ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish3 218
Obunachilar
+18224 soatlar
+2627 kun
+63730 kun
Postlar arxiv
ፋኖ በቆረጣና በከበባ ታክቲክ ተጠቅሞ በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ የተደረጉበትና ከ50 በላይ ክላሽንኮቭ የተማረከበት የእብናት ግንባሩ ትንቅንቅ!
"ምርጫ አስፈጽማለሁ፣ ቀጠናውንም ነጻ አደርጋለሁ" በሚል እብሪት ዛሬ ሚያዚያ 12/2018 ዓ/ም በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የብልፅግና ወራሪ ሠራዊት፡ በአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ በ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አርበኞች ከበባ ተፈፅሞበት ዶግ አመድ መደረጉ ተረጋግጧል።
ከአዲስ ዘመን፣ አምቦ ሜዳና ቦረን መስክ እንዲሁም ከእብናት ዝሀ መነሻውን አድርጎ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ነው ሊመከት የማይችለው የቆረጣና የከበባ ማጥቃት እርምጃው የተወሰደው።
በኮሩ ምክትል አዛዥ አርበኛ ጌቴ መሳፍንት በተመራው በዚህ ከባድ የቆረጣና የከበባ ማጥቃት፡ ከጄኔራል ፈንታ በላይና ከፋሲል ክፍለ ጦሮች የተወጣጡ አሃዶች እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ተናበው ጠላትን ቀለበት ውስጥ በማስገባት እንዳይወጣም ሆነ ተጨማሪ እንዳይመጣ ዙሪያ ገባውን ክርችም አድርገው በመዝጋት ከባድ እርምጃ እንደወሰዱበት መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
በዚህ የተቀናጀ የቆረጣ ማጥቃት፡ ቀሪው የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛውን ሳይሰበስብ ትጥቁንና ስንቁንን በትኖ መፈርጠጡ ታውቋል።
አርበኞቹ የቆረጣ ውጊያ ሣይንስን ከአማራዊ የጦር ብልሃትና ፍፁም ጀግንነት ጋር በማዋሃድ በወሰዱት በዚህ የቆረጣ እርምጃ፡ የጠላት ኃይል ለደቂቃ እንኳን ቆሞ መመከት አቅቶት ተፍረክርኮ ከባድ ኪሳራን ተከናንቧል።
በዚህ ተጋድሎ ከ70 በላይ የጠላት አባላት ሲገደሉ፡ ዛሬ ማምሻውን የአካባቢው ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ የሟች ወታደሮችን አስከሬን በጅምላ ሲቀብር አምሽቷል።
በዚህ እጅግ ፈጣንና ጠንካራ የቆረጣና የከበባ ማጥቃት ከተገደሉት በተጨማሪ ከ30 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች በፅኑ ሲቆስሉ፡ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እጅ ከፉንጅ መማረካቸውን ነው
ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ከ204ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ የቻለው።
ፋኖ እምቅ ኃይሉንና ልዩ የቆረጣ ውጊያ ጥበቡን ባሳየበት በዚህ ተጋድሎ፡ ከ50 በላይ ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ በርካታ ተተኳሾች ማርኮ ታጥቋል።
በአሁኑ ሰዓት ቀጠናው ሙሉ በሙሉ በጄኔራል ፈንታ በላይ እና በፋሲል ክፍለ ጦር ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን፡ የፋኖ ኃይሎችም በአስተማማኝ የንቃት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
አንድ ኮሎኔልን ጨምሮ የሻለቃ አዛዦችና ከ60 በላይ ወታደሮች ያለቁበት የዛሪማው ትንቅንቅ!
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር በሰሜን ጎንደር አዲ አርቃይ ወረዳ ዛሪማ ግንባር የዐብይ አህመድን ወራሪ ሠራዊትና ተላላኪ ባንዳዎቹን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል።
የብልፅግናን አገዛዝ እድሜ ለማራዘምና በአማራው ላይ የሚፈፀመውን ሁለተናዊ እልቂት ለማስቀጠል ከከባባድ እስከ ቡድን የጦር መሣሪያዎች ታጥቆ ምርጫ አካሂዳለሁ በሚል ሲንቀሳቀስ በነበረ ግብረኃይል ላይ ነው እርምጃው የተወሰደው።
ከድብ ጠለምት ተከዜ እና ከጭና ክፍለ ጦር የተወጣጡ የ208ኛ ኮር ጥምር አሃዶች፡ ጠላት ከዛሪማ ተነስቶ ወደ ብስኒትና ጥራይና ቀበሌዎች ለመግባት እየተንቀሳቀሰ ባለበት በሁለትና ሦስት ቦታ ቆርጠው በመምታት እንደደመሰሱት መረብ ሚዲያ ከበላይ ዘለቀ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
የጠላት ኃይል በሁለት አቅጣጫዎች ተከፍሎ ያደረገውን እንቅስቃሴ፡ አርበኞቹ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት እርምጃ በመውሰድ ድባቅ የመቱት ሲሆን፡ ማምለጥ ያልቻለው የጠላት ኃይል በአሁኑ ሰዓት በተራራ ላይ ተከቦ መውጫ አጥቶ እየባዘነ ይገኛል።
ፋኖ እምቅ ኃይሉንና ልዩ የውጊያ ጥበቡን በተጠቀመበት በዚህ ተጋድሎ፡ ለጊዜው በስም ያልታወቀ አንድ ኮሎኔልንእና የሻለቃ አዛዦችን ጨምሮ ከ60 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን ነው ጣቢያችን ከበላይ ዕዝ ለማረጋገጥ የቻለው።
በተጋድሎው ከ40 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከ20 በላይ የሚሊሻ አባላት ናቸው የተገደሉት።
በዚህ ተጋድሎ ከተገደሉት የጠላት ኃይሎች መካከል አንድ የአዲ አርቃይ ወረዳ የምርጫ አስተባባሪ አመራር እንደሚገኝበት ታውቋል።
በተጨማሪም በተጋድሎው እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገዛዙ ወታደሮች ቆስለው፡ ሁለት ኦራልና አንድ አይሱዚ በተደጋጋሚ እየተመላለሱ ወደ ደባርቅና አዲ አርቃይ ሆስፒታሎች እንደወሰዷቸው ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።
በዚህ አስደማሚ ኦፕሬሽን ከ38 በላይ የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና በርካታ ያልተቆጠሩ ተተኳሾች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
ጠላት ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ወደ መጣበት ለማምለጥ እየተፍጨረጨረ ቢሆንም፡ የ208ኛ ኮር አርበኞች ቀሪውን ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ከበው ከባድ እርምጃ እየወሰዱበት ይገኛሉ ተብሏል።
ፍኖተ አማራ ሚዲያ ውጊያው እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃዎችንና የምርኮ ምስሎችን ይዞ የሚመለስ ይሆናል።
+2
#ስርዓቱ_በየቀኑ_መፈራረሱን_ቀጥሏል‼️
በደ/ወሎ አልብኮ ወረዳ ካለው አድማ ብተና የ26ኛ ሻለቃ አባል የነበሩ አራት አድማ ብተናዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን ስርዓቱ አማራ ላይ ከሚደርገው ማንነት ተኮርና ጭፍጨፋ ይባስ ብሎ አሁን ላይ ተስፋ ስለቆረጠ ወንጀለኞችን ነፍስ ያጠፉ ዘራፊና ወንበደዎችን ኑ ተጎኔ ተሰለፉና አማራን እናጥፋ አይነት ዘመቻ ሲጀምር በየሄድንበት ንፁሀንን ሲገደል ሀብት ንብረ ሲዘረፍ የዚህ ስርዓት ተባባሪ አንሆንም ከአሁን በኋላ ከፋኖ ጋር ሆነን ህዝባችንን እንክሳለን ብለዋል። የ25ኛ ክ/ጦር አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል የ104ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለንስር አማራ በላከው መልዕክት ገልጿል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
13/ዐ8/2018 ዓ.ም
#የባንዳ_መጨረሻው❌
ይሔን ባንዳ ልጅ አስታወሳችሁት?
በአንድ ወቅት ከሸዋ በረኸት አካባቢ የፋኖ አባል ነኝ ሲል የቆየ በሚዲያ ፋኖን የሚከፋፍል፣ ከዛም ወደ ደብረብርሀን ከተማ ሔዶ ለጠላት እጅ የሰጠ፣ ቀኑን ሙሉ በTicktok Live ላይ ተቀምጦ ፋኖን ሲከፋፍል የከረመ ነበር። ጊዜ እውነትን ያሳያል።
የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ የሚገኘውን አማራ ጠል ገዳያችንን "ዓብይ አህመድ ሺ ዓመት ይንገስ!፣ ኤልያስ አበበ የኔ ሙሴ!፣ ብልፅግና ዕድሜ ዘመኔን ይግዛኝ!" በሚለው አባባሉ ይታወቃል።
ብልፅግና ለጊዜው ተጠቅሞ እንደ ማስቲካ ይጥልሀል።
"እናትነት ከንቱ"
እናትና ሀገር አንገት ቀረቀሩ፣
ልጅ ነኝ ባለ ባዕዳን እየተቸገሩ።
እርስት ተሸጨ ተቆረሰ ዛሬ፣
እዳ በእዳ ሆና ባዕድ ሆነች ሀገሬ።
ውሃ ልውቀጥ ብሎ ውሃ ዕንቡጩን፣
እንቡጭ ሲል አየሁ መንቦጫቦጩን።
ተደረደረና ቶፋ በድንጋይ፣
ቶፋውም አለቀ ሰባሪ ድንጋይ።
ዘርሽ ሳይቀደስ ተረግሞ ልጅ ሆኖ፣
እናትነትሽ ከንቱ ማህፀንሽ መክኖ።
ኢትዮጵያዬ እናቴ የአለም መድሀኒት ነሽ፣
አሳነሰሽ እንጂ መጣና በክብርሽ።
አጥርሽ ፈራረሰ ድንበርሽ ተገፋ፣
መሀልሽ ዳር ሆነ መሀል የለም ተስፋ።
ታሪካዊቷ አለም ምድረ ገነቲቱ፣
ምድርሽ በዳ ሆነ መራራ መሬቱ።
በምኒልክ ሀገር በአፄ ቤተ መንግስት፣
ዳር ድንበር መጠበቅ በተመከረበት፣
የአድዋ ድል ዝክረ ታሪክ በተከበረበት።
ዛሬ ላይ ብቅ ብለው ይሉናል እኛ ነን፣
ሀገር የመሰረትን ሀገር የገነባን።
እያፈራረሷት አይናችን እያዬ፣
እየታዘባቸው አንበሳው ገብርዬ።
በተሰራው መንደር መኖር አቅቷቸው፣
የበሉትን በልተው ያበላ በላቸው።
ምነው መካን በሆንሽ ጡትሽ ባላጠቡ፣
ላይጦሩሽ ባቀናው አድርገው በቅጡ።
ያማረ ነበረ ከስር መሰረቱ፣
ዛሬ ላይ ሆነ እንጂ እናትነት ከንቱ።
ቀኘው ነኝ።
ሚያዚያ 2018 ዓ.ም
አስቸኳይ ⚠️
የጥንቃቄ መልዕክት ⚠️
አሁን ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በሳሲት፣ በመዘዞ፣ በዘረት፣ በከምር ድንጋይ፣ በባሾ እና በአንኮበር ቀጠናዎች የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የተሳካ የደፈጠ ኦፕሬሽን ፈጸመ።♨️
የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አካል የሆኑ ክፍለ ጦሮች ማለትም ጀኔራል ፈንታ በላይ ክፍለ ጦር እና ፋሲል ክፍለ ጦር በጥምረት ዛሬ:-
▪ከአዲስ ዘመን፣ አምቦ ሜዳ፣ ቦረን መስክ
እንዲሁም
▪ከእብናት እስከ ዝሀ ቦረን መስክ በሁለት አቅጣጫ ጀኔራል ፈንታ በላይ ክፍለ ጦርን እና ፋሲል ክፍለ ጦርን ለማፈን እና ቀጠናውን ነጻ ለማድረግ፤ እንዲሁም መሀሉን ነጻ በማድረግ ሬሽን እንደልቡ ለመቀባበል፤ በተጨማሪም የደም ምርጫውን ለማስፈጸም በማሰብ የተንቀሳቀሰው ወራሪ ሀይል በደፈጣ ተቀጥቅ*ጧል።
ማፈን አይደለም ለደቂቃ ቦታው ላይ መቆየት ሳይችል ምርኮኞቹን፣ ቁስለኞቹን እና የሞቱትን ሳይሸክፍ እግሬ አውጭኝ ብሎ ትጥቁን፣ ተተኳሹን እና አባላቱን አስረክቦ የተወሰኑ ከሞት የተረፉትን በዙ 23 አጂቦ በዘፈ ቀደ እየተኮሰ ወደ መጣበት ተመልሷል።
♻️ በዚህ ኦፕሬሽንም የተገኙ ድሎች:-
🔸በምርኮ ከ20 በላይ ወራሪ የጠላት ሀይል ሲማረክ፣
🔸 ከ70 በላይ ሙት (ማህበረሰቡ እንዲቀብራቸው የተደረጉ)
🔸 ከ30 በላይ ቁስለኛ
🔸 በትጥቅ ደረጃ ከ50 በላይ ነብስ ወከፍ መሰሪያወች ገቢ ተደርገዋል!!
🔸 ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ በርካታ ተተኳሽ ተማርኳል።
አሁን ባለው ሁኔታ ቀጠናው በጀኔራል ፈንታ በላይ ክፍለ ጦር እና ፋሲል ክፍለ ጦር ቁጥጥር ስር ነው።
ተጋድሎው ይቀጥላል...
ምስል:- በአንድ አቅጣጫ ብቻ የተማረከ የጠላት ሀይል
በማጀቴ የአርሶ አደሩን ሰብል ሲያቃጥሉ የነበሩ የአብይ አህመድ ቅጥረኞች ኃይሎች ተደመሰሱ!!
የአማራን ሕዝብ የህልውና መሠረት የሆነውን የግብርና ምርት በማውደም ሕዝቡን ለረሃብና ለስደት ለመዳረግ የታቀደውን ሴራ፣ የሸዋ ጀግኖች የአባት አርበኞች እና ማልበረሰቡ በወሰዱት መብረቃዊ እርምጃ አከሸፉት። ትናንት በኤፍራታ ግድም ወረዳ ማጀቴ ዙሪያ፣ የገዥው ፋሽስታዊ ሥርዓት ተላላኪ የሆኑት የኦሮሞ ብልፅግና እና የብአዴን ሚሊሻዎች፣ የአማራን አርሶ አደር የዓመት ድካም የሆነውን የጤፍ ክምር በእሳት ሲያቃጥሉ መዋላቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
ይህን የጥፋት ተግባር በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት አሞተ ኮስታራዎቹ የአባት አርበኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በጋራ በመቀናጀት ሰብላችንን በደማችን እንጠብቃለን በሚል ቆራጥነት በጠላት ላይ አይቀጡ ቅጣት ጥለውበታል። በተወሰደው የተቀናጀ ጥቃት፣ የአርሶ አደሩን ቤትና ንብረት ሲያወድም እና ሲያቃጥል የነበረው የጥፋት ኃይል ክፉኛ የተመታ ሲሆን፣ የሚከተሉት ውጤቶች ተመዝግበዋል፦
በዚህም በንጹሐን ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ዋነኛ መሪና የሥርዓቱ ታማኝ አገልጋይ የነበረው የሚሊሻ አስተባባሪ ሰይድ አንድሮ፣ በጀግኖች ክንድ ተመትቶ ዳግም በማይመለስበት ሁኔታ ወደ መቃብር ተሸኝቷል። በውጊያው በርካታ የኦህዴድና የብአዴን ዳይፖር ሚሊሻዎች ላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ በማድረስ የጠላት ስምሪት እንዲበታተን ተደርጓል።
ጀግኖቹ በወሰዱት ፈጣን እርምጃ፣ ተጨማሪ የጤፍ ክምሮች ሳይቃጠሉ ማዳን የተቻለ ሲሆን፣ የአካባቢው አርሶ አደርም በቆራጥነት ራሱን እንዲከላከል ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሯል። የፋሽሽቱ አብይ አህመድ ሥርዓት አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚያደርገው ማንኛውም ሙከራ በጀግኖች ክንድ ይመክናል። አማራ የሆነ ሁሉ በያለበት ተደራጅቶ ንብረቱንና ማንነቱን የመጠበቅ ታሪካዊ ግዴታ አለበት" ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
ሚያዝያ 12/08/2018 ዓ.ም
በዛሬው እለት #1ቲም ፓራ ኮማንዶወች እና #3ሶስት የመከላከያ አባላት ጋንታ መሪውን ጨምሮ ፋኖን ተቀላቅለዋል።
===========================
.............ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም
ያለአንድ ጥይት ተኩስ ያለምንም መስዋትነት የፀጥታ መዋቅሩን በተደራጀ መንገድ እያፈረስነው ነው ፦
1.አበበ ባለው ....ፓራኮማንዶ.74ክ/ጦር
2.መልካሙ ደረጃው..ፓራ ኮማንዶ74ክ/ጦር
3.ጨመረ ይመን.....ፓራ ኮማንዶ74ክ/ጦር
4.ማቲያስ ከበደቃሚሶ...መከላከያ74ክ/ጦር
5.ሸጋው ክንድየ ....ፓራ ኮማንዶ74ክ/ጦር
6.ታደሰ ሙልጌታ......ፓራ ኮማንዶ74ክ/ጦር
7.ይበልጣል ማርከሻ....ፓራ ኮማንዶ74/ክ/ጦር
8.ይበልጣል አለቤ...ፓራ ኮማንዶ 74ክ/ጦር
9.አበበ ዋለ.....ሚሊሻ 74ክ/ጦር
10.አስር አለቃ ታዴ ጌታቸው...መከላከያ ጋንታ መሪ ወደ 54ክ/ጦር
11.ንጉስ ዳምጥ...መከላከያ ከ25ክ/ጦር
12.ፀዳሉ ውቤ......መከላከያ ከ25/ክ/ጦር
ሲሆኑ እስካሁን ድረስ ተታለን ቆይተናል ከዚህ በሗላ ማንም ተቋሙ ላይ መቆየት የሚፈልግ የለም ሁሉም ለመውጣት ምቹ ሁኔታ እየጠበቀ ነው ያለው በማለት አስተያየታቸውን የገለፁ ሲሆን በአማራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
<< አሁንም አልረፈደም ኑ አማራዊ ግዴታችን እንወጣ >>
የአፋብን የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት!
"የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት አልቻልኩም።
ይሄንን ፀረ አማራ ስዓት ለመገርሰስ ከሁለት ዓመት በፊት ፋኖን ተቀላቀልኩኝ። በአሁን ሰዓት በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 21ኛ ክፍለጦር ብሬን ምድብተኛ ሆኜ እየታገልኩ ነው)
"...አርቀህ አታሳደው፡ የተመለሰ እንደው መከራው ላንተ ነው" እንዲሉ አበው፡
አዲስ አበባ ላይ አትኖሩም ተብለው ተገፍተው በረሃ የወረዱት እነዛ ጀግኖች፣ ዛሬ በጦር ግንባር ላይ ጠላትን የሚያርበደብዱት እነሱው ናቸው። ገፊው አካል ገፍቶ መጨረሻው ላይ ስላደረሳቸው፡ ዛሬ ተመልሰው እየመጡ ነው።
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት!
"የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት አልቻልኩም።
ይሄንን ፀረ አማራ ስዓት ለመገርሰስ ከሁለት ዓመት በፊት ፋኖን ተቀላቀልኩኝ። በአሁን ሰዓት በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 21ኛ ክፍለጦር ብሬን ምድብተኛ ሆኜ እየታገልኩ ነው)
"...አርቀህ አታሳደው፡ የተመለሰ እንደው መከራው ላንተ ነው" እንዲሉ አበው፡
አዲስ አበባ ላይ አትኖሩም ተብለው ተገፍተው በረሃ የወረዱት እነዛ ጀግኖች፣ ዛሬ በጦር ግንባር ላይ ጠላትን የሚያርበደብዱት እነሱው ናቸው። ገፊው አካል ገፍቶ መጨረሻው ላይ ስላደረሳቸው፡ ዛሬ ተመልሰው እየመጡ ነው።
አሳዛኝ የአፈና ዜና
መርሻ ትባላለች የደ/ብርሃንከተማ ልጅ ነች።በደቂቀ-ዘርዓያዕቆብ ማህበር ብዙ መንፈሳዊ ተግባራትን ስታስተባብር ብዙዎች ያውቋታል። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለማንነቷ ከአማራ ልዩ ሀይል እስከ ፋኖ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ጭምር በመያዝ ከጠላት ጋር ግንባር ለግንባር የምትፋለም የሸዋረገድ ገድሌ መንፈስ ወራሽ ሴት አርበኛ ነበረች። ታድያ ከቅርብ ግዜ ወድህ ከትግል እርቃ ትዳር መስርታ የግል ህይወቷን እየመራች ብትገኝም በደቂቀ-ዘርዓያዕቆብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዋና በደ/ብርሃን የከተማ ሰላማዊ ትግል ወቅት ከፍተኛ ጫና አሳድራብናለች በሚል ቂምና በቀልተኝነት የቀድሞው ጓዶቿን መሰዋት ተከትሎ ሀዘንሽን በሚዳ ገልጸሻል በሚል የሰ/ሸዋ ዞንና ደ/ብርሃን ከተማ የኦዴድ ብልፅግና አሽከሮች እህታችንን ከሰወሯት ሰንብተዋል።ይገርማል ሀዘን እንኳ መግለጽ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው አማራ የሚገኘው። pls ሁላችንም ለእህታችን ድምጽ እንሁናት!!!
ሰበር የድል ዜና !!
ቀን 12/8/2018ዓ.ም
🔸208ኛ ኮር በሰሜን ጎንደር በአዲያርቃይ ወረዳ በዛሪማ ግንባር ከ60በላይ ጠላት በመደ*ም*ሰስ ድል አደረገ!
የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር ከድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር እና ከጭና ክፍለጦር የተወጣጡ አህዶች በጥምረት ጠላት ከዛሪማ ወደ ብስኒት እና ወደ ጥራዒና ቀበሌዎች ቀጠና በማምራት የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ በማቀድ በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰውን ጠላት ተከላክሎ መልሶ በማጥቃት ድባቅ በመም*ታት አቅዱን ከሽፎበት ሙት እና ቁስ*ለኛውን ተሸክሞ ወደ መጣበት ቢመለስም ማምለጥ ያልቻለ ሀይል ተራራ ተሰቅሎ በጀግናው ሰራዊታችን ተከቦ ይገኛል።
በዚህ አውደውጊያ በስም ያላረጋገጥነው አንድ ኮለኔልን እንዲሁም የሻለቃ አዛዦችን ጨምሮ በርካታ ሰራዊቱን አስ*ደምስሶ ሙት እና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እያፈገፈገ ወደመጣበት ለማምለጥ እየተፍጨረ*ጨረ ይገኛል።
በአውደ ውጊያው የተገኙ ድሎች :-
✅ ከ40በላይ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ የመከላከያ ሰራዊት መግ*Deደል ተችሏል!
✅ከ20በላይ የሰላም አስከባሪ እና የሚኒሻ ሰራዊት መግ*Deል ተችሏል!
✅ አንድ የአዲርቃይ ወረዳ የምርጫ አስተባባሪ አመራር ተገድ*ሏል!
✅ሁለት ኦራል እና አንድ አይሱዚ ቁስ*ለኛ ወደ ደባርቅ እና አዲያርቃይ ሆስፒታል ገብቷል!
✅ከ38በላይ የነብስ ወከፍ ክላሽ እንዲሁም ያልተቆጠረ በርካታ ልዩ ልዩ ተተኳሽ ተማ**ርኳል!
ውጊያው እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል!
ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን !
የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የ208ኛ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ ሳሙኤል አበራ !
ድል ለአማራ ፋኖ
