ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

الذهاب إلى القناة على Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
195
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-730 أيام
أرشيف المشاركات
......ጀግና አባት..... የሐቁን ባንድራ ሱናን ተሸካሚ፡ ቢዲዓ ጥመትን ሽርክን ተቃዋሚ፡ ሐቅን የሚናገር በአደባባይ መድረክ፡ ማነው የሚተቸኝ ለዚህ ሰው ብማረክ፡ ✅የኔ አባት‼️ የአሏህን ቃል ኪዳን ቁርዓኑን ይዘው፡ ከሱፍያ ጥመት ሽርካቸውን መዘው፡ ሐቅን ተከተሉ ብለው ያለቅሳሉ፡ አወ ለህዝባቸው እጂጉን ያዝናሉ፡ እሳት እንዳይገቡ ያስጠነቀቅቃሉ፡ ሐቀኛው ጎዳና የቱ እንደሁ ያውቃሉ፡ ✅ኸረ አሏህ ይጠብቅሁ ሽርክን ሲቃወሙ እንባቸው ይመጣል፡ የሚሰጡት ምክር እጂግ ይጣፍጣል፡ ኸረ አሏህን ፍሩት ይላሉ ዘወትር፡ ሐራራ ሳይፈሩ በሞቃት በቀትር፡ ለሱና መታገል እንደዚህ ነውና፡ አባትህን አይተህ የኔ ወጣት ፅና፡ ተመልከት አባቴን እድሜው በጣም ሔዷል፡ በሚፈጠረው ሽርክ ግን በጣም ተናዷል፡ ለዛ ነው በለቅሶ እሚያስጠነቅቀው፡ የአህባሽን ኮተት ሁሉም ሰው እንዳውቀው፡ ...አቦ ጀግና ይኑር....!! ምን ይሰራል ህይወት ጥንቆላ እየሰሩ፡ ምን ይሰራል እድሜ በጫት ከሰከሩ፡ ልክ እንደዚህ ጀግና ለተውሒድ ካልኖሩ፡ .....ለካ..... ጀግና የትም አለ የትም ይፀነሳል፡ በየትም ነው ምድሩ በየትም ይነሳል፡ ተውሒድ አስተማሪ አዋቂና በሳል፡ ቃላት ተምታታብኝ በምኔ ልክተባት፡ አሏህ ይወፍቀን ያንቱ አይነት ጀግና አባት። ....እድሜዎ ይባረክ አሏህ ይጠብቆት አባቴ...!! .....ኑረዲን አል-አረብ...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

የረሳቹትን ለማስታወስ ያህል ‼ ==================== ፋኖ ማነው ? እንዴት ተደራጀ ? ጥንስሱስ ? አላማውስ ? ==============★★================ ከዚህ ቀደም ከአመት በፊት ታስታውሱ እንደሆን በየቦታው በሚከሰቱ ግጭቶች የተነሳ ግድያዎች የሚሞ ሰዎች ከሁሉም እምነትና ብሄር ሆኖ ሳለ" አማራ ብቻ ተገደለ" በሚል ይሉኝታ በሌለው የውሸት ጩኸት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሲያጦዙት በወቅቱ እየሞተ የነበረው ከሁሉም ብሄር መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥባቸው ለምሳሌ በጃዋር ተከበብኩኝ ጊዜ በደፈናው አማራ ብቻ ተመርጦ ተገደለ ብለው ሙሾውን ሲያወርዱ ከሞቱት 86 ሰዎች 51 ኦሮሞ 20 አማራ 15 ሌላ የሞተ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ በሚዲያ መጥተው በማብራራት ስውር እቅዳቸውን ቀዝቃዛ ውሃ ሲቸልሱበት ኩምሽሽ በማለታቸው በፍጥነት ጩኸታቸውን ቀይረውት " የኦርቶዶክስ ምእመኖቻችን በየቦታው እየታረደ ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ ምእመኖችሸን ጠብቂ " በማለት ቅዱስ ሲኖዶስን ከፊት አሰልፈው የተለመደውን ሙሾ ማውረድ ጀመሩ ። ሙሾውን አጧጡፈው በመጨረሻ "ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅ የራሷ ጦር ሰራዊት ያስፈልጋታል" የሚል ሀሳብና ቅዠታቸውን በፕሮፖዛል ሰንደው ያለ ምንን ሀፍረት ይዘው ለመንግስት ቀርበው እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ነገር ነው ። ፋኖ ማለት የዛ ጥንስስ ሴራና ድብቅ ሚሽን የኦርቶማራ እቅድ የመስቀል ጦርነትን ለማስነሳት ተፀንሶ የተወለደ ህገወጥ ሀይማኖታዊ ጦር ሀይል ነው ። ይህን ለማረጋገጥ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም ዋና ዋና መሪዎቻቸውን እና ዋና ዋና ዲያቆናት አደራጅና ገቢ አሰባሳበቢዎቻቸውን፣ ዲያቆናት አክቲቪስቶቻቸውን ብቻ ማየት በቂ ነው ። ሙስሊሞችም አሉ እነ ሸህ ሀሰን ከረሙ ምናምን ወዘተ የሚል ሞኝ ላይጠፋ ይችላል እነሱ የአደረጃጀት እቅድ ውስጥ ፈፅሞ የሉምበትም አጋጣሚ በወያኔ ወረራ በተደረገው ውጊያ የተቀላቀሉ ናቸው እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው በዛውም ለማሟያነትና ለፕሮፖጋንዳ ድጋፍ ለማሰባሰብ ይጠቀሙባቸዋውና ነገ ግን ዋና የመስቀል ጦርነትቱ የመጀመሪያው ሰለባ እነሱኑ እራሳቸውን እንደሚያረጓቸው ፈፅሞ አያጠራጥርም ። የጎንደሩ የመስቀል ጦርነት መነሻ ዘመቻ ክፍል አንዱ የሙከራ አካል ነው ። የነ ዳቆን ዘመነ ካሴና መሰል ጠቅላላ ቄሶችና ዳቆናት መምህራን በየ ሚዲያዎቻቸው በየቀኑ በግልፅ ሲያወሩ እንደምንሰማው ከሆነ "ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ የመጀመሪያ ጠላታችን እስልምና ነው ኦርቶዶክስን አጥፍተው ኢስላሚክ ስቴት ሊመሰርቱ ነው " በማለት አውጀው የተዘጋጁበት ዘመቻ እነ ሸህ ሀሰን ከረሙን በምን ሂሳብ ነው ሊምራቸውና አዝኖና ለይቶ ሊያተርፋቸው ሚችለው ። ??? ‼ አስታጥቁን የሚለውንስ ዘመቻ አስታወሳቹት ግን ???

📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ! ✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እ
📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ! ✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል። 📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦ ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ) ◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ። 🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን   ከደሴ ▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ         ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ    ከደሴ ▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ       ከደሴ ▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ           ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን     ከቢስቲማ ▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን       ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ          ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ ▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ  ከመረሳ ▪️ ሸይኽ አወል አህመድ          ከከሚሴ ▪️ሸይኽ ዒሳ አደም                 ከደሴ 🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ         ከከላላ 🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር       ከአ.አበባ 🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ         ከአ.አበባ 🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ     ከከሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም          ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ  ዐብደሽኩር          ከአሶሳ 🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን   ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን   ከሀርቡ 🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ      ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ ሙርሰል        ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር      ከኮንቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን        ከመርሳ 🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ 🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ    ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን        ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ         ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ       ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ     ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ         ከደሴ 🔸ኡስታዝ ጀውሀር  ክፍሌ    ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ      ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ            ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ            ከኮንቦልቻ 🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ       ከደሴ 👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ... 👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር  በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ! 📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦ የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። 🏘 ማሳሰቢያ፦ ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።— 🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦ 📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር @Abuhureirehonline    0923467646 📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ   092 588 7118 @Attewhid11 📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን @Abu_Hibetillah_Al_aseriy 0942819970 💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡ 📞 ወንድም አንዋር 0916582567 📞 ወንድም አቡ አማር 0913803997 📞 ወንድም ሰኢድ 0935568513

📌 ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን رحمه الله እንዲህ ብለዋል፦ "احرص على أَنْ تَصْحَبَ أناسًا أَهْلَ خَيْرٍ، يُرشِدُونَكَ إِذا غَوَيْتِ، يَهْدُونَكَ إِذا ضَلَلْت، يُذَكِّرُونَكَ إِذا نَسِيت، يُعَلِّمُونَكَ إِذا جهلت. "መልካም ሰዎችን ጓደኛ በማድረግ ላይ ጉጉትህን አሳድር ማለትም :- ስትሳሳት የሚመክሩህ፣ ስትጠፋ ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመሩህ፣ ስትረሳ የሚያስታውሱህ፣ ባታውቅ የሚያስተምሩህን ሰዎችን ተጠጋ።" 📚 ሸርሕ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ (1/62)።

አብሺር! ~ አንድ አዕራቢይ ነብዩ ﷺ ዘንድ መጣና أَلَا تُنْجِزُ لِي مَا وَعَدْتَنِي؟ "የገባህልኝ ቃል አትፈፅምልኝም?" አላቸው። " أَبْشِرْ" "አብሺር!" አሉት። [አልቡኻሪይ፡ 4328] [ሙስሊም፡ 2497] Ibnu Munewor

የነብዩ (ﷺ) ሲራ ክፍል 2.mp38.75 MB

◼️ፈተና ላይ መኮረጅና አደጋው ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✅ በፈተና ጊዜ፦ 🔹መኮረጅ 🔹ማስኮረጅ 🔹ተቆጣጣሪው መምህር 🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

ሞራል መስጠት የብርታት ስንቅ ሲሆን ~ ሞራል ለብዙ ሰዎች ትልቅ ስንቅ ነው። ቀላል በሚመስሉ ማበረታቻዎች ትልቅ ለውጥ ያመጡ ብዙ ሰዎች አሉ። አቅም ሳያንሳቸው በሞራል መቀዛቀዝ ተሰናክለው የቀሩ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ። እዚህ ላይ የራሴን አንዲት ሚጢጢ ገጠመኝ ላንሳ። ልጅ እያለሁ በትምህርት ስለሚገኝ ቁምነገር ይሄ ነው የሚባል ግንዛቤ ባይኖረኝም እንዲሁ ትምህርት በጣም እወድ ነበር። ክፍል በጨመርኩ ቁጥር ግን የመማር ተስፋ እንደሌለኝ እየተሰማኝ መጣ። ይሄ ስሜት ውስጤ ሲያድር ለትምህርቱ የነበረኝም ፍላጎት እየቀዘቀዘ ሄደ። 9ኛው ክፍል ስደርስ ውጤቴ የተወሰነ ቀንሶ ነበር። ይሄ ነገር ምንም የተለየ ስሜት አልፈጠረብኝም። ከውጤቴ መቀነስ ይልቅ በዚህ ደረጃ ስሜት አልባ መሆኔ ገረመኝ። ክረምቱ ይበልጥ ከባድ ነበር። ስሜቴን በሚጎዳ ሁኔታ ውስጥ አሳለፍኩ። 10ኛ ክፍል ረዘም ያለ ጊዜ አሳልፌ ለመመዝገብ ሄጄ ብዙ አንገራግረው ተቀበሉኝ። መፅሐፍ የለኝም። ሌሎችም ብዙ ነገሮቼ አልተሟሉም። አልከታተልም። አላጠናም። ሰው መቅረብ አልፈልግም። ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ አንድ ታች ክፍል እያለሁ የሚያውቀኝ ወንድም ያዘኝና * "ማትሪክ ተፈታኝ ነህ፤ ለምን አታጠናም? ለምንድነው በዚህ ደረጃ ቸልተኛ የሆንከው?" አለኝ። - "ለምን አጠናለሁ? ዩኒቨርሲቲ ቀርቶ 11ኛ እና 12ኛ እንኳ መማር እንደማልችል እያወቅኩት ምን አደክመኝ? ወይ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም /TTI/ ወይም ግብርና ኮሌጅ ነው የምገባው። ለዚህ ደግሞ ማጥናት አይጠበቅብኝም" አልኩት። * "እሺ ትምህርትህን መቀጠል አትችልም እንበል፤ ግን መስራት እየቻልክ ውጤትህን ስታበላሽ አይሰማህም?" አለኝ። ያ ወንድም ይቺን ምልልሳችንን ላያስታውስ ይችላል። እኔን ግን ሙሉ ትኩረቴን ነበር የቀየረችው። የተለየ ተስፋ ባልሰንቅም ያቅሜን መስራት እንዳለብኝ ቆርጬ በሁለት ወር አካባቢ ጊዜ ውስጥ የተለየ ዝግጅት አደረግኩኝ። የአላህ እገዛ ሆኖ ውጤቱም ጥሩ ነበር። ላወራችሁ የፈልግኩት የኔን እንቶ ፈንቶ መተረክ አይደለም። በዚያ ወንድም - ምናልባትም የጥቂት ደቂቃዎች ምልልስ - ሰበብ ያደረብኝን የውሳኔ ለውጥ መጠቆም ነው የፈልግኩት። እንዲያውም ከዚህ የኔ የማይረባ ኮተት ይልቅ አንድ አስተማሪ ታሪክ ልጠቁማችሁ። የታሪኩ ባለቤት በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ጫፍ የደረሱት አልኢማም ሙሐመድ ብኑ አሕመድ ብኒ ቃይማዝ አዘሀቢይ ናቸው፣ ረሒመሁላህ። ዘሀቢይ ስለ ሸይኻቸው ዒልሙዲን አልቢርዛሊይ ባወሱበት ላይ ነው ጉዳዩን ያነሱት። አልቢርዛሊይ በአንድ ወቅት ለዘሀቢይ "የእጅ ጽሑፍህ የሙሐዲሦችን የእጅ ጽሑፍ ይመስላል" ይሏቸዋል። አሁን ይቺ ቃል የህይወትን አቅጣጫ የሚቀይር ተፅእኖ ይኖራታል ብሎ ማን ይገምታል? ውጤቱ ግን ፍፁም የማይገመት ነበር። ይቺ ቀላል የምትመስል ንግግር ዘሀቢይ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አሳደረች። አልኢማሙ ዘሀቢይ እንዲህ ይላሉ፦ "ይሄ ንግግራቸው እኔ ላይ ተፅእኖ አሳደረ። ሐዲሥ መማርን እንድወድ አደረገኝ።" [አዱረሩል ካሚናህ፡ 4/ 278] በቃ! ይቺ ቀላል የምትመስል ንግግር አሻራዋ ዘመን ተሻጋሪ ነበር። የአላህ መሻት ሆኖ ዘሀቢይን ያክል እጅግ ትልቅና የበቃ የነቃ የሐዲሥ ሊቅ እንዲገኙ ሰበብ ሆናለች። እና ለኛ ቀላል የሚመስለን ነገር ትልቅ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላልና የሰዎችን ሞራል የሚያለመልሙ፣ የብርታትን ስንቅ የሚያስታጥቁ፣ ለዱንያም ለአኺራም፣ ለእውቀትም፣ ለስራም እገዛ ያላቸው ምክሮችን ለመለገስ ልንሰስት አይገባም። ምን ይታወቃል? የኋላ ኋላ ለትልቅ ኸይር ሰበብ ልንሆን እችላለንኮ። = Ibnu Munewor

የነብዩ (ﷺ) ሲራ ክፍል 1.mp313.07 MB

ቁርአን የልብ ብርሀን ! የዱኒያ የአሄራን ሂወት የሚያቀና ውብ የማይጠገብ የአላህ ቃል ነው። ||

የመጅሊስ ዝምታ እስከ መቼ?
የመጅሊስ ዝምታ እስከ መቼ?

ሰለፍይዋ ጅን እውነትን ተናገረች 📌🔺ከእለታት አንድ ቀን ኢምም አህመድ ቢን ነስር አልኹዛኢይ የተባለው አሊም ከሱቆች መሀከል በአንዱ ሱቅ ላይ ሆነው ሳለ አንድ የታመመ ሰው፣ ሸይጧን በመጥፎ የነካው አይነት ሰው አዩ። የዚህን ጊዜ ኢማሙ ኹዛኢም ይዘው ቁርአን መቅራት ጀመሩ። ሲቀሩበት በሰውየው ላይ ሴት ጅን እንዳለችበት ተረዱ። 🔺እሳቸውም ቁርአን መቅራታቸውን ቀጠሉ የዚህን ጊዜ ሴቷ ጅን እንዲህ ብላ ተናገረች 🔺ኢማም ሆይ አትቅራብኝ አልወጣም። ይህን ሰው አለቀውም አለች ምክንያቱም【ቁርአን መኽሉቅ ነው የአላህ ቃል አይደለም ይላል አለች】ከዚህ ንግግሩ እስካልቶበተና ቁርአን የአላህ ቃል ነው እስካላለ አልወጣም ብላ ተናገረች። ሱብሀን አሏህ ይህንን ታሪክ ሸህ ኢብኑ ባዝ በሰሙት ጊዜ የግርምት ሳቅ በመሳቅ በጣም በመደነቅ ፦ {جزاها الله خيرا}《አላህ መልካም ምንዳዋን ይክፈላት》አሉ። 📚منقولة من شريط " لقاء مع إخوة في الله " الشريط رقم 4 للعلامة الإمام عبدالعزيز بن باز رحمه ﷲ በአቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

ለእህቶች በተለይ በድግምት በቡዳ እና በዓይንናስ ህመም ለምትሰቃዩ፦ ~አላህ ግዴታ ያደረገባችሁን ሒጃባችሁን በአግባቡ ልበሱ ~ሶላታችሁን በአግባቡና በጊዜ ስገዱ ~ ከሶላት በኋላ የሚባሉ ዚክሮችን ማለትን አትርሱ ~ የጧትና የማታ እንዲሁም የመኝታ ዚክሮችን አዘውትሩ ~ተገቢ ያልሆነና ከመጠን በላይ የሆነ ሃሳብና ጭንቀትን አስወግዱ ~ ተውበት፣እስቲግፋርና ዱዓእ አብዙ ~ ራሳችሁን በሩቃ ህክምና አድርጉ፤ካልቻላችሁ ቤተሰብና ሙሕሪም የሆነ ሰው ያድርግላችሁ ~ ግርግር ጫጫታ፣ከወንድ ጋር መቀላቀልን፣ፊልምና ሙዚቃ ከሚገኝበት ራቁ ~ ሳቅ አታብዙ ~ፎቷችሁን በየሶሻል ሚዲያው አትልቀቁ ~ ምናልባት አላህ ወንጀላችሁን ሊምርላችሁና ይቅር ሊላችሁ ይሆናልና ትዕግስት አይለያችሁ ኢንሻ አላህ አንድ ቀን አላህ ፈውስ እንደሚያመጣላችሁም እርግጠኞች ሁኑ •አላህ ሙሉ ጤንነታችሁን ይመልስላችሁ፣ደረጃችሁን ከፍ ያድርገው !ለጤነኞቹም ከላይ የተጠቀሱት እናንተንም ይመለከታልና ቀድሞ በመጠንቀቅ ራሳችሁን ጠብቁ! አላህ ያግራላችሁ!

ሰኔና ሰኞ ... . ... ቢገጥሙም ባይገጥሙም ያው ነው። አንድም ነገር የተለየ አይፈጠርም አላህ ከቀደረው በስተቀር። ነገር ግን በጃሂሊያ ዘመን የነበሩ የቁረይሽ ዓረቦች ቀናትና ወራትን ተንተርሰው ሰዎችን በገድ እንደሚያስፈራሩት ዛሬም ካፊሮች ሰኔ ከሰኞ ከገጠመ አንዳች ነገር እንደሚፈጠር ያወራሉ። ይህ በገድ ማመን ውሸት ነው፣ ሽርክም ነው! ሁሉም ቀናት ሁሉም ወራት የአላህ ናቸው። በሁሉም ውስጥ የሚፈጠረውም አላህ የወሰነው ብቻ ነው። በእንዲህ ያሉ ተረቶች ተንተርሶ ፍርሀት ውስጥ መውደቅ ክልክል ነው። እንደውም ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዳስጠነቀቁት ሽርክ ነው። "ገድ ከጉዳዩ የመለሰው ሰው በርግጥ (በአላህ) አጋርቷል" ብለዋል ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ኢብኑ መስዑድ ባወሩት ሐዲስ "ገድ ሽርክ ነው፣ ገድ ሽርክ ነው" ብለዋል። እንጠንቀቅ በእንቶፈንቶ ወሬ እምነታችንን አናበላሽ! ሽርክ ስራን በሙሉ ያበላሻልና! ﴿...لَئِن أَشرَكتَ لَيَحبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكونَنَّ مِنَ الخاسِرينَ﴾ [Az-Zumar: 65] "(በአላህ) ብታጋራ ስራህ ይበላሻል፣ ከከሳሪዎችም ትሆናለህ" አዙመር 65 አላህ ይጠብቀን!

ወሎየው ወለጋ ላይ ሲገድደል በሙስሊምነቱ ሳይሆን "በአማራነቱ ነው" ብለህ ስትቀስቅስና ስታስለቀስ ነበርኮ። ለምን ታዲያ አማራው አርሲ ላይ ሲገድደል በዘሩ ሳይሆን በሃይማኖቱ ነው ትላለህ?!