uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 664
Obunachilar
+2024 soatlar
+3787 kun
+1 08530 kun
Postlar arxiv
የደረስንበት ደረጃ የመጣንበትን የትግል መንገድ ውጣውረድ ሁሉ በሚገባ ላይገልፀው ይችላል። ያለምንም ማቅማማት ግን ህዝባችንን ከየትኛውም ጥቃት መከላከል የሚያስችል የኃይል ግንባታ ላይ የተሳካ ሚናን
+1
የደረስንበት ደረጃ የመጣንበትን የትግል መንገድ ውጣውረድ ሁሉ በሚገባ ላይገልፀው ይችላል። ያለምንም ማቅማማት ግን ህዝባችንን ከየትኛውም ጥቃት መከላከል የሚያስችል የኃይል ግንባታ ላይ የተሳካ ሚናን ተወጥተናል። በዚህ የኃይል መደርጀት ውስጥ የጠላትን ወ ገብ አገ-ዳው ላይ ተሰ ብሮ እንዲ ልወሰወስ ካደረጉት ፊታውራሪዎቻችን፣ የብሬኑ ቄስ፣ በጣት የሚቆጠር ኃይል እየመራ ሙሉ ክፍለጦር እንደቤርሙዳ ዋጥ አርጎ ያስቀረ፣ የዲሽቃ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ክምር እና ዙ-23 ማርከህ ያሳየኸን፣ ንግግር አዋቂው፣ የውትድርና አቅም ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውንም በቅጡ የተረዳ፣ የትግሉ እርሾዎችና ወጋግራዎች ውስጥ አንዱ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ነው። ‎ ‎ሁለንተናዊ ከትላንት የተሻለ አቅምን እየፈጠርን ወደፊት ለምናደርገው ፈጣን ግስጋሴ አብረን የመከርንባቸውን እያንዳንዷን ሰከንድ ሁሉ ደስ የሚሉኝ ናቸው። ከዚህ የተሻሉ ተአምራዊ ትዕይንቶችን ከአንተ እንጠብቃለን። ‎ ‎ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል መወለድህን አትርፈንበታልና በድጋሜ እንኳን ተወለድህ ወንድሜ! የትግልህን ፍሬ ለማየት ያብቃህ!

♦በእነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች ለጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል። እነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ (23) በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የመናገር እና አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውን ተጠቅመው የፍትህ ሂደቱን እና በተከሳሾች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል በዳኞች ፊት በመግለጻቸው ጉዳዩ ከችሎት መድፈር ጋር ተያይዞ በፕላዝማ እንዲከታተሉ ከተደረገ ወራት ተቆጥሯል። በዚህ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግስትና የፀረ ሽብር ችሎት ውሳኔ ቅር የተሰኙት ተከሳሾች በአካል በችሎት እና በዳኞች ፊት ተገኝተን የፍትህ ሂደቱን ልንከታተል ይገባል በማለት በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለታቸው እና ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወቃል። የካቲት 12/2018 በነበረው የፕላዝማ ችሎትም ይግባኝ ሰሚ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ እና የግራ ቀኙን ክርክር መመርመሩን አስታውቋል። በዚህም መሰረት የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ከማድረግ አልፎ ነተከሳሾች ጉዳይ ከችሎት መድፈር ጋር መያያዙ ካልሆነ በስተቀር በቴክኖሎጅ እየታገዙ የፍትህ አገልግሎቱን ከማሳለጥ አንጻር የተያዘ አቅጣጫ በመሆኑ በዛው በፕላዝማ ችሎት መቀጠላችሁ አግባብ ነው ሲል መወሰኑን አስታውቋል። ተከሳሾች በውሳኔው ቅር መሰኘታቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ምንጫችን እንደገለጹት ውሳኔው አገዛዙ ከለመደው ድምፅን የማፈን መመሪያ ፣ አቅጣጫ እና አቋም ጋር ተያይዞ እና ተመሳስሎ የተሰጠ ብይን ነው ብለው እንደሚያምኑ ለማወቅ ተችሏል። በእለቱ ከተከሳሾች መካከል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በፍ/ቤቱ ውሳኔ ቅር መሰኘቱን በመግለጽ በታሪክ ፊት እንገናኛለን ማለቱን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል። በዚሁ መዝገብ ተከሰው ጉዳያቸውን በቂሊንጦ እና በቃሊቲ ማ/ቤት ሆነው እየተከታተሉ ከሚገኙ 23 ተከሳሾች መካከል ጥር 28/2018 በተሰጠው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ብይን ከሶስት ዓመታት ገደማ የእስር ቆይታ በኋላ ስድስቱ በነጻ ሲሰናበቱ የሁለት ተከሳሾችን አንቀጽ መሻሻሉ ይታወቃል። ይሁን እንጅ 15 የሚሆኑ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ተወስደው በግፍ እስር ከከረሙት ተከሳሾች መካከል 15 የሚሆኑትን ከ15 ዓመት ጀምሮ እስከ እድሜ እና ሞት በሚያስፈርድ የሽብር አዋጅ አንቀጽ 3 (2) ሳያሻሽል ተከላከሉ ማለቱ የፍትህ ተቋማት ምን ያህል የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የጥላቻ እና የማጥቂያ መሳሪያ መሆናቸውን በግልጽ ያመላከተ መሆኑ ተገልጧል። (አውሎግሶን አንድነት )

ፋኖ በመርሀቤቴ ግንባር ሬማ ከተማ አከባቢ በነበረ የአገዛዙ ኃይል ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ ወታደሮች ተገደሉ! በዚኸው ቀጠና ከፋኖ እርምጃ የተረፉ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን
ፋኖ በመርሀቤቴ ግንባር ሬማ ከተማ አከባቢ በነበረ የአገዛዙ ኃይል ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ ወታደሮች ተገደሉ! በዚኸው ቀጠና ከፋኖ እርምጃ የተረፉ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ፋኖን መቀላቀላቸውን የመረብ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል። ከሬማ ከተማ በቅርብ ርቀት ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ነው ፋኖ ዛሬ ማለዳ ጀምሮ የአገዛዙ ወታደሮችን 360° በመከበብ ከባድ እርምጃ የወሰደባቸው። ፋኖ የአገዛዙ ወታደሮች የሰፈሩበትን ካምፕ ጥሶ በመግባት በሚፈፅመው ጥቃት፡ እራሱን ተከላክሎ ማዳን ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል የአፈሙዝና የቦምብ ሲሳይ ሆኖ እየቀረ ይገኛል።

አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ሳንቃ ከተማ ዙሪያ በርካታ የጠላትን ሰራዊት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ከገዶበር እስከ ሳንቃ መግቢያ ወጥሮ አመራር ለማሳለፍ ያሰበን በርካታ የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ማጥቃት በማድረግ ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በተጋድሎው የአሳምነውን ልጆች ክንድ መቋቋም ያቃተው ጠላት በርካታ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ ቦታውን አስረክቦ ወደ ወልድያ ከተማ ለመሸሽ ተገዷል:: የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ባለፈው ጊዜ እዚሁ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ ጊዜ ተደምስሶ ዙ23 ጭምር መማረኩ ይታወሳል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 12/2018 ዓ.ም

አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ 10 የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ‼️ የምህረት አዋጁን በመጠቀም የካቲት 10 እና 11/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለ
+2
አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ 10 የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ‼️ የምህረት አዋጁን በመጠቀም የካቲት 10 እና 11/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት 10 የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነውን ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላትም እየፈረሰ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከ803ኛ ኮር 12ኛ እና 61ኛ ክፍለ ጦር በመውጣት አስር ጥቁር ክላሽ፣2100 የክላሽ ተተኳሽ፣18 የእጅ ቦምብ፣ 24 የክላሽ ካዝና፣ 16 የደረትና የወገብ ትጥቅ ይዘው ተቀላቅለዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ቃል አቀባይ አርበኛ የፀዳው አመረ መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 12/2018 ዓ.ም

መዋሸትና ማጭበርበር፣ ንፁኋንን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደልና ማፈናቀል፣ ፅንፈኝነትና ጦረኝነት ሁነኛ መገለጫው የሆነው የብልፅግና ቡድን ዙፋኔን ይጠብቁልኛል ያላቸው ወታደሮቹ ልክ እንደ እምቧይ ካብ እየተናዱ ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል። በአራቱም የአማራ ቀጠናዎች ያለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ110 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን መረብ ሚዲያ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል። "በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ ከዚህ ሰው በላ አገዛዝ ጋር ተሰልፋችሁ የገዛ ወገናችሁን ስትጨፈጭፉ የነበራችሁ ወታደሮች ከአሁን በኋላ የአገዛዙ ሴራና የጥፋት መንገድን በውል ተረድታችሁ ፋኖን ተቀላቀሉ" በሚል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ያቀረበውን ጥሪ የአገዛዙ ወታደሮች በደስታ ተቀብለው የቻሉ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው፡ ትጥቃቸው ተጠርንፎባቸው መያዝ ያልቻሉ ደግሞ ባዶ እጃቸውን ወደ ፋኖ እየጎረፉ ነው። በምስራቅ አማራ ቀጠና አንድ ወታደራዊ አዛዥ በስሩ የሚገኙ ወታደሮችን ጠርንፎ እንደያዘ ፋኖን ሲቀላቀል በምዕራብ አማራ ደግሞ ሁለት ሁለት ክላሽ ደርበው ያነገቡ ወታደሮች ፋኖን መቀላቀላቸውን ፍኖተ አማራ ሚዲያ ተመልክቷል። በተጨማሪም ከወራት በፊት በምዕራብ አማራ ቀጠና በተካሄደ ልዩ ዘመቻ ሙሉ በሙሉ ተደምስሳ የነበረችውና በኋላም ላይ ከሌሎች ክፍለጦሮች በተወጣጣ ሰራዊት ዳግም የተዋቀረችው የ25ኛ ክ/ጦር ዘመቻ መሪ ከነ ሙሉ ትጥቁና አጃቢዎቹ ፋኖን ተቀላቅሏል።

ፋኖ ‹‹እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፤ እንደ ነብር ቁጡ፤ እንደ ርግብ የዋህ በሆነዉ..በዚህም ባህሪው በሽተኛን ጠያቂ፤ የተጣላን አስታራቂ፤ የደከመን አነቃቂ፤ እኔ ሳይሆን እኛ በሚል ክንደ ብርቱ የዓላ
ፋኖ ‹‹እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፤ እንደ ነብር ቁጡ፤ እንደ ርግብ የዋህ በሆነዉ..በዚህም ባህሪው በሽተኛን ጠያቂ፤ የተጣላን አስታራቂ፤ የደከመን አነቃቂ፤ እኔ ሳይሆን እኛ በሚል ክንደ ብርቱ የዓላማ ሰዉ፤ ቁሞ ከሚሸነፍ ሙቶ ማሸነፍን የስነልቦናዉ መሰረት ያደረገ የአሸናፊነት ምልክት፤ በሞትና ህይዎት መካከል በሚደረግ ብርቱ ትግል በሚገኝ ወርቃማ ስም መሆኑን "ፋኖነት" የሚለው መፅሀፍ ደራሲ አቶ ጌትነት ይርሳው ገልጿል:: በዚህ ትርጓሜ መሰረት ፋኖነት ዋርካው ምሬ ወዳጆነት መሆኑን ልብ ይሏል:: ዘመናዊ የፋኖ ጦርን በመገንባቱ ሂደት ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ወንድሞቻችን መካከል አንዱ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ነው:: አሁንም እንደ ጆሲ Yoseph Asmare Et ያሉ የቀድሞው አማራ ልዩ ኃይል አሰልጣኞች የነበሩትን ተወርዋሪ ኮማንዶዎች ከጎኑ በማድረግ ዘመናዊ ጦር በመገንባት ላይ ያለ የትግል ፊታውራሪ ነው::

በደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ በተደረገ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ! ውጊያው ለተከታታይ 5:00 ሰዓታት የዘለቀ ሲሆን የአገዛዙ ኃይል ከአየር መቃዎሚያና ሞር
በደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ በተደረገ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ! ውጊያው ለተከታታይ 5:00 ሰዓታት የዘለቀ ሲሆን የአገዛዙ ኃይል ከአየር መቃዎሚያና ሞርተር ጀምሮ በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ታግዞ እራሱን ለመከላከል ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተወሰደበትን የከበባና የቆረጣ ማጥቃት መቋቋም አቶት ሙትና ቁስለኛውን ማንሳት በማይችልበት ደረጃ መሽመድመዱን የመረብ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። ፀረ ዐምሓራው የብልፅግና ቡድን ስልጣኑን ለማራዘም ሲል የደሀ ልጆችን አስገድዶ የለብ ለብ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት በዐምሓራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲፈፅሙ ማሰማራቱን የቀጠለ ሲሆን፡ በተመሣሣይ ፋኖ በሕዝቡ ላይ የተቃጣውን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ አገዛዙ ያሰማራቸው ወታደሮችን በደፈጣና በጨበጣ እንዲሁም በከበባና በቆረጣ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ግብዓተ መሬታቸውን መፈፀሙን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ከፋኖ እርምጃ የተረፉ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከአገዛዙ ጋር በአማራ በሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ለሚገኙ የአድማ
ከፋኖ እርምጃ የተረፉ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከአገዛዙ ጋር በአማራ በሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ለሚገኙ የአድማ ብተና፣ሚኒሻ፣ ፓሊስ፣ መከላከያና ማንኛውም በብልፅግናው ቡድን ውስጥ ለሚያገለግሉ ግለሰቦች የምህረት አዋጅ ማውጣቱ ይታወቃል። ይሄንን ጥሪ ተከትሎ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803ኛ ስር የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ሌሎች ወታደራዊ ሰነዶችን እንደያዙ በምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮርን ተቀላቅለዋል።

ከመገናኛ አንስቶ እስከ ደብረብርሃን ነባር የአማራ ይዞታዎችን የማፍረስና አማራዎች እየተለዩ ልዩ የማቆያ ስፍራ ተወስደው የሚመረመሩበት እቅድ ተነድፎ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ታወቀ። ከመገናኛ አንስቶ፣ ኮተቤ፣ ካራ፣ ለገጣፎ፣ ሰንዳፋ፣ አሌልቱ፣ ሸኖ ፣ ጫጫ አድርጎ ደብረብርሃን ድረስ የሚዘልቀው ይህ አማራውን ነባር ይዞታ የማሳጣትና ባለፉት አመታት የገነባውን ማሕበራዊ ትስስር የመበጠስ እንቅስቃሴ ለበርካታ ወራት አገዛዙ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግበረ ኃይል ብሎ የሚጠራቸው መከላከያ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት (ኢንሳ) ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተውጣጣ ኮሚቴ ሲሰራበት ቆይቶ ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑ ነው የተሰማው። በሬድዋን ሁሴንና በትዕግስት ሀሚድ በበላይነት የሚመራው ይህ አማራውን አንገት ለማስደፋት የሚደረግ እንቅስቃሴ፣ ከነባር ይዞታው ከማባረር ከማፈናቀል ባሻገር እስከ ሀብት ንብረቱን ማሳጣት፣ በሕጋዊ መንገድም ቢሆን የታጠቀውን መሳሪያ ማስፈታት ድምፅ አልባ መሳሪያን ጨምሮ መንጠቅ የሚሉት እንደሚገኙበት ተሰምቷል። እነዚህ የተለዩት አካባቢዎች ፋኖ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ቢጀምር መንገድ ጠራጊና ደጀን ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው ተብሎ በጥናቱ እንደቀረበ ለማወቅ ተችሏል። ባለፉት ጊዜያት ሸዋ ላይ ኢንተርኔትና የስልክ ግንኙነት አቋርጦ ኤሊት ፎርስ የሚለውን በሔሊኮፍተር አስገብቶ ዘመቻ ያደረገው የዚሁ እቅድ አንዱ አካል እንደሆነ ምንጮች አክለው ገልፀዋል። ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘውንና ሸዋ ላይ የሚንቀሳቀሰውን ፋኖ ቢቻል ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ካልተቻለ ግን ማዳከምና ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ማድረስ የእቅዱ አንዱ አካል እንደሆነ ታውቋል።

የአርሶ አደሩን መሬት ለእርሻና ለመኖሪያ ቤት ለመቀራመት አሰፍስፎ የመጣው ሚሊሻ በከበባ ተመታ!! =============== በዛሬው ዕለት የካቲት 12/2018 ዓ. ም ከምዕ/ጎጃሟ ቡሬ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኛዋ ውንድጊ ቀበሌ ንጉስታ ጎጥ የሚገኘውን የአርሶ አደር መሬት ለአብይ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ ለቤት መስሪያና ለእርሻ ቦታ ለመከፋፈል የመጣውን አረመኔው ፍሽስቱ እና ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ሰራዊትን 77ኛ ክ/ጦር አካል የሆነችው 5ተኛ ሻለቃ በመክበብ በአብሪ ጥይት ሲገርፉት አርፍደዋል፡፡ የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር 5ተኛ ሻለቃ በአደረገችው መብረቃዊ ጥቃት ጠላት ጥምር ሀይል እያለ የሚጠራው የሚሊሻና የፖሊስ ስብስብ ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ እገሬ አውጭኝ በማለት ወደ ቡሬ ከተማ ፈርጥጧል። 👉መረጃው የ77ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ነው! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ የካቲት 12/2018ዓ.ም

ሰበር ዜና!! 👉የ109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር አነፍናፊ አዳኝ ቡድን ፍኖተ ሰላም ከተማ የመሸጉ ሁለት ቅጥረኛ ባንዳ ሚሊሾችን በቁጥጥር ውስጥ አዋለ:- ================= በትናንትናው ዕለት በቀን 11/06/2018 አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በክንደ ነበልባሉ 109ኛ ኮር የሚመራው የ77ኛ ክ/ጦር አነፍናፊው አዳኝ ቡድን የምዕራብ ጎጃም ዞን ርዕሰ መዲና ከሆነችው ፍኖተሰላም ከተማ ከምሽቱ 2:30  ሁለት ባንዳ ሚሊሻዎችን አንገታቸውን አጠንጥሎ ከእነ ነፍሳቸው በቁጥጥር ውስጥ በማዋል ከከተማ ይዟቸው ወጥቷል። ➡️ቅጥረኛ ባንዳ ሚሊሾች ለማምለጥ ተኩስ ቢከፍቱም #ከአቦ ሸማኔ በእጥፍ የሚፈጥነው ዘሎ ጠላት ተክሻ ላይ የሚከመረው ይህ አነፍናፊ አዳኝ ቡድን ከእነትጥቃቸው በቁጥጥር ውስጥ አውሏቸዋል። ➡️በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ውስጥ የዋሉት እነዚህ ቅጥረኛ ባንዳ #ሚሊሾች:- 👉#አንደኛው ፈጠነ አለሙ የሚባል ሲሆን የዞኑ ሰላምና ደህንነት #ተገኔ ከልካይ የእህት ባል 👉#ሁለተኛው ያለው የሻነህ  የሚባሉ ሲሆኑ እስከ ተያዙበት ሰአት ድረስ የብልጽግና ካድሬ በሚሰጣቸው ግዳጅ ወጣቶችን እያስገደዱ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ ካምፕ ሲልኩ የነበረና ከአንድ ጎጥ ብቻ በህገወጥ መንገድ ከ80,000 ብር በላይ  መሰብሰባቸውን በሰጡት የቃል ማስረጃ አረጋግጠዋል። ⛔️ይህ አነፍናፊ አዳኝ ቡድን የባንዳ መድሀኒት ሲሆን ከተማ መሽገው ህዝባቸውን የሚገሉና የሚያስገድሉ ባንዳዎችን ስርዓት ያስይዛል፣ በቁጥጥር ውስጥ ያውላል፣ እርምጃም ይወስዳል። 👉ምህረት ለሚፈልጉ የምህረት በራችን ክፍት ነው!!! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ የካቲት 12/2018 ዓ.ም

ቆፍጣናው መሪ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ በቡልጋ ሰማይ ስር ከአድስ ምልምል የፋኖ ሰራዊታችን ጋር ያደረገው ቆይታ!! አማራራው ተራራው ወደ ፊት #መቅደድ ብቻ ነው👂🙏

የምህረት አዋጁን የተቀበለው ሶስት የ አድማ ብተና አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ:: ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል የነበሩ ሶስት
+1
የምህረት አዋጁን የተቀበለው ሶስት የ አድማ ብተና አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ:: ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል የነበሩ ሶስት የአድማ ብተና አባላት በተዛባ መንገድ ከተረኛው ስርዓት ጋር ተሰልፈው የነበሩ ምህረት አዋጁንና ጥሪችንን ተቀብለው የካቲት 12/2018 ዓ.ም አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የየጎፍ ክ/ጦር አመራሮችም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት የካቲት 12/2018ዓ.ም

#ኦህዴድን_ማጋለጥ‼️                                                                                                                በመንግስት መዋቅር የታገዘ የዘር ማጽዳት ዘመቻ እና የአማራ ህዝብ ራስን የማዳን የህልውና ትግል‼️ ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸሙት ግፎች የታሪክ ጠባሳ ሆነው የሚቀጥሉ ናቸው። ይህ ሂደት ከንግግር ተነስተው ወደ ስልታዊ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል የተሸጋገሩ ድርጊቶች ድምር ውጤት ነው። የጥላቻ ንግግር እና የፖለቲካ ሴራ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ "ነፍጠኛን ሰበርን" በሚል የሰነዘሩት ንግግር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አማራውን እንደ "መጤ" እና "ወራሪ" አድርገው መሳላቸው፣ ለታችኛው ታጣቂ ኃይል እና ለጽንፈኛ ቡድኖች የጭፍጨፋ የሞራል ድጋፍ ሆኗል። ይህም ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ እንዲገደሉ መንገድ ጠርጓል። የመረጃ እና የአሃዝ ማጠቃለያ የንጹሃን እልቂት፦ በወለጋ፣ በቤኒሻንጉል እና በሌሎች አካባቢዎች ከ 5,000 በላይ ንጹሃን በግፍ ተጨፍጭፈዋል። መፈናቀል፦ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ አማራዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለከፋ ስቃይ ተዳርገዋል። የቤት መፍረስ፦ በሸገር ከተማ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ100,000 በላይ ቤቶች በብሔር ማንነት ላይ ተመስርቶ እንዲፈርሱ ተደርጓል። የጸጥታ መዋቅሩ ተባባሪነት፦ በወለጋ እና በቤኒሻንጉል በተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ወቅት፣ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ሰዓታት በፊት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው እና ጥቃቱ ለሰዓታት ሲካሄድ በቅርብ ርቀት ሆነው ጣልቃ አለመግባታቸው በሪፖርቶቹ ላይ በዝርዝር ተመዝግቧል። የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባ፦ CNN፣ BBC እና Al Jazeera የመሳሰሉ ተቋማት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት "ዘግናኝ እና ስልታዊ" (Horrific and Systematic) በማለት የዘገቡት ሲሆን፣ ድርጊቱ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋልጠዋል። ህልውና ትግሉ አስፈላጊነት እና የጦርነቱ መንስኤ አሁን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን፣ ለዓመታት ለዘለቀው ስልታዊ ጭቆና እና ጥቃት የወለደዉ/ የተሰጠ የመጨረሻ ምላሽ ነው። የመንግስት መዋቅር እንደ ጥቃት መሣሪያ፦ በአዲስ አበባ ዙሪያ "የሸገር ከተማ" በሚል ስያሜ የተካሄደው የቤት ማፍረስ ዘመቻ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን ለጎዳና እና ለረሃብ ዳርጓል። ይህ ተግባር በመንግስት መዋቅር የታገዘ የከተማ ውስጥ "የዘር ማጽዳት" (Urban Ethnic Cleansing) ተደርጎ ይወሰዳል። ከጄኖሳይድ ራስን መከላከል፦ ሕዝቡ ከመንግስት ጥበቃ ከማጣት አልፎ፣ የመንግስት የጦር መሣሪያዎች (ድሮን እና ከባድ መሣሪያዎችን ጨምሮ) በእሱ ላይ ሲዘመቱ፣ ራሱን ከመጥፋት (Genocide) ለመከላከል እና መሰረታዊ ሰብአዊ መብቱን ለማስከበር ወደ ህልውና ተጋድሎ ገብቷል። ይህ ትግል የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት ሳይሆን፣ የመኖር እና በሰላም የመንቀሳቀስ መብትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነው። ማሳሰቢያ፦ የታሪካዊ እና ህጋዊ ተጠያቂነት ግዴታ ለእነዚህ ሁሉ ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ለንጹሃን ደም መፍሰስ እና ለሚሊዮኖች መፈናቀል የሚከተሉት አካላት ቀጥተኛ ተጠያቂነት አለባቸው፦ የብልጽግና ፓርቲ (ገዥው ፓርቲ)፦ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ እና በስሙ የሚመራው መዋቅር ለጥቃቶች መንገድ በመክፈቱ። የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፦ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት፣ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችን ለታጣቂዎች አሳልፎ በመስጠት እና ስልታዊ መፈናቀልን በመምራታቸው። የጸጥታ መዋቅር አዛዦች፦ ጥቃቶችን ባለማስቆማቸው እና በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመደገፋቸው ተጠያቂ ይሆናል!! 12/ዐ6/2018 ዓ.ም