uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 401
Obunachilar
+124 soatlar
+757 kun
+1 40730 kun
Postlar arxiv
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ሚስጥራዊ በረራዎች ወደ አዲስ አበባ ተደርገዋል ለምን ?? በኢትዮጵያ እና በየተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለው ትብብር በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ካለው ጦርነት ጋ
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ሚስጥራዊ በረራዎች ወደ አዲስ አበባ ተደርገዋል ለምን ?? በኢትዮጵያ እና በየተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለው ትብብር በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ አጠያያቂ ሆኗል! ​ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ADD) ከየተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሁለት አጠራጣሪ በረራወችን አስተናግዷል፦ 1ኛ. ​ሌላኛው በራራ የግዙፉ አን-124 ጭነት አውሮፕላ (UR-ZYD) የተሰኘው አንቶኖቭ An-124-100 ከባድ ጭነት ጫኝ አውሮፕላን (ከአቡ ዳቢ የተነሳ) የበርካታ ቶን ክብደት ያላቸውን ሚስጥራዊ ጭነቶች ይዞ አዲስ አበባ አርፏል። ይህ አውሮፕላን ለወታደራዊ ወይም ለከባድ የኢንዱስትሪ ዕቃዎች መጓጓዣ በስፋት ይታወቃል። 2ኛ. ​የመንግሥት ቻርተር በረራ ሲሆን 5Y-FQA የተባለ የቦይንግ 737 የተሳፋሪ ቻርተር አውሮፕላን ደግሞ በየተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መንግሥት ተከራይቶ ከፍተኛ ዲፕሎማቲክ ወይም ወታደራዊ ልዑካንን ጭኖ በቀጥታ ከአቡ ዳቢ ወደ አዲስ አበባ በረራ አድርጓል። ለምን ሁለቱም በረራወች በአንድ ቀን ተከሰቱ ? ይህ በአንድ ጊዜ የተካሄደ የከባድ ወታደራዊ ጭነት ማጓጓዣ እና የከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉብኝት አገዛዙ በአማራ ክልል እያካሄደ ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ለመደገፍ ከውጭ የሚደረጉ የሎጂስቲክስና የልዑካን ድጋፎች እንዳሉበት አንዱ ማሳያ ነው ። ወንድም Henok Ab

እናተ ስላላችሁ ነው በጎንደር ፋኖ ተስፋ ያልቆረጥነው🙏 የከተማ ልጅ መንደር፣ጎጥ፣ቀበሌ የለውም ❤ ላደረጋችሁት ለከፈላችሁት ሁሉ በጎንደር ወጣቶች ስም ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏🙏
+7
እናተ ስላላችሁ ነው በጎንደር ፋኖ ተስፋ ያልቆረጥነው🙏 የከተማ ልጅ መንደር፣ጎጥ፣ቀበሌ የለውም ❤ ላደረጋችሁት ለከፈላችሁት ሁሉ በጎንደር ወጣቶች ስም ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏🙏

የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አስልጣኞች ወደ ሚቀርባችሁ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል አፋብሃ እንድትቀላቀሉ እና ሃላፊነታችሁን እንድትዋጡ በዚህ ስዓት የአማራን ህዝብ መታደግ ከአማራ ህዝብ ጎን መቆም እና
+3
የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አስልጣኞች ወደ ሚቀርባችሁ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል አፋብሃ እንድትቀላቀሉ እና ሃላፊነታችሁን እንድትዋጡ በዚህ ስዓት የአማራን ህዝብ መታደግ ከአማራ ህዝብ ጎን መቆም እና አማራዊ ሃላፊነትን መወጣት መቻል አለባችሁ

አርበኛ ዘመነ ካሴ በኤርትራዊው በኮ/ል ገብረኣብ ተክሌ አንደበት! "ኮስታራ፣ ከዓላማው ንቅንቅ የማይል፣ አንባቢ፣ አስተዋይ፣ ንግግሩ ቁጥብ እና ሳቢ ነው። ለኢትዮዽያ እና ኢትዮዽያዊነት እንዲሁም ለህ
አርበኛ ዘመነ ካሴ በኤርትራዊው በኮ/ል ገብረኣብ ተክሌ አንደበት! "ኮስታራ፣ ከዓላማው ንቅንቅ የማይል፣ አንባቢ፣ አስተዋይ፣ ንግግሩ ቁጥብ እና ሳቢ ነው። ለኢትዮዽያ እና ኢትዮዽያዊነት እንዲሁም ለህዝቦቿ እኩልነት የማያወላውል አቋም ያለው ከመሆኑም ባሻገር ለአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለም ላለው ሰንደቅ ዓላማ ልዩ ፍቅር አለው። የኢትዮዽያን ሰንደቅ ዓላማ "ኢትዮዽያዊ ሲወለድ ከእናቱ ማሕፀን እንደወጣ የሚጠቀለለው በዚህ ልዩ ጨርቅ ነው!" ይለኝ ነበር።" ይላል ኮ/ል ገብረኣብ ተክሌ Ertean Press Agency Amharic

201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ወደፊት ብቻ 11የአገዛዙ አባላት ፋኖን ተቀላቅለዋል። ከእነዚህም ውስጥ 9ሚሊሻ 2 የመከላከያ አባላት ሲሆኑ ፦ ➢ 8 ክላሽ ➢1አብራራው ➢ 2 ቦንብ ➢ 300 የክላሽ ተተኳሽ ➢ 8 የወገብ ትጥቅ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል ። ዛሬ "ከእነበላይ አገር ጎጃም ተወልጀ በነጋ በጠባ ይከበባል ደጀ " የሚለው ስጋት የበዛበት ጎጃምኛ ዘፈን ወደጎን ተብሎ "ዙሪያ ዳር ድንበሩን አፈሩን ኩሩበት፣አነበላይ ናቸው የተወለዱበት!" የሚለው ጎጃምኛ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ በታጋዪ ስነ ልቦና ላይ ነፍስ ዘርቶ አጥንት አለምልሞ በመጨፈር ላይ ይገኛል። ከድርጅቱ በተቀበለው ተልዕኮ መሠረት አረንዛው ጎንቻ፤አባይ ሸለቆ እና ሶማ ብርጌዶችን ይዞ የነበረው የ9ኛ ሳሙዔል አወቀ ክፍለጦር ወደ ግዙፋ 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር በማሳደግ በቀጠናው ከፍ ብሎ አየበረረ ይገኛል። ክፍለጦሩም በ5 አንጋፋ ሬጅመንቶች ተዋቅሮ የመጀመሪያው ምዕራፍ የፕወዛና አባላቱን በተመደቡበት ቦታ የማስገባት ስራቸውን በድል በማጠናቀቅ ሁሉም ሬጅመንቶች እና አባላቱ በተመደበት ቦታ ተገኝተው ቀጠናቸውን በንቃት መከታተልና ትዛዝ በመጠባበበቅ ላይ መሆናቸውን የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ ፋኖ በላይነህ እናውገው አሳወቀዋል። ለዚህ ድል መገኘትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የ74ኛ ክ/ጦር አመራርሮች፣ ለሬጅመንት አመራሮች፣ ለሬጅመንት አባላት፣ ለወረዳዎቹ ጊዜያዊ መስተዳድር አባላት እና በጦሩ እንቅስቃሴ ወቅት ልዩ አሸኛኘት እና አቀባበል ላደረገልን እነብሴ ሳር ምድር ፣ጎንቻ ሲሶ እነሴ እና እናርጅ እናውጋ ወረዳ ማህበረሰብ፣የጎበዝ አለቃ መዋቅር እና የገበሬው ጦር በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናየን በክ/ጦሩ ስም አቀርባዋል። ይሄንን የአደረጃጀት ስራ በጥራትና በፍጥነት

ጨቅላው አብይ አህመድ ዋይ ዋይ ማለት ጀምሯል! የአፋር ክልላዊ መንግሥትን አልቅሱ ያላቸው ጨቅላው አብይ አህመድ ነው። የአፋር ክልል ያለቀሰው የአብይ አህመድን እንባ ነው። ጨቅላው አብይ አህመድ በኤርትራ ላይ ሲወበራ የሰነበተ ቢሆንም፣ እነ UAE እንደሚገፋፉት ሁሉ "ተው አያዋጣም፤ ያልቅልሃል፣ ያልቅልናል" የሚሉ ምክሮችም እየተሰጠው ነው። በዚህም ምክንያት እራሱ በአፋር ውስጥ ባደራጀው ኃይል አማካኝነት ቅድሚያ ጥቃት ከፍቶ "ህውሃት ጥቃት ከፈተብኝ" በሚል ከኤርትራ ወደ ትግራይ በድንገት ለመቀየስ እያሰበ ይመስላል። ያን ሁሉ በኤርትራ ላይ ለጦርነት ተፈግልተህ እንዳይባል፣ ቦቅቧቃነቱን ሸፍኖ በትግራይ ላይ አምሮቱን ሊወጣ ነው። እኛም እንግዲህ ይህንን እንላለን፦ 1) ከኤርትራም ጋር ይጀመራል ወይም ከትግራይ ጋር ጦርነቱ የኢትዮጵያ ሳይሆን፣ "የኦሮሞ ብልጽግና ከኤርትራ ጋር ወይም ከህውሃት ጋር" ተብሎ የሚገለጽ ነው። ትናንት አማራን "አዲስ አበባ አትገባም" ያለው፣ ዛሬ "ድሬድዋንና ጅጅጋን የኦሮሞ ነው" ያለው ኦህዴድ መቼም ለኢትዮጵያ ጥቅም ዘመተ የሚለን ተብታባ ይኖር ይሆናል። እንቅጩን ለመናገር አማራን ከኦሮሞ ብልጽግና ጋር በጋራ የሚያሰልፈው አንድም አጀንዳ የለም፤ ሊኖርም አይችልም። 2) ሌላው ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ በይፋዊ ይሁንታና እውቅና የትግራይን ክልል ለህውሃት ያስረከበው በጨቅላው አብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ ነው። ታዲያ የትግራይን ክልል እያስተዳደረ ያለውን የክልሉ መንግሥት በኃይል ለመናድ የተደራጀ ኃይል ካለ፣ የአፀፋ መልስ ቢሰጥ ይቅርና ካለ በቅድሚያ ማጥቃት ቢከፍት እራሱ ምክንያታዊ ነው። ይህ በጨቅላው አብይ አህመድ ቋንቋ "በክልል መንግሥት ላይ የተቃጣ መፈንቅለ መንግሥት ነው¡" 😋😀 በቀጣይ ምን እንጠብቅ? በአፋር በስምረት ታጣቂዎች አማካኝነት እንዳደረጉትና የአፋር ክልል መንግሥትን መግለጫ እንዳስወጡት፣ በቀጣይ የአማራ ሕዝብ ከትግራይ ጋር ወደ ዳግም ጦርነት እንዲገባ ደግሞ የጨቅላው አብይ አህመድ ሰራዊት በወልቃይት በኩል ቅድመ-ትንኮሳ ሊፈፅም ይችላል የሚል ግምት አለን። ከዛም ሆዳቸው እንደአዞ አፍ ቦግ ያለው እነ ቅንጭሪት አያሌው መንበር መንደፋደፍ ይጀምራሉ። ነገር ግን ይህንን መሰል ሊከሰቱ የሚችሉ ሴራዎችን ሁለቱም ሕዝቦች (የአማራና የትግራይ ሕዝቦች) ያለመቸኮልና በስክነት መመልከት ይኖርባቸዋል የሚል ፅኑ እምነት አለን። ጥቂትም ቢሆን ለትግራይ ሕዝብ የሚያስብ አመራር፣ ወደ አማራ አፈሙዝ ማዞርን ሊያስብ አይችልም፤ አይገባም።

ተጨማሪ 9 (ዘጠኝ) ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸው ታወቀ፡፡ በአርሲ ዞን በጃጅ ወረዳ፣ በሰጉሬ፣ በወሸባ፣ በተሬ አሜና እና አንጌ (ጓ) ዳቼ አካባቢ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 2018 ዓም በነበረው
ተጨማሪ 9 (ዘጠኝ) ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸው ታወቀ፡፡ በአርሲ ዞን በጃጅ ወረዳ፣ በሰጉሬ፣ በወሸባ፣ በተሬ አሜና እና አንጌ (ጓ) ዳቼ አካባቢ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 24 2018 ዓም በነበረው ጭፍጨፋ ታፍነው ከተወሰዱ 16 ኦርቶዶክሳውያን መካከን ዛሬ ዘጠኙን ገድለው ጥለዋቸው ተገኝተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ስድስቱ እስከአሁንም በገዳዮች እጅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአንድ ሳምንት ብቻ የሟቾች ቁጥር 43 ደርሷል። ለኦሮሚያ መንግሥት፣ ለአርሲ ዞን እና ለብልጽግና ይኸ ልማታቸውና ሰላማቸው ነው፡፡

አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በበርካታ ቀጠናዎች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ ራሱን በሰው ሃይል እያጠናከረ ያለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ በመደራጀት ላይ ያለችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸው
+2
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በበርካታ ቀጠናዎች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ ራሱን በሰው ሃይል እያጠናከረ ያለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ በመደራጀት ላይ ያለችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን ልዩ ኮማንዶዎች አስመርቀዋል:: በበርካታ ቀጠናዎች እየተዘዋወረች ተጋድሎ እያደረገች ያለችው በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠነቻቸውን ምልምል ፋኖዎችን በልዩ ኮማንዶ ደረጃ አስመርቃለች:: ከዚህ ጋር ተያይዞም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም ኮሮቹና በዕዙ ልዩ ዘመቻ በበርካታ ቀጠናዎች እያሰለጠነ ነባሩን ፋኖ በሰው ሃይል እያጠናከረ የህልውና ትግሉ በሚፈልገው ልክ ራሱን እየተደራጀ ይገኛል:: ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ስልጠናውን በቀላል ወጭ ነገር ግን የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ የከፍተኛ እውቀትና ስነምግባር ባለቤት እያደረገ ለህልውና ትግሉ እያቀረበ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

"እጅ ስጥ አለኝ ፈረንጅ፣ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ምን እጅ አለውና የእሳት ሰደድ፣ አያውቅም‘ንዴ ክንዴ እንደሚያነድ!?" አለ ያ የመቅደላ ጀግና ታላቁ ንጉሣችን ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ❗ የብልጽግና ዲጅታል ሚሊሻ ''ለመንግስት እጁን ሰጠ'' እያለ እንደሆነ በግዳጅ መሀል ሰማሁ። መቼም ለነዚህ ነውረኞች እንደሰው ቆጥሮ ምላሽ መስጠት ባይጠበቅብኝም፣ ለባለጌ ዝምታ ዕድል ይሰጣልና "አለን በሜዳው" ማለት አስፈልጓል! ''በህይወቴ ሁለት ቀናትን አከብራለሁ አንዱ የተፈጠርኩበት ቀን ሁለተኛው ለምን እንደተፈጠርኩ ያወኩበትን ቀን።" ይላል ማርክ ትዌይን። አሁን ላይ እኔም ለምን እንደተፈጠርኩ ያወኩበትን ቀን አከብረዋለሁ። ይህም ቀን ለአማራ ህዝብ ጠበቃ፣ ከለላና ደጀን ሆኜ ወደ ትግሉ የገባሁበትን ቀን ነው። "እጁን ለመንግስት ሰጠ" የሚል አሉባልታ በመንዛት የሚቀየር እውነት የሚለወጥ ትግል አልጀመርንም። እስካሁን መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ የብልጽግና ዲጅታል ሚሊሻዎችን ከየትኛው እንስሳ ውስጥ እንደምንመድባቸው ነው። ለጊዜው ባለ ሁለት እግር አህዮች ምድብ ላይ አስቀምጠናቸዋል። እንደሕዳር አህያ የመጣ የሄደው የሚጭናቸው የአማራ ህዝብ የምንግዜም የጥቃት ምንጮች ናቸው። ለእነዚህ ሁለት እግር አህዮች የአማራ ፋኖ ትግል ምላሽ አለው። ምላሹንም ትግል ሜዳው ላይ እየሰጠ ነው። እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን ስንል በፉከራና በቀረርቶ ብቻ ሳይሆን ክንዳችንንም እየቀመሱ በግብር ተመሳስለን ነው። ዘጠኝ ሞት መጣ ብባል ዘጠኙንም ግባ በለው የምል የሸንቁጥ ልጅ ነኝ። ሞት ሲመጣ በክብር የምንሞት እንጂ ተልፈስፍሰን የሚጨበጥ ክንድ የለንም። እንደ ገብርዬ እምቢ ብለን፤ እንደ ገበየሁ አለን ብለን አደራችንን እንወጣለን ዓላማችንን እናሳካለን። እንደአባ ዳኘው ምኒልክ በጥበብ የምንመራው የኀልውና ትግላችን የመጨረሻውን ሳቅ እኛው እንደምንስቀው ውጤቱን እያየነው ነው። ኢትዮጵያ የምትባል አንዲት ተክል ብልፅግና በሚባል አረም ተከባ አንድ እየወጋ ሲያደማት፣ አንዱ ሊሸጣት ሲያስማማት፣ ሌላው በሃሰት ሲሸነግላት ማየቱ በቅቶን አረሙን ለመንቀል አንድ..ሁለት.. ሦስት ሆነን ጀምረን ሚሊየኖች ሆነናል። ይህ ሁሉ ደግሞ የሞት አዋጅ ለታወጀበት የአማራ ህዝብ ማንነቱ የሞቱ ትኬት ለሆነበት ህዝባችን መንግስት ሆነን እንጠብቀዋለን ብለን ትልቅ አላማ አንግበን በድል ጎዳና እየተጓዝን እንገኛለን። አማራነት መስመራችን አድርገን ትግላችንን ከግብ እናደርሰዋለን። እኛ እንደራጃለን፣ እኛ እንሰባሰባለን ይህን የምናደረገው ህዝባችንን ካጋጠመው የህልውና አደጋ ነፃ አድርገን ሀገራችንን ለማዳን እና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስተካከል ነው። የእሳተ ነበልባሉ ትውልድ አካል ነን የሚጨበጥ ክንድ የለንም✊✊✊ አርበኛ ኢ/ር ብሩክ ስለሺ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች የሲቪል አስተዳደር መዋቅር ዝርጋታ መጀመሩ ተገለፀ:: የምኒልክ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢ እና የፓለቲካ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አርበኛ ሔኖክ አዲሴ ከአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊው ከአርበኛ አበበ ቀዬ ጋር በመመካከር የሲቪል መዋቅር ስራው በቅንጅት እንድሰራ በመወሰን ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ውስጥ የሚኖረውን ህዝብ የፓለቲካ ንቃተ ህሊና ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን የዕዙ ፓለቲካ ክንፍ ሲሰራ የአደረጃጀት ክንፉ ደግሞ የየቀበሌዎችን ሊቀመናብርት፣ የፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም የማህበራዊ ሸንጎ መዋቅር የመዘርጋት ስራ መስራቱ ታውቋል:: በዚህም መሰረት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ 012 ሚናያ ቀበሌ የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ አለልኝ ተሰማ ጭምር በተገኘበት ከህዝብ ጋር ውይይት ተደርጓል::  የውጭ ባዳ እና የሀገር ውስጥ ባንዳ በሚል ርእስ የአሸባሪው ብልጽግና ካድሬዎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመሰብሰብ የሚሰሩትን ፕሮፓጋንዳ ለማክሸፍ ህዝብን የማንቃት ስራ ተሰርቷል:: የህልውና ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን የዳሰሰ ውይይትም ተደርጎ በተለይ አፈንግጠው በዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ፀረ ህዝቦችን አሳዶ የመያዝ ግዳጅ በስኬት ተጠናቆ ቀጠናው ከሌቦች መፅዳቱ ለህዝብ ግልጽ ተደርጓል:: የፋሽስቱ አብይ ሰራዊትም ከይዞታው ተነቅሎ የማድረግ አቅሙ ተልመሽምሾ በቡድን እየከዳ እንደሆነም ነው አርበኛ አለልኝ ተሰማ በመድረኩ ላይ ለህዝብ የገለፀው:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠኑ ማስመረቁን አጠናክረው ቀጥለው ዛሬም ደጀን ክፍለጦር አስመርቋል:: በቅርቡ የተደራጀው የደጋው መብረቅ ኮር ሁሉም አሃዶቹ ምልምል ፋኖዎችን በእ
+1
የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠኑ ማስመረቁን አጠናክረው ቀጥለው ዛሬም ደጀን ክፍለጦር አስመርቋል:: በቅርቡ የተደራጀው የደጋው መብረቅ ኮር ሁሉም አሃዶቹ ምልምል ፋኖዎችን በእግረኛ እና በልዩ ኮማንዶ ደረጃ እያሰለጠነ እያስመረቀ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ደግሞ ደጀን ክፍለጦር ለወራቶች የሰለጠኑ ለልዩ ተልዕኮ የሚውሉ ኮማንዶዎችን አስመርቋል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም ኮሮቹና በዕዙ ልዩ ዘመቻ በበርካታ ቀጠናዎች እያሰለጠነ ነባሩን ፋኖ በሰው ሃይል እያጠናከረ የህልውና ትግሉ በሚፈልገው ልክ ራሱን እየተደራጀ ይገኛል:: ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ስልጠናውን በቀላል ወጭ ነገር ግን የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ የከፍተኛ እውቀትና ስነምግባር ባለቤት እያደረገ ለህልውና ትግሉ እያቀረበ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

~ ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ  ግንባር ለፋኖ ኃይሎች የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ! የተከበራችሁ መላው የአፋር ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ  እንደምታወቀው የአፋር "ኡጉጉሞ" ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም እንዲሁም ልዑላዊነትና ድህንነት ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት እንዲጠበቅና እንዲከበር ለበርካታ አመታት በደምና በአጥንት ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ግንባር መሆኑ ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ወደመደበኛ የትጥቅ ትግል በመሸጋገር ላይ እንዳለን ይታወቃል። የአሁኑን ትግላችን ከዚህ ቀደሙ የተለየ ያደረገው፦ አንደኛ፡- የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለሌላ አሳልፎ ሊሰጥ በመሆኑ፤ ሁለተኛ፦ ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የብልጽግና አገዛዝ የሚቀሰቅሰው ጦርነት፣ በይበልጥ አፋርና አፋርን ለማጋደል የተጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ፤ ሦስተኛ፡- ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት ወንጀል  እየፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ፤ አራተኛ፡- በአፋር መሬት ላይ ለአብይ አህመድና የአገዛዙ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሰለጠኑ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች አፋርን የደም መሬት ሊያደርጉት እየሰሩ በመሆኑ፤ በእነዚህና ሌሎች የትግል መነሻ ምክንያቶች   የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ የአሁኑን የትጥቅ ትግላችን የተለየ ያደርገዋል። በአሁኑ ሰዓት በምናደርገው የተደራጀ ትግል የአብይ አህመድ ወኪል፣  አድርጎ ያስቀመጠውን የአወል አርባን አገዛዝ ከውጭም፣ ከውስጥም ሁነን እያፈረስነው እንገኛለን። በዚህም አመርቂ ውጤቶችን አግኝተንበታል። በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው የአወል አርባን ወታደራዊ አመራሮችና ሲቭል አመራሮች እየተቀበልን እንገኛለን። ከዚህ በፊት በመግለጫችን እንዳስታወቅነው፣ በሶማሌ ክልል እጅ አዙር መሪነትና በጂቡቲ ስፖንሰርነት፣ የተባበሩት የሶማሌ አሸባሪዎች የአፋር ህዝብ ላይ በኢሳ ሽፋን ያወጁት ወረራ ለ7 አመታት በንጹሃን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።  ከወትሮ በተለዬ የአፋር ህዝብ በገዛ ቤቱ እያሸበሩና እየገደሉ ቢሆንም የአፋር ህዝብ በብርቱ ክንድና በሙሉ ልብ እየመከታቸው ከራሱ አልፎ ኢትዮጲያን ከዚያድ ባሬ ህልምና ቅዠት እየታደጉ አብዛኛው አሸባሪዎችን ወደ መሬት እቀበሩ የተቀሩት ደሞ በመመከት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ላይ ነው። ሕዝባችን በራሱ ትግል ክልሉን ከወራሪው ነፃ ያደረገ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ይሄንን የተባበሩት ሶማሌ ተስፋፊያን የከፈቱብን ግልፅ ወረራ የፌድራል መንግስት ወራራውን ከማስቆምና ከመከላከል በተቃራኒ የአብይ ቡድን በጂቡቲ ያለውን የሥልጣን ጥቅምና ቀጠናዊ የቡድን ፍላጎት በማስቀደም በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፀም የተባበሩት ሶማሌ ወረራ በግልፅ እየደገፍ ይገኛል። አፋርን በቴክኒካል ሴራና የእጅ አዙር ተፅዕኖ በማዳከም አሸባሪዎቹን ወደ አፋር ልዑላዊ ግዛት እምብርት ላይ እንዲመለስ ግፊት በማድረግ ላይ ነው። ይህ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ህዝብን ለመውጋትና የሚሰለጥኑ ኃይሎች ለአፋር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአካባቢው የከፋ አደጋ እንደሚያመጣ ህዝባችን ያምናል። በትላንትናው ዕለትም የአፋር ሕዝብ ይሄ ነገር መቆም እንዳለበት ተቃውሟውን በተለያዩ መንገድ ገልጿል፣ ይሄ ጉዳይም እስከ ነጻነት ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ያስታውቃል። የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ከሰሞኑ በአማራ ክልል ወሎ ግንባር በአገዛዙና በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውጊያዎችን በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል። የፋኖ ኃይሎች ከባዶ እጅ በመነሳት ዛሬ ላይ በመካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል። የተሰየመው ዘመቻም ዘመቻ አደም አሊ የሚል መሆኑን፣ ዘመቻው የተሰየመለት ፋኖ፣ በትግል ላይ የተሰዋ ሙስሊም ፋኖ መሆኑንም አረጋግጠናል። ይህ የፋኖ ኃይሎችን የአንድ ኃይማኖት ሰዎች ናቸው፣ የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው የሚታገሉ የሚለውን የብልጽግና አገዛዝ የሐሰት ፍረጃ፣ እንዲሁም በፍረጃው ለተሳሳቱ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ አግንተነዋል። የፋኖ ኃይሎች እያደረጉ ላለው ከባድ ትግል እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን። የአማራ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከትናንት እስከዛሬ በመከራም፣ በደስታም የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል።  አሁን ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ተቀባይነት የሌለውና ለሀገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብም ይሄ የማይገባው መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን። በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከነሱም መግለጫዎች በተደጋጋሚ እንደተረዳነው የመላው ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ነጻነት እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል። እኛም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር በቀጣይ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በጋራ በመታገል የአብይ አህመዱን የብልጽግና አገዛዝ ለአንዴና ከመጨረሻ ጊዜ በመጣል በእኩልነት የጋራ አገር ለመገንባት  በትብብር እንደምንሰራ ስንገልጽ በደስታ ነው። በመጨረሻም አፋርን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ የአማራ ሕዝብን ለማውድም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መላው የአፋር ሕዝብ እንዲቃወምና እንዲያስቆም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ይጠይቃል፣ እንዲቆም እንደምንሰራ መግለጽ እንፈልጋለን። መላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የትግል መነሻዎቻችን ተረድቶ በሀገራችን ላይ የተደቀነው ብሄራዊ አደጋ በጋራ ትግል እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን። ግመሎቻችን ጭምር የሚያውቋት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳትወድቅ፣ ነፃ ሀገር እንድትኖረን ለትግላችን አስፈላጊውች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን ! ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ

‎ ማቻክል ግራ ቅዳምን ከተማ፤ ‎ ‎ ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች ከባድ ም * ት የደረሰበት ጡት #ቆ* ራጩ የአብይ አህመድ ሰራዊት ንፁሐንን #እየ* ገደለ ነው። ‎ ‎
‎ ማቻክል ግራ ቅዳምን ከተማ፤ ‎ ‎ ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች ከባድ ም * ት የደረሰበት ጡት  #ቆ* ራጩ የአብይ አህመድ  ሰራዊት ንፁሐንን #እየ* ገደለ ነው። ‎ ‎ማቻክል  ግራቅዳምን ከተማ ላይ #ከተገ*ደሉት  መካከል  ቤተክርስቲያንን  አገልግሎ ሲወጡ #ቄስ መዝገቡ ስማቸው   ይገኙበታል። ‎እምንታገለው እኒህን #ግፈኞች ነው:: ‎ጥቅምት 27/ 2018 ዓ/ም ‎

#የደጋው_መብረቅ_ኮር_አንሻ_ክፍለጦር💪 የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለጦር ክንዱ አሻግሬ ሻለቃ በዛሬው እለት ከጥላት ጋር በተደረገ አውደ ውጊያ ትልቅ ድልን ሻለቃው አገኝቷል። በአውደ ውጊያው ከተገኙት አሁናዊ ድሎች ከአስር በላይ የጥላት ሰራዊት ሲደመሰሱ፤ከ15 በላይ ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል:: በመቄት ወረዳ  ገረገራ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ላይ ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም በነበረው ጦርነት የፋሽስቱ ሰራዊት ጥምር ሀይሉን ጨምሮ አራት ድሽቃ እና ሞርተር አዋቅሮ በአንድ አውደ ውጊያውን ያካሄደ ቢሆንም በአንድ ሻለቃ ፋኖዎች ግባር ግባሩን ሲባል እግሬ አውጭኝ ብሎ የተደመሰሱ ወታደሮቹን ሳያነሳ ፈርጥጧል። ለተከታታይ ሳምንታቶች በደጋው መብረቅ ኮር የሚደርስበትን በትር አንድያ ህይዎቱን መታደግ የተሳነው የፋሽስቱ ሰራዊት ከፋኖዎቹ በሚደርስበት ጥቃት በዬ አውደ ውጊያው እየተበታተነ ከሚፈረጥጠው ሰራዊት ባሻገር በርካታው የአሞራ ሲሳይ ሆኖ ቀርቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር የሚድያ ክፍል 27/ዐ2/2018 ዓ.ም

መረጃ ባህር ዳር‼️ በባህር ዳር ከተማ ከማለዳው ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ወጣት እየታፈሰ ነው የከተማዋ ወጣቶች ብርቱ ጥንቃቂ እንዲያደርጉ ከስፍራው ለአማራ ድምፅ አድርሰውናል ስራ የሌለውና ፖል ቤት የተገኘው በሙሉ እንዲታፈስ ትዕዛዝ ወርዷል