ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish2 976
Obunachilar
+2324 soatlar
+367 kun
+41430 kun
Postlar arxiv
ከምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠ መግለጫ
ሚያዚያ 30/2018ዓ.ም
---------------------------------------------------------------------
"በምርጫ ሰበብ ያለአግባብ የታፈኑ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 የተቋማችን ተማሪዎች በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የደህንነት ሰዎች በትናትናው ዕለት ከኮሌጁ ቅጽር ግቢ ተወስደዋል።
የትምህርት ተቋማት ለማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማስፈፀሚያነት እንደማይውሉ እየታወቀ በአለፉት 30 ቀና ውስጥ በኮሌጁ ግቢ ተማሪዎችን ፣መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች በግዳጅ ከ5-7 የሚደርስ የምርጫ ካርድ በተለያዩ ስሞች እንዲያወጡ በመገደዳቸው ተቋማችን ይህ ተግባር እንዲቆምለት ለሚመለከተው አካል ማቅረባችን የሚታወስ ነው።
በተደጋጋሚ በተጻፈልን ደብዳቤ መሰረት በኮሌጁ ውስጥ የምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን ፣ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን ሪፖርት እንድናቀርብ በመጠየቃችን ሒደቱ የአልተገባ እና ህገ-ወጥ በመሆኑ ተቋሙ በምርጫ ሒደቱ በቀጥታ እንዲሳተፍ እየተገደደ መሆኑን ለሚመለከተው አካል ብናሳውቅም አጥጋቢ ምላሽ በማጣታችን ምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን በስም ዝርዝር ማሳወቃችንም የሚታዎስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 29/2018 ዓ.ም የብልጽግና ፓርቲ በደብረ ማርቆስ ከተማ በጠራው የምርጫ ቅስቀሳ አልተሳተፋችሁም፤ የምርጫ ካርድም አላወጣችሁም፤ የተባሉ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 ተማሪዎቻችን በደህንነት ሰዎች ታፍነዋል።
በመሆኑም በተደጋጋሚ ኮሌጁን ለምርጫ ማስፈፀሚያነት ከመጠቀም ባለፈ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሲንገላቱ ቆይተዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ እንዲንቀሳቀስ መደረጉን አጥበቀን እየተቃወምን በቁጥጥር ስር የዋሉ መምህራን እና ተማሪዎቻችን እንዲለቀቁልን እንጠይቃለን። መላ ህዝባችንም ከተቋሙ ጎን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ።
የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
+4
በአገዛዙ በአስገዳጅ ሁኔታ ተገደው ስልጠና እየወሰዱ የነበሩ አምስት ህፃናት አገዛዙን በመክዳት 64ኛ ክ/ጦር እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
የአብይ አህመድ አገዛዝ የሚዘው የሚጨብጠው አጥቷል። 64ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና እነማይ እና ሸበል በረንታ ህፃናትን ለጦርነት ለመማገድ በአስገዳጅ ሁኔታ አፈና በማድርግ የለብ ለብ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ፖራ ኮማንዶ እያለ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ቢያሰራጭም በአስገዳጅ ሁኔታ የገቡት ህፃናት አገዛዙን በመክዳት ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል። ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ.እንቻለው ዘውዱ የትውልድ ቦታ አያልፉሽ ፖራ ኮማዶ
2ኛ.ኤርሚያስ ሚሊሻ ከየትመን ንዑስ ከተማ
3ኛ.ጥልጣል መስፍኔ ፖራ ኮማንዶ የትመን ንዑስ ከተማ
4ኛ.አትመን በላቸው ከሸበል በረንታ መርገጭ 01 ጥምር ጦር አንድ ኮሪያ ክላሽ ከ60 ጥይት ጋር
5ኛ.በልስቲ ገብሬ ፖራ ኮማንዶ ቲም መሪ የቀብሀና ተወላጅ የ15 ዓመት ህፃን ሲሆን የ2ኛ ዙሪ ፓራ ኮማንዶ ለ45 ቀናት ስልጠና የወሰዱ አገዛዙን በመክዳት 64ኛ ክ/ጦር እየተቀላቀሉ ይገኛል።
ሚያዚያ 30/02018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት
አፋብን ወሎ (ቤተ- አማራ) ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር ከሻለቃ አመራር በላይ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት በደማቅ ሁኔታ ተሀድሶ አደረገ።
በወሎ (ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር አካል የሆነው 12ኛ ክፍለ ጦር ከግዳጅ ጎን ለጎን ከሻለቃ አመራር በላይ የሰራዊት አባላት የተሀድሶ ፕሮግራም በማድረግ ለወደ ፊት ለሚደረጉ ግዳጆች ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለ ጦሩ አመራሮች ገልፀዋል።
በመርሀ ግብሩ ከተካሄዱት መካከል በ12ኛ ክፍለ ጦር ለአማራ ፋኖ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የተሻለ አበርክቶ ላላቸው ለምኒልክ ዕዝ ም/ሰብሳቢ ለአርበኛ ቀኝ አዝማች ረዳ ውበቱ እና ለምኒልክ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አማካሪ ለኮ/ል ሞገስ ዘገየ የካባ ሽልማትና የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል።
እንድሁም በአፋብን ወሎ (ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ የ102ኛ ኮር አካል የሆነችውና ለአማራ ህዝብ ትግል ፋና ወጊዋ 12ኛ ክፍለ ጦር የትግል አጋር ለሆኑት ለ6ቱ ኮሮችና ለልዩ ዘመቻ ለአማራ ህዝብ ሲሉ መሳዋትነት የከፈሉ ጀግኖችን ፎቶ በፍሬም በማሰራት በሽልማት ተሰጥቷል።
የተሀድሶ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የ102ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ የነበሩት አሁን የአፋብን ምኒልክ ዕዝ ም/ሰብሳቢ የሆኑት አርበኛ ቀኝ አዝማች ረዳ ውበቱ ሲሆኑ ለ12ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ አመራርና ለተጠሩ እንግዶች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የምኒል ዕዝ ም/ሰብሳቢው አያይዘው እንደገለፁት የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክ የመጣውን ነውረኛ አገዛዝ ለመደምሰስ የሰራዊት አባላችን፣ የአማራ ወጣቶችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን እንድሰለፍ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዛሬም ድረስ አማራ ጠሉ ጨፍጫፊ ስርዓት በምርጫ ስም በህዝባችን ላይ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል በማስቀጠልና አለኝ የሚለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ሙከራ ቢያደርግም ህዝባችንን ይዘን ስለሆነ የአማራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተስኖታል ሲሉ ገልፀዋል።
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የ12ኛ ክ/ጦር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሀብተማሪያም መንበሩ ለ12ኛ ክ/ጦር የሻለቃ አመራር የሰራዊት አባላት፣ ጥሪ ለተደረገላቸው የኮር፣የክፍለ ጦር አመራርና ለአፋብን ምኒልክ ዕዝ በአድሱ አደረጃጀት ሀላፊነት ለተሰጣቸው አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁና መልካም የስራ ዘመን እንድሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የ12ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዝ እንደተናገሩት ሰራዊታቸው ሁሌም በጥላት ላይ የሀይል የበላይነትን በመውሰዱ በስነ-ልቦና የዳበረና የህዝባችንን የጭቆና ህይወት የተረዳ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ጦርነቱን እንደሚያጠናቅቁ ገልፀዋል።
በ3ኛ ደረጃ ንግግር ያደረጉት የአፋብን ወሎ (ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ለ12ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ አመራር፣ ለከ/ጦር አመራር አንድሁም ለኮር አመራርና ጥሪ ለተደረገላቸው የድርጅት አመራር እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ወታደራዊ አዛዡ ካስተላለፉት ሀሳብ መካከል ስለ አላማ ፅናትና የትግል ባህሪያት በመግለፅ ማንም የአማራ ፋኖ ታጋይና አታጋይ የአማራ ብሔርተኝነትን ተላብሶ በህዝባችን ላይ በግደታ የተጫነበትን ቀንበር ከትክሻው ለማስወገድ ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ንግግር ያደረጉት የአፋብን ወሎ(ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ ዋና ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ በለጠ ሸጋው (ተራራው) ለ12ኛ ክ/ጦር የሻለቃ አመራር ፣ የክ/ጦር አመራር ፣የ102ኛ ኮር አመራር፣ የ101ኛ ኮር አመራር፣የልዩ ዘመቻ አመራርና ጥሪ ለተደረገላቸው የምኒል ዕዝ አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የህዝብ ልጅ ፋኖ ጤዛ ልሶ ድንጋይ ተተርሶ በምድር ላይ ውድ የሆነውን ህይወቱን በመሰዋት ስግብግቡን አገዛዝ በአፈሙዝኛ ቋንቋ በልኩ በማናገራችን በአማራ ክልል እንደፈለገ እንዳይንቀሳቀስ አድርገነዋል ሲሉ ገልፀዋል።
የምኒልክ ዕዝ ዋና ዘመቻ እንደ ተናገሩት ለማይቀረው የሞት ሽረት ትግል ሁሉም የአማራ ወጣቶችና የኢትዮጵያ ህዝቦች ከጎናችን እንድሰለፉ ሲሉ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ወሎ ቤተ-አማራ አመራር የሆኑት አርበኛ አሸናፊ ገናን (ወይራው አማራ) በዝግጅቱ በመገኘት ለ12ኛ ክ/ጦር ሻለቃ አመራርና ጥሪ ለተደረገላቸው የድርጅት አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ወይራው አማራ እንደተናገረው ከሆነ ጨፍጫፊውንና አምባገነኑን አገዛዝ ለመፋለምና ህዝባችንን ከገባበት ቅርቃር ውስጥ ለማውጣት ሰራዊቱ ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአፋብን ወሎ (ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አማካሪ ኮ/ል ሞገስ ዘገየ ለ102ኛ ኮር አመራር፣ ለ12ኛ ክፍለ ጦር አመራር፣ ጥሪ ለተደረገላቸው ኮሮችና የድርጅት አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከዚያ በመቀጠል አማካሪው እንደተናገሩት ከሆነ የብልፅግናን አገዛዝ በተግባር የማሸነፋችን ሚስጥር ህዝባዊ ሰራዊት በመገንባታችንና ህዝባዊ ድጋፍ ስላለን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የአፋብን የፖሊት ቢሮ አባልና የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ሀላፊ አርበኛ አበበ ፈንታው(የምስራቁ) እንደተናገሩት የአማራ ህዝብ የፍትህ፣ የነፃነትና የህገ-መንግስት ጥያቄ ስላለው በወርድና በቁመቱ ልክ የፖለቲካ ውክልና እስኪኖረው ድረስ ጠንካራ የአማራ ፋኖ ታጋይ እንድፈጠር ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።
የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ሀላፊው የአብይ አህመድ የብልፅግና አገዛዝ በ2010ዓ/ም በትረ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ በአማራ ህዝብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጭፍጨፋ በማድረጉ ምክኒያት ተገፍተን የወጣን መሆኑን በመረዳት አምባገነኑን ስርዓት ለማስወገድ ከምን ጊዜውም በላይ የአማራ ወጣቶችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን እንድሰለፉ ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የደባይ ጠላት ግን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
=======================================
የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የጦር መኮንኖች በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግ ልዕልናዋን እንደገፈፏት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት አመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህም 206ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ ከሐይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት
አፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47 ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ከደማቁ ምርቃት ማግስት ባንዳና አጎብዳጅ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ድል ተቀዳጁ::
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም በዕለተ አርብ ከመሃል ሳይንት ወረዳ( ደንሳ) ከተማ የኦህዴድ/ብልፅግና አመራሮችንና የምርጫ አስፈፃሚዎችን በዙ-23 አጅቦ ወደ ባህርዳር በመሄድ ላይ እያሉ ትንታጎቹ የአትሮንስ ሻለቃ ቃኞች ወርቅ ማውጫ ከተማ ዳርቻ ላይ ድባቅ መተዋቸዋል።
ጨፍጫፊውና ወንጀለኛው ቡድን ኦህዴድ/ብልፅግና አይኑን በጨው አጥቦ፣ የመኖር ሰብዓዊ መብቱን የነፈገውን የአማራ ህዝብ በአፈ-ሙዝ እያስፈራራ ምርጫን ተግባራዊ ለማድረግ እየተጋጋጠ ይገኛል።
የአማራን ህዝብ በመድፍና በድሮን በመጨፍጨፍና ለሰማይ ለምድር የከበደ ግፍና ሰቆቃ እየፈፀመ ስለ ምርጫ ማሰቡና ለተግባራዊነቱም እንቅስቃሴ ማድረጉ ኦህዴድ/ብልፅግና የነውረኞች ቁንጮ መሆኑን ያሳያል።
በደፈጣ ጥቃቱ የበሻሻው ወፈፌ (አብይ አህመድ) ስልጣን ጠባቂዎች 2ቱ ተቀንድሸው ወደ ከርሰ-መቃብር ሲወርዱ 9(ዘጠኝ) በላይ ቁስኞች ሆነዋል። ከቁስለኞች መካከል በሆዱ ዳዴ የሚል የባንዳነት ስነ-ልቦና የተጣባው ካድሬ መኖሩ ታውቋል።
ለኦህዴድ/ብልፅግና ወንጀለኛ ቡድን አፋሽ አጎንባሽ፤ አጎብዳጅና አሸርጋጅ የሆናችሁ ፍርፋሪ ተመፅዋች ባንዳዎች ከፀያፍ ድርጊታችሁ የማትታቀቡ ከሆነ መጨረሻችሁ የውሻ ሞት ነው!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ ተከሳሾች ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ በተደጋጋሚ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ አላከበሩም የተባሉት የማ/ቤቱ ኃላፊም ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋል።
በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው ከሚከታተሉ 16 ተከሳሾች መካከል 13ቱ ሚያዝያ 29/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር።
በተደጋጋሚ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ያላከበሩት የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ጣሰው ግዛውም በእለቱ ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋል።
መዝገቡ የተቀጠረው ተከሳሾች በተደጋጋሚ ያቀረቧቸውን አቤቱታዎችን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ለቂሊንጦ ማ/ቤት እና ለፌደራል ፖሊስ የሰጠውን ትዕዛዝ ምላሽ ለመጠባበቅ ነበር።
የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ በተደጋጋሚ ሲያጥፉ የከረሙት የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ጣሰው ግዛው በችሎት ተገኝተው በስራ መደራረብ ምክንያት በቀደሙ ቀጠሮች አለመገኘታቸውን በማስተረዎስ ለቀረቡላቸው አቤቱታዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የቀደመ የፍ/ቤትን ትዕዛዝ በራስ ስልጣን መጣስ ፣ ከቤተሰብ ግንኙነት ፣ ከመጽሀፍ እና ከሽፍን ጫማ ጋር በተያያዘ በተከሳሾች እና በቤተሰቦቻቸው ላይ እያጋጠመ ያለውን የመብት ጥሰትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር
አቤቱታዎች ቀርበዋል።
የምክር ቤት አባላት እነ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ፣ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፣ ዶ/ር ካሳ ተሻገር እንዲሁም ከአባ ሳሙኤል ማ/ቤት መሪጌታ በላይ አዳሙ ፣ እነ ሻንበል አድማሱ አለሙ እና ሙሉጌታ አገዘው በቂሊንጦ እና በአባ ሳሙኤል ማ/ቤቶች ስላለው ሁለንተናዊ ችግር አስተያየታቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል።
በተለይም የቤተሰብ ፍተሻው ሰብአዊ ክብርን የጠበቀ አለመሆኑ ፣ መጽሀፍት ከሕግ ውጭ ሳንሱር እየተደረጉ 'አማራ' የሚል ስም ያላቸው 'ያፋጃሉ' እየተባለ እንዳይገቡ እንደሚደረግ በአንጻሩ በኦሮሞ ስም የተጻፉት ግን እንደሚገቡና ይህም አድሎአዊ አሰራር ተገቢ እንዳልሆነ ተገልጧል።
በቂሊንጦ ያለው የውሃና የፀጥታ ችግር ፣ በምርመራ ወቅት በፖሊስ በደረሰበት ድብደባ የተነሳ ታሞ በአማኑኤል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ላይ የሚገኘው አማረ መለሰ እና ሌሎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እነ እንዳሰኘው ክበብ ፣ ሸጋው ምሃባው ፣ ስንታየሁ ንጋቱ እና ሌሎች የእድሜና ተያያዥ ችግር ያለባቸው ተከሳሾች ማ/ቤቱ ከአባ ሳሙኤል ይልቅ ደህንነታቸው ሊጠበቅና ቤተሰብም ሊጠይቃቸው በሚችሉበት ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት እንዲያዛውሯቸው እና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ኃላፊውም በምላሻቸው የፍ/ቤት ትዕዛዝን እየፈፀሙ መሆኑን ገልፀው ፣ ነገር ግን የአፈጻጸም ስህተት ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።
ያልተመለሱ አቤቱታዎችንና የፍ/ቤትን ትዕዛዝን ከተከሳሾች ጋር እየተነጋገሩ ምላሽ እንደሚሰጡም ለችሎቱ ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ ከተከሳሾች እየቀማ የወሰደውን ንብረት አላውቅም በማለት ክዷል ፤ የት እንዳለም በግልጽ ለመናገር አልፈለገም።
ተከሳሾች እንደተፈቱ የተወሰደባቸውን ንብረት ለማስመለስ ወደ ሜክሲኮ ሲሄዱ ፌደራል ፖሊስ ለምን ጠየቃችሁን በማለት እያሰረ እንደሚያንገላታ እና እንደሚያስፈራራ ፣ ንብረትም እንደሚዘርፍ በብዙዎች በተደጋጋሚ እየቀረበ ያለ ቅሬታ ሆኖ እንደቀጠለ ነው።
በፍ/ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ የአፈጻጸም ሂደት ለመከታተል በሚል ለግንቦት 28/2018 ቀጠሮ ተይዟል።
©መረጃው የአውሎግሶን አንድነት ነው።
ሰበር ዜና አድማ ብተና 💯🛑
የአማራ አድማ ብተና የልዩ ኃይል እጣፋንታ ሳይገጥመው አልቀረም
በአመራር ደረጃ የአድማ በታኝ አመራሮች በመከላከያ ውስጥ የስልጣን ቦታቸውን አውቀዋል
ለበርካታ ቀናት ሲደረግ የነበረው የአማራ ክልል የፀጥታ ዝግ ስብሰባ ዛሬ በይፋ ወጥቷል
አባሎቹ እንዴት እንገራችው ይበተኑብናል በማለት ነው እንጅ የአመራሮች ሹመት ተጠናቋል
የሌሎቹ ክልሎች እንደማይፈርስ እና ባለበትም እንደሚቆይ ተረጋግጧል
የሚፈርሱበት ዋነኛ ምክንያት አልተማመንም ሲሆን ፋኖን ይቀላቀላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን ሲል የመከላከያ ዋና አዛዥ አስታውቋል
አማራ ክልል ላይ መሳሪያ የታጠቀ ሃይል ማየት አይፈልጉም ምክንያቱም አማራን ማ*ዳ*ከ ነው ህልማቸው እራሱን እንዳይከላከል የማድረግ ህልም ላይ ስለሆኑ
እናም የአማራ አድማ ብተና አባላት እና አመራሮች እናንተን የሚፈልግ ህዝብ እና ሀይል አላችሁ በናንተም አይፈረድም የማይሆን ፖለቲካ ስላጠጧችሁ ነው አሁን ግን እውነታውን መጋፈጥ አለባችሁ ከመበተናችሁ በፊት ወንድሞቻችሁን ተቀላቀሉ አድማ እና ፋኖ አንድ ከሆነ አይደለም መከላከያ ቀርቶ ማንም አይቆቋመንም የወንድሞቻችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ
ሊበትነን የመጣን መንግስት ነን ባይ እኛ ቀድመን እንበትነው
የመረጃ ምንጮች ከስብሰባው አካል ለአማራ ህልውና የሚቆረቆር አመራር ነው
አፋብን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በአብይ አህመድ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀናጀ!!
እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አየር ወለድ መከላከያ ጥምር ጦር በተከታታይ ለሦስት ቀናት በኤፍራታ ግድም ወረዳ ማጀቴ ዙሪያ በታንክና በመድፍ የታገዘ ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ አገዛዝ በተለይም ለኦሮሞ ብልፅግና ሚሊሻ ሽፋን በመስጠት ከ400 (አራት መቶ) በላይ የማጀቴ ዙሪያ ማህበረሰብ የቀንድ ከብቶችን ዘርፎ ወስዷል። ይህም አልበቃው ብሎ የአማራ ማህበረሰብ የሰብል ምርቶችን እያቃጠለና እያወደመ ይገኛል።
ሆኖም ይህንን የኦሮሙማ ሥርዓት ከምድር ገጽ ለማጥፋት በዱር በገደሉ የሚዋደቁት የአማራ ፋኖዎች እውነታውን በተግባር አሳይተዋል። በዚህም የተበሳጩት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በትላንትናው ዕለት ቆሪ ሜዳ እና ካሮ ቆሪ በመግባት፣ በሰርጎ ገብነት በብአዴን አንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ በመውሰድ አንድ ሙት እና አንድ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በዚህም በአንቃር ኮበኮብ ሚካኤል (አንቃ ሚካኤል) አካባቢ በአብይ አህመድ አየር ወለድ መከላከያ ኮማንዶ አዋጊ ላይ ቀጥታ የሞርተር ጥቃት በመጣል እሱ እንዲቆስልና አጃቢዎቹ እንዲሞቱ ተደርጓል!
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በአብይ አህመድ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀናጀ!!
እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አየር ወለድ መከላከያ ጥምር ጦር በተከታታይ ለሦስት ቀናት በኤፍራታ ግድም ወረዳ ማጀቴ ዙሪያ በታንክና በመድፍ የታገዘ ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ አገዛዝ በተለይም ለኦሮሞ ብልፅግና ሚሊሻ ሽፋን በመስጠት ከ400 (አራት መቶ) በላይ የማጀቴ ዙሪያ ማህበረሰብ የቀንድ ከብቶችን ዘርፎ ወስዷል። ይህም አልበቃው ብሎ የአማራ ማህበረሰብ የሰብል ምርቶችን እያቃጠለና እያወደመ ይገኛል።
ሆኖም ይህንን የኦሮሙማ ሥርዓት ከምድር ገጽ ለማጥፋት በዱር በገደሉ የሚዋደቁት የአማራ ፋኖዎች እውነታውን በተግባር አሳይተዋል። በዚህም የተበሳጩት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በትላንትናው ዕለት ቆሪ ሜዳ እና ካሮ ቆሪ በመግባት፣ በሰርጎ ገብነት በብአዴን አንዳ ሚሊሻ ላይ እርምጃ በመውሰድ አንድ ሙት እና አንድ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በዚህም በአንቃር ኮበኮብ ሚካኤል (አንቃ ሚካኤል) አካባቢ በአብይ አህመድ አየር ወለድ መከላከያ ኮማንዶ አዋጊ ላይ ቀጥታ የሞርተር ጥቃት በመጣል እሱ እንዲቆስልና አጃቢዎቹ እንዲሞቱ ተደርጓል!
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም
ኮሩ የቀድሞ አመራሩን ፶ አለቃ ፀሐዬ ወልዴን የ40 ቀን መታሰቢያ የዝክረ ሰማዕታት ዕለት አክብሮ ውሏል።
አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ምክትል ጦር አዛዥ የነበረው ጀግናው አርበኛ ፶ አለቃ ፀሐዬ ወልዴ ለወጣለት ትክክለኛ አላማ፣ ለአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ ሲል ለአንድያ ህይዎቱ ሳይሰስት መጋቢት 20 ቀን 2018ዓ.ም ውድ መስዋዕትነት መቀበሉ ይታወሳል።
የአማራ ህዝብ የምንግዜም ባለውለታ የሆነው የጀግናው አርበኛ ፶ አለቃ ፀሐዬ ወልዴ የ40 ቀን መታሰቢያ የዝክረ ሰማዕታት ቀን የትግል ጓዶቹ፣ በየደረጃው የሚገኙ የዕዝ፣ የኮርና የክፍለጦር አመራሮች እንዲሁም ሰራዊታችን በተገኘበት ቀኑ በክብር ታስቦ ውሏል።
በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ "ጓዳችን ጀግናው ፶ አለቃ ፀሐዬ ወልዴ የተሰዋህለትን ትግል ከግብ ለማድረስ ቃል እንገባለን!" በሚል የወል የቃልኪዳን አደራ በመግባት ዕለቱ ተከብሮ ያለፈ ሲሆን፣ በመረሀ ግብሩ ላይ ከተሳተፉት የተለያዩ የክብር እንግዶች የአማራ ህዝብ የህልውና ትግልን በተመለከተ የዛሬዋ መራር ቀን የነገው የነፃነታችን ዋስትና መሆኑን የሚገልፁ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ሰማዕታትን እንዘክራለን፣አላማቸውን እናሳካለን!!!
ጀግናችን ሁሌም በልባችን ትኖራለህ!!
ታጋይ ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
በራያ ቆቦ በአገዛዙ የከባድ መሳሪያ ድብደባ የህፃናት ህይወት አለፈ፤ ንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል
የብልጽግና አገዛዝ በበርካታ ግንባሮች እየደረሰበት ያለውን ወታደራዊ ሽንፈት ተከትሎ፣ ከተሞችንና የገጠር ቀበሌዎችን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ የንጹሃን አማራዎችን ህይወት በጅምላ የመቅጠፍ እርምጃውን መቀጠሉ ታወቀ።
በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለይም ባለፉት ሁለት ቀናት በራያ ቆቦ አካባቢ በደረሰ የመድፍ ጥቃት ህፃናት ሰለባ ሆነዋል።
ትላንት ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ላይ፣ አገዛዙ በራያ ቆቦ "ጮቢ በር" ላይ መድፍ በማጥመድ ወደ ራያ አላማጣ "ኩቢ ቀረንሳ" በመተኮሱ፣ በአቶ ወዳጅ ደሳለ ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
በዚህ ጥቃት ገነት ወዳጅ የተባለች የ6 ዓመት ህፃን እና ሞነን ወዳጅ የተባለች የ12 ዓመት ታዳጊ በጽኑ ቆስለው በሕክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የቤተሰቡ ንብረት የሆነና በ110 ሺህ ብር የተገዛ ግመልም ተገድሏል።
ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጮቢ በር የተተኮሰው መድፍ በራያ ቆቦ "ጃሮታ አዲሱ መንደር" ላይ ባረፈው ጥይት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ታዳጊዎች ተመተዋል።
በዚህም ዮሐንስ ሙለታ የተባለ የ13 ዓመት ታዳጊ ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ፣ ዳዊት ሙለታ የተባለ የ10 ዓመት ታዳጊ ደግሞ ለከባድ ቁስለት ተዳርጓል። ከሰው ህይወት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የቀንድ ከብቶች ተጨፍጭፈዋል።
አገዛዙ የፋኖን ሰራዊት በውጊያ ሜዳ መቋቋም ሲሳነው፣ ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሃንንና ህፃናትን በከባድ መሳሪያ ኢላማ ማድረጉን ቀጥሏል።
ይህ ድርጊት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ቁጣንና ሀዘንን የፈጠረ ሲሆን፣ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አገዛዙ በተስፋ መቁረጥ የጅምላ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ገልጿል።
+1
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በፈፀመው ኦፕሬሽን የምስራቅ ጎጃም ነባር ካድሬዎች የሚጠቀሙበት ሰሌዳ ቁጥር (4)02916 መኪና ተማርኳል።
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
=======================================
መንፈስ የሆነው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ ጠንካራ ግዳጆችን የፈፀመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከጠላት መዳፍ መኪና ማርኮ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ማውጣቱን አስታውቋል።
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከታህሳስ 24-2018 ዓ.ም _ሚያዚያ 29 /2018 ዓ.ም የተሳኩ ኦፕሬሽን በመፈፀም ድሎችን ያስመዘገባቸው
- ደብረ ማርቆስ
-ሉማሜ
- ቁይ
- ደብረ ኤልያስ
- ጎዛምን
- ደጀን ከተሞች ላይ 41 የተሳኩ የቦምብ ጥቃት በመፈፀም 168 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ 105 የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ከ273 የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት ማድረስ ተችሏል።
-7 የሚደርሱ ካድሬዎች ሀምሳ አለቃ፣ መቶ አለቃ፣ የኢንስፔክተርና የሻምበል ማዕረግ ያላቸው የጠላት አመራሮች ከተገደሉት መካከል የሚገኙ ሲሆን 12 የሚደርሱ ፓትሮልና የጭነት መኪኖች ከጥቅም ውጭ ሁነዋል።
የጠላት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ የምስራቅ ጎጃም ነባር ካድሪዎች ይገለገሉባቸው የነበሩ ሁለት መኪኖችንም ማውጣት ተችሏል።
በፀረ -መረጃ ኦፕሬሽን በሰራዊታችን እና በህዝባችን የተሰገሰጉ ከጠላት ጋር ግንኙነት ያላቸው 27 ባንዳዎች 27 በቁጥጥር ስር በማድረግ በ12ቱ ላይ አስተማሪ እርምጃ ተወስዷል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
