uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 194
Obunachilar
+4524 soatlar
+967 kun
+45930 kun
Postlar arxiv
የአርበኛ መከታው ማሞ ወቅታዊ መልዕክት፡ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30 የሚቆየው የዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ (Global Protest)ጥሪን አስመልክቶ፣ የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ ያስተላለፉት አጭር መልዕክት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል፦ 👉አርበኛው በቆራጥነታቸው እንደሚታወቁት ሁሉ፣ በዚህ በታወጀው የወር ዘመቻ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ተቃውሞ የግለሰብ ሳይሆን የፍትህና የነፃነት ጥያቄ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። 👉በአገር ውስጥ እየደረሰ ያለውን በደልና ጭቆና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በግልጽ ማሳወቅ። =>የሕዝብን የህልውና ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር። =>ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመፍጠር የለውጥ እንቅስቃሴውን ማፋጠን። 👉አርበኛ መከታው ማሞ ሰልፉ በታቀደለት መንገድ፣ በስነ-ምግባር እና በታላቅ ዝግጅት እንዲከናወን አሳስበዋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የአገሩን ባንዲራና የትግል ዓላማውን አንግቦ በየሄደበት አደባባይ ሁሉ እውነቱን እንዲመሰክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። "ድል ለተገፋው ሕዝባችን! ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!" በማለት በፅናትና በተስፋ የተሞላውን መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በ182 የተለያዩ መድረኮች 167,539 አርሶ አደሮች ጋር በትግሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል። የድርጅቱ አራቱ ዕዞች በሚያስተዳድራቸው ቀጠናወች በተካሔደው የአርሶአደሮች የንቅናቄ መድረክ ከድርጅቱ የወረዱት የአሰራር መመሪያወች፣ የመወያያ ሰነዶች፣ የማስፈፀሚያ ፕሮቶኮል መርሆወችን በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል። በዚህም መሰረት ከሚያዝያ 17-19/2018 ዓ.ም በተካሔደው የአርሶ አደሮች የንቅናንቄ መድረክ:- ➡ ምኒልክ በወሎ ቤተ-አማራ 51 ማዕከላት ላይ የተሳኩ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን በእነኝህ መድረኮች  42,987 ( አርባ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሰባት አርሶ አደሮችን ማሳተፍ ተችሏል። ➡ በቴዎድሮስ ዕዝ 52 ያህክል መድረኮች በስኬት ማጠናቀቅ ሲቻል በእነኝህ መድረኮች 39,700 ( ሰላሣ ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ) አርሶ አደሮችን ማሳተፍ ተችሏል። ➡ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በ37 ያህክል የመድረክ ውይይቶች 30,100 (ሰላሳ ሺ አንድ መቶ) አርሶ አደሮችን ማወያየት ተችሏል። ➡ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ ስር ባሉ ቀጣናወች 42 መድረኮች የተዘጋጁ ሲሆን በእነዚህ መድረኮች 54,752 (ሃምሳ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሁለት) አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል። በአጠቃላይ በ182 የተለያዩ መድረኮች 167,539 (አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ) ጋር ውይይት ማድረግ ተችሏል። በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ግንዛቤ ይዳብራል ፤ ህልውናውም ይረጋገጣል። ' በሚል መሪ ቃል የተካሔደው መድረክ ወቅታዊ የትግሉ ጉዳዮችን ጨምሮ በርካታ ጭብጦችን የዳሰሰ ውይይት ያደረግንበት ነው።  ከድርጅት አመራር ጀምሮ የዕዝ፣ የኮር ፣ የክፍለ-ጦር ወረዳ ግዜያዊ መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር አመራሮች በመገኘት መድረኮችን መርተዋል፤ የድርጅቱን ሰነድ በማብራራት እና ውይይቱን በመምራት ግዴታቸውን ተወጠዋል ። የውይይት ተሳታፊ አርሶ-አደሮቻችን በርካታ ሃሳቦችን አንስተዋል። ከተነሱት መሰረታዊ ፍሬ ሃሳቦች መካከል:- ፩) አደረጃጀቶች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ በጠላት ላይ አብራችሁ ልታዘምቱን ይገባል፤ የግል ትጥቅ ያላቸውን አርሶ አደሮች በአባት አርበኞች አደረጃጀት መዋቅራዊ መንገድ ልንታገል ይገባል፤ ፪) በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ሆነው የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን እና ወንጀል የሚሳሩትን ድርጅቶ ሊያርማቸው እና ሊታገላቸው ይገባል፤ ፫) የነፍስ አባቶቻችን፣ ሐኪሞችንና ህፃናት አድኖ የሚገድል መንግስት በታሪክም ሰምተን አናውቅም፡፡ ይህን መንግስት ሁሉም ለመፋለም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነን፤ ፬) ነፃ በወጡ ከተሞች ላይ  በተለይ ለቅሶና ምሽት ላይ ጥይት ተኩስ አስቁሙልን፣የህዝን አስተዳደርንና ፍትህ ስርዓት ከወታደሩ ውጭ በሆነ መዋቅር እንዲሰራ አድርጉልን፤ ፭) መንግስት የሚገድለን አንሶ እና ደግ በጥቁር ደም እርስ በእርስ በእርስ መገዳደልን በአዋጅ አስቀሩልን፣  ህዝቡ በኑሮ ውድነት እና ትራንስፖርት ችግር መኖር የማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው፣ ትግሉን ተረባርበን በድል ማጠናቀቅ አለብን፤ ፮) የትምህርት አገልግሎት በተጀመረበት ቦታም ጭምር ትምህርት በአግባቡ እየተሰጠ አይደለም፡፡ ጠላት በመጣ ጊዜም ፋኖ የተቆጣጠራቸውን ትምህርት ቤቶች ንብረታቸውን እየዘረፈ እየጫናቸው ነው፡፡ ኮምፒዩተሮችን ጨርሶ ጭኗቸዋል፡፡ ጤና ጣቢያዎች መድሃኒት እመጣላቸው አይደለም፡፡ መንግስት ጤና መድህን እያለ ይበዘብዘናል ነገር ግን ጤና ተቋም ስንሄድ ሁሉም ነገር የለም ነው የሚባለው፡፡ ይህንንም መፍትሄ ብትፈልጉልን፡፡ ፯) በጦርነቱ ምክንያት አካል ጉዳተኛ የሆኑን ወላጅ አልባ የሆኑ በርካታ የገበሬ ልጆች አሉና ድጋፍ ብታደርጉላቸው፣ መንገዶችን ጠላት እየዘጋብን እንቅስቃሴ ተቸግረናል፡፡ ፰) ከመሬት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የፍትህ ችግር አለ። ፋኖ በተቆጣጠረው አካባቢም በሰፊው ግጦሽ እርሻ እየታረሰ ነውና የመሬት ሕግ  የመሬትና መሰል ማህበራዊ ጉዳዮችን በእድር ኮሚቴ እንድንፈታ እውቅናና ድጋፍ ስጡን፡፡ ከአቅማችን በላይ የሆነውን ግን ወደ ፋኖ ጊዜአዊ መንግስት እናመለክታለን የሚሉ እኔ ሌሎችም ይገኙበታል። በሁሉም መድረኮች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ተሳታፊወች ሀሳብ የተሰጠ ሲሆን ተሰብሳቢወችም የአንድነት ቃል ኪዳናቸውን የሚያድስ የአቋም መግለጫ በማውጣት መድረኮቹ ተጠቃለዋል። መድረኮች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ የህዝቡ የመሰብሰብ ፍላጎቶች እና ተነሳሽነት መኖሩ፣ የመድረኮችን አስፈላጊነት በተመለከተ ለማህበረሰቡ ግልፅ መልዕክቶች መተላለፋቸዉ፣ ከማዕከል በታቀደ እና በተደራጀ መንገድ ሰነዶች እና የስራ መመሪያወች ተደራሽ መደረጋቸው በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። በመድረኮች የመዋቅራችን መካከለኛ አመራር መድረኮችን የመምራት አቅሙን ያሳዬበት፣ የመፈፀም አቅሙ የተረጋገጠበት፣ ከማህበረሰቡ የተነሱ እና ድርጅታዊ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች መኖራቸውን፣ ትግሉ የደረሰበት ደረጃ አሁናዊ እና የቀጣይ ሁኔታውን ለአርሶአደሩ ማስረፅ መቻሉን፣ የብልፅግናን የምርጫ ቀልድ ያአማራ አርሶ አደር ፈፅሞ የማይቀበለው መሆኑ ከህዝቡ አንደበት የተረጋገጠበት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። በተለይም በዚህ የህልዉና ተጋድሎ ፈርጀ ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው የአማራ አርሶ አደር እጣ ፋንታው ይህንን አገዛዝ ማስወገድ መሆኑን ስለማመኑ የተረጋገጠበት እንደሆነም ታይቷል።  ለሚደረጉ ድርጅታዊ ዘመቻወች ወደፊት የተጠናከረ ህዝባዊ ድጋፍ የሚኖር መሆኑንም ያመላከተ መድረክ ነው።   የመድረክ አፈፃፀሞች አስደናቂ የሥራ ቅንጂት የታየበት እንዲሁም የተሻለ ጥበቃ እና የፀጥታ ስራ የተሰራበት ቢሆንም የሚዲያ ባለሞያዎች እጥረት እና የሚዲያ ቁሳቁስ ችግር መኖሩ የመድረኮችን ድባብ ለሚዲያ በፍጥነት እና በጥራት ማድረስ ላይ ድክመት መኖሩ እንዲሁም ሥራውን ለመስራት በቂ በጀት አለመኖር እና በርካታ ቦታወች ላይ ውጊያ በመኖሩ የመድረኮችን ሽፋን በታቀደው ልክ አለማድረጉ በህዝብ ንቅናቄው አብይ ኮሚቴ መድረክ ተገምግሟል። በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በትግሉ ላይ ያለው እምነት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ፤ ድርጅቱም ለህዝብ የገባውን ቃል ኪዳን ያደሰበት መድረክ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህ መድረክ እንዲሳካ ያደረጉ በተዋረድ ያሉ የድርጅቱ አመራር እና አባላት፣ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር አመራሮች እና ተሳታፊወችን ከልብ ያመሰግናል። አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

የነፃነት ንስር እና የሸፍጥ ተኩላዎች፡ የፋኖ የክብር ጉዞ! 🦅 ​የንጋት ወፎች በዜማ እንደሚቀበሉት አዲስ ቀን፣ የፋኖ የነፃነት ጉዞም የህዝብን የህልውና ተስፋ ያበስራል። ይህ ጉዞ ውበት ብቻ አይደ
የነፃነት ንስር እና የሸፍጥ ተኩላዎች፡ የፋኖ የክብር ጉዞ! 🦅 ​የንጋት ወፎች በዜማ እንደሚቀበሉት አዲስ ቀን፣ የፋኖ የነፃነት ጉዞም የህዝብን የህልውና ተስፋ ያበስራል። ይህ ጉዞ ውበት ብቻ አይደለም፤ የጀግንነት ጥግ፣ የፅናት ማማ እንጂ። ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እንደ ጋሻ፣ የነፃነት ህልሙን እንደ ሰንደቅ ይዞ ወደ ማይቀረው ድል እየገሰገሰ ነው። በዚህ የጀግንነት ጎዳና ላይ ግን፣ አማራን ለማጥፋት አማራ መስለው የተሸፈኑ የክፋት አውሬዎች አሉ። የአማራን መልክን ተላብሰው፣ የቃልን ተንኮል አዝለው፣ የህዝቡን የነፃነት ጉዞ ከውስጥ ለመሸርሸር የሚዶልቱ የሸፍጥ ተኩላዎች የመጨረሻቸው ደግሞ አሁን ነው። የፋኖ ጉዞ ግን እንደ ንስር ነው! ንስር ከአድማስ በላይ እንደሚመለከት፣ ፋኖም የነዚህን በሸዎች ተንኮል ከአድማስ ይለያል። የእውነትን ጎዳና ተከትሎ፣ የክፋትን ሴራ በፅናት እየረገጠ፣ ወደ ነፃነት ማረፊያው እየበረረ ነው። ​ይህ የነፃነት ጉዞ የቆራጦች መታወቂያ፣ የጀግኖች ማረጋገጫ ነው። ​💪 አብሮነት፣ ጽናት፣ እና የንስር ብርታት ለነፃነት! ​#ፋኖ #የነፃነትጉዞ #የአማራህዝብ #የንስርመንፈስ #ጀግንነት #ነፃነት #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የነፃነት ንስር እና የሸፍጥ ተኩላዎች፡ የፋኖ የክብር ጉዞ! 🦅 ​የንጋት ወፎች በዜማ እንደሚቀበሉት አዲስ ቀን፣ የፋኖ የነፃነት ጉዞም የህዝብን የህልውና ተስፋ ያበስራል። ይህ ጉዞ ውበት ብቻ አይደ
የነፃነት ንስር እና የሸፍጥ ተኩላዎች፡ የፋኖ የክብር ጉዞ! 🦅 ​የንጋት ወፎች በዜማ እንደሚቀበሉት አዲስ ቀን፣ የፋኖ የነፃነት ጉዞም የህዝብን የህልውና ተስፋ ያበስራል። ይህ ጉዞ ውበት ብቻ አይደለም፤ የጀግንነት ጥግ፣ የፅናት ማማ እንጂ። ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እንደ ጋሻ፣ የነፃነት ህልሙን እንደ ሰንደቅ ይዞ ወደ ማይቀረው ድል እየገሰገሰ ነው። በዚህ የጀግንነት ጎዳና ላይ ግን፣ አማራን ለማጥፋት አማራ መስለው የተሸፈኑ የክፋት አውሬዎች አሉ። የአማራን መልክን ተላብሰው፣ የቃልን ተንኮል አዝለው፣ የህዝቡን የነፃነት ጉዞ ከውስጥ ለመሸርሸር የሚዶልቱ የሸፍጥ ተኩላዎች የመጨረሻቸው ደግሞ አሁን ነው። የፋኖ ጉዞ ግን እንደ ንስር ነው! ንስር ከአድማስ በላይ እንደሚመለከት፣ ፋኖም የነዚህን በሸዎች ተንኮል ከአድማስ ይለያል። የእውነትን ጎዳና ተከትሎ፣ የክፋትን ሴራ በፅናት እየረገጠ፣ ወደ ነፃነት ማረፊያው እየበረረ ነው። ​ይህ የነፃነት ጉዞ የቆራጦች መታወቂያ፣ የጀግኖች ማረጋገጫ ነው። ​💪 አብሮነት፣ ጽናት፣ እና የንስር ብርታት ለነፃነት! ​#ፋኖ #የነፃነትጉዞ #የአማራህዝብ #የንስርመንፈስ #ጀግንነት #ነፃነት #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር

በአፋብን ታሪክ የተመዘገበ ግዙፍ ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ ከ167 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በትግሉ ቀጣይነትና በወሳኝ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መከሩ! (ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ 251 ሚዲያ) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በሚያስተዳድራቸው አራት ዕዞች ሥር በሚገኙ ቀጠናዎች፣ ከሚያዝያ 17 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ታሪካዊና ግዙፍ የአርሶ አደሮች የንቅናቄ መድረክ ማካሄዱን አስታወቀ። “በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ግንዛቤ ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል በተከናወነው በዚህ ንቅናቄ፣ በ182 የተለያዩ መድረኮች በአጠቃላይ 167,539 (አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ) አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል። የንቅናቄው መረጃ እንደሚያመለክተው፦ • በምኒልክ በወሎ ቤተ-አማራ፦ 42,987 አርሶ አደሮች በ51 ማዕከላት፤ • በቴዎድሮስ ዕዝ፦ 39,700 አርሶ አደሮች በ52 መድረኮች፤ • በአሳምነው ዕዝ (ሸዋ)፦ 30,100 አርሶ አደሮች በ37 መድረኮች፤ • በበላይ ዕዝ (ጎንደር)፦ 54,752 አርሶ አደሮች በ42 መድረኮች ተወያይተዋል። በእነዚህ መድረኮች ላይ የተገኙት አርሶ አደሮች ለአፋብን አመራር ያቀረቧቸው ነጥቦች የትግሉን የወደፊት አቅጣጫ የሚጠቁሙ ሆነው ተገኝተዋል። አርሶ አደሮቹ በፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ በጠላት ላይ በጋራ እንዲዘመት፣ በፋኖ ስም ወንጀል የሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድና በነጻ በወጡ ከተሞች አስተማማኝ የሕዝብ አስተዳደርና የፍትሕ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠይቀዋል። በተለይም አገዛዙ የነፍስ አባቶችን፣ ሐኪሞችንና ሕፃናትን ሳይቀር እየገደለ መሆኑን የጠቀሱት አርሶ አደሮቹ፣ ይህንን የግፍ አገዛዝ ለመፋለም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በውይይቱ ወቅት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው የኑሮ ውድነት፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች መቋረጥ እንዲሁም አገዛዙ በየሐሰተኛ የምርጫ ስም የሚያደርገው ማጭበርበር በከፍተኛ ሁኔታ ተኮንኗል። አርሶ አደሩ “የብልጽግናን የምርጫ ቀልድ በፍጹም አንቀበልም” በማለት የሕዝቡ እጣ ፈንታ ይህንን አገዛዝ ማስወገድ ብቻ መሆኑን በአንድ ድምፅ አረጋግጧል። የአፋብን የሕዝብ ንቅናቄ አብይ ኮሚቴ በሰጠው ግምገማ፣ መድረኩ የመካከለኛ አመራሩን የማስፈጸም አቅም ያረጋገጠበትና ከሕዝቡ ጋር ያለውን መተማመን ያጠናከረበት መሆኑን ገልጿል። ምንም እንኳን የሚዲያ ባለሙያዎችና የቁሳቁስ እጥረት እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ውጊያዎች ለዜና ሽፋን እንቅፋት ቢሆኑም፣ ንቅናቄው የአማራን ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ወደማይቀለበስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑ ታምኖበታል። በሁሉም መድረኮች ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎቹ የነጻነት ጉዟቸውን በድል ለማጠናቀቅ ቃል ኪዳናቸውን በአቋም መግለጫ አድሰዋል። ኢትዮ 251 ሚዲያ የነጻነት አንደበት

ህያው ጀግና ቀኝ አዝማች ጨለፍ ተስፋው ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም ውድ ህይወቱን ለአማራ ህዝብ ህልው መሆን አሳልፎ ሰጠ! አርበኛ ጨለፍ ተስፋው የአባቱን ክላሽ በማንሳት በ2013 ዓ.ም ጋሸና ግባር ላይ ተከሰተ። ብላቴናው በሰሜኑ ጠርነት እልክ አስጨራሽ ተጋድሎ በማድረግ በድል ተራራ ላይ ታሪኩን በደም ፃፈ። የሰሜኑ ጦርነት አደቡን እንደያዘ አርበኛ ጨለፍ ተስፋው በአምባሰል ተራሮች እየተጎባለለ ከስምንት ጓዶቹ ጋር ፋኖን ማሰባሰብ ጀመረ። ሰማዕቱ ራምቦ የጨለፍ የአንጀት ወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ሁለታቸው አብረው ለበርካታ አመታቶች የጥላትን ሰራዊት በደፈጣ ዶግ አመድ እያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ወደር አልባ ታሪክን በፋኖነት ስም አስመዘገቡ። አርበኛ እራቦና ጨለፍ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። አርበኛ ጨለፍ ከአምባሰል ተራሮች ተነስቶ ሸዋ ምድር ተከስቶ በርካታ ታሪኮችን ከሰራ በኋላ ወደ ምዕራብ ወሎ ተቀሳቅሶ በወግዴ፤በሳይንትና በሌሎች ወረዳዎች ፋኖን በማደራጀት ጉልህ ሚናን ተጫውቷል። አሞካሽተው ቀኜ ብለው የሚጠሩት ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ከሸዋ ምድር አንድ ታላቅ ታሪክን ለመስራት በደራ በኩል ተከሰተ። እርሱ የሚገድበው ቀጠና የለምና በአገዛዙ በአብይ አህመድ ተሰርተው ሰልጥነውና አቅጣጫ ተሰቷቸው በጃልሰኒ የሚመሩ አካላቶች በአማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍን ይፈፅሙ ነበርና፤ ቀኝአዝማች ጨለፍ በደራ በኩል ጃልሰኒና ቡድኖቹ ወደሚገኙበት አቀና። ያኔ ጃልሰኒ የአማራን ንፁሀኖችን መጨፍጨፍ የዘወትር የአብይዚም ተልኮው ስለነበር የጨለፍን ነፍጥ ፈፅሞ አልጠበቀም። ጨለፍ ግን የአማራን ህዝብ የጨፈጨፈን ጥላት ከከተመበት ድረስ ዘልቆ የህልውና መዳኛ ነፍጡን በነ ጃልሰኒ አርከፈከፈው። በርካታ የጃል ሰኒ ሰራዊቶች ተደመሰሱ። ጃልሰኒም ወደ አለቃው አብይ አህመድ እሩጦ እጀን ሰጠሁ አለ። የእሳቱ ጉራጅ ጨለፍ ተስፋው በደራ ምድር በጀብደኝነት በአማራዊ ኩራት ጎልቶ ታዬ። አፀፋ ጥቃቱን በሚገባ የተወጣው አርበኛ የአብይ አህመድንና የሽመልስ አብደሳን ገዳይ መሪ ጃልሰኒን በማስጨነቅ የጥፋት ካባውን ገፈፈው። ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው የደራን ኦፕሬሽን በሙሉ ፈፅሞ ወደ ወግድ ተሻገረ። ወዳውኑ ወደ ትውልድ ቦታው መቄት በመሻገር ከጓድኛው አርበኛ ቅዱሴና አርበኛ ማረጉ እንድሁም በርካታ አርበኛ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ታሪኩ ተነግሮለት የማያቀውን የመቄትን ህዝብ ታሪክ በደም በአጥንታቸው ለመፃፍ ቆርጠው ተነሱ። በመቄት ምድር ፋኖነትን ለማስፋፋት ከቀናቶች የዘለለ ጊዜ ሳይውስድባቸው ሳር ቅጠሉን በፋኖ አንቆጠቆጡት። በመቄት ምድር ላይ ጥላት የእግሩ መረገጫ እስኪያጣ ድረስ ቀኝ አዝማች ጨለፍ ተስፋው ቆላ ወርዶ ዳገት ተቃቶ ፋኖን አደራጀ። የፋኖ ትግልን ጠላፊዎች ጨለፍን ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በሴራ ትብታባቸው ሊታቱት ሞከሩ እንጅ ከአማራነት ክብሩ ፈፅሞ የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ሊያሳጡት አልተቻላቸውም። በርካታ ሆድ አደር የአማራ ህዝብ ጥላቶች ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋውን እንደ ተኩላ ከበው ይጠዘጥዙት ዘንድ ቋመጡ።ቀኝአዝማች ጨለፍ ግን ወይ ሞት ወይ አማራነት በማለት እስከ ህይወት ፍፃሜው ድረስ በአማራዊያን የአባቶቻችን ታሪክ ቁሞ ተገኜ። በዚህ አቋሙ በርካታ ባንዳዎች የልመና በራፋቸውን ለማስከፈት በቀኝአዝማች ጨለፍ ላይ የሀሰት ትርክትና ስም ማጥፋት ዘመቻ ቢከፍቱበትም ቅሉ እስከ ሞት ድረስ በአላማው ፀንቶ ዘለቀ። የደፈጣው ንጉስ ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ለአማራ ህዝብ ታምኖ ከኦሮሙማው ጥላት ጋር ከሶስት አመት በላይ ሲፋለምና የጥላትን ሰራዊት በየቀኑ በአስከሬን አንስተህ ጫን በመቄት ወረዳ የምስጥ ሲሳይ እያደረገ በርካታ አካባቢዎችን ከጥላት ነፃ በማውጣት የፌደራል ጥቁር አስባልት መቆጣጠር ቻለ። ቀኝ አዝማች ጨለፍ መነሻ ቦታውን መቄት ያድርግ እንጅ በድርጅቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ በርካታ ታሪኩችን መስራት የቻለ የዘመናችን በላይ ዘለቀ ነበር። ቀኝአዝማች ጨለፍ ከሶስት ወራቶች በፊት በተንታ አጅባርና በተንታ ሚካኤል የቀድሞዉ የደጋው መብረቅ የአሁኑ 106ኛ ኮር ዘመቻ መሪ ሆኖ የጥላት ሙሉ ሰራዊትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ህያው ታሪክን ሰርቷል። በብዙ ፈተናዎች ውስጥ 106ኛ ኮርን ለመመስረት ጨለፍ እጅግ የላቀ ሚናን በማድረግ  ኮሩ በሁለት እግሩ እንድቆም አይረሴ አስተዋፆ ነበረው። በቁልምጫ ቀኜ እያልን የምንጠራው ተናዳፍው አርበኛ ከወሎ እስከ ሸዋ ከሸዋ እስከ ጎንደር ጎጃም እግሮቹ እስኪቀጥኑ ተከራቶ አማራዊ ግዳጁን በመወጣት ተከድቶ እስኪወድቅ ድረስ በፍፁም ታማኝነት ተወጥቷል። በደቡብ ጎንደር የቀድሞዋን አንሻ ክፍለ ጦር የአሁኗ 22ኛ ክፍለጦርን በመምራት ንፋስ መውጫ የጥላት ሀይልን በመደምሰስ እና በርካቶችን በመማረክ ቀጠናዊ ትስስርን በማይዝል ቃልኪዳን አስተሳስሯል። ቀኝአዝማች ጨለፍ በርካታ ክፍለ ጦሮች ላይ ትልቅ አስተዋፆ ከማድረጉም በላይ የአማራ ታጋዮች አንድ እውነተኛ ድርጅት እንድኖረው ጉልህ ሚናን ተወቷል። በመጨረሻም አርበኛ ቀኝ አዝማች ጨለፍ አስፋው ባመነውና ጓዴ ባለው ጥቁር አማራ ከጀርባው ተወግቶ ወደቀ። ለአማራ ህዝብ ነፃነት ትክ አልባ ህይዎቱን ሰጠ! እስከ ህቅታ ታምኖ የኖረው አርበኛ ሽህ ጨለፎችን አሰልጥኖ መሪ አድርጎ ታጋዮች አድርጎ አንድያ ህይዎቱን ለአማራ ህዝብ ህልውና ሰጠ! የተሰዋህለትንና ውድ ህይወትህን የከፈልክለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም

ለተከታታይ ሁለት ቀናት በቀጠለው አውደ ውጊያ ከ35 በላይ የብልፅግና ጦር የተደመሰሰበት የ19ኛ ክፍለ ጦር አኩሪ ተጋድሎ!     ሚያዚያ:-22/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ክንፍ የሆነው 19ኛ ክፍለ ጦር በቡግና ወረዳ ከአይና እስከ ብርኮ ጉልሃ በሸፈነ የአውደ ውጊያ ቀጠና ጠላትን በመጣበት ልክ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት እንደ እብድ ውሻ እየተክለፈለፈ ወደ መጣበት እንዲመለስ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል። ከሚያዚያ 21/2018 ዓ/ም ጀምሮ የአካባቢውን ኔትወርክ በማጥፋት መነሻውን ከቡግና ወረዳ አይና ከተማ በማድረግ ወደ ብርኮና ጉልሃ አድርጎ ፋኖን አፍናለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው የብልፅግና ጦር ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ለማፈን አስቦ የሄደውን ስቦ በማስገባት ራሱ ታፍኖ ጠላት ከማጥቃት ወደ መከላከል ተሸጋግሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲቀጠቀጥ ውሎ አድሯል። በዚህ አውደ ውጊያ 35 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ20 በላይ ቁስለኛውን በሦስት አምቡላንስ ጭኖ ወደ አይና ከተማ ፈርጥጧል። የጨበጣ ውጊያው እስከ ሚያዚያ 22/2018 ዓ/ም ረፋድ 5:00 ሰዓት የቀጠለ ሲሆን ፋኖዎቹ አራት የጠላት ምሽግን በማስለቀቅ ወደ ሙሉ ማጥቃት የተሸጋገሩ ሲሆን የብርሐኑ ጁላ ጦር ይህንን መቋቋም ሲያቅተው ከብርኮ ወደ አይና ከተማ እግሬ አውጭኝ ብሎ የፈረጠጠ ሲሆን ሐሙሲት ከተማ ላይ ለጥቂት ከፋኖዎች እጅ ሊገባ የነበረውን ዙ-23 በሞርተርና በመቶ ሰባት ሽፋን በመስጠት ከሰብዓዊነት ቁስን በማስበለጥ ከ15 በላይ እስከሬኑን ሳይቀብር አንጠባጥቦ ተመልሷል። በዚህ መብረቃዊ ምት የተደናገጠው የአገዛዙ ሰራዊት በንፁሃን ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈፀመ ሲሆን ሚያዚያ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ንግስ ክብረ በዓል ወደ ብልባላ ጊዮርጊስ በእግራቸው የሚጓዙ ምዕመናንን አንድ ህፃንን ጨምሮ ሦስት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፍጭፏል፤ የአንድን ወጣት የቀኝ እግሩን በጥይት በመምታት እንዲቆረጥ በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት በንፁሃን ላይ መፈፀሙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል። አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ       ሚያዚያ:- 22/2018 ዓ/ም

በአለም አቀፍ ደረጃ ''No ballots while bullet fly" የሚል ታላቅ የሕዝብ ተቃውሞ ሰልፍ ሊካሄድ ነው! በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የድሮን ጥቃቶችን እና የአገዛዙን "የውሸት ምርጫ" (Fake Election) ድራማ ለመቃወም በተለያዩ የአለም ከተሞች ተከታታይ የሰልፍ ጥሪዎች መቅረባቸው ተገለጸ። "ዛሬ የእኛ ዝምታ ነገ የእነሱ ጉልበት ነው፤ ዛሬ የእኛ ድምፅ እነሱን የሚቀይር ነው" በሚል መሪ ቃል የሚካሄዱት እነዚህ ሰልፎች፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በንጹሃን አማራዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንዲገነዘብና አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለማሳሰብ ያለሙ ናቸው። በወጣው መርሃ ግብር መሠረት፦ • በስዊድን (Sweden): ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን (May 1) ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል። • በቤልጂየም (Brussels): ሰኞ ግንቦት 3 ቀን (May 11) የአውሮፓ ኅብረት መቀመጫ በሆነችው ብራሰልስ ድምፅ ይሠማል። • በፈረንሳይ (Paris) እና በእንግሊዝ (London): ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን (May 23) በሁለቱም ዋና ከተሞች የተቀናጀ ሰልፍ ይካሄዳል። • በጣሊያን (Italy): እሁድ ግንቦት 9 ቀን (May 17) ሰልፉ ቀጥሎ ይውላል። .  በኖርዌይ May 29 . በካናዳ ኦቶዋ May 16 እና በ Monitoba May 17 . በአሜሪካ ሲያትል May 9 ፣ እና ዲሲ May 14 በአውስትራሊያ ሜልበርን May 17 ሰልፎቹ ይደረጋሉ። አዘጋጆቹ "ለፍትሕ አብረን እንቁም" (Stand Together for Justice) በሚል ባስተላለፉት መልዕክት፣ በነዚህ ሀገራትና በአቅራቢያቸው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በነቂስ ወጥተው ለወገኖቻቸው ድምፅ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም አገዛዙ በደም የተጨማለቀ "የምርጫ ሳጥን" (Fake Election Box) በመጠቀም ዓለምን ለማታለልና ሥልጣኑን ለማራዘም የሚያደርገውን ሙከራ ለማጋለጥ ሰልፎቹ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል። የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ እነዚህ ሰልፎች በሀገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የህልውና ተጋድሎ በዲፕሎማሲው መስክ ለማጠናከር ታስበው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል።

ሰበር ዜና አምስት የአድማ ብተና አባላት መቶ አለቃውን በመሸኘት ግዙፋን ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።   አምባጊወርጊስ ከተማ መቀመጫውን አድርጎ ለአገዛዙ ወንበር  ጥበቃ ሲያገለግል ከነበረው ሀይል ውስጥ አምስት  የአድማ ብተና አባላት ስዓቱ አሁን ነው በማለት መቶ አለቃ  ምስጌ አስናቀውን   እና ሶስት አባላቱን ወደ ላይኛው ላይመለሱ  በመሸኘት ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ  የህዝብ ልጅ የሆነውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ  የዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር  ግዙፋን  ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነውን   ቴውድሮስ ብርጌድ ራስ አሞራው ውብነህ ቁጥር አንድ ሻለቃን  በመቀላቀል ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግልን የድርሻቸውን ለመወጣት ሲሉ ከአገዛዙ አሽከርነት   ወደ ፋኖ የነፃነት ተፋላሚነት  አምስት ክላሽ በመያዝ  ተቀላቅለዋል ። የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን  ራስ አሞራው ውብነህ ቁጥር አንድ ሻለቃን የተቀላቀሉ የአድማ ብተና አባለት ስም ዝርዝር 1,  ኮንስታብል ሙሉቀን ተፈራ   2,  ኮንስታብል ተመስገን ውበቱ    3,  ኮንስታብል ሀብታሙ ጌጡ   4,  ኮንስታብል የኔነህ ዋጋው   5, ኮንስታብል ፍቅሩ በላይነህ  ሲሆን በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ22 በላይ የመንግስት  የፀጥታ  አካላት  የተለያዩ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ብርጌዶችን ተቀላቅለዋል።   ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  በሚንቀሳቀስበት  ቀጠና አንዱ በሆነው   ወገራ ወረዳ ብቻ  በባለፋት ሶስት ወራት 6  ወይም ግማሽ ደርዘን  ወታደራዊ መሪዎች ላይመለሱ    የጥይት ቀለብ ሁነው ሜዳ ላይ ቀርተዋል።  የመንግስት ወንበር አስጠባቂዎች አሁን ላይ መሰልጠን ፣መታጠቅ  ከመሞት ቀድሞ  ፋኖን መቀላቀል በሚል ከብልፅግና ስርዓት  እየወጡ ወደ አፋብን ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየመጡ ነው እኛም በክብር እየተቀበልን ነው ። የአገዛዙ ወታደራዊ መሪዎች ሰራዊታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየከዳ በመቸገራቸው የተነሳ መሳሪያ እና ስልክ ቢጠረንፋም ጀግኖች ግን እነሱን እና ባንዳዎችን  እየገደሉ ፋኖን ከመቀላቀል ሊያቆሟቸው አልቻሉም። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን  !!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ ሚያዚያ 22/2018 ዓ/ም

በንጉስ ሳህለ ሥላሴ ስም የተሰየመው አዲሱ ክፍለጦር የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ሲፈፅም፣ ዕዙ ለወራት ያሰለጠናቸውን የአርበኞች ጦር ሰራዊት አስመርቆ አዲስ ብርጌድ መስርቷል። ሚያዚያ 22/2018ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆነው የንጉስ ሳህለ ሥላሴ ክፍለጦር የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው በሰላድንጋይ ከተማ ትላንት ሚያዚያ 21 ቀን 2018ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ላይ በከተማዋ አደባባይ በልዩ ኦፕሬሽን ሰርገው በመግባት በአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት ላይ በፈፀሙት የከተማ ውስጥ ጥቃት አንድ የሰራዊቱ አመራር ሲገደል፣ በውል ያልታወቁ አባላት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ኮሩ ገለፀ። በተፈፀመው የተጠና የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የተደናገጠው አገዛዝ አቶ አባየሁ ኃ/ስላሴ የተባለ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ አባላል የፋኖ ተባባሪ ነሕ በሚል ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመበት በኋላ የታሰረ ሲሆን ተጨማሪ በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ወደ እርስ በርስ ግጭት በመግባት ለእስር መዳረጋቸውን ኮሩ በመረጃው አረጋግጧል። ይህ በእንዲሕ እንዳለ በትላንትናው ዕለት የዕዙ አካል የሆነው የአርበኛ መሃመድ ቢሆነኝ ኮር ግዙፉ አስቴጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ መቅደላ ቀበሌ ላይ በአገዛዙ 102ኛ ልዩ ዘመቻ አየር ወለድ ሰራዊት ላይ የተሳካ የፈንጅ ጥቃት መፈፀሙን ኮሩ ገልጿል። በግሼ ራቤል የሰፈረው የብልፅግናው ወራሪ ኃይል በጀግናው ሰራዊታችን በተፈፀመበት የፈንጅ ጥቃት በርካታ ጉዳት ማስተናገዱን ኮሩ አክሎ ገልጿል። በሌላ የሸዋ መረጃ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአርበኞች ጦር ሰራዊት በአንኮበር ቀጠና ለወራት ያሰለጠናቸውን አንድ ሙሉ ብርጌድ በማስመረቅ "መርዕድ አዝማች አብዬ ብርጌድን" በይፋ መስረቷል። በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አንኮበር ወርዳ ሐራምባ ክላስተር ስር የነበሩ የአርበኛ ጦር ሻለቆች ወደ አንድ አደረጃጀት በመምጣት ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም መርዕድ አዝማች አብዬ ብርጌድን መመስረቱን የዕዙ የአባት አርበኞች ጦር ሰራዊት መምሪያ አስታውቋል። አዲስ የተመሰረተው ብርጌድ ስያሜውን ያገኛው በታሪካዊቷ የሐራምባ ከተማ መስራች መርዕድ አዝማች አብዬ ስም ሲሆን፣ መርዕድ አዝማች አብዬ አዲስ አበባ የነበረው የሸዋ ስልጣኔ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከፈረሰ በኃላ በሐራምባ ከተማ ቤተመንግስቱን ያደረገ 3ተኛው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት መሪ ነው፣ አብዬም የመርዕድ አዝማች ስብስቴ ልጅ ነው። በምስረታ ፕሮግራሙ ላይ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አመራሮች፣ የጣይቱ ክፍለጦር አመራሮች፣ የክላስተርና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል። በመጨረሻም በብርጌዱ ምስራታ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዕዝና የክፍለጦር አመራሮች ለብርጌዱ የአመራር ምድባና የስራ ስምሪት ሰጥተዋል ሲል መምሪያው በላከው መረጃ አስታውቋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሚያዚያ 22/2018ዓ.ም

206ኛ ኮር ከብቁ ወጣቶች ጋር !! በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም የደባይ ጠላት ግን ወረዳ ዳማ ቀጠና የወጣቶች  መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም ======================================= ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል። በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ የዳማ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን አርሶአደሩ ተሳታፊ ሁኗል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት!

"ለመብቃት መሰልጠን ለመግባባት መመካከር" አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ለተከታታይ 3ቀናት  አጠቃላይ የኮራችን ዕንቅስቃሴ ዙሪያ ተወያይቷል!! 🌲🌲🌲🌲==========🌲🌲🌲🌲 በውይይታችንም በዋናነት ⛰ የክብር ሽልማት እና የማዕረግ ስም ስያሜ ⛰ ከዚህ በፊት የመጣንባቸው የትግል ሂደቶች ከዚህ በኃላ መሆን ስላለበት የትግል ዕንቅስቃሴወች ⛰ ስለ ቀጣይ የትግል ግዳጂ ⛰ ስለ ጎንደር እንዲሁም ስለ አማራ ፋኖ አንድነት ⛰ የኮሩ የሰው ሀይል አያያዝ እና ትጥቅ አጠቃቀም ⛰ህዝብ አያያዝ እና አስተዳደር አፈጻጸም እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከድርጅት; ከዕዙ; እንዲሁም በኮሩ ስር ያሉ የሁሉንም ክፍለ ጦር አመራሮች  ማለትም 🔗 እትጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 🔗 ጋፋት ክፍለ ጦር 🔗 ጀኔራል ፈንታ በላይ ክፍለ ጦር 🔗 ፋሲል ክፍለ ጦር 🔗 ታዲወስ ታንቱ ክፍለ ጦር የክፍለ ጦር አመራሮች  እና ውስን የኮሩ ተወርዋሪ ሀይል በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል:: "የንጉሱን ለንጉሱ" መሪን እናከብራለን መሪን እንጠብቃለን መሪን እናጀግናለን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር  ለኮሩ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው ትልቅ የዕውቅና እና የማዕረግ ስያሜ ተሰጥቷል::   ፋኖ ለመሆን መለኪያ ቢኖረው ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባውን መሆን ይመስለናል። ተሾመ ማለት እውነት ነው; ቅንነት ነው; ሀቀኝነት ነው; ጀግንነት ነው; ታማኝነት ነው;  ለአላማው የመነነ ሀብቱም ንብረቱም ትግሉ ብቻ የሆነ ሁሉን ነገሩን ለአማራ ህዝብ የሰጠ እንቁ መሪያችን ነው። ጥንቅቅ ያለ የሀቅ ሰው በቃ የፋኖነት መለኪያው መመዘኛው ሚዛኑ ራሱ ነው። ታሪኩ በአጭር ጹሁፍ ለመግለጽ ይከብዳል። እንደ አማራ የገጠሙንን ፈተናወች ሁሉ ለመመከት ገና በለጋ እድሜው ከወንዱ አስቻለው ደሴ ጋር ትግል የጀመረው እንቁው ታጋይ ፋኖነትን ተወልዶበት; ፋኖነትን አድጎበት; ፋኖነትን  እየኖረለት የሚገኘው የዋሁ ገራገሩ የግዙፉ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር  ዋና መሪ  ከዚህ በፊት የተለያዩ ስሞች አንድአንዴ ሻለቃ አንድአንዴ አርበኛ እያልን ስንጠራው ቆይተናል። ነገር ግን ከሰራው ጀብድ እና ለትግሉ ካደረገው አስተዋጾኦ አንጻር የአማራ ህዝብ እና መላው ሰራዊታችን የመጠሪያ እና የማዕረግ ዕድገት እንድናደርግ ተደጋጋሚ ሀሳቦች አስተያየቶች ሲሰጡበት ቆይተዋል:: በመሆኑም ከዚህ በፊት በተለያየ ስያሜ ስንጠራው የነበረው ታማኙ የትግላችን ምልክት ከዛሬ ሚያዚያ 20/08/18 ዓ.ም ጀምሮ 🌷"ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው"🌷 ተብሎ የተሰየመ መሆኑን እንገልጻለን!! የዚህ ሀሰብ ባለቤቶች የድርጂት የዕዝ እንዲሁም የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ስራ አስፈጻሚወች እንዲሁም መላው ሰራዊታችን ምስጋና ይገባችኋል!! መሪያችን ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው እንደ እስካሁኑ በጽናት; በእምነት; በጀግንነት;በትብብር;በአንድነት;በቅንነት; ተተኪ መሪወችን በማፍራት ትግሉን ጫፍ እንደምታደርሰው እንተማመናለን:: ጠላቶቻችን ጠፋተዋል; ተበትነዋል;ፈርሰዋል;የሉም ; አይችሉም ሲሉን አይ እነ አሳምነው ጽጌ እነ አስቻለው ደሴ እና ሌሎችም በጎንደር;በሽዋ; በወሎ; በጎጃም የነበሩ እንቁ አርበኞቻችን በአጥንታቸው; በስጋቸው; በደማቸው አዋህደው ለዘላለም ላንናወጥ በጽኑ አለት ላይ የተገነባን መሆናችን ያሳየንበት ብቻ ሳይሆን ለጠላቶቻችን መራራ ኮሶ የእግር እሳት የሆንበት ጊዜ ላይ ሁነን እስከ ክብራችን አለን። እንደ ኮር ወንዱ አስቻለው ደሴ 204ኛ ኮር ብለን ስንሰይም ስንሰባሰብ ያለ ምክንያት አይደለም! አስቻለው (ገብርየ) በምርጥ ዘር ደረጃ አዘጋጂቶ ወደ ችግኝነት ቀይሮ ከችግኝ ወደ ዛፍነት ከዛፍነት ወደ ፍሬነት ተቀይሮ በዚህ ልክ ስንሰባሰብ አስቻለውነት ፋኖነት አስቻለውነት ጽናት አስቻለውነት ታማኝነት አስቻለውነት አማራነት አስቻለውነት ድል አድራጊነት አስቻለውነት እውነት አስቻለውነት ሀገርነት  መሆኑን አውቀን; ተረድተን; ተገንዝበን;  በምክንያት በስሙ ተሰባስበን ; በስሙ ተወያይተን; በስሙ ተዋግተን; በስሙ ተከብረን; በስሙም አሸናፊወች እንደምንሆን በመተማመን ነው። የአደራው የአላማው የግቡ ተሸካሚወች መላው ሰራዊታችን በህጻንነቱ በገብርየ ተኮትኩቶ ባደገው የታማኝነት የጀግንነት የጽናት ምልክታችን ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባው  የሚመራ ኮር መሆኑ በራሱ ልዩ ያደርገዋል!! በኮር ደረጃ መሰባሰባችን እንደ አማራ የገጠሙንን የህልውና ፈተናወች ሁሉ በቅርብም በሩቅም ካሉ አጋር የትግል ጓዶቻችን ጋር በፍጹም አማራዊ ስነ ልቦና; ፍቅር እና ወንድማማችነት እንዲሁም አንድነት ፈላጊነት በመላበስ እንደምንታገል ከዚህ በፊትም አሳይተናል ከዚህ በኃላም እናሳያለን እንደራጃለን! እንወያያለን! እንሰለጥናለን! እንታጠቃለን! እናሸንፋለን! አንድነታችን እያጸናን ልዩነቶችን እያጠበብን አሸናፊነታችን በቅርቡ እናውጃለን!! ድል ለአማራ ፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!!