ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 393
Obunachilar
+2924 soatlar
+2547 kun
+1 45030 kun
Postlar arxiv
#ሰበር ሰከላ ግሽ አባይ‼️
105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር መብረቁና ናደው ሻለቃ በጥዋቱ የወረዳ አስተዳድሩን ጨምሮ የሚሊሻ አዛዡንና በቁጥር ብዛት ያለው ሚኒሻን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ፣ እንዲሁም በርከት ያለ አጥቦ አይለብሴ ተሸኝቷል።
ዝርዝር ይዘን የምንመለስ ይሆናል
25/ዐ3/2018 ዓ.ም
+1
#የመጨረሻ_ማስጠንቀቂያ_መልዕክት ‼️
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ፣መንደር 3፣መንደር 14 እና መንደር 22 አካባቢ ብልፅግና ያሰማራቸው የሌባ እና ዘራፊ ቡድን እንዳለ ከህዝብ በደረሰን ጥቆማ አረጋግጠናል ።
ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል እና የፋኖን ስም ለማጠልሸት በተለይም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ መሪዎችን ስም እየጠቀሱ የሱ ልጆች ነን እንዲሉ ከብልጽግና ተልዕኮ የተሰጣቸው እንዚህ እኩይ የጥፋት ሃይሎች።
የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እየመዘበሩ ይገኛሉ።
በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በአሙሩ ወረዳ እንዳደረግ ነዉ ሁሉ በዚህ የዉብድና ተግባር ላይ የተሳተፉ ላይ ፋኖ የማያዳግም ዕርምጃ የሚወስድ መሆኑን ለሰፊዉ ህዝባችን ለመግለጽ እንወዳለን።
ፋኖ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ
የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ
ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
ህዳር 25/2018 ዓ/ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና ከአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ ዐምደፂዮን ኮር የተውጣጣ የፋኖ ኃይል በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀመ::
በቅንጅት በተሰራው ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ጠላት የተማረከ ሲሆን ጠላት 3 መኪና የሚሆን ሙት እና ቁስለኛ ጭኖ ፈርጥጧል:: በትናንትናው እለት በደገር ግንባር የተጀመረው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ ፋኖ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏታል::
ከዚህ በተጨማሪ ከደገር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙት ቲርቲራ እና ቆርኬ ታዳጊ ከተሞችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል::
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ትንቅንቅ በቲርቲራ በኩል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሳ ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲያስፈረጥጠው ቆርኬ ላይ ደግሞ የዚሁ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ታሪክ ሰርታለች:: የፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከቲርቲራ ጎራ ወርዶ እየፈረጠጠ ተጉዞ ቀነሶ መንደር ሲደርስ አቶ ሁሴን ከማል የተባለ ገበሬን በአጨዳ ላይ ሳለ እረሽኖታል::
በቆርኬ ግንባር 17 የጠላት ኃይል የተመታ ሲሆን 5ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 12ቱ ቁስለኛ ሆነዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር በጃማ ግንባር በተለይም በአቦልድ፣ ዘርቃሚ እና ደጎሎ በኩል የጠላትን አከርካሪ መስበሩ ተረጋግጧል:: የወረዳው መቀመጫ የሆነችው ደጎሎ ከተማ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በተኩስ ስትናጥ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል:: ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የዋሲል ክፍለ ጦር 2ተኛ መብረቅ ሻለቃ አባላት ጠላትን እረፍት ነስተውት ሰንብተዋል:: በዚህ የተበሳጨው ጠላት ከአረብ ሀገር ከመጣች 1 ወር በትክክል ያልሞላትን እህታችንን መረሸኑም ታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም
ከ1ቲም በላይ 10 የጠላት ሀይል 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።‼️
#ያለምንም_ዉጊያ_ጦሩን_እያፈረስነው_ነው
በሸበል በረንታ መረገጭ ከተማ የአገዛዙ ስረዓት ከ6ኛ ዕዝ 601ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ እሪጅመንት ቀኝና መሀንዲስ የነበሩ አገዛዙን በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።
1ኛ.አማኑኤል የሽዋስ
2ኛ.ነፃነት አበበ
3ኛ.ማሩ ውለተው
በተጨማሪም በደራ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት 6ኛ ዕዝ 601 ኮር እና 605 ኮር 26 ክፍለ ጦር 1ኛ እና 5ኛ እሪጅመንት አባል የነበሩ ፦
1ኛ.ይሆንስ ምስጋነው
2ኛ.ግዛቸው ክንፉ
3ኛ.ደሳለኝ ደሞዝ
4ኛ.ብርሀኑ ጥላሁን
5ኛ.ሞሀበው እንዳልኬ
6ኛ.ሞገስ ዳዊት
7ኛ.ሞላልኝ ይበን የተባሉ ከሰሜን ሽዋ ደራ ወረዳ ሰለልኩላ ቀበሌ የአገዛዙን ስረዓት በመክዳት 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።
#ስቦ_የማስከዳት_ስራ_በሰፊው_እየሰራን_ነው‼️
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህዳር 24/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ የ24 ስዓት ውሎ
_፩
201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለጦር
5ኛ ዙር እግረኛ ፋኖ ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ በሸበል በረንታ አስመርቋል።
_፪
፲ አለቃ መሳፍንት ወረታው የ25ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አዛዥ አጃቢ የነበረውን ጨምሮ ከ7በላይ የአረመኔው ሰራዊት አባላት 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአረመኔው ሰራዊት በየ አቅጣጫው ፍርስርሱ መውጣቱ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር በመክዳት ትግሉን የሚቀላቀሉ የጠላት የሰራዊት አባላት ቁጥር ቀን በቀን እየጨመረ ሲሆን በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 7 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ስርዓቱን ከድተው በመውጣት የ206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
፲ አለቃ መሳፍንት ወረታው የ25ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አዛዥ አጃቢ የነበር ስናይፐር ይዞ የተቀላቀለ ሲሆን ገመቱ ባንቴ እና ስዩም ውቤ ጨምሮ ሌሎችም መሉ ትጥቃቸውን በመያዝ 206ኛ ኮርን መቀላቀላቸው ታውቋል።
_፫
ፋኖ የህዝብ ልጅ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ ቀጥሏል።
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በዛሬው እለት ህዳር 24/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ አብረቁይ ቀበሌ የአቅመ ደካማ እና ረዳት የሌላቸውን አርሶአደሮች የሰብል በማሰባሰብ ሕዝባዊነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 24/2018 ዓ.ም
+1
አረመኔው ስርዓት በዛልማ ሸምበቁማ ቀበሌ የሚገኘውን የጤና ኬላ ላይ ጥቃት ፈጸመ...
(አፋብኃ ምዕ/ አ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ዓባይ ሻለቃ)
በቁጭ ከተማ መሽጎ የተቀመጠው የአረመኔው ስርዓት ወምበር ጠባቂ ሰራዊት በዛልማ ሸምበቁማ ቀበሌ የሚገኘውን የጤና ኬላ ቁልፎችን ሰባብሮ ዶክመንቶችን በታትነው መድሃኒቱን ዘርፈው የተረፈውን ከአቧራ ደባልቀውታል ሲሉ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ተናገሩ።
የህጻናት መታከሚያ የሆነውን የጤና ኬላ በማውደማቸው ህፃናቶቻንች በሰፊው ለበሽታ ተጋለጭ ናቸው ሲሉም የቀበሌው ኑዋሪዎች ገለጹ።
ሕዳር 24/2018 ዓ.ም
© አይቸው ጌታሰው
በራያ ግምባር ተኩለሽ ላይ በተደረገ ተጋድሎ አንድ የጠላት ምሽግ ሙሉ በሙሉ ሲሰበር በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ!
በተኩለሽ ዙሪያ በተደረገው ትንቅንቅ የአገዛዙ ኃይል ለወራት ገንብቶት የነበረው ጠንካራ የተባለው ምሽግ በዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጆች ክንድ በሰዓታት ልዩነት መናዱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
የጠላት ኃይል የአርሶ አደሮችን የእርሻ በሬ አርዶ ምሽግ ውስጥ እየበላ ባለበት ነው፡ ደመላሾቹ ፋኖዎች ጠላት ያላመጠውን ሙዳ ስጋ ሳይውጥ ተወርውረው ማንቁርቱን ያነቁት።
+2
እየተቀላቀሉን ነው!!
የዓብይ 57 ክ/ጦር ዓባል ወታደር ነው።አገዛዙ አማራን ጨቋኝና አማራን ጨፍጫፊ ስለሆነ የአማራ ፋኖን ለመቀላቀል መወሰኑን እያስረዳ ነው።
ከ1:00 ሰዓት በፊት የብርሃኑ ጁላን ጦር እስከ ሙሉ ትጥቁ በመክዳት ሰራዊታችን የተቀላቀለው ወታደር በላይ
በላይ ይበልጤ መኮነን የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርን በመቀላቀል ለመታገል መወሰኑን አስረድቷል።
የአማራና የኢት/ያ ሀገራችን ቀንደኛ ጠላት ዓብይ አህመድና ቡድኑ አፓርታይዳዊ አደገኛ "ዘረኛ" አገዛዝ መሆኑን ከጦር ሰራዊቱ በተደጋጋሚ እየተመሰከረም ይገኛል።ወታደር በላይ ይበልጤም ይህንኑ በንግግሩ አስረድቷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
+2
#ፋኖነት_ህዝባዊነት_ነው፡
የአፋብኃ ምዕረብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206 ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የደብረ ማርቆሱ ንጉስ #ተክለሃይማኖት_ብርጌድ_አባላት_በየጋግና_ቀበሌ አርሶ አደሩን ሰብል በመሰብሰብ እያገዝ ይገኛል።
ስንቅህም ትጥቅህም ልብስህም ጉርስህም የሆነውን ማህበረሰብ በሁሉም ዘርፉ ማገልገል የትግልህ መርህ ሊሆን ይገባል።
Endaylalu Belachew Chemere Mekonenn Estibel A Zerihun
በመርሳ ከተማ አቧሬ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከ16 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች አስ*ከ*ሬ*ን ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፀመ!
ወታደሮቹ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከመርሣ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠዶት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተደረገ ውጊያ በባለሽርጡ ክፍለጦር ፋኖ እርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው።
በፋኖ የተገደሉ ከ16 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች አስ*ከ*ሬ*ናቸው በመርሳ አቧሬ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቀበሩ ተሰምቷል። የአገዛዙ ኃይል የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታይ ያልሆኑ ወታደሮቹን ጭምር ነው "ማንም አይከለክለኝም" በሚል በቤተክርስቲያኑ እንዲቀበሩ ያስደረገው ተብሏል።
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከመርሣ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጠዶት ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ከህዳር 19/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 21 ምሽት ድረስ በተደረገ ውጊያ የአገዛዙ ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መከናነቡን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በዚህ ቀጠና በጠላት ላይ ልዩ እርምጃ በመውሰድ ድል የተቀዳጀው በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ "ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶ" በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት የባለሽርጡ ክፍለጦር ፋኖዎች መሆናቸው ታውቋል።
በውጊያው በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከሟቾቹ መካከል ከ16 በላይ አስ*ከ*ሬ*ን በመርሳ አቧሬ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቀበሩ ተሰምቷል።
የአገዛዙ ኃይል የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታይ ያልሆኑ ወታደሮቹን ጭምር ነው "ማንም አይከለክለኝም" በሚል በቤተክርስቲያኑ እንዲቀበሩ ያስደረገው የተባለ ሲሆን፡ ይህም በአከባቢው ማሕበረሰብ ዘንድ ታላቅ ቅሬታን ፈጥሯል።
በውጊያው ከተገደሉት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ወታደሮች በመርሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።
በዚህ ውጊያ በደረሰባቸው መራር ሽንፈት የተበሳጩት የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች፡ "መከላከያ ሰራዊቱ ሲዋጋ እናንተ በቂ እገዛ አላደረጋችሁም" በሚል አራት የሚኒሻ አባላትን ሲረሽኑ በርካታ የሚኒሻ አባላት ደግሞ ለእስር እንደዳረጓቸው ነው ከሚኒሻ ቤተሰቦች የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው።
በተመሣሣይ ከቀናት በፊት በመርሣ ከተማ ዙሪያ ጠዶት ሚካኤል አከባቢ ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን፡ ከደፈጣ ጥቃቱ በኋላ "መከላከያ ሰራዊቱ ሲዋጋ እናንተ በቂ እገዛ አላደረጋችሁም" የተባሉ መንገድ መሪ የነበሩ የሚኒሻ አባላት መረሸናቸውን መረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ህዳር 19/2018 ዓ/ም በምሽት ዜና እወጃው መዘገቡ አይዘነጋም።
እየተናቁና ምራቅ እየተተፋባቸውም የሚላላኩት ሆድ አደሮቹ የሚኒሻ አባላት፡ ህሊናቸውን ሸጠው የሚያገለግሉት የብልፅግናው ስርዓት ልክ እንደ ሸንኮራ አገዳ አላምጦ እየተፋቸው ነው።
አገዛዙ "ግልገል ፋኖ" ብሎ በሚጠራቸው የሚኒሻ አባላት ላይ የሚወስደው ደረቅ እርምጃ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።
+3
፲ አለቃ መሳፍንት ወረታው የ25ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አዛዥ አጃቢ የነበረውን ጨምሮ ከ7በላይ የአረመኔው ሰራዊት አባላት 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
ህዳር 24/ 2018 ዓ.ም
የአረመኔው ሰራዊት በየ አቅጣጫው ፍርስርሱ መውጣቱ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር በመክዳት ትግሉን የሚቀላቀሉ የጠላት የሰራዊት አባላት ቁጥር ቀን በቀን እየጨመረ ሲሆን በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 7 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ስርዓቱን ከድተው በመውጣት የ206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
፲ አለቃ መሳፍንት ወረታው የ25ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አዛዥ አጃቢ የነበር ስናይፐር ይዞ የተቀላቀለ ሲሆን ገመቱ ባንቴ እና ስዩም ውቤ ጨምሮ ሌሎችም መሉ ትጥቃቸውን በመያዝ 206ኛ ኮርን መቀላቀላቸው ታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በገባሪዎች እና በክህደት አበጋዞች የሚደናቀፍ ትግል የለም!!
ትግላችን በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ አይደለም።
እኩይ ቡድኖች እና ምስለ አማራ ታጋዮች ከውስጥ እና ከውጭ በሚያደርጉት ያልተገባ ነውር የሚቆም ትግል አልጀመርንም።
የቁስ ስቀቀናሞች እና የስልጣን ጥመኞች የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ሲሰልሉ ቆይተው ወደ ጠላት ካምፕ መግባታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።
የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል የአማራ ህዝብ ከገጠመው ብሔራዊ የህልውና አደጋ ለመውጣት የተጀመረ አብዮት እንጅ ድንገት ግለሰቦች ወደ ጠላት ካምፕ ዘው ብለው ስለገቡ የሚቀለበስ የህዝብ ትግል አልጀመርንም!!
አማራነት/ሞት በማለት ሲልከሰከስ የነበረው ሁሉ ራሱን በቁስ እና በስልጣን ያረካበትን ነውረኛ ሁሉ በታሪክ የምንፋረደው ይሆናል።
ስለሆነም ከሃድዎች ዛሬም ነገም ይኖራሉ።
ራሱን የአፋህድ መሪ ነኝ ሲል የነበረው ማስረሻ ሰጤ ለብልፅግና ዕጅ መስጠቱን ተከትሎ እዚህም አዛም የሚወሩ አሉባልታዎች መሰረተ ቢስ ናቸው።
ማስረሻ ሰጤ ከጥር 2017 ዓም ጀምሮ ከመንግስት ሃይሎች ጋር እንደሚያወራ ይታወቃል።
በተለይም የአማራ ፋኖን ትግል ወደ አንድ ቋት እንዳይሰበሰብ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ የተወጣ ሲሆን ሰሞነኛው ግርግር እና እጅ መስጠትን በወገን በኩል የተደራጀ መረጃ በመኖሩ ምክንያት ተልዕኮውንም በአግባቡ የጨረሰ ሲምስለው ተሰወሮ ወደ ጠላት መግባቱ የሚጠበቅ ነው።
በአማራ ህዝብ ትግል በርካታ የትግል አረሞች ተሰግስገው መግባታቸው የሚታወቅ ነው።
ነገር ግን ሂደቱ ጥርት እና ኩልል እያለ መጥቷል።
ፅናት የሌላቸው አላማ ቢስ ግለሰቦች በሚፈፅሙት ክህደት የሚቆም ትግል አልጀመርንም።
በብዙ ተግዳሮት ውስጥ ሆነን ትግላችን እናስቀጥለዋለን።
ተስፋ ቆራጮች በአማራ ህዝብ ስም እየማሉ እየተገዙት የጠላት ተልዕኮ አስፈፃሚ የነበሩት ደግሞ ከትግላችን እየተነቀሉ መጥፋታቸው ይቀጥላል።
ደም የተገበረበትን ትግል አዳድስ ገባሪዎች እና የስልጣን ጥመኞችም በሚያደርጉት ሴራ አሳልፈን አንሰጥም!!
የብልፅግና አዳድስ ገባሪዎች በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ተላልፈው የተሰጡ ለመምሰል የሚያደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም።
በትግላችን ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ወዶ ገቦችንና ከሃድዎች የታሪክ ምርኮኞች ናቸው።
አሰባሳቢውንና ትልቁን የአማራ ህዝብ አብዮት አሳልፎ ለመስጠት በባንዳነት ስራ ስምሪት ወስዶ ዋጋውን ማሳነስ ጥቁር ክህደት ነው።
የአማራ ህዝብ ትግል ብዙ ሴራዎችን እያከሸፈ የድል ዋዜማው ላይ ይገኛል።
የትግል ሾተላዮች እና ቅጥረኛ ባንዳዎችን ከትግሉ ነጥሎ ለፍርድ እንዲቀርቡ የማድረግ እንቅስቃሴያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።
አሸናፊው ትውልድ ዋንጫውን ለመያዝ በመገስገስ ላይ ነው።
መደረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል።
አይበገሬው ትውልድ በፅናት ታግሎ ካሰብንበት ቦታ ይደርሳል🙏🙏
አርበኛ ማሬ ባዘዘዉ ከጠላት ጋር ተፋልሞ ተሰዋ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ፬ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ሻለቃ በሪሁን ገ/እየሱስ ብርጌድ አባል የሆነዉ አርበኛ ማሬ ባዘዘዉ ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ሞገሴ ቀበሌ ላይ በነበረዉ አውደ ዉጊያ ጥቅምት 22/2/2018 ዓ.ም
የፋሽስቱ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ጠላትን ከፍተኛ ሙትና ቁስል ካደረገ በኋላ ቦንብ በመወርወር ምሽጉን ከሰበረ በኋላ፤ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲል የማይተካ ህይወቱን ሰጥቶ በ60 ዓመቱ አርፏል።
ዘላለማዊ ክብር ለነፃነት ሲሉ ለተሰዉ ታጋዮች!!!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ በ4 ግንባሮች ከፋሽስቱ ሃይሎች ጋር እየተፋለመ ይገኛል።
ጀብደኛዉ ምኒሊክ ዕዝ በምዕራብ ቤተ ዐማራ ከለላ ወረዳ ደገር ከተማን ለመያዝ ትንቅንቅ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን በማዕከላዊ ወሎ ቤተ ዐማራ ደግሞ ዳዉንት እና ፀሃይ መዉጫ እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ፍልሚያ እንደቀጠለ ይገኛል።
ሌላዉ እና 4ኛዉ ግምባር በራያ ቆቦ ወረዳ ተኩለሺ የተደረገ ዉጊያ ነዉ ።
እንደሚታወቀው ከዘመቻ አባ ናደዉ ቀጥሎ አሁንም ያለ ዕረፍት እየተዋጋ ያለዉ ጀብደኛዉ ምኒሊከሰ ዕዝ ጠላትን እያፈራረሰዉ ይገኛል።
አይበገሬዉ ትዉልድ ያሸንፋል 🙏❤️
ሰበር ዜና!
ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ያለውን የፋሽስቱ ሰራዊት አንዱን ምሽግ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ላይ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ካሉት የፋሽስቱ ሰራዊት ምሽጎች አንዱ ላይ በሬ አርዶ ከሚበላበት ተስበው በመግባት ምሽጉን ሙሉ ለሙሉ በመስበርና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ብሎም በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
የጠላት ሃይል ምንም አይነት ዋርድያ ባላስቀመጠበትና በሌለበት ሁኔታ ምሽጉ ላይ በሬ አርዶ በሚበላበት ቀን 10:00 ላይ ተስበው በመግባት እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሲረመርሙት አምሽተው ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ከዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ማግስት ፋሽስቱ አገዛዝ ቤተ-አማራ ከነበሩት ዕዞች በተጨማሪ ሁለት ዕዝ በማስገባት ወረራ ቢያደርግም ምኒልክ ዕዝ ጠላትን ወደሚመታበት ወረዳ በማስገባት ወደ ደፈጣ ውጊያ በመግባት ሲያመች ደግሞ መደበኛ ውጊያ በማድረግ በርካታ ሃይሉን ሙት ቁስለኛ እና ምርኮኛ እያደረገ በተጨማሪም እያስኮበለለ እያፈረሰው ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
