ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 057
Obunachilar
+6824 soatlar
+3957 kun
+1 39230 kun
Postlar arxiv
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ነበልባል ክፍለ ጦር ከጦርነት ይልቅ ስቦ በማሥከዳት ከፍተኛ የብልፅግናን ሰራዊት እያፈረሱት ይገኛሉ‼️
የነበልባል ክፍለ ጦር የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች አርበኛ በላይሁ አድማሱ የነበልባል ከ/ጦር ወታደራዊ ዋና አዛዥ እና አርበኛ ሞገሥ የነበልባል ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ የመጡትን የመከላከያ ሰራዊት አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የተቀላቀሉትም ሰራዊት የአማራን ፋኖ አንድነት በሰማን ጊዜ ከፍተኛ ደሥታ የተሰማን ሲሆን እኛም የአማራን የኅልውና ትግል የበኩላችንን ለማገዝ መጥተናል በማለት በነበርንበት የመንግሥት ሥርዓት ደሥተኛ እንዳልነበርንና አሁን በተመቻቼልን ምቹ ሁኔታ ወደ እናንተ መጥተናል ብለዋል።
አርበኛ በላይሁን አድማሱ እና አርበኛ ሞገሥ ወደ ነበልባል ክ/ጦር የመጡትን የመከላከያ ሰራዊት እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በዚህ የአማራነት ትንቅንቅ የኅልውና ትግል እኛን መርጣችሁ በመምጣታችሁ ደሥተኛ ነን በማለት በጋራም እንታገላለን አማራን ወደ ከፍታው ማማ እንመልሳለን ብለዋል።
➔ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን💪💪💪
➔ክብርና ሞገሥ ለትግሉ ሰማዕታት🙏🙏🙏
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተር
19/ዐ5/2018 ዓ.ም
"በግራው መክቶ በቀኙ ካልመታ፡
በምን ያስታውቃል ቦረናና ሜታ"
ተብሎ ስንኝ የተቋጠረላቸው እነዛ ፀያይም አናብስቱ፡ የጠላት ኃይል አይደፈሬ በሚል ሲተማመንበት የነበረውን ምሽግ ድርምስምሱን በማውጣት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችን መግደላቸው ተሰምቷል።
የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋና የአርበኛ አደም አሊ እንድሁም የይታገሱ አራጋውና የሌሎች ሰማዕታት አደራ ተሸካሚዎቹ እነዛ የአባይ ዘብ ፀያይም አናብስቱ ድንግዝግዝ ባለው በድቅድቁ ጨለማ የጠላት ምሽግን በመደረማመስ የጠላት ደረትን በሳንሻ ሲመሸልቁት አድረዋል።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ስር ከሚገኙት ከኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክ/ጦር እና ከመብረቅ ክ/ጦር የተውጣጡ አሀዶች ጥር 17 ለጥር 18/2018 ዓ/ም ለአጥቢያ ለሊት በመካነሰላም ከተማ ውስጥ የነበረ ጠንካራና አይደፈሬ የተባለውን ዙሪያውን በፈንጅ የታጠረ የጠላት የኮንክሪት ምሽግ ላይ ስኬታማ እርምጃ በመውሰድ አንፀባራቂ ድል እንደተቀዳጁበት መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሶዬ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ኔትዎርኩ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ ጠላት ዙሪያውን በፈንጅ አጥሮ ሰርቶት የነበረው አይደፈሬ የተባለው ምሽግ ነው አጥቢያ ለሊቱን ብርግድግዱ የወጣው።
የፀረ አማራው ብልፅግና ጦር መካነሰላም ከተማን ተቆጣጥሬ እቆያለሁ በሚል ከመከላከያ እግረኛ አባላት፣ ከአየር ወለድ ኮማንዶ እንዲሁም የአድማ ብተናና የሚኒሻ ጥምር የሆኑ በርካታ ወታደሮችን አከማችቶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ሁሉ ግትልትል ኃይል በፋኖ ፊት ኢምንት ሆኗል።
ከዚህ ቀደም በከተማዋ የነበረው የጠላት ኃይል የፋኖን ክንድ መመከት ባለመቻሉ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር በኮሎኔል ዮሀንስ የሚመራ የ43ተኛ ክ/ጦር በከተማዋ ሰፍሮ የነበረ ሲሆን፡ ነገር ግን ይህም የፋኖ አፈሙዝ ሲሳይ ከመሆን ያለፈ ስራ ሳይሰራ በለሊቱ
ኦፕሬሽን አከርካሪው ተሰብሮ ማደሩን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።
በ4 አቅጣጫ በተደረገው የሌሊቱ ኦፕሬሽን ጠላት ይዞታውን ላለመልቀቅ የመጨረሻ አቅሙን የተጠቀመ ቢሆንም ነገር ግን የፋኖን ክንድ መቋቋም ባለመቻሉ አብዛኻኛው የጠላት ኃይል ነፍሱን ለማትረፍ ወደ ደሴ መስመር ፈርጥጧል።
ውጊያው በድቅድቅ ጨለማ የተካሄደ በመሆኑ የተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች ቁጥር በውል ባይታወቅም ነገር ግን በርካቶች የአፈር ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።
ከተገደሉ ወታደሮች መካከል አብዛኻኛውን ቁጥር የሚይዙት በፋኖ ሳንጃ ደረታቸውን የተወጉ መሆናቸው ሲገለፅ፡ በርካቶችም ክፉኛ ቆስለው በመካነሰላም ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።
የፋኖ አባላቱ አይደፈርም የተባለውን ምሽግ ሰዓታትን ባልፈጀ ውጊያ ድርምስምሱን በማውጣት በርካታ ወታደሮችን ከደመሰሱ በኋላ በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችን ከነ ተተኳሾቻቸው እንዲሁም ሌሎች ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶችና ግብአቶችን ማርከው በድል ታጅበው ቀጠናውን ለቀው መውጣታቸውን ነው ጣቢያችን ፍኖተ አማራ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።
ሰበር የድል ዜና!!!
ሚኒሻው አከርካሪውን ተመታ!!!
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የአድዋ ክ/ጦ ተወርዋሪ በትናንትናው እለት ጥር 18/2018 የአገዛዙ አሸርጋጅ ሆድ አደር ሚኒሻ ከአፀደማርያም ተነስቶ ወደ ጋራስጌ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ደፈጣ በመያዝ ዘከር ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። ይሄን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የአማራ አስገዳይ ደላላ ሆድ አደር ሚኒሻ የድረሱልኝ ጩኸቱን እየቀባጠረ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል።
በዚህ የደፈጣ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት=4
ከባድና ቁስለኛ =6
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ጥር 19/2018 ዓ.ም
+1
##የአገዛዙ ሰራዊት በዚህ መልኩ እየፈረሰ ነዉ።
ስሙ ዳንኤል ምንችል ይባላል።ከድቶ የመጣዉ ከ35ኛ ክ/ጦር ዉጫሌ ከተማ ነዉ።
#እንደት እንደገባ ስጠይቀዉ በሳቅ ነዉ የገለፀልኝ ያች የተረገመች ቀን አለ ፤ባህር ዳር ከተማ ቅኔ ቤት 8 ጓደኛሞች በአንድ እየተማርን እያለ እጅግ ሲበዛ የፋኖ ደጋፊ ከመሆናችን የተነሳ ስለ ፋኖ ጀግንነት ቅኔ ስንቀኝ ሁላችንንም አፍሰዉ ጦላይ ማሰልጠኛ ወሰዱን።
#ከዚያም በኋላ ሁላችንም ተበትነን እኔ ዉጫሌ አካባቢ ደረሰኝ ፌክ ሰሮቶኝ ነበር ፌክ ሰራሁት ሲል በአንድ ወቅት አርበኛ ዘመነ ካሴ የተናገረዉ ትዝ አለኝ 33ኛ ዙር የአድማ ብተናን ተመራቂዎች "የዛሬ ተመራቂዎች የነገ ፋኖዎች"ያለዉን
#ያንን ህይወት እንደት ታስታዉሰዋለህ ብዬ ጠየኩት?
ብዙ ጓደኛቹን እያዘነ ያወራኛል እትና የሚባል አድስ አበባ ሊታከም ሄደ እትና የሚባለዉ ግን ከድቷል ይለኛል።በሁለት ሳምንት ብቻ 27መከላከያ ከድቷል ይላል።አጠቃላይ ቪድዮዉን እለቀዋለሁ።በጣም ደስ የሚለኝ አለ 8ቱም የቅኔ ተማሪዎች ወጣን በሰላም እያለ በደስታ ይደዉልላቸዋል።መከላከያ ይሄ ልጅ ካወራኝ በኋላ አሳዘነኝ ያላችሁበት ሰቀቀን!!
ቃለ አብ ወርቅዬ ደምሤ
የብሔርተኝነቱ መስመር ከገባህ በእለታዊ ግጭት ከገዛ ወድምህ ጋር የቱንም ያህል ብቴጋጭ ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ባሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረህ ከፈታህ ጠላቶችህን ድል የምታረግበትን የማሸነፊያ የአድነት ቁልፉን ያዝከው ማለት ነው!
እነኝህ ወድሞች ውድ የሰውልጅ ሂወት በሚያስከፍለው ለአድ አላማ የተሰለፉ ግን ሰይጣንም ይሁን ግላዊ ኢጎ ለግዜው አሸንፏቸው ተጋጭተው ነበር አሁላይ ችግሮቻቸውን በውይይት ፈተው በፍቅር በአድ ለመሰለፍ ስምምነት ፈጥረዋል ደስ የሚል ተግባር በሁሉም ቦታ ይህ ቢተገበር መልካም ነው።
አድነት ያሸናፊነት ቁልፍ መሳሪያ ነው!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል በድርጅታችን ምስረታ ሂደት እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከFree Press ሚዲያ ጋ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ ከቀኑ 8:30 ይለቀቃል።
አብይ አሕመድ በፎከረበት የአየር ኃይል ትርኢት ላይ የUAE የጦር ሔሊኮፍተሮችና ጀቶች በተውሶ መጥተው ትርኢት እንዳሳዩ ተሰምቷል።
በዚህም ባለቤትነታቸው የUAE የሆኑ ስድስት የጦር ሔሊኮፕተሮችና ስድስት የጦር ጀቶች በደብረዘይት (ሀረር ሜዳ) አየር ኃይል መታየታቸው ታውቋል።
በዋዜማው ምሽት ደግሞ ከቻይና ለ10 ደቂቃ 120,000 ዶላር ከፍሎ በተከራያቸው ድሮኖች ሰማዩ የኛ ነው ብሎ ማፃፉ አይዘነጋም።
ኦህዴድ መራሹ ነውረኛው የብልፅግና ቡድን "ሰማዩም የኛ ነው" በሚል ሀሰተኛ ድስኩር ባሰማበት ወቅት፡ በተመሣሣይ ሰዓት በጄነራል አብደል ፋታኅ አል ቡርኻን የሚመራው የሱዳን መንግስት ጦር የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ በመግባት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአየር ጥቃት መፈፀሙን በእለቱ ጣቢያችን መዘገቡ አይዘነጋም።
ዐብይ አህመድ ሀገሪቱን፡ የጎረቤት ሀገራት መንግስታት ተቀናቃኝ የሆኑ ኃይሎች ማሰልጠኛ ጣቢያ ካደረጋት ቆይቷል።
በአብደል ፋታኅ አል ቡርኻን የሚመራው የሱዳን መንግስት ጥቃቱን የፈፀመው ተቀናቃኙ የሆነው በሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሰፈረባቸው አከባቢዎች ላይ መሆኑንም ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ጥር 15/2018 ሲሆን፡ ከሣምንት በፊትም ተመሣሣይ የሆነ ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር ተገልጿል።
የሱዳን መንግስት ጦር የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ በመግባት ጥቃት በፈፀመበት ወቅት፡ ነውረኛው የብልፅግና አገዛዝ ደግሞ፡ ከአረብ ሀገራትና ከቻይና ከነ አብራሪዎቻቸው ባስመጣቸው የጦር ጄቶች እንዲሁም ድሮኖች "ሰማዩም የኛ ነው" በሚል ሀሰተኛ ድስኩር እያስተጋባ ውሏል።
የኢትዮጵያ ሰማይ በጎረቤት ሀገር ያሉ ታጣቂዎች ድሮኖቻቸው እንዲሁም የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የጦር ጄቶችና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ያለ ከልካይ በኢትዮጵያ ሰማይ እየተሽከረከሩ ሕዝቡን በቦምብ አረር የሚገድሉበት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና የአበው ብሂል፡ አብይ አህመድና ቡድኑ "ሰማዩ የኛነው" በሚል ድስኩር ባሰሙበት የአየር ኃይል ትርኢት ላይ ባለቤትነታቸው የዩናይትድ አረብ ኤምሬት የሆኑ ስድስት የጦር ሔሊኮፕተሮችና ስድስት የጦር ጀቶች በተውሶ መጥተው ትርኢት እንዳሳዩ ዘገባዎች መውጣት ጀምረዋል።
በዋዜማው ምሽት ደግሞ "ሰማዩ የኛ ነው" የሚል ፅሁፍና የዐብይ አህመድን ምስል ሲያሳዩ የነበሩት ድሮኖች የቻይና መንግስት እንደሆኑና ለ10 ደቂቃ በ120,000 ዶላር የኪራይ ክፍያ የተከፈለባቸው ናቸው ተብሏል።
+7
የ14ኛ ክፍለ ጦር በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጎፍጭማ ቀበሌ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ከጎፍጭማ ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች የመሩት ሲሆን በትግላችን መሠረታዊያን ጉዳዮች ዙሪያ፣ በመልካም አስተዳደርና በማሕበረሰብ ሰላም አጠባበቅ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም በአዲሱ የፋኖ መንግስት አደረጃጀት መሠረት የቀበሌ መዋቅሩን በመፈተሽ የቀበሌዎቹ አመራሮችን ሹመዋል።
ጥር 19/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ!
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራን የህልውና ትግል ለሚደግፉ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች የተላለፈ ጊዜያዊ የአሰራር ስነ ስርዓት አቅጣጫ
እንደሚታወቀዉ ላለፉት 3 አመታት መሬት ላይ ያለዉ ትግል በአንድ ወጥ ድርጅት ያልታቀፈ ሆኖ መቆዬቱ የትግሉ ደጋፊ ሚዲያወች በተለያዬ ፍረጃ እና መካሰስ ውስጥ እንዲቆዩ ምክንያት ሆኗል።
በተለይም ቡድናዊ አሰላለፍ፣ ልዩ ፍላጎት እና የጥቅም ትስስር እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ባለመሻገሩ ምክንያት ሚዲያወቻችን ባላቸው አቅም ልክ ገንቢ ሚና እንዳይጫወቱ አድርጓቸዋል፡፡
ስለሆነም ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም የተመሰረተው አታጋይ ድርጅታችን የትግሉ ደጋፊ ሚዲያ አካላትን በድርጅቱ የአሰራር መርህ መሠረት መደገፍ እና የመምራት ሀላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።
በመሆኑም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በሚመራው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል፣ በሚዲያ የትግል አግባብ ፣ በህዝብ ግንኙነት እና ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም ፖለቲካል አክቲቪዝም ዘርፍ የምትሳተፉ የሚዲያ ባለቤት እና ባለሞያዎች የሆናችሁ አካላት ከታች የተዘረዘሩትን የአሰራር አቅጣጫወች ተከትላችሁ እንድትሰሩ በጥብቅ እናሳስባለን።
1) ድርጅት አምኖባቸዉ ሀላፊነት በሰጣቸው በየደረጃው ባሉ አመራሮቻችን ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ባስቸኳይ እንዲቆም ማድረግ፤ እንዲሁም አንድን አመራር በተለዬ መንገድ ማወደስ እና ለትግሉ ከሌላው የተለዬ አስተዋፅኦ እንዳለው አድርጎ ፕሮፖጋንዳ አለመስራት፤
2) የአፋብን አመራሮች ያከናወኑትን የይቅርታ መድረክ በሚዲያውም ዘርፍ ያሉት የይቅርታ መድረክ እንዲፈጥሩ ማድረግ እና የውስጥ መጠላለፉን በማስወገድ “መሬት ላይ አንድ ወገን አንድ ጠላት” የሚለዉን በተግባር በማከናወን የአብይ አህመድ አገዛዝ ላይ ብቻ ማነጣጠር፤
3) በዚህ የህልዉና ትግል ዉስጥ የድርጅቱን መርህ የማያከብሩ የሚዲያ አካላት ካሉ በአግባቡ መታገል የሚገባ ሲሆን ከዲሞክራሲያዊ መተጋገል አግባብ ውጭ ሆነው ከድርጅት መስመር እና መርህ በመጻረር የሚቆሙትን ድርጅቱ በሚሰጠው አጣጫ መሠረት ጠላትነታቸው በህዝቡ ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ፤
4) ትግሉን መደገፍ በድርጅት የትግል መስመር ገብቶ መታገልን ግድ የሚል መሆኑን በመረዳት የሚዲያ ባለቤት እና ባለሞያዎች የድርጅት አሰራርን በማክበር፣ ከጣልቃ ገብነት በመራቅ፣ የራስን ሚና ለይቶ አውቆ በዚያ መስመር መሰለፍ፤
5) ለድርጅቱ ይጠቅማሉ የሚባሉ ገንቢ ሀሳቦችን ድርጅቱ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በሚገናኝባቸው መድረኮች ለውይይት ማቅረብ እና መሟገት፤
6) በድርጅቱ ውሳኔ እና ብያኔ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ወደ አደባባይ አለማውጣት እና በዘመቻ ተጽዕኖ አለማድረግ እንዲሁም ውሳኔ እና ብያኔ ባገኙ ጉዳዮች ላይ ያልተገባ ጩኸት በማሰማት በሰራዊት እና በህዝቡ ውስጥ ያጥርጣሬ አለመፍጠር፤
እና መሰል መርሆወችን የኢዲቶሪያል ፖሊሲያችሁ አካል በማድረግ ትግሉን እና ድርጅታችሁን በመርህ መደገፍ እና የድርጅቱን ውሳኔ አክብሮ መስራት ከእናንተ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው።
በመሆኑም ድርጅታችን በቀጣይ የሚዲያን የትግል አግባብ፣ አሰራር፣ ተግባር እና ሀላፊነትን በሚመለከት ግልፅ መመሪያ የሚያወጣ ሲሆን እስከዚያ ድረስ ይህ የአሰራር ስነ ስርአት ጊዜያዊ አቅጣጫ በሁሉም የድርጅት ደጋፊ ሚዲያ እና ባለሞያዎች እንዲተገበር ለማሳሰብ እንወዳለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አብይ አህመድ ከወያኔ ጋ የነበረው ጦርነት የትናንት ትዝታችን ነው።
አብይ ከፕሪቶሪያ በኋላ ከወያኔ ጋ ሲጨባበጥ አማራን ከሚስቱ ውጭ ለማየትም፣ለማናገርም የተጠየፈው ሰውዬ ከዚህ እኩይነቱ በላይ አማራን እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን አስልቀዋለሁ ብሎ ፎከረ። ወረራ ውስጥ ገባ። ይሄው አሁን ድረስ እየዳከረ ነው።
የአማራ ህዝብ እንደ አብይ አህመድና ደጋፊዎቹ የሰላም አስፋላጊነትና የጦርነት ጎጆነት እያሉ በየሚዲያው መዘባነንና ማቅራራት ሳይሆን በበደምና አጥንት በተከፈለ መስዋእትነት አማራ ብዙ ትምህርት ወስዷል። የክህደትን ጥግም አይቶበታል።
Now what?
አማራን ስሜታዊ እያደረጉ በስሜት መንዳት ዛሬም ያምራችኋል?
ቀሽም!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ !!
https://t.me/Afnmnewschannel
#ያኔ Faኖ ወያኔ ጋር ሲዋጋ፦👇
ብልፅግናዎች - ''የሀገር መከታ ፣ የኛ ቼኩቬራ ወዘተ'' ይሉት ነበር።
#ሻዕቢያንም - '' የቁርጥ ቀን ወዳጅ ፣ የነፍስ አባታችን ፣ የሀገራችን አለኝታ'' እያሉ ሲንቆለጳጵሱት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው!
ህወሓት ደግሞ - '' አብይ አህመድንና ብልፅግናን ለማዳን የተሰለፈ ኃይል'' ምናምን ይል ነበር።
#አሁን Faኖ '' ተቀዳሚ ጉዳዬ! ህልውናችንን አደጋ ላይ ከጣለው ሀይል ጋር ነው!''' ሲል፦👇
ብልፅግና - '' የህወሓት ተላላኪ ፣ መንገድ መሪ ፣ የሻዕቢያ ቅጥረኛ ፣ ..እኙኙ እኚኚ..''
ያኔም የተቃጣው ጥቃት በገዛ ህዝቡ ላይ ስለነበረ እንጂ አገዛዙ ህወሓት አላማጣ ሲደርስ ዞሮ እንደሚገጥመው ጠፍቶት አልነበረም። የሆነውም ያው ነው!
ብላዘር! አሁን ላይ ማንም እያገላበጠ ከጥቅሙና ከፍላጎቱ ጋር እየመዘነ የሚፈርጀውና የሚነዳው ትውልድ የለም! በፍረጃም ሆነ በኩረጃ የሚለወጥ ነገርም ፈፅሞ የለም!
''እኙኙ እኚኚ አትበልብኝ'' ነው ያለው ያ የነሱ አክቲቪስት !😂
ይህ ለእናንተ ለእኔ ትልቅ መልክት ነው።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ አንዱ ነገር የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል ነው።
የአማራ ፋኖዎችን ለብልፅግና ዕጅ ስጡ፣መሳሪያም አስረክቡ፣ሀገር ሰላም ነው,,,,,,ብልጽግና ያሻግረናል ይሉናል። በተዘዋዋሪ የፕሪቶሪያን ውል እናክብር እያሉን ነው። በቃ ተሰብስበው ለብልፅግና ዕጅ ሰጡልን እያለ የሚፎክር አካል ብልጽግናን መማጸን እንጂ አማራ የሚለውን ስም የመጥራት ሞራል የለውም። ለምሳሌ ተመስገን ጥሩነህ አማራ ነኝ ቢል አማራነቱን አምኖ የሚቀበል አማራ በጭራሽ የለም።
የሚፎክር ሰው፣ለዓላማዬ መስዋዕትነት እከፍላለሁ የሚል አካል ወደ በረሃ ወርዶ ለሚያምኑበት ጉዳይ ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል። ትግል ያለው ሶሻል ሚዲያ ላይ ሳይሆን መሬት ላይ ነው።
👉 ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ቶሎ ቀጥታውን ከግንባር መረጃዎችን እንዲደርሳችሁ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ይህ ለእናንተ ለእኔ ትልቅ መልክት ነው።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ አንዱ ነገር የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል ነው።
የአማራ ፋኖዎችን ለብልፅግና ዕጅ ስጡ፣መሳሪያም አስረክቡ፣ሀገር ሰላም ነው,,,,,,ብልጽግና ያሻግረናል ይሉናል። በተዘዋዋሪ የፕሪቶሪያን ውል እናክብር እያሉን ነው። በቃ ተሰብስበው ለብልፅግና ዕጅ ሰጡልን እያለ የሚፎክር አካል ብልጽግናን መማጸን እንጂ አማራ የሚለውን ስም የመጥራት ሞራል የለውም። ለምሳሌ ተመስገን ጥሩነህ አማራ ነኝ ቢል አማራነቱን አምኖ የሚቀበል አማራ በጭራሽ የለም።
የሚፎክር ሰው፣ለዓላማዬ መስዋዕትነት እከፍላለሁ የሚል አካል ወደ በረሃ ወርዶ ለሚያምኑበት ጉዳይ ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል። ትግል ያለው ሶሻል ሚዲያ ላይ ሳይሆን መሬት ላይ ነው።
በጠለምት???
የፌዴራል መንግሥቱ የዛሬ ዓመት የጠለምትን አስተዳደር ለሕወሓት በይፋ አስረከበ።
ዛሬ በዓመቱ ፦"ሕወሓት በጠለምት ወረራ ከፈተ፤ተደመሰሰ።" የሚል ፕሮፓጋንዳ በአክቲቪስቶቹ በኩል ለቀቀ። ወረራውም፣ድምሰሳውም በሰዓታት ውስጥ !
ሕወሓት ለምን ብሎ በራሱ አስተዳደር ላይ ወረራ ከፈተ?
ኧረ በፈጠራችሁ ፕሮፓጋንዳ ስትሠሩ ትንሽ እንዲመስል ቦታውን እንኳ ቀየር አድርጉት።
ያልተነገረለት የአማራይቱ ልጅ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ልበ ሙሉ የአሳምነው ልጅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር መሪ አርበኛ አረጋ ሙሉነህ የብሬኑ ተኳሽ ነበልባል ሞት አይፈሬው!!
በአማራ የትግል ታሪክ ውስጥ ስማቸው በደማቅ ቀለም ከሚጻፉ ጀግኖች መካከል አረጋ ሙሉነህ አንዱ ነው። የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባልና የአሁኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዋና መሪ የሆነው አረጋ ሙሉነህ በጦር ሜዳ ውሎው "ባለ ብሬኑ ጀግና በሚል መጠሪያው በወዳጅ ዘንድ አድናቆትን፣ በጠላት ዘንድ ደግሞ መርበትበትን የሚፈጠር ተዋጊ እና አዋጊ ነው። የልዩ ኃይል ወታደራዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አረጋ ሙሉነህ በመጀመሪያ በልዩ ኃይል ውስጥ በነበረው ቆይታ፣ ወታደራዊ ዲሲፕሊንና ብስለትን አትርፏል። ያካበተውን ወታደራዊ እውቀትና ልምድ ተጠቅሞ፣ ሕዝባዊ መሠረት ላለው የአማራ ፋኖ ትግል ትልቅ አቅም ሆኗል።
እሱ ጋሻ ሆኖ ሕዝቡን ከመከላከል በላይ፣ ለጓደኞቹ ትልቅ የሞራል ምንጭ ነው። ባለ ብሬኑ እና የሰባት ለሰባው አዋጊ ተዋጊ አረጋ ሙሉነህ በውጊያ መሃል ብሬን ሲታጠቅ ለየት ያለ ግርማ ሞገስ አለው። የብሬኑ ድምፅ በጠላት ምሽግ ላይ ሲያስተጋባ፣ በአውደ ውጊያ ማርሽ ቀያሪ ነው የተባለለት እና የሚመሰክሩለት ብዙዎች ናቸው። እጅግ አስቸጋሪ በሆኑና ፈታኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ ጦሩን እየመራ፣ ለጠላት የማያፈገፍግ የጀግንነት መገለጫዎቹ ጽናት በትግሉ ሂደት ውስጥ ለገጠሙ ፈተናዎች እጅ ሳይሰጥ፣ እስከ መጨረሻው ድረስ በአቋሙ የጸና ተዋጊ ነው።
ቆራጡ አርበኛ አረጋ ሙሉነህ ለሕዝቡ ነጻነትና ክብር ሲል ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደ ኋላ የማይል የቁርጥ ቀን ልጆች ተምሳሌት ነው። የውጊያ ጥበብ ከከባድ መሣሪያ ጋር ያለው ቁርኝትና በጦር ሜዳ ላይ ያለው የአመራር ብቃት፣ የጀግንነት ተምሳሌት እንዲሆን እያደረገ ይገኛል።
አረጋ ሙሉነህ ለሀገሩና ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር በተግባር ይሚታይ በታሪክ መዝገብ ላይ ስሙ ከፍ እንዲል እያደረገ ያለ ጀግና ብሬን ቀለበቱ አርጋ ሙሉነህ ጀግንነት ይቀጥላል.....................
