uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 389
Obunachilar
-324 soatlar
+2587 kun
+1 43630 kun
Postlar arxiv
የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመጀመሪያ ግምገማ እና ቀጠይ የስራ አቅጣጫ ተሠጥቷል:: አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ በኮር እና ክ/ጦር መልሶ አደረጃጀት ደጋ ዳሞት ደምበጫ እና ማቻከል ወረዳ በ 109ነኛ ኮር 99ነኛ ክ/ጦር ሆኖ መዋቀሩ ይታወቃል:: በዚህ አደረጃጀት ከሲቢል እስተዳዳር እስከ ወታደራዊ አስተዳደር ሠራዎች የተሰሩ ሲሆን ዛሬ ቀን 17.03.2018 ዓ.ም  የመጀመሪያ ግምገማ በማድርግ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሠጥቷል። አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዋድሮስ እዝ ፋይናንስ ኃለፊ ስሜነህ ሙላቱ ይህ የኮር እና የክ/ጦር አደረጃጀት ከመጣንበተ የሁለት አመት የትግል ጉዞ ሁለት እና ሶስት እርምጃዎች መራመዳችንን አስታውሰው'' እስካሁን የነበረን መተቻቸት ፣ መጓተት እና የተሳሳተ አስተያየታችንን በማስወገድ የፋይናንስ እና የሎጀስቲክ አያያዝ እና አሠባሠብ ወደፊት በሚኖርን ስራ አዘምነን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። አያይዘውም የቅዱስነት ካባ ተላብሠው በውስጣችን የተሠገሠጉ ሊኖሩ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል:: አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አስተዳዳር ፶/ አለቃ ታደሰ ልንገሬ ክፍለ ጦሩ ከሁሉም ተዋጊ በስነ ልቦና  የታጠቀ ፣ በሀብት ፣ በማህበረሰብ ድጋፍ እና ጦሩ  ግዳጁን በላቀ ብቃት የሚወጣ መሆኑን አንስተው የድርጅቱን መምሪያ በመቀበል ለወደፊት በሚደርጉ ግዳጆች ህዝብ የጣለብንን አደራ ከዚህ በፊት ከነበረ ግዳጅ የበለጠ ጠላትን መመከት እና መደምሠስ ይገባል ብለዋል። አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዋድሮስ ዕዝ የዘጠና ዘጠነኛ ኮር ም/ሰብሳቢ አርበኛ ክንፈ መላክ በበኩላቸው የተሸከምነው አደራ በማሠብ በቅንነት ፣ በታታሪነት እና ብልህነትን በመላበስ የተጣለብንን ሀላፊነት ለመምራት የተሠጠንን  ጦር ከማህበረሠቡ ጋር አጣምረን በሁለቱም በኩል ክፍተት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን በቅርበት በመከታተል ችግሮችን እየፈታን ልንመራ እንደሚገባ ተናግረዋል። ድል ለፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ ድል በተገፉ ኢትዮጵያውያን!!! አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ነኛ ኮር 99 ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ

#ነገረ_እጅና_ጀሮ_ቆረጣ‼️ አምባገነን መንግስት እጅግ ፈሪና ጨካኝ ነው። ፈሪ ከመሆኑ የተነሳም የአገኘውን ሁሉ ወንበሬን ከመነጠቅ ያድንልኛል ብሎ ያሰበውን ሁሉ ያለምንም እርህራሄ ይፈፅማል። እጅ ቆረጣውም ፋኖን ከህዝብ እነጥላለሁ፣ በሀገርም ከሀገር ውጭም በአሸባሪነት አስፈርጃለሁ በማለት ድርጊቱን ደራሲ፣ ዳይሬክተር ፣ተዋናይ በመሆን እጅግ አሰቃቂ ተግባር ፈፅመዋል‼️ ይህ ተግባር በፋኖ እንደተፈፀመ በአዲስ መልኩ ስለመጡ ንስር አማራም ይህ አሰቃቂ ተግባር የአገዛዙ እንደሆነ ነጥብ በነጥብ ለማሳዬት ትሞክራለች። 1ኛ.እጅና ጀሮ ሲቆርጥ የሚታየው ጭራቅ በቀን ህዳር 3/2018 ዓ.ም (November 12/2025) የሰላም አማራጭን በመቀበል ወደ ብልፅግና እንደገቡ የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ፣የወረኢሉ ወረዳ ኮምኒኬሽንና የብልፅግና ልሳኖች ዘግበዋል። 2. ከ12 ቀን በኋላ (ህዳር 15/2018 ዓ.ም)  እጅ ሰጠ የተባለው ግለሰብ አሰቃቂ ተግባር ሲፈፅም የሚያሳይ ቪዲዮ እንዲሁም ይህንን ተግባር የፈፀመው ሰው #በሰበር_ዜና #ቀጨም ተደርጓል ሲሉ ዘግበዋል። 3ኛ. አሰቃቂ ድርጊት የተፈፀመበት ግለሰብ ከህክምና ተቋም ገብቶ በአገዛዙ ቃለ መጠየቅ እየተደረገለት በትናትናው ዕለት ቪዲዮ ተለቋል። አሁን ነገሮችን እንገጣጥም፣    👉ህዳር 3 እጅ የሰጠ ሰው ስልኩ ሲፈተሽ እጅ ከመስጠቱ በፊት ያን ድርጊት እየፈፀመ ቪዲዮ ቀርፆ ስለነበረ ቪዲዮው ተገኘ ብንል 1ኛ. ብልፅግና ትክክለኛ ፋኖን የሚያጠለሽ ነገር አግኝቶ 13 ቀን አይታገስም ወዲያውኑ ይለቀው ነበረ! 2ኛ. ድርጊቱ የቆየ ከሆነ ተበዳዩ #ቁስሉ_ደርቆ (ከሆስፒታል ወጦ) ነበረ አገዛዙ አግኝቶ ቃለ መጠየቅ ሊያደርግለት የሚችለው! 3ኛ. ልጁ እጅ ከመስጠቱ በፊት እጁና ጆሮውን ተቆረጠ ቢባል እንኳን ልጁ እጁ ሲቆረጥ ለብሶት የነበረውን #ቲሸርትና_ሱሪ ትናነት ከሆስፒታል ሆኖ ቃለመጠየቅ ሲሰጥ ያች ልብስ ለብሶ አይገኝም ነበረ ። ነውስ ልብሶቹ ቆዳ ናቸው አይቀየሩም🤔 ለማንኛውም እንኳን ታማሚ ሆነሆ (በጤናም ) ይህንን ያህል ጊዜ አይለበስም!! 4ኛ. ድርጊቱ የቆየ ነው የሆስፒታል ቃለ ምልልሱም ቆይቶ የተቀረፀ ነው ቢባል አገዛዙ ለፕሮፓጋንዳ ሲል ሲቆረጥ የሚያሳይ ቪዲዮ ባይኖረውም የተጎጂውን ምስክርነት ብቻ እንደሚያወጣው 100% እርግጥ ነው። #ማጠቃለያ ይህ ድርጊት ድርጊት የቀረፃ ሂደቱን ጠብቆ የወጣ ( ልጁ ተያዘ - አጅና ጀሮ እንዲቆርጥ ተደርጎ ተቀረፀ - የተቆረጠውን ልጅ ደግሞ ህክምና አስገብተው አመጡ) ይህ ማለት ደግሞ 100% ልጁን ከያዙት በኋላ (ከህዳር 3-15 2018 ዓ.ም) ባለው  የተሰራ አሰቃቂ ድራማ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለሆነም ከአማራ ህዝብ የወጣው የነፃነት ታጋይ ፋኖ ይህንን አንዳላደረገ ፣ አገዛዙ ደግሞ ለእርካሽ ፖለቲካ ሲል የሚፈፅመውን አሰቃቂ ተግባር ነጥብ በነጥብ ለማሳዬት ሞክረናል። የእናተን እይታም አስቀምጡ‼️በተረፈ ገለልተኛ ቡድን ማጣራት ይችላል! #መዝገቡ_ተዘግቷል_መዝገብ_ቤት_ይመለስ🔨 17/ዐ3/2018 ዓ.ም

ሀያሉ አማራ ላይመለስ ተነስቷል ወራሪው ብልፅግና የመጨረሻህ ምርጫህ እንደ አባቶችህ እጅ መስጠት ነው እጅ ስጥ ።
+2
ሀያሉ አማራ ላይመለስ ተነስቷል ወራሪው ብልፅግና የመጨረሻህ ምርጫህ እንደ አባቶችህ እጅ መስጠት ነው እጅ ስጥ ።

ውይይት ተካሄደ ... አፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ በቀን 17/03/2018 ዓ/ም በ፻፱ኛኮር ውስጥ የሚገኘው ፺፱ኛ ክፍለጦር የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ባሉበ
+1
ውይይት ተካሄደ ... አፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ በቀን 17/03/2018 ዓ/ም በ፻፱ኛኮር ውስጥ የሚገኘው ፺፱ኛ ክፍለጦር የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ያለፈ የስራ ግምገማ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫን በተመለከተ ውይይት አካሄደ። መረጃውን ያደረሰን ኢንጅነር ዲያቆን ደጀኑ ✍️ ደጋ ዳሞት በሰዓቱ 🤌 Dega Damot Timely

#Kur Kur ከተባለ ደቡብ ሱዳናዊ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ የተላከ ደብዳቤ !! 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 ግልፅ ደብዳቤ ለክቡር አርበኛ ዘመነ ካሴ _____ ርዕሰ ጉዳይ፦ ስለ ፋኖ አንድነት ያሳሰበው የደቡብ ሱዳን ዜጋ ለፋኖ አንድነት የተማፅኖ መልዕክት ፅፏል። ክቡርነትዎ እንደ ደቡብ ሱዳን ተቆርቋሪ ዜጋ በጥልቅ አክብሮት እና በአገር ወዳድነት ይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ለህዝበ አማራዊ ፍቅር እና በናንተ አመራር የአማራ ህዝብ አሁንም ሰላሙን፣ ደህንነቱን እና ፍትህን የማስፈን እድል እንዳለው በማመን ነው። ክቡርነትዎ ህዝባችን በአንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ ወሳኝ ተግዳሮቶች እያጋጠሙት ነው፤ በፋኖ ውስጥ ያለው ማህበራዊ አንድነት እና የስምምነት ተደራሽነት ውስን ነው። መሬት ላይ ያለው እውነታ ብዙ መከናወን እንዳለበት ይነግረናል፤ እናም ጊዜ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።‼️ ከዚህ ላይ በሚከተሉት ቀጣይ እና ለወቅታዊ እርምጃዎ አክብሮት ይገባል እላለሁ። የአማራን ህዝብ የወደፊት ዓላማ ማጠናከር፣ የፋኖ ሰላም ማረጋገጥ ትልቅ ጉዳይ ነው። በማህበረሰብ ደረጃ አንድነት ማምጣት ያስፈልጋል።‼️ ተራ ዜጎች ማለትም የትግሉ ደጋፊ ማህበረሰብ መንግስት/መሪ እንዳላቸው እንዲሰማቸው፣ በተለይ በትግል ሜዳ ማኅበራዊ አንድነትን ማሳደግ አስፈላጊ ነው። አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ ጎሰኝነትን፣ ወገንተኝነትንና የፖለቲካ መለያየትን ተስፋ ማስቆረጥ፤ እንዲሁም ሁሉም የአማራ ሕዝብ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ሥር እንደ አንድ ሕዝብ እንዲታይ ማበረታታት ይኖርበወታል።‼️ ክቡርነትዎ ታሪክ እንደ ነፃ አውጪ/አራማጅ መሪ አድርጎ አክብሮዎታል። የእኔ ትሁት ጥያቄ፣ ከሚሊዮኖች መካከል እንደ አንድ ዜጋ፣ ወደ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልጽግና ወደ አዲስ ምዕራፍ ይምሩን ነው።‼️ 👉ፋኖ የተባለውን ኃይል እየመራህ ስትቀጥል እግዚአብሔር ጥበብ እና ብርታት እንዲሰጥህ እመኛለሁ። ከአክብሮት ጋር የደቡብ ሱዳን ተቆርቋሪ ዜጋ። @Kur Kur Kur Deng 11/24/2028

‎የ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት በይፋ ስራ ጀመረ ‎የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝና 105ኛ ኮር ከ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ። ‎በ66ኛ ክ/ጦር የጃዊ ወረዳ፤ ፓዊ
‎የ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት በይፋ ስራ ጀመረ ‎የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝና 105ኛ ኮር ከ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ። ‎በ66ኛ ክ/ጦር የጃዊ ወረዳ፤ ፓዊ ወረዳና ዳንጉር ወረዳ ግዜያዊ መንግስት አመራሮች የእርስ በርዕስ ትውውቅ፤ ተግባርና ኃላፊነትና በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በኮርና ድርጅት አመራር አማካኝነት ተደርጓል። በውይይቱም ከ3ቱ ወረዳዎች ማለትም ከመተከል ዞን ፓዊና ዳንጉር እንዲሁም ጃዊ ወረዳ የብልጽግናው ወረዳ የተቋጣጠረውን የቀበሌ መዋቅር ሙሉ በሙሉ መፈራረሱ ይታወቃል። በምትኩም የፋኖ ነጻ ወረዳ በማስፋት ግዜያዊ መንግስት መዋቅር ከዋና አስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ሸንጎ መዋቀሩ ሠፊው ማህበረሰባችን በደስታ ማዕበል ይገኛል በማለት የወረዳ አመራሮቹ አስተያየቶቻቸውን ገልጸዋል። ‎ #መተከል_ብረሳሽ_ቀኘ_ትርሳኝ! Demelash Andnew ‎

ጄኔራሉን ፍለጋ? ወይስ ጉብኝት? ይችን ዜና እንዴት አያችኋት? ጉብኝት የሚያደርጉ ይመስላሉ? ወይስ የጠፋ ነገር እየፈለጉ? መከላከያ፣አድማ፣ ብተና፣ ፖሊስ፣ ጥምር ጦር... ይሄ ሁሉ አንድ ፋኖን ለመ
ጄኔራሉን ፍለጋ? ወይስ ጉብኝት? ይችን ዜና እንዴት አያችኋት? ጉብኝት የሚያደርጉ ይመስላሉ? ወይስ የጠፋ ነገር እየፈለጉ? መከላከያ፣አድማ፣ ብተና፣ ፖሊስ፣ ጥምር ጦር... ይሄ ሁሉ አንድ ፋኖን ለመግጠም ነው? ለማንኛውም ዙ 23 እና ወታደሮቹን አስከትሎ የጠፋውን ጄኔራል ፍለጋ በሚል ከትናንት ጀምሮ በዚሁ ዜናው ላይ በተጠቀሰው አካባቢ የተደረገው የአሰሳ ዘመቻ ውጤት ሳይገኝበት ቀርቷል። አሰሳው አልሳካ ሲል "ጉብኝት" ይላሉ እንዴ? ምኑን ነው የሚጎበኙት?!

"ከዚህ በኋላ "ቅዝናም አማራ" እየተባልን አንቀጥልም! ቀጣይ ምን አልባትም ከመካከላችን አንዳችንን ልታጡ ትችላላችሁ። ከመጋፈጥ ወደ ኋላ አንልም!... ይሄ ሰውዬ ይብቃን! " የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው~ ሕዳር 16/2018 ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ልደታ ም/ችሎት ከተናገሩት የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ሕዳር 16/2018 በፌደራል ከፍተኛ ቤት ልደታ ም/ችሎት ተከሳሾች በቀረቡበት ወቅት የቂሊንጦ ማ/ቤትን እና የግቢው ጥበቃ እና ደህንነት ኃላፊ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታን በተመለከተ ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል:- ✍️ ክቡር ዳኞች ልታዳምጡን ይገባል። መስማት ካልቻላችሁ ግን ከዚህ በኋላ በሕይወታችን ጉዳይ ኃላፊነት የምትወስዱ እናንተ ናችሁ! ✍️ ዳኛው ከቤቱታችሁን በጽሁፍ አቅርቡልን ሲሉ የሰጡት ምላሽ ~ "ትንሿን ይህችን ሰሙን ፤ ይህን እናንተ ሌላውን መንግስት እንደሚያደርገው እናውቃለን። " ✍️ ከዚህ በፊት የተፈቀደው መብታቸው ሳይነካ ተፈጻሚ ይሁን ብላችሁ ትዕዛዝ እና አለፍ ብላችሁም ምክር ጭምር መስጠታችሁ እየታወቀ ነገር ግን እስካሁን አንድም ትዕዛዝ ተፈጻሚ አልሆነም። ✍️ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ "ብትከሱ ምን ታመጣላችሁ ከላይ እስከ ታች ያለነው እኛው ነን" ያሉትን ተግብረውታል። ✍️ ቤተሰብ ጥየቃ የለም ፤ ቤተሰቦቻችን ቢመጡም ምግብ እንደ ውሻ ጥለውልን እንዲመለሱ ነው የሚያደርጉት። ✍️ ግፍና መከራ፣ ወከባ ፣ ስድብና ማስፈራራት በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦቻችን ላይ ጭምር እንደቀጠለ ነው። ✍️ ከዚህ በኋላ "ቅዝናም አማራ" እየተባልን አንቀጥልም! ቀጣይ ምን አልባትም ከመካከላችን አንዳችንን ልታጡ ትችላላችሁ። ከመጋፈጥ ወደ ኋላ አንልም! ✍️ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዳይገባ ከልክለዋል! እኛ ኦርቶዶክሶች ነን ፤ የ40 ቀን ጾም እንጾማለን። ከጤናም አንጻር ቀላል ያለ ምግብ ~ አትክልትና ፍራፍሬ እንጠቀማለን። በሙዝ ውስጥ ሲም ካርድ ተገኘ ይሉናል ፤ እኛ ምን አገባን? ይህ የእኛ ስራ አይደለም! ✍️ ፌደራል ፖሊስ በኢ/ር ድሪባ ላይ የወንጀል ፍሬ ነገሩን እንዲያጣራ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ፤ ፖሊስ ግን እስካሁን አንድም ምርመራ አላደረገም! ✍️ ዐቃቤ ሕግ ይህን እንዴት ያየዋል? የአማራ ሕዝብ የዐቃቤ ሕግ እና የመንግሥት አይደለም ? ✍️ የታጠቁ ሸፍቶች ናቸው እየጠበቁን ያሉት። እንድንገደል እንደተፈረደብን ነው የምንቆጥረው ! ✍️ ከአሁን በኋላ ዳኝነት ካላገኘን ቤተሰቦቻችን እየተሰደቡ ፣ አማራነት እየተዋረደ አንቀጥልም ፤ ከዚህ ሰውዬ  አውጡን! ይሄ ሰውዬ ይብቃን!    (አውሎግሶን አንድነት ፣ ሕዳር 17/2018)

ጥብቅ መልዕክት !! ዛሬ 17/03/2018 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ ደምበጫ ገብርኤል ኮብል ደጋ ዳሞት መዞሪያ እና ሌሎችም የገብያ መግቢያዎች ላይ ከገጠር የሚገባን አርሶ አደር እና ወጣት እያፈሱ ነው
ጥብቅ መልዕክት !! ዛሬ 17/03/2018 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ ደምበጫ ገብርኤል ኮብል ደጋ ዳሞት መዞሪያ እና ሌሎችም የገብያ መግቢያዎች ላይ ከገጠር የሚገባን አርሶ አደር እና ወጣት እያፈሱ ነው ። " ዞረብኝ በል ስትዞር ዋልና " አይነት ድርጊት ነውኮ የገጠመን ጎበዝ በርህ ድረስ ሊበላህ መጦ አማራ ተደራጅ ስንልህ ፌዝና ሳቅ የያዝክ የአማራ ወጣት የአማራ ህልውና ለማስከበር ከተደራጁ የአማራ ፋኖ ወንድሞችህ ጋርየትግል አደረጃጀት ግባና ጠላቶችህን ታገል ስንልህ ቁጭ ብለህ እያየህ አፈሱኝ አትበል ። ተደራጅ ተደራጅ አሁንም ተደራጅ ከተማ ውስጥ ከጠላቶችህ ጋር አትርመስመስ ደምህና የአማራ የዘር ማንነት የማይፈቅደውን ከጠላቶችህ እግር ስር አትርመጥመጥ !

ህዳር 17/2016 ዓ.ም‼️ 🕯🕯🕯ዝክረ ሰማዓታት🕯🕯🕯 እለተ ሰኞ ህዳር 17/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ልክ በዛሬው እለት የአብይ አህመድ አረመኔው ሀይል ከ18 በላይ ዋበር ከተማ
+2
ህዳር 17/2016 ዓ.ም‼️ 🕯🕯🕯ዝክረ ሰማዓታት🕯🕯🕯 እለተ ሰኞ ህዳር 17/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ልክ በዛሬው እለት የአብይ አህመድ አረመኔው ሀይል ከ18 በላይ ዋበር ከተማ ከግለሰብ ቤተ ላይ በተጠቀመው ድሮን የተሰው አመራሮቻችን 2ኛ ዓመት ሙእተ ዓመት በከተማው ወጣቶች እና በጎዶቻቸው ታስበው ውሎሏል። እናተ የተሰዋላቹህለትን አላማቹህን ለማሳካት  ዛሬ ላይ ሽወችን ፍሬ አፍርቷል። 🕯ነፍሳቹህን በአፀደ ገነት ያኑርልን🕯 🕯🕯ትግለ ቅብብሎሽ ነው🕯🕯 ህዳር 17/2018 ዓ.ም

ኅዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ገለልተኛ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ እንዲደረግ ሁሉም የበኩሉን ግፊት እንዲያደርግ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የቀረበ ጥሪ!!! ሰሞኑን የሰው እጅ በመጥረቢያ ሲቆረጥ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ታይቷል። ይህ አይነት ድርጊት በማንም ይፈፀም በየትኛውም ቦታ ይደረግ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ሊፈፀም የማይገባ አሳፋሪ ድርጊት በመሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ድርጊቱን ፈፅሞ ያወግዛል። ይሁን እንጅ መሰል ድርጊቶችን በእጅ አዙር እና በቀጥታ በመፈፀም የሰው አካላትን መበለትን መደበኛ ተግባሩ ያደረገ ሰራዊት በአማራ ክልል ያሰማራው የብልፅግና መዋቅር አፈ-ቀላጤወች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የፋኖ መዋቅርን እየከሰሱ ይገኛሉ። ዓለም አቀፍ የጦር ህግን አክብሮ የማረካቸውን የጠላት ሰራዊት አባላት እንኳን በምንም መመዘኛ ልዩነት ሳያደርግ ፍፁም ሰብአዊነትን በተላበሰ መንገድ የሚታገለውን ሰራዊታችንን በማይገልፅ መንገድ እና መዋቅራችን በማያውቀው ድርጊት መነሻነት በተከፈተው የስም ማጥፋት እና ትግሉን ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ግብረ ገባዊ ግብራችንን ጠንቅቆ የሚያውቀው ህዝባችን እንደማይደናገር  እናምናለን። አገዛዙ በደረሰበት የዲፕሎማሲ ኪሳራ፣ በሰብአዊነት ላይ እየፈፀማቸው ያሉት ወንጀሎች መጋለጥ፣ በተጀማመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት ቅርቃር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ መሰል ነውረኛ ተግባራትን በስውር በማስፈፀም እና በሚዲያ በማስተጋባት ህዝብን ማደናገር የዘወትር ስልቱ መሆኑም ይታወቃል። የፋኖን የህልዉና ትግል ከህዝብ ለመነጠል በደህንነት መ/ቤቱ እና ሌሎች የጥፋት መዋቅሮቹ አረመኔ ነፍሰ-ገዳዮችን በማዘጋጀት በቡድን ሴቶችን መድፈርን ጨምሮ ከሰብአዊነት በወጣ መንገድ በመጥረቢያ የሰውን አካል በመቆራረጥ፤ በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ልጆችን አንገት በስለት በማረድ ይህንንም በመቅረፅ በወገን ሰራዊት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፍታል። ከሰሞኑ በአማራ ክልል እየፈፀማቸው ያሉት ድርጊቶች በቅርቡ በአርሲ እና በመተከል-ቡለን ከተፈጠረው ጅምላ ፍጅት የቀጠለ የአገዛዙ ስልት ነው። ለአብነት በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ንፁሃንን በመረሸን እና ምላሳቸውን በመቁረጥ፤ ግንቦት 9/2016 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በረከት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ አድዬ አክሊለ የተባለች ግለሰብን በቡድን አስገድዶ ከደፈሩ በኋላ ጡቷን እና እጆቿን ቆራርጠው በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል አረመኔነቱን አሳይቷል።  በመሆኑም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አብይ አህመድና ተላላኪዎቹ እየፈፀሙ ያሉትን አሰቃቂ ድርጊት እንዲያወግዙ እና ገለልተኛ መርማሪ ቡድን እንዲቋቋምና ምርመራ እንዲጣራ ግፊት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እያስተላለፋን በእኛ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን።                   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ

‎የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ‼️ ‎በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና በጃዊ ፤ ፓዊ እና ዳንጉር ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራ
+4
‎የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ  የ105ኛ ኮር በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና  ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ‼️ ‎በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና  በጃዊ ፤ ፓዊ እና ዳንጉር ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራሮች የእርስ በርዕስ ትውውቅ፤ ተግባርና ኃላፊነትን በተመለከተ እንዲሁም በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት  የድርጅት አመራርና የ105ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት  ተደርጓል። በተደረገው ውይይትም  ከሶስቱ ወረዳዎች ማለትም ፦ከመተከል ዞን ፓዊና ዳንጉር ወረዳ እና  ጃዊ ወረዳ  ውስጥ በቴዎድሮስ ዕዝ  የተቆጣጠርነውን ሙሉ የቀበሌ መዋቅር ፍትህ የመስጠት፣የማስተዳደር ፤ መሰል ህዝባዊ አገልግሎቶችን እንዲሁም  የተለመደ የዕለት ከዕለት ተግባራትን ፣ህዝባዊ አገልግሎት እና ህዝባችን ከድርጅታችኝ  የሚፈልገውን ሁሉን  አቀፍ ግልጋሎት በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ያስችል ዘንድ  ለጊዚያዊ የወረዳ አመራሮች መመሪያ ተሰጧል፤የስምሪት አቅጣጫ ተቀምጧል ። በዚሁ አጋጣሚ  ከላይ በተጠቀሱት  ወረዳዎች የቀበሌ መዋቅር ሙሉ በሙሉ መፈራረሱ የሚታወቅ ሲሆን  ፥ በምትኩም የፋኖ ነጻ ወረዳ በማስፋት ግዚያዊ መንግስት መዋቅር ከዋና አስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ  የፍርድ ሸንጎ መዋቅር በመዘርጋት ሠፊው የማህበረሰብ ክፍል  በድርጅታችን መምሪያ መሰረት ተገቢውን አገልግሎት እያገኘ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን ።ድርጅታችን ይህንን ተግባርና ሃላፊነቱን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የጀመረውን መዋቅራዊ እንቅስቃሴውን  በቀጣይ ነፃ በሚወጡ ቀጠናዎች  ሁሉ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንን  እንገልጻለን ። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!! Hailemichael Bayeh ‎

ጀግናው ዘራፌዋ ጀግናው ፋኖ በሉ ጀግናው ዘራፌዋ ምነው ዝም አላቹ ሀገር በወንበዴ ወድቃ ተከባቹ ወጡና ከቆላ በሉት ለሀገራቹህ ፋኖ ዘራፌዋ .....አኸኸ ከጀግናው ጆን የአማራ ልጅ የተገኘ ለአማራ ማህበረሰብ የተላለፈ የሙዚቃ ስራ ነው ለሁሉም አማራ እንዲደርስ መልክታችን ነው።

አውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙ ጀርመን እና በአጎራባች የአውሮጳ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ  ውስጥ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ ይፈፀማል ያሉትን ግድያ፣ ግፍና ማፈናቀል ዛሬ በርሊን-ጀርመን ውስጥ ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍ አወገዙ። ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት የተጠራ ሲሆን በተለያዩ የጀርመን ከተሞች፤ እንዲሁም በጀርመን አጎራባች የአውሮጳ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመውን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም። «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚፈጸመው በቃላት ተገልጾ የሚያልቅ አይደለም» ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከተሰላፊዎቹ አንዱ የሆኑት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራችና የኮሎኝ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ፤ «ሰዎች በቋንቋቸው፤ እንደዚሁም በሃይማኖታቸው ተለይተው እየታረዱ፣ እየተጨረሰ ይህን ያህል ግፍ ሲፈጸምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬ ይህን ሰቆቃ ሊያስቆም አልቻለም» በማለት ዛሬ ድምጻቸውን በዓለም ሸንጎ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያውያን ካህናትና ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎችም አብረዋቸው ድምጻቸውን እያሰሙ እንደሆነም አመልክተዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ፤ ጅማ፤ ወለጋ፣ ሻሸመኔ፣ እንዲሁም በሐረር ክርስቲያኖች መገደላቸውን የገለጹት ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ፤ ባጠቃላይ «በሀገሪቱ ግፍ እየተፈጸመ ነው» በማለት በጀርመንዋ ዋና ከተማ በርሊን ለሰልፍ ያስወጣቸውን ምክንያት ዘርዝረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው «ዓለም ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው» ያሉት የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊ ልሳነ ወርቅ ውቤ በበኩላቸው ከሚገደሉት ሌላ «የታፈኑ፤የታገቱ፤ የተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው የተወሰደባቸው፤ እንደው ጨረቃ ላይ የቀሩ፤ በረሃብ እያለቁ ያሉ፤ አካለ ስንኩላን የሆኑ ክርስቲያኖች ናቸው » በማለት እነዚህ ወገኖች የሚደርስላቸው አጥተዋል ነው ያሉት። በዋና ከተማ በርሊን ሰልፉ የተካሄደው የኢትዮ ጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር ጉባኤ እየተከናወነ ባለበት ዕለት ነው። በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk