ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish2 955
Obunachilar
+424 soatlar
+127 kun
+38830 kun
Postlar arxiv
የብልፅግና ይሁዳዊ ጉባኤ በ31ኛ ክፍለ ጦር በዳውንት ወረዳ በግስላዎች ቅፅበታዊ ጥቃት ተበተነ!
ግንቦት 9/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የ31ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች የብልፅግናን ጉባኤ የጉም ስር አድርገውታል!!
ከብዙ ፈተናዎች ማግስት በበረሀ ላይ ራሷን ያፀናችው 31ኛ ክፍለ ጦር (የድሞዋ ሰንጥቅ) የብልፅግና ይሁዳዊ ጉባኤን በመበታተን የብልፅግናን የጨረባ ምርጫ መበታተን ተችሏል።
ታች ዳውንት ገርሳ ከሚባል ቦታ የዳውንት ማህበረሰብን በወታደሮች ክንድ እያስደበደበ ወደ ይሁዳዊ ጉባኤ የወሰደው የፋሽስቱ ሰራዊት ለሚያጎበድድላቸው የብልፅግና ካቢኔዎች እጅ መንሻ ሳይደርስ የአማራ ህዝብ መዳኛ ልጆች በ31ኛ ክፍለ ጦር ቅፅበታዊ ጥቃት ከቀሳ እስከ ገደባ የጁላ ሰራዊት ቂጥ ቂጡን ሲለበለብ ውሎ ስብሰባውም ተበትኗል።በማዳበሪያና በእርዳታ ማስፈራሪያ የሚንቀራፈው የምርጫ ጋሪ በዳውንት ወረዳ የውሻ ሞት በፋኖዎች ክንድ ተበርክቶለታል።
የወረዳው ማህበረሰብ በፋኖዎች ቅፅበታዊ ጥቃት እጅጉን የተደሰተ ሲሆን የፋሽስቱን አንባገነናዊ ጭቆናን ያራገፉላቸው ፋኖዎችን እጅጉን አመስግነው ወደ ቀን ተቀን ስራቸው ተመልሰዋል። የአማራን ህዝብ አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በስብሰባ በማዳከም ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚቀሳቀሰው ራሱን ብልፅግና እያለ የሚጠራውና ከአረብ ኤሜሬትስ ተልዕኮን በመቀበል የጥፋት እንቅስቃሴዎንና ተላላኪ አመሉን ለመፈፀም 24 ሰዓት የሚሰራው ብልፅግና በአማራ የተባበረ ክንድ ተከሽፏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ106ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 9/2018 ዓ.ም
+2
ግንቦት 9/2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 7:15 በደብረ ማርቆስ ከተማ የቦምብ ጥቃት ሲፈፅም ሽመልስ ጌትነት፣ ታየ ወንድይፍራው፣ ቀናው ካሳ የተባሉ ሶስት የጠላት ወታደሮች 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
አነፍናፊው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ነሐሴ 30 ሆቴል ፊት ለፊት ከሌሊቱ 7:15 ሲንቀሳቀስ በነበረ ኮድ( 3)62415 መኪና ላይ ባደረገው የቦምብ ጥቃት 7 አድማ ብተና አባላት ህይወታቸው ሲያልፍ 9 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሁነው በወታደራዊ ካምፕ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሽመልስ ጌትነት፣ ታየ ወንድይፍራው እና ቀናው ካሳ የተባሉ የአድማ ብተና፣ የሚኒሻና የፖራ ኮማንዶ አባላት ከደብረ ማርቆስ፣ የጁቤና፣ አምበር ከተማ በመውጣት 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ !
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦር በሰርአቱ ወንበር አሰጠባቂ ላይ የተጠና ጥቃት መፈፀሙን ኮሩ አስታወቀ።
አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ወቀሎ ቀበሌ ካምብ ሰርቶ ህዝብን በምርጫና በማዳበሪያ ሰበብ እያሰቃየ የሚገኘው የፋሸስቱ አገዛዝ ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻ ላይ ከለሊቱ 6:00 ላይ ከፍለጦሩ የማያዳግም እርምጃ ወሰዷል።
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደጽዮን ኮር ራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የአርበኛ አሊ ሻለቃ ቃኝወችና ከክፍለጦሩ ሻለቆች በተውጣጡ የፋኖ ሰራዊት በተፈፀመ የለሊት ኦፕሬሽን የውሻ ሞት ለመሞት በወሰነው 2 የሚሊሻ ባንዳ ላይ የማያዳግም ርምጃ ሲወስድ 3 ቆሰለው ህክምና ላይ መሆናቸውን ኮሩ በግንባር መረጃው ገልጧል።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ተጠናክሮ በቀጠለው የአገዛዙ ሰራዊት ፍልሰት 1 የሚሊሻ አባል የአፄ አምደ ፅዮን ኮር 7ለ70 ክፍለጦርን ሲቀላቀል፣ ከፋኖ ጋር ባለው ግንኙነት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የነበረው የ104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባል የንጉስ ሣህለስላሴ ክፍለጦርን ተቀላቅሏል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 09/2018ዓ.ም
ከሞት የተረፈው የአገዛዙ መዋቅር በየቀኑ እየፈረሰ ይገኛል!
ግንቦት 9/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ የጠፉት አማሮች ተገኝተው ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ፋኖን ተቀላቅለዋል።
በዋድላ ወረዳ ኮን ከተማ ላይ የሚኒሻ መዋቅር እየፈራረሰ ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ የሚኒሻ አባል የነበሩ በርክተዋል። ሶስት የሚኒሻ አባል የነበሩ ጥምጥም ወጣቶች በዛሬው እለት የ22ኛ ክፍለ ጦር አባላቶችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ሶስት ክላሽኮ መሳሪያቸውን አንግበው የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በክፍለ ጦሯ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ወደ ህዝባቸው የተመለሱት የቀድሞቹ የሚኒሻ አባል የነበሩት ስለ ብልፅግና አስከፊና የጥፋት እንቅስቃሴ "በርካታ ጓድኞቻችንን ረሽኗቸዋል። ለርሸና ያበቃቸው ጉዳይ በፋኖ ስም ሌሊት ዘረፋና የአማራን ህዝብ እግልት ፈፅሙ ተብለው ትዛዝ ሲሰጣቸው እምቢኝ ህዝባችንንስ እንድህ አናደርግም።በማለታቸው ለርሸና አብቅቷቸዋል።" ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሶስት ቀን በፊት ሶስት ሚኒሾች ሲረሸኑ አምስቱ ሚኒሾች ደግሞ አምልጠው ጋይንት ከፋኖ ጋር ተቀላቅለዋል። ሲሉ ተናግረዋል።
በስተመጨረሻም "በአረቂ ለሚያልቅ ብር እና ስትሞትለትም የሰባት ሽህ ብር አህያ ከዚህ ጋር ሙቷል እያለ ለሚዘባበትልህ ስርዓት አትሙት። ወደ ወንድሞችህ ፋኖ ተቀላቀል። ይህ ስርዓት የአማራ ህዝብ ጥላት ነው። እኛም አማራዎች ነን። በአማራነታችን እንቁም። አንድ አማራዎች ነን። ለነ ሽመልስ አብደሳ፣ለአዳነች አበቤ ውስኪና ወንበር ሲባል ለምን እኛ አማራዎች እርስ በርሳችን እንገዳደል? ምንስ ልናተርፍ? በቃ እራሳችሁን አድኑ! ህዝባችሁን ከብልፅግና መዋቅር ውጡና ካሱት!" ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
እኛም ኑ አማራነታችንን ከምንም በላቀ እናስቀድም! የአብይ አህመድን የጥፋት እግሮች እንስበራቸው የዘወትር መልክታችን ነው።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ106ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!
ግንቦት 9/2018 ዓ.ም
የጭቆናው መዋቅር ሰለባ የነበሩ ወገኖች በይቅርታ ወደ ማህበረሰባቸው ተቀላቀሉ!
(ሚያዚያ 9/2018 ዓ.ም — አሻራ ሚዲያ)
የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በሰላም አስከባሪነት ስም ሲያገለግሉ የቆዩ አባላት የሥርዓቱን የጥፋት መንገድ በመረዳት ወደ ወገናቸው መመለሳቸውን ተከትሎ፣ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሐቤቴ አውራጃ ለሚገኘው ሕዝብ የይቅርታ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከጥንትም ጀምሮ አርቆ አሳቢነቱና ለወገኑ ያለው ሩኅሩኅነቱ የሚታወቀው የመርሐቤቴ ሕዝብ፣ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአሳምነው ዕዝ እና የናደው ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የቀረበለትን የይቅርታ ጥያቄ በታላቅ ክብርና ወንድማማችነት ተቀብሎታል።
ይህን ታሪካዊ ሒደት ተከትሎም፣ የሕዝባችንን የነጻነት ትግል በመረዳት ወደ ትክክለኛው መስመር የተመለሱት እነዚህ ወገኖች ሙሉ ነጻነታቸው ተከብሮላቸዋል። በመሆኑም ያለምንም ስጋት ወደ መደበኛው ማኅበራዊ ሕይወታቸው እንዲቀላቀሉና ከማኅበረሰቡ ጋር አብረው እንዲኖሩ ተደርጓል።
ይህም ክስተት የአማራ ሕዝብን የማይበገረውን የአንድነትና የወንድማማችነት እሴት በተግባር ያሳየ መሆኑን አርበኛ አንዳርጋቸው አሰፋ እና አበባው ፍስሀ ከቦታው በመገኘት ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል።
አሻራ ሚዲያ - የአይበገሬዎች ልሳን!
የጀግንነት ማህደር የዋልታ እና የማገሩ ስልጣኔ አርበኛ መከታው ማሞ፤
አማራ ማለት ለዚህች ውድ አገር ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ነው! ታሪክ የገመደው፣ ጀግንነት የወለደው ይህ ታላቅ ህዝብ፣ ለሀገረ መንግስቱ መመስረትና መጽናት የማይናወጥ አለት ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።
ከዳግማዊ አፄ ሚኒልክ መንገሻ፣ ከታላቋ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት... ታሪክ ደጋግሞ ከሚያነሳቸው የጀግኖች አውድማዎች መካከል የሸዋ መሬት ቀዳሚዋና ዋናዋ ነች። ይህች መሬት በአቀማመጧ አስደናሚ ናት ደመናን የሚቧጥጡ ተራራዎቿ፣ ቅዝቃዜያቸው አጥንት የሚሰረስር ብርዳማ ስፍራዎቿ፣ እና ታሪካዊ ሚስጥርን ያቀፉት ቆላማ ግዛቶቿ የጀግኖች መፈልፈያ እቶን ሆነው አገልግለዋል።
በዚሁ አስገራሚ መልክዓ ምድር በታላቁ ስምጥ ሸለቆ፣ በሸዋረቤት ዙሪያ ተፈጥሮ ካበቀለቻቸው እምቡጥ ጀግኖች መካከል ዛሬ የአንዱን ስም በወርቅ ቀለም እንድፅፍ አማራዊ ግዲታዬ ያስገድደኛል። እርሱ.የታላቁ የአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት የሆነው የድርጅታችን (የአፋብን) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ ነው!
እርበኛ መከታው ማሙ በንግግሩ መልካም፣ በአስተሳሰቡ እጅጉን ጥበበኛና አስተዋይ ሰው! ከመሆኑም በላይ የአርበኛው መከታው ማሙ ማንነት የሚገለጠው በቃላት ድርደር ብቻ አይደለም። የእርሱ መልካም ባህሪ፣ ለህዝቡ ያለው ተቆርቋሪነት፣ እና በጦር ሜዳ ላይ የሚያሳየው ስልታዊና አስደማሚ የሰራዊት እንቅስቃሴ እርሱ እውነተኛ፣ ባለማዕተብና ታማኝ የአማራ ልጅ መሆኑን በግልጽ ያሳብቃሉ።
እርሱ ለወገኑ ጋሻ፣ ለጠላት ደግሞ የማይሻገር የቁም ቅዠት ነው! በሸዋ ምድር የበቀለው ይሄ ጀግና፣ የአባቶቹን አደራ ተሸክሞ፣ የማንነትንና የነጻነትን ሰንደቅ አንግቦ በቁርጠኝነት እየተጓዘ ይገኛል።
ታሪክ ሁሌም ጀግኖቹን ያስታውሳል። የሸዋ መሬት ዛሬም እንደትላንቱ መከታዎችን ማፍራቷን ቀጥላለች! የአርበኛ መከታው ማሙ የጀግንነት ጉዞ ይቀጥላል! #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር!!
የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እርስበርሱ መታኮሱን ቀጥሏል‼️
አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በፋግታ ለኮማ ወረዳ አዲስ ቅዳም ከተማ ትናንት ማታ ግንቦት 7-9_2018 ዓ.ም የእናት ጡት ነካሹ አድማ ብተና እርስ በእርሱ ሲተኳኮስ በማምሸት ሌሊቱን ብዛት ያላቸዉ አባላቱ ፈንድተዉ ብሬን ጨምረዉ በመያዝ ወደ 44ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል።
በዚህ የተደናገጠዉ ካድሬ የቀረዉን ሀይል በመያዝ የተበተነዉን ጦር በየ ሰፈሩ ፍለጋ በመዉጣት ከከተማዋ ቅርብ እርቀት ከምትገኘዋ #አመሻ_ሽንኩሪ ቀበሌ _ዘርቲ_ጎጥ
አቶ #እስከዚያ_አበበ የተባለ የ55 አመት ከበርቴ አርሶ አደር የኮበለሉ አድማ ብተና አባላትን ከቤትህ ደብቀሃል በሚል ተልካሻ ምክንያት ከከተማዋ አጠገብ ከሚገኘዉ አዋባራ ዋሻ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ በመዉሰድ ረሽነዉታል።
ከዚህ በፊትም በዚሁ ሰፈር የአድማ ብተና አባላት ቤቱ ድረስ በመሄድ ዉድነህ ጓዴን ረሽነዉት መሔዳቸዉ አይዘነጋም።
በተመሳሳይ ሁኔታ ትናንት አንዲት #አሳየች_ሞላ የተባለች የ 19 አመት ወጣት ሴት ከሌሊቱ 5:00 ኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ አካላት አፍነዉ በወስድ አድራሻዋ እንዲጠፋ አድርገዋል።
እንላለን በማፈን፣ በመረሸን የሚፀና መንበር የሚቆም ትግል የለም ሲል የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
በደባራይ ግንባር ዘጠኙ ሲደመሰሱ ሰባቱ የአገዛዙ ብልፅግና ጦር አባላት ከባድ ጉዳት አስተናገዱ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 21ኛ ክፍለ ጦር ልዩ ዘመቻና ሁለተኛ ሻለቃ ቃኝዎች በጥምረት ላስታ ወረዳ ገነተ ማርያም መገንጠያ ደባራይ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ የነበረውን የአገዛዙ ጦር ከፊሉን በመደምሰስ ገሚሱን በማቁሰል ከአካባቢው እንዲፀዳ አድርገዋል።
ደባራይ ላይ መሽጎና ኬላ በማዘጋጀት የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የነበረው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ መብረቃዊ ኦፕሬሽን በመስራት ግንቦት 08 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧቱ አንድ ሰአት ጀምሮ ፊት ለፊት በመግጠም የክፍለ ጦሩ አሃዶች በጠላት ላይ ድል የተቀናጁ ሲሆን በውጊያው አምስት ሚሊሻ እና አራት የመከላከያ አባላት ሲደመሰሱ 11ንዱ ከባድ ቁስለኞች መሆናቸው ታውቋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ግንቦት 08/2018 ዓ/ም
+3
ሰበር!!
አራት /4/ የአገዛዙ 54ኛ ክ/ጦር 402ኛ ኮር 2ኛ ሪጅመንት አባል የነበሩ የሰራዊት አባላት በዛሬዉ ዕለት በቀን 08/09/2018 ዓ/ም ከጃንሱማ በመነሳት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ 305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር 52ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
እኒህ የሰራዊት አባላትም እንደገለጹት የሃገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ሲገባዉ አገዛዙ ግን ለፓለቲካ ጥቅም እና ስልጣን ማራዘሚያ እንደ መሣርያ በመጠቀም በአለም አቀፍ እውቅና እና ክብር ያለውን የመከላከያ ተቋም ክብር እንዲያጣ አድርጓል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን የወገናችን እና የአገራችንን ደህንነት ከውጭ ጠላት ለመጠበቅ እንጅ ራሣችን በራሣችን አጥፍተን እና ተጣፍተን ሀገራችን ለማፍረስ አላማ የለንም በሚል ዉሳኔ እንደመጡ ገልፀዋል።
አርበኛ አንደርግ ጫቅሉ!!
🌟የ77ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈጽማለች!!
{ግምቦት 08/09/2018 ዓ.ም}
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት መነሻው ከቡሬ ያደረገውን ጠላት መምጫ መንገዱ ላይ ደፈጣ በመያዝ አከርካሬውን በመምታት ሙት እና ቁስለኛውን አሸክመው በመጣበት እግሩ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።
ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ጓዙን ጠቅልሎ ከቡሬ ወደ ደረቋ ከተማ እንቅስቃሴ ያደረገው ጠላት ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ አንደኛ ሬጅመንት በከፈተችው ጥቃት 6 መከላከያዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ማድረጓን ሬጅመንቷ አስታውቃለች።
ከፍተኛ ጉዳትን እያስተናገደ የሚገኘው ከቡሬ የመጣውን ለማገዝ ከአጉት እንቅስቃሴ ቢያደርግም ከጥቃት አላዳናቸውም ስትል 1ኛ ሬጅመንት አክላ ገልጻለች።
✅የነገ ተስፋችን በእኛ እጅ ይፃፋል:- አርበኛ ዘመነ ካሴ ባውቄ💪
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
{ግምቦት 08/09/2018 ዓ.ም}
ቀን ግንቦት 07/2018 ዓም
ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች አሰመረቀ"
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በደማቅ አሰመርቋል። ዛሬ ይህን የምረቃ ፕሮግራም ስናካሂድ ጨፍጫፊው የአብይ ስርዓት በነፋስ መውጫ ከተማ የምርጫ ድጋፍ ሰልፍ በተለመደ የጭካኔ ክንዱ በዋቢ ድርጅት በር የረሸናቸውን አስከሬን እንዳይነሳ በመከልከል ላይ እያለ: ለወራት እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው የቆዩ የባጃጅ ሹፌሮችን በየቤታቸው ለድጋፍ በማስወጣት : የማንኛውም ንግድ ድርጅቶች በማዘጋት : ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ቢሮዎች ተዘግተው እንዲወጡ : በኑሮ ውድነት ዳሽቆ የሚገኘውን ማህበረሰብ እና ትናት ሳሊና ጎብጎብ ረሽነው የተረፋ ካህናትን እንዲሁም በግፋ የተገደሉባቸው ቤተሰቦች ጥቁር እንደለበሱ አስገድዶ በማወጣት ላይ እያለ ከከተማ በመውጣትም ወደ ፋኖ የቡድን መሳሪያዎችን በመተኮስ እንደለመደው እየወጣ እየገባ ከሚወሸቅበት ዋሻ ውሏል።
" ፅናት መሰረታችን ነው " የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አመራሮች ትናንት ለአማራ ህልውና ስንወጣ ነፃነት ለተገፋው አማራ ሀቀኛ እምነትና መተማመን ስለቻልን አብረውን ከጎን የነበሩ ወንድሞችን ስናጣ ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን የጀመሩትን በበላይነት ለማጠናቀቅ እንጅ ጀምረን ለማቋረጥ አለመሆኑን ሰራዊታችን እና ህዝባችን ሳይሆን ጠላቶቻችንም መስክረውታል ቁጥራችን: ድላችንና ትጥቃችን አበዛን እንጅ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
እናንተን አሰልጥነን በክህሎትና አስተሳሰብ አብቅተን ስናስመርቅ የአማራን የግፍ ፅዋ ለመሰበር አናንተን ለየፀና መሰረት አስቀምጠናል: የተፈተነው የከበርነውን የከበርነውን መሰረት : የፀናውን የማዕዘን ድንጋይ እናንተን በአላማ ስናንፅ ልናፍር ሳይሆን አምነን በኩራት ነው። ሞቱ የቀረበው ብልፅግና ከወላጅ አባቱ ኢህአዴግ ጎን ቅበሩኝ ያለው ከአፋፍ ጫፍ ሁኖ የሚናዘዘው የአማራን ህዝብ እንባ ብቻ ሳይሆን ደም ያፈሰሰው በርካታ ልቦችን የሰበረው ጊዜው ደርሶ በቅርብ ለዘላለም እንዲሰናበት ብአዴንም በሰላም አርፎ
በአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ ትዝታ በልብ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር የተሰጠው ቃለ መሀላ ፀንቶ ይኖራል።
# ድል ለአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
# ለራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ሻምበል ተስፋ ቃል አቀባይ
