ተዝኪራህ | Tazkirah | تَذْكِرَة
الذهاب إلى القناة على Telegram
🎀ሴት ልጅ የዲን እውቀቶችን ሳታውቅ ስትቀር ◈1_ባሏን ታደክማለች ◈2_ልጆቿን ታበላሻለች ◈3_ኡማውን ታጠፋለች ►ኢብኑል-ቀዩም (رحمه الله تعالى) ለዛ እውቀት ተማሩ ባረከአሏሁ ፊኩም።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
5 541
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+587 أيام
+31630 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ (አቡ ዘከሪያ)
🎁 በማይመለከትህ አትጠመድ!
የልብ እረፍት እና ሰላምን ከምናገኝባቸው ትላልቅ በሮች መካከል በጉዳያችን ሆነን የማይመለከተን ነገር መተው ነው። ብዙ ጊዜ ሰዓታችን የሚባክነው በተራ ወሬዎች፣ በማያገቡን ጉዳዮች እና በማይጠቅመን ነገር ላይ በመጠመድ ነው።
قال النبي ﷺ: «من حسن إسلام المرء تركه ما لا يعنيه» رواه الترمذي وحسنه النووي.
ጊያችን ላይ የብዙሀን መገናኛዎች የተጠመደው በተራ ወሬ ነውና ከኛ የሚጠበቀው ግዜ እና ምላሳችንን መጠበቅ ነው።
- ያወከውን ሁሉ አትናገር።
- ያየሀውን ሁሉ አትከታተል።
- በሰማሀው ሁሉ ቢዚ አትሁን።
- የማይመለከትህን እለፈው።
- ግዜህ ሰፊ፣ ልብህ ንፁህ እና ሒሳብህ ቀላል ሆኖ ታገኘዋለህ። ተግባባን?!
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed
💫ዶክተሩ እንድትወስድ ያዘዘልህን መድሃኒት በወቅቱ ካልወሰድክ ጤናህ እንደሚጎዳ ሁሉ
✨አሏህም ያዘዘህን ሰላት በወቅቱ ካልሰገድክ አኼራህን ይጎዳል
ሰላትን በወቅቷ ስገዱ🙌
Repost from 🕌 አል-መድረሰቱል ወልቂጢያህ “ብሎክ አንድ ለጀማሪዎች”
🕌 الْمَدْرَسَةُ الْوَلْقِطِيَّةُ الْمُسْتَوَى الْأُولَى [لِلْمُبْتَدِئِينَ]
🎁 እዚህ ቻናል ውስጥ እስከ 50 የሚሆኑ የአጫጭር ኪታብ ደርሶችን ታገኛላችሁ። ጀማሪዎች ገብታችሁ ተጠቀሙባቸው። ለጓደኞቻችሁም ሼር አድርጉላቸው።
በአጫጭር ደቂቃዎች የተቀዱ በተመጣጣኝ ማብራሪያ በውስን ሪከርዶች ያለቁ ኪታቦች ናቸው። በርካታዎቹን በአፕልኬሽን ተዘጋጅተው ታገኟቸዋላቹ።
👆 ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዙር በድጋሚ የተቀሩ ኪታቦችንም ታገኛላችሁ።
🎁 Join & Share 🎁
https://t.me/muhamed_al_wolkitey
Repost from ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ (አቡ ዘከሪያ)
🎁 ታላቅ የምስራች ለሀዲይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች!
እጅግ ጠቃሚ የሆነ መሰረታዊ የእስልምና እምነት ነጥቦችን የሚያብራራው የ«ኹዝ ዐቂደተክ» ኪታብ የሀዲዪኛ ትርጉም እና የተርጓሚውን ተጨማሪ ማብራሪያ የያዘው መፅሀፍ ታትሞ ለአንባብያን ገበያ ላይ ቀርቧል።
✍ ዝግጅት፦ በሸይኽ ሙሀመድ ጀሚል ዘይኑ «ረሒመሁላህ»
✍ የሀዲይኛ ትርጉም፦ በኡስታዝ ሙህዪዲን በድሩ «ሀፊዘሁላህ»
📕 የመፅሀፉ ዋጋ 300 ብቻ
☎️ መፅሀፉን ለማግኘት 0926271919
👆 ሼር በማድረግ የዳዕዋው አጅር ተቋዳሽ ሁኑ!
|| የቴሌግራም ቻናል⤵️
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed
ውድ እህቴ ሆይ! ሰዎች ባንቺ ላይ የሚፈርዱት ውጫዊውን ገጽታሽን ብቻ አይተው ነው። ዋናው ግን የውስጥሽ ንፅህና እና አላህ ስላንቺ ያለው እውቀት ነው። ትላንትና አልፏል፤ ዛሬ ግን አዲስ እድል ነው።
ፈጣሪ ካንቺ የወሰደውን ነገር ሁሉ፣ ፈገግታሽን በሚመልስና ካልገመትሺው አቅጣጫ በሚመጣ ታላቅ በረከት እንደሚተካልሽ ሙሉ እምነት ይኑርሽ። አንቺ ውድ እና ጠንካራ ነሽ! አላህ ካንቺ ጋር ነውና ብቻሽን አይደለሽም።
Repost from የሙመይዓ መንጋ ጥመት በመረጃ ሲጋለጥ⓵
💬 ለዒምራን አባት የተሰጠ መልስ!
በመጀመሪያ ደረጃ አላህን መፍራት ያስፈልጋል። ለቡድንህ ድጋፍ እና ለጠላትህ ውድቀት ስትል እንዲህ ያለ ከተጨባጭ እና እውቀት የራቀ ፅሁፍ መፃፍህ በጣም የተሳሳተ ተግባር ነው። በውሸት ቡድንህን ዝቅ ብታደርግ እንጂ አትረዳም። በደንብ ቆም ብለህ አስብ።
«فكر قبل أن تكتب، فالكلمة لا تعود!
والرسالة أسيرة عندك فإذا نشرت صرت أسيرها»
መለኪያ የሌለው የትችት ፋብሪካ የሆነውን የህያ አል'ሀጁሪይ እና ሸይኽ ዑብዱልሀሚድን ማመሳሰል ፈፅሞ ተጨባጭን የማይገጥም ድፍረት ብቻ የወነጨፈው ሀሳብ ነው። ሸይኽ ዐ/ሀሚድ የተቿቸውን አካላት ከሱ ትችት ጋር ማስተያየትህም እጅጉን የሚገርም ነው። የሙነወር ልጅ በባዶ ሜዳ ያለምንም ማስረጃ ዘግይተው የመጡ ሀጁሪዮች ብሎ ሲያንቋሽሽ የቅርብ አመታት ትውስታችን ነው። ያንተውም ከዛ የሚለይ ነገር የለውም።
«لا تخلط الحابل بالنابل فليس كل ما يلمع ذهبا!»
እንዲህም አልክ፦ "...ሸይኽ ዓብዱ ልሐሚድም ሸይኽ ኢልያስንና መሰል ሰዎችን ተብዲዕ በማድረግ ኢልዛም ያደርጋል።"
የኢልያስ እና የመሰሎቹ ሙብተዲዕነት አደባባይ የወጣ እውነታ ነው። አሳማኝ መረጃዎቹም እጅግ በርካታ ናቸው። እንደውም የሱን ሙብተዲዕነት የሚያረጋግጡ መረጃዎች አንተ ሰለፍይ ነኝ ብለህ ከምታቀርባቸው ማሳያዎች ይበልጣሉ ብዬ አስባለው። ሲጀመር ከሳቸው ውጪ በርካታ መሻይኾች እና ሰለፍዮች ያመኑበት ጉዳይ ነው። ከፊል ሙመይዖች እና ኢኽዋኖች እንኳ የመሰከሩት እውነታ ነው። ኢልያስ የሚሰራውን አታይም?! አትሰማም?! አታስተውልም?!
فهذا يقال فيه يراه الأعمى ويسمعه الأصم ولكن حالك كما قال الشاعر:
قد ينكر العين ضوء الشمس من رمد
وينكر الفم طعم الماء من سقم
وقال آخر
الحق شمس والعيون نواظر
لكنها تخفى على العميان
የኢልያስ ሙብተዲዕነትን የሚስረግጡ መረጃዎች ደርሰውት ሲያበቃ አይ ሰለፊይ ነው እያለ የሚከላከልለት እና የሚያወድስ ሰው ያለምንም ጥርጥር ሙብተዲዕ ነው።
قال ابن تيمية «ومن كان محسنا للظن بهم وادعى أنه لم يعرف حالهم عرف حالهم، فإن لم يباينهم ويظهر لهم الإنكار، وإلا ألحق بهم وجعل منهم.» المجموع ٢/ ١٣٢.
فالحق أبلج والباطل لجلج.
እንዲህም አልክ፦ "እና የሰዎች መለያየት የነገሩን ቢድዓነት ያስወግዳልን?"
መቼም እና በማንም ቢሆን ኢልዛም ማድረግ አይቻልም እያልክ ነው¿¡ ይህማ የእውቀት ክፍተት ወይም ስሜትን መከተል ካልሆነ በስተቀር በርካታ መረጃዎችን የተቃረነ የወደቀ አስተሳሰብ ነው።
فمن مشاهير النقول التي دارت على ألسنة السلفيين سؤال أبي داود الإمام أحمد بقول "قلت لأبي عبد الله أحمد بن حنبل أرى رجلا من أهل السنة مع رجل من أهل البدع أترك كلامه؟ قال: لا، أو تعلمه أن الرجل الذي رأيته صاحب بدعة، فإن ترك كلامه فكلمه، وإلا فألحقه به." وهذا بلا تعليق.
👌 ጀርህ እና ታዕዲል ኢጅቲሀዲይ ሳይሆን ሚን ባቢል አኽባር ነው የሚለው አቋም የሸይኽ ዐ/ሀሚድ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዑለማኡ ሱና አቋም ነው። ከዑለማኦች ተቃራኒ አድርገህ የሳቸው አቋም ብቻ ማድረግህ እጅግ ገርሞኛል።
لا غرو فإن الهوى يعمي ويصم
የመርከዙ ሰዎች ኢኽዋኒይነትን የሚያስረግጡ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ማሳያዎችን በዚህ ቻናል ተለቋል ብዬ አስባለው። የዚህ አይነት ፍንትው ያለ ጉዳይ ሲደርሳቹህ ቆም ብላቹህ ከማሰብና ማስረጃን ከመመልከት ይልቅ "በምን መልኩ መልስ ልከላልላቸው?" ብላቹህ መጨነቅና መጠበብ ቢቀርባቹህ አይሻል ወይ? በርግጥ ከናንተ ውስጥ የነበሮ ብዙዎች ተመልሰዋል። ብዙዎች ደግሞ ሙብተዲዕ እንደሆኑ ያምናሉ። ትተዋችሁ ወደ ሀቁ ይመጣሉ ብለን በአላህ ላይ ትልቅ ተስፋ አለን።
የመርከዙ ሰዎች ጉዳይ በጣም ግልፅ ነው። ከሀገር ውጪም ውስጥም የሆኑ መሻይኾች ሙንሐሪፎች መሆናቸውን እንደተናገሩ ኡስታዝ ባህሩ ተካ በርካታ መሻይኾችን በማውሳት አስነብቧል።https://t.me/aredualelmumeyia/987 ለመሆኑ እስከመቸ ነው የሙነወር ልጅ እና የከሚሴው አክሮባተር በጎተቷቹህ እየተጎተታቹህ ከማስረጃ ተጣልታቹህ ከሱና ዑለማእ ተቃርናቹህ የምትቀጥሉት? ብሽሽቅና ነቆራውን ትታቹህ ሳይመሽባቹህ ወደ ሩሽዳቹህ ብትመለሱ፣ ከእንቅልፋቹህ ብትነቁ አይሻልም? ብዥታስ ካለ በውይይት መፍታትና ሐቅ ወዳለበት ሁኖ በእውነት ላይ መሰባሰብ አይሻልም? ተው ልብ ግዙ ወንድሞቸ! አላህ ልቦና ይስጣቹህ ይስጠን።
|| የቴሌግራም ቻናል⤵️
https://t.me/aredualelmumeyia
Repost from 📡 ኢብኑ ተይሚያህ - Ibn Taymiyyah (የእውቀት ማእከል)
👉 ስድስቱን የኢማን ማዕዘናት በአጭሩ መገንዘብ!
🎁 ክፍል ስድስት
6ኛ, በቀደር ማመን እና ተያያዥ ነገሮች!
* በማወቁ ማመን።
- ለአላህ ጥንታዊ ጅማሮ የሌለው ዘላለማዊ የማይጠፋ እውቀት በመኖሩ ማመን!
- ክስተቶች ከመከሰታቸው በፊት እንደሚያውቃቸው ማመን!
* በመፃፉ ማመን።
- ክስተቶችችን ከመከሰታቸው በፊት እንፃፋቸው ማመን!
- በለውሕ እና ቀለም ማመን!
- በለውሑ ላይ የተፃፈው እንደማይሻር ማመን!
- በተለያዩ ግዜያት ቅርንጫፋዊ የቀደር መፃፍ እንዳለ ማመን!
- ክፉም ደጉም፤ አላህ የሚወደውም የሚጠላውም እንደተፃፈ ማመን!
- የተፃፈው እስከ ቂያማህ የሚከሰተው ብቻ መሆኑን ማመን!
* በመሻቱ ማመን።
- ክስተቶች በአላህ ፍላጎት እንደሚከሰቱ ማመን!
- የአላህን ፍላጎት የሚከተል ፍላጎት እንዳለን ማመን!
* በመፍጠሩ ማመን።
- ፍጥረቱን ከመፍጠሩ በፊት የመፍጠር ባህሪ እንዳለው ማመን!
- ተፅፎ ባለፈው መሰረት ክስተቶችን እንደሚፈጥር ማመን!
* ተጨማሪ ነጥቦች።
- ወንጀለኛ በቀደር ማሳበብ የለበትም!
- አደጋ የደረሰበት መታገስ እና አደጋውን ወደ ቀደር ማስጠጋት አለበት! «ቀደረ'ላሁ ወማ ሻአ ፈዐል»
- ሰበብ ማድረስ በቀደር ከማመን ጋር አይጋጭም!
- ቀደር እና የሸሪዓ አገዛዝ አይጋጭም!
- ቀደር እና የአላህ ምንዳ አይጋጭም!
- አላህ ማጥመሙ ለሚስጥር እና ፍትህ ነው መምራቱ በእዝነቱ እና ትሩፋቱ ነው!
- የባሮች ስራ የአላህ ፍጡር የነሱ ድርጊት ነው!
- ክፋት ወደ ፍጡሩ እንጂ ወደ አላህ አይጠጋም!
- በቀደር ድጋፍ ስራ አይተውም!
👆 የመጨረሻ ክፍል!
✍ በተማሪ ቢንት ያሲን
|| የቴሌግራም ቻናል⤵️
https://t.me/ibnuteimiyya
https://t.me/ibnuteimiyya
|| የኢሞ ቻናል⤵️
https://s.channelcom.tech/6FRsoK?from=other
📚 የዲን እውቀትዎን በቤቶ ይገንቡ!
ከቤታችሁ ሆናችሁ በቀላሉ ዲናዊ እውቀቶችን፣ ትምህርቶችንና ማብራሪያዎችን ማግኘት ከፈለጉ፡
🔹 ትምህርቶችን ለመከታተል
🔹 ጥያቄና መልሶችን ለማግኘት
🔹 ጣፋጭ ሙሀደራዎችን ለማግኘት
👇 ከታች ካሉት ዝርዝሮች/ሊንኮች አንዱን ይጫኑ!
We're talking about 📚ቁርአን እና ኪታብ መቅራት የምትፈልጉ ምዝገባ ጀምረናል ግቡ 📳. Click the link to join us! https://s.imoim.net/JJl9WQ?from=copy_link
ቁርአን እና ኪታብ በኢሞ መቅራት የሚትፈልጉ ግቡ
🚨ማሳሰቢያ⁉️
لا تبغض المنهج السلفي بسبب أخطاء بعض السلفيين
በከፊል ሰለፊዮች ስህተት ምክንያት የሰለፊያን ጎዳና አትጥላ!!
المنهج السلفي معصوم والسلفي ليس معصوما
የሰለፊያ ጎዳና ጥብቅ ሲሆን ሰለፊይ የሆነ ግለሰብ ግን ስህተተኛ ነው።
https://t.me/sead429
https://t.me/sead429
🎁 የስልክ አያያዛችን!
ስልክ እንደ ባለ ሁለት ስለት መሣሪያ ነው። በአንዱ ስለት ስትጠቀምበት ሌላኛው ስለት እንዳይጎዳህ መጠንቀቅ አለብህ። ስልክ ውስጥ ብዙ ጥቅም አለ። እውቀትን መማር፣ ማስተማር እና ብዙ ጥሩ ነገሮችን ማድረግ ይቻላል። ነገር ግን ጎዳትም አለው። ወንጀል፣ ጊዜን ማባከን፣ ልብን ማድከም እና ቁጭትን ማስከተል...
ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች የስልክ ሱሰኞች ሆነዋል። ልክ እንደ ሌሎች ሱሶች የኢንተርኔት ሱስ ውስጥ ወድቀዋል። አንዳንዶች አንድ ሰዓት ያለ ስልክ መቆየት እንኳ ያስጨንቃቸዋል። ከእንቅልፉ ሲነሳ እጁን ወደ ስልኩ የሚዘረጋ ሰው አለ። ቀኑን በስልክ ጀምሮ በስልክም የሚያጠናቅቅ ሰው አለ። መንገድም እየኋደ ስልኩን የሚጎረጉር አለ። በዚህ ምክንያት አእምሮው የተበታተነ፣ ልቡ የደከመ፣ እድሜው የባከነ፣ ዓላማውን የረሳ፣ የወደፊት ጉዞው የተቋረጠ፣ ሕይወቱን በትንሹ የስልክ እስክሪን ውስጥ የዘጋ ሰው ብዙ ሆኗል። የተጠቀምበት እየመሰለው ራሱን እየጎዳ ያለ ሰው አለ።
- ራስህን ፈትሽ!
- ስልክህ ጠቅሞሃል ወይስ ጎድቶሃል?
- ጥቅሙ ከጉዳቱ ይበልጣል ወይስ ጉዳቱ?
- ስልክ አያያዝህን አስተካክል።
- ተገልገለው እንጂ አገልጋዩ አትሁን።
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed
ወላሂ በጣም ያሳፍራል
ከ1400 ዓመታት በፊት ላለቀሱልሽ ነብይ
ዉለታቸዉ ሱሪ በሻርፕ መልበስ ከሆነ !
🫵ወላሂ በጣም ያሳፍራል©
➥https://t.me/nesiheti_linisa
