ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
319
المشتركون
-124 ساعات
-27 أيام
+5430 أيام
أرشيف المشاركات
✍ ቤታችሁን መቃብር አታድርጉት።
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
﴿صَلُّوا في بُيُوتِكُمْ، ولا تَتَّخِذُوها قُبُورًا.﴾
“ሶላትን በቤታችሁ ውስጥ ስገዱ። መቃብር አድርጋችሁ አትያዙት።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 777
በቤታችሁ ስገዱ ሲባል የተፈለገው ከግዴታ ሰላት ውጪ ያሉትን ለምሳሌ የሌሊት ሰላት፣ ዱሃ፣ ተሀጁድ የመሳሰሉ ሱና ሰላቶችን ነው።
https://t.me/Deewaselefyya1448
https://t.me/Deewaselefyya1448
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
ክፍል : 01
📚ኪታብ : አልቀዋዒዱል ሙስላ
🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን
📔የኪታቡን PDF ለማግኘት
https://t.me/sefinetunuh/9009
ደረሱ የሚሰጠዉ
📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ
በኡስታዝ አብዱሰላም ሸህ ሀሰን
ከኡሱሉ ደዕወቱ ሰለፊየህ ደርስ የተቀነጨበ
☝️እጅግ ወሳኝ መልዕክት
እስከመጨረሻው እናዳምጠው
ባረከሏሁፊኩም
Repost from ✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
⭕ ለጫት ቃሚ ወንድሜ(እህቴ)
ስለ ጫት እና ጉዳቶቹ ይወቁ
ጫት ከአምፌታሚን (Amphetamines) ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ኬሚካሎችን ይዟል። እነዚህም የነርቭ ሴሎችን በማነቃቃት ጥቅም ላይ በዋለባቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዓታት የድካም እና የማስመለስ ስሜትን ይቀንሳሉ። በመቀጠል ግን የሰነፍነት፣ የጭንቀት እና የድብርት ስሜት ይከተላል።
👌 ጫት እና ጫት የመቃም ሱሰኝነት በርካታ አካላዊ እና አእምሮአዊ በሽታዎችን ያስከትላል።
👉 በምግብ መፈጨት ስርዓት ላይ ያለው ተጽዕኖ
የጫት ሱሰኞች በአፍ፣ በድድ እና በመንጋጋ ላይ በሚከሰቱ ሥር የሰደዱ ቁስሎች ይሰቃያሉ ። ይህም ለመጥፎ የአፍ ጠረን ዋና ምክንያት ነው። በተጨማሪም ጫት የመቃም ሱሰኝነት የድድ መላላጥን ስለሚያስከትል ለድድ እና ለጥርስ በሽታ ይዳርጋል።
👉 ጫት የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ ለምግብ ፍላጎት ማጣት እና ለሆድ ድርቀት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ይህም ለኪንታሮት (Bawasir) እና ለምግብ እጥረት ይዳርጋል። በአብዛኞቹ ጫት ቃሚዎች ዘንድ የሚታየውን የሰውነት መክሳት እና የጡንቻ ልፍስፍስነትን ያስከትላል።
👉 በልብ እና በደም ዝውውር ስርዓት ላይ ያለው ተጽዕኖ
በጫት ተክሎች ውስጥ የሚገኙት ኬሚካሎች የልብ ምትን እንዲጨምሩ እና የደም ሥሮችን እንዲጠበቡ ያደርጋሉ። ይህም የደም ግፊት ባላቸው ሰዎች ላይ ግፊቱን ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ የደም ግፊት መድኃኒቶችም ግፊቱን ለመቀነስ እንዳይሠሩ ያደርጋል። በተጨማሪም እነዚህ ኬሚካሎች ጤናማ ሰው ለደም ግፊት በሽታ የመጋለጥ እድሉን ይጨምራሉ።
👉በሽንት እና በስነ-ተዋልዶ ስርዓት ላይ ያለው ተጽዕኖ
ጫት ለሽንት መከልከል (የሽንት ማነስ) እና ከሽንት በኋላ ወይም በሚቃምበት ጊዜ ያለፍላጎት የሚፈስ የዘር ፍሰት ዋና ምክንያት ነው። ይህም ጫት በፕሮስቴት (Prostate) እና በዘር ከረጢት ላይ ባለው ተጽዕኖ፣ በሚፈጥረው እብጠት እና ቁርጠት ምክንያት የፕሮስቴት ማበጥን የሚያፋጥን ሲሆን፣ ይህም ወደ ወሲባዊ ድካም ያመራል። በአሁኑ ሰአት በባልና ሚስት መካከል ለፍች መንስኤ እየሆነ ነው።
👉 የነርቭ እና የአእምሮ ተጽዕኖ
ጫት ቃሚው ከአጭር ጊዜ የውሸት ንቁነት በኋላ በቁጣ እና በነርቭ ስሜት ይታወቃል። እንዲሁም ከተቃመ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ አእምሯዊ ስንፍና ያደላና በፍጥነት በጭንቀት፣ በድብርት እና በተቆራረጠ እንቅልፍ ይጠቃል።
👉 ጫት እና ካንሰር
ሐኪሞች በተለይም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በአፍ እና በመንጋጋ ካንሰር መጨመር እና በጫት ሱሰኝነት መካከል ግንኙነት እንዳለ አስተውለዋል። ይህ የሆነው በጫት እርሻ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተፈቀዱ ኬሚካሎች በመረጨታቸው ነው። በተጨማሪም ጫት በሚታኘክበት (በሚቃምበት) ጊዜ አፍ ውስጥ የሚፈጠረው የቆዳ መቧጨር የአፍ ውስጥ ሽፋንን በመቀየር ለካንሰር መከሰት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
👉 ጫት እና ስኳር በሽታ
ጫት የመቃም ሱሰኝነት በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እንደሚጨምር በሳይንስ ተረጋገጧል፤ ይህም ቃሚውን ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድሉን ይጨምራል። እንዲሁም የልብ/የስኳር ታካሚው ጫት የሚቅም ከሆነ ከኢንሱሊን ህክምና ብዙም አይጠቀምም።
ይህ ስለ ጫት የተዘጋጀ የተሟላ ጥናት ነው።
💊 ጤና ለሁሉም 💊
#ሕይወት_ያለ_ጫት_ያማረች_ናት።
#አብረን_ጫትን_እንታገል
Repost from ✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
ጫት!!!!!
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👈| ጫት በአገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፍት እየተለመደ የመጣ አደገኛ በሽታ ሁኗል።
👈| እርሱ በጊዜ ሂደት ወሰን የሌለው መከራ ሆኗል።
👈| ህጻናት፣ ወጣቶችና አዛውንቶች በሙሉ እርሱን በመቃም ተጠቅተዋል።
👈| ሁሉም በእርሱና ከዋጋው መናር የመጣውን ችግር በመቃወም ይቃጠላሉ።
👈| አንዳንዶቹ ስለ ዕቃዎች ዋጋ መናር ያወራሉ፤ ነገር ግን በየቀኑ ሲቃሙ ታገኛቸዋለህ።
👈| ጫት ለመቃም ቃል የገባህ ሰው ሆይ "ቃሚ/ሱሰኛ" ተብለህ መጠራትህ ውርደት ይበቃሃል።
👈| ነገር ግን የሚያስብ ልብም ሆነ የሚያስተውል አእምሮ የለም።
👈| ለሰውነት ፈጣን እርጅናንና ድካምን የሚያፋጥኑ በርካታ ገዳይ በሽታዎችን ያመጣል።
👈| በጥርስና በአፍ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ሳንቆጥር።
👈| ስለዚህ አንዳንዶቹ ተኝተው ሳለ "ጭንቀት/ተጫናኝ (ተኙ)" እንዳይመጣባቸው በመፍራት ለመቃማቸው ምክንያት ሲያቀርቡ ታገኛቸዋለህ።
👈| አንደኛው ጫቱን ተፍቶ ካወጣ በኋላ የተለያዩ ሀሳቦችና ጭንቀቶች ያጠቁታል።
👈| ሲቃም ሳለ ሲገነባና ሲያቅድ ነበር፤ በቅጽበት ግን ሁሉም ነገር ፈረሰ።
👈| ቃሚ ሆይ! ራስህን መመርመር አለብህ፤ እድሜ አጭር ናትና መቼ እንደምትጨርስ አታውቅም፤ በኋላ እንዳትጸጸት።
👈| አንተ ሙስሊም ሆይ! መልካም ሥራዎችን ሥራ፤ ጊዜህን አታባክን፤ ተጠቀምበት።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
👈 ጫት 🌿 የዛሬውና የመጪው ጊዜ ገዳይ ⚔️ ነው፤ ዛሬውኑ ካላቆምነው በስተቀር...፤
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
💜 ጌታዬ ሆይ !!ሰላትን እረፍት ሊያገኙባት እንጂ ከእሷ ለማረፍ ብለው ከሚሰግዱት አታርገን🤲
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
⭕️👉አሏህን የተገናኘ ሰው የቂያማ እለት (የውመል ቂያማ) ፦
ሸይኽን እያመለከ ❌
በቀብር ተበሩክ እያደረገ ከቀብር በረካን እየፈለገ❌
በተሚማ አንጠልጥሎ ተበሩክ እያደረገ❌
አሏህን የተገናኘ።
መልካም ስራ የለውም ፣ ሰባት ገዜ ሀጂ ቢያደርግ ፣ ብዙ የሆኑ የረመዷን ወሮችን ቢፃም፣በጣም ብዙ ሶላቶችን ቢሰግድ አይጠቅመውም።
አሏህ እንዲህ ብሏል፦
وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡
ይሄ ሽርክ ለዚች አገር መከራ ነው
🎤 ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂር (ሀፊዘሁሏህ)
👉⭕️አወ ጀማ ንጉስን፣ ማምለክ ፣ገታን ማምለክ ፣ማይባርን ማምለክ ፣አርባ ጫማን ማምለክ፣የቦረናውን ሸይኽ ማምለክ ፣አናን ማምለክ ፣ዳናን ማምለክ ፣ቁጥብን ከማምለክ ሰይፉ ጨንገሬን ማምለክ፣ ጭሌን ማምለክ፣ ለዛፍ ማረድ፣ በየ ሾላው ስር ከማረድ፣በየ ወንዙ ዳር ከመገበር፣በየሜዳው ላይ ለባድገዝ ድንኳን ጥሎ ከማጫጫስ፣ለጅን መገበር፣ ማረድ፣ቃልማ እያሉ መስከረም መስከረም ጥቁር በግ ገነጣጥሎ ማጫጫስ፣ ነጭ ፍየል ገዝቶ ቃልማ ብሎ ሀገሩን ማዞር፣መቃም ወ~ዘ~ተ የዚች ሀገር በተለይ የወሎ ሙሲባ ማነቆ መከራ ችግር ነው
ነጃ መውጣት ከፈለግን ይህንን አጉል ኮተት እምነት ህዝባችን እንዲተወው መስራት አለብን በተለይ በገጠር ለእናት ለአባቶቻችን ማስተማር ለወገናችን ማሰብ ይኖርብናል።
ወንድም አቡ ሹራ አህመድ
ለተጨማሪ ጠቅ አርጓት👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/5064
https://t.me/Sobabilalmesjid/5064
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 من سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
የቴሌግራም ቻናል፦
=
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
በሐገራችን እና በሌሎች ቦታዎች የሚደረጉ የሀዘን/የለቅሶ ስነ-ስርዓት ልማዶች ህግጋት፦
👉 ሰው በሚሞትበት ጊዜ ማክበር ወይም ድግስ ማዘጋጀት አይፈቀድም። የሟች ቤተሰቦች በዓል/ድግስ ማዘጋጀት፣እርድ ማረድና ለሰዎች ምግብ ማዘጋጀት የለባቸውም። ይህ ሁሉ ከቢድዓ (በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ከተፈጠሩ ነገሮች) እና ከጃሂሊያ (ከእስልምና በፊት የነበረ የመሃይምነት) ተግባራት የሚቆጠር በመሆኑ መተው ግዴታ ነው።
ከጀሪር ብን አብደላህ አል-በጀሊ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንደተወራው፡ "ከሞት በኋላ ከሟች ቤተሰቦች ዘንድ መሰብሰብንና ምግብ ማዘጋጀት ከኒያሃ (ከለቅሶ ዋይታ/ሙሾ) እንቆጥረው ነበር።" (ኢማም አህመድ በትክክለኛ የስነድ ሰንሰለት ዘግበውታል)።
ስለሆነም ሙስሊም በሞተ ጊዜ ለሙስሊሞች የተደነገገው አላህ ዘንድ ምህረትንና እዝነትን እንዲለምኑለት እንዲሁም እነዚህን የጃሂሊያ ድግሶች እንዲተዉ ነው። ነገር ግን ጎረቤቶቻቸውና ዘመዶቻቸው ለሟች ቤተሰቦች ምግብ ሊሰሩላቸው ይደነገጋል።
ምክንያቱም በሙሲባው (በመከራው) ተጠምደዋልና። ከአብደላህ ብን ጀዕፈር ብን አቢ ጣሊብ (ረዲየላሁ ዓንሁማ) እንደተረጋገጠው የጀዕፈር ብን አቢ ጣሊብ የሞት ዜና በሶሪያ ምድር በተደረገው የሙዕታ ዘመቻ ተ7ድለው ወደ መዲና በደረሰ ጊዜ ነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለጀዕፈር ቤተሰቦች ምግብ እንዲሰሩላቸው አዘዋል።
የሟች ቤተሰቦች ግን ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ለሰዎች ምግብ ማዘጋጀት የለባቸውም።
የቴሌግራም ቻናል፦
=
http://t.me/Deewaselefyya1448
http://t.me/Deewaselefyya1448
ራሳቸውን ወደ ሱና በሚያስጠጉ አካላት ላይ በሰፊው ከሚታዩ ነውረኛ ተግባራት ውስጥ አንዱ ሰዎችን በተመለሱበት ጉዳይ መክሰስ ነው። አንድ ሰው ከሆነ የተሳሳተ አቋም ወይም ጥፋት ከተመለሰ ያንን ጉዳይ #እያወቀ ሆን ብሎ በሱ ላይ የሚለጥፍ ሰው
1ኛ፦ ዋሾ ነው።
2ኛ፦ ውሸትን የደዕዋው መንገድ አድርጎ የያዘ መጥፎ ሰው ነው።
3ኛ፦ ዓላማው ዲን ሳይሆን ቂም ማወራረድና ብሸሸቅ ነው።
ይሄ ነገር የሰውየውን መመለስ #ሳናውቅ ሊገጥመን ይችላል። መመለሱን ካወቅን በኋላ በተመለሰበት ጉዳይ መወንጀል ግን ያለ ወንጀሉ ሰውን መክሰስ ነው። ቡድናዊ ሽኩቻ ላይ ያነጣጠሩ "ረዶች" በብዛት ይሄ ችግር ጎልቶ ይታይባቸዋል።
ሰውን በተመለሰበት ጥፋት መክሰስ ባልፈፀመው ጥፋት እንደ መክሰስ ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَٱلَّذِینَ یُؤۡذُونَ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ وَٱلۡمُؤۡمِنَـٰتِ بِغَیۡرِ مَا ٱكۡتَسَبُوا۟ فَقَدِ ٱحۡتَمَلُوا۟ بُهۡتَـٰنࣰا وَإِثۡمࣰا مُّبِینࣰا }
"እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡" [አልአሕዛብ: 58]
ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
من قال في مؤمنٍ ما ليس فيه أسكنه اللهُ رَدْغَةَ الخَبالِ حتّى يخرُجَ ممّا قال
"በአማኝ ላይ የሌለበትን የተናገረ ሰው አላህ የጥፋት ማጥ ውስጥ ያኖረዋል፣ ከተናገረው ነገር እስከሚወጣ ድረስ።" [ሶሒሑ ተርጊብ: 2845]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!"
~
እንዲህ ዓይነቱ መጃጃል በዲን ስም መፈፀሙ ያሳዝናል። ተሶውፍ ሌላ ዓለም ነው። አሁን ይሄ ትልቅ ዒባዳ ነው በሱ ቤት። በሃገራችንም ያለው የመንዙማ ጭፈራ ከመጠነኛ ልዩነት ውጭ ይሄው ራሱ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን መጃጀል ነው እንግዲህ "ነባሩ እስልምና" የሚሉት። ይሄ ነባር ሳይሆን ነብራራ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
👉 በሟች ቤት ለመብላት፣ ለመጠጣት ፣ጫት መቃምና ካርታ መጫወት እና ቁርኣን ለማንበብ መሰብሰብ ቢድዐ (አዲስ ፈጠራ) ነው።
በሟች ቤት ለመብላት፣ ለመጠጣት እና ቁርኣን ለማንበብ መሰብሰብ ቢድዐ ነው። እንዲሁም በቤት ውስጥ ሶላት መስገድ አይፈቀድም። ይልቁንም በወንዶች ላይ የተጣለው ግዴታ በ መስጂድ ከጀማዐ (ከህብረት) ጋር መስገድ ነው። ወደ ሟች ቤተሰቦች የሚኬደው ለማጽናናት ፣ መልካም ለመመኘት እና ለሟቹ እዝነትን (ተረሁም) ለመጠየቅ ብቻ ነው።
ነገር ግን በልዩ ንባብ ወይም በልዩ ዱዓዎች ወይም በሌሎች መሰል ነገሮች የሐዘን ስብሰባ ለማቋቋም መሰብሰብ ቢድዐ ነው። ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ ደጋግ አባቶቻችን (ሰለፎች) ይቀድሙን ነበር። መልእክተኛው (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ይህንን አላደረጉትም። ጃዕፈር ቢን አቢ ጣሊብ፣ ዐብዱላህ ቢን ረዋሐ እና ዘይድ ቢን ሓሪሣ (ረዲየላሁ ዐንሁም) በሙእታ ዘመቻ በተደደሉ ጊዜ ወሕይ (ራእይ) መጥቶላቸው የሞታቸውን ዜና ለሶሓቦች አበሰሩ፤ እርቅንም ወረደላቸው፣ ዱዓ አደረጉላቸው፤ ነገር ግን የሐዘን ስብሰባ አላዘጋጁላቸውም።
ከእርሳቸው በኋላ የነበሩት ሶሓቦችም ቢሆኑ ከዚህ ውስጥ ምንም አላደረጉም። አቡ በክር አሥ-ሥዲቅ (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ሲሞቱ የሐዘን ስብሰባ አላዘጋጁላቸውም። ኡመር (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ሲገደሉ አላደረጉላቸውም፣ ቁርኣን እንዲያነቡም ሰዎችን አላሰበሰቡም።
ከእርሳቸው በኋላ ኡሥማን እና ዐሊይ (ረዲየልላሁ ዐንሁማ) ሲገደሉም ሶሓቦች ከነዚህ ነገሮች ምንም አላደረጉም።
ትክክለኛው ሱና ግን ለሟች ቤተሰቦች ዘመዶቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ምግብ አዘጋጅተው መላክ ነው። ነቢዩ (ሶለልላሁ አለይሂ ወሰለም) የጃዕፈር የሞት ዜና በመጣ ጊዜ ለቤተሰቦቻቸው፡ «ለጃዕፈር ቤተሰቦች ምግብ አዘጋጁላቸው፤ የሚያስጨንቃቸው ነገር መጥቶባቸዋልና» እንዳሉት ማለት ነው (ከነሳኢ በስተቀር አምስቱ የሐዲስ ዘጋቢዎች ዘግበውታል)። ሕጋዊና የተወደደው አሠራር ይህ ነው።
ነገር ግን ከደረሰባቸው መከራ በላይ ሌላ መከራ እንዲሸከሙ ማድረግ እና ለሰዎች ምግብ እንዲያዘጋጁ ማስገደድ ከሱና ያወጣና ቢድዐ ነው።
ቀደም ሲል እንደጠቀስነው እና ጀሪር ቢን ዐብዲላህ አል-በጀሊይ (ረዲየልላሁ ዐንሁ) ባሉት መሠረት፡ «ከቀብር በኋላ በሟች ቤተሰብ ዘንድ መሰብሰብን እና ምግብ ማዘጋጀትን ከኒያሓ (ዋይታ/ሙሾ) እንቆጥረው ነበር» ብለዋል (ኢማም አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ በትክክለኛ የሐዲስ ሰንሰለት ዘግበውታል)።
ኒያሓ ማለት፡ ድምፅን ከፍ አድርጎ በለቅሶ መጮህ (ሙሾ ማውጣት) ሲሆን እርሱም የተከለከለ (ሐራም) ነው። ሟችም በገደለው/በተላቀሰበት ሙሾ ምክንያት በቀብሩ ውስጥ ይቀጣል፤ ከነቢዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሶሒሕ ሐዲስ እንደተረጋገጠው። ስለዚህ ከዚህ ነገር ጥንቃቄ ማድረግ واجب (ግዴታ) ነው።
ለቅሶን በተመለከተ ግን ያለ ኒያሓ (ያለ ሙሾና ጩኸት) በአይን እንባ ብቻ ከሆነ ምንም ችግር የለውም፤ ነቢዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልጃቸው ኢብራሂም ሲሞት፡ «አይን ታነባለች፣ ልብም ያዝናል፤ ጌታችንን የሚወደውን እንጂ አንናገርም። እኛ በአንተ መለየት ኢብራሂም ሆይ! እጅግ አዝናናል» ብለዋልና።
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me/Deewaselefyya1448
http://t.me/Deewaselefyya1448
Repost from ተውሂድ ሱና በገኜ(አብዱልናስር)
አዲስ የተለቀቀ — እጅግ ወሳኝ ፒዲኤፍ (PDF)
📖 ርዕስ፦ «ላ ኢላሀ ኢልለላህ» — ትርጓሜዋ፣ ታላቅነቷና በተግባር የሚኖራት መገለጫ
✍️ አዘጋጅ፦ አቡ ሙሐመድ አብዱልናስር ሙኑር አል-ጃቢሪይ
“ወደ መልካም ነገር ያመለከተ ሰው ልክ እንደሰራው ሰው አምሳያ አጅር አለው።” (ሐዲስ)
📲 ሼር በማድረግ የዳዕዋው ተካፋይ ይሁኑ!
https://t.me/twhidsunabegegnea
Repost from 🔹قَناةُ أبي جُلَيبيب الأثري
የሺርክና የቢድዐ ጉዳዮች በብዙ አስተማሪዎች የማይደፈሩ ርእሶች ናቸው። ከዚህም የባሰው ግን የዘረኝነት ርእስ ነው። እንደ ሃገር በአራቱም ማእዘናት በዘረኝነት ብንታመስም ስለ ጉዳዩ ደፍሮ የሚያስተምረው ግን ከጥቂትም ያነሰ ነው። ዘረኝነት የእልፎችን ህይወት ቀጥፏል። ሌሎች እልፎችን አፈናቅሏል። በውል የማይታወቁ ንብረቶችን አውድሟል። እምነታዊ ትስስራችንን በእጅጉ ሸርሽሯል።
በዘረኝነት በዚህ ልክ ብንግጎዳም ሸይኹም ምሁሩም ፀጥ ብሏል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሁለት ነው።
1ኛ፦ እነሱ ራሳቸው የችግሩ ሰለባዎች መሆናቸው ነው። እንኳን ስለ ጉዳዩ ሊያነሱ በሌሎች ጠንከር ያለ ትምህርት ቢስሰጥ የማይጥማቸው ናቸው። ይሄ በተግባር የታየ አሳፋሪም፣ አሳዛኝም ሐቅ ነው።
2ኛው ምክንያት ደግሞ መንጋውን መፍራት ነው። በዘረኝነት ልክፍት የተበከለው መንጋ ርህራሄ የለውም። ስም ከማጉደፍ፣ በስድብ ከማጥረግረግ በላይ ህይወት ሊነጥቅ ይችላል። መስማት የሚሻው የሚያስፈልገውን ሳይሆን የሚፈልገውን ነው። የፖለቲካውም ይሁን የእምነት ቅኝቱ ይሄው ነው። ከዚህ ለወጣበት ምላሱም እጁም ጨካኝ ነው። በዚህ ስጋት የተነሳ መሬት ላይ በሚያዩት መሪር እውነታ ልባቸው ቢደማም ለችግሩ የሚመጥን ጥንካሬ ያለው ትምህርት ለመስጠት የማይደፍሩት ብዙ ናቸው።
ግን እስከ መቼ በዚህ ሁኔታ መዝለቅ ይቻላል? ችግሩን ከመሰረቱ ካልተጋፈጥነው መጨረሻው ለሁሉም በጣም አስፈሪ ነው። አላህ ልብ ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቀብርን፣
ሲራጥን፣
ሒሳብን፣
ከአላህ ፊት መቆምን፣
እንዳጠቃላይ ኣኺራችንን ደጋግሞ ማስታወስ ያስፈልገናል። ከተቅዋ ለመራቃችን፣ ወንጀል ለመዳፈራችን፣ በደል ለማ ብዛታችን፣ ከአላህ ትእዛዝ ለመራቃችን ዋናው ሰበብ የየቂን ድክመት፣ በዱንያ ውጥንቅጥ ውስጥ መስመጣችን ነው።
ህይወት ማለት የኣኺራ ህይወት ነው።
{ وَمَا هَـٰذِهِ ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا لَهۡوࣱ وَلَعِبࣱۚ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلۡـَٔاخِرَةَ لَهِیَ ٱلۡحَیَوَانُۚ لَوۡ كَانُوا۟ یَعۡلَمُونَ }
"ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)።" [አልዐንከቡት: 64]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የተውሒድ ሀይልና ጥቅሞች ነብዩ ሰሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለአብደሏህ ኢብኑ አባስ የመከሩት ምክር...
በአቡ ሂበቲላህ ሑሰይን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy