uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 482
Obunachilar
+1124 soatlar
+887 kun
+88530 kun
Postlar arxiv
#የብልፅግና ቅሌት ሲጋለጥ!!         =================== ➱የብልፅግና እና የበአዴን ሆድ አደር ካድሬዎች በጋራ አማራን የማጥፋት ዘመቻ ተያይዘውታል።     ➱2018 ዓም በጄት ዓመት ለአማራ ክልል ወጣቶች የትምህርት መስጫ ወይም የመማሪያ ደብተሮችን በሽፋን ልባዳቸው ላይ የአማራን ብሎም የኢትዮጲያን ወግ ባህል እና ታሪክ በማበላሸት በሽፋኑ ላይ የአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችና በኢትዮጲያ 82% ኦሮሞ እንደሆነ የኦሮሞ የበላይነትን የሚያንፀባርቅ ፁሁፍና ጥቅሶችን በማተም የተንሸዋረረና የተዛባ ታሪክ ለማሥተላለፍ የተሞከረ ሲሆን     በዚህም የአማራ ካድሬና የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎች ሆን ብለው ለተማሪዎች ደብተሩ እንዲከፋፈልና ለሆዳቸው በማደር አማራነታቸውንና ኢትዮጲያዊነታቸውን በመርሳት የታሪክ ብሎም የማንነት የማጥፋት ዘመቻቸውን ተባባሪ በመሆን በተደጋጋሚ አማራን ገድለዋል።       ይህንን የተረዳው አፋብሃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ሀይለማርያም ማም ክፍለ ጦር ይህን የታሪክ ብልሽት ለማሥተካከል ማንኛው አማራ የሆነ ግለሰብ በደብተሮችና በመርጃ መሳሪያ ላይ የተሳሳት የውሸት ትርክት የያዙ መፅሃፍትንም ሆነ ደብተሮችን ገዝታችሁ መጠቀም እንደሌለባችሁና ይህንን በግድ ኢትዮጲያዊና አማራዊ ወግ ባህል እምነት ለማጥፋት የሚመጣን መንግሥትንም ሆነ ድርጂት በፅኑ መታገል ይኖርባችሁዋል በማለት ያሳሥባል።     ማሳሰቢያ:- እንደነዚህ አይነት ደብተሮችንም ሆነ መፅሃፍትን ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ማህበረሰብ እንዲሁም የት/ቤት ሱፐርቫይዘረሮች ስታሰራጩም ሆነ ሥትሸጡ የተገኛችሁ የሀይለማርያም ማም ክፍለጦር ርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሥጠነቅቃል።         💪ነፃነታችን በተባበረ ክንዳችን!!           #ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!           #ድል ለትግሉ ሰማዕት ለሆኑ ታጋዮች!!! ➱የሀይለማርያም ማሞ ህ/ግንኙነት ክፍል!!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ! መስከረም 07/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ለተከታታይ ሦስት ቀናት በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ሁሉን አቀፍ ተሐድሶ አደረገ። በተሐድሶው ላይ የተገኙት የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት ሻለቃ ያረጋል አሰፋ፣የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ፣ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ታዘበው ሻምበልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ሙሴ አያሌው ለሰራዊቱ አቅም ግንባታና ማበረታቻ የሰጡ ሲሆን ሰራዊቱም የነበሩባቸውን ጥቃቅን ክፍተቶች እንደሞሉበት ታውቋል። ጠላት ስሙ ሲጠራ የሚርበተበትለት ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ወቅቱን የዋጄ በግዳጅ አፈፃፀም የላቀ ሰራዊት እየገነባ ያለ ክፍለ ጦር ሲሆን ከተራ ተዋጊ አባል እስከ ክፍለ ጦር መሪ ቅልቅልና አዲስ አደረጃጀት በመስራት ለቀጣይ ግዳጅ በወትሮ ዝግጁነታቸው እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በዚህ ጥልቅ ተሐድሶ የክፍለ ጦሩን አመራሮች:- 1. አርበኛ ፋኖ አውራሪስ ደረሰ:- የክፍለ ጦሩ አዛዥ 2. አርበኛ ፋኖ አለምነው አበበ:- የክፍለ ጦሩ ም/አዛዥ 3. አርበኛ ፋኖ ምስጋን አበበ(ጢሞ):- ዘመቻ መምሪያ 4. አርበኛ ፋኖ ኃይሉ ታክሌ:-አስተዳደር 5. አርበኛ ፋኖ ተፈራ ካሴ:- ሎጅስቲክ 6. አርበኛ ፋኖ አምባው ነጋሽ:- አማካሪና የበላይ ጠባቂ 7. አርበኛ ፋኖ ስንታየሁ ይግዛው:- ፋይናንስ 8. አርበኛ ፋኖ ዮሐንስ ደርቤ:- የሰው ኃይል 9. አርበኛ ፋኖ ጎበዝየ አያናው:- ኦርድናንስ 10. አርበኛ ፋኖ አሻገረ ባየ:- ስምሪት 11. አርበኛ ፋኖ የፀዳው አማረ:- ህዝብ ግንኙነት 12. አርበኛ ፋኖ ሞላ ወንዴ:- የጤና መምሪያ ኃላፊ 13. አርበኛ ፋኖ 𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥:- መረጃና ደህንነት 14. አርበኛ አታለለ መላሽ:- ስልጠና መምሪያ አድርገው በመምረጥ በሰራዊቱ ፊት ቃለ መሃላ በመፈፀም ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 07 / 2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ንጉስ ሚካኤል ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከላላ ወረዳ ላይ ጀብድ በመፈፀም ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሸዋንግዛው ክፍለጦር ከከላላ ወደ ቲርቲራ ሲንቀሳቀስ የነበረ ጥምር የጠላት ሃይል ላይ ደፈጣ በመያዝ ውጊያ በመክፈት እስከ አስር የሚደርስ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: ከአዲስ አመት መባቻ ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ተጋድሎ እያደረገ ያለው ሸዋንግዛው ክፍለጦር ዛሬ መስከረም 7/2018 ዓ.ም ማለዳ 12:00 ላይ ከቲርቲራ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ አቦል ሻለቃ ጠላትን አንገት አስደፍተው ድል ተቀዳጅተዋል:: በዚህ የደፈጣ ጥቃት የተበሳጨው የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር ማለዳ ወደ መስጊድ ይሄድ የነበረን ወጣት መረጃ ሰጥተህ አስጠቅተኸናል በሚል የውሸት ሰበብ በግፍ ረሽነውታል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 7/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ሕዝባዊ ውይይት በደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ በሚያስተዳድረው ቀጠናዎች ተከታታይ ሕዝባዊው ይይቶችን እያደረገና
+4
ሕዝባዊ ውይይት በደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ በሚያስተዳድረው ቀጠናዎች ተከታታይ ሕዝባዊው ይይቶችን እያደረገና እየመከረ  ከማህበረሰቡ ጋር እየመከረ ይገኛል። በዛሬው እለትም የደጎልማ ቀበሌ  ነዋሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የሕልውና ትግሉ አሁን ላይ የደረሰበትን የእድገት ደረጃና በቀጣይ ስለ ሚፈልገው ጉዳይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን  በመልካም አስተዳደር ዙሪያም ከሕዝቡ ጋር ውይይት ተደርጓል። ድል ለሕዝባችን! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎የከሰም ክ/ጦር ተስፋ ብርጌድ እሬሽን እና የወረዳ ባለስልጣን ለመቀባበል በተንቀሳቀሰ የመከላከያ ኃይል ላይ እርምጃ ወሰደ ‎============ ‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክ/ጦር የተስፋ ብርጌድ ባህር ዳር ስብሰባ ቆይተው የመጡ ባንዳ የበረኸት ወረዳ የብልጽግና አመራሮችን ወደ መተህብላ እንዲሁም ከመተህብላ ወደ ደብረ ብርሃን ለስብሰባ የሚሄዱ ካድሪዎችን ለመቀባበል በተንቀሳቀሰ የመከላከያ ኃይል ላይ እርምጃ በመውሰድ ባለበት እንዲቆም አድርጓል:: ‎ ‎ይህ የጥፋት ኃይል 2ዙ 23 ሞርታር እና በርካታ ዲሽቃዎችን ይዞ እሬሽን እና ካድሪ ለመቀባበል ቢንቀሳቀስም በተስፋ ብርጌድ በአክርሚት እና ተሬ በተባሉ ቦታዎች በተወሰደበት እርምጃ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት ለመመለስ ተገዷል:: ‎ ‎የአፋብኃ ከሰም ክፍለ ጦር ተስፋ ብርጌድ ከምንጃር አረርቲ ከተማ መስከረም 7/2018 ዓ ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እሬሽን እና የበረኸት ወረዳ ካድሪዎችን ለማቀበል የተንቀሳቀሰው 21ኛ የብርሃኑ ጁላ ክፍለጦር አክርሚት በተባለ ልዩ ቦታ በተወሰደበት እርምጃ ከባድ የሚባል ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አስተናግዷል:: ‎ ‎በተመሳሳይ መቀመጫዉን በረኸት ወረዳ መተህብላ ከተማ ያደረገዉ 84ኛ ክፍለጦር የብርሀኑ ጁላ ግሪሳ የጥፋት ቡድን ተሬ ላይ በተወሰደበት እርምጃ ቁስለኛውን እና አስከሬኑን ይዞ ወደ መጣበት ተመልሷል:: ‎ውጊያው ለሰዓታት ቆይቶ የጥላት ኃይል የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት ወደኋላ የተመለሰ ሲሆን ከውስጥ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጨማሪ የመከላከያ ሀይል ካልተጨመረ መንቀሳቀስ አንችልም ማለታቸውን ሪፖርተራችን ቦጋለ ምንዳ ከቦታው አድርሶናል። ‎ ‌‎     " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል መስከረም 07/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ከቤተ-መንግሥት የተወሰደብህን ጫካ ሁነህ አታስመልሰውም ጫካ ገብተህ እንጂ:: ጫካ መደራጂያ መሰልጠኛ ሃይል መሰብሰቢያ ጉልበት መፍጠሪያ እና የራስህን የትግል መንገድ ፍኖተ ካርታ መቅረጪያ እና መታገያ እንጂ እንደ ሃገር የተፃፈን ህግ ተነጋግረህ አቅደህ መቅደጂያም መፃፊያም ወንበርና እስክሪብቶ በዛ የለም፡፡ በዛ ያለው ዓላማ :ለመታገል ራሱን በዓላማ ያዘጋጀ ኀይል እና ነፍጥ ብቻ ነው። የወልቃይትም የራይም የደራም የመተከልም ሆነ የአዲስ አበባ ርስትህንና ማንነተህን የተገፈፍከው ጫካ በነበረ ፍላጎት እና ጫካ በተወለዱ ኀይሎች ግን ታግለው ቤተ መንግሥት በደረሱ የጫካ ኀይሎች ነው። ጫካ የበደል እና የብሶት ጥያቄዎች መፀነሺያ ሃይል ማሰባሰቢያ መሰልጠኛ እና መታገያ ስፍራ እንጂ ህግ መሻሪያ እና ማፅደቂያ ስፍራ ሊሆን አይችልም፡፡ ሌላው ህዝብ ሊያውቀው የሚገባው እውነት ከብአዴን ጋር ተለጥፎ የሚመለስ የትኛውም የአማራ አፅመ ርስትም ጥያቄም የለም፡፡ ምክኒያቱም ብአዴን ለአማራ ህዝብ እንጂ መንግሥት ለፌዴራሉ መንግሥት ሎሌ ነው። ሎሌ መጫን እንጂ ለህዝብ የመታገል ስነልቦናም የለውም፡፡ ስለሆነም ብአዴን ደምህንና አጥንትህን አብዝቶ የሚፈልገው ለስልጣኑ ማቆያ እንጂ ርስትህን የማስመለስ ምንም ፍላጎትም አቅም የለውም፡፡ ብአዴን ፍላጎትም አቅምም ቢኖረው ኖሮ ቅድሚያ የራያንም የወልቃይትንም የደራንም ሆነ የመተከልን ግዛቶች በፌዴራሉ ህገ መንግሥት እንኳ ማድረግ ባይችል በራሱ ክልል ህገ መንግሥት ላይ የአማራ ግዛት እንደሆኑ በማድረግ የህገ መንግሥት ማሻሻያ ያደርግ ነበር፡፡ በክልሉም ሆነ በፌዴራሉ የህገ መንግሥት ማሻሻያ ሳታደርግ ለወልቃይት ሆነ ለራያ እታገላለሁ ብትል የአገኘው ተሻገር መስሪያ ቤት እንዳለህ የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ በህገ መንግሥት ይታይ ሲልህ አንተም የዋህው ወገኔ እሺ ብለህ ህገ መንግሥት መግለጥ ስትጀምር የክልሉም የፌዴራሉም ህገ መንግሥት የሚልህ ወልቃይት እና ራያ የትግራይ ደራ እና አዲስ አበባ የኦሮሚያ መተከልን የቤኒሻንጉል ነውና አርፈህ ተቀመጥ ትባላለህ። ያኔ ሌላ ሮሮ ነው ወንድም አትልፋ ከብአዴን ጋር ተሰልፈህ የአማራን ጥቅም አታስከብርም ሎሌነትህን በደምህ ታረጋግጣለህ እንጂ፡፡ ደግሞ ለማስታወስ ያህል የርስት እና የማንነት ጥያቄዎች ያሉን ከትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ክልልም እንዳለን ሳንዘነጋ ለሁሉም እኩል ትኩረት መስጠት ይኖርብናል፡፡ በመጨረሻም ወልቃይትም ራያም መተከልም ደራም አዲስ አበባም እኩል የትግል ቀይ መስመሮቻችን ናቸው። አንዱ ከአንዱ አይበልጥም ሌላው ከሌላኛውም አያንስም፡፡ ጀግናው የበርኃው ጓዴ ስንቱዬ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

#ከአማራ ክልል 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች 21% ብቻ ተመዘገቡ‼️ ትምህርት ቤቶች በድሮን እና በፋሽስቱ አገዛዝ ወታደሮች ወድመዋል፣ የተረፉት የኦህዴድ ስልጣን ጠባቂ መንጋ ሰራዊት ካምፕ ሆኖ እያገለገለ ነው። የአምሓራ ጀኖሳይድ አካል የሆነው ትውልድን •ከትምህርት •ከኢኮኖሚ እና •እርስቱ የመግፋት አሻጥር እና የፋሽስታዊ አገዛዙ የደባ ጉዞ ማሳያው ይህ ሪፖርት ነው። በ #አማራ ክልል ይመዘገባሉ ተብሎ ከሚጠበቀው የሁለተሻ ደረጃ ተማሪዎች መካከል የተመዘገቡት 21% የሚሆነው ብቻ ናቸው - የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአማራ ክልል ይመዘገባሉ ተብሎ ከተጠበቀው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የተመዘገቡት 21% የሚሆነው ብቻ መሆናቸውን የክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ምንም እንኳ በክልሉ 7.4 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመዝገብ የተማሪዎች ምዝገባ ባሳለፍነው ዓመት ነሃሴ 19 ቀን በይፋ ቢጀመርም እስከ መስከረም ሁለት ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተመዘገቡት ሶስት ሚለየን እንደማይሞሉ ተገልጿል። የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፤ “መንግስትም ይሁን የትኛውም አካል ትምህርትን ከፖለቲካ ነጻ አድርጎ ትምህርት ቤቶቻችንን እና የትምህርት ስራዎቻችንን እንዲተውልን አደራ እላለሁ” ብለዋል። “እንደ ሀገርም እንደ ክልልም ትልቅ ጉድለት ያየንበት የሁለተኛ ደረጃ እና የፀጥታ ችግር ያለባቸው አከባቢዎች ናቸው፤ እነሱም ላይ ከአምናው የተሻለ ለውጥ ይኖራል ብለን ነው የምንጠብቀው” ሲሉም ጠቁመዋል ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሚሊሻም ፋኖም መሆን አይቻልም አንዱን ምረጡ፡፡ እኔ ፋኖ ነኝ ግን ሚሊሻውን ወንድሜ ለምን ትነካብኛለህ ማለት ኖ አይሰራም፡፡ ፋኖ ከሆንህ ሚሊሻው ጠላትህ ነውና ጥላው። 1 በግ + 1 ፍየል= 1 በግ
ሚሊሻም ፋኖም መሆን አይቻልም አንዱን ምረጡ፡፡ እኔ ፋኖ ነኝ ግን ሚሊሻውን ወንድሜ ለምን ትነካብኛለህ ማለት ኖ አይሰራም፡፡ ፋኖ ከሆንህ ሚሊሻው ጠላትህ ነውና ጥላው። 1 በግ + 1 ፍየል= 1 በግ X 1 ፍየል= 1 በግ ፥ 1 ፍየል = 1 በግ - 1 ፍየል = ተመሳሳይ ያልሆኑ ማናቸውም ነገሮችን በየትኛውም የሂሳብ ስሌት ውጤት እንደማይሰጡን ሁሉ ሚሊሻና ፋኖም ተደምረውም ተቀንሰውም ተካፍለውም ሆነ ተባዝተው የሚሰጡት ምንም ውጤት የለም ፡፡ ሌላው ለሚሊሻ የዚህን መንደር ንኩ የዛኛውን መንደር አትንኩ በሚል አንዱን እርኩስ ሌላውን ቅዱስ ለማድረግ ደረጃ ስላላወጣን እስክናወጣ ድረስ ሁሉም እርኩሶች ናቸው እና ጠላቶቻችን ስለሆኑ አበላልጠን እርምጃ አንወስድም፡፡ በተደጋጋሚ ተናግረናል ወንድማዊ ጥሪም አድርገናል አሁንም ወደነሱ ከመሄዳችን በፊት ቀልብ ገዝተው ከተመለሱ አክብረን እንቀበላቸዋለን፡፡ አልያ እንቢ ብለው ሰልፍ ከለዩ እናጠፋቸዋለን፡፡ ሌላው የወልቃይትም ሆነ የራያ የማንነት እና የርስት ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት ራያ ላይ ወይም ወልቃይት ላይ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈህ ስለተጋደልክ ሳይሆን ሥርዓቱን ወዲያ ጥለህ ራስህ መንግሥት መሆን ስትችል ነው። ምክኒያቱም *ጉልበት ሲኖርህ የአለም ህጎች ሁሉ በእጅህ ያፃፋሉ የተፃፉትም ይቀደዳሉ*፡፡ መንግሥት ለመሆን ታገል፡፡ °° የመዳን ቀን ዛሬ ነው። °° መዳን ከፈለክ ናና ፋኖ ሁን:: °° እንዲድንልህ ከፈለክ ፋኖ እንዲሆን አድርገው። * ክብር ለፋኖ * ክብር ፋኖ ሆነው ውድ አካላቸውን አጥተው በየቤታቸው ተቀምጠው ድል ለሚናፍቁ * ክብር ፋኖ ሆነው ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ቀን08/01/2018 ዓም ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን‼️ 👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ለዚህ ነው፤እስርቤት በሚገኙ፣ጫካ ባለነው እና አገር ጥለው በተሰደዱ ሐቀኛ ጋዜጠኞች የምኮራው!!! ጋዜጠኝነት ማለት ባጭሩ፦ እራስን አደጋ ላይ ጥሎ፣ለድምፅ አልባዎች ድምፅ መሆን ነው። ሕግ አውጭው (ፓርላማው)፣አስፈፃሚው (የሚንስትሮች ምክርቤት በዋነናነት /ጠ/ሚንስትሩ) እና ተርጓሚው (ፍርድ ቤቶች በዋናነት ጠ/ፍ/ቤቱ) በአጠቃላይ መንግስት በአግባቡ፣ ግልፀኝነትን እና የሕግ ተጠያቂነትን አካቶ ለሕዝብ አየሰራ መሆኑን የሚከታተል ነው። ታንኩን(ወታደሩን)፣ባንኩን(ኢኮኖሚውን)፣ መረጃና ደህንነቱን እና በአጠቃላይ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት አካላት(Monopoly of Power) ያላቸው በስልጣን እንዳይባልጉ፣ ዜጎችን፣በዜግነታቸው ብቻ በዕኩልነት እያመሩ መሆናቸውን የሚከታተል፤ ድሆችን(ድምፅ አልባዎችን) ስልጣናቸውን ተጠቅመው እንዳያንገላቱ የሚመለከት፤ለሕዝብ ቃል የገቡትን በአግባቡ አየፈፀሙ መሆኑን የሚከታተል፤የመንግስት አካላት እና ተቋማት በስልጣን ባልገው የአገርን ብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት እንዲሁም ሕዝብን እንዳይጎዱ መከታተል እና ባልገው ሲገኙ ደግሞ የሕግ ተጠያቂነት በአስቸኳይ እንዲሰፍን፣በቁርጠኝነት ዘብ(watchdog) ሆኖ 24/7 ካሜራውን፣የሰላ ብዕሩን እና ዓንደበቱን ከአገር እና ሕዝብ ጥቅም ላይ የማይነቅል ነው።(ይህንን በማድረጉ ደግሞ በአምባገነኖች ለሚደርስበት ማንኛውም የአካል፣የሥነልቦና እና የአዕምሮ ጉዳት ራሱን ያዘጋጀ ነው።) እንጂ፣በንፁሃን ደም የጨቀዩ እጆችን የሚልስ፤በድሆች እንባ የቆሸሹ እጆችን የሚያፀዳ፤በገዛ ዜጎቹ ላይ በመወስለት የከረደደን እጅ የሚያለሰልስ፤የአገሩን ሕዝብና ብሔራዊ ጥቅም ለስልጣኑ ሲል አሳልፎ የሸጠን ይሁዳ እጆች የሚሳለም፣በወንጀል የቀለለን አምባገነን ለሕግ እንዲቀርብ ከመስራት ይልቅ ዝቅ ብሎ ማንገስ፤የሕዝብንና የአገርን ጥቅም፤ሙያዊ ሥነ ምግባር በማይፈቅደው ሁኔታ ከርስን ለመሙላት ሲባል የሚደረግ ስናዳሪያዊነት አይደለም፤ጋዜጠኝነት። ክብር በጫካ እና በእስር ላሉ ጋዜጠኞቻችን!! የክርስቲያን ታደለ የህክምና መብት ይከበር!! CPJ HUMAN RIGHTS WATCH AMNESTY INTERNATIONAL UN HUMAN RIGHTS COMMISSION where are you??? ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከግንባር ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ከወሎ ቤተ አምሓራ ሰማይ ስር የምኒልክ ዕዝ ኮማንዶ ዳንኤል አለሙ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ተቋም መምህር የሆነው ኮማንዶ ኩራት ተስፋዬ #ምኒልካውያን ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተ
ከወሎ ቤተ አምሓራ ሰማይ ስር የምኒልክ ዕዝ ኮማንዶ ዳንኤል አለሙ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ተቋም መምህር የሆነው ኮማንዶ ኩራት ተስፋዬ #ምኒልካውያን ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አንዳንድ ነጥቦች:- ከአገዛዙ ወገን የሆነ ሁሉ የፋኖና የአማራ ሕዝብ ጠላት ነው፣ ጃራ ካምፕ ላይ የነበሩትም በአገዛዙ በጀት ሲሰለጥኑ የነበሩ የሰሜን ወሎ ዞን ሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ አ
አንዳንድ ነጥቦች:- ከአገዛዙ ወገን የሆነ ሁሉ የፋኖና የአማራ ሕዝብ ጠላት ነው፣ ጃራ ካምፕ ላይ የነበሩትም በአገዛዙ በጀት ሲሰለጥኑ የነበሩ የሰሜን ወሎ ዞን ሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ አባላት ነበሩ። ፋኖ ኦፕሬሽን ሲሰራ እንዳይሆኑ ሆኑ በመቀጠል በነ ዋርካው ምሬ ወዳጆና ጓዶቹ ቂም ይዞ የነበረው የሚሊሻና የአገዛዙ ስልታዊ ደጋፊ እየዬ እያለ ነው። ባለሽርጡ ሸጋው እንድሪስ ጉድሌም 2:35 በፈጀ ውጊያ ኦፕሬሽን ሙሉ ለሙሉ ለወሪ ነጋሪ ሳያስቀር ለቀማቸው በመቀጠል ምን ሆነ በፋኖ ደጋፊዎች መካከል ደስታ በአገዛዙ ስልታዊ ደጋፊዎች፣ በሚሊሻ ልጆች፣ ዋርካው ምሬ ወዳጆን ስሙን ያጠፋን የሚመስላቸው አንዳንድ ለቀስተኞች እየዬ ይላሉ። የሆነው እንደዚህ ነው። የአርበኛ አበበ ፈንታውን አባት የገደሉት ሚሊሻ መሆናቸውን እናስታውሳችሁ እንዴ፣ የአርበኛው አባት ሲገደሉ አንድ ነጠላ መስመር ያልጻፈው ሁሉ ዛሬ “የራያ ሚሊሻዎች አለቁ” ቢል የሚሰማው የለም ምክንያቱም ሚሊሻ ዘመድ የለውም። ከመከላከያ በላይ 8ሺ ብር እየተከፈለው ሲሰለጥን የነበረው ለሕውሓት ነው አትለኝም፣ ሕውሓትንማ ብአዴን ጋር እየሰራች ነው፣ የራያ አማራዎችን በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ማነው? ብአዴን አይደለም? ቀልደኛ ሁላ! አማራ አሁን ላይ የሚሊሻ ዘመድ የለውም! ለማንኛውም እነ አረጋ ከበደ ቀንድ አውጣው ባህርዳር ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ተቀምጠው ነበር፣ ዝርዝሩን ይዤ እመለሳለሁ። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እስከምመጣ ሙሉ አማራ ይደረሰው ዘንድ ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አብይ አህመድ ኮሚቴ ሆኖ ያሰራው የአኖሌ ልበወለድ ሃውልት በተግባር የሚቆም ህያው ሀውልት አስርክክቦናል‼️ የአኖሌ ትርክት በርካታ አማሮችን አስጨፍጭፏል፣እጅና እግራቸውን አስቆርጧል፣ጡት አስቆርጧል‼
አብይ አህመድ ኮሚቴ  ሆኖ ያሰራው የአኖሌ ልበወለድ ሃውልት በተግባር የሚቆም ህያው ሀውልት አስርክክቦናል‼️ የአኖሌ ትርክት በርካታ አማሮችን አስጨፍጭፏል፣እጅና እግራቸውን አስቆርጧል፣ጡት አስቆርጧል‼️ ለዚህም በርካቶች አካለ ጎደሎ ሁነው በየቤታቸው ተቀምጠዋል፣የታገቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጡታቸው ተቆርጦ አዲስ አበባ መንግስት ከተርከባቸው እና አስለቅቀናል ካለ በኋላ የህዝብ ለህዝብ ፍጅት ያስከትላል ተብሎ መገደላቸው ይታወቃል‼️ እንድ ቀን እውነቱ መውጣቱ አይቀርም❗️ እነዚህ ምስሎችም ህያው ምስክር ናቸው፣በአጭር ግዜ እንዲህ አይነት ነበልባል ትውልድ ከመጣ ይህን እያየ ያደገ ወደፊት ምን አይነት የአማራ ትውልድ እንደሚመጣ መገመት አይከብድም‼️ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

" ለሁሉም ጊዜ አለው"…! ይላል መፅሃፉ:~ ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው ~ ~ ~ ~ አማራ አራት ኪሎ የሚገባበትን "4" ወርቃማ እድሎችን አጋጥመውታል።"3" ቱን እድሎችን በአግባቡ ሳይጠቀም በመቅረቱ ላለበት ችግር አስተዋፅኦ አድርጓል እያንዳንዱ እንድል በማባከናችን ግፉ እና መከራው እየጨመረ ሄደ። አሁን 4ተኛው እድል ላይ ነን።በጣም ወርቃማው እድል ነው። ይህ ጊዜ:- ሁለት ነገሮችን በአማራ ህዝብ ላይ ያመጣል 1/ ከተጠቀምንበት የአማራ ታሪክ "መታጠፊያ ነው" 2/ ካልተጠቀምንበት የአማራ "መጥፊያ ነው" ከትግሉ አንዱ ስልት "ጊዜን አጥንቶ" በጊዜው ሁኔታ ያሉትን እድሎች ሳይሸራርፉ መጠቀም ነው። ከብዙ ህዝባዊ አመፆችን እንደነረዳነው "ኔፓልን" ጨምሮ ጊዜን በፍጥነትና በአግባቡ መጠቀም አሸናፊ ያደርጋል በእኛ አገር አንድ አባባል አለ" ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው"~ የሚል።ይህ የትግል ውጤታማነት መቼ እንዴት እንደሆነ ይናገራል የብልፅግና መንግስት መጀመሪያ አካባቢ" የጋለ ብረት ነበር"…በዚህ ጊዜ ቀጥቅጠነው ውጤታማ ነበርን አሁን ግን እርስ በርስ ሽኩቻ፣መሪ ባለመምረጥ፣ድርጅት ባለመመስረት ምክንያት ይህ ግሎ የነበረው ብልፅግና "ቀዝቅዟል"… ለአብይ ጊዜ በመስጠታችን ሶስት ነገር እንዲያገኘ ሆኗል 1/ ያለቀበትን መከላከያ፣ልዩሃል፣ሚኒሻ፣አድማ ብተና እንዲያሰለጥን ቦታም፣ጊዜም፣ሰውም ጊዜ አገኘ 2/ የፋኖ መሪዎችን ፣ተዋጊዎችን ዘልቆ ገብቶ እንዲጠልፍ ጊዜ አግንቷል 3/ ለትግል ከፍተኛ ስሜት የነበረውን ህዝብ እንዲያቀዘቅዘው ጊዜ ሰጥተነዋል ይህንን ሁኔታ መገልበጥ ይቻላል እንዴት?? በቻልነው መጠን፣ባለን መሳሪያ ሁሉ ያለማቋረጥ ትንሽም፣ትልቅም የተጠና ጥቃት በጠላት ላይ ማድረግ ተኝቶና ኬላ ጥሎ የሚኖር ብርጌድ አደለም፣አንድ ፋኖ መኖር የለበትም። በጣም መፋዘዝ፣መዘናጋት፣ማኩረፍ፣ትግል ማቆም ታይቷል ይህንን ህዝብ አንቀሳቅሳችሁ ለዚህ ትግል ማብቃታችሁ መልካም ታሪክ ሰርታቹሃል ደግሞ መልሶ እንዲቀዛቀዝና ጠላት ሃይል እንዲያገኝ አድርጋችሁ ትግሉ ከተጠለፈ ወይም ከተኮላሸ "በዚህ የፋኖ ትግል ውስጥ ያላችሁ የፋኖ አመራሮች ሁሉ የአማራ የምንጊዜም ጠላት!…ተብላችሁ ትመዘገባላችሁ"…አስቡበት ለማለት ነው።በስራችሁ ያለውን ሃይል በአግባቡ ተጠቅማችሁ አታግሉት። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

"በሀረር እና አርሲ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አምሓራ ነው" የሚል የተሳሳተ አረዳድ አለ። እናም ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ኦሮሞዎችም በኢላማነት እየተገደሉ ነው። «በአርሲ_የእልቂት_ድግሱ_በአዲሱ
"በሀረር እና አርሲ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አምሓራ ነው" የሚል የተሳሳተ አረዳድ አለ። እናም ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ኦሮሞዎችም በኢላማነት እየተገደሉ ነው። «በአርሲ_የእልቂት_ድግሱ_በአዲሱ_ዓመትም_አንድ_ብሏል!» -እናት ፓርቲ ሰኞ፣ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሮቤ ወረዳ ቤተክህነት በእንዴቶ 01 ቀበሌ ከሌሊቱ 5፡00 ሃይማኖትን መሠረት ባደረገ ጭፍጨፋ 2(ኹለት) ሰዎች የተገደሉ ሲኾን ሦስተኛው በሞትና በሕይወት መሐል ነው። ከሞቱት መሐል የ 65 ዓመት የሀገር ሽማግሌ አቶ ከበደ ማሞ እና ያለአባት የሚያሳድጓቸው ኹለት ልጆች እናት የኾኑት ወ/ሮ አበሬ ስዩም ናቸው። በሞትና ሕይወት መሐል ያለው የ14 ዓመት ታዳጊ የሟች ወ/ሮ አበሬ ልጅ መኾኑን ማረጋገጥ ችለናል። በአርሲ ሮቤ የዜጎች ዕጣ ፈንታ ሞት፣ ስደት፣ የንብረት መዘረፍና መውደም ኾኗል የሚሉት ነዋሪዎችበገጠር የሚኖሩ ወደ ከተማ ተሰደዋል፤ መሬታችንንም ማረስ አልቻልንም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች። ፓርቲያችን የንጹኃንን ተደጋጋሚ ግድያ በጽኑ ያወግዛል። ወዲኽም መንግሥት ሕዝቡን የመጠበቅ ሥራውን ከዘነጋው ሕዝቡ ራሱን እንዲከላከል መፍቀድ ይኖርበታል።  ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ መስከረም ፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk