ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish3 019
Obunachilar
+4524 soatlar
+967 kun
+45930 kun
Postlar arxiv
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ አስቴሪዮ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
.......ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ አስቴሪየ ቀበሌ ውይይት የተደረገ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ወጣቱ ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
በቋሪት የክርስቲያን ታደለ የአባት አርበኞች ሻለቃ ለግዳጅ ዝግጁ መሆኑን አበሰረ
ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር አካል የሆነው ቋሪት ወረዳ ጣሊያ ቀጠና የሚንቀሳቀሰውና በጀግናው ክርስቲያን ታደለ ስም የተሰየመው የአባት አርበኞች ሻለቃ፣ አደረጃጀቱን በማጠናከር ለማንኛውም ኦፕሬሽናል ግዳጅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።
የሻለቃው አመራሮች እንደገለጹት፣ ሻለቃው በሰው ኃይልና በሥነ-ልቦና ራሱን እንዲያጠናክር ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት፦
▪️ወታደራዊአደረጃጀት፦ ሻለቃው በቲምና በጋንታ ደረጃ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተዋቅሮ ለግዳጅ ዝግጁ ሆኗል።
▪️የአመራር ማሟላት፦ በሻለቃው ውስጥ የነበሩ የአመራር ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ በመሙላት፣ ግልጽ የሆነ የዕዝ ሰንሰለት ተፈጥሯል።
▪️ቅንጅታዊ አሰራር፦ ሻለቃው ከቀጠናው የዐፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ጋር በቅርበት እንዲተሳሰር ተደርጓል።
ይህ የተጠናከረ ዝግጅት የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና የሚሰጡትን ተልእኮዎች በብቃት ለመወጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል።
©️102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር ህዝብግንኙነት
+1
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እራሱን እንደ ንስር አድሶ ከፍ ብሎ እየበረረ ይገኛል‼️
44ኛ ክፍለ ጦር ከመቼውም በላይ ጠንካራ አደረጃጅት በመያዝ ደማቅ ድልን እያስመዘገበ ባለበት በዚህ ወቅት የክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተከታታይ ለሁሉም ሻለቃዎች የስነልቦና የፓለቲካና ሌሎች ወቅታዊና አካሂዳዊ ጉዳዮችን የማስገንዘብ ስራ በጥልቀት እግር በግር እየተከታተሉ እየሰሩ ይገኛሉ።
ጀብደኛው 44ኛ ክፍለ ጦር የነበረውን ዝና ቀደም ብሎ መመለሱ የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ካለበት ጥንካሬ ልቆ ለመገኘት ሌት ቀን በልዩነት መስራቱን ቀጥሏል።
በቅርቡ ምድር አንቀጥቅጥ የሆነ ስራን ሰርቶ እጅ አፍ ላይ የሚያስጭን ድል ለመላው አማራ የሚያበስር ይሆናል።
©አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሚኒሊክ ዕዝ 104ኛኮር 25ኛ ክ/ጦር በቁጥጥራቸው ስር ባሉ ነፃ ቀጠናዎች የህዝባዊ ምክክር መድረኮችን በስኬት አጠናቀዋል።
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተካሄዱት በእነዚህ መድረኮች፣ የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ወጥ የሆነ አሰራርን በተመለከተ ከማህበረሰቡ እና ከአመራሮች ጋር በጋራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ የውይይት መድረኮች ህዝቡ በነቂስ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ምክክሩ ተካሂዷል። ተሳታፊዎች የህልውና ትግሉን አስመልክቶ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹ ሲሆን፣ የአፋብን የአንድነት አሰራር የአሸናፊነት ጉዞው የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑን በአጽንኦት አረጋግጠዋል።
በዚህም በግሼ ክላስተር (የላይኛው እና የታችኛው መንዝ ቀጠና) በወሎ ቤተ_አምሐራ ምኒልክ ዕዝ እና በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ጥምረት በተዘጋጁ መድረኮች፣ በግሼራቤል ወረዳ ደል እና በኮረብቲት ቀበሌ የአርሶ አደሮች የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። በመድረኩም ማህበረሰቡ ከፋኖ ጎን ቆመን ስረዓቱን እናፈርሳለን እንጂ ገዳያችንን አንመርጥም ብለዋል። በዕለቱ አርሶ አደሩ በአካባቢው የህልውና ትግል ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከአንድነት በኋላ እያሳየ ያለው ወጥ የሆነ አሰራር፣ ለህልውና ትግሉ ድል አድራጊነት ወሳኝ መሆኑ በመድረኮቹ በስፋት ተነስቷል። ማህበረሰቡ በነፃነት ባንጸባረቀው ሃሳብ መሰረት፣ የህዝብ እና የፋኖ አንድነት የድል ጉዞው የጀርባ አጥንት መሆኑን አረጋግጠዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ሚኒሊክ ዕዝ 104ኛ ኮርየህዝብ ግንኙነት መምሪያ
+1
ሦስት ጥቁር ክላሽ የያዘ ወታደር ፋኖን ተቀላቀለ!
መነሻውን ላሊበላ ከተማ ሁለት ቁጥር ተብሎ ከሚጠራው ካምፕ ያደረገው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባል፡ የራሱንና ሁለት ጨምሮ በድምሩ ሦስት ጥቁር ክላሽ፣ 300 ተተኳሽ፣ ሁለት የእጅ ቦምብ በመያዝ ዛሬ ሚያዚያ 23/ 2018 ዓ/ም ፋኖን ተቀላቅሏል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር 30ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀለው የመከላከያ ሰራዊት አባሉ፡ ግፈኛውን አገዛዝ ከድቶ ፋኖን በመቀላቀሉ እጅግ ደስተኛ እንደሆነ መናገሩን ጣቢያችን ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በዘመቻ አባናደው ሙሉ በሙሉ ተደምስሳ ዳግም ከተቋቋመችው 12ኛ ክፍለ ጦር ከ5ኛ ሬጅመንት የወጣው ወታደር ኤፍሬም ከፊያለው፡ የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉለት ደማቅ የክብር አቀባበል እንደተደሰተ ተናግሯል።
ወታደር ኤፍሬም ከፍያለው አክሎም የዚህ አስከፊ ስርዓት አካል ሆኘ እስካሁን በማገልገሌ ተፀፅቻለሁ በማለት ለቀጣይ ከፋኖ ጎን ሁኝ በመታገል የበደልኩትን ህዝቤን እክሳለሁ ሲል ቃል መግባቱን ጣቢያችን ከምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
"ዝም ነው ጭጭ ነው ውሃ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም "
ትዕዛዦች በሙሉ ያለ ምንም ማወላወል እና ማመንታት ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ ይፈፀማሉ ።
ሰሞኑን የጠላት ሰራዊት የሚባለው የአትሌቶች ስብስብ የብሬ አስታጥቄ ትጥቅ አቀባይ ሚሊሻዎች ኑ እጅ እንሰጣለን አብዝተዋል ። የእኛም መልስ ..
ትክክለኛ ውሳኔ ወስናችኋል ለአንድ ዱርዬ ስልጣን ብላችሁ ከምትmoቱ ውሳኔው ቢዘገይም ተገቢ ነው ግፉበት የሚል ነው ። 😁
ያው እንዳልነው ተዋጋችሁም አልተዋጋችሁም ብልፅግና የሚባል ማፍያ ድርጅትን እና አብይ የተባለ ጄnoሳይደርን ከፈጣን ውድቀት አታድኑትም ። ለዚህ ቃል የጣቴን ያክል እንርግጠኛ ነኝ ።
ይህ ከህዝባችን እና ከነበልባሉ ሰራዊታችን አቅም አንፃር ሊታሰብ አይችልም ።ድርድርም ቢባል እጅ ስጡ ጥሪ ጊዜያቸው አልፏል ። ያለው ብቸኛ አማራጭ የእኛ ማሸነፍ ብቻ ነው ።
መጨረሻውን ጠብቁ ውድ አማራውያን ...
የአብይ ብልፅግና መቃብር ቅርብ ነው ።
@ዱሩ ቤቴ
+7
24ኛ ክ/ጦር ከደባይ ጠላት ግን ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር !!
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ደባይ ጠላት ወረዳ ጀረምስ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ ጀረምስ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወጣቶች ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
⏭የድሮን ቅኝት⚠️
ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በሸዋ ቀጠናዎች፣ በመሀል አምባ፣በጭምብሬ ፣በመንዝ ቀጠና፣ በተጉለት ቀጠና፣በከሰም ቀጠና፣በኮረማሽ እና በሸረር ቀጠናዎች የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
✅ከዕዙ መረጃና ደህንነት መምሪያ⚠️
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የብልፅግና አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ!!
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆንርኝ ኮር የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በየዕለቱ የጠላትን አከርካሪ እየሰበረ፣ ህዝብን በጨረባ ምርጫ ሰበብ የሚያሰቃየውን የብልፅግና ቡድን ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ አሸናፊነቱን በድል እያስመሰከረ ይገኛል።
ማያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ፣በዚሁ የአገዛዙ መንገድ መሪና የህዝብን ስቃይ ለማራዘም ተልዕኮ ፈፃሚ ሀይል ላይ በተጠና ኦፕሬሽን መብረቃዊ ጥቃት ተፈፅሟል።
በመኮይ ዜሮ አምስት (05) ቀበሌ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፣ፋኖን በማስወጋትና አስገዳጅ በሆነ መንገድ ህዝቡን የሚያሰቃዩትን የወረዳውን የብልፅግና አመራሮችና ካቢኒዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረች መኪና ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል። በዚህም መሠረት
ደምስ አበራን ጨምሮ ስምንት (8) የብልፅግና አመራሮች ላይ ከባድ እርምጃ ተወስዷል። ጥቃቱ የደረሰባቸው አመራሮች በሶስት አምቡላንሶች ተጭነው ለህክምና ወደ ደሴ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል።
ክፍለጦሩ የህዝባችንን መከራና ሲቃይ በሚያራዝሙ ባንዳዎች ላይ ይህና መሰል እርምጃዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያረጋግጧል።
የመረጃ ምንጭ- የመሃመድ ቢሆነኝ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ወሳኝ የደፈጣ ጥቃት ተፈጸመ፤ የብልፅግና አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ!!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆንርኝ ኮር የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በየዕለቱ የጠላትን አከርካሪ እየሰበረ፣ ህዝብን በጨረባ ምርጫ ሰበብ የሚያሰቃየውን የብልፅግና ቡድን ጉሮሮ ለጉሮሮ በመናነቅ ላይ ይገኛል።
ማዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ፣ የክፍለጦሩ ብቁ የጦር አመራሮች ባቀዱት የተጠና ኦፕሬሽን፣ የአርበኛ አያሌው መክት እና የአርበኛ ሸጌ መርድ ሻለቆች በጋራ በመቀናጀት በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈጽመዋል።
በመኮይ ዜሮ አምስት (05) ቀበሌ በተፈጸመው በዚህ ደፈጣ ጥቃት፣ የወረዳውን የብልፅግና አመራሮችና ካቢኒዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረች መኪና ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል። በዚህም መሠረት
የጠላት ጉዳት ደምስ አበራን ጨምሮ ስምንት (8) የብልፅግና አመራሮች ላይ ከባድ እርምጃ ተወስዷል። በዚህም ተሽከርካሪዋ በመገለባበጥ ለሁለት በመከፈሏ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ ሆናለች። ጥቃቱ የደረሰባቸው አመራሮች በሶስት አምቡላንሶች ታጭቀው ወደ ደሴ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል።
ይህ ድል የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በጠላት ላይ እየወሰደ ካለው ተከታታይ እርምጃ አንዱ ሲሆን፣ ትግሉ አላማውን እስኪያሳካ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዕዙ ያረጋግጣል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ በቁጥጥራቸው ስር ባሉ ነፃ ቀጠናዎች የህዝባዊ ምክክር መድረኮችን በስኬት አጠናቀዋል።
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተካሄዱት በእነዚህ መድረኮች፣ የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ወጥ የሆነ አሰራርን በተመለከተ ከማህበረሰቡ እና ከአመራሮች ጋር በጋራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ የውይይት መድረኮች ህዝቡ በነቂስ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ምክክሩ ተካሂዷል። ተሳታፊዎች የህልውና ትግሉን አስመልክቶ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹ ሲሆን፣ የአፋብን የአንድነት አሰራር የአሸናፊነት ጉዞው የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑን በአጽንኦት አረጋግጠዋል።
በዚህም በግሼ ክላስተር (የላይኛው እና የታችኛው መንዝ ቀጠና) በወሎ ቤተ_አምሐራ ምኒልክ ዕዝ እና በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ጥምረት በተዘጋጁ መድረኮች፣ በግሼራቤል ወረዳ ደል እና በኮረብቲት ቀበሌ የአርሶ አደሮች የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። በመድረኩም ማህበረሰቡ ከፋኖ ጎን ቆመን ስረዓቱን እናፈርሳለን እንጂ ገዳያችንን አንመርጥም ብለዋል። በዕለቱ አርሶ አደሩ በአካባቢው የህልውና ትግል ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከአንድነት በኋላ እያሳየ ያለው ወጥ የሆነ አሰራር፣ ለህልውና ትግሉ ድል አድራጊነት ወሳኝ መሆኑ በመድረኮቹ በስፋት ተነስቷል። ማህበረሰቡ በነፃነት ባንጸባረቀው ሃሳብ መሰረት፣ የህዝብ እና የፋኖ አንድነት የድል ጉዞው የጀርባ አጥንት መሆኑን አረጋግጠዋል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 23/08/2018 ዓ.ም
+2
👉 በቀን 21/08/2018 ዓ/ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ➊ⓞ❷ኛ ኮር
❷❷ኛ ክ/ጦር
የተፈፀ ጀብድ !
ልክ በሆነ ስሌት ፍፁም በሆነ ወንድማማችነት መከባበበር መደማመጥ ቅንነት የተሞላበት ያለምን ኮሽታ በወጣቶቹ የጦር መሀንዲሶች :-
1. ም/ወአዛዥ➝ ገደፋው አይዘንጋው
2. ዘመቻ መምሪያ➝ ባየልኝ ወንዱ
በትላንትናው ዕለት ቀጠናውን የሚመጥን ህዝባችን የሚያነቃቃ የጠላት ቅስም የተሰበረበት ድል እንካችሁ ብለውናል ::
👉 እኛም ከመቀመጫችን ብድግ ብለን እጅ ነስተናል 🤝
እኒህ አብሪ ኮከቦች አክለው እንደተናገሩት ይህ ጅምር ነው ነገ ባህር ዳርንና አካባቢውን እንደአጠቃላይ ምንም ዓይነት የጠላት ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ አፈራርሰን ትልቅ ድል እናበስራችኃለን ብለውናል ::
+3
201ኛ ኮር ከሰዴ ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ሰዴ ወረዳ የሰዴ ከተማ የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ሚያዚያ 23 የቅዱስ ጊዮርጊስን የዕረፍት በዓል በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በድምቀት ተከብሯል።
~~~~
64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። ሐገሩ ፍልስጤም አሁን እስራኤል ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ አሁን (ሉድ) ይባላል።
ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታትን ያስጨነቀ፣ ቤሩታዊቷን ከዘንዶ አፍ ያዳነ፣ የመበለቷን ቤት ምሰሶ ያለመለመ፣ ሰባት ዓመት በፅኑ ተጋድሎ የተጋደለ በኋላ በ27 ዓመቱ በ304 ዓ.ም ሚያዚያ 23 ቀን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ነፍሱን የሰጠ ፅኑ ሰማዕት ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን እያልን ዲማ ጊዮወረጊስ የመላከ ብረሃን አድማሱ ጀንበሬ፤ የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ፤ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ የፍቅር እስከ መቃብር ድርሰት መነሻ፤ እሳቸውም የቤተክነት ትምህርት የተማሩበት የቅዱሳን እና የጀግኖች አርበኞች መፍለቂያ ቦታ ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ነው።
በክብር በአሉ ከተለያዩ ቦታ የተገኙ የሐይማኖት አባቶች፣ ካህናት፣ ምዕመናን እና በአካባቢው የሚገኙ የከተማዋ ኖሪዎች እንዲሁም ከአገዛዙ ጋር እየተደረገ ባለው የህልውና ትግል ሶስት ዓመት ሙሉ ዲማ ከተማን ያላስደፈሩ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት በተገኙበት በዲማ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አክብረውታል።
ክብር በአሉ አገዛዙ አስርጎ በአስገባቸው ሐይሎች እንዳይደናቀፍ በጀግኖች የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የመንፈስ ልጆች 64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት ከፍተኛ ጥበቃ በማድርግ በዲማ ጊዮርጊስ በተገኘው ምዕመናኑ ጋር በሰላም ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ከታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ሰማይ ስር
