uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 444
Obunachilar
+1624 soatlar
+487 kun
+1 15030 kun
Postlar arxiv
አሳዛኝ መረጃ!...ሼሁ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ! ሼሁ ከሚያስተምሩበት መስጂድ በአገዛዙ ወታደሮች እጃቸውን የፊጥኝ ታስረው ተረሽነዋል። ሼክ ጉንጃ ሮበሌ ይባላሉ። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቲ ወረ
አሳዛኝ መረጃ!...ሼሁ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ! ሼሁ ከሚያስተምሩበት መስጂድ በአገዛዙ ወታደሮች እጃቸውን የፊጥኝ ታስረው ተረሽነዋል። ሼክ ጉንጃ ሮበሌ ይባላሉ። በኦሮሚያ ክልል አርሲ  ዞን መርቲ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። የተከበሩ የሐይማኖት አባትና የሀገር ሽማግሌ ናቸው። ለሀገር ሰላምና እርቅ የሚለፉ ፣ አስታራቂና ተወዳጅ  ሼህ ነበሩ። ከሳምንታት በፊት ከሚያስተምሩበት መስጂድ ባልታወቀ ምክንያት በአገዛዙ ወታደሮች ተይዘው፡ በወረዳው አቦምሳ ተብሎ በሚጠራው ከተማ ታስረው ነበር። የነውረኛው ስርዓት አገልጋይ የሆኑት ወታደሮቹ፡ ትናንት መስከረም 24/2018 ዓ/ም እነዚን የሐይማኖት አባት ከእስር ቤት አውጥተው እጃቸውን ወደኃላ አስረው አደባባይ ላይ ከረሸኗቸው ቦኋላ አስ*ክሬና*ቸው እንዳይቀበርና ቤተሰቦቻቸውም ለቅሶ እንዳይቀመጡ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኃይለማርያም ማሞ ብርጌድ የሁለት ዓመት የምሥረታ በአልና የአደረጃጀት ሪፎርም ማድረጉን አሥታወቀ !      መሥከረም 24/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ የኃይለማርያም ማሞ ብርጌድ የ2ኛ ዓመት የምሥረታ በአሉን በደማቅ ሁኔታ እክብራል። ብርጌድ ለአለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም በሀገረ ማርያም ወረዳ በኮረማሽ፣ ውሃ ሜዳ፣ በዬነቾህ፣ አባቡኖ፣ ሰኮሩ፣ ንፋሥ አምባ በጎርፎ፣ ይርማታ አገር፣ አክርሚት፣ ሀገረማርያም አቦ፣ በዮላት እንዲሁም ስቻት፣ ዛላ ዘንባባ እና የረር ሦሥት አምባ ቀበሌዎች በመቆጣጠር ታላቅ ተጋድሎ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት በመተናነቅ የጠላትን ሀይልን በማፈራረስና በመደምሰስ በርካታ ተጋድሎ ሲፈፅም ቆይቷል ። ብርጌዱ ብርካታ ቀጠናዎችን በመቆጣጠርና ብዙ የሰው ሀይል በማደራጀትና በማብቃት እንዲሁም ወታደራዊ የቡድን መሳሪያና ነፍስ ወከፍ ትጥቆችን በማሟላት አደረጃጀቱን ከብርጌድ ወደ ክፍለ ጦር ማሳደጉን መሰከረም 24/2018 ዓ.ም በይፋ አሥታውቋል። በምሥረታው በአሉና በአደረጃጀት ሪፎርሙ የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል አርበኛ ረ/ ፕሮፌሰር ማርከው መንግሥቴ የአፍብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች መቶ አለቃ አሥማማውና ኃምሳ አለቃ ካሳ ጌታቸው እና የክፍለ ጦር አመራሮችና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በምሥረታ በዓሉ ላይ የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባል አርበኛ ረ/ፕሮፌሰር ማርከው መንግሥቴ እንዳሉት፤ "ይህን የህልውና ትግል እዚህ ደረጃ ለማድረስ ዋጋ የከፈሉና መስዕት የሆኑ ጀግና ታጋዎችን በማሰብ የተጀመረውን ከግቡ የምናደረስበት ቀን እሩቅ አይደለም ብለዋል። በመቀጠልም ትላንት ከሰፈር በቁጥር ትንሸ ሆነን የጀመርነው ትግል በብረጌድ በክፍለ ጦር እንዲሁም በዕዝና በአማራ ደረጃ የተዋቀረና የተደራጀ ጦር መሥርተናል ብለዋል ። አያይዘውም ገና ከጠላት በላይ ገዝፈን ጠንክረን የጠላትን አከርካሪ እስከወዲያኛው የምንሸኜው ከዚህ በበለጠ ጠንክረን ስንደራጅና አንድ ሆነን  መታገል ሥንችል ነው" ብለዋል ።     በመቀጠል የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ከፍተኛ አመራራ ኃምሳ አለቃ ካሳ ጌታቸው ይህንን የሁለት አመት የምስረታ በአልና ለትግሉ መስዕዋት የከፈል ጀግና ሰማዕታት መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሳችሁ በማለት እንዚህ ሰማዕት የሆኑ ጀጋና ታጋዮች አጥንታቸውን ከስክው ደማቸውን አፍሰው ለእኛ አደራ ሰጥተውን አልፈዋል በማለት እኛም እነሱ አደራ የሰጡንን ዋጋ የተከፈለበትን ትግል ከዳር ለማድረስ ከፍተኛ ሃላፊነትም አደራም አለብን ብለዋል።አማራ ላይፈርሥ ላይመለሥ የወጣበትን አላማ ከግብ ለማድረስ ከአለት የጠነከረ ህዝቦች በመሆናችን ገና እንሰለጥናለን እንደራጃለን ጠላቶቻችንን እንዳይነሱ አድርገን ከአፈር እንቀላቅላቸዋለን ብለዋል።   የኃይለማርያም ማሞ ብርጌድ የዕለቱን ፕሮግራም ለትግሉ ሰማዕት የሆኑ ታጋዮችን በማሰብ በሀይማኖት አባቶች የፀሎት ፕሮግራምና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በማድረግ ተጀምሯል። ላለፉት 2 አመታት ያደረገውን ተጋድሎና አሁናዊ ሁኔታ ግምገማ ያደረገ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የክፍለ ጦር አመራር በእንዳልካቸው ግርማ ማብራሪያ ተደርጓል።  ኃይለማርያም ማሞ ብርጌድ ላለፉት ሁለት አመታት በአማራ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክፍለ ጦር ስር ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ። በመሆኑም አሁናዊ የብርጌዱን እንቅስቃሴና የትግል ሁኔታ በመገምገም በርካታ የተቆጣጠራቸው ቦታ በመያዝና የሰው ሀይሉንና የወታደራዊ ትጥቁን በማዘመን የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባልና የአሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና የክፍለጦር አመራሮች በተገኙበት  ከብርጌድ ወደ ክፍለ ጦር እንዲያድግ  ተደርጓል ።  በማጠቃለያ ንግግርና ወቅታዊ የትግል አቅጣጫን በተመለከተ የክፍለጦር ከፍተኛ አመራር በአርበኛ እሸቱ ተ/ሚካኤል የቀርበ ሲሆን፤ ይህንን ትግል ስንጀምር ተወልደን ባደግንበት ሀገር እንደ ባዕድ ተቆጥረን ሰርተን እንዳንበላ በማንነታችን በብሄራችን  እንድናፍር በማንነታችን ተመርጠን እንድንታረድ በዘግናኝ ሁኔታ እንድንጨፈጨፍ እንድንፈናቀል እንድንታሰርና እንድንሰቀል የሞት ፍርድ ታውጆብን ነው። ከላይ የዘረዘርኳቸውን በደል የግፍ ግፍ ስላደረሱብን  እኛ ግን የአባቶቻችን ልጆች እጃችንን አጣጥፈን የማንቀመጥ ሽንፈትን ያለመደብን በጭርሽ የማንቀመጥ የእነ እምዬ ሚኒሊክ፣ የነ በላይ ዘለቀ የእነ አሥራት ወልደጌሥ የእነ አሥማረ ዳኜ ልጆች ክንዳችን እንደሳት የሚያነድ በጭራሽ የማይንበረከክ አሥተሳሰባችን አመለካከታችን የሰለጠነ የተስተካከለ ለሰው ልጆች ሁሉ ክብር ያለን በጀግንነት የምንሰዋ ዘመኑ ያፈራን የቁርጥ ቀን ልጆች ነን። ምንም እንኳን ጠላቶቻችን በመካክላችን ገብተው ለማፈራረስ ለመበታተን ትግሉን ለመጥለፍ  ቢሞክሩም ይህ መደራጀታችን መሰባሰባችን የማንበረከክና የማንሸነፍ መሆናችን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ኃይለማርያም ማም ክፍለጦር ማሳያ ነው በማለት፤   በመጨረሻም፤ ለአላማው የጠነከረ በክብርና በጀግንነት ተሰውተው አደራ ብለው ያሥረከቡንን ትግል ከዳር ለማድረስ በወርቅ የተፈተነ አደረጃጀቱን ጠብቆ በእዝ ሰንሰለት የሚመራ  ሰራዊት በማፍራት የምንደራጂና የምንሰባሰብ መሆኑን እዬገለፅሁ ይህንን አረመኔና ዘራፊ የዱርዬ መንግሥት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የምናሥወግድበት ጌዜ ቅርብ ነው በማለት ትግል ውስጥ ያልገቡትን የአማራ ህዝብና ተወላጂ የመጨረሻ ጥሪ በማድረግ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።             🔥 ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !!             💪 ነፃነታችን በተባበረ !! ክንዳችን!!!             👉ድል ለሰፊው አማራ ህዝብ !!! የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ኃ/ማርያም ማሞ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት!!   መስከረም 24/01/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

ለዛምበራሃ ብርጌድ አመራርና አባላቶች በተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ወታደራዊ እና የፖለቲካ ስልጠና ተጠናቀቀ።           መስከረም 25/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የስልጠና ኮርሶች ተጠናቀዋል። ስልጠነው የሰራዊቱን አቅም የሚያጎለብት፣ግዳጁን በብቃት ለመወጣት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ሲሆን ስልጠናው በ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች ተሰጧል። ከስልጠናው ጎን ለጎን የዛምበረሃ ብርጌድ አመራር በመገምገም የብርጌዱ አሁናዊ ቁመና በመፈተሽ በብርጌዱ ያልተሟሉ አመራር በመተካት አደረጃጀቱን ማጠናከር ተችሏል። በመጨረሻም ብርጌዱ ለቀጣይ ለሚሰጠው ማንኛውም አይነት ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን  አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ በሰላም ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ! ፋኖ ይበልጣል ጌቴ የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

በአፋብኃ አርማ ያሸበረቀ ኮማንዶ ከቴወድሮዝ እዝ እየመጣ ነው። ጠላትን ያፍረከረክነው አስበን እና አቅደን በፈፀምነው ድንቅ ተጋድሎ ነው። የጠላት ኃይል እየፈረሰ የእኛ ኃይል እየተገነባ ቀጥሏል። የአማራን ህዝብ ህልውና የሚታደግ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም የሚያዋልድ፣ የምስራቅ አፍሪካን የኃይል ሚዛን የሚጠብቅ ዲስፕሊንድ ሰራዊት መገንባቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ግዙፉ እና ነባሩ አብራጅት ብርጌድ እንዲሁም በእሳት ተፈትኖ ወርቅ መሆኑን ያረጋገጠው የደብረ ኤልያሱ ቀስተ ደመና ብርጌድ እጩ የሰራዊት አባላትን አስመርቀዋል። በፊልድ ማርሻል፣ በበርካታ ሙሉ ጀነራሎች በብዙ ብርጋዴር እና ሜጀር ጀነራሎች እና በባለ ብዙ ማዕረግተኞች የሚመራው የአብይ ሰራዊት የእናቶችን መቀነት በመቁረጥ፣ በመድፈር እና በመድፈር፣ በእጁ የገባውን ምርኮኛ በስለት ወግቶ በመግደል አሸባሪነቱን አሳይቷል። በሌላ በኩል ያለ በቂ ልምድ እና ተሞክሮ በቅንነት እና በፅናት በተሰራ ስራ በሲቪሊያን ጥበቃ፣ በምርኮኛ አያያዝ፣ በወታደራዊ ጨዋነት ያሳዬነው ብቃት የሚያኮራ ነው። ይህንን ስርዓት የገባ ሰልፈኛ ሰራዊት ለመፍጠር ሌት ከቀን የደከሙ ወታደራዊ አመራሮቻችን ክብር ይገባቸዋል። የኃይል ግንባታው ይቀጥላል... ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

በሌላኛው ቀጠና ባህርዳር ብርጌድ ህዝባዊ ውይይቶችን አካሂደዋል። በዛሬው እለት በቀን 25/2018 ዓ.ም በጢስ አበይ ቀበሌ ማጅ ደብረንግስት መጠነ ሰፊ የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት እና ህዝባዊ አ
+4
በሌላኛው ቀጠና ባህርዳር ብርጌድ ህዝባዊ ውይይቶችን አካሂደዋል። በዛሬው እለት በቀን 25/2018 ዓ.ም በጢስ አበይ ቀበሌ ማጅ ደብረንግስት መጠነ ሰፊ የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት እና ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በማጠናከር መዋቅሮችን የመደገፍ አሰራሮችን በመዘርጋት  የማብቃት ስራ ተሰርቷል።      ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መስከረም 25/2018 ዓ.ም

#ደምበጫ_የጠላት_መቅጫ💪 በዛሬው ዕለት የደምበጫ ተርቦች( እንጂነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ) አናብስቶች አንጀኔ ቀጠና ላይ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ሲሆን በዚህ ተጋድሎ በርካቶች የተደመሰሱ ሲሆን ፣ 1 መኪና #ጋይቷል💪 ምትና ቁስለኛውን እንዲሁም የጋየውን መኪና ተጨማሪ ኃይል በማስመጣት ይዘው ተመልሰዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ይሆናል.... 25/ዐ1/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

የሀይል ግንባታ ስራው እንደቀጠለ ነው። ቀስተደመና ብርጌድ ለ6ወር ያክል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕ
+3
የሀይል ግንባታ ስራው እንደቀጠለ ነው። ቀስተደመና ብርጌድ ለ6ወር ያክል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ         መስከረም 25/2018 ዓ.ም

የጠላት ሀይል እየተበተነ እየተማረከ ነው እኛ ከእለት እለት በትጥቅም በሰራዊትም እየጠነከርን ነው። ዛሬ አፋብሀ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ሀዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር አብራጅት ብርጌድ ለወራት ያሰለጠናቸውን 3ተኛ ዙር ኮማንዶወች አስመርቋል። ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

ይህ ነው የእኛ ትውልድ አማራነት የነፃነት መሰራታችን ነው ፋኖነት የአማራዊያን የነፃነት ተምሳሌታችን ነው። እነዚህ ዱኩማን በልኩ የማያውቁን ዘመን የወለዳቸው የአማራ ጠል ሌትና ቀን አማራን በመከፋፈል በዘር በሃይማኖት በአራቱም ማዕዘን ልክ እንድ ይሁዳ አረመኔያዊ አሰራር መስራት የማይሰለቻቸው የታሪክ አተላዎች መሆናቸውን በእውኑ ያልተረዱ  ግብዞች ትናትና በወለጋ፤በአጣዬ፤በመተከል በደራ፤በወልቃይት አማራውን በኦሮምማው መንግስት እንደበግ ሲታረድ ያልደረሱ የብልፅግና ቀንበር ተሸካሚ ባላደራዎች የሆኑ። ዛሬ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ ድባቅ የተመቱም መሆናቸውን ያመኑ በአርበኞች በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ደባቅ የተመታ መሸነፉን የማያምን ነገር ገን ዙሯ የማይሰለቸው የሲራ ፖሊቲካ በመስራት እርጅም የሚመስለውን መንገድ የሄድ ዛሬ ግን እንደ ቁራ በሳይበር የሚጮህ ዳናቁርት ምንግርግር ድንግርግር ያለበት አገዛዝ አብይ አህመድ አሊ ነው። ለዚህም ነው የአማራ ሙሲሊም እና ክርሰቲያን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውን አጥብቂ የምናገረው ሆኖም ግን አይበገሬው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ የአማራን ነፃነት የሚያበስርበት ቀን ቅርብ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሰባት ለሰባ አስተዳደር ዋና ኃላፊ የጀግናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ የኢሳያስ ደመቀ ታላቅ ወንድም አርበኛው ደመላሽ ደመቀ!! መስከረም 25/01/2018 ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎                     

🔥#ኮማንዶዎች_ተመረቁ‼️ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ በኮማንዶ ውትድርና ለ6 ወራት ያሰለጠናቸውን ወታደሮች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ! መስከረም 25/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ  በኮማንዶ ውትድርና ለ6 ወራት ያሰለጠናቸውን ወታደሮች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ። እንደ አማራ የተጋረጠብንን ሁለንተናዊ አደጋ ለመቀልበስ ትኩረት ሰጥተን ከምንሰራባቸው ጉዳዮች አንዱ ማሰልጠን ነው። በምረቃ መርሐ ግብሩ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የብርጌዱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በተመራቂ ኮማንዶዎች በርካታ ወታደራዊ ትርዒቶችና አርቶች ለታዳሚው ቀርበዋል። በጀግንነት ሲዋጋ የክብር መስዋትነት በተቀበለው የቀስተ ደመና ብርጌድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሆነው አርበኛ በላይነህ ሞላ መታሰቢያነት የተሰየሙት እኒህ የኮማንዶ ተመራቂ አባላት ከስልጠና ወጥተው በሚሰማሩበት የግዳጅ ቀጠና የሰማዕቱን አደራ ማስፈጸም እንደሚገባቸውና፤ በብዙ መሰዋዕትነት እያለፉም ቢሆን በሕዝባችን ላይ የተደቀነውን ሁለንተናዊ የሕልውና አደጋ ለማስወገድ አማራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ በዕለቱ ከተገኙ አመራሮች የአደራ መልዕክት ተላልፏል። በተጨማሪም በስልጠና ሂደቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትና ለክቡራን ተመራቂዎች ሰርተፍኬትና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን የወረዳው ተወላጅ በሆነውና በርካታ ሀገራዊ አበርክቶቶችን ባበረከተው በሊቁ መላኩ በጎሰው በተሰየመው የቀሰተ ደመና ብርጌድ የመላኩ በጎሰው የኪነት ቡድን የሙዚቃና ውዝዋዜ በመቅረብ መርሐ ግብሩ ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል። ድል ለሕዝባችን! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ 25/ዐ1/2018 ዓ.ም

🔥#ሰበር_ዜና‼️ በመልሶ ማጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላትን ሚካኤል ደብር ከተማ መቆጣጠር ተችሏል።      ዛሬ መስከረም 25/2018 ዓ.ም የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ከባህር ዳር ጀምሮ ሃይሉን በማሰባሰብ አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ትላንት የደረሰ ሲሆን አዲስ ዘመን ላይ ተጨማሪ ሃይልን በማከል በ2 አቅጣጫ ማለትም በደሪጣ አስታ አቅጣጫና ከአዲስ ዘመን አርኖ ጋረኖ በጅራት አቅጣጫ ሌሊቱን ሲጓዝ አድሮ በጠዋቱ ሚካኤል ደብር ሊደርስ ችሏል።   ሌላው የውጊያ ቀጠና ደግሞ ከአዘዞ ከጠዳና ከማክሰኝት ኃይሉን ለቃቅሞ ደጎማ ላይ በመድረስ መነሻውን ደጎማ በማድረግ ቀጥታ በአዲስ ዘመን ከመጣው የጠላት ኃይል ጋር በመናበብ የወገንን ኃይል መደምሰስ ነበር እቅዱ፤ ያልጠበቀው ነገር የገጠመው ጠላት በ3ቱም የውጊያ ቀጠናዎች ከፍተኛ ምትን አስተናግዷል።      ከደጎማ ወደ ሚካኤል ደብር የመጣውን የጠላት ኃይል መብረቅ ክ/ጦር በድሽቃ በታገዘ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ችለዋል።     ከአዲስ ዘመን በአስታ አቅጣጫ የመጣውን ጠላት ደግሞ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦርና  የጎ/በጋሻው ክ/ጦር አባላት በሚገባው ቋንቋ አናዘውታል።      ከአዲስ ዘመን አርኖ ጋርኖ ጅራት አቅጣጫ ፋናየ ውቤ ክ/ጦርና የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር የተወሰኑ አሃዶች በመናበብ ጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አድርሰዋል።       ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በ3ቱም የውጊያ ቀጠናዎች የተመዘገቡ ድሎች        ** 28 የጠላት ኃይል የሞተ        ** 35ቱ ደግሞ የቆሰሉ ሲሆን በአዲስ ዘመን ጤና ጣቢያና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ፣ በእንፍራዝ ጤና ጣቢያ ፣ በማክሰኝት ጤና ጣቢያና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ከመሆኑም በላይ ክፋኛ የቆሰሉት ደግሞ ወደ ጎንደር ለከፍተኛ ህክምና በሪፈር እንደተላኩ ለማወቅ ተቸሏል።    በበቀል የሰከረው ጠላት በሚካኤል ደብርና በአካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ማንገላታትን የፈፀመ ሲሆን የህዝብን ሃብትና ንብረትንም ዘርፋል።     ከዚህ በተጨማሪም ንጹሃን አርሶ አደሮችን ጠመንጃ አላችሁ አምጡ ብለው የጠየቁ ሲሆን አርሶ አደሮችም ጠመንጃ የለንም በማለታቸው ተረሽነዋል።     **  3  አርሶ አደሮች ዋሻ ማርያም ቀበሌ ላይ     **  2  ደግሞ የሚካኤል ደብር ቀበሌ ነዋሪዎች ናቸው                  የተረሸኑት ።   ** 1 ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲያገለግል የነበረው ዲያቆንን ክፋኛ በማቁሰልና   **  1 ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፈጣሪው ጋር ተገናኝቶ በጸሎት ለይ የነበረን ግለሰብም አቁስለዋል።                ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን ኃላፊ አብነት ሞላ         25/ዐ1/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ነፃ ባወጣቸው የሰሜን  ወሎ ዞን መካከል በሀብሩ ወረዳ ኸሚገኙ ከተሞች መካከል በጊራና  ከተማ  ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡ ዛሬ በዕለተ ማክሰኞ በቀን 25/01/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ ጋራና ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች 1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?   * ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ   * ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ   * የትግሉ ተግዳሮቶች    * የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ  2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ   * በወታደራዊ ቁመና   * በፖለቲካ ተቀባይነት   * የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም 3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ   * የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት   * የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት   * ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ 4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?  በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡ በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡ በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት  ፋኖ መሀመድ ሞገስ መስከረም 25/2018 ዓ.ም

የአገዛዙ የአብይ አህመድ በአማራ ላይ ያሰበውን ሲራ ሚስጥር ሲጋለጥ እናመሰግናለን አምሓራዊት ጀግና ነሽ ሽር አድርጉ በፈጣሪ ሙሉ አማራ ይስማው ይህን ሸርና ጆይን የማያደርግ አማራ ባንዳ ነው ሙስሊም ክርሰቲያን በሚኖርባት አማራ ፋኖን መውቀስ የመጨረሻው የመፍራት አላም ነው ሽር ሽር ሽር ሸር ሸር አለቀ አምሓራዊት ያአፂዎች እናመሰግናለን

ከግንባር የተላከ መረጃ ! ፈንታው ሙሀቤ እና ብርሌው ከብአዴን ጋር ድርድራቸውም ጨርሰው ሊገቡ ነው። ኮሮኔሉ የአድማ ብተና ኃላፊ ሊሆን ጨርሰዋል ከስሩ የነበሩ የተወሰኑ አመራሮችን ቦታ ተመቻችቶላቹሀ
ከግንባር የተላከ መረጃ ! ፈንታው ሙሀቤ እና ብርሌው ከብአዴን ጋር ድርድራቸውም ጨርሰው ሊገቡ ነው። ኮሮኔሉ የአድማ ብተና ኃላፊ ሊሆን ጨርሰዋል ከስሩ የነበሩ የተወሰኑ አመራሮችን ቦታ ተመቻችቶላቹሀል ብሎ ቢያወያያቸውም እኛ ለነፃነት እንጅ ለስልጣን አልወጣንም በማለት ሁሉም በሚባል ደረጃ ከእሱ በመውጣት ሌላ ቀጠና ገብተዋል። አሁን እሱ ጋር የቀሩት ከአምሳ እንደማይበልጡ እዛው ያለ ልጅ መረጃ ልኮልኛል !! በመሆኑም አንደራደርም በማለት ከእሱ የወጡትን በጠላት ለማስከበብ እንቅስቃሴውን ስለጀመረ በአካባቢው ያላችሁ የምኒልክ ዕዝ ሰራዊት ተገቢውን ከለላ በመፈፀም እንድትተባበሯቸው ስንል እናሳስባለን!🙏

"ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ጥንቃቄ" ከቡሬ ወደ አለፋ አቅጣጫ በዚህ ሰዓት የጠላት ሰራዊት በበቆሎ ውስጥ መንደር ለመንደር እና ቀጥታ አስፖልቱን ይዞ እየመጣ ይገኛል። ያው ለጥንቃቄ እና እንዳንዘናጋ ነው እንጂ ቀን አለቀን እየመጣ መረጃው ገና ከካንፕ ሲነሱ እንደሚደርሳቹ ጠፋቶን አይደለም !🙏 ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎