የሚካኤል መዝሙሮች
Kanalga Telegram’da o‘tish
2 231
Obunachilar
-124 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+6730 kunlar
Postlar arxiv
2 231
♡ ኦ ቅዱስ ሚካኤል ♡
ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)እረቂቁ መላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2) አዝ= = = = = እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2) አዝ= = = = = እርህሩ ነው እና የነፍሳችን ወዳጅ ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2) አዝ= = = = = የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2) ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
