uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
2 944
Obunachilar
-1024 soatlar
+77 kun
+37930 kun
Postlar arxiv
በየዕድውሃ ከተማ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት እርስ በእርሱ ተኩስ ሙት እና ቁስለኛ ሆኖል!! ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በሸበል በረንታ የዕድውሃ ከተማ ሰፈሮ የሚገኘው የአገዛዙ ወ
በየዕድውሃ ከተማ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት እርስ በእርሱ ተኩስ ሙት እና ቁስለኛ ሆኖል!! ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በሸበል በረንታ የዕድውሃ ከተማ ሰፈሮ የሚገኘው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ መከላከያ እና ሚሊሻ ሰራዊት እርስ በርሱ ሲታኮስ አድሯል። የአገዛዙ ሰራዊት እርስ በእርሱ ለመታኮስ ምክንያቱ የሆነው በቅርብ ቀን ወደ 64ኛ ክ/ጦር የተቀላቀለ ሚሊሻ አሌ አለሙ የተባለ  አርሶ አደር የቀንድ ከብት ለዕርገት ክብረ በአል መዋያ ለመውሰድ ባለመግባታቸው የተነሳ መህኑን ተረጋግጦል። በየዕዱውሃ ከተማ የእርስ በእርስ ተኩስ ልውውጥ በደረሰው ጉዳት: ✍️ ቢላው አየለ የተባለ ሚሊሻ ወዲያውኑ ሲወገድ ✍️ ሁለት መከላከያ እና አንድ ሚኒሻ ከባድና ቀላል ቁስለኛ በመሆን የዕዱወሃ የመጀመርያ ደርጃ ሆስፒታል መግባታቸው ተረጋግጦል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!                ግንቦት 13/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

ሁለገቡ ምሁር ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ እባብዬ ጀነራል ከፊያለው ደሴ (206ኛ) ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦርን ተቀላቀለ። ​የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በአስተማሪነትና በአለም አ
+1
ሁለገቡ ምሁር ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ እባብዬ ጀነራል ከፊያለው ደሴ (206ኛ) ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦርን ተቀላቀለ። ​የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በአስተማሪነትና በአለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሁለገቡ ምሁር ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ እባብዬ፣ የአገዛዙን ፀረ-ሕዝብ አቋም በመቃወም ፋኖን መቀላቀላቸው ታወቀ። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በላቀ ውጤት ተመርቀው እስከ ረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የደረሱት ይህ ምሁር፣ ቀደም ሲል በነበረው የህወሓት ጦርነት በጋሸና፣ በአንቺም፣ በዳውንትና በጋግቢያ ግንባሮች የሻምበልነት ማዕረግ እስከማግኘት የሚያደርስ አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ የጦር ሜዳ ጀግና ናቸው። ​ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የነበራቸው ቆይታ፣ ተቋሙ ለሕዝብ ወገንተኝነት የሌለውና ለሥልጣን ማራዘሚያነት ብቻ የተጠለፈ መሆኑን እንዲገነዘቡ እንዳደረጋቸው የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ፣ "ከእንግዲህ ለዚህ ሥርዓት አልገብርም!" በሚል ቁርጠኝነት ዛሬ የጀግኖቹን የገብርዬ ልጆች ተቀላቅለዋል። የ206ኛ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት እንደገለጸው፣ ምሁሩና አርበኛው ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ በአሁኑ ወቅት ክፍለ ጦሩን ተቀላቅለው ወደ ግንባር በመድረስ የነጻነት ተጋድሎውን ተቀላቅለዋል።

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ #share አድርጉ @@የብልፅግና የጭካኔ ጥግ በቁይ ከተማ@@ አረመኔው የብልፅግና ሰራዊት በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሸጎ የሚገኘው አረመኔው የብልፅግና ስርዓት ግንቦት10/2018 ዓ.ም ቁይ አስንዳቦ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ውባለ አወቀን የ12 ዓመት ወንድ ልጅ በመድፈር ሞተ ብለው ጥለውት መንገደኛ እ አንስቶ ደ/ማርቆስ ሆስፒታል ገብቶ በሞትና በህይወት መካከል ይገኛል።ሌላኛው በዚሁ ጎጥ አስንዳቦ ማርያም የአቶ እንቻለው ባይሌ የ14 አመት ህፃን ወንድ ልጅ ከብት በመጠበቅ ላይ እያለ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ተፈራርቀው ደፍረውት በፅኑ የህመም ስቃይ ጣዕረ ሞት ላይ ይገኛል። ይህ ሁሉ ሲሆን የወረዳው የብልፅግና አመራሮች እንዲህ እንምታዩዋቸው በባህል ቀሚስ አሸብርቀው እንደ ሰዶምና ገሞህ ህዝቦች እየተዳሩ ይገኛሉ እናንተ የእፍኝት ልጆች ዛሬ እንዲህ በግፍ የተደፈሩት ልጆች የእናንተ የአብራካችሁ ክፋይ ቢሆኑ ብላችሁ እስኪ ለአንድ ሰከንድ እንኳ አስቡት?? ውድና የተከበርከው የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ ህዝብ ሆይ የአብራክህ ክፋይ ፋኖ በቅርቡ እኒህን አረመኒዎች በህይወት እንደሚፋረዳቸው እያሳሰብና እሰከዚያው ከነዚህ ሰይጣኖች ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን!!! ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ!!!! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል

ዲላን ፔጅን (Dylan Page) በአግባቡ እንጠቀምበት! አገዛዙ አዶናይን በመጠቀም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ታዋቂውን የቲክቶክ ዜና አቅራቢ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷል። አገዛዙ በጦርነትና እየታመሰች ያለችውን ሀገር በብልጭልጭ መብራቶቹ በመሸፈን  "ሰላም ነች" የሚል ትርክት ለመስራት ነው ደፋ ቀና እያለ የሚገኙው። አማራው ደግሞ ይህንን እድል በመጠቀም እየተካሔደበት ያለውን መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት፣ የድሮን ጥቃት፣ የሴቶች መደፈር ማሳወቅ አለበት። አዶናይ ከዲላን ፔጅ ጋር ለመገናኘት የቻለው በዲላን ቪዲዮዎች ስር ተከታዮቹን በሰፊው አስተባብሮ "ኮሜንት" በማስደረግ እንደነበር ይታወቃል። ስለዚህ እኛም ይኸው ስልት በመጠቀም አጀንዳችንን ለመሸጥ እንጠቀምበት። ዲላን በሚለቃቸው ቪዲዮዎች ስር ሁሉ በነቂስ በመግባት፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቹም ጭምር እንዲጠይቁ እና እሱ ራሱ ጉዳዩን እንዲመረምር ግፊት ማድረግ ይገባናል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን መጠነ-ሰፊ የዘር ማጥፋት (Genocide) እና የድሮን ጥቃት ለዓለም ለማሳወቅ ይህ ትልቅ መድረክ ነው። Millions of Amharas are facing drone strikes and ethnically motivated genocide right now. Please investigate and report! 🇪🇹❌ #AmharaGenocide⁠ እንደዚህ አይነት ኮመንቶችን በፌስቡክም በቲክቶክም በሚለቃቸው ቪዲዎች ስር ኮመንት እናድርግ። 📌 አሁኑኑ ወደ ተግባር! ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉ

አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለጦርና ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጅተዋል።    ቀን 13/09/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር ከ3ኛ ሻለቃና ከ4ኛ ሻለቃ የተውጣጡ ሻበሎች በጠላት ላይ የህይውትና ቁሳዊ ጉዳት አድርሰውበታል። ሰሞኑን በአንኮበር ወረዳ የአብይ ዙፋን አስጠባቂውንና የወረዳው ባንዳዎችን እስከወዳኛው መሸኘታቸው ይታወቃል። ጀግናው ሰራዊታችን በጠላት ላይ ዛሬም የበላይነቱን  በማሳየት ሲረፈርፈው ውሏል። መነሸውን ከደብረብረሀን በማድረግ አንኮበር ወረዳ አልዩ አምባ ከተማ ካለው አድማ በታኝና የወረዳው ሚሊሾች በጋራ ጥምር አድርጎ ወደ ጎርጎ በሚጓዝበት ሰአት የ3ኛ ሻለቃ ሰራዊት ከአረዳ በቦሩ ውድማ እስከ ኩሬ አምባ በመዝጋት ቦሩ ውድማ ላይና ኩሬ አምባ ላይ ሲደርስ ከለሊቱ 10፡30 ላይ በጨበጣ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። አይበገሬው ጀግናው ሰራዊታችን ቦታዎችን በማሻሻል ድጋሚ ማርፈጃ ላይ ጎርጎ ከተማ ጀምሮ እስከዲር ጉባ መልሶ ማጥቃት በማድረግ በጠላትን ሲደቁሱት ውለዋል። በሌላ በኩል በዚሁ ወረዳ በጎርጎ ዙሪያ፣ በበርበሬ ውሀና በእንዶዴ በተባለ ቦታ አስፍቶ ልዩ ቦታዎችን በመያዝ ሻለቃ 4 በጠላት ላይ ታላቅ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመውበታል። በአጠቃላይ በዛሬው እለት ከአይን እማኞች በተረጋገጠ መረጃ የተደመሰሰ የጠላት ሃይል 👉የሞተ ከ18 በላይ ሲሆን 👉 አንዱ የመከላከያ ሻበል መሪ 👉 አንድ የአድማ በታኝ ሻበል መሪ 👉 የቆሰለ 22 የወረዳው ቀንደኛ ሚሊሻ አባተ ንጋቴ የዋሻ ቀበሌ የነጋሪት ባህር ተወላጅ ነው በክፍተኛ የቆሰለ ሆኖ ሀኪም ቤት የሚማቅቅ ሲሆን በአጠቃላይ እቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር በጠላት ላይ የበላይነቷን  አረጋግጣለች ። በሌላ ዜና ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር በይፋት አውራጃ ሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያ ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል። አይበገሬዎቹ የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር አናብስቶች በሸዋሮቢት ከተማ 06 ቀበሌ የአገዛዙን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ከጧቱ 4:00 ስአት ጀምሮ ሲያራግፉት ውለዋል። የብልጽግና ስርአት  ጨፍጨፊና ዘራፊ፥የሰላም ፀርና አማራ ጠል አረመኔ ቡድን ሲሆን እራሱን ለህዝብ እደቆመ ለማስመሰልና ለህዝቡ የመኖሪያ ቤት ችግር ፈቺ መስሎ በማስተዳደር ስም የሚገድለውን ህዝብና ሰራዊት  በመሸወድ ንፅሃኑን በግዳጅ ሰልፍ በማስወጣት ሆድ አደሩን ካቢኔ በግፍ የሚገለውን ገበሬ መሬት እዲሸነሸን በብድር ያስታጠቀውን የስርዓቱ ገረዶች እዲዋጉለት ቢያሰልፋቸውም በአይበጌሬዎቹ ሴራውን አክሽፈውበታል የአብይ ሰው መሳይ ውሾች አማራን ለመጨፍጨፍ በጎዜ ተራራ፥ እንቀሬ ጉባ፥ፍየሎች ማጎሪያ፥ ገበሮች ተራራና በአቦ ፀበል ያለ የለለ ሃይሉን አሰልፎ ቢወጣም ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር አንዲት ግራር ሻለቃና አስማረ ዳኘ ሻለቃ ከአባት አርበኞች ጋር በመናበብ የእሳት እረመጥ ሆነውበታል። የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የመከላከያ አመራሮች ከአጣየና ከጀውሃ ተጨማሪ ሃይል ቢያመጣም የመጣው የጠላት ሃይል ዶጋ አመድ አድርገውታል። አጠቃላይ በአውደ ውጊያው ጠላት ከፍተኛ የሰው ሃይልና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ክብርና  ለትግሉ ለሰማዕታት አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት

በቴዎድሮስ ዕዝ 88ኛ ክ/ጦር የአንድ ሬጅመንት አርበኞች በዚገም ወረዳ ጁመራ ቀበሌ ላይ የነበረውን የጠላት ኃይል በመደምሰስ አከባቢውን ተቆጣጠሩ! በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር
+3
በቴዎድሮስ ዕዝ 88ኛ ክ/ጦር የአንድ ሬጅመንት አርበኞች በዚገም ወረዳ ጁመራ ቀበሌ ላይ የነበረውን የጠላት ኃይል በመደምሰስ አከባቢውን ተቆጣጠሩ! በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር ዚገም ወረዳ ጁመራ ቀበሌ የነበረ የብልፅግና አገዛዝ ወታደሮችን በመደምሰስ ድል መቀዳጀታቸውቴ ከ109ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል። ዛሬ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም የ88ኛ ክ/ጦር ስር ከአንድ ሬጅመንት የተወጣጡ አርበኞች በወሰዱት የተጠና ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮችን ደምስሰው ሁለት የሚኒሻ አባላትን በመማረክ አከባቢውን ተቆጣጥረዋል። በኦፕሬሽኑ ከተደመሰሱትና ከተማረኩት በተጨማሪ፡ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን ስድስት ጠመንጃዎች እና ከ1ሺ 500 በላይ የተለያዬ አይነት ተተኳሾች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በጁመራ ቀበሌ የነበረውን የብልፅግና መዋቅርን ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ የፋኖ ጊዜያዊ አስተዳድር መዋቅር መዘርጋቱን አፋብን ወሎ ቤ109ኛ ኮር  ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ የቻለው።

#የፎገራው ጥላሁን ደጀኔ የተባለ ብአዴን ብል[]ፅግና ከምርጫው በፊት ከስንዴ ነዶ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል። ከግንቦት 24 በፊት በግንቦት ወር ወደ መቃብር ሊወስዱት እየታሰበ ይገኛል። በጥላሁን ደጀ
#የፎገራው ጥላሁን ደጀኔ የተባለ ብአዴን ብል[]ፅግና ከምርጫው በፊት ከስንዴ ነዶ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል። ከግንቦት 24 በፊት በግንቦት ወር ወደ መቃብር ሊወስዱት እየታሰበ ይገኛል። በጥላሁን ደጀኔ ብአዴን በድንጋጤ ላይ ይገኛል ከዚህ ካልተማረ በየተራ ያል[]ቃል።

የዛሬ አራት ዓመት ግንቦት 13/በ2014 ዓ.ም የመቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን ልጅ ነህ በሚል አገዛዙ የ3 ዓመት የሆነው ህፃን ልጄን አሸናፊ አበበ ሰውመሆንን ከቤቱ ወስዶ የጁቤ ፖሊስ ጣቢያ አሰሩት። ምክነያታቸው ደግሞ አባትህ የፋኖ መሪ ስለሆነ መምጣት እና እጅ መስጠት አለበት በሚል ነበር። ስርዓቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት አስሮ ካንገላተው በሗላ በህዝቡ የተጠናከረ አለም አቀፋዊና አገራዊ የሚዲያ ዘመቻ  ግንቦት 18/09/2014 ዓ/ም ህፃን አሸናፊን ለቀቀው። ከታች ካለው ፎቶ ጋር በወቅቱ የተከበሩ አቶ ክርስቲን ታደለን ጨምሮ ሌሎች እህት ወንድሞቼ ለህፃን አሸናፊ አበበ ከፍተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አድርገውለት ነበር።   በዚህ ትግል ያልተከፈለ ዋጋ የለም ! እልፎች ለዚህ ትግል መስዕዋት ሆነው፣ለእስር ተዳርገዋል፣ተፈናቅለዋል ተሰደዋል። ስለዚህ በፋኖ ትግል ቀልድ የለም!! ትግሉን የመጠበቅ የመጀመሪያ ስራችን ነው!!! አዲስ ትውልድ !! አዲስ አስተሳሰብ!! አዲስ ተስፋ!!    13/04/2018 ዓ.ም መቶ አለቃ አበበ ሠውመሆን

የዛሬ አራት ዓመት ግንቦት 13/በ2014 ዓ.ም የመቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን ልጅ ነህ በሚል አገዛዙ የ3 ዓመት የሆነው ህፃን ልጄን አሸናፊ አበበ ሰውመሆንን ከቤቱ ወስዶ የጁቤ ፖሊስ ጣቢያ አሰሩት።
+2
የዛሬ አራት ዓመት ግንቦት 13/በ2014 ዓ.ም የመቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን ልጅ ነህ በሚል አገዛዙ የ3 ዓመት የሆነው ህፃን ልጄን አሸናፊ አበበ ሰውመሆንን ከቤቱ ወስዶ የጁቤ ፖሊስ ጣቢያ አሰሩት። ምክነያታቸው ደግሞ አባትህ የፋኖ መሪ ስለሆነ መምጣት እና እጅ መስጠት አለበት በሚል ነበር። ስርዓቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት አስሮ ካንገላተው በሗላ በህዝቡ የተጠናከረ አለም አቀፋዊና አገራዊ የሚዲያ ዘመቻ ግንቦት 18/09/2014 ዓ/ም ህፃን አሸናፊን ለቀቀው። ከታች ካለው ፎቶ ጋር በወቅቱ የተከበሩ አቶ ክርስቲን ታደለን ጨምሮ ሌሎች እህት ወንድሞቼ ለህፃን አሸናፊ አበበ ከፍተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አድርገውለት ነበር። በዚህ ትግል ያልተከፈለ ዋጋ የለም ! እልፎች ለዚህ ትግል መስዕዋት ሆነው፣ለእስር ተዳርገዋል፣ተፈናቅለዋል ተሰደዋል። ስለዚህ በፋኖ ትግል ቀልድ የለም!! ትግሉን የመጠበቅ የመጀመሪያ ስራችን ነው!!! አዲስ ትውልድ !! አዲስ አስተሳሰብ!! አዲስ ተስፋ!! 13/04/2018 ዓ.ም መቶ አለቃ አበበ ሠውመሆን

የአገዛዙ ፓራ ኮማንዶ ሚሊሻ የነበሩት ወደ ቀድሞ ቤታቸው አማራ ህዝብ እየተመለሱ ነው!!! ግንቦት 13 /2018 ዓ.ም አፋፋብን 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎ
+2
የአገዛዙ ፓራ ኮማንዶ ሚሊሻ የነበሩት ወደ ቀድሞ ቤታቸው አማራ ህዝብ እየተመለሱ ነው!!! ግንቦት 13 /2018 ዓ.ም አፋፋብን 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዷ ከሆነችው ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሽጎ ከሚገኘው የአረመኔው አገዛዙ ሰራዊት ጋሻ ጃግሬ በመሆን ሲያገለግል የነበረው  በደም አማራ የሆነ በግብር የገዳዩ አብይ አህመድ ሎሌ የነበረው #ፓራ_ኮማንዶ_ደሴ_አዳም  የተባለ   እስከ አሁን ከገዳይ ጎን ቆሜ  የህዝባችንን መከራ ና ስቃይ ማራዘሜ ቆጭቶኛል ከእንግዲህ ግን  የአማራን ህዝብ ከሚጨፈጭፍ ሰረዓት ጋራ ቀመቆም  የራሳችንን  ህዝብ አልጨፈጭፍም የበደልኩትን ህዝብም ይቅርታ በመጠየቅ በቀጣይ በፋኖ አደረጃጀት ሆኜ ለመካስ ዝግጁ ነኝ በማለት በታላቅ አማራዊ ወኔ የደባይ ጮቄ ሻለቃን በክብር ተቀላቅለዋል!!! ወጣቱ ፋኖን ሲቀላቀል  አንዱን ሚሊሻ ከመሬት በመቀላቀል በመግደል ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎችን ገረዶችን በማቁሰል ደባይ ጮቄ ሻለቃን በክብር ተቀላቅሏል። ደባይ ጮቄ መቶአለቃ አዳነ ሻለቃ  ጠላትን ስቦ በማስከዳትም ይሆን በመምታት እና የጠላትን ኃይል በማፈራረስ በኩል በርካታ ስራዎችን እየሰራች ሲሆን በዛሬው ዕለትም በጀግንነት ለተቀላቀለው  አባልም  የክብር አቀባበል አድርጋለች!!! አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ !!! ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር  24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል ‎

በአመራር ጥበብ እና ወታደራዊ ሳይንስ ዙርያ ሲካሄዱ የቆዩ ስልጠናዎች በስኬት ተጠናቀቁ። ========================= አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ስራ አስፈጻሚ ፣ በስሩ ካሉ የክፍለ ጦር ስራ አስፈጻሚ አመራሮች እና የብርጌድ አመራሮች ጋር በአመራርነት ጥበብና ወታደራዊ ሳይንስ ዙርያ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል። ስልጠናውን የሰጡት ኮረኔል ሙላቴ ሲሳይ የአመራርነት ጥበብ (The Art of Leadership) ማለት ሰዎችን በአንድ የጋራ ራዕይ ዙሪያ በማሰባሰብ፣ በፈቃደኝነትና በታማኝነት እንዲከተሉ የማድረግ እና የማይቻሉ የሚመስሉ ግቦችን በተግባር የመለወጥ የማሳመን፣ የመቀስቀስና የስነ-ልቦና የበላይነት ክህሎት ነው ብለዋል። የአመራርነት  "ሳይንስ" ብቻ ሳይሆን "ጥበብ" የተባለበት ዋና ምክንያት በጽንሰ-ሃሳብ ወይም በደብተር ላይ ባሉ ህጎች ብቻ የማይገዛ  ነው ያሉት ኮረኔል ሙላቴ  ከተለዋዋጭ የሰው ባህሪ ፣ ስሜት እና ሁኔታዎች ጋር አብሮ የሚቀያየር በመሆኑ ነው። ሳይንስ "ምን መደረግ አለበት?" የሚለውን ሲያጠና፣ ጥበብ ግን "እንዴት መደረግ አለበት? ሰዎችንስ እንዴት ማስከተል ይቻላል?" የሚለውን በተግባር ይፈታል ሲሉም አክለዋለል ። ስለሆነም በየደረጃው ያለው  አመራርም የአመራርን ጥበብ ከወታደራዊ ሳይንስ ጋር አጣምሮ የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ  በአንድነት ፣ በወንድማማችነትና  በእውቀት መምራት ጊዜ እማይሰጠው መሆኑን  ያስረዱት ኮረኔሉ ወታደራዊ መረጃዎች ፣ የውጊያ መመሪያ እና ዘመኑን የዋጀ የአሰራዊት አደረጃጀት እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ለተከታታይ ቀናት በሰጡት  የስልጠና  አስምረውበታል። ስልጠናውም ለታችኞቹ አደረጃጀቶች  ቀጣይታይነት ያለው ቢሆንም በደረጃው የተሰጠው ስልጠና  በትልቅ ወንድማማችነትና ፍቅር የተሞላ መከባበር ስጦታዎችን በመለዋወጥ በክብር ተፈጽሟል። ድል ለአማራ ህዝብ !!! ድል ለአማራ ፋኖ !!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!

ሰበር ዜና! በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ  የ102ኛ ኮር በአገዛዙ ምርጫ አስፈፃሚዎች እንድሁም በፖሊስ መኮነኖችና የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ ወሰደ። የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ በጋራ በመሆን ግንቦት 12/ 2018ዓ/ም የተኩለሽ ከተማን ህዝብ በግዳጅና በድብደባ የምርጫ ካርድ በመስጠት ላይ የነበረውን ራሱን ጥምር ጦር በማትለት የሚጠራውን ህዝብን የማይወክል የአገዛዙ ሚሊሻና ፖሊስ እንድሁም የስርዓቱ አገልጋይ  የመከላከያ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመ። የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ የምረጫ ካርድና አመራር አጅቦ ከተኩለሽ ከተማ ወደ ቆቦ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረው የአገዛዙ ቅልብ ወታደር በተለምዶ አጠራር ዝሀ ውሀ ድልድይ በመባል በሚታወቀው አካባቢ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት በራያ ቆቦ ወረዳ ተኩለሽ ከተማ የፖሊስ አዛዥ የነበረ መሰለ አባዩን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላት ተደመሰሱ። የጥቃቱ ምክኒያት በሰሞኑ በአማራ አርሶ አደርና የከተማ ነዋሪ  በየ መንገዱና ቤት ለቤት በመዞር የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ሲያስገዲድ የነበረ የጥምር ጦሩ አካል ላይ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ ከህይወት መሳዋትነት በተጨማሪ ከባድና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሶበታል። ተራማጅ ያልሆነውና ቆሞ ቀሩ የብልፅግና አገዛዝ  ከሐምሌ 28/2015ዓ/ም ጀምሮ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ  በሐይል የአማራ ፋኖን በ14 ቀናት ውስጥ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ሰበብ በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ግፍ  የፈፀመ ቢሆንም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ህዝቡን ከጥቃት በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት ለተከታታይ 3 ዓመት በክልሉ ከ90% በላይ አካባቢዎችን በአሸናፊነት ተቆጣጥሮ ይገኛል ። የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክና ትጥቅ ለማስፈታት በተሳሳተ መንገድ የመጣው የብልፅግና አገዛዝ  ከትናንቱ ስህተት ሳይማር ያለ ህዝብ ፍላጎት አለም አድርጎት የማያቀውን  በጉልበት ጦርነትና የጨረባ ምርጫን በተመሳሳይ ሰዓት ለማካሔድ እየቋመጠ ቢሆንም የአማራ ልጅ ፋኖ የማይናወጥ አቋም በመውሰድ በክልሉ ምንም አይነት የአምባገነኖችና ጨፍጫፊዎች ምርጫ እንዳይካሔድ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው። ከማንም ጋር ሰላም መፍጠር የማይፈልገወ አገዛዙ በመላው ሀገሪቱ የጦርነት አዙሪት በመለኮስ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣በቤንሻንጉልና በአፋር ክልል እንድሁም ከጎረቤት ኤርትራና ሱዳን ጋር የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ያልተረጋጋች ሀገር ለትውልድ በመፍጠር ዜጎች በኑሮ ውድነት፣ በረሐብና ቸነፈር በስራ አጥነትና ጉስቁልና በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ። በመጨረሻም በሁለት ሳምንታት ውስጥ ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ ወደ አማራ ክልል የገባው የአብይ አህመድ የግል ወታደር ላይ ጀግናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በየ አውደ ውጊያው የጥላትን እንቅስቃሴ በማንበርከክና የሀይል የበላይነት በመውሰድ ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ ዙ-23ና ሞርተር 120 ድረስ በመማረክና በመታጠቅ አለምን ጉድ አሰኝቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

የበረራው ንጉስ ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በሬማ ከተማ በፈፀመው ልዩ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ሰባት የሚሊሻ አባላትን በመማረክ ቀሪዎች ላይ እርምጃ ሲዎስድ፣ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር አሃዶች በአገዛዙ ታማኝ አገልጋይ ሚሊሾች ላይ ያነጣጠረ የተሳካ ጥቃት ፈፀሙ። ግንቦት 13/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአሳምነው ዕዝ አሃዶች በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ላይ የተጠናከረ ዘመቻ እያካሔዱ ሲሆን በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ በሬማ ከተማ በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ በአፄ አምደ ፅዮን ኮር በጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር አማካኝነት ከለሊቱ 7:00 ላይ በተፈፀመ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ሰባት (7) የሚሊሻ አባላት ከከተማዋ አደባባይ ሲማረኩ በውል የማይታወቁ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ኮሩ በምስል አስደግፎ በላከው የአውደ ግንባር መረጃ ገልጿል። ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በሰራው ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የተደናገጠው አገዛዝ ከሚዳና አካባቢው የተወጣጡ ዘጠኝ (9) የሚሊሻ አባላት ዛሬ ረፋዱን ጨምሮ ወደ ሰራዊታችን ተቀላቅለዋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር የ7ለ70 ክፍለ ጦር የደመላሽ ሻለቃ ቃኚዎች ዛሬም እንደትላንቱ የጦር ወንጀለኛው ወንበር አስጠባቂ ሚሊሾች ላይ እየወሰዱ ያሉትን እርምጃ አጠናክረው መቀጠላቸውን ኮሩ አስታወቀ። በኤፍራታና ግድም ወረዳ በፈረድዉሀ ቀበሌ በመግባት የአገዛዙ ታማኝ አገልጋይ በሆነው የሚሊሻ ጠርናፊ አቶ ነጋሽ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ሆድ አደር ሚሊሾች ላይ የማያዳግም እርምጃ ሲወስዱ ቀሪው የጠላት ኃይል መሳሪያውን በምርኮ አስረክቦ እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ አጣዬ ከተማ መፈርጠጡን ኮሩ በመረጃው ገልጿል። በተመሳሳይ የድል ዜና የኮሩ አካል የሆኑት አናብስቶቹ የናደው ክፍለጦር የፋኖ ሰራዊት በፈፀሙት ጥቃት የብልፅግናው ታማኝ አገልጋይ፣ የህዳር አህያ ሆኖ ሲጫን በነበረ እራሱን የሰላም አስከባሪ ብሎ የሚጠራው የህዝባችን ፀረ-ሰላም አባል ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ ግለሰቡ ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀምበት የነበረውን የጦር መሳሪያ ገቢ ማድረጉን የኮሩ የግንባር ዘጋቢ ገልጿል። በመርሓቤቴ ወረዳ ፌጥራ ከተማ ከጠዋቱ 01:30 ላይ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት በፈፀሙት የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የተደናገጠው አገዛዝ እንደተለመደው የፈሪ በትሩን ወደ ሲቪሊያን በማዞር ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመ ሲሆን በፋኖ ቤተሰቦች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ዕዙ በረጃው አረጋግጧል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ