uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 721
Obunachilar
+4524 soatlar
+1767 kun
+1 15530 kun
Postlar arxiv
❗️የሸዋ መረጃ❗️ ብልፅግና በሸዋ ቀጠና :- 1: የሪፐብሊካን ጋርድ 2 ክፍለጦሮች 2: የአየር ወለድ እና ኮማንዶ 6 ክፍለጦሮች 3:- የባህር ኃይል ኮማንዶ 1 ክፍለጦር 4:- የ6ኛ ዕዝ አካል የሆ
❗️የሸዋ መረጃ❗️ ብልፅግና በሸዋ ቀጠና :- 1: የሪፐብሊካን ጋርድ 2 ክፍለጦሮች 2: የአየር ወለድ እና ኮማንዶ  6 ክፍለጦሮች 3:- የባህር ኃይል ኮማንዶ 1 ክፍለጦር 4:- የ6ኛ ዕዝ አካል የሆኑ  እግረኛ ሁለት ክፍለጦሮች እንሳሮ እና በጅሩ በኩል። 5. እንዲሁም ከአድማ ብተና እና ሚሊሻ አሰማርቶ የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ  በቀጠናው የስልክ ኔትወርክ በማጥፋት :- 6. ደብረዘይት ይገኝ የነበረውን የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር ከ3ኛ መካናይዝድ ጋር በማቀናጀት በአፋር ዞሮ በከሚሴ በኩል ወደ ሸዋ ቆላማ ቦታዎች አስገብቷል። 7. የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ታጣቂዎችን ጨምሮ የዞኑን ሚሊሻዎች ወደ ራሳ፣ ቀወት፣ኤፍራታ ግድም እና ማጀቴ አካባቢ ሰምሪት ሰጥቶ እየተዋጋ ይገኛል።   ይሄ ተስፋ የቆረጠ የመከላከያ ሰራዊት የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጦር አዝምቶ አበክሮ እየሰራ ነው።  እነሱን መደም*ሰስ ፍላጎት ቢኖረውም የገባው ሰራዊት ለራሱ እየተደ*መሰሰ እየተ*ማረከ ይገኛል።በአገዛዙ ላይም ትልቅ መደናገጥ ፈጥሯል። ጋዜጠኛ አደራ ዘላለም(ባዶ እግር ሚዲያ)

ጀኔራሎች ጭኖ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ጥቃት ተሰነዘረበት። ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆነችዉ እሸት ክፍለ ጦር ጀኔራሎችን እና የብልፅግና ተላላኪ የሲቪል አመራሮችን አሳፍሮ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ ጠቃት ሰነዘረችበት። ጀኔረሎቹ እና የሲቪል አመራሮቹ  ከ ሰቆጣ ከተማ የቆዩ ሲሆኑ ወደ ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ)ቀበሌ ለመግባት በ 2 ክፍለ ጦር ታጅበዉ እየመጡ እያለም በ ሀይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እየተገረፈ እንደምንም ኤሪፖርቱ ላይ ቢደርሱም እሸት ክፍለ ጦርም ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጋለታለች። ጀኔራሎችን ጭኖ የነበረዉ አንቶኖፉ በመጀመርያዉ በረራ ትንኩሳ ሲደረግበት አቅጣጫዉን ስቶ የበረረ ሲሆን በድጋሜ ተመልሶ ኤሪፖርቱ ጋር ያረፈ ቢሆንም በሁለተኛዉ በረራ በከባድ መሳርያ እገዛ እንደምንም ብሎ ያለፈ ሲሆን እግረኛ ሰራዊቱ ከከባድ መሳርያዉ በተጨማሪ በ 3 አቅጣጫ ቢዘረጋም በአንደኛዉ አቅጣጫ ዘርግቶ የነበረዉ ግትልትል ሰራዊት  በተለምዶ ሳይና በር ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል። ትንቅንቁም በዛሬዉ ዕለት ማለትም የካቲት 2/2018 ዓ.ም የተደረገ  ሲሆን  ብዛት ያለዉ የአገዛዙ  ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሁኗል። እሸት ክፍለ ጦር ከላሊበላ ኤሪፖርት(ሽምሽሃ) ቀበሌ በ10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ እምትገኝ ክፍለ ጦር መሆኗም አይዘነጋም። በመጨረሻም የእሸት ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ  መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌም ''የአብይ አህመድ አፈ ቀላጤዎች በቅርቡ ከ ቱርክ እና ከአረብ አገር በ ክራይ በመጡ ድሮን እና ጀቶች በአየር ኃይል 90ኛ አመት ላይ ትርኢት ሲያሳዩ ''ሰማዩ የኛ ነዉ'' ያሉ ቢሆነም ሰማዩም ምድሩም  የናንተ ሳይሆን የኛ ነዉ ሲል ተናግሯል''። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 2/2018 ዓ.ም

በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለ
በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለውና ለሀገራችን ሕዝቦች ዋስትና የሚሆን ርዕዮተ-ዓለምን ያነገበ ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን! አሁን ከዚህ ኃይል ጋር ተሰልፋችሁ ለነጻነታችሁና ለሀገራችሁ የምትቆሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ። ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለ
በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለውና ለሀገራችን ሕዝቦች ዋስትና የሚሆን ርዕዮተ-ዓለምን ያነገበ ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን! አሁን ከዚህ ኃይል ጋር ተሰልፋችሁ ለነጻነታችሁና ለሀገራችሁ የምትቆሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ።

ሰበር ዜና! የምስራቅ አማራ እና የሰሜን አማራ መገናኛ የሆነችው ንፋስ መውጫ ጋይንት ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች! በከተማዋ ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ/ም ሰዓታትን  የፈጀ ከባድ ውጊያ ከተደረገ በኋላ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል። የብልፅግና መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ከአራት ወረዳዎች የተሰባሰበው የአድማ ብተናና የሚኒሻ እንዲሁም የፖሊስ ኃይል ከፋኖ ጋር ግማሽ ቀን የፈጀ ውጊያ ያደረገ ሲሆን፡ በመጨረሻም የፋኖን እርምጃ መቋቋም አቅቶት ገሚሱ ሲደመስስ ገሚሱ ደግሞ ከተማዋን ለቆ ፈርጥጧል። ፀረ አማራው የብልፅግና አገዛዝ "በጋይንት ቀጠና ፋኖ እጅ ሰጥቶ አብቅቷል፣ ቀሪውን ደግሞ ደምስሼ ጨርሸዋለሁ" በሚል የበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ ባለበት ወቅት ነው ከተማዋ በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባችው። የክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ከፊያለው ደሴ እስትንፋሶች በአሁን ሰዓት በከተማዋ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ካለ ለማጥራት የአሰሳ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል!

ከተማረኩ የአብይ ወታደሮች መካከል በትንሹ ለቅምሻ ይችን እያያችሁ ቆዩ..! እንመለስበታለን፡፡ ሁላችህም አፋብን እያላችሁ ኮምቱ ..!
+1
ከተማረኩ የአብይ ወታደሮች መካከል በትንሹ ለቅምሻ ይችን እያያችሁ ቆዩ..! እንመለስበታለን፡፡ ሁላችህም አፋብን እያላችሁ ኮምቱ ..!

የአደረጃጀት ዜና! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የኮር 2 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለበርካታ ቀናት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የኮርና የክ/ጦር ስያሜ በመቀየር እንዲሁም የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርጓል። በመሆኑም የበፊት ስሙ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 የነበረውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በማለት ቀይሯል። ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር እንዲሁም በስሩ የሚገኙትን ሁሉንም ክፍለ ጦሮች በሰሩት ጀብዱ መሰረት የስም ስያሜ ሰጥቷል:: 1ኛ.ዞብል አምባ ክፍለ ጦርን 12ኛ ክፍለጦር 2ኛ.ካላኮርማ ክፍለ ጦርን 49ኛ ክፍለጦር  3ኛ.ታጠቅ ክፍለ ጦር ዲቢና ወርቄ ባለሸርጡ ብርጌድ እና የኮር መካናይዝድ በአንድ ላይ በመበወዝ 65ኛ ክፍለጦር በሚል ተሰይመዋል:: በመጨረሻም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ-ሂስ (ግምገማ) በማድረግ በቀን 28/05/2018 ዓ.ም አዳዲስ የስራ ሃላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል። 1.ዋና ሰብሳቢ...............አርበኛ ረዳ ውበቱ 2.ወታደራዊ አዛዥ............አርበኛ ጌታቸው መልኩ 3.ም/ወታደራዊ አዛዥ.........አርበኛ ዘውዱ ዳርጌ 4.ወታደራዊ አማካሪ.........አርበኛ ሻ/ል እንድሪያስ ሽፈራው 5. ዘመቻ መምሪያ ............አርበኛ ዋሴ ጫኔ. 6.ም/ዘመቻ መምሪያ........ አርበኛ በላይ መንግስቱ 7.ወታደራዊ አሰተዳር.......አረበኛ ፈለቀ ደጉ 8.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ መ/ር ሞላ ዝናቤ 9.ጤና መምሪያ..............አርበኛ ተፋየ ታደሰ 10.ፋይናንስ ሃላፊ................አርበኛ አለሙ ፈንቴ 11.ም/ፋይናንስ ...................አርበኛ ምስጋን ታደሰ 12.የፖለቲካ መምሪያ..............አርበኛ ሻምበል አሌ 13.የህዝብ አስተዳደር.........አርበኛ ሳሙኤል ሞገስ 14.የህዝብ ግንኙነት.........አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ 15.ሀብት አፈላላጊ...............አርበኛ ሀበቴ ዘውዱ 16.መረጃና ደህንነት.............######## 17.ስልጠና መምሪያ......አርበኛ መ/አለቃ ሲሳይ መንግስቴ 18.አማካሪና ፀሀፊ...............አርበኛ ባየ ዝናቤ 19.የህግ መምሪያ................አርበኛ መስፍን አያሌው 20.ሎጅስቲክ መምሪያ..........አርበኛ ዝናቤ በሪሁን 21.ኦርድናንስ...................አርበኛ ፈንታቢል ደርሶ 22.ም/ኦርዲናስ................አርበኛ አንዱአለም አዲሴ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ የካቲት 2/2018 ዓ.ም

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር በእሥቴ መዳረሻ [የካቲት 02/2018ዓ.ም] 🔑ጉና ክፍለ ጦር ✔እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ✔ሐገረ ቢዘን ብርጌድ ✔አንዳ ቤት ብርጌድ 🔑ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር በእሥቴ መዳረሻ [የካቲት 02/2018ዓ.ም] 🔑ጉና ክፍለ ጦር ✔እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ✔ሐገረ ቢዘን ብርጌድ ✔አንዳ ቤት ብርጌድ 🔑ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን በጥምረት እየገረፉት ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ወደፊት ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ብሬኑንም መትረየሱንም ይዘውት እየመጡ ነው‼️‼️ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በስቦ ማስከዳት ሁለት(02) መትረየስ አንድ ክላሽ በመያዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። ሌሎቻችሁስ የአብይ አህመድ
+1
ብሬኑንም መትረየሱንም ይዘውት እየመጡ ነው‼️‼️ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በስቦ ማስከዳት ሁለት(02) መትረየስ አንድ ክላሽ በመያዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። ሌሎቻችሁስ የአብይ አህመድ ስልጣን የምትሞቱት እስከመቸ ድረስ ነው?? የካቲት 02/2018 ዓ/ም

ሰበር ዜና!! መካነ ኢየሱስ ከተማ በድጋሜ ተሞሸረች! ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጨረው ተጋድሎ የድል ዜና ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ======================== የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሜካናይዝድ መሳሪያዎች ከወደቁ ቆራሌዮ ብረታ ብረት የዘለሉ አይደሉም !! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቂ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የግዙፉ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ አንደኛ ኮር መንትዮዎቹ ጉና ክፍለ ጦር እና ዘረ ውባንተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በጋራ የብልፅግናን ጠላት ሃይልን በመደምሰስ ታሪክ ስርተዋል ። የበሰበሰው የብልፅግና አገዛዝ ምላስ ብቻ የቀረው ሰርዓዊቱን በየ ቀኑ እየቀበረ ስልጣኑን ለማቆየት እየተፍጨረጨረ ቢገኝም ከሽንፍቱ ግን አልዳነም። ከማለደው 3:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9:35 ሰዓት በፈፀሙት ጥቃት ልዩ ስማቸው መካነ ኢየሱስ ከተማ፣ እስቴ ዴንሳ ተራራ፣ ለዋዬ፣ ማይነት ኢየሱስ፣ ሚድርቋ እና ጋሳይ ከተማ ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠረው ስብስብ በክንደ ረመጦች የፋኖ አባላት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ሲያስተናግድ ውሏል። ይህ በእንዳህ እንዳለ በተመሳሳይ ዜና ስማዳ ወረዳ 265 በላይ የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። ወረዳዋም በጀግኖች ፋኖ ተሞሽራ ትገኛለች። በቀጣይ ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የካቲት 02/2018 ዓ.ም ፋኖ መ/ር ያሬድ ገደፍው የጉና ክፍለ ጦር ህ/ ግ ሃላፊ

የአገዛዙ ወታደሮች በምዕራብ አማራ ቀጠና ቡሬ ወረዳ ሰርተከዝ ማርያም ቤተክርስቲያን በተሰበሰቡ አማኞች ላይ ጥቃት ፈፀሙ! ትናንትናው የካቲት 01/2018 ዓ.ም በምዕራብ አማራ ቀጠና ቡሬ ወረዳ ሰርተከዝ ቀበሌ የማሪያምን ቤተክርስቲያን የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ለማክበር ከህጻናት እስከ አዛውንት በተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀይማኖት አባቶች ላይ የፀረ አማራው ብልፅግና ወታደሮች ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ወከባ መፈፀማቸው ተሰምቷል። የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በተሰቡበት የጠላት ሃይል ከበባ በመፈጽም #የቃል ኪዳኑን ታቦት በተሸከመው ካህን እና ምዕመናን ላይ የተኩስ እሩምታ በመክፈት የቃል ኪዳኑን ታቦት ከካሀኑ ላይ ወርውሮ መሬት በመጣልና ቄስ ጌትነት ገላው የተባለ ታቦቱን ተሸክሞ የነበረ የቤተክርስቲያን አገልጋይ አስረው እንደወሰዱት እና በርካታ ንጹሃን አርሶ አደሮችን አግተው መውሰዳቸውንም በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ለ77ኛ ክ/ጦር መረጃውን አድርሰዋል። አሸባሪው ሀይል የሀይማኖት ተቋማትን በተደጋጋሚ የምሽግ ቦታ ከማድረግ በዘለለ የቤተክርስቲያኗን ቅርሶች በመዝረፍ አማኞቿን በመግደልና በማንገላታት እኩይ ተግባሩን  አጠናክሮ ቀጥሎበታል። መረጃው በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

ትግሉ ፅናት ይጠይቃል!! የካቲት 02/2018 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ በመቃወም ለአማራ ህዝብ ነፃነት የህልውና ትግል ለማሻገር የተንኮታኮተውን የአገዛዙ ኃይል ለመቅበር እና ትግሉን ቀጥ ባለ ቁመና በመምራት ጫፍ ለማድርስ በ64ኛ ክፍለ ጦር የሚገኙ አመራር እና አባላት ድርጅቱ እና ህዝባችን የሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ እየታገሉ ይገኛል። የጀግኖች ስብስብ የኮስትር ግርፎች የሽፈራው ልጆች ከውስጥም ከውጭም ያለውን ጫና ተቆቁመው ክፍለ ጦር የተሻለ ቁመና ይዞ እንዲሄድ ሌት ተቀን ድምፃቸውን አጥፍተው እየሰሩ ይገኛል። የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል መሪዎቹን መርጦ ወደ አንድ መምጣቱ እና ቀጥ ያለ ቁመና እየያዘ መምጣቱን ተከትሎ በክፍለ ጦሩ እየታዩ የሚገኙት አንዳን የጠላት ተልኮ ተሸካሚ ቅርብ ወራጆች ድርጅቱ በፋይናስ እና ኦዲት ኢንስፔክሽን ወደ መሬት ወርዶ መስራት ሲጀምር አገዛዙ አስርጎ ያስገባቸው ተለላኪዎች ታጋይ መሳይ የሌባ ስብስቦች ተልዕኮቸውን ፈፅመው ከህዝብ እና ከድርጅቱ የዘርፍት ገንዘብ በኦዲት እንደሚጠየቁ እርግጠኛ ሲሆኑ እጅ እየሰጡ ይገኛሉ። ትግሉ እየጠራ ነው!! 64ኛ ክፍለ ጦር የትግሉን መነሻ እና መድርሻ፣ ዓላማ ያለው፣ ጠላት በስሙ ሲጠራ የሚያስፈራ ጠላትን  መመከት እና መደምሰስ የሚችል የሰለጠነ ሰራዊት እየገነባ ይገኛል። በክፍለ ጦራችን የአማራን ህዝብ ተዋርሰው በሆዳቸው ያደሩ ተራ ግለሰቦች ከአማራ ህዝብ ጠላት ጋር በማበር በባንዳነት በመሳተፍ የራሳቸውን ወገን አሳልፈው ክብራቸውን አዋርደው በተራ ጥቅማ ጥቅም አማራነታቸው በመሸጥ #እንቁ_ጀግኖችን በሸበል በረንታ በየኮሬ የኩበት አካባቢው ቀበሌ ከአንዴ ሁለቴ በከበባ አስበልተው የክ/ጦር አመራሮችን በጠላት ጥይት ለማስመታት ሲሰሩ ቆይተዋል። እነዚህ የአማራ ህዝብ የደም ግብሮች ከአገዛዙ ጋር በመሰለፍ  የአማራ ህዝብ ታሪክ ያጠፉ ባንዳዎች መሆናቸውን ለታሪክ መዝግበን ይዘናል። የአማራ ህዝብ ዘብ የጀግኖች የአርበኞች ስብስብ ብዙ ጀግኖች የወደቁበት የአማራ ፋኖ ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እየሰራን እንገኛለን። የፋኖን ዩኒፎርም በመልበስ በትግላችን ተመሳስለው የአገዛዙን ስረዓት የሚደግፉ፣ የፋኖን ስም የሚያጥላሹ፣ በትግሉ ስም ህዝባችንን እና ተዋጊው ወታደሩን በእንግልት ሲያሰቃዩ የቆዩ ግለሰቦች መሆናቸው ክፍለ ጦሩ ከህዝብ እና ከፋኖ አባላቱ የተሰጠው ጥቆማ ተቀብሎ የኦዲት ስራ እየሰራ መሆኑን እና እርምጃ እንደሚወሰድባቸው በማወቃቸው ወደ ጠላት መግባታቸውን ማሳወቅ እንወዳለን።                                  አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!          የካቲት 02/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

ሰበር ሰበር የድል ዜና !!! ከ50 በላይ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ሲደመሰሱ ቀሪዎች ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። በካምፕ ዉስጥ ከተጠረነፉት የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አባላት አንድ አባል ብቻ ሲቀር ሌሎች ሙት እና ቁስለኛ ሆነዋል። በቀን 02/06/2018 ዓ.ም የአፋብን ምዕ/አ/ቀ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ እና 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር የክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ ሻለቃ አንድ(1) ሻምበል በተሳተፉበት አዉደ ዉጊያ በመተከል አዉራጃ ፓዊ ወረዳ መንደር 21 ቀበሌ ላይ ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት በተደረገዉ አስገራሚ ኦፕሬሽን:- 1.ከ50 በላይ ተላላኪ ሚሊሻ እና አድማ ብተና ሲደመሰሱ ቀሪዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቆስለዋል። 2.ሶስት/3/ ብሬን፣ 55 ክላሽንኮቭ፣ 4 አብራራው፣ 6 ኤስኬኤስ መሳሪያዎችን ማግኘት/መማረክ/ ተችሏል። 3.አጅግ በጣም በርካታ ተተኳሽ እስከ ትጥቁ እና የእጅ ቦንቦችን ማግኘት ተችሏል። ማስረጃዉን በፎቶ ይዘን እንመለሳለን ። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት የካቲት 2/2018 ዓ.ም

ወቅታዊና ትኩስ መርጃዎች እንዲያገኙ ይወዳጁት https://t.me/minilik28