ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 487
Obunachilar
-524 soatlar
+677 kun
+84830 kun
Postlar arxiv
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር በአባይ ሸለቆ ብርጌድ ለአለፉት ሁለት ሳምንታት የተደረገው የስልጠናና የውይይት መድረክ በስኬት ተጠናቋል።
የአፋብሐ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የም/ አ/ ቴ/ዕዝ ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ፣የምዕራብ አማራ ቴ/ዕዝ ም/ስትራቴጂክ ክፍል ኃላፊ አርበኛ ዳዊት መሐሪ በተገኙበት የተደረገው ወይይትና የስልጠና መድረክ የዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አመራሮች ጨምሮ የብርጌዱ አመራሮች ተሳታፊዎች ሁነዋል።
በወቅታዊና አሁናዊ አንኳር ጉዳዬች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከሻንበል መሪዎች እስከ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት መድረክ የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ለድርጅታዊ ልዩ ግዳጅ በመሰለፍ እና ለአማራ ፋኖ ትግላዊ አንድነት ለአበረከተው አስተዋጽኦና የከፈለው መስዋትነት በከፍተኛ አመራሮች እውቅና ተሰጧል።
የአባይ ሸለቆ ብርጌድ የሚንቀሳቀስበት የአባይ ጎርጅ አራቱን ክ/ሀገራት እንደ ማዋሰኑ መጠን ለአማራ ፍኖ ትግል ለወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መደላድሎችን ለመፍጠር ተሞክሮዎችን በማጠናከር የድርጅቱን ተልዕኮ ለማስፈፀም የብርጌድ አመራሮች ብሎም የሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ ቁመው ለተሻለ ግዳጅ እንዲዘጋጁ በመድረኩ ጥብቅ መልዕክት ተላልፏል።
አሳታፊ በነበረው ውይይት የብርጌድ አመራሮችን ስራ አፈፃፀም በተመለከተ ግምገማ በማድረግ በተለያዩ መደቦች ለተሻሉ የሰራዊት አባላት የብርጌድ አመራር ምደባ ተሰጧል። ተቋማዊ እድገትና የአመራር ብቃት ፍተሻ በተደረገበት ጠንካራ ግምገማ ድርጅታዊ እድገትን በተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ መሰል የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በሁሉም ቀጠና አጠናክሮ የቀጠለው ድርጅቱ አመራሩ ማዕከላዊነትን በጠበቀ መልኩ የስራ ስምሪት ወስዶ ስራ አስፈጻሚው በቅንጅት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ተብሏል።
በመጨረሻም በትግሉ ወቅታዊ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን በአሰራር ክፍተት የተፈጠሩ ችግሮችን በጋራ ለማስተካከል ሁሉም በአንድ ላይ በመሰለፍ ተስፋ እየታየበት የሚገኘውን የአንድነት ጉዞ ዳር ለማድረስ የሚመለከተው ሁሉ ለሰራዊቱና በሁሉም ቀጠና ለሚገኘው ህዝብ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"በቸርነትህ_ዓመትን_ታቀዳጃለህ_ምድረ_በዳውም_ስብን_ይጠግባል።" መዝሙር ፷፬፤ ፲፩
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ለ2018 ዓ.ም የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት:
በዘመናት ዑደቶች ውስጥ ከምናከብራቸው በዓላት አንዱ የሆነው የዘመን መለወጫ በዓል (ዕንቁጣጣሽ ) አንዱ ነው ። ከዘመን መለወጫው ዋዜማ ጀምሮ ዕንቁጣጣሽ ተብሎ እንደሚጠራ ኢትዮጰያዊያን አባቶቻችን አስተምረውናል። ዕንቁጣጣሽ "እንኳን መጣሽ" በምትባለው ወርሃ ጷጉሜ እንቁ በሆኑ በባህላዊ ጭፈራዎቻችን እና በቤተ እምነቶቻችን በዜማዎች በተለየ ሁኔታ ይከበራል። ይህ ሁሉ ለሀገራችን የከበረ የባህል ውርስ እና ልዩ መለያ ጌጥ ሆኖ ኖሯል ወደፊትም ይኖራል።
“መስከረም ከእነ ሥሩ ለምለም” የሚለው የማህበረሰባችን አነጋገር፣ የተዘሩ አዝርዕት ፍሬ የሚጀምሩበት ፣ውሃ የሚጠራበት ፣ብርሃን የሚገለጥበት ክረምቱ ተግ የሚልበት ጊዜ በመሆኑ፣ በአዲስ ዓመት አዲስ መንፈስ፣ አዲሱ ትውልድ፣ አዲሱን አስተሳሰብ ፣ አዲሱን ተስፋ ፣ በአዲስ ቃል ኪዳን የአማራን አንድነት የሚያበስርበት ዓመት ነው።
በሀገራችን “መስከረም ሲጠባ፣ አደይ ሲፈነዳ፣ ሰው እንኳን ዘመዱን ይጠይቃል ባዕዳ” ይባላል። በመስከረም ውሃዎች ስለሚጎድሉ፣ ሰው ወንዞችን ተሻግሮ "ባዕድ ዘመድ" ሳይል የሚጠያየቅበት ጊዜ በመሆኑ፣ ንጉስ ተከለሃይማኖት ብርጌድም አዲሱን ዓመት በዚሁ አዲስ የተስፋ መንፈስ ሆኖ ይቀበለዋል።
የተከበርከው የአፋብኃ ሰራዊት ይሄው ፀሃይም ብርሃኗን ፈነጠቀች አካባቢው ሁሉ በአበቦች ፈካ አዲሱ ትውልድም በአዲስ አመት አዲስ ተስፋ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ብሩህ ራዕይ እና የተቀደሰ አላማ ይዞ በአሸናፊነት ታጅቦ ብቅ አለ። መጭዉ ዘመን እቅዶቻችንን የምናሳካበት የትግሉን ፍፃሜ በአሸናፊነት የምንቋጭበት ዘመን እንዲሆን ተቋማዊ ምኞታችን ነዉ።
ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድም ለሁሉም አመራሮቻችንና ጓዶቻችን ፣ በየደረጃዉ ያለ ሰራዊታችን ፣ ለመላዉ የዐምሐራ ሕዝብና ደጋፊዎቻችን እንኳን ለ 2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ እያልን መላው የአማራ ህዝብ እና መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ አዲሱ አመት የአንድነት፣የአሸናፊነት፣የድል አድራጊነት እና የተድላ ይሁንልን እንላለን።
ባለፉት 2 ዓመታት በነበረው እልህ አስጨራሽ ትግል የተሰው ሰማዕታት ጓዶቻችንን እና የንፁሃንን ነፍስ ቸሩ ፈጣሪ በደጋግ አባቶቻችን በአብርሃም በይስሃቅ አቅፍ ያኑርልን እንላለን!!!
መልካም አዲስ አመት🙏🙏
ክብር እና ሞገስ ለተሰዉ ሰማዕታት!!!
ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል!!!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
#የንጉስ_ተከለሃይማኖት_ብርጌድ_ህዝብ_ግንኙነት_መምሪያ
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር በአባይ ሸለቆ ብርጌድ ለአለፉት ሁለት ሳምንታት የተደረገው የስልጠናና የውይይት መድረክ በስኬት ተጠናቋል።
የአፋብሐ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የም/ አ/ ቴ/ዕዝ ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ፣የምዕራብ አማራ ቴ/ዕዝ ም/ስትራቴጂክ ክፍል ኃላፊ አርበኛ ዳዊት መሐሪ በተገኙበት የተደረገው ወይይትና የስልጠና መድረክ የዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አመራሮች ጨምሮ የብርጌዱ አመራሮች ተሳታፊዎች ሁነዋል።
በወቅታዊና አሁናዊ አንኳር ጉዳዬች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከሻንበል መሪዎች እስከ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት መድረክ የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ለድርጅታዊ ልዩ ግዳጅ በመሰለፍ እና ለአማራ ፋኖ ትግላዊ አንድነት ለአበረከተው አስተዋጽኦና የከፈለው መስዋትነት በከፍተኛ አመራሮች እውቅና ተሰጧል።
የአባይ ሸለቆ ብርጌድ የሚንቀሳቀስበት የአባይ ጎርጅ አራቱን ክ/ሀገራት እንደ ማዋሰኑ መጠን ለአማራ ፍኖ ትግል ለወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መደላድሎችን ለመፍጠር ተሞክሮዎችን በማጠናከር የድርጅቱን ተልዕኮ ለማስፈፀም የብርጌድ አመራሮች ብሎም የሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ ቁመው ለተሻለ ግዳጅ እንዲዘጋጁ በመድረኩ ጥብቅ መልዕክት ተላልፏል።
አሳታፊ በነበረው ውይይት የብርጌድ አመራሮችን ስራ አፈፃፀም በተመለከተ ግምገማ በማድረግ በተለያዩ መደቦች ለተሻሉ የሰራዊት አባላት የብርጌድ አመራር ምደባ ተሰጧል። ተቋማዊ እድገትና የአመራር ብቃት ፍተሻ በተደረገበት ጠንካራ ግምገማ ድርጅታዊ እድገትን በተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ መሰል የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በሁሉም ቀጠና አጠናክሮ የቀጠለው ድርጅቱ አመራሩ ማዕከላዊነትን በጠበቀ መልኩ የስራ ስምሪት ወስዶ ስራ አስፈጻሚው በቅንጅት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ተብሏል።
በመጨረሻም በትግሉ ወቅታዊ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን በአሰራር ክፍተት የተፈጠሩ ችግሮችን በጋራ ለማስተካከል ሁሉም በአንድ ላይ በመሰለፍ ተስፋ እየታየበት የሚገኘውን የአንድነት ጉዞ ዳር ለማድረስ የሚመለከተው ሁሉ ለሰራዊቱና በሁሉም ቀጠና ለሚገኘው ህዝብ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አስቸኳይ ቀዶ ጥገና አደረጉ
የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በዛሬው ዕለት መቅረዝ ሆስፒታል ታሞ ገብቶ ባለፈው ሰርጀሪ የተሰራበት ቦታ ላይ እባ'ጭ ተገኝቶባቸው #አንጀታቸው አካባቢ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል።
የሆስፒታሉ ዶክተሮች ሕመሙ ከባድ የሆነ እና ለ3 ቀን ያለማቋረጥ ደም የሚፈስ ስለሆነ የተወሰነ ጊዜ ተኝቶ መታከም አለበት ቢሉም ፖሊሶች #ደም_እየፈሰሳቸው መልሰው ወስደውታል ሲሉ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።
ክቡር አቶ ክርስቲያንን እግዚአብሔር ይማርህ በሏቸው !
#ለሆዱ_ያልተሸጠ_ህሊናውን_ያስቀደመ
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመ ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ በዛሬው እለት ከአዴት ወደ ጎሸየ ሲንቀሳቀስ በነበረ ሚሊሻና ፓሊስ ላይ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጎሸየ ቀበሌ ላይ ደፈጣ በመጣል ጥቃት ፈፅመዋ።
በጉዳቱም 4 የሚሻ እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን 5 የፓሊስ እና ሚሊሻ አባላት ላይ በከፍተኛ ጉዳት ቆስለው ሆስፒታል መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለናል።
መቶ አለቃ አበው ፈጠነ የተባለ የይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ የዙሪያ ወረዳ ፓሊስ አዛዡ በከባድ ሁኔታ ቆስሎ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብቷል።
በቀጣይም ከጠላት ጋር የሚሰሩ የተሰለፉ ተባባሪወችን በተጠና መንገድ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 1ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
05/13/2017 ዓ.ም
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
~ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ድል ተቀዳጅቷል!
በዛሬው እለት ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም የአፋብኃ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክ/ጦር
በረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ በየቀጋት ቀበሌ መሽጎ በሚገኘው የጠላት ካምፕ ላይ ከባድ ጥቃት ፈጽሟል።
ስም አጠራራቸው የጠላትን መቅኒ የሚያፈሰው የበረሀው ፈርጦች ቀስተኞቹ የቀስተ ደመና አናብስቶች ሌሊቱን ተስበው ከጠላት ምሽግ በመገኘት ከምሽጉ የተወሸቀውን የሙታን ስብስብ በጨበጣ ተኩስና በቦምብ ሲያርመጠምጡት አርፍደዋል።
በዚህ መብረቃዊ ጥቃትም:
~ ብዛት ያለው የጠላት ሃይል የተደመሰሰ ሲሆን ጠላት ሬሳውን ከየጢሻው ሲለቅም አርፍዷል።
~ ሁለት አምቡላንስና አንድ ፓትሮል የጠላት ቁስለኛ መነሳት ችሏል።
~ አንድ የጠላት ወታደር ከነ ጥቁር ክላሹ ተማርኳል።
ቀስተ ደመና
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ህዝብ አገዛዙን ለአኔዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ሁለተናዊ ትብብርና ቁርጠኛ ትግል እንዲያካሂድና አገዛዙን አስወግዶ ቀሪ ዘመኑን በሰላም የሚወዳትን ሀገሩን ሰርቶ መኖር እንዲችልባት የሚያደርግ ዝግጅት እንዲያደርግ እናሳሰባለን።
ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ፣ የድርጅት መሪዎችና የማህበረሰብ ተወካዮች የሀገር ተቆርቋሪዎች በውጭ ሀገር ሆነው በበቅርብ ጊዚያት የሚያደርጓቸው የሚፈጥሯቸው የትብብር እንቅስቃሴዎች በእኛ በኩል በበጎ የሚታዩና ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባቸው ናቸው ብለን እናምናለን። ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁሉን አካታችነትና ግልፅነትን እየተላበሱ ከመጡ ለሁለንተናዊ ፀረ ዘረ ፈጅ ትግሉ ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታሉ ብለን ስለመናምን በ2018ዓ.ም ተጠናከረው እንዲቀጥሉ እንመኛለን።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሰላማዊ አመራጭም ሆነ በትጥቅ ትግል የሚደረጉ የተኛውንም ተጨባጭ ፀረ ብልፀገና አገዛዝ ትግሎችን በሙሉ የአማራን ህውብ ጥቅምና የኢትዮጵያን አንድነት እስካከበሩ ድረስ በበጎ የምናያቸው መሆኑን ማሳወቅ አንወዳለን።
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ
ኢትዮጵያ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም
"የማንወጣው ተራራ የማናሸንፈው መከራ የለም"
አዲሱን የ2018 ዓ.ም አስመልክቶ ከአፋብኃ የተላለፈ መልእክት
የተከበርኸው የአማራ ህዝብ ፣ የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የተከበርኸው የአማራ ታጋይ መላው ሰራዊታችንና የድርጅታችን ደጋፊዎች አማራ ጊዜ ቆጥሮ ፣ ዘመን አመሳጥሮ፣ ሰውን ከተፈጥሮ ፣ ፈጣሪን ከጊዜ አስተሳስሮ በሚከተለው የራሱ የአቆጣጠር ሥልት አዲስ ዓመትን ይቀበላል፣ ያከበራል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ህዝባችን የመንግስት ስልጣንን በተቆናጠጡ የራስ ወራሪዎች ግልፅ ጦርነት ተከፍቶበት ከሩቅ ሳይሆን ከቅርብ ቤት ለቤት ፣ በጓዳው ፣ በቀየውና በከተማው፣ በመንደሩና በአድባሩ በድሮን ፣ በጅምላ ጨራሽ መሳሪያና በአልሞ ተኳሽ ሀይል እየተገደለ ፣ እየተሳደደ ፣ እየተረሸነ ይገኛል፤ ከዚህም አልፎ ሀብትና ንብረቱን እየተዘረፈ ፣ እየተቃጠለበት ነፍት የለሽ ጥቃትና በደል እየተፈፀመበት ይገኛል። በእነዚህ ሁለት ዓመታት ህዝባችን በሰጠን ባደረገው ግልፅ ትግል ፣ በሰጠን ልዩ ድጋፍ ፣ በከፍለልን የነፍስ ዋጋ ላይ ቆመን ይሄንን ፀረ ፍጥረት እና ዘረ ፈጅ የሆነ ስርአት እየታገልነው አንገኛለን። በተለይም ባለፈው ዓመት ዘረ ፈጅ አገዛዝ አጅግ በተጠናከረ መልኩ ታግለን የገባው እንዳይወጣ የሚወጣው እንዳይመለስ፣ የሚመለሰው አንዳይሰነብት አደርገን ለምድሩ ባዳ ለሰው አንግዳ እንደሆነ ወራሪነቱን ሳያሳካ በየቀየው በየሸንተረሩ በየሜዳው በለኮሰው እሳት ተለብልቦ እንዲቀር አድርገነዋል።
ጀግናው የፋኖ ሰራዊት በአራቱ የአማራ ግዛቶች ባደረገው ተጋድሎ በእየለቱ ከሚያስመዘግበው ድል በላይ በእየለቱ እየተደራጀ ፣ እየጠነከረ በቁጥርም በጥራትም የሰራዊት ደረጃን እያሟላ የአማራንሀ ህዝብ ህልውና ከማስጠበቅ ባሻገር ላለው ግልፅ የመንግስትነት አላማ ጉዞ እራሱን በሁሉም ዘርፍ እያበቃ ይገኛል።
በዚህም ምንም እንኳን በዘረ ፈጁ አገዛዝ ቤት ንብርትህ ወድሞብህ ፣ ቤተሰብ ወዳጅህን አጥተህና ሰውተህ ጥቁር ብትለብስም፣ በወገብ ገመድ በልብህ የሞተ ዘመድ ብትሸከምም ፤ በየቀኑ በምታየው የፋኖ ሁለተናዊ ለውጥ ደስተኛ የሆንኸው የአማራ ህዝብ ሆይ ለ2018 አዲስ ዓመት እንኳን አደረስህ።
እስካሁን እንደ አማራ ለወጠንነው ትልቅ ጉዞ፣ ለምንደርስበት የነገ መዳረሻችን እንዲሁም ለምንወጣው ሀያል ተራራ ፣ ለምንከፍለው እልፍ መከራ ከጎናችን ሆነህ ልብስም ጉርስም ፣ አልጋም ትራስም ሆነህ እዚህ አድርሰኸናልና በቀጣይ በክንዳችን ለምናስከብረው ህልውናችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሙሉ በሙሉ ድርጅታዊ ቅርፁን ጨርሶ ፣ ሰራዊቱ አውቆና ታጥቆ ሊጠብቅህ ብቻ ሳይሆን ነፃ ሊያወጣህ የተዘጋጀ መሆኑን ስናበስርህ እንኳን ለ2018 ዓ.ም አደረሰህ በማለት ጭምር ነው።
ይህ ዓመት ከሰሞኑ የጀመርነው የአፋብኃ አጠቃላይ የድርጅት ምስረታ ጉዞና የአንድነት መንፈስ አጠናከረን የምንቀጥልበት እንዲሁም ከቀሪ የአማራ ህልውና ትግል ውስጥ ከሚሳተፉ እኛን መሰል ድርጅቶች ጋር አንድ የምንሆንበትና የምናብርበት ዓመት እንደሚሆን ስንገልፅ በቁርጠኝነትና በተስፋ ነው። በተለይም ከአፋሕድ ጋር በስርዓት በመነጋገርና በመወያየት ለወጣንለት ህዝብ ህልውናን የማትረፍ አላማ በመታመን አንድነታችንን ተግባራዊ ለማድረግና በጋራ አንድ ተቋም ለመመስረት ከሁል ጊዜውም በላይ ልዩ ጥረት እናደርጋለን። በዚሁ አጋጣሚ መላው የአፋሕድ አመራር ሰራዊትና ደጋፊዎች መጪው አዲስ አመት የእኛ የአማራ ህልውና ታጋዮች አመት እንጅ የሰርጎ ገቦች የመጫወቻ ፣ የጠላቶቻችን መዘባበቻ መሆናችን የሚያበቃበት እንዲሁም እርስ በእርስ ፖለቲካዊ መጎነታተልና መጓተት የማናደርግበት እንዲሆን ሁላችንም በቅንነትና በእውነት እንድንተባበር ጥሪ እናቀርባለን።
አፋብኃ በአዲስ መንፈስ በአዲስ ስልትና በጠነከረ ድርጀታዊ ማንነት ተገልጦ ለአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ መቀልበስና ለዘላለማዊ ክብር ክብርና ፍትሃዊና አሳታፊ ስርዓት ለመፍጠር የማንወጣው ተራራ የማንሸከመው መከራ የለም።
የተከበራችሁ የመላው የአማራ ፋኖ ሰራዊት ቀጣዩ ዓመት አሁን የተጀመሩና ላለፉት ሁለት አመታት የቀጠሉ ዓለም የመሰከረላቸው፣ ጠላት ቃላት ያጣላቸው፣ በአስገራሚ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጥበብ የተፈፀሙ ተጋድሎዎች፣ልዩ ጀብዶዎቻችን እና ጠላትን የማንበርከክ ዘወትራዊ ተግባራችን፣ ሁሌም አዲስ ፣ ሁሌም ልዩ የሆኑ የሰራዊት ግንባታዎቻቸን አጠናክረን የምንቀጥልበትና ጠላትን ሙሉ በሙሉ አንበርክከን ህዝባችንን ነፃ የምናወጣበት ዓመት ነው።
የተከበራችሁ በውጭ ሀገር የምትኖሩ ውድ አማራውያን የትግላችንና የድርጅታችን ደጋፊዎች እስካሁን ያደረጋችሁት ድጋፍ የሰጣችሁን ጊዜ ሀብትና ትኩርተ እንዲሁም ያሳያችሁን ወገናዊነ ቁጭጭና ትእግስ ለእኛ ለሄልውና ታጋዮች እጅግ ከፍተኛ የሚባልና በምንም ሊገመት የማይችል መሆኑን እንረዳለን። አሁንም ይሄንን አማራዊ ድጋፋችሁንና ወገናዊ ትብብራችሁኔ አጠናክራችሁ በመቀጠል ለአንድነታችና ለህልውና ትግላችን ውጤታማነት ከጎናችሁ ቁማችሁ ቀጣዩ ዓመት የአማራ ህዝብ ነፃ የሚወጣበትን አገዛዙን የምናስወግድበት አመት አንደሚሆን ተረድታትሁ የጀመራችሁዋቸውን የዲፕሎማሲ ፣ የህዝብ ለህዝብ ብሎም መሰል አይተኬ ተግሎች አንድታጠናክሩ እንጠይቃለን።
በአገዛዙ የግድያ ስርዓት ውስጥ ላላችሁ ወታደራዊ አመራሮች ፣ የመከላከያ፣የአድማ ብተናና ሚኒሻ አባላት በሙሉ ከአንዳንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ውጭ ብዙዎቻችሁ ልባችሁም ሀሳባችሁ ከህዝባችሁ ጎን መሰለፍ አንደሆነ እንረዳለን። ለጊዜው በግልፅነት ማነስና በሚደረግባችሁ ጫና አገዛዙን እያገለገላችሁ ኸገናችሁን እየገደላችሁ አንጨፈጨፋችሁ እረፍት እያሳጣችሁት ለመቀጠል የማትችሉበት ደረጃ ላይ መደረሳችሁን ትረዱታላችሁ። በመሆኑም በ2018 ወደ ህዝባችሁ መከታነት መጥታችሁ ፋኖን በመቀላቀል ቀሪ ዘመናችሁን በሰላምና በነፃነት ከህዝብ ጎን በመሆን እንድትኖሩ ራሳችሁን ጨምሮ ካለ እረፍት እየበላ ያለውን ስርአት ትታችሁ በመውጣት በየ አካባቢያችሁ ያለውን የፋኖ ሀይል ተቀላቅላችሁ ይሄንን አገዛዝ አብረን እንድናስወግድ እንጠይቃችኋለን።
የተከበርኸው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ዘረፈጅ የአብይ አህመድ አገዛዝ ባለፉት አመታት በተሳና በተጠና መንገድ ሲገድልህ ፣ ሲያሳድድህ ፣ ሲያፈናቅልህ፣ ብሎም ባሕር በየብስ የአዞና የአውሬ እራት ሲያደርግህ፣ ከጦርነትና ከስደት የተረፈውን ጊዜውን ተጠቅሞ በኑሮህ እንዳትቃና በየቀኑ የገብር እንዳ እየጫነብህ በሀይል ሊገዛህ የሚያደርገውን ጥረት አሁንም አላቆመም። ከዚሀም አልፎ በተያዩ ቦታዎችና የህዝባችን የህብረት መታያ ሊሆኑ በሚችሉ ቦታዎች ሁሉ አንዱን በአንዱ ሲም ሲያፈናቅል ሲያሳሳድድ ሲያገጭ መቆየቱ ይታወቃል። ከሰሞኑ አንኳን በወለጋ ንፁሃንን ኦሮሞዎችን በራሱ ታጣቂዎች ማስጨፍጨፉና ፋኖ አደረገው ማለቱ የአደባባይ ሀቅ ነው። አፋብኃ እነዚህን አይነት የአገዛዙ የውንብድና የጭካኔ መሌኮች የሚጠፉት በትብብር በሚደረግ ቴግል፣ አብሮነትን ለማፅናት በሚከፈል መስዋእትነት እንዲሁሜ በጋራ በሚገነባ ፍትሃዊ ስርዓት መሆኑን ያምናል። ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ሀይሎች ፣ የፖለቲካ ቡድኖችና ማህበራት በሙሉ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ እና የደረሰበትን አስከፊ በደል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመመለስና ለመካስ ብሎም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለማፅናትና ዘረ ፈጅና ግፋዊ አገዛዝን ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል በንግግርና በትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እናሳውቃለን። በተለይም በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ
📌ከህሊና እስረኞች የተላከ መልዕክት!
የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ይህንን ማስታወሻ የሰደድንልህ እንደ አባቶቻችን ወግና ልማድ እንኳን አደረሰህ ልንልህ አይደለም። አዲሱ ዓመት እንደ ባለፉት አመታት አገራችን በማያበራ ጦርነት ውስጥ ተነክራ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የማይቻልበት ልጅ ወልዶ ማሳደግ፣ ዘርቶ መቃም ፈፅሞ የማይቻልበት ሆናለች።
ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከጎረቤት አገራት ተነጥላ እና ተንቃ የቅልውጥ ፖለቲካ በማካሄድ መንግስት የምትመራ ሆናለች።
ሕዝባችን እጅግ አሰቃቂ በሆነ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዬ የአንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ደመወዝ አንድ ዳውላ ጤፍ የማይሸምትባት የጉድ አገር ሆናለች። ቤቴ ንብረቴ፣ ካርታዬ ይዞታዬ የማይባልባት በኮሪደር ልማት ስም ከህግ ውጭ በቀላጤ ትዕዛዝ ሙሉ መንደሮች በዶዘር ተጠርገው የሚነሱባት አገር ተደርጋለች።
ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀሳቅሶ መስራት የማይቻልባት የንግድ ስራ እንደ ወንጀል የሚቆጠርባት ስልጣን የያዘው ቡድን ገንዘብ እያተመ የሕዝቡን ጥሪት የሚዘርፍባት፣ የውጭ ኃይሎች በቀጥታ እጃቸውን አስገብተው አድራጊ ጀጣሪ፣ ሿሚ ሻሪ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። በሌላ በኩል " እነ" ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ በሚሊዮን ሚቆጠር ገንዘብ ለአንድ ምሳ የሚከፈልበት፣ እንደ ለሆሊውድ ተዋንያንያን ቅንጡ ሕይዎት የሚመሩበት፣ ሰውነታቸውን በፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና የሚያስውቡበት ነው። አዲሱ ዘመን።
ውዱ የአማራ ሕዝብ ሆይ:- ልጆቻችን የመማር የማደግ መብታቸውን መንግስት ነኝ በሚል አካል የተነጠቁበት፣ በሕዝብ ግብር የሚተዳደሩት የሕዝብ ተቋማት ገንዘብ ላለው ብቻ ትምህርትን ለመሸቀጥ የተስፋፉበት ነው አዲስ ዓመት።
አሁንም 4.9 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝባችን ተፈናቅሎ በካምፕ ውስጥ ይኖራል። አሁንም የዘር ፍጅት የተፈፀመበት የወገናችን ደም የፍትህ ያለህ እያለ እያለ ከመቃብር በላይ ይጣራል።
ዛሬም በአገራችን ተስፋ የቆረጡ ወጣቶቻችን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩት ድንበር አቋርጠው በመሰደድ ላይ ናቸው። አንዳንዶቹ የበርሀ ሲሳይ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የባህር አሳ እራት ሆነዋል።
የሕግ በላይነት የሚባለው መርህ ሙሉ በሙሉ ወድቆ ፣ አቃቢ ሕግ፣ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤት፣ የአንድ ድርጅት አባላት እና የአንድ ብሔር ሰዎች በመሆናቸው በእየለቱ ሰዎችን ያፍናሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ያፍናእንገልፃለን፣ ይሰውራሉ።ሕግን እንደ ማጥቂያ መሳሪያ በመጠቀም ንፁሀንን በማጎሪያ አስረው ያሰቃያሉ።
የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ያልተቋረጠ፣ የመንግስት ታሪክ ካላቸው ጥቂት ሕዝቦች መካከል አንዱ የሆነ፣ በተፃፈ ህግ ሲተዳደር የኖረ፣ የራሱ ፊደል እና የዳበረ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ያለው እና የራሱን ታሪክ በራሱ ፊደል እና ቋንቋ ፅፎ ያኖረ ሕዝብ ነው።
የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዘመናት ነፃነቱን በደም እና በአጥንት ያስከበረ፣ ለዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምሳሌ የሆነ፣ መዓዛው እንደ መልካም ሽቶ፣ ዓለምን ያወደ፣ የገናና ስም ባለቤት ነው። እንድሁም የአማራ ሕዝብ ፈሪሐ እግዚአብሄር ያለው፣ የመልካም አኗኗር መርሆችን፣ ገንዘቡ ያደረገ፣ ለጠላት ሳይቀር የሚራራ ሕዝብ ነው።
የአማራ ሕዝብ በርእስቱ የማይደራደር፣ ንብረቱን የማያስነካ፣ የሌላውንም የማይነካ ነው። ራሱን በመቻል እንዲሁም ለሌሎች በመትረፍ መርህ የሚመራ ነው። ከሁሉ በላይ የአማራ ህዝብ ለህግ የበላይነት መከበር ቁርጠኝነት ያለው፣ መንግስትን አክብሮ የሚያስከብር ሲሆን፣ ሕግ የማያውቁት ጨካካኝና ዘራፊ ስልጣን ሲይዝ ደግሞ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ዱር ቤቴ የሚልም ነው።
እንደ ሕዝብ የአማራ ሕዝብ ጠላታችን ነው እናጥፋው ያሉ ጠላቶቻችን ተባብረው ተሰልፈዋል። የፖለቲካ ስልጣን ተቆጣጠረው ሕገ ከመንግስት ጀምሮ ፀረ አማራ ሕጎችን ፣ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን በስራ ላይ አውለዋል።
ለዓመታት የዘለቀ የጥላቻ ዘመቻ በአማራ ሕዝብ ላይ አካሂደዋል፣ በዚህም በአማራ ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገ ትውልድ አፍርተዋል።
ከዚህ ዘመቻ በኋላ የአማራን ሕዝብ ንብረት መዝረፍ እና ማውደም። እስር እና ስቃይ ቀጥሎ የአማራ ሕዝብ በሚሊዮኖች ተፈናቅሏል። የዘር ፍጅት ተፈፅሞበታል። አሁንም በኮሪደር ልማት ስም ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ሃምሳ አምስት ከተሞች የማፈናቀሉ ስራ ቀን ከሌት እየተሰራ ነው።
የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች የሆኑት እነዚህ ሐይሎች የአማራን ሕዝብ ለማጥቃት ቀን ከሌት በመትጋት ይሰራሉ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ድልብ ሀብት ጠቅልለን፣ የአማራን ሕዝብ በማፈናቀል ፣ ጠራርጎ በማስወጣት እና በመፍጀት የራሳችንን አዲስ አገር እንመሰርታለን ላሉ ተስፈኞች ቦታ ቦታ ለመልቀቅ ሲባል የአማራን ህዝብ ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲፈጅ ተፈርዶበታል።
መላው የአማራ ሕዝብ ታጋዮች ለትግሉ በፅናት እና በታማኝነት በመቆማችሁ በዚህ ዘመን ሊደረግ ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ደረጃ የማንነት ድምሰሳ እና የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት፣ ላለው ሕዝባችን የሕይዎት መስዋትነት በመክፈላችሁ እንድሁም የአንድነት ብስራት እያሰማችሁን በመሆኑ በርቱ ቀጥሉ እንላለን።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ለማስቆም የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአፅዕኖት እንጠይቃለን።
እኛ በቂሊንጦ እስር ቤት የምንገኝ ብዙሃን የአማራ የፖለቲካ እስረኞች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ እንገኛለን። በተለይ ኮሽ ባለ እና አገዛዙ በደነገጠ ቁጥር ከሰብዓዊነት ውጭ በሆነ ደረጃ ተደራራቢ የሆነ ግፍና በደል ይደርስብናል። የአገዛዙ የቁጣው ሁሉ ማረፊያ እኛ እስር ቤት ውስጥ ያለነውን እስረኞች ቢያደርግም ከተነሳንበት ዓላማ አንፃር የሚደርስብን ሁሉ በፀጋ እንቀበላለን።
በዚህ የሕዝባችን መከራና ስቃይ ባላባራበት እንደውም ተጠናክሮ የቀጠለበትን 2018 ዓ/ም የአዲስ ዓመት መባቻ " ገና ያልጠባው አዲስ ዓመት" ብለን ሰይመነዋል።
ይህን የአዲስ ዓመት ጨለማ እለትም በመከራ እና በስቃይ ውስጥ ያለውን ሕዝባችንን በማሰብ፣ በእኛ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም እና በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ጥቃት ለመቃዎም ስንል የርሀብ አድማ አድርገን ለማሳለፍ መወሰናችንን ለሕዝባችን እንገልፃለን።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን።።
~ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ድል ተቀዳጅቷል!
በዛሬው እለት ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም የአፋብኃ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክ/ጦር በረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ በየቀጋት ቀበሌ መሽጎ በሚገኘው የጠላት ካምፕ ላይ ከባድ ጥቃት ፈጽሟል። ስም አጠራራቸው የጠላትን መቅኒ የሚያፈሰው የበረሀው ፈርጦች ቀስተኞቹ የቀስተ ደመና አናብስቶች ሌሊቱን ተስበው ከጠላት ምሽግ በመገኘት ከምሽጉ የተወሸቀውን የሙታን ስብስብ በጨበጣ ተኩስና በቦምብ ሲያርመጠምጡት አርፍደዋል።
በዚህ መብረቃዊ ጥቃትም
~ ብዛት ያለው የጠላት ሃይል የተደመሰሰ ሲሆን ጠላት ሬሳውን ከየጢሻው ሲለቅም አርፍዷል።
~ ሁለት አምቡላንስና አንድ ፓትሮል የጠላት ቁስለኛ መነሳት ችሏል።
~ አንድ የጠላት ወታደር ከነ ጥቁር ክላሹ ተማርኳል።
ድል ለፋኖ
ድል ለሕዝባችን
ክብር በክብር ለተሰውት ሰማዕታት
ጳጉሜን 5/13/2017 ዓ.ም
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ሕ/ግንኙነት
የህዳሴ ምርቃት ስንስርዓት የዲፕሎማሲያዊ ኩስምና ማሳያ
የህዳሴው ግድብ መዓት ጋሬጣዎችን ተራምዶ ለምረቃ መድረሱ ትልቅ ሀገርዊ ስኬት ነው። የምረቃው ስነ- ስረዓት ግን ሀገራችን የደረሰችበትን ዲፕሎማሲያዊ መገለል ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ክስተት መሆኑን ሳናመነታ መቀበል አለብን። በስነስረዓቱ የብዙ ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ አብይ በድፍረት እና በኩራት ለብልጽግና ደሴት ነዋሪዎች ሲናገር ነበር። ይህን ተስፋ ለማሳካትም ከመቶ በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ፣ ኤሲያ፣ ላቲን አሜሪካ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እና ሩሲያ፣ እንዲሁም እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የIMF፣ የWorld Bank አመራሮች ተጋብዘው ነበር። በኤምባሲዎቻቸው በኩል ከተላከው የግብዣ ደብዳቤ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ የደህንነት ሹሙ፣ ኢታማጆር ሹሙ ወ.ዘ.ተ ስልክ በመደወል ተማፅነውም ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አውሮፓ በአካል በመጓዝ የፈረንሳይን፣ ኢንግሊዚን፣ ጣሊያን፣ ጀርመንን መሪዎች በድግሱ እንዲሳተፉ ለማሳመን ሞክረው ነበር። የደህነነት ሹሙ በቀርብ ዋሺንግተን ዲሲ በመሄድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩን ካልተቻለም የበታች ሹም እንኳን እንዲልኩ ጠይቀው ነበር። ከዚህ ሁሉ የኑልን ውትወታ በኋላ የተገኙት አምስት መሪዎች ብቻ ናቸው፤ የኬኒያ፣ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ባርቤዶስ። የአለም አየር ፀባይ ስብሰባን ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የኬኒያው ፕሬዘደንት ዊሊያም ሩቶ የህዳሴ ግድብ ምርቃት ዋና እንግዳ (chief guest) ሆነዋል። ለዚህ ቦታ ታጭተው የነበሩት ግን የተባበሩት መንግስታቱ ጉተሬዝ፣ የቻይናው ሺ፣ የሩሲያ ፑቲን ወይም የፈረንሳዩ ማክሮን ነበሩ። አልተሳካም። የዛሬ ሁለት አመት በናይሮቢ የተካሄደውን የአየር ጸባይ ስብሰባ ተከፍለው የነበሩት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ፣ ሰበባሰብ ፈልገው ከአዲስ አበበው ቀርተዋል።
ለመንኛውም እህን ዲፕሎማሲያዊ መግለል ለምወጣት ጠንክረን ካልሰራን የባሰ ውርደት ይጠብቀናል። ለዚህ ደግም ዲፕሎማሲያዊ ውድቀቱ ዋና ምክንያት ሀገሪቷ በእርስበርስ ጦርነት እና ኢክኖሚያዊ መድቀቅ ምክንያት፣ በአህጉራችንም ሆነ በአለም የነበራት ቁመና መመናመኑ ስለሆነ፣ ጦርነቶችን አስቁመን ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ ተግተን መስራት አለብን። ይህ ደግም አብይ አህመድ በስልጣን እስካለ የሚታለም አይደለም። አብይ ከተወገደ በኋላ እንኳ እሱ የፈጸውማቸውን ዘርፈብዙ ዲፕሎማሲያዊ ስህተቶች እና ጥፋቶች አርመን ሀገራችን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ብዙ ጊዜና ድካም ይጠይቃል።
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሁለተናዊ አማራዊ አንድነት የሚፈለግበት ዘመን ላይ ነን። በዲያስፖራው ፣በሚዲያው ፣መሬትላይ ባለው ታጋይ አንድነት የግድ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይነን።
ለብዙ ጊዜ ያላሳካናውን እውነተኛ አማራዊ ተቋም በእኛ ትውልድ እውን መሆን አለበት። ለዚህ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካል በጥልቀት ማሰብ ማሰላሰል ይጠበቅበታል።
የአማራ ህዝብ እንደ አንበሳ ደፋር፣ እንደ ንስር አጉልቶና አርቆ የሚያይ ፣እንደ ንብ ታታሪ ሕዝብ ነው። ይህን ሕዝብ የሚመጥን አንድ አማራዊ ተቋም ማዋለድ ቀጣዩን ብዙ አመታት የሚፈጀውን የአማራን ትውልድ እጣ ፈንታ መወሰን ነው። ይህን የሚያሻግር ታትሮ የሚሰራ ፣አለምን የተረዳ ባለ ራዕይ መሆንና ከጊዜአዊ ፍላጎት ወጣ ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው።
አሮጌውን አመት ብዙ ጀግንነት እና ብዙ መሰናክል ያለፍንበት ፣ብዙ ተፈትነን ብዙ የተማርንበት አመት ነበር ። አሮጌ አስተሳሰብ ፣ጎጥ እና ኢጎ ለአዲዙ መጪ ዘመን የሚመጠኑ ሀሳቦች አይደሉም። የሕዝባችንን መከራ ለመቋጨት በአባቶቻችን የጥበብ እና የወኔ መንገድ ተጉዘን አያደርጉትም የተባልነውን አድርገን ማሳየት ትንሹ ግዴታችን ነው።
አዲሱ ዓመት የልዕልና ፣የአንድነት ፣የአሸናፊነት ፣ የጠራ ራዕይ እና የጠራ የፖለቲካ አመለካከት ይዘን የምንነሳበት ዘመን ነው። አሁን ያለንበት የወታደራዊ አቅም ፣ ዝግጁነት ፣ሞራል እና የሕዝብ ድጋፍ ከምንፈልገው ጫፍ ለመድረስ ከበቂ በላይ ነው።
አዲሱ አመት ትግሉን የምንቋጭበት ዓመት ነው።
መልካም አዲስ ዓመት!
ትዕግሥት ፣ፅናት ፣ እምነት ፣እውነት።
ፅና!
ጳጉሜን 05/2017ዓ.ም
©አርበኛ እስቲበል ዓለሙ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ም/ል ቃል አቀባይ
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የአዲስ አመት ዋዜማን ዘራፊዎችን እና የብልፅግናን ጥምር ሀይል በማስወገድ አዲስ አመትን በድል ተቀበለ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ 5 ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ከአምባጊዮርጊስ እስከ ዳባት ከተማ ድረስ ህብረተሰቡን ሲዘርፋና ሲያግቱ በነበሩ ወሮበሎች ርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል።ከራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ጋር በመጣመር እየተወሰደ ባለው ስርዓት የማስያዝ ዘመቻ ቀጠናው ከወዲሁ እፎይታ እ ያገኘ ሲሆን ይሄን ተግባር ለማደናቀፍ ዓላማ በማድረግ አገዛዙ ሰራዊት አሰማርቶ ለዘራፊዎች ሽፋን ለመስጠት የሞከረ ቢሆንም የበላይ ዘለቀ ዕዝ አሃዶች ከባድ ምት ደርሶበታል።
ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም ከወርቅ ደቦ እስከ ገደብየ ከተማ ለዘራፊዎች ሽፋን ሊሰጥ የመጣው የዘራፊው አገዛዝ ጥምር ሀይል በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል በሆኑት ቴዎድሮስ እና አጥናፋ ብርጌድ አባላት እና መንገድ በመዝጋት የአገዛዙ ሀይል ለድጋፍ እንዳይደርስ ያደረገችውን ይታየው ብርጌድ አባላትን ጨምሮ በማስተባበር ጀኔራል ተዘራ ንጉሴ እና የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርዬ አድማሴ እንዲሁም የብርጌድ አመራሮች በአካል በመሩት ኦፕሬሽን ጠላት ላይ ከፍተኛ ድምሰሳ ተደርጓል ።
በቀጠናው ዛሬ የአገዛዙ ሀይል እንደ ልማዱ በውርደትና በሽንፈት ካባ የተመለሰ ሲሆን አዲስ አመትን በሞትና በመርዶ ተቀብሏል።
ከወርቅ ደሞ እስከ ገደብየ ከተሞች በነበረው አውደ ውጊያ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ነውና ዘራፊዎችን ለማዳንና ለሽፋን ፎክሮ የመጣው የአገዛዙ ሀይል ይዟቸው የነበሩ ሁለት ምሽጎችን ለቆ ሙትና ቁስለኛውን እያንጠባጠበ እየፈረጠጠ ወደ አምባጊወርጊስ ከተማ በሀዘንና በእለቅሶ ተመልሷል ።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ከመንግስት ጎን የሚሰለፋ ሀይሎችንና ሌቦችን ማጽዳቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጠናው ያሉ ህብረተሰቡን ቀለበት ፣ ስልክ ፣ብር እና የተለያዩ ሀብቶችን እንዲሁም እገታ ጭምር ሲፈፅሙ የነበሩ ቀማኞች እና አጭበርባሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተወግደው ቀጠናው ፍፁም ሰላማዊ ይደረጋል ሲሉ የክፍለ ጦሩ ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ወርቁ ዘገየ አክለው ገልፀዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🌼🌼ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት🌼🌼
የተከበራችሁ የሁሉም ክፍለጦር አመራሮች፣ የተከበራችሁ የ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የ፯ቱ ብርጌድ አመራሮች፣ አባሎቻችን እንዲሁም ሰፊው የአማራ ሕዝብ፦
በቅድሚያ እንኳን ለ፳፻፲፰ ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በአዲሱ ዓመት የአማራ ሕዝብ አሁን ከአለበት የጀግንነት፣የአሸናፊነት፣የድል አድራጊነት ግስጋሴ ከፍ ብሎ እንደ ንስር የመብረር ዓመት እንዲሆንልን እየተመኘን ማህበረሰባችን ለሚያደርግልን እና እያደረገልን ላለዉ ሁለተናዊ ድጋፍ ከልብ እያመሰገን ለትግላችን ቀጣይነት ድል አድራጊነት ከነበረው የበለጠ ተግተን የትግል ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ሁነት ውስጥ እንገናኝ።
አዲሱ ዓመት የፋኖ የድል ግስጋሴ የሚያንሰራራበት፣ የአማራ ህዝብ ነፃነት እንደ አደይ አበባ የሚፈካበት፣ የአረመኔው አገዛዝ ስርዓት የሚያከትምበት፣ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚበሰርበት ዘመን እንደሚሆን አንጠራጠርም‼️
በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ‼️
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር
አዲስ ትዉልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!!