يَصُدُّه ذلك عن دينِه، واللهِ لَيَتِمَّنَّ هذا الأمرُ، حتَّى يَسيرَ الرَّاكِبُ مِن صَنعاءَ إلى حَضرَمَوتَ، لا يَخافُ إلَّا اللهَ، والذِّئبَ على غَنَمِه، ولَكِنَّكُم تَستَعجِلونَ.
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ በከዕባ ጥላ ስር ኩታቸውን ተንተርሰው ሳሉ ስለሚደረስብን መከራ አቤቱታ አቀረብንላቸው፤ ‘እርዳታን አትለምንልንምን? ዱዓእ አታደርግልንምን?’ አልናቸው።
እርሳቸውም እንዲህ አሉ። ‘ከእናንተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ዘንድ አንድ ሰው ተይዞ መሬት ይቆፈርለትና በውስጧ ይገባ ነበር፤ ከዚያም መጋዝ መጥቶ በራሱ ላይ ይደረግና ለሁለት ይከፈል ነበር። በብረት ማበጠሪያዎችም ሥጋው ከአጥንቱ ይበጠር ነበር። ይህ ሁሉ ግን ከሃይማኖቱ አይመልሰውም ነበር። በአላህ እምላለሁ! ይህ ጉዳይ (እስልምና) ሙሉ ይሆናል! ተጓዥ ከሰንዓ ተነስቶ እስከ ሐድረመውት ድረስ፣ ከአላህና በበጎቹ ላይ ከሚመጣ ተኩላ በስተቀር ምንም የሚያፈራው ነገር ሳይኖር የሚጓዝበት ጊዜ ይመጣል። ነገር ግን እናንተ #ትቸኩላላችሁ።’ " [አልቡኻሪይ፡ 6943]
አስተውሉ! ያ ሁሉ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ስሞታ ቢያሰሙ ነው "ትቸኩላላችሁ" ብለው የገሰጿቸው። ከዚህ የማይቀርቡ ፈተናዎችን መታገስ አቅቶን ለስንት የባሰ መከራ ተደርገናል?! ይልቁንም አስፈላጊ ሰበቦችን በማድረስ እንደታዘዝነው በመታገስ ፈረጃን ከአላህ እንጠብቅ። ካልሆነ ግን የሚቀረው ምርጫ የከፋና የመረረ ይሆናል። አዎ! ሶብርን መልቀቅ ለከፋ ፈተና መጋለጥ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
عامة الفتن التي وقعت من أعظم أسبابها: قلة الصبر؛ إذ الفتنة لها سببان: إما ضعف العلم، وإما ضعف الصبر
"የደረሱ ፈተናዎች (ሁከቶች) እንዳለ ከዋና መንስኤዎቻቸው ውስጥ አንዱ የትዕግሥት ማነስ ነው። ምክንያቱም ለፈተና ሁለት መንስኤዎች አሉት፡ ወይ የእውቀት ማነስ ወይም ደግሞ የትዕግሥት ማነስ ናቸው።" [አልፉሩዕ፡ 10/181]
||
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 16 /1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
⏩አድስ ሙሃደራ ርዕስ👇👇
↪️በተውሂዳችን ላይ ድርድር የለንም።
✅በውስጡ የተወሱ ነጥቦች
➲ ሀገራችን ላይ የሚሰሩ ሽርኮች በዝርዝር የተዳሰሱበት ነው
➲ማይባር፡ንጉስ፡አርባጫማ፡ላይ ሶባ፡እና ሌሎችም የሽርክ ቦታወች ና ሽርኮች እንዲሁም በዝርዝር ታይተዋል።
➲ወጣቶች ይህን ሙሀደራ ተምራችሁ ላልደረሳቸው አድርሱ።
➲የተውሂድን የበላይነት የሽርክን የበታችነት እና አዋራጅነት ለኡማው በዝርዝር አብራሩ።
👉በደንብ ይደመጥ ሺርም እናድርገው
🎙በወንድማችን አቡ ሹራ ሀፊዘሁላህ
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
ከአላህ በስተቀር ሁሉም ምትክ አለው!
የሰው ልጅ ላጣቸው ነገሮች ሁሉ ይብዛም ይነስም ምትክ ( አማራጭ ) ሊያገኝ ይችላል። አላህን ያጣ ( ከርሱ የራቀ፣ እሱን ያስቆጣ ) ሰው ግን ምንም ዓይነት ምትክና አማራጭ መቼም ማግኘት አይችልም።
ስለዚህ መቼም ቢሆን፣ ለማንም ለምንም ብለህ አላህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ!
ዛዱል መዓድ
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ናፈቀኝ ገጠሩ፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ጎራው ሸንተረሩ፤
👉ያደኩበት ሀገር ናፈቀኝ መንደሩ፤
👉የተጫወትንበት ያ የ ድንጋይ ቤቱ፤
👉ናፈቀኝ እቃቃው ያየጭቃ ድስቱ፤
👉ያ የድንጋይ ምጣድ የቅጠል እንጀራ፤
👉በጭቃው ጀበና በጠጠሩ ሲኒ
ቡና ጠጡ ብለን ጎረቤትት ስንጠራ፤
👉ቅጠሉን ጎዝጉዘን አርሂቡ ኑ ብለን፤
👉ቡናውንም ቀድተን ቁርሱንም አድለን፤
👉ያኔ ያ ጫወታ የቀልድ ቢሆንም፤
👉ልዩ #ትውስታ አለው ያለፈ ቢሆንም፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ያ የቦረኩበት፤
👉ያ የወንዝ ውሀ የተራጨንበት፤
👉ቦይ እያበጀን የተጫወትንበት፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ሜዳው ሸንተረሩ፤
👉ሲጠማን ጠጥተን፣
👉የዱር ፍሬበልተን፣
👉ዳቦው ተገመሰ፣
👉ጫወታው ፈረሰ፣
👉ብለን ተባብለን ልክ ስንለያይ፤
👉እንሸኛኝ ነበር ተባብለን ባይባይ፤
👉በደህና እንገናኝ ደህና እደሩ፤
👉ምጣዱ ተሰብሮ ሳትበሉ እደሩ፤
👉የቅጠሉን ጫማ እግራችን ጠምጥመን፤
👉ዱፍ ዱፍ እያልን ስንሄድ ሰልፍ ይዘን፤
👉ያየን ሰው ሁሉ በኛ ሲስቅብን፤
👉ትንንሽእንደሄድን ቁርጥርጥ ሲልብን፤
👉ውሀ ሂዶ ሂዶ ጭረቻው ቀሪ ነው፤
👉ትዝታውን ትቶ ቀን ሁሉ ዘማች ነው፤
👉የወፎቹ ጩኸት ቀዝቃዛው አየሩ፤
👉ሰላሙ የሚያምር ሰው ገራገሩ፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ሜዳው ሸንተረሩ፤
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወላጆችህን ከቻልክ አቅምህ በሚፈቅደው አስደስታቸው። ካልሆነልህ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የመከፋታቸው፣ የመጨነቃቸው፣ የመተከዛቸው ሰበብ አትሁን። "አይዟችሁ"፣ "ከጎናችሁ ነኝ" ማለት ቢቀር "አትስጉ፣ ደህና ነኝ" ማለት ልናሳጣቸው አይገባም። ሰርቶ ማገዝ፣ ከጎን መቆም ካቃተ፣ ፊትን ከመከስከስ፣ የሻከረ ቃል ከመናገር መቆጠብ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
▶️ተጀመረ - ክፍል 4 - 😂😘
አዲስ የኪታብ ደርስ📚ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 - - https://t.me/sefinetunuh?livestream=75d18b52dfdccaf7d2
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አላህ እንዲህ ይላል፦
{ یَوۡمَىِٕذࣲ تُحَدِّثُ أَخۡبَارَهَا }
"በዚያ ቀን (ምድር) ወሬዎቿን ትናገራለች።" [አዝ-ዘልዘለህ፡ 4]
ወሬዎቿን ማለት በገጿ ላይ የተፈፀመን ሁሉ ማለት ነው። በቂያማ ቀን ምድር በላዩዋ ላይ የተፈፀመን ክፉም ሆነ ደግ ትናገራለች። ምድር ላይ ስንትና ስንት ተመልካች ምስክር የሌለባቸው ወንጀሎች ተፈፅመዋል?! ስንት ነፍስ ጠፍቷል?! ስንት ንብረት ተወስዷል/ ወድሟል?! ስንት ግፍ ተፈፅሟል?!
ቢሆንም ሁሉ ከንቱ አይቀርም። ያኔ ምድር ትናገራለች፣ አካላት የሰሩትን ይመሰክራሉ። ከፍጡር እይታና ትዝብት፣ ከፍትህ የተረፉ የመሰላቸው ሰዎች የሚያፍሩበት ቀን ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
+6
👂👂👂ወቅቱ ክረምት ነው!!!
ት/ቤቶች ዝግ ሲሆኑ በተቃሪኒው ደግሞ እስላማዊ ተቋሞቻችን
👉ቁርአን በሚቀሩ
👉አቃዳ በሚማሩ
👉አህካሞችን እና ሌሎች የአረብኛ ትምህርቶችን በሚቀስሙ ተማሪዎች የሚጨናነቁበት ወቅት ነው። ስለዚህ ለልጆቻችሁ እነዚህን መጽሐፍቶች በብዛትም ይሁን በነጠላ እንዲሁም መድረሳ ገብተው ለሚማሩ የዲን ተማሪዎች ገዝታችሁ ወቅፍ ማድረግ ለምትችሉ ሙስሊም ወንድምና እህቶች መከተበቱ ሱና (ደሴ) ኩቱቦች በብዛትም ይሁን በነጠላ በምትፈልጉት መልኩ እዘዙን በምታዙን ቦታ ሁሉ በፍጥነት እናደርሳለን እያሉ ይገኛሉ።
👌ስለዚህ ሙስሊሙ ለጀመረው የቀለም አብዮት "1ቁርአን ለአንድ ልጅ" የሚለውን መርህ ተከትላችሁ ወቅፍ በማድረግ የአኼራ ቤታችሁን ገንቡ እንላለን!!!!!!!
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ህክምና በጣም ምርጥ ሙያ ነው። በዚህ ትልቅ ሙያ ላይ የተሰማራ ሰው ከገንዘብ ያለፈ ኒያ ሊኖረው ይገባል። ቅንነት፣ ተቆርቋሪነት፣ ሐቀኝነት፣ ሰው አክባሪነት ሲኖረው ስሙም፣ ዋጋውም፣ ቦታውም ይለያል። የተጎዳን፣ የተጨነቀን ሰው መፈረጅ ዋጋው በምን ይገለፃል? ክፋት፣ ማታለል፣ ግዴለሽነት ከሌለበት እና አላህን ካሰቡበት ሁሌም ዒባዳ ላይ ፣ ሁሌም አጅር የሚያስገኝ ዘርፍ ላይ ነው የተሰማሩት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from 🍃 العلم نور المؤمن 🍃
ልጁ ሶላተል ፈጅርን ስላሳለፈ መጫዎቻውን ሸጠበት
ይህ ነው ትክክለኛ አባት ማለት ይህ ነው ኢስላማውይ ተርብይል ማለት ያረብ ሰው አርገን ያረብ በነብስያችን ላይ አግዘን ያረብ ሀቅህን እንኳን መወጣት አልጀመርነውም ያረብ እራሳችንን በዳዮች ሆን
https://t.me/Eslamikkk
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
🟢አዲስ ደዕዋ
ርዕስ:– የአላህን ድንበሮች እንጠብቅ።
የተውሒድ አሳሳቢነት እና የሽርክ አደገኝነት በሰፊው ተዳሷል።
ደሴ ከተማ አሬራ ሰላም መስጂድ የተደረገ
🎙🎤በኡስታዝ አቡ ሒዛም (አብዱረህማን ሰዒድ)
🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088
فَفِرُّوۤا۟ إِلَى ٱللَّهِ
إذا أردت النجاة من كل الاهوال التي نزلت!!!
ففروا الى الله ..
إذا ضاقت بك الارض بما رحبت!!!
فالجأ اليه سبحانه ..
سبحانك اللهم لا ملجأ منك إلا اليك🌸
Repost from SadatKemal Abu Meryem
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለይለተል ኢስራ ወል ሚእራጅ ሰባት ሰማያትን አቋርጠው ሲሄዱ በያንዳንዱ ሰማይ ያገኟቸው ነብዮች የሚከተሉት ናቸው
1ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ አደም፣
2ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ዒሳን እና የህያ፣
3ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ዩሱፍ፣
4ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ኢድሪስ፣
5ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ሀሩን፣
6ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ሙሳ፣
7ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ኢብራሂም ናቸው።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
Repost from SadatKemal Abu Meryem
መውሊድ የሺርክ መነሀሪያ ለመሆኑ እጅ ከፍንጅ ማስረጃ።
አስደንጋጭ ቪድዬ
አማራ ክልል ያለ በአላህ ላይ ማጋራት፡፡
ይህን ቀብር አምላኪዎች አላህን ትተው እንዲህ ይላሉ
“ጤና ስጡን እንላለን፣ ጤና እናገኛለን፡፡….”፣
ከአላህ ውጭ ይህን ቀብር ውስጥ ያለ ለራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ሙት “ልጅ ስጠን ብለው” ስለት ይሳሉለታል፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በአላህ ላይ ማጋራት ለሁለት ሀገር ውርደት ይዳርጋል፡፡
የአላህን እርዳታ ከሺርክ፣ ከቢድዓ፣ ከወንጀል እና አላህ ከጠላው ሁሉ ካልራቅን ማግኘት አንችልም፡፡
አላህ የተውሒድ እና ሱና ዘቦች፣ ሺርክ እና ቢድዓን የሚፀየፉ፣ የሚርቁ፣ የሚጠነቀቁ እና የሚያስጠነቅቁ ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
🎙 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
ተቀርተው የተጠናቀቁ ሙሉ ዱሩሶችን በቀላሉ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑት
0⃣1⃣ ኪታቡ ተውሒድ ፈውዛን 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1659
0⃣2⃣ ኡሱሉ ሱና ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሃምበል 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1760
0⃣3⃣ ቀዋዒዱል አርባኣ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1768
0⃣4⃣ አርባዒን አነወዊያ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1802
0⃣5⃣ ሀዚሂ ደዕወቱና ወአቂደቱና 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/1827
0⃣6⃣ ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳህ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2030
0⃣7⃣ ሚን ዑሱል አቂደቱል አህለ ሱና ወል ጀማዓ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2049
0⃣8⃣ ዓቂደቱል አህሊ ሱናቲ ወልጀማዓሕ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2068
0⃣9⃣ አቂደቱ ሰለፍ ወዓስሓቡል ሓዲስ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2406
1⃣0⃣ ሰላሰቱል ኡሱል (ኡሱሉ ሰላሳ) 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2460
1⃣1⃣ ፈትሁ ረቡል በሪያ ቢተልኺሲል ሃመዊያ (ተልኺስ)👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2562
1⃣2⃣ ኪታቡ ተውሒድ ሙሓመድ አብዱል ወሓብ👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2644
1⃣3⃣ሸርህ አቂደቱል ዋሲጢያ ሊል ኻሊል ኻራስ👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2836
1⃣4⃣ ዑምደቱል አሕካም ሚን ከላሚ ኸይሪል አናም👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/2984
1⃣5⃣ ሸርሁ መንዙመቱል ሓዒያ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3207
1⃣6⃣ አል ኡሱል ሚን ዒልመል ኡሱል 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3265
1⃣7⃣ ሸርሑ ሙስጦለሁል ሓዲስ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3428
1⃣8⃣ ኹዝ አቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወሱነቲ ሰሒሓ
👇https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3461
1⃣9⃣ ኢና ኩና ፊ ጃሂሊያ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3497
2⃣0⃣ ሙምቲዕ ሸርሑ አል አጅሩሚያ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3749
2⃣1⃣ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ ሊል ዑሰይሚን 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3882
2⃣2⃣ ተብሲሩል ኸለፍ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3913
2⃣3⃣ ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዷን 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3925
2⃣4⃣ ሚንሐጅ ፊርቀቱ ናጂያ ወጧኢፈቱ መንሱራ 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/3985
2⃣5⃣ ኹላሰቱል ኑሪል የቂን ጁዝ —1 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4025
2⃣6⃣ ተብሲሩል ባዲዒን ቢስጢላሓት አል ሙሓዲሲን 👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4073
2⃣7⃣ ቀዋዒዱል ሙስላ ፊ ሲፋቲላሂ ወዓስማኢል ሑስና👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4125
2⃣8⃣ ረውደቱል ባዲዒን ሚን አሓዲሲ ሰይዲል ሙረሰሊን👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4145
2⃣9⃣ ብሉግ አል መራም ሚን አዲለቲል አሕካም👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4448
3⃣0⃣ ተንቢሑ ዘዊል አፍሐም ኢላ ረእቢ ሰድኢ ወልዊአሚ አላ መንሐጅ ሰለፊል ኪራም👇
https://t.me/ABUJUWEYRIYAA/4515
