uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 613
Obunachilar
+1324 soatlar
+4187 kun
+1 05630 kun
Postlar arxiv
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ጊዜዊ መንግስት ለወረዳ አስተዳደሮች ስልጠና ሰጠ ። መጋቢት 02/2018ዓም ጊዜያዊ መንግስቱ በቀን 30/6/2018ዓ ም ጀምሮ የቋሪት ፣የጎንጅ ቆለላ ፣የይልማና ዴ
+1
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ጊዜዊ መንግስት ለወረዳ አስተዳደሮች ስልጠና ሰጠ ። መጋቢት 02/2018ዓም ጊዜያዊ መንግስቱ በቀን 30/6/2018ዓ ም  ጀምሮ የቋሪት ፣የጎንጅ ቆለላ ፣የይልማና ዴንሳ ፣የሜጫ ወረዳ መንግስታዊ አስተዳደሮች እና  ህግና ስነስርዓቶች ፣እንዲሁም ፋይናንስ መምሪያወች ፣ በተገኙበት ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስልጠናውን መስጠት ተችሏል ። በስልጠናውም ➡️አጭር  የአመራር ሥልጠና ➡️የፍትህ አሰጣጥ ሂደትን ➡️የፋይናንስ አሠራር ሂደትን ➡️የህዝብ አስተዳደር ሂደትን እና የመሳሰሉትን ስልጠና ሰጥቷል ። ብቁ የህዝብ አገልጋይ እና ሀገር ተረካቢ አመራር መፍጠርን ዓላማው ያደረገው ይህ ስልጠና በኮሩ ጊዜያዊ መንስት ሀላፊ አርበኛ ይፍረድ ውዴ እና የጊዜዊ መንግስቱ አመራሮች ተሰጠቷል ። ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በምርጫ አስፈጻሚነት የትኛዉም የአማራ ክልል ላይ የሚሳተፍ አካል እርምጃ ይዎሰድበታል አለቅ 4። አገዛዙ በአማራ ክልል አስመራጭ በማጣቱ የዩኒቨርሲትይ መምህራንን እባካችሁ የሚል በት/ም ሚኒሲቴ በኩል
+5
በምርጫ አስፈጻሚነት የትኛዉም የአማራ ክልል ላይ የሚሳተፍ አካል እርምጃ ይዎሰድበታል  አለቅ 4። አገዛዙ በአማራ ክልል አስመራጭ በማጣቱ የዩኒቨርሲትይ መምህራንን እባካችሁ የሚል በት/ም ሚኒሲቴ በኩል እየተማጸ ነ ነዉ ።  በጠቅላላ ደግሞ አማራ ክልል ቢቻ ነዉ፣ ይህ የሚያሳየው ምንያህል አማራ ክልል ላይ በራሱ መረጃ እንኳ ከግዛቱ ውጭ እንደሆን ያመነበት ነው።

ጀግናው እንዳለ እንየው የማበረታቻ እና የጀግነት ዕውቅና ሽልማት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ተበረከተለት!! =========================== በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ ከንቲባ እና ሰላምና
+3
ጀግናው እንዳለ እንየው የማበረታቻ እና የጀግነት ዕውቅና ሽልማት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ተበረከተለት!! =========================== በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ ከንቲባ እና ሰላምና ደህንነት አመራር በመሆን ለአገዛዙ በሆዳቸው በመገዛት የአማራን ህዝብ ሲያስጨፈጭፉ፣ሴቶችን ሲደፍሩ፣ባለሀብቱን ሲዘርፉ፣ ወጣቶችን ከተለያዬ ቦታ በማፈን ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ በግዳጅ ሲልኩ የነበሩ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ፋኖን የተቀላቀለው #ጀግና እንዳለ እንየው የጀግና አቀባበልና የሽልማት ፕሮግራም ተደረገለት።          የአፋብን ሊቀመንበርና የቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ ከአርበኛ ዘመነ ካሴ  የጀግና ዕውቅና ሰርተፊኬት እና 50,000(ሃምሳ ሽህ) ብር፣ ከቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 50,000(ሃምሳ ሽህ) ብር፣ ከቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ሁለት እግር ክላሽ የማበረታቻ ሽልማት የ109ኛ ኮር እና የ77ኛ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ተበርክቶለታል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ መጋቢት 01/2018 ዓ.ም

4/አራቴት የአድማ ብተና አባላት 12/አስራ ሁለት  ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ‼️‼️‼️ መጋቢት  01/2018 ዓ/ም የአገዛዙ  4/አራት የአድማ ብተና አባላት አዲስ ቅዳም ከመሸገው የጠላት ካፕ በመውጣት 105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለ ጥር የፋኖ አባላትን ተቀላቅለዋል። 1ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል 2ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል 3ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል 4ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል ናቸው የአድማ ብተና አባላቱ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሁለተናዊ ውድመት በማየታቸው  ምሬትና ቁጭት ሲፈጥርባቸው እንደቆየ ተናግረው፣አጋጣሚውን ተጠቅመን ታሪክ ለመሥራትና ለህዝባችን አንድ ውለታ ለማዋል ጥረት ስናደርግ ቆይተናል ብለዋል። ጊዜና ሁኔታወችን ለማመቻቸት ጊዜ ቢወሥድብንም በመጨረሻ ተሳክቶልን ጋ/መሪውንና ዋርድያው  መጋዘን ሲጠብቅ  የነበረን ተላላኪ ቦንዳ አፉን አፍነው ከግድ ጋር በማሠር መካዘን ውስጥ የተቀመጠን 12/አስራ ሁለት መሳሪያና 12/አስራ ሁለት ትጥቅ ይዘን ወንድሞቻችንን ተቀላቅለናል ሲሉ አስረድተውናል። ከአገዛዙ ጋር በመወገን ወገናቸውን ለሚወጉ የተለያዩ አባላት ማለትም አድማ ብተና፣ሚሊሻ፣ፓሊስ፣ መከላከያና ማንኛውም የብልጽግና አደረጃጀት ውስጥ ለሚያገለግሉ አማራዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል። የአማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በተወለደበት ቀየ እንደአውሬ እየታደነ ሲገደል፣ሴቶች ሲደፈሩ፣የሚበላው የአመት ቀለብ ሲቃጠል፣ቤተምነቶች ሲወድሙ፣የሀይማኖት አባት ሲገደሉ፣የህዝብ ተቋማት ሢወድሙ ባይናችን አይተን ተመልክተናል።ስለዚህ ከዚህ አረመኔ ስርዓት  ጋር መወገን በታሪክ ባንዳ  ከመሆንም አልፎ እራስን እንደማጥፋት ስለሚቆጠር፣ፈጥናችሁ ወደወገናችሁ በመቀላቀል ለታላቁ አማራ ውለታ እንድትውሉለት ሲሉ መልክታቸው አስተላልፈዋል። በመጨረሻም ከፋኖ ሲቀላቀሉ በኮር አመራር፣በክፍለ ጦር አመራርና አባላት የጀብደኝነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር  ሕዝብ ግንኙነት

4/አራት የአድማ ብተና አባላት 12/አስራ ሁለት  ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ‼️‼️‼️ መጋቢት  01/2018 ዓ/ም የአገዛዙ  4/አራት የአድማ ብተና አባላት አዲስ ቅዳም ከመሸገው የጠላት ካፕ በመውጣት 105ኛ ኮር የ44ኛ ክፍለ ጥር የፋኖ አባላትን ተቀላቅለዋል። 1ኛ.እስራኤል እየሱስ አድማ ብ/አባል 2ኛ.ሞገስ እሸቱ አድማ ብ/አባል 3ኛ.አበበ መልካሙ አድማ ብ/አባል 4ኛ.ሞገስ ክንዱ አድማ ብ/አባል ናቸው የአድማ ብተና አባላቱ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሁለተናዊ ውድመት በማየታቸው  ምሬትና ቁጭት ሲፈጥርባቸው እንደቆየ ተናግረው፣አጋጣሚውን ተጠቅመን ታሪክ ለመሥራትና ለህዝባችን አንድ ውለታ ለማዋል ጥረት ስናደርግ ቆይተናል ብለዋል። ጊዜና ሁኔታወችን ለማመቻቸት ጊዜ ቢወሥድብንም በመጨረሻ ተሳክቶልን ጋ/መሪውንና ዋርድያው  መጋዘን ሲጠብቅ  የነበረን ተላላኪ ቦንዳ አፉን አፍነው ከግድ ጋር በማሠር መካዘን ውስጥ የተቀመጠን 12/አስራ ሁለት መሳሪያና 12/አስራ ሁለት ትጥቅ ይዘን ወንድሞቻችንን ተቀላቅለናል ሲሉ አስረድተውናል። ከአገዛዙ ጋር በመወገን ወገናቸውን ለሚወጉ የተለያዩ አባላት ማለትም አድማ ብተና፣ሚሊሻ፣ፓሊስ፣ መከላከያና ማንኛውም የብልጽግና አደረጃጀት ውስጥ ለሚያገለግሉ አማራዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል። የአማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በተወለደበት ቀየ እንደአውሬ እየታደነ ሲገደል፣ሴቶች ሲደፈሩ፣የሚበላው የአመት ቀለብ ሲቃጠል፣ቤተምነቶች ሲወድሙ፣የሀይማኖት አባት ሲገደሉ፣የህዝብ ተቋማት ሢወድሙ ባይናችን አይተን ተመልክተናል።ስለዚህ ከዚህ አረመኔ ስርዓት  ጋር መወገን በታሪክ ባንዳ  ከመሆንም አልፎ እራስን እንደማጥፋት ስለሚቆጠር፣ፈጥናችሁ ወደወገናችሁ በመቀላቀል ለታላቁ አማራ ውለታ እንድትውሉለት ሲሉ መልክታቸው አስተላልፈዋል። በመጨረሻም ከፋኖ ሲቀላቀሉ በኮር አመራር፣በክፍለ ጦር አመራርና አባላት የጀብደኝነት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር  ሕዝብ ግንኙነት ፍሬዘር መንግስት ዘለቀ

ስምንት(08) የአገዛዙ ወታደሮች ፋኖን ተቀላቀሉ‼️ በምዕራብ አማራ ቀጠና ወምበርማ ወረዳ ከመሸገው የአገዛዙ ወራሪና ጨፍጫፊ ኃይል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመኮብለል በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።   1. መሠረታዊ ወታደር ዳኔል ታምሩ ፣   2. መሠረታዊ ወታደር ብሩክ ፈቃዱ፣   3. መሠረታዊ ወታደር አብዲ ነገሳ ጨምሮ ሌሎች ሦስት አባላት በድምሩ 6 አባላት ከምስ/ዕዘ 73 ክ/ጦር 3 ሬጅመንት አባላት 5 ጥቁር እና 1 ሠደፍ ክላሽ ፣ 18 የክላሽ ካዘና፣ 07 f-1 ቦንብ በመያዝ በ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል። በተመሣሣይ፡ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ መሽጎ ከነበረው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት መካከል በ23ኛ ክፍለጦር ሁለት የጠላት ኃይሎች የምህረት አዋጁን ተቀብለው በሌሊት በመውጣት የ109ኛ 99ኛ ክፍለጦር ሻለቃ 03 ተቀላቅለዋል ። 1.አብዩ አለልኝ =አንድ ኮሪያ ክላሽ            -150የክላሽ ጥይት            -አንድ f1 ቦንብ 2.እሸቱ ሁሪሳ=አንድ ጥቁር ክላሽ            =90የክላሽ ጥይት በመያዝ 03ኛ ሻለቃን ተቀላቅለዋል። ©አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል! 01/ዐ7/2018 ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና‼️ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ልዩ ዘመቻ በማድረግ ድል ተቀዳጀ ። የካቲት 30/2018 ዓ.ም፡ ምሽት አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ድረስ የቆየ እና በኃይማርያም ማሞ ክፍለጦር "ዘመቻ ሸዋ አንድነት" በሚል የተሰየመ፤ የከሰም ወረዳ ሀገረማርያም ከተማ ላይ የሚገኙ የጠላት መጠቀሚያ ይዞታዎች ላይ ያነጣጠረ ልዩ ዘመቻ መካሄዱ ተገለፀ  ። በዚህ የሸዋ አንድነት በተበሰረበት ሌሊት በተካሄደ ዘመቻ ሁሉም የኃይላማርያም ማሞ ክፍለጦር ሻለቃዎች ቃኚ ሻለቃ እና አባት አርበኞች የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የከሰም ኮር ተወርዋሪ ጦር በጋራ የተሳተፉበት እንዲሁም ጠላትን መውጫ መግቢያ ያሳጣ በሌሊት ጨረቃ ብርሃን ተጀምሮ  በቀን በፀሐይ ብርሃን የቀጠለ ውጤታማ ዘመቻ መሆኑ ተነግሯል ። በዚህ "ሸዋ አንድነት" ተብሎ የተሰየመ እና አምስት ሰዓታትን በፈጀ የመጀመሪያው ክፍል የሌሊት ዘመቻ  በቀጥታ የጠላት መቀመጫ ምሽጎች ላይ ያነጣጠረ መብረቃዊ ጥቃት ተከትሎ ጠላት በደረሰበት ከባድ ድብደባ  ከምሽጉ ወጥቶ በመሄዱ፤ የሀገረማርያም ከተማን እስከ ንጋት ድረስ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በቁጥጥር ስር ለሰዓታት መቆየቱንም አክሎ ተገልጿል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በዛሬው ዕለት ንጋት አከባቢ ላይ በሌሊቱ ጨረቃ በተሰራው በ"የሸዋ አንድነት" የተሰየመው ዘመቻ በደረሰበት ኪሳራ የተበሳጨው የጠላት ኃይል ተጨማሪ ኃይል ከያለበት አሰባስቦ እንደተለመደው በሞርተር ጭምር የተደገፈ ጥቃቶችን በኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ላይ የሰነዘረ ሲሆን በምላሹም የማይቀመሱት ጀግኖቹ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሻለቆች ልክ እንደ ሌሊቱ ዘመቻ በተናበበ መልኩ አፀፋዊ ምላሽ ሰጥተው እንዳመጣጡ አስተናግደውታል ። በ3 ግንባሮች በየቁር ግምባር፣ በይርማታ ሀገር ግምባር እና በሀገረማርያም ግምባር ሲግተለተል የመጣውን ፀረ አማራ የጠላት ሀይል፤ የአብይ አህመድ ቅጠረኛ ሰራዊትን የቤዛ ሻለቃ አይቀጡ-ቅጣት በመቅጣት ባለበት ስፍራ ሁሉ እያደነ መራር የፋኖነት ክንዱን ግቶታል ። በሌላ ግምባር የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ተወርዋሪ በአራት አቅጣጫ ለጥቃት የመጣውን የጠላት ኃይል ቀጥቅጠው መልሰውታል ። በትናንቱ ዕለት ማለትም የካቲት 30/ 2018 ዓ.ም፡ ጠላት ለወረራ የላከው ሞርተር እና ዲሽቃ የታጠቀውን 112ኛ ክፍለጦር እና ከሁሉም የጦር ክፍሎቹ፤ አየር ወለድ ፥ ባህር ኃይል ፥ ፀረ ሽምቅ ብለው የሚጠሩት ኃይልን ጨምሮ፤ ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር  ወደሚገኝበት ቀጠና ቢያጓጉዝም በቂውን ምላሽ በመስጠት መመለሱ ተሰምቷል ። ይህ የጠላት ተደጋጋሚ ሙከራ ዋና አላማው ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦርን በማዳካም እና ቀጠናውን በቁጥጥር ስር ለማድረግ የታሰበ ቢሆንም ሁሉም የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር የማይቀመሱ ሻለቆች እና ተወርዋሪው ሻለቃ በተናበበ እና በተቀናጀ ውጊያ የጠላትን ሃሳብ በተደጋጋሚ አክሽፈውታል ። አረመኔው ወራሪ የብልፅግና የኦሮሙማ ኃይል አንድ ንፁሃን ካህን ስማቸው #ቄስ_መምሬ_ኃይሉ_ንጉሴ የተባሉ የጎርፎ ከተማ አጉራሜዳ ነዋሪ የሆኑ እቤታቸው በራፍ ላይ የረሸናቸው ሲሆን፤ እንዲሁም በዚያው በጎርፎ ከተማ መደቡት ጎጥ ነዋሪ በሆነው አርሶ አደር #ስዩም_ተገኝ የተባለ አርሶ አደር ቤት ላይ የጣለው ሞርታርም በርካታ የቤት እንስሳቶችን የገደለ ሲሆን የአርሶ አደሩን ቤትንም ማፍረሱ ታውቋል ። በዚህ ዕለት ብቻ ጠላት 25 የሞርተር ጥቃቶችን አድርጓል ። የማይደፈረውን ደፍሮ የመጣው የአቢይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በአጠቃላይ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ እስከ ወዲያኛው የተሸኘበትን አስክሬኖቹን በአምቡላንሶች እና ፒካፖች ለቃቅሞ የሄደ ሲሆን 11 ቁስለኞቹን ደግሞ ለማንሳት አምፑላንሶች እየተመላለሱ እንደሚገኙ፤ አፋብን ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሪፖርተራችን መረጃውን ከግምባር አድርሶናል ። © አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ፡ አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ። - አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።

ከአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የተላላፈ #_የማስጠንቀቂያ_መግለጫ!! ​በእነሴ ወረዳ በሞጣ ከተማ አስተዳደር መሸገው የሚገኙት የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የሥርዓቱ ተላላኪዎች ባንዳዎች የአማራ የሕዝቡን የትግል ወላፈን ለማብረድ ሌላ አዲስ የዳቦ ቆረሳ ሴራ ይዘው ሰሞኑን ብቅ ብለዋል። ሆኖም የአብይ አህመድን ወንበር ለማስጠበቅ የሚቆምሩት እነዚህ ምስለኔዎች ዛሬም የአማራን የህልውና ትግል በሽርፍራፊ ጥቅማጥቅም ለመደለል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ሆኖም በከተማው አስተዳደር የመሸጉት የሥርዓቱ ተላላኪዎች የአማራን ህዝብ የማታለያ ስልት ነድፈው የከተማ ቦታ ለፖሊስና ለሚሊሻ አባላት እንሰጣለን የሚል የከንቱ ተስፋ ስርጭት ሲሆን ይህ ተግባር ግን ላይበሉት መነጨሩት ለውጤት ሳይሆን ለጊዜያዊ መደለያ የታለመ መሆኑ የአማራን ህዝብ ለማወናበድ መረባቸውን ዘርግተው እየሰሩ የሚገኙበት ዋና አላማቸው ሲሆን ይህ ተግባራቸው ግን ሊይዙት የሚጨብጡት ካጡበት ጭንቀት የመነጨ እንጂ ለሕዝቡ አስበው እንዳልሆነ የሚታወቅ ኃቅ ነው። ​ይህ አማራ ጠል ሥርዓት እድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት የማታለያ ስልት በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ራሳቸውም ያውቁታል። ሕዝቡ ይህንን አረመኔያዊ አገዛዝ አንቅሮ መትፋቱን የተረዱት ካድሬዎች አሁን ደግሞ የሕዝብን መሬት ለሥርዓቱ አገልጋዮች በመከፋፈል ልዩነት ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ። ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር በአማራ ህዝብ ላይ የሚሰራውን የሲራ ፖለቲካ​ በአገዛዙ የብአዴን ካዴሬዎች ከመሬት አስተዳደር ለፖሊስና ለሚሊሻ አባላት የሚረከቡት ማንኛውም ንብረት በጥብቅ ክትትል እየተደረገበት ይገኛል። ​ይህ ንብረት የሕዝብ ሀብት በመሆኑ በቅርቡ በአደባባይ በይፋ ለትክክለኛ ባለቤቱ ለሆነው ሕዝብ የሚመለስ መሆኑን እናረጋግጣለን!! በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ማንኛውም አካላት ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ መጋቢት 01/07/2018 ዓ.ም ​ድል ለአማራ ሕዝብ! ​የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር

ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ‼️ በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ መርሳ ዙሪያ ገንቦ በር ተራራ እንደ ዝንጀሮ ተሰቅሎ የሚገኘው የሚዋጋለትን አላማ በ
+1
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ‼️ በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ መርሳ ዙሪያ ገንቦ በር ተራራ እንደ ዝንጀሮ ተሰቅሎ የሚገኘው የሚዋጋለትን አላማ በቅጡ የማያቀው የአረመኔው የአብይ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል ። የ104ኛ ኮር ቃኝ ከአረመኔው ስርዓት ጎን ሆነን የአማራን ህዝብ አንጨፈጭፍም በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መዳረሻችው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበር ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 01/ዐ7/2018 ዓ.ም

በሸዋ የሚገኘው የአገዛዙ ጥምር ጦር በየቀኑ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ፋኖን እየተቀላቀለ ነው ‼️ የአማራ ፋኖ ትግል ወደ አንድ እየተሸከፈ ሲመጣ የብልፅግና ሠራዊት እየፈረሰ ነው።የአፋብን መመስረት
በሸዋ የሚገኘው የአገዛዙ ጥምር ጦር በየቀኑ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ፋኖን እየተቀላቀለ ነው ‼️ የአማራ ፋኖ ትግል ወደ አንድ እየተሸከፈ ሲመጣ የብልፅግና ሠራዊት እየፈረሰ ነው።የአፋብን መመስረትን ተከትሎ ድል ለፋኖ ፊቱን ሲያዞር ሽንፈት እና ድንጋጤ  የአገዛዙ ሆኗል።ወትሮም ሲጠበቅ የነበረው የአሸናፊነት ቁልፍ የፋኖ ሀይል ወደ አንድ መሰብሰብ እውን ሲሆን በፋኖ ሠራዊት እና በትግሉ ደጋፊዎች ዘንድ መነቃቃቱ ሲያይል በብአዴን ጋድሬዎች እና በሚያሰማሩት ጦር በኩል የተስፋ ጭላንጭል እየጠፋ ነው። ለአመታት በጦርነት ተጠምዶ የነበረው የአገዛዙ ሠራዊት የመዋጋት ወኔው ከድቶት ቢቆይም  ከነፃነት ተዋጊው የፋኖ ሀይል ጋር የሚገጥምበት ምክንያት እንደሌለ  ተረድቷል።አሁን በሁሉም የአማራ ግዛቶች በቡድን እየከዳ ፋኖን የሚቀላቀለው ሀይል ከቀን ቀን እየጨመረ ነው።ከሰሞኑ ሁለቱ ሸዋ ውስጥ ያሉ የአፋብን ዕዞች ወደ አንድ መምጣታቸው ሲበሰር ወዲህ ደግሞ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ያለው ጥምር ጦር እየፈረሰ ነው። ከሰሞኑ በርከት ያሉ የአየር ሀይል አባላት ራንቦ ክፍለጦርን ሲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት ደግሞ ከሸዋሮቢት የተነሱ አንድ ሠላም አስከባሪ የሚሊሻ አባል እና  አንድ አየር ወለድ  የመከላከያ አባል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ተቀላቅለዋል።የመከላከያ አባሉ አንድ ስናይፐር እና ጥቁር ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ የያዘ ሲሆን የሚሊሻ አባሉም አንድ ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

ፋኖ ለምርኮኛ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት የቅያሪ ልብስ አከፋፈለ! በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ሰሞኑን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ዙሪያ ባደረገው ተጋድሎ ለማረካቸው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት የቅያሪ ልብስ ስጦታ አበረክቷል። ይህ የፋኖ ድርጊት፡ አለም አቀፍ የምርኮች አያያዝ ሕገ ደንብን ከማክበር ባሻገር ፋኖ የወጣበትን ማሕበረሰብ እሴትን የጠበቀና የሰብአዊነትን ጥግ ያሳየ ነው ተብሏል።

የቡግና ወረዳ አባት አርበኞች በአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!       መጋቢት:-01/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው የቡግና ወረዳ አባት አርበኞች በአገዛዙ ብልፅግና ጦር ሰራዊት ላይ ደፈጣ በመጣል ታላቅ ጀብዱ ፈፀሙ። ከስድስት ያልበለጡ የቡግና ወረዳ የፋኖ ሲቪል መዋቅር አባት አርበኞች ዳሪያ (ጃሮ) 06 ቀበሌ ለስራ በተላኩበት ቅፅበት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ነፃ ቀጠና ነው ብሎ እግረኛ ሳይዘረጋ ሦስት ካሶኒ ሰራዊት ከላሊበላ ወደ አይና ቡግና አሳልፋለሁ ሲል አርበኞቹ የካቲት 30/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ገደማ ጃሮ ወንዝ ላይ ደፈጣ በመያዝ እንደ ሸቀጥ ዕቃ ተጭኖ በመጣው የጁላ ሰራዊት ላይ ፈጣን ጥቃት በመክፈት በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዋል። በዚህም ፈጣን ጥቃት ሰባት የጠላት ኃይል ወዲያውኑ ሲደመሰስ ከ10 በላይ የቆሰለ፣ ሁለት ካሶኒ ከአገልግሎት ውጭ የተደረገ ሲሆን ሙትና ቁስለኛውን በአምቡላንስ ሲያመላልስ አምሽቷል። በመጨረሻም የ303ኛ አሳምነው ኮር ከፍተኛ አመራሮች የቡግና ወረዳ ሲቪል መዋቅር አባት አርበኞች ላደረጉት ተጋድሎ እውቅና የሰጡና ምስጋና የቸሯቸው ሲሆን ለቀጣይም የወሎና ዋግ መንገዶች፣ ተራሮችና ወንዞች ለጠላት ኃይል እንደ እሳት የሚፋጁ አይነኬ እናደርጋቸዋለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ     መጋቢት:-01/2018 ዓ.ም

ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ! በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ መርሳ ዙሪያ ገንቦ በር ተራራ እንደ ዝንጀሮ ተሰቅሎ የሚገኘው የሚዋጋለትን አላማ በቅ
+1
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ! በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ መርሳ ዙሪያ ገንቦ በር ተራራ እንደ ዝንጀሮ ተሰቅሎ የሚገኘው የሚዋጋለትን አላማ በቅጡ የማያቀው የአረመኔው የአብይ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል ። የ104ኛ ኮር ቃኝ ከአረመኔው ስርዓት ጎን ሆነን የአማራን ህዝብ አንጨፈጭፍም በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መዳረሻችው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበር ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 1/2018 ዓ ም

ዋና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ ዛሬም የምረት ጥሪውን ተቀብለው በ201ኛ ኮር ባሉ ክፍለ ጦሮች ውስጥ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ናቸው ➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽ ........መጋቢት 01/2018 ዓ.ም 1.አበባው
+4
ዋና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ ዛሬም የምረት ጥሪውን ተቀብለው በ201ኛ ኮር ባሉ ክፍለ ጦሮች ውስጥ ፋኖን በመቀላቀል ላይ ናቸው ➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽ ........መጋቢት 01/2018 ዓ.ም 1.አበባው ምንይበል...አድማብተና ከመርጦ ለማርያም ኮርያ ክላሽ 2 ካዘና እና 2 ቦንብ በመያዝ 2.አየለ ሙናይ ....ምሊሻ ከግንደወይን አብራራው በመያዝ 3.ዳዊት ሙቀት...መከላከያ ከ25ክ/ጦር ሁለት አባላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ከድጎ ፅዮን ብሬን ተኳሽ የነበረ ሲሆን በክፍለ ጦር አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ምርኮኛ ልጆቻቸው በሰላም ወደ ቤታቸው የተሸኙላቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለፋኖ ምስጋና አቀረቡ! በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የስርዓቱ አገልጋይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተማርከው በፋኖ እጅ ይገኛሉ። ፋኖ እነዚህ ምርኮኛ ወታደሮችን የአለም አቀፍ የምርኮኛ አያያዝ ሕገ ደንብን ባከበረና አማራዊ እሴትን በጠበቀ መልኩ ተንከባክቦ እንደያዛቸው  የግምባር ዘጋቢዎች በተንቀሳቀሱበት ቀጠና ለመመልከት ችለዋል። ከምርኮኛ ወታደሮች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ "ይህ ስርዓት የኦሮሞ ስርዓት ነው።እንዳይፈርስ መታደግ አለባችሁ" በሚል ፕሮፓጋንዳ ተታለው መከላከያ ሰራዊትን እንደተቀላቀሉ ይናገራሉ። የፋኖ አባላቱም በፈቃደኝነት አላማቸውን ተጋርተው ከእነሱ ጋር ለመቀላቀል የፈለጉ ምርኮኛ ወታደሮችን የተሀዲሶ ስልጠና በመስጠት እንዲቀላቀሏቸው ያደረጉ ሲሆን፡ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ የፈለጉትን ደግሞ የትግሉን አላማ በማስረዳትና የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን በሰላም የሚሄዱበትን ቀጠና በማመቻቸት እየሸኙ ይገኛሉ። ልጆቻቸው ከሞት ተርፈው በሰላም የመጡላቸው በወለጋ፣ በሸዋ፣ በቦረና እና በሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች የሚገኙ የምርኮኛ ወታደር ወላጅ የሆኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለፋኖ ምስጋና ማቅረባቸውን ነው  በየቀጠናው ያሉ የፋኖ አመራሮችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው። በፋኖ ከተማረከ በኋላ የመጓጓዣ ወጭ ተሸፍኖለት የተሸኘ ልጇን በሰላም ያገኘች በምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ አከባቢ ነዋሪ የሆነች አንዲት እናት ምርኮኛ ልጇ ይዞት በነበረው የፋኖዎች ስልክ ቁጥር በመደወል "ልጄን ዳግመኛ እንደወለዳችሁት ነው የምቆጥረው። ይህ አካሄዳችሁ ትግላችሁ ሀቅ እንዳለው የሚያስመሰክር ነው። የእውነት አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነው የፋኖ አመራሮቹ ለጣቢያችን የገለፁት። ምርኮኛ ልጃቸው በሰላም ወደ ቤቱ የተመለሰላቸው ሌላኛው በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ አባት "ልጄ በፋኖ መማረኩን ስሰማ አለቀስኩ።ምክኒያቱም እኛ በቀበሌ ስብሰባም፡ በኦቢኤንና በኦኤሜን ቴሌቪዥንም የሚነገረን ፋኖ ገዳይና አራጅ ነው በሚል ነው። አሁን ግን ልጄ በሰላም መጥቷል። በዚህም የትግላችሁን ሀቀኝነት አረጋግጣችሁልኛል። ዋቃ(አምላክ) ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ምርኮኛ ልጆቻቸው በሰላም ወደቤታቸው መሸኘታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አርሲ አከባቢን ጨምሮ በጉጂ፣ በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ እና በሌሎች የክልሉ አከባቢዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ተመሣሣይ የምስጋና መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነው የፋኖ አመራሮቹ የገለፁት።