✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
الذهاب إلى القناة على Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
195
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-730 أيام
أرشيف المشاركات
አርሲዎች ትክክለኛ መረጃ ስጡን
«አልቃሾቹን አናምናቸውም እነሱ ከተኩላው ጋር በልተው ከእረኛው ጋር ማልቀስ ይችሉበታል»።
" ብዕር ገደል ይግባ!!! "
አይ ተማርን የምንል ሰዎች!!!!!!
ከእውነት ጎን ቆሞ ግፍን ካልሞገተ፣
በተበዳይ ሚዛን ሰፍሮ ካልዘመተ፣
ጥበብ ገደል ይግባ ብዕር ይሰባበር፤
ከግፈኞች ጋራ በሀሰት ከሚያብር!!!
ከእናት ጎን ቆሞ ግፍን ካልረገጠ!
ለእህት ተከራክሮ ፍትሕ ካላሰጠ!
ለህት እንባ ስቃይ ቀድሞ ካልደረሰ!
የግፈኛን ድልድይ ከአላፈራረሰ!!!
ጥበብ ምን አባቱ ብዕር ገደል ይግባ!
መፍትሔን ካላመጣ ለምስኪኖች እንባ።
"" ጥሩ ጓደኛ ማለት ይህ ነው!!!!!
የኔ የምትለው ጓደኛ ይኑርህ
ሸኽ ሀሰን አልበስሪ እንዲህ በማለት ስለ ሷሊህ ጎደኞች አወሱ…..
ሷሊህ ጎደኞችን አብዙ ከእነሱ ጋርም ተዋዋሉ ለዛች ለጭንቅ ቀኗ ለቂያም ቀን አማላጅ ይሆንዋችኃል፡፡ በማለት ሲናገሩ… ከአድማጮቹ አንዱ እንዴት ያ ሸኽ በማለት ጥያቄ ያቀርባል …
ሸኹም እንዲህ በማለት በጣፈጠ አንደበታቸው አስረዱት :-
የጀነት ሰዎች ጀነት ፣ የጀሃነም ሰዎች ጀሃነም ከገቡ በኃላ የጀነት ሰዎች ስለሚያውቋቸው ሰዎች ይጠያየቃሉ፡፡ ይተዋወሳሉ፡፡ በዛ መካከል ከእነሱ ውስጥ አንዱ የዱንያ ጎደኛውን ካላገኘው ጀሃነም መግባቱን ካረጋገጠ የእሳት መሆኑን ከሰማ … ወደ ጌታው እጆቹን ዘርግቶ እንዲህ በማለት ዱአ ያደርጋል "" ያ ረብ የጀነት ደስታዬም ምቾቴም ከዚህ ጀሃነም ካለ ባርያህ ጎደኛዬ ውጭ ሙሉ አትሆንልኝም"" በማለት ጌታውን የጎደኛውን ወደ ጀነት መምጣት አጥብቆ ይማፀናል ይለምናል …
ምን እነደሚፈጠር ታውቃላችሁ????!!!!
አሏሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዱዓውን ይቀበለውና ያን የሚወደውን ጎደኛውን ከጀሃነም እሳት ቅጣት ወደ ጀነት ምቾት ድሎት እንዲዘዎወር ያደርግለታል…በሱ በአሏህ ማሃሪነት ለዛ ለሷሊህ ባርያው ክብር ጀሃነም እሳት ውስጥ የነበረውን ጎደኛውን ወደ ጀነት ድሎት ያመጣለታል…
ሱብሃነላህ! አይደንቅም የ አላህ ራህመት ስፋቱ??!!
ከዛም የጀሃነም ሰዎች ባልደረቦቹ የነበሩት በሁኔታው በመደነቅ በእድሉ በመጎጎት… ይህ ሰው አባቱ ወይም ወንድሙ ሸሂድ መሆን አለባቸው አልያም መላኢካ ሸፋአ ሆኖት ይሆናል፡፡ በማለት የጉጉት ጥያቂያቸውን ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን መልሱ ከጠበቁት እና ካሰቡት ውጭ ነበር…
ዱንያ ላይ የነበረው ሷሊህ ጎደኛው እንደሆነ ሸፈአ የሆነው ይነገራቸዋል፡፡ ያኔ እንዲህ በማለት የቁጭት ቃላቸውን ይሰጣሉ…
{مالنا من شافعين ولا صديق حميم}
سورة الشعراء
{አማላጂም ለእኛ የለንም አዛኝ ወዳጂም የለንም} (አሹወራ)
ምነው ወደ ዱንያ ተመልሰን ሷሊህ ጎደኞችን ባበዛንም በማለት የቁጭት ምኞታቸውን ያቀርባሉ…
አማላጅነት በአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ፍቃድ ብቻ የምትፈፀም ከእዝነት በሮቹ አንዷ ናት… ለጠየቀው የሚሰጠውም ሆነ የሚነፍገው እሱ ራህመተ ሰፊው አላህ ብቻ እና ብቻ ነው።
በተከበረው ቃሉም ስለ ሸፋዓ እንዲህ ይለናል:-
{من ذا الذي يشفع عنده الا بإذنه} سورة البقرة
{እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማነው} አልበቀራ
{ولا تنفع الشفاعة عنده الا لمن اذن له} سورة سبأ
{ምልጃም እሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም} ሲል ያረጋግጥልናል!።
ሰው በሰው ነውና ውበቱ አላህ ከሷሊህ ባርያዎቹ ይቀላቅለን፣ ሷሊህ የሆኑ ወዳጆችንም ያበርክትልን፣ እኛንም፣ ወዳጆቻችንንም ፣ ቤተሰባችንንም፣ ሙስሊሙን ኡማ በአጠቃላይ ከደጋጎች ያድርገን!! .... አሚን!!
ማስታዎሻ:–
ለደግ ወዳጆቼ ሁሌም ደግ በሆነው ዱአችሁ ውስጥ አስታውሱኝ!!
ጉርሻ
➊የአንተ መሥተካከያና መታነጫ ዛሬ እንጂ ነገማ የፍጻሜህ ዕለት ሊሆን ይችላል
➋ ራስህን ድል ሳታደርግ በሌላዉ ላይ አትዝመት
➌ መታገስ ለራስ ግዜ መስጠት ነዉ
➍ ንዴት ለችግሮች መፍትሄ ሳይሆን መንስኤ ነዉ,,
➎ ጠላቶችህን ባትወዳቸዉ እንኳን አድንቃቸዉ፡፡ ስተትህን
ለመመልከት የመጀመሪያዎቹ ናቸዉና።"
➏ ጠላቶችህ ወደአንተ ቢገሰግሱም ወደ ኀላ አታፈግፍግ
ወደነሱም አትንደርደር ባለህበት ሁንና ተዘጋጅተህ ጠብቃቸዉ።
ሐጅ ማድረግ ላልተሳካላቸው የሐጅና የዑምራ ምንዳ የሚያስገኙ ሥራዎች፦
አልባኒ ሐሰን ባሉት እና አት-ቲርሚዚ አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ ጠቅሰው በዘገቡት የሐዲስ ሰንሰለት፣
የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«ሱቢሕን በጀመዓ ሰግዶ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ አላህን ያወሳ፣ ከዚያም ሁለት ረከዓ የሰገደ፣ ለእርሱ የተሟላ እና ፍፁም የሆነ፣ የሀጅና የዑምራ ምንዳ አለው።»
ኢማሙል አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:-
"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሁሉ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በስተቀር በእውነት የሚከተሉት የለም።"
(ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር 175)
አንድ ሰው ለኳስ ያለው ፍቅር
* ሶላት እስከሚያሳልፍ፣
* በቡድን እስከሚጣላ፣
* ሰዓት እላፊ እየጮኸ ጎረቤት እስከሚበጠብጥ፣
* የወላጆቹን ሐቅ እስከሚጥስ፣
* ሌሎችም ሐራም ነገሮች ላይ እስከሚወድቅ ያደረሰው ከሆነ
በሱ ላይ ኳስ ሐራም ነው። ወደ ሐራም የሚወስድ ነገር ሁሉ ሐራም ነውና።
=
IbnuMunewor
◼️ከጅሙአ ሶላት መዘናጋት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔹ከጅሙአ ሶላት ለሚዘናጉ ቅጣት
🔹ከጅሙአ አዛን በኋላ መሻሻጥ
🔹ለጅሙአ ኡዝር ያላቸው ሰዎች
🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
Repost from ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል
• የአያሙ ተሽሪቅ ትሩፋቶች!
• አያሙ ተሽሪቅ የተባሉበት ሰበብ!
• በነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች!
• የዚክር ትሩፋና ጥቅሞች !
🎙 አቡ አብደላህ ኢብኑ ኸይሩ
|•| t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ወረፋን አለመጠበቅ
~
ወረፋ በሚጠበቅበት የትኛውም ቦታ ላይ የቀደሙ ሰዎች እያሉ በጉልበትም ይሁን በመሸወድ ቀድሞ መግባት ነውረኛ ተግባር ነው። የታክሲ፣ የውሃ፣ የክፍያ ቦታዎች፣ ሃኪም ቤቶች፣ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች፣ ... ከኛ የቀደሙ ተገልጋዮች እያሉ በየትኛውም ጤነኛ ባልሆነ መንገድ ቀድሞ ተጠቃሚ መሆን አላህን ለሚፈራ ሰው ሞኝነት እንጂ ብልጠት አይደለም።
=
IbnuMunewor
የአረፋ ቀን በላጩ የዱአ ወቅት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሸይኽ ሱለይማን አሩሀይልይ አላህ ይጠብቀውና እንዲህ ብለዋል፦
ከዱአዎቹ ሁሉ በላጩ የአረፋ ቀን ዱአ ነው። በዚህ ቀን ለዱአ በላጭና የተሻለ ወቅት የሚሆነው፦ ፀሀይ ከተዘነበለችበት ሰአት ጀምሮ ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ያለው ጊዜ ነው። ምክንያቱም ይህ ወቅት ነብዩ ዱአ ያደረጉበት ወቅት ነውና። በተለይ ግን ከአሱር ሶላት በኋላ ፀሀይ እስክትገባ ያለው ይበልጥ የሚከጀል ወቅት ነው። ምክንያቱም ይህ ወቅት አላህ ወደ ባሮቹ የሚቀርብበት፣ ለመላኢካዎች በምድር ባሮቹ የሚያወድስበት፣ ወንጀል የሚማርበት ሰአት ነውና። በዚህ ውድ በሆነ ወቅት ላይ ከዝንጉዎች እንዳትሆን ተጠንቀቅ።
📚من حسابه على تويتر
0ረፋን መፆም ለማይችሉ
~
ነገ ዐረፋ ነው፣ ዙልሒጃ ዘጠኝ። ይህንን ቀን መፆም ትልቅ ዋጋ እንዳለው የሚታወቅ ነው። በተቻለ መጠን ሊያልፈን አይገባም።
በወር አበባ፣ በወሊድ፣ በህመም ሰበብ መፆም የማትችሉ ደግሞ ለመፆም ቁርጠኛ ውሳኔ ከነበራችሁ አትቆጩ። የምታመልኩት የልባችሁን የሚያውቅ ጌታ ነው። በኒያችው የሚፈፅሙ ሰዎችን አምሳያ ይመነዳችኋል። ይህንን የሚጠቁሙ መረጃዎች ብዙ ናቸው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"وهذه قاعدة الشريعة: أن من كان عازماً على الفعل عزما جازما، وفعل ما يقدر عليه منه، كان بمنزلة الفاعل".
"ይሄ የሸሪዐ ህግ ነው። አንድን ተግባር ለመፈፀም ቁርጠኛ ውሳኔን የወሰነና የሚችለውን ያደረገ ሰው በፈፃሚ ደረጃ ነው የሚሆነው።" [አልፈታዋ፡ 23/236]
=
IbnuMunewor
