ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 387
Obunachilar
+124 soatlar
+757 kun
+1 40730 kun
Postlar arxiv
ትግላችን ከዳር እንዲደርስ የአማራው ወንድምህን አቅም ተቀበል ተጠቀምበት ጠብቀውም እርስ በራሳችን እንዋደድ የሀሳብ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው የተገፋውን ማሕበረሰባችንን ከስቃይ እንታደገው ።
የዕለቱ መልዕክቴ ነው Dega Damot Timely
* አንድነት ኃይል ነው 💪
* የሀሳብ የበላይነትን እናክብር 💪
* አማራነት ይለምልም 💪
# አዲስ ትውልድ
# አዲስ አስተሳሰብ
# አዲስ ተስፋ
ፎቶ ደጋ ዳሞት በሰዓቱ
- ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው
- ሻለቃ ሙላቱ ሲሳይ
+5
በቅርብ ቀን የተዋቀረው የጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ውይይቱ እያካሄደ ይገኛል።
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
በእነማይ ወረዳ 3 ቀበሌወችጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት በማካሄድ ከውጊያው ጎን ለጎን የስርአተ መንግስት ተከላ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ደብር፣ ደንሳ እነቆራ እና አዲስ አለም ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በሶስቱም ቀበሌዎች ህዝብ ያመነባቸውን የቀበሌ አስዳደር፣ ም/አስተዳደሪ፣ ፀሀፊ፣ ፀጥታ ዘርፍ፣ የፍትህ አካላት፣ ገቢና ሀብት አሰባሰብ፣ ወጣት ተጠሪ እና በሶስቱም ቀበሌዎች የህዝብን ችግር ለመፍታት ህዝብ ያመነባቸው ችግር ፈች ሽማግሌዎችን አዋቅሯል።
አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ አስተሳሰብ!
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና #በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ድልን ተቀዳጀ።
በዛሬዉ እለት ህዳር 05/2018 ዓ.ም ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር አርበኛ ገብረመስቀል ደርብ ብርጌድ #ጋፋት ሻለቃ፣ #ኮከብ ሻለቃ እና #ታቦር ሻለቃ በመቀናጀት ከደብረታቦር ወደ እብናት ሲጎዝ በነበረ የስርአቱን ቅጥረኛ ከ12፡00 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡40 ሰአት ልዩ ቦታዉ ቡሮ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ደፈጣ በመጣል የጠላት ሀይልን በሚገባ አስተናግደዉታል።
ከደብረታቦር 18 መኪና ጠላትና ሬሽን የጫነ ሲሆን ከእብናት የወረደው አመራር ከ10 መኪና በለይ ታጅቦ ሲመጣ አናብስቶቹ ምን ዉስጥ ገባሁ ብሎ ሲርበተበትና ነብሱን ለማትረፍ ሲፍጨረጨር ዉሏል።
በአዉደ ዉጊያዉም የተገኙ ድሎችም የሞተ 14 እና ቁስለኛ ደግሞ ከ20 በላይ አድርጎ በሁለት መኪና ጭኖ ሙትና ቁስለኘውን ወደ ደብረታቦር ይዞ ተመልሷል። በጥቃቱ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሰራዊቱ ቁስለኛውንና አስከሬኑን በመያዝ ወደ ደብረታቦር ገብቷል።
በዚህም የተነሳ ቁስለኛውንና አስከሬኑን ለማንሳት ተጨማሪ የጠላት ኃይል ከደብረታቦር ከተማ ተነስቶ ውጊያው ከተካሄደበት ቦታ በመድረስ በወገን ሃይል ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎቹ ፋኖዎች የለመደውን የሽንፈት ካባ አከናንበዉታል ሲል የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ በላይነዉ ልብሱ ተናግራል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
በላይ ዕዝ ዳ/ ቴዎድሮስ ፭ ኮር በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመ።
በትላንትናው ዕለት ህዳር 4/2018 ዓ.ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ቃኘው ብርጌድ ፤ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ጅብ አስራ ብርጌድ እና ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ቃኘው ሻለቃ በመቀናጀት ምንዝሮ ልዩ ስሙ አርሴማ ከተባለው ቦታ በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
በጥቃቱ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው የዓብይ ቅጥረኛ አስከሬኑን እና ቁስለኛውን አዝረክርኮ ወደ ጎንደር ከተማ ፈርጥጦ ገብቷል።
በዚህም የተነሳ ቁስለኛውንና አስከሬኑን ለማንሳት ተጨማሪ የጠላት ኃይል ከጠዳ ከተማ ተነስቶ ውጊያው ከተካሄደበት ቦታ በመድረስ በወገን ሃይል ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎቹ የለመደውን የሽንፈት ካባ አከናንበውታል።
በውጊያው 06 ላይመለስ ሲሸኝ 08 ቁስለኛ ሁኗል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
#ወንድማማችነት: በነገራችን ላይ ከወዳጅ ጋር ብዙ ነገር ይወራል:: ማማት መታማትም ያለ ነው:: ወንድ ልጅ ሲታማ ሲጠረጠር ሲታሰር ሲፈታ ነው:: ወንድ እና ውሻ ሲታሰር ይበልጥ ወንድ ይሆናል ይባላል:: ሀሜትም ኖርማል ነው::
በሀሜት መሀል እና በወዳጅ ወሬ መሀል ለጠላት ግብዓት የሚሆን ፍሬ ነገር ይገኛል:: የብልግናው ስርዓት የግለሰቦችን የመልዕክት ልውውጥ እና ውይይት ቀንጭቦ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ እየመጣ ይበልጥ ወንድማማችን ማራራቅ እና ትግላችንን መስበር ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው::
ነገር የሚቀምል መንግስት አይቼ አላውቅም ነበር ዘንድሮ ግን አየሁ:: የብልግናው መንግስት ባልና ሚስት የሚያወሩትን ጭምር መቅዳት ይፈልጋል:: ይህ ሊደንቀን አይገባም!!
አለቃ ወንድሙ ማሩ ከሌላ ጓዱ ጋር ያደረገውን የስልክ ንግግር በመቅዳት ወንድማማችን ለማጣላት የብልግና መንግስት ያደረገው ጥረት ውጤት አልባ ነው:: ማንም የፈለገውን ቢል የሚኳረፍ የለም ምክንያቱም እኛ አማሮች ነን:: በአስተውሎት ነው የምንጓዘው:: በጦር ያልተፈታ ፋኖ በወሬ ሊፈታ አይችልም!!
እውነታው ይህ ነው:: አለቃ ወንድሙ ማሩ እና አርበኛ በለጠ ሸጋው ትናንትም ዛሬም ወንድማማቾች ናቸው👥
የጠላት ራስ ምታት 201ኛ ኮር 54 ክፍለ ጦር መብረቁ ተፈራ ጠላት ሲያርበደብው አርፍዷል።
ለጠላት የማይንበረከከው መብረቁ ተፈራ በመካናይዝድ ደረጃ ተደራጅቶ ጠላት ውጊያ ብከፍትም የመጣውን የአረመኔአዊ ሠራዊት ንስሮቹ የመብረቁ ተፈራ ልጆች እማይቀመሱ ሆነዋል ።
ከሞጣ_ባህርዳር አገር አቋራጭ መንገድ ከተዘጋ አምስት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ይኸንም አድርጎ ያልተሳካለት የአብይ ወንበር አስጠባቂ ስርአት
በቀን 05/03/2018/በጠዋት 12:00 ከሞጣ ተነስቶ ዙ 23 ታጥቆ የመጣ ቢሆንም የ መብረቁ ልጆች አራጢ ላይ እንደ እባብ ሲቀጠቅጡት አርፍደዋል ምቱን መቋቋም ሲያቅተው ከወይን ውሀ እና ከሞጣ ተጨማሪ ሀይል በማምጣት ሙትና ቁስለኛ ተሸክሞ ወደ መጣበት ተመልሶ ሂዷል።
መብረቁ ጠፍታችኋል ለምትሉን ምን ተሠራ ብላችሁ ጠይቁ አራጢ ላይ ?
ከተናገረው ዝም ያለው ያስፈራል !!!
ሐብታሙ የሱፍ የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
ስቦ_ማስከዳት_ተጠናክሮ_ቀጥሏል‼️
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
ስርአቱ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመበት ያለውን ግፍ እያየን መቀጠል ስላልቻልን ከወንድሞቻችን ጎን ተሰልፈን ህዝባችን መካስ አለብን በማለት
በዛሬው እለት ወደ ፋኖ 74ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
1. ሳጅን መለሰ.......መደበኛ ፓሊስ
2. ስማቸው ሙጫው.... ጅም ስሪ እና ክላሽ ከነሙሉ ትጥቁ በመያዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ሁሉም የአማራ ተወላጅ ለመውጣት ይፈልጋሉ ነገር ግን ይገሏቹሀል ነው የሚባለው ቢሆንም ግን ለመውጣት አልመቻች እያለ ነው እንጂ አሁን ላይ ማንም መቆየት አይፈልግም በማለት ገልፀዋል።
የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
05/ዐ3/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃንና እንስሳትን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ !
ህዳር 05/2018ዓ.ም
የአገዛዙ ብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጨፍጫፊ ሰራዊት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ላስታ ወረዳ 04 ቀበሌ ሳርዝና ልዩ ስሟ ወምበርኮ ማርያም ከምትባል ደብር እህል በመዉቃት ላይ ያሉ ንፁሃንን ላሊበላ ከተማ ልዩ ስሙ ሁለት ቁጥር ከሚባለው ቦታ በመሆን በዘፈቀደ ሞርተር 120 ወደ ንፁሃን በመተኮስ የአንድ ቤተሰብ ልጆች
1. ህፃን ወርቅየ ጌታቸው ዕድሜ=15 ወዲያውኑ አውድማው ላይ ሲሞት
2. ህፃን ደባሽ ጌታቸው ዕድሜ=8 ቀኝ እጁ የተቆረጠ እንዲሁም
3. የልጆቹ አባት አቶ ጌታቸው መለሰ ዕድሜ=46 በከባድ ሁኔታ የቆሰለ
4. ሰባት ከብቶች ወዲያውኑ ሲሞቱ
5. አውድማው ላይና በዙሪያው የነበረ ሦስት ክምር እህል ከ30 ኩንታል በላይ የሚገመት እህል ወድሟል።
የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት ግብረ ሰዶም የሚፈፅም፣ህፃናትን የሚያርድ፣ንፁሃንን የሚረሽን በመድፍ አረር የሚቆላ፣አራጅ፣ደፋሪ ፀረ አማራ በመሆኑ በህዝባዊ ማዕበልና እምቢተኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ተባብረን እናስወግደው ሲሉ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ሃምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ ጥሪ አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄ/ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ፋኖ ሽፈራው አለልኝ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 05/ 2018 ዓ.ም
+4
የዚህ ዘመን ትውልድ ከምንሆን ምነው በጨነገፍን ኖሮ፡፡ ምነው ይህን ከሚያሳዬን በእናታችን ማህፀን ውሀ በሆንን ፡፡ አሁን የእኛ መኖር መኖር ነው? እነዚህ ሰዎች ሲታረዱ በአይነ ህሊና ማየት እንዴት ያስመርራል፣ የወገን ያለህ ! የሰው ያለህ እያለች የምትቃትት ነብስ መስማት ስንት ሞት ነው? አቅም አጥቶ አንገት መስጠት !! በእሱ ቦታ ሆኖ ሲያስቡት እጅግ እጅግ እጅግ …….. ልብ ይሰብራል፡፡
ቀሩትን ከማን ጋር ቆመን፣ እንዴት አብረን፣ በምን ሥርአት እናድናቸው? አሁን በዚህ ግሩፕ ላይ ያለ 1025 ሰው ብቻ ታምር አይሰራም ነበር? ግን ለምን ከገዳዮቹ በላይ ጨካኝ ሆነን ? ግን ለምን ልባችን ደነደነ? ግን ለምን ግን ለምን…………… በእነዚህ ሰዎች መታረድ ውስጥ እየታረዱ ዝም ብሎ ያዬስ የለበትም? ለታረዱት ሰዎች ማዳን እየቻሉ ዝም ያሉት ምን ጠቀሟቸው? ወገኔ ሆይ በአንድነት እንምረር፡፡
ወርቁ ለንደን ፋኖ
በሲዳማ ክልል የመንግሥት ሰራተኞች እና ህዝቡ በጋራ በፋሽሽቱ ብልፅግና ስራት ላይ የተቃውሞ ድምጽ እያሰሙ ነው።
ህዝባዊ ተቃውሞው የተነሳበት ዋና ምክኒያት ፋሽሽቱ ብልፅግና ለመንግሥት ሰራተኞች ያደረገው የደሞዝ ጭማረ ትላንት ለመምህራን ከተከፈለ በኋላ ለብሮና የጤና መስርያ ቤት ለመክፈል አቅም የለኝም በማለቱ ነው ተብሏል!!
#አባት_አርበኛ_መሳፋት_ተስፉ_መልዕክት
🔹አርበኛ ጌትነት መሳፍት ተሰዋ እንጅ አልሞተም
(ህዳር 5/03/2018 ዓ.ም)
🔹የአባት አርበኛው የድምፅ መልዕክት እነሆ‼️
" አማራ አንድ ባለመሆኑ ከባድ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው"
በቀን 5/3/2018 ዓ.ም
በደምበጫ ግንባር የተማረኩ የፋሽሽቱ አቢይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ አራዊት ሰራዊቶች!!
በጋምቤላ ክልል የንፁሃኖች ሞት ይቁም በሚል የመደበኛ ተማሮች የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ባለበት ሰዓት የስራቱ ስልጣን ጠባቂ ሃይሎች ለሰልፍ በወጡ መደበኛ ተማሮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቢሞክሩም ተማሪዎች ግን አንመለስም በሚል የተቃውሞ ሰልፋቸውን ማሰማት መቀጠላቸው ነው የታወቀው!!!
በእውነቱ ጨክኖ የሚገፈትረው ሃይል ነው የጠፋ እንጅማ የፋሽሽቱ አቢይ አህመድ ስራት አብቅቶለታል ነበር👨🏽🦽
+3
በአርሲ ምድር ላይ እናቶችና ህፃናት በሚታ*ረዱበት በዚህ አስጨናቂ ሰዓት እነዚህ የብልፅ*ግና ፕሮፓጋንዲስት ካልጠፋ ቀን "አርሲ ሰላም ነው፣ ምንም አልተፈጠረም" የሚል የጭካኔ መልዕክት ለማስተላለፍ በአርሲ ተራሮች ላይ ጉዞ Hiking) ላይ ናቸው።...
ከገዳ*ዮቹ ባልተናነሰ የንፁሀንን ድምፅ በማፈን የጭፍጨፋው አስፈፃሚ አካል ናችሁ።
ቀን ይመጣል! ተሸማቅቃችሁ የምትኖሩበት ጊዜ ይመጣል፤ አንረሳውም!
#followዋችን እናንሳ🙏
፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ!!!
ችጓሊ እና አዲስ ቅዳም በጠላት ዋይታ ተሞልተዋል።
ዛሬ ህዳር 5/2018 ዓ/ም አመለኛዋ ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ባደረገችዉ የሁለት ከተሞች ልዩ ኦፕሬሽን ጠላትን ስትረፈርፈዉ አርፍዳለች።
በዚህ ከለሊቱ 12:00 ጀምሮ አዲስ ቅዳም ከተማ እና ችጓሊ ታዳጊ ከተማ ላይ በተደረገ ልዩ የማፅዳት ኦፕሬሽን አዲስ ቅዳም ከተማ የተከማቸዉ የብልፅግና ታጣቂ ከምሽጉ ሳይወጣ በአለበት የተረፈረፈ ሲሆን ችጓሊ ከተማ ዉስጥ በመግባትም ጠላት ይዘርፍባቸዉ በነበሩ ችጓሊ እና ችጓሊ አቅራቢያ የሚገኙ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ጠላትን ወደ አፈርነት ቀይራዋለች።
በዚህም መሰረት
ችጓሊ ላይ 6 የብልፅግና ታጣቂ ተወግዶ 13 ቁስለኛ ብዛት ካለዉ ቁሳቁስ ጋር ጋር በዉጤት አስመዝግቦ መዉጣት የተቻለ ሲሆን በአዲስ ቅዳሙ ኦፕሬሽንም
9 የተደምሰሰ ከ10 ቁስለኛ ጋር እስካሁን ባለዉ ማረጋገጥ ተችሏል።
አጠቃላይ በዛሬዉ የሁለት ከተሞች ልዩ ኦፕሬሽን
_ጥላየ እንየዉ
_ምንችል ክንዴ
_ ደሴ አብዬ የተባሉ የከተማ ወሻ |ፖሊሶችን| ጨምሮ
15 ጠላት ተደምስሶ፣
23 በላዩ ቁስለኛ በመሆን የነገ ሞቱን ቀብድ ሲቀበል ፣
8 ሰልጣኝ | ግልገል | የብልፅግና ታጣቂ ምርኮኛ፣
3 ክላሽንኮቭ ፣
2 የቃታ መሳሪያ
1የብሬን ሸንሸል 71 የብሬን ተተኳሽ ፣
8 የክላሽ ካዝና ከ176 ተተኳሹ፣
5 ኩንታል የተፈጨ እህል
20 ሊትር ዘይት፣
150 ኪ/ግ ምስር
9 ኩንታል ድንች
ከተለያዩ የማብሰያ ቁሳቁሶች ጋር ገቢ ተደርጓል ።
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!
ህዳር 5/2018 ዓ/ም
ይቀጥላል ገና........
በአርሲ የኦርቶዶክሳውያኑ ጭፍጨፋ እንደቀጠለ ነው፡፡
ትናንትም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በጓሮው ገድለው ጥልውት፣ ንብረቱን ነድተው እንደሄዱ ታውቋል፡፡ መንግሥት ደግሞ 'የግድያውን መረጃ ወደ ውጭ እያወጣችሁ ነው' በማለት ኦርቶዶክሳውያኑን እያሰረና እያሳደደ ይገኛል፡፡
በአጭሩ ገዳዮችም፣ መንግሥትም በአንድነት ኦርቶዶክሳውያኑ ላይ ዘምተዋል፡፡ የመንግሥት ተጠያቂነት ዕጠፍ ድርብ ነው፡፡ በወንጀሉ በመሳተፉም፣ ወንጀለኞችን በማስቻሉም ጭምር፡፡ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ዐለም አቀፍ ተቋማት ግንዛቤ እያገኙ፣ የጉዳዩንም አሳሳቢነት እየገለጡ ነው፡፡
በሚቀጥሉት ቀናትም ይኸ ይቀጥላል፡፡ በዚህ የተበሳጨው መንግሥት ጭፍጨፋውን ከማስቆም ይልቅ ኦርቶዶክሳውያኑን ማሳደድ፣ ማፈናቀል እና ማሰርን አማራጭ አድርጓል፡፡
እኛም በአርሲ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በሰላም መኖሩ እስኪችሉ፣ በግፍ ለተጨፈጨፉትም ፍትሕ እስኪሰፍን ድረስ ጩኸታችን አይቋረጥም፡፡
ፍትሕ በግፍ እየተጨፈጨፉ ላሉ የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን፡፡
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ በላይ ዘለቀ ሻለቆች ፣ የኢንጅነር ክበር ተመስገን ልጆች ቀስተደመና ሻለቃ በጥምረት በሶስት አቅጣጫ ወደ ግራ ቅዳምን ቀጠና የተንቀሳቀሰው ጡት ቆራ* ጩ ሰራዊት መውጫ አጥቶ እየተርመሰመሰ ነው።
ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም ጀምሮ ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ወደ ወርቅማ ፤ ከደብረ ማርቆስ እና ከአማኑኤል ከተማ ተነስቶ ወደ ግራ ቅዳምን በሌላ አቅጣጫ ከእንቡሊ ከተማ ወደ ግራ ቅዳምን ከተማ ለመግባት በመድፍ የታገዘ ሙከራ ያደረገው አረመ* ኔው ሰራዊት በሁሉም ቀጠና ውጊያ ያደረጉት 99ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላት በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰውበታል።
በርካቁ ስለኛው ወደ አማኑኤል ጤና ጣቢያ እና ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል መግባቱን አረጋግጠናል።
በተመሳሳይ ከደብረማርቆስ እና ደብረኤልያስ በመነሳት ወደ ቸርተከል እና ሊባኖስ የተንቀሳቀሰውን ጠላት 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር በሚገባ በማናገር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወደ ምሽጉ እንዲመለስ አድርጎታል።
በተመሳሳይ የጠላት ራስ ምታት የሆኑት 201ኛ ኮር 54 ክፍለ ጦር አራጤ ላይ ጠላትን ሲያርበደብው አርፍዷል።
ለጠላት የማይንበረከከው መብረቁ ተፈራ በመካናይዝድ ደረጃ ተደራጅቶ ጠላት ውጊያ ብከፍትም የመጣውን የአረመኔአዊ ሠራዊት ንስሮቹ የመብረቁ ተፈራ ልጆች እማይቀመሱ ሆነዋል ።
ከሞጣ_ባህርዳር አገር አቋራጭ መንገድ ከተዘጋ አምስት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ይኸንም አድርጎ ያልተሳካለት የአብይ ወንበር አስጠባቂ ስርአት
በቀን 05/03/2018/በጠዋት 12:00 ከሞጣ ተነስቶ ዙ 23 ታጥቆ የመጣ ቢሆንም የ መብረቁ ልጆች አራጢ ላይ እንደ እባብ ሲቀጠቅጡት አርፍደዋል ምቱን መቋቋም ሲያቅተው ከወይን ውሀ እና ከሞጣ ተጨማሪ ሀይል በማምጣት ሙትና ቁስለኛ ተሸክሞ ወደ መጣበት ተመልሶ ሂዷል።
አዲስ ቅዳም ችጓሊ እና አዴት ከተማ በመግባት የአረመኔው ሰራዊት አገልጋይ የነበሩ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን መስራት ተችሏል።
በሁሉም አቅጣጫ የደረሰበትን ምት መቋቋም ያቃተው የአረመኔው ሰራዊት አባላት እየከዱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 05/2018 ዓ.ም
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
ሻለቃ መሪው በፋኖዎች በቁጥጥር ስር ዋለ!
ህዳር 05/2018ዓ.ም
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር ተከዜ ክፍለ ጦር መረጃን በማነፍነፍ የ61ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሻለቃ ምክትል መሪ የሆነው መቶ አለቃ በእውቀቱ ምስጋናው ከድልብ ወደ ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም ከተማ በሚወስደው መንገድ ዴንሳ ከተማ ላይ በተከዜ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ህዳር 04/2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል።
ይህ ግለሰብ ላስታ ወረዳ ኩልመስክ ከተማ ላይ ከዚህ በፊት ስምንት ንፁሃንን የረሸነና ያስረሸነ፣የብዙ ወጣቶችን አካል ያጎደለ፣የአባውራ ሴቶችን የደፈረ፣ህዝባዊ መድረክ ላይ በይፋ ኩልመስክ ከተማን ጥቁር አለብሳታለሁ እያለ ማህበረሰቡ ላይ ግልፅ የስነ ልቦና ጫና ያደርስ የነበረ፣ከነጋዴው ብሎም ከማህበረሰቡ ሙስና የሚቀበልና የግል ጥቅሙን የሚያግበሰብስና ፍፁም ስነ ምግባር የጎደለው ጥቁር አማራ ነበር።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 05/ 2018 ዓ.ም
የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አላማው አድርጎ የገባው የኦሮማው ጨፍጫፊ ስርአት ሙህራንና የተማረውን አካል ታርጌት አድርጎ መግደል ስራው ሁኗል፡፡
አማራ እንዳይማር፡የተማርው እንዲባርረና እንዲገደል፡ተቆርቋሪ እንዳይኖርውና ወደ ድንጋይ ዘመን እንዲለወጥ ሆን ተብሎ እየተሰራ ነው፡፡
ይህን ዶክተር ሌሊት ከቋሪት ገበዘማሪያም ወደገጠር ወይበይኝ በሌሊት ወጥተው ከቤቱ አውጥተው እረሽነውታል፡፡ምንም ምክንያት የላቸውም፡፡አማራ ነው ፣ፋኖን ሊያክም ይችላል በሚል ነው፡፡
