uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 057
Obunachilar
+6824 soatlar
+3957 kun
+1 39230 kun
Postlar arxiv
## መረጃ ጎንደር ዛሬ ጥር 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ከንፋስ መውጫ ወደ ደብረ ታቦር እጅ የሰጡ የብልጽግና ወዶ ገቦችን ይዞ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን ኃይል ዘበራ የተባለ ቦታላይ
## መረጃ ጎንደር ዛሬ ጥር 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ከንፋስ መውጫ ወደ ደብረ ታቦር እጅ የሰጡ የብልጽግና ወዶ ገቦችን ይዞ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን ኃይል ዘበራ የተባለ ቦታላይ በደፈጣ ተመታ። በተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ ተመስገን አብርሃም አማካኝነት በተጣላ ደፈጣ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችና እጅ የሰጡ አካላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲያስተናግድ ተደርጓል።በዚህ የደፋጣ ልዩ ኦፕሬሽን እጅ የሰጡ እና የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ አካላት 5 ሙት ሲሆን ከ10 በላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ሮቤል በእደማርያም

#Ashara_Inbox #*የባህርዳር ከተማ ገዥ የሆኑት አቶ ጎሹ እንዳላማው በባህርዳር ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለ ግፍ*# 1)እኝህ ግለሰብ ከገጠር መንገድ አዳባባይ እስከ ዘጌ መገንጠያ ባለው መንገድ ዳር ላይ ያሉ ባለ ይዞታዎችን# ያለካሳ ክፍያ  ቤታቸውን አፍርሶ ለመሸጥ በዝግጅት ላይ ናቸው። ዋና አላማው ለመንገድ ነው ይባል እንጅ 200 ሜትር  ራዲዬስ የግለሰቦችን ቤት አፍርሰው  በመሸጥ #ለሚሊሻ የሚከፈል ክፍያ  እና #ለልዩልዩ ወጭወች በመጥፋቱ የበጀት እጥረታቸውን ለመሸፈን እንደሆነ ተገልጿል። ተፈናቃይ ግለሰቦችም ለዕርሰ መስተዳድሩ #አረጋ ከበደ ቅሬታው ለማቅረብ  በተደጋጋሚ ቢሄዱም እንዳላገኟቸው ገልጸዋል። ባለሙያወችም ከንቲባውን ካሳ እና የቤት ኪራይ ሳይከፈል ቤት ማፍረሱ ህዝቡ ማሰቃዬት ነው #ህዝቡ እናንተን እየፈራ ከኛ ጋር እየመጣ  ያለቅሳል እኛ ምን እናርግ በማለት ሀሳብ ቢያቀርቡም ለዚህ ስራ እንቅፋት የሚሆን ባለሙያ ካለ #ከስራ አባርራለሁ። ለብልጽግና ስራ እንዳይታይ የሚፈልግ #የጽንፈኛው ተላላኪ አለ ማለት ነው በማለት ባለሙያዎችን  አስፈራርተዋል ። 2) ከዚህ በፊት በ2017ዓ.ም የቀበሌ 5፣6፣10 እና 12 ባለ ይዞታወችን ካሣ ይከፈላችኋል በማለት ቤታቸውን ከፈረሱ በኋላ   ከ 11 ወር በላይ  ካሣ ሳይከፈላቸው በመቅረቱ አብዛኞቹ አረጋውያን ችግር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ #ከንቲባውን ጨምሮ #3የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ከሚሸጠው መሬት በአዲስ አበባና በውጭ አገር አቤት እንዳላቸው መረጃዎች አሉ። ###በሚዲያው በማዛመት ድምጽ እንሁናቸው###

የጎንደር squad የአማራ ፋኖ አንድነት እንዳይመጣ ለምን ይፈልጋል? የፈኖ አንድነት መጣ ሲባልስ ለምን ያለቅሳሉ? መልሱ በሁለት ምክንያቶች የሚገለፅ ነው። ይኸውም፦ 1• ብልጽግና ከሌለ ከወልቃይት የዘረፍነውን ሃብትና ንብረት መልሱ እንባላለን ብለው በፍራትና 2• ከፌዴራል ጀምረው እስከ ክልል መንግስት መስሪያ ቤት፥ ልማት ድርጅቶችና መሰል አደረጃጀቶችንና ባንኮችን ጨምረው የተቆጣጠሩ በመሆኑ ስልጣኑን እናጣለን በሚል ስጋት ነው። ሌላ ደግሞ ከግልና ከቡድን ጥቅም ያለፈ ምንም አይነት ህዝባዊ ስሜትና አላማ የሌላቸው ስብስቦች በመሆናቸው ነው።አርባ አራት ነጥብ። ለምሳሌ በፌደራል መንግሥት የአማችዝም አደረጃጀት የሚከተለውን ይመስላል። 1• ዝናሽ ታያቸው *ሃላፊነት- የበላይ ጠባቂ *ትውልድ ቦታ-አርማጭሆ 2• ታየ አጽቀስላሴ *ሃላፊነት-ፕሬዝዳንት *ትውልድ ቦታ-ጎንደር(ደባርቅ) 3• አገኘሁ ተሻገር *ሃላፊነት- የፌደሬሽን አፈጉባዔ *ትውልድ ቦታ-ጎንደር(ሻውራ) 4• መላኩ አለበል- *ሃላፊነት- ኢንዱስትሪሚ/ር *ትውልድ ቦታ-ጎንደር(ወረታ) 5• መሃመድ እንድሪስ *ሃላፊነት-ሰላም ሚ/ር *ትውልድ ቦታ-ጎንደር ከተማ 6• ፈንታ ደጀን *ሃላፊነት- ከተማ ልማት ሚ/ር ዴእታ *ትውልድ ቦታ-ጎንደር (ሊቦከምከም) 7• ዶ/ር ጌታቸው ጀንበር *ሃላፊነት- ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ል *ትውልድ ቦታ-ጎንደር (ታችጋይንት) 8• ዲ/ን ዳኔል ክብረት *ሃላፊነት- አማካሬ ሚ/ር *ትውልድ ቦታ-ጎንደር(ላይ ጋይንት) 9• ደሳለኝ ጣሰው *ሃላፊነት-የፌደራል ሥራ አመራር ኢንስቲትውት *ትውልድ ቦታ-ጎንደር(ወረታ) 10• መሰረት ዳምጤ *ሃላፊነት- የፈዴራል ዋና ኦዲተር ጀነራል *ትውልድ ቦታ-ጎንደር ( ጋይንት) 11• ሜላተወርቅ ኃይሉ *ሃላፊነት- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ *ትውልድ ቦታ-ጎንደር ከተማ የፈደራል ቦታን 80% ሸፍነዋል። የእስኳድ Fund provider ታደሰ ምህረቴ (የአማችን) ፎቶ በ3ሚሊዮን ብር የገዛው ባለሀብት) •ሃላፊነት-አደረጃጅቱን በገንዘብ መደገፍና ጎጃምና ጎንደር እያሉ ለሚከፋፍሉት ለእነ አያሌው መንደሬና መሰሎች ቀለብ መስፈር •ትውልድ ቦታ- ጎንደር( ወረታ) written by john criss

ጅፎ ባጠለቀው ከዘራ ጭንቅላቱን በማለት ክላሹን የማረከው የደምበጫው ጀግና!! ======== ደምበጫ የጠላት መቅጫ የወንዶች መውጫ ፣በትናንትናው ዕለት በቀን16/05/2018 ዓ.ም በጭንቅላቱ ሳይሆን
ጅፎ ባጠለቀው ከዘራ ጭንቅላቱን በማለት ክላሹን የማረከው የደምበጫው ጀግና!! ======== ደምበጫ የጠላት መቅጫ የወንዶች መውጫ ፣በትናንትናው ዕለት በቀን16/05/2018 ዓ.ም በጭንቅላቱ ሳይሆን በሆዱ የሚያስበውን የብልፅግናውን አሽከር በጠራራው ፀሃይ በጅንፎ ሽመል ጭንቅላቱን በማለት ክላሹን ማርኮ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ፋኖን ተቀላቅሏል። ይህ ትውልድ ለመኖር ያለው አማራጭ እንደዚህ ወጣት ወንድማችን ወኔን ሰንቆ ትጥቅን ከጠላት እየማረኩ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ አማራን ነፃ ለማውጣት፣ህልውናውን ለማረጋገጥ ከሚታገሉ ወንድሞቻችሁ ጋር መቀላቀል ብቻ ነው። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 17/2018 ዓ.ም

‎የአረመኔው ስርዓት #አፍ*ሯል። ‎ ‎ከመላው ኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ወጣቶችን #እያ*ፈነ በተለያዩ ማሰልጠኞዎች እያስገባ ‎ወደ ጦርነት መማገዱ የሚታወቅ ነው። ‎አሁን ላይ በመላው አማ
+1
‎የአረመኔው ስርዓት #አፍ*ሯል። ‎ ‎ከመላው ኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ወጣቶችን #እያ*ፈነ በተለያዩ ማሰልጠኞዎች እያስገባ ‎ወደ ጦርነት መማገዱ የሚታወቅ ነው። ‎አሁን ላይ በመላው አማራ ወጣቶችን እያፈነ ወደ ጦር ሜዳ ለማስገባት በማቀድ፤ ‎ቡሬ ፍኖተሰላም ጅጋ እና ደምበጫ ወጣቶችን እያፈነ ወደ #ፍኖተሰላም ከተማ እየሰበሰበ መሆኑን አረጋግጠናል። ‎ስለሆነም ደብረ ማርቆስን ጨምሮ በቀጠናው ያላችሁ ወጣቶች ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን። ‎ ‎ከአፈርሁ አይመልሰኝ ያለው የአብይ አህመድ ስርዓት ከዚህ በፊት ያሰለጠናቸውን ጡት ብልት #ቆ*ራጭ ሰራዊት አንድም በመደምሰስ ሁለትም በማስከዳት ባዶ እንዳደረግንበት የአደባባይ ሚስጥር ነው። ‎ ‎ጥር 17/2018 ዓ/ም ‎ ‎

ተብለው የመለሱ አሉ። ገበሬዎችን የሚያሰቃዩ አሉ። ትግሉን የምናሸንፈው በግብስብሶች በአሰስገሰስ አይደለም፤ መገፈፉ ጥሩ ነው ለማለት ነው።" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከአማራ የውጊያ ስነልቦና ጋር በተያያዘ ጭምር ማብራሪያ የሰጡት ጄኔራሉ፤ "የአማራ ትግል በጣም ጥሩ የሆነው ይሄ የተሰባሰበው ብሄርተኛው ነው። የአማራው ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው የሚል ነው።" ያሉ ሲሆን የውትድርና ስልጠና የሰለጠነው በፓሊስ፣ በልዩ ኃይል...የነበረውም ወደ ትግሉ መቀላቀሉ ትልቅ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል። "ኃይሉ በደንብ የተዋሀደ (ከሁሉም ያለ) ነው። ኮማንዶዎች እና ፓለቲከኞችም አሉበት። ለዚህ ነው ባለፈው ብዙ ወረዳዎችን በአንድ ጊዜ መያዝ የተቻለው። በመከላከያ ውስጥ ያሉ ማንነታችን እየተጠቃ እዚህ መኖር የለብንም ያሉት ሁሉ ከጠላት ወደ ፋኖ መጥተዋል። ይህ አይነት ቅንጅት አለ።" የሚል ሀሳብም ሰንዝረዋል። የሽምቅ ትግልን በተመለከተ ጋዜጠኛ በቃሉ በተለይም በሽምቅ ዙሪያ ባጫ ደበሌ ፃፈ ስለተባለው መፅሀፍ ጄኔራል ተፈራን ሲጠይቃቸው:- "ጄኔራል ባጫ እውነት መፅሀፍ ፅፎ ስለሆነ ስለ ኪነት/የባህል ቡድን ፅፎ ከሆነ ጥሩ ነው። የባህል ቡድን ለትግል ሚና የለውም አልልም።" ነው ያሉት። "ጄኔራል ቢሰባሰብም ምርጥ ተዋጊ ከሌለበት ምንም አያመጣም እንጅ ከትግራይ ጭምር ጄኔራሎችን ሰብስበው ሽምቅ ሞክረው ነበር። በሌሊት መንቀሳቀስ ምናምን። ሸማቂ ህዝብን ካልያዘ ዋጋ የለውም። እኛ ህዝባችን ውስጥ ነን።" ብለዋል። "ሀይላችን ከሽምቅ ያለፈ ውጊያ እያደረገ ስለሆነ ፈጠነብን። አልፈው እየሄዱ ነው። ሽምቅም መደበኛም እንድንገባ እየየገደድን ነው።" የሚል አስተያየትም ሰጥተዋል። ስለ ጥቁር ክላሽ ጄኔራሉ እንዲህ ብለዋል:- ። "ተዋጊዎችን ባገኘሁት አጋጣሚ ይሄ የጠላት መሳሪያ የሚያስፈልገው ተኩሶ መሬት ላይ ለማያሳርፈው ለአማራ ፋኖ ነው፤ ንጠቀው አልኩት። ነጥቆት ሲያበቃ ደግሞ እኛ የምንፈልገው አንገታሟን (ስናይፕሯን) ነው አለ። ይሄ ስነልቦና ነው እየተፈጠረ ያለው።" በማለት የፋኖን የማድረግ አቅም መጨመርን የሚያመላክት ገለፃ አድርገዋል። "አብይ ጄኔራሎችን ሰብስቦ በእናንተ አልተማመንም፤ በቴክኖሎጅ ነው አለ። ሁልጊዜ በየወሩ ዘመቻ ሲል ከርሞ ምንም አላመጣም። ድሮን እና እየሱስን ይዤ አሸንፋለሁ።" ማለቱንም ጄኔራሉ ተናግረዋል። ፋኖ "አማራ አቀፍ ኃይል እየሆነ ስለሚሄድ ሰፋ ያለ ዝግጅት ይጠይቀናል።" ሲሉም ተደምጠዋል። ስቦ ማስከዳትን በተመለከተ:- "ተቀብለን ማስተናገድ እንፈልጋለን፤ ልዩ ኃይሉ በአብዛኛው ገብቷል። ስግብግቡ ነው የቀረው። ተቸግረው... በስነልቦና የተናቀ ስራ ሲሰሩ ስለነበረ የተወሰነ ገንዘብ ምናምን ሲያገኝ ደፍጦ የተቀመጠ አለ። ራስ ወዳድ፣ ገንዘብ የሚወድ ጎመን በጤና የሚል አለ።" ሲሉ ገምግመዋል። በትግሉ ሂደት የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላትን ሚናም አድንቀዋል። "ትልቁን ሚና የተጫወተው ልዩ ኃይሉ ነው" የሚል አስተያየትም ሰንዝረዋል። በአማራ ላይ ስለተፈፀመው ግፍም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይም ለዚህ ሁሉ ግፍ ተጠያቂው ማነው ሲባሉ:- "ተጠያቂው ራሱ አማራው ነው። ከሁኔታ ጋር መሄድ አልቻለም ምክንያቱም ሁሉም ድርጅቶች አማራን ለማጥፋት ኢትዮጵያ በአማሮች ፍላጎት ነው የተገነባችው እኛ ሚና የለንም የኛ አይደለችም። አማራ ጨቋኝ ነው። አማራ የሚባል ነገድ ነው ኢትዮጵያን እንደ ሙጫ አጣብቆ የያዛት። አማራ የሚባል ቋንቋን እናጥፋ አሉ። ይህን ያለው ሀይል ወደ ስልጣን መጣ። መጀመሪያ ያጠቃው አማራን ነው። አማራ ከስራ እየተፈናቀለ የተናቀውን ብቻ እንድሰራ ተደረገ፤ ትጥቁን እንድፈታ ተደረገ። የት ሄደ ስንል ጭነው ወስደውታል አሉ። የሚያደራጀው አካል ትግሉን መቀየር ሲገባው ወደ አውሮፓ ወደ አሜሪካ ፈርጥጦ ጎመን በጤና አለ። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብቻ ተገኙ። ተረባርበው ዝም አስባሏቸው። መመከት የሚችል የአማራ ብሄርተኝነት መፍጠር አልተቻለም። አንዳንዱ ከገዣ ጋር ተለጥፎ ሀብት የሚሰበስብ ቅራቅንቦ ሆነ። ስለዚህ ተጠያቂው ራሱ አማራው ነው። እንደ ብሄር ቢደራጅና ቢሰባሰብ ይህ አይሆንም ነበር። ክፍተቱ ከኛ ነው። ፋሲል ደምወዝ ይሄን ይሄን አረሱት፤ እነሱ ምን ያርጉ ከኛ ሰው ሲታጣ አለ።" የሚል እይታ አጋርተዋል። "የማንም የበላይ መሆን አንፈልግም። መኖር የምንፈልገው አብረን በእኩልነት ነው። ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተዳድር የሁሉንም ተሳትፎ የሚያረጋግጥ ስርአት ነው የምንፈልገው።" ሲሉም ማብራሪያ ሰጥተዋል። "አማራ ሆኖ ሳለ አማራ እየተጠቃ ለአማራ የማይቆም ምን ይሰራል? ታድዮስ ታንቱ እኮ በራሳችሁ ኩሩ ብሏል።" ማለታቸውም አይዘነጋም። ፋኖዎች አንድነታቸውን ቢያውጁ ከጎናቸው ነን ስላሉት ጄራሉ ሲናገሩ:- "ትግሉ መሪ ድርጅት ወልዷል፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም የድርሻውን መጫወት አለበት። አማራነታችን የጋራችን ነው፤ አሁን ወደፊት የወጣው ኃይል ብቻ አይደለም። የሁላችንም ነው። አይታችኋል በማንነታችን እንዴት እንደተጠቃን። የሁላችንንም ቤት አንኳኩቷል። አንዱ ይህ ነው። ሁሉም በተቻለው መደገፍ፣ የተበላሸ ነገር ካለ በተደራጀ መጠቆም፣ እንድስተካከል ኃላፊነት መውሰድ ይህ ከደጋፊዎቻችን ይጠበቃል። አሁን ይሄን የፋኖ ኃይል ብዙዎች የሚያዩት ለሌላው ፀር እንደሆነ ነው። እኛ ከመላው ኢትዮጵያዊ በላይ ኖረን አያምርብንም፣ አይደምቅልንም፤ ዘላቂም አይሆንም። የፋኖ ትግል ዘላቂ የሚሆነው ፍትህ ገዥ ሲሆን ነው። የኃይል እና ፓለቲካ ሚዛን ቋሚ አይደለም። ዘላቂ የሚሆነው የፍትህ የበላይነት ሲኖር ነው። የማይቀየረው፤ ከህዝብ ጋር የሚያኖረው ፍትህ ነው። አሁን ያለው የኃይል እና ፓለቲካ ሚዛን በፍትህ ካልተደመደመ በድንጋይ ብሎ ያባርርሀል። ለግላጋ የኦሮሞ ወጣቶች ይማረካሉ። መጀመሪያ ፋኖን ጭራቅ አድርገው ነው የሚያዩት። ወደ ቤተሰቦቻቸው እስከሚሄዱ አያምኑም ነበር ግን ተቀብሎ ሲንከባከባቸው ሲያጫውታቸው፣ መታወቂያ፣ ልብስ፣ ገንዘብ ሰጥቶ ሲልካቸው ይደነቃሉ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ሀገራችን በጋራ የምንገነባበት ሁኔታ እንድፈጠር ድርሻ ይኑረው። የሚያዋጣንን ነገር በጋራ ተሰብስበን እንወስን። ሁሉም ድርሻ አለው። ያሉ ችግሮችን በውይይት እየፈታን ዘላቂ ልማት እና እድገት እንድኖር መስራት አለብን። አሁን ያለው መንግስት ሁሉንም በጉልበት እጨርሰዋለሁ የሚልና ለውይይት ቦታ የሌለው ነው። በኃይልና ገንዘብ ነው የሚተማመነው።" ብለዋል። በጥቅሉ ቃለመጠይቁ ደስ የሚል እና ፍሬ ነገር አዘል ነበር። እንደ ምስካቤ ሸንኮራ እጅጉን እየጣፈጠኝ ነው ያደመጥኩት። በጄኔራሉ ንግግር ውስጥ ደግነት፣ ጀግንነት፣ ፅናት እና ወታደርነት ግልጽ ሆኖ ይታያል። ይህ ሁሉ እሴት ንግግሩ እየጣፈጠን እንድናደምጠው አስችሎናል። በመጨረሻም የላስታ እናቶችን የግጥም ስንኝ አስታውሻችሁ ፅሁፌን ልቋጭ:- "ያ ተፈራ ማሞ አንድ ነው ለእናቱ፣ ማርያም ትከተለው በየሄደበቱ"

ጄኔራሉ ምን አሉ? ✍️በአርበኛ ደርብ ተፈራ የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ሸማቂው ኮማንዶ ጄኔራል ተፈራ ማሞ በትናንትናው እለት ከኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኛው ከወንድማችን Bekal Alamirew ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸው ስለ አንድነት፣ ስለ ፋኖ የማድረግ አቅም፣ ስለ ትግሉ፣ ስለ ሸምቅ ውጊያ፣ ስለ ከሃድዎች፣ ስለ ቀይባህር፣ ስለ ትብብር፣ ስለ አማራ ብሔርተኝነት፣ ስለ ዲያስፓራው፣ ስለ ሚዲያ፣ ስለ ትግል ጠለፋ እና መሰል ጉዳዮች በፍሬነገር እና በሚያምር አገላለጽ ልክ እንደ እስከዛሬው በቂ ምላሽ ሰጥተዋል። የኢንተርኔት ወይም የጊዜ ችግር ኖሮባችሁ ዩቱብ ላይ ገብታችሁ ለማድመጥ ለማትችሉ ወገኖች በማሰብ ቃለመጠይቁን ወደ ፅሁፍ ልቀይረው ችያለሁ። ይህን ሳደርግ የጋዜጠኛውን እና የሚዲያውን መልካም ፍቃድ ባለመጠየቄ ይቅርታ። ሙሉ ቃለ መጠይቁ በዚህ ሊንክ ይገኛል:- https://youtu.be/xNAd7vSHYo4?si=3nCvXbh1qlvJMS8g በነገራችን ላይ ጋዜጠኛውንም አለማድነቅ አይቻልም፤ የትኛው ጥያቄ ከየትኛው መቅደም እንዳለበት ወስኖ ቃለመጠይቁን የመራበት አግባብ ብቻ ሳይሆን በትግሉ ዙሪያ ያለው መረዳት ድንቅ ነው በእውነቱ። አዋቂ ሲጠይቅ አዋቂ ሲመልስለትም ማድመጥ ደስ ይላል። የጄኔራሉን የማስረዳት አቅም ያሳየን የጠያቂው ብቃት አስተማማኝ መሆን ነው። ወደ ጄኔራሉ ስንመለስ "ጠላትህን መናቅ የለብህም:: ሳታጋንን ሳታቃልል ተገቢ ሚዛን ለጠላት መስጠት ያስፈልጋል::" ማለታቸውን ልብ ይሏል። ይህ ንግግራቸው ጎበዝ ሰው አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል፤ ቅማል እንኳን በአቅሙ ሱሪ ያስወልቃል የሚለውን አባባል አስታውሶኛል። አዎን፤ ጠላትን መናቅ ራስን አዘናግቶ ለጥቃት ያጋልጣል። ስለዚህ ጄኔራሉ የተናገሩት ነገር ፋኖ ሳይዘናጋ ወትሮ ዝግጁነት ኖሮት አለብኝ ብሎ በተጠንቀቅ እንድታገል ያደርገዋል። ጄኔራሉ አክለውም "ኢትዮጵያ ውስጥ አጀንዳው ፋኖ ብቻ ነው:: ይህ የፋኖን ጥንካሬ ይናገራል::" ብለዋል። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዳሰሳ ብናደርግ በግልጽ የምንታዘበው እውነታ መሆኑንም ጠቁመዋል። ይህ ምንም ጥርጥር የለውም። "ከዚህ በኋላ የአማሮች ችግር በአማሮች ነው የሚፈታው፤ ከሌሎች ቀና ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር አብረን እንሰራለን:: ውስጣዊ ክፍተቶችን እየዘጋን ከሌሎች ጋር ስርዓት ባለው መልኩ እንጓዛለን። የፋሽስቱ አብይ መንግስት እስከምንቀብረው ድረስ ራሱን እያታለለ ይኖራል። ከማን ጋር መገናኘት እንዳለብን የምንወስነው እኛ ነን፤ እነማን ጋር ታክቲካል እና ስትራቴጅክ አሊያንስ እንደምንፈጥር እኛ ነን የምንወስነው። አሁን ድርጅት አለን ከዚህ በኋላ ነው ብዙ ጥያቄዎች የሚመለሱት። እነሱ (ጠላቶቻችን) ቸኩለው ይናገራሉ፤ ጠንከር ያለ ምት ሲመቱ ህወሓት ወጋን ይላሉ። የወጋው ግን ፋኖ ነው። ጄኔራሎች የሚባሉት ግልብ (በላይ በላይ ያለ ብቃት) ማዕረግ ያገኙ ስለሆኑ እነዚህ ኃይላት አንድ ከሆኑ ያልቅልናል በሚል ፍርሀት ውስጥ ስላሉ ብዙ ያወራሉ።" በማለት ጄኔራል ተፈራ ስለ ትብብር እና አጋርነት የሰጡት ማብራሪያም ቅቡልነት ያለው ነው። በዚህ ላይ ሀሳብ ለመጨመር ብሞክር ማበላሸት ይሆንብኛል። ጄኔራሉ በንግግራቸው "ራሳችን እንበቃለን። እኛ ነን ወሳኞቹ ብለን ነው ወደ ትግል የገባነው።" በማለት ራሰ በቅነትን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። አክለውም "በዋነኛነት ብልጽግናን ለመምታት ራሳችን ነን የምንቆመው፤ የጋራ ጠላትን በጋራ መምታት የጋራ ፍላጎትን ለማሳካት ይረዳል። ከሌሎች ጋር የምናደርገው ውይይት ይኖራል። እኛ ጋር ለመስራት ጥያቄ ያቀረቡ አሉ፤ ለምሳሌ የአፋር ኃይል። ሌሎችን ሳንይዝ ኢትዮጵያን መስራት አንችልም።" ከሚል ማብራሪያ ጋር የትብብርን አስፈላጊነትም ጠቁመዋል። "አላማችን ነው ከማን ጋር መተባበር እንዳለብን፤ ማን ጋር እስከየት መሄድ እንዳለብን እንድንወስን የሚያደርገን።" የሚል ሀሳብም ሰንዝረዋል፤ ጄኔራሉ። "አንድ ቁጥር ጠላታችን ብልጽግና ነው፤ በቀኝ በግራ የምናየው ሌላ ጠላት የለንም።" ማለታቸውንም ልብ ይሏል። ይህ ማለት እርብርብ ማድረግ ያለብን ብልጽግና ጋር ነው፤ ጠላት ማብዛት የለብንም ማለት ነው። ሁላችንም ይህንን መገንዘብ አለብን። ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን የተሸከምነው እኛ መሆናችንንም ጄኔራሉ አስረግጠው ተናግረዋል። ከእንግዲህ የአማራ መሬት መረማመጃም ይሁን የሌሎች ኃይላት መዳለቂያ የጦር አውድማ ሊደረግ እንደማይችል ለማስረዳት:- "እኛ እያለን በእኛ ላይ ተረማምዶ የኤርትራንም ይሁን የትግራይን ህዝብ ሊያጠቃ አይችልም።" ሲሉም ተናግረዋል። "ብልጽግና የውሸታሞች ስብስብ ነው። "ጀኔራሉ ቀይ ባህርን እንይዛለን" ይላል። ምርኮኞች ናቸው። በውጊያ ላይ ሁለት እጁን አንቀርፎ እጅ ሲሰጥ የነበረ ሁሉ ነው። ደንፍተው ደንፍተው አሁን ሟሸሹ። ጀግና ከሆኑ እስኪ በአማራ ላይ ተረማምደው ቀይ ባህርን ይቆጣጠሩ። 20 ሺህ ምርኮኛ የነበረው መንግስት ባህር አመጣልሀለሁ ሲል የመንጋው ግትልትል ያጨበጭባል። እማታደርጉትን አታውሩ።" የሚለው ንግግርም የእሳቸው ነው። "አማራ የማይሰራውን አይናገርም።" ሲሉም ተደምጠዋል። ትግሉ ተጠልፏል ስለሚባለው ሀሜት ደግሞ "የአማራን ትግል ለመጥለፍ ከአማራ በላይ እና ከፋኖ በላይ መሆንን ይጠይቃል።" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የጠለፋ ድስኩር እና ሀሳቡም "ከልፍለፋ አያልፍም፤ ይህን የሚል አካል ማፈሪያ መሆኑን ነው ሀሜቱ የሚያመለክት። ከኢትዮጵያ ተሰዶ ኑሮውን ውጭ ያደረገ ትግል ይጠልፋል ብሎ ይለፈልፋል እንዴ?" ሲሉ ጥያቄ አዘል ምላሽም ሰጥተዋል። ጄኔራሉ በንግግራቸው መሀል ስለ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አንስተው በተለይ ጋሽ ተክሌ የሻው በአንድ ወቅት እባክህ ጄኔራል ከኢትዮጵያ ውጣ እነዚህ ሰዎች ይገድሉሀል በማለት ከሀገር የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይሁንታቸውን ጠይቀዋቸው እንደነበር አስታውሰው:- "አመሰግናለሁ፤ እኔ ሀገሬን ጥዬ አልወጣም። የአማራ ወጣት እያለቀ ዳር ሆኜ ዜና አላዳምጥም።" የሚል ምላሽ እንደሰጡ ገልፀዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጄኔራሉ "ፋኖ ያለው መሪ እንደዚህ ያለው ነው። ታች ያሉ መሪዎችን ስጠይቃቸው እጃቸው ወርቅ ነው። ብዙ ሙያ አላቸው።" ብለዋል። ፋኖ የችጋራሞች ጥርቅም እንዳልሆነ ይልቁንስ ብዙ የህይወት አማራጮች እያሉት ሁሉንም እርግፍ አድርጎ በመተው እኔ ሞቼ ህዝቤ ይዳን ባይ ኃይል መሆኑን አስረጅ ንግግር ነው ጄኔራሉ ያደረጉት። ለምናገባኝ ባይ የዳር ተመልካቾች መልዕክት ያስተላለፉት ጄኔራሉ:- "ዳር ሆነህ እንደዚህ ቢሆን ብትል እድሜ ልክህን እንደጮክ ትኖራለህ።" የሚል ምክር ሰጥተዋል። በተለይ ዲያስፓራው በተለያየ መንገድ ትግሉን እንድያግዝ ጥሪ አቅርበዋል። ዳር ሆነው የሚጮሁትን ሲወቅሱ ሌሎችንም አልረሷቸውም። "ቀና ሆነው ትግሉን የሚያግዙ አማራዊ ስነልቦናቸው ተራራ የሆነ የሉም ማለት አይደለም። ይጠለፋል እያለ የሚለፈልፈው ግን እድሜ ልኩን ይለፍልፍ።" ብለዋል። የሚከዱ ሰዎችን በተመለከተ ደግሞ፤ "በትግል የሚያጋጥምህ ነው። ትግሉ በስሜት ይገባና መጨረሻ ላይ ግን ውጊያውን ሲያየው መቋቋም አልችል የሚችል አለ። በፅናት መዋጋት የማይችለው ሁሉ ትግሉ ተጠለፈ ብሎ ይወጣል። ሰርጎ የገባ ሞላጫ ሌባም አለ። ሰርገው ከመግባታቸው ስለ ቀይ ባህር ይለፈልፋሉ። ከንንግራቸው ትረዳለህ። ውጊያ ላይ ጠንክሮ አይዋጋም፤ ምክንያት ያበዛል። ሌላኛው ደግሞ የንዋይ ጥማት ያላቸው አሉ። ስጋቸውን ቦርቡሮ አጥንታቸውን በስቶ እስከመቅናቸው የሚሰማቸው ንጣታሞች አሉ። በፋኖ ስም የሚዘርፉም አሉ። መልሱ

የአርበኛ ከበደ ሀብቴ የፊስ ቡክ አካውንት ነው የአርበኛችን አካውንት ይወደጃቱ ቶሎ ቶሎ መረጃዎች ያገኙበታል። https://www.facebook.com/share/p/1DVrLdrshU/

"በአማራ እናት አስከሬን ላይ የዘነበው የብልፅግና ጥይት!" ​[ሸዋ ደራ - አባሎ ኢየሱስ] ​በሸዋ ደራ ምድር የሰው ልጅ ክብር ከሞት በኋላም ተረግጧል። በትላንትናው ዕለት በሽብርተኛው ኦነግ ሸኔ የግፍ ጥይት ሕይወታቸው ያለፈው የአማራ እናት ወይዘሮ ትርጎ አቢ፣ ሥርዓተ ቀብራቸው በክብር እንዳይፈጸም የብልፅግና ሰራዊት በለቀስተኞች ላይ ጥይት በማዝነብ ክልከላ አድርጓል። ይህ ድርጊት አገዛዙ ሕያው አማራን ብቻ ሳይሆን የአማራን ሬሳና ሐዘን ጭምር እንደሚፈራ ያሳየበት የታሪክ ጥቁር ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል። ​3ኪሎ ሜትር ለሽብር — 20 ኪሎ ሜትር ለሬሳ! ​የክስተቱ አስገራሚና አሳፋሪ ገጽታ ሰራዊቱ ያሳየው "ቅልጥፍና" ነው። ወይዘሮ ትርጎ አቢ በተገደሉበትና ንጹሃን ታግተው በተወሰዱበት ስፍራ የብልፅግና ሰራዊት በ፫ ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ሆኖ ጥቃቱን ለመከላከልም ሆነ ታጋቾችን ለማስለቀቅ "አልሰማሁም" በሚል ቸልተኝነት መርጧል። ይኸው ሰራዊት ግን በአባሎ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብር ለመፈጸም የተሰበሰቡ እናቶችንና ሕፃናትን ለመበተን ከ፳ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ በመምጣት በለቀስተኞች ላይ ተኩስ ከፍቷል። ​የነባ ርዕዮታዊ ምት፦ "ኢላማው አማራነት ነው!" ​ነባ ይህንን ግፍ አስመልክቶ የሰጠው ፖለቲካዊ ትንታኔ እንዲህ ይነበባል፦ ​የሥራ ክፍፍሉ ሲጋለጥ፦ "አሸባሪው ሲገድል፣ አገዛዙ ደግሞ ሬሳ እንዳይቀበር ሲከላከል መዋቅራዊ አንድነታቸውን መስክረዋል። አንዱ ገዳይ፣ ሌላው ደግሞ የሐዘን ዘበኛ ሆኖ አማራን የመጨረሻውን የሰውነት ክብር ሊነፍገው ቆርጦ ተነስቷል።" ​አማራነት የሞትና የሕይወት መስመር፦ "ይህ ግፍ ለሚያመነቱ ወገኖቻችን ትልቅ ትምህርት ነው። አገዛዙ ጠላቱ አማራው ብቻ እንደሆነ በድጋሚ አረጋግጧል። ሐዘኑን እንኳን በክብር መውጣት የማይችል ሕዝብ፣ ብቸኛ አማራጩ የራሱን 'ቤተ-አማራ' መገንባት ብቻ ነው።" ​ላትጨርሰው አትንካው!፦ "አገዛዙ በአንዲት እናት አስከሬን ላይ ጥይት በመተኮስ ክብራችንን ነክቷል። ከዚህ በኋላ የሚኖር ድርድርም ሆነ 'ሰላም' የለም። የነፍጠኛው አርበኛ ምላሽ የሚሆነው የዚህን ሸንካላ ሥርዓት ግብአተ-መሬት ማፋጠን ብቻ ነው።"

ሰበር ዜና!! 206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 አስደናቂ የቦንብ ጥቃት ፈፅሟል ጥር 17/2018 ዓ.ም =================================== 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 በአንድ fsr መኪና ተጭነው ከ ስላሴ ካምፕ ወደ የጁቤ ሊንቀሳቀሱ የነበሩ የአረመኔዊት ሰራዊት ላይ በተደረገባቸው የቦንብ ጥቃት 1 የጦር አዛዡ ጨምሮ 14 የጠላት ኃይል ሲገደሉ 9 ከባድ እና 6 ቀላል ቁስለኞች በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛሉ። የቀጠናው ልዩ ክስተት የሆነው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደጋጋሚ በሌሊት፣ በቀን እና በምሽት በጠላት ላይ ያነጣጠረ ተሳካ የቦንብ ጥቃት በማድረግ አስደናቂ ኦፕሬሽን የፈፀመ ሲሆን ከሌሊቱ 7:10 የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከስላሴ ካምፕ በመውጣት ወደ የጁቤ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት በfsr ተጭነው የነበሩ 30 የአረመኔው ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሁነዋል። በተመሳሳይ ሰዓት የአብማ ክፍለ ከተማ ሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ በሆነው አለኸኝ አስማረ መኗሪያ ቤት በተደረገ የቦንብ ጥቃት አለኸኝ አስማረ ከባድ ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጧል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

⚡️🗣የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ (፭) ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ) ከየፈረንሳዩ የድረ ገጽ ጋ
+1
⚡️🗣የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ (፭) ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ) ከየፈረንሳዩ የድረ ገጽ ጋዜጣ ሚዲያፓርት (Mediapart) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የሚከተለውን ተናግረዋል:: «የእኛ ተነሳሽነት ሕፃናትን ጨምሮ በግዳጅ ከተመለመሉት ወታደሮች ሠራዊት የላቀ ነው። ፋኖዎች ለነጻነታቸውና ለሕዝብ ነፃነት ነው የሚታገሉት» ሙሉ የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ማግኘት ይቻላል:: ⚡️🗣 The following quote is taken from an interview of Amhara Fano National Movement (AFNM) Belay Zeleke Command Dagmawi Tewodrose (5th) Corps Gondere Begashaw Division Public Relations Head Arbegna Tadlo Dessie (Kastiro) with French digital newspaper Mediapart. “Our enthusiasm is greater than that of the army, made up of soldiers who were forcibly recruited, including children. The Fano, by contrast, fight for their freedom and for the freedom of the people,” Read the full news article below https://www.mediapart.fr/journal/international/261225/ils-ont-tout-brule-au-nord-de-l-ethiopie-le-conflit-entre-le-pouvoir-central-et-les-milices-des-fan

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር፣ ገብርዬ ክፍለ ጦር በጊዜያዊ አመራሮች የተሰጠ የአደረጃጀት መግለጫ የአደረጃጀታችን መነሻ መሰዋትነት፣ ፅናት፣ ቃል ኪዳን፣ ታማኝነት፣ አገር ሰሪነት፣ እንዲሁም ለአማራነታቸው መሰዋዕት ለሆኑ ጀግኖች ያለን እምነት ነው። ከፍያለው ደሴን በሕይወት ሳለ ብቻ ሳይሆን በሞትም የምንገዛው እና የምንመካበት እንደ አባት የምንቆጥረው ልጆቹ አለን። "ከማይመስልህ ጋር አትጠመድ" እንደሚለው፣ ከማይመስሉት ጋር ጎን ለጎን በጥርጣሬ ከመኖር፣ መመንጠር የተሻለ ነው። ስለሆነም የብብት መደገፊያዎችን አራግፈን እንደ ንስር በጥበብ፣ እንደ ዝሆን በኀይል፣ እንደ ነብር በመከራከሪያ ባህሪ የምንነሳ የከፍያለው ደሴ ልጆች ነን። የንዋይ ፍቅር ወይም የከተማ መቀመጫ በመፈለግ ወይም ርካሽ የሆነ የብልፅግና ስልጣን በመከተል ወደ ታጋይነት አልገባንም። የአባቶቻችንና የወንድሞቻችን መቃብር የምንበላ ከዳተኞችም አይደለንም። ክህደት ከፍጥረት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ እንደዚህ ዓይነት ግልጽ እና የተዋቀረ ሰይጣናዊ ክህደት ግን አላየንም፣ አልሰማንም፣ አናውቀውም። ዛሬ በአደባባይ ክህደታቸውንና ውሸታቸውን ያሳዩን፣ የስልትና ፖለቲካቸውን የጀመሩት፣ በታላቁ አርበኛ፣ በአባታችን በሜጄር ጄኔራል ከፍያለው ደሴ መስዋዕትነት ያዘኑ መስለው፣ ነገር ግን በውስጣቸው “እንደ ሣር ውስጥ እባብ እና የጭቃ ውስጥ እሾህ” እያሉ በለስላሳ ባህሪ ያታለሉ እና ኢ-ጎሳዊ ድርጊቶቻቸውን የጀመሩት ናቸው። ከዳተኞቹና ከስራዓታቸው ጋር የጀመሩትን የስልት ሴራ እንደተጀመረ መረጃዎች ቢያሳዩንም፣ "አሉባልታ" ነው ብለን በትዕግሥት ይዘን ቆየን። ከሰይጣናዊ ውይይታቸው ስንራራ እና ስንለይ፣ የቡድን መሳሪያ ሳይቀር በወገን ጥይት ሲወርድብን፣ በውስጥ ታጋዮች ሲፈተኑ፣ ዘጠኝ የጨለማ ወራትን አሳልፈናል። ዛሬን በእሳት የተፈተን ነገን በተስፋ እስከ ቀራኒዮ የምንፋለም እንጂ፣ በተቀላቀለ ፖለቲካ እጃችንን አንከርፍም፣ ለማንኛውም የጨፍጫፊ አስተዳደር ስርዓት እጅ የምንሰጥ የሚሊሻ ልጆች አይደለንም። ስለዚህ፣ የገብርዬ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ግለሰብ አዲሱ ደባልቄ እና የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ የነበረው አዳነ ተስፋ ወደ ጠላት ተቀላቅለው ሲገቡ፣ በተቋማችን ላይ በትንሹም ቢሆን የትጥቅ እና የስንቅ ጉድለት ቢያደርሱም፣ ትናንትም ሕዝባችን ነበር ነገም ሕዝባችን ነው፣ የትግላችን መሠረት በመሆኑ፣ አንገታችንን ቀና አድርገን የምንሄድ የዳግማዊ ገብርዬ ልጆች ነን። በመሆኑም "በህይወት ኖሮ ከመቆሸሽ ይልቅ ሞቶ መወደስን" የምንመርጥ የስመኘው መብራቱ (ጋሼ) የቃል ኪዳን ዕዳ ያለብን አቡነ ጴጥሮስ ነን። ፈንገሶችን አራግፈን በንጹህ ህሊና የምናስብ፣ በጤናማ ሳምባ የምንተነፍስ ዮቶራይያን ነን። በዚህ መሠረት አንዳንድ ነገሮችን ለድርጅታችን (አፋብን)፣ ለተከበረው ሰራዊታችን፣ ለመላው ሕዝባችን፣ እንዲሁም ለመላው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙት የትግላችን ደጋፊዎች ማሳሰብ የምንፈልገው እንደሚከተለው ነው። 1. ለመላው የአማራ ሕዝብ፣ በተለይም በቀጠናችን ለሚገኘው ለራስ-ጋይንት ሕዝብ፡ የብአዴን ማደጎ ቤት ልጆች በሰሩት የጠራራ ፀሐይ ክህደት ብንበሳጭም፣ የእውነት ልጆቻችሁ ከጎናችሁ መሆናችንን ይወቁ። 2. ለድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፡ ከደረሰብን ድንገተኛ የውስጥ ጥቃት ተነስቶ የሚፈለግ የሃሳብ፣ የገንዘብ እና የአደረጃጀት ድጋፍ እንዲደረግልን እንጠይቃለን። 3. ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ደጋፊዎች፡ ጥቅምተኞች ትግላችንን በአደባባይ ሲሸጡት ሞራላችሁ ቢሰበርም፣ ታማኞች ወንድሞችና እህቶቻችሁ፣ እንዲሁም ልጆቻችሁ ክንዳችንን ሳንንተርስ እና ትከሻችን ሳንዝል፣ የአማራን ሕዝብ ለማንኛውም ለጨፍጫፊ ስርዓት አሳልፈን አንሰጥም። 4. ለመላው ሰራዊታችን፡ እንደምታውቁት በትግላችን ውስጥ የጥቅም ባልደረቦች እንጂ ቃል ኪዳን ታጋይ አልነበረም። የፍርሃትም ሆነ የመረበሽ ስሜት ሳይነካችሁ፣ ባለፈው ጊዜ ውስጣዊ ከሓዲዎችንና የጠላትን የጋራ ጥቃት በማፈራረስ መኪናና ዲሽካ የተቀበላችሁ፣ ዘረ-ከፍያለዋውያን መሆናችሁን በተግባር አሳይታላችሁ። ወደፊትም በጀግንነትና በታማኝነት እንድትቀጥሉ እናሳስባለን። 5. **በዓመታዊ የፋኖ ድጋፍ ሰበብ ሕብረተሰባችን መቀነት የፈቱ፣ "ሠራዊታችን የበተኑ አመራር ነን" ተብለው የሚጠሩ፣ በአማራ ትግል ስም የሚሸጡ አካላት መሆናቸውን የአማራ ሕዝብ በጥቁር የታሪክ መዝገብ እንዲጽፍላቸው የአማራ የህልውና ትግል ሕዝብና ደጋፊዎች ኃላፊነቱን እንሰጣለን። በመሆኑም እነዚህንና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ለማስተካከል እና ወቅታዊ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ፣ የሰራዊታችንና የሕዝባችን ሞራል ለማሳደግ፣ እንደ ገብርዬ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ አደረጃጀት መሥራታችንን እናመለክታለን። ቀጣዩ ድርጅት (አፋብን) በሚያወጣው መመሪያ መሰረት አደረጃጀቱ እንደገና እንደሚዋቀር እንገልፃለን። በዚህም መሠረት የጊዜያዊ አደረጃጀቱን መሪዎች እንደሚከተለው ሰይመናል። 1. አርበኛ ኢ/ር ደመወዝ ግዳፍ — ጊዜያዊ ሰብሳቢ 2. አርበኛ ክንድሰው ከፍያለው — ምክትል ሰብሳቢ 3. አርበኛ ያለው ጥላሁን — ወታደራዊ አዛዥ 4. አርበኛ አንዷለም አዳሙ — ዘመቻ መምሪያ 5. አርበኛ አማረ ጌታው — ምክትል ዘመቻ 6. አርበኛ ሲሳይ — ልዩ ዘመቻ (ልዩ ኦፕሬሽን) 7. አርበኛ ብርሃን ጌታው — ፖለቲካ ዘርፍ 8. አርበኛ ዘላለም በላይነው — ፋይናንስ ክፍል 9. አርበኛ ልየው ተካልኝ — ሕዝብ ግንኙነት ከዚህም በተጨማሪ በአራት ብርጌድ አሰራር እና በሶስት ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ እና የተጠረነፈ ሰራዊት ይዘን ወደ ሥራ የገባን መሆኑን እንገልፃለን። ማሳሰቢያ፡ ለረጅም ጊዜ በጉጉት የተጠበቀውን የአማራ ፋኖ አንድነት በሙሉ ድምጽ የተቀበልነው እና በድርጅታችን አፋብን፣ እንዲሁም በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮቻችን በሚሰጡት አቅጣጫ መምራታችንን እናመለክታለን። አስፈላጊው የገንዘብ እና የሃሳብ ድጋፍ እንዲደረግልን በታጋዮቻችን እና በተገፋው ሕዝባችን ስም እንጠይቃለን። © የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር፣ ገብርዬ ክፍለ ጦር አርበኛ ኢንጂነር ደመወዝ ግዳፍ፣ ጊዜያዊ ሰብሳቢ 16/05/2018 ዓ.ም.

በሽዋ የመሃል ሜዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የተደረገ የህዝብ ስብሰባ ላይ ያሳለፉት ጥያቄዎች እና ተግባራዊ ውይይት በመሃል ሜዳ ከተማ አስተዳደር በሚገኘው 01 ቀበሌ፣ የህዝብ ተወካዮች (ብልጽግና) ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ አካባቢው ነዋሪዎች የተለያዩ ጉዳዮችን በመነሳት ጥያቄ አቅርበዋል። ስብሰባው በ2018 ዓ.ም. የካቲት 15 ቀን (ግሪጎርያን ካሌንዳር ጋር በማነፃፀር ማረጋገጥ ይገባል) በአዲስ የተገነባ አዳራሽ ተካሂዷል። የስብሰባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ ከአካባቢው ለተወሰነ ጊዜ የተካሄደውን የፋኖ ጉብኝት እና እርምጃ መጨረሻ ላይ መድረሱን መግለጽ ነበር። ስብሰባው ላይ የቀበሌ፣ የከተማ አስተዳደር እና የዞን አስተዳደር አመራሮች ተገኝተው፣ ከፋኖ አመራሮች እና አባላት ጋር የተደረገው የጋራ ስራ እንደተጠናቀቀ አስታውቀዋል። ይህን ሲያቀርቡ አካባቢው ነዋሪዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርበዋል። የነዋሪዎቹ ዋና ዋና ጥያቄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ 1. መንግሥት የፋኖ ደጋፊ በማለት በፖለቲካ እና የሃሳብ ምክንያት ያሰረባቸውን ዜጎች (‹‹የህሊና እስረኞች››) እንዲፈታ መደረግ አለበት። 2. መንግሥት በአማራ ክልል በተደረጉ እርምጃዎች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት በመቀበል ይቅርታ ማወጅ አለበት። 3. መንግሥት ለኑሮ ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትሉትን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አልቻለም። ህዝቡ በኑሮ ውድነት እየተጨቆነ ነው። 4. ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ አማራዎች ችግር እየገጠማቸው ነው። በአንዳንድ ቦታዎች በ‹‹ሸኔ›› ስም የሚፈጸም የጭፍጨፋ ተግባር እንደተካሄደ በመጥቀስ፣ ለዚህ መንግሥት ኃላፊነት እንደሚሸከም አስቀምጠዋል። 5. ነዋሪዎቹ ከሰዓታት በፊት ለመድረኩ እንደተቀመጡ፣ በግፍ እንደተደበደቡ በመግለጽ ይህን ማቆም እንዳለበት ጠይቀዋል። 6. ፋኖ ከተሰማራ በኋላ ወደ ጫካ ለመግባት የተወሰኑ ጥያቄዎችን (ለምሳሌ፣ የፖለቲካ መፍትሄ ስለማግኘቱ) እንዳቀረበ በመጥቀስ፣ እነዚህ ጥያቄዎች የአማራ ህዝብ የጋራ ጥያቄዎች መሆናቸውን እና መልስ ማግኘት እንዳለባቸው አስፍረዋል። የአመራሮቹ ምላሽ በተሰጡት መረጃ መሰረት፣ በስብሰባው ላይ የተነሱት ጥያቄዎች ግልፅ እና ተግባራዊ ምላሽ አላገኙም። የህዝቡ ቁጣ እና መቃወም በሚገርም ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት፣ አመራሮቹ ተገቢውን ምላሽ ሳይሰጡ ስብሰባውን ትተው እንደሄዱ ተገልጿል። ከስብሰባው በኋላ፣ አንድ አመራር "ከባድ ነው" በማለት ምላሽ ሰጥቷል። ሌላ ተሳታፊ ደግሞ "ሌላ መድረክ መከላከያ ይሰብስብ" የሚል አስተያየት መስጠቱን መረጃው ያመለክታል። ይህ ሁኔታ በአካባቢው አስተዳደር እና በህዝቡ መካከል ያለውን የግንኙነት ከባድ ነው ሲሉ መረጃዎቹ ይገልፃሉ። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjF

ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ በሰሜን ወሎ በጉባላፍቶ ወርዳ በወልዳያ ዙሪያ መሽጎ የሚገኘው የምርኮኛው የአስር አለቃ የብርሀኑ ጅሉ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላ
+1
ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ በሰሜን ወሎ በጉባላፍቶ ወርዳ በወልዳያ ዙሪያ መሽጎ የሚገኘው የምርኮኛው የአስር አለቃ የብርሀኑ ጅሉ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። የ58ኛ ክ/ጦ 2ኛ ሽ አለቃ 2ኛ ሻንበል ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሁለት የሰራዊቱ አባሎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል ። መዳረሻዉ ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ህልውናችን በተባበር ክንዳችን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሚሊኒክ ዕዝ ጥር  16 / 2018 ዓ ም

የመሀልሜዳ ህዝብ በመድረክ ብልፅግናን ተቃወመዋል ። ተቃውሞው ምንድነው ? በመሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ብልፅግና በ15/05/2018 ዓ.ም አጠቃላይ ህዝቡን ሰብስቦ ነበረ አዲስ ገነበሁት ባለው አዳራሽ ላይ አጀደው ምን ነበር ? አጀንዳ፦1. ክልላችንን ከፋኖ አፅድተነዋል የሚል ነበር ከመድረክ የቀበሌ ፣ የከተማ አስተዳደር እና የዞን አመራሮች ተገኝተው የፋኖ አመራሮች እና ሰራዊት እጅ እየሰጡ ነው ። ብለው ሲደሰኩሩ የ01 ቀበሌ ህዝብ ነዋሪዎች ያነሱት ጥያቄዎች ። 1. መግስት የፋኖ ደጋፊ ብሎ ያሰራቸውን የህሊና እስረኞች ይፈቱ? 2. መግስት ነጥሎ አማራን በድሏል ይቅርታ ይጠይቅ ጥፋቱን ይመን ? 3. ህዝቡን በኑሮ ውድነት እየተጠበሰ ነው የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት አልቻለም ? 4.አማራ ከቅዬው ተፈናቅሎ እየኖረ ነው በዳቦ ስም ሸኔ እያለ የዘር ጭፍጨፋ ተደርጎብናል ለዚህ ተጠያቂው መግስት ነው ። 5. እኛን ሰብስባችሁ አትስደቡን ሚኒሻ ከ12.00 ጀምሮ በግፍ እየደበደበን ነው አስቁሙልን ? 6. ፋኖ ይዞት ወደ ጫካ የወጠው ጥያቄ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ነው ጥያቄዎቹ አልተመለሱም መመለስ አለባቸው ። እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን ጠይቀዋል ለጥያቄው ምን ተመለሰ ህዝቡ ሲጠይቅ ጭብጫቦ በዝቶ ስለነበረ አመርቂ መልስ ሳይሰጥ ህዝቡ አመራሮቹ እደተቀመጡ ትተዋቸው ነው የሂዱት የመረጃ ምንጫችን ከቦተው ነው ። ትተዋቸው ሲሄዱ ምን አሉ አንድ አመራር ከባድ ነው ብዓሉም ላይ ወጣቱ ጨፈረብን ሌላ መድረክ መከላከያ ይሰብስብ አለ ምን ይመስላችኋል ገምቱ ? ለመረጃ ጥራት ደውላችሁ አረጋግጡ ? ህዝብ ከጣለ መድረክም መምራት አይቻልም !!! የፋኖ ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ነው !!!