uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 136
Obunachilar
+724 soatlar
+2087 kun
+1 20130 kun
Postlar arxiv
ጀብደኛው ሾፌር ዛሬ አመሻሽ በሸበል በረንታ ታሪክ ሰርቷል ። ተቅበዝባዡ የአብይ አህመድ ጦር ምሽቱን ሸበል በረንታ ላይ ከነተሽከርካሪው ካፈር ተቀላቅሏል ። ተርቦቹ የአባኮስትር በላይ ዘለቀ ልጆች ሸበል በረንታ ላይ በደፈጣ ቅልጥሙን ሰብረው እንደመለሱት መግለፃችን ይታወሳል። አመሻሹን ደግሞ አመራራቸውን ሲቀብሩ የዋሉት የአብይ አህመድ ሰራዊት አባላት ተሽከርካሪ አስገድደው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ አሽከርካሪው በወሰደው ድንቅ ውሳኔ ከነተሽከርካሪው በአፍጢማቸው ገልብጦ አምልጧል። በጠላት ላይ የደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት:- ➡ መኪናው ውስጥ የሞቱ ➡12 ➡ ሆስፒታል የሞቱ ➡1ሞርተር ተኳሽ እና 1 ሐኪም ➡ከባድ ቁስለኛ➡17 ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ➡ጠቅላላ ሟች ➡14 ሲሆኑ በህክምና ላይ እያሉ የሞቱት ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የውስጥ መረጃችን ያመለክታል። ድል ለጀግናው አማራ ድል ለጀግናው ፋኖ አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

@ዛሬ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሙ ብርኮ በተባለ ቦታ አፍብኃ ሚኒልክ እዝና በላይ እዝ ማለትም ላስታ አሳምነው ኮር ተፈራ ማሞ ክፍለጦርና ዋግሹም ብርጌድ ከበላይ እዝ አንደኛ ውባንተኮር ጉና ክፍለጦር በጋራ
@ዛሬ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሙ ብርኮ በተባለ ቦታ አፍብኃ ሚኒልክ እዝና በላይ እዝ ማለትም ላስታ አሳምነው ኮር ተፈራ ማሞ ክፍለጦርና ዋግሹም ብርጌድ ከበላይ እዝ አንደኛ ውባንተኮር ጉና ክፍለጦር በጋራ ታሪክ ሰርተዋል ከአይና ቡግና መነሻውን ያደረገው ወራሪ በነበልባሎቹ በሁለቱ ንስሮች ተቀጥቅጦ ተመልሱአል ሙትና ምርኮኛ አድርገውት ውለዋል ብሬን እና ክላሽ ሲታፈስ ውሎአል

በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። ሁሉም አማራ የሆነ ሁሉ ቻናሉን ጆይን ያላለ ጆይን በማድርግ ግሩፑን ደግሞ አንድስው ሁለት መቶ አማራ አድ በማድርግ የአንድነት አጋራችን አብርን እንስራ ለመላው አማራና ለትግል ደጋፊዎቻችን እንዲደርስ በአማራ ፋኖ ሰማዕታት ስም እጠይቃለሁ። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

#አስቸኳይ_መልዕክት‼️ ምዕራብ ጎጃም ጃቢጠናን ወረዳ በተለይም ማክሰኝን ዙሪያና አካባቢው ከለሊቱ 5 ጀምሮ የድሮን ቅኝት ስላለ የወገን ሀይልና ማህበረሰባችን ጥንቃቄ ያድርግ‼️ #ማሳሰቢያ ቅኝቱ በተ
#አስቸኳይ_መልዕክት‼️ ምዕራብ ጎጃም ጃቢጠናን ወረዳ በተለይም ማክሰኝን ዙሪያና አካባቢው ከለሊቱ 5 ጀምሮ የድሮን ቅኝት ስላለ የወገን ሀይልና ማህበረሰባችን ጥንቃቄ ያድርግ‼️ #ማሳሰቢያ ቅኝቱ በተጠቀሰው ቦታ ብቻ ተወስኖ ስለማይቀር ሁሉም በተጠንቀቅ ይሁን‼️

የአብይ ደናቁርት ወንበር አስጠባቂ ጡት ቆራጭ መከላከያ ኃይልና ከተረኛ ወታደር እሰክ #አመራሩ_በሜዳ_ቀርቷል‼️ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803ኛ ኮር የ61ኛ ክ/ጦር የሰው ኃይል ኃላፊ አስከሬን! ፋኖ ጠ
የአብይ ደናቁርት ወንበር አስጠባቂ ጡት ቆራጭ መከላከያ ኃይልና ከተረኛ ወታደር እሰክ #አመራሩ_በሜዳ_ቀርቷል‼️ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803ኛ ኮር የ61ኛ ክ/ጦር የሰው ኃይል ኃላፊ አስከሬን! ፋኖ ጠፍቷል እያሉ ቢደሰኩሩም ከተራ ወታደር እስከ አመራር በሜዳ ወድቀው የአሞራና የዱር አራዊት እየሆኑ ይገኛሉ💪💪💪💪💪💪 20/ዐ4/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ  ውሎ ___፩ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል ።     አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ 109ኛ ኮር  77ተኛ ክፍለጦር  ጡት ቆራጭ ጨፍጫፊውና አረመኔውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እንደቅጠል ሲያራግፈው ውሏል። በቀን 18/04/2018 ዓ.ም መነሻውን ከገነት አቦ ፣ከጂጋ እና ከፍኖተሰላም ያደረገው የጠላት ሀይል ማክሰኝን ላይ በ3 አቅጣጫ ዙ 23 ጨምሮ ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ለመግባት ቢሞክርም ክንደ ነበልባሉ የ77ኛ ክፍለጦር ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እሰከ 10:00 ሰአት  6ተኛ ሬጂመንት/ቃኝና መሀንዲስ / ፣3ተኛ ሬጂመንት፣1ኛ ሬጂመንት፣5ኛ ሬጅመንት እና ሌሎች የሬጅመንት አባላት በመቀናጀት የመጣውን ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ ሰራዊትን እያጨደ ሲከምረው ውሏል።   አማራን ከምድረገፅ አጠፋለሁ ብሎ ያቀደው ይህ አረመኔ ስረአት በክንደ ነበልባሎች የ77ኛ ክፍለጦር አናብስቶች ከጥዋቱ12:00-10:00 በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሻምበል አዛዡና መቶ መሪዎችን ጨምሮ  ከ40 በላይ የጠላትን ሀይል ደምስሰውታል።  ወደ አናብስቶቹ 77ኛ ክ/ጦር  ምሽግ ዘሎ የገባው የጠላት ሀይል መውጫ አጥቶ የድረሱልኝ ሲቃ ሲያሰማ ውሏል። ከበባ ውስጥ  የገባውን የጠላት ሀይል ለማስለቀቅ ከጅጋ ተጨማሪ ሀይል ወደ ማክሰኝን ለማስገባት ቢሞክርም በደፈጣ ስፔሻሊስቶች ሻለቃ 1 ቀደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን ጠላት ያሰበው ዕቅድ ሳይሳካለት ቀርቷል። የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው ጨፍጫፊው የጠላት ሀይል ግማሹን አስከሬን ቀብሮ ሌላውን ትቶ ጨለማውን ተገን አድርጎ በሦስት መኪና ቁስለኛውን ጭኖ ወደ ጅጋ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። በዛሬው ዕለት የአካባቢው ማህበረሰብ የጠላትን አስከሬን እያነሳ እየቀበረ ይገኛል።        -በዕለቱ ከ40 በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሷል        -ሦስት መኪና የጠላት ሀይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል        -በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ ተማርኳል የዕለቱ አውደውጊያ በክንደ ነበልባሎቹ በ77ኛ ክ/ጦር የበላይነት የተጠናቀቀ ሲሆን ማክሰኝን ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች። ___፪ የመከላከያ ኦፕሬተሩ እና የሞርተር ኦፒው ፋኖን ተቀላቅለዋል ደ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ሙሉ ጥቃቸውን በመያዝ ወደ  ፋኖን ተቀላቅለዋል። 1ኛ 10 አለቃ ሰለሞን አለምነው 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25 ክፍለ ጦር 6ኛ ሬጅመንት የሞርተር ኦፒ 2ኛ 10 አለቃ ደሳለኝ አባይ አፕሬተር 602ኛ ኮር  25ኛ ክፍለጦር  6ኛ ሬጅመንት ሲሆኑ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል።     ____፫ "ህግ የማስከበር እርምጃው እንደቀጠለ ነው"!! ➛የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ስር የነበሩ የድርጅቱን ወቅታዊ የአደረጃጀት የጦር ፕወዛ በማስመልከት #ቃልኪዳን_ሊቁ ከ64 ክፍለ ጦር በማፈንገጥ በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ ተቀምጠው የአካባቢው ማህበረሰብን የሚዘርፎ፣ ወጣት ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ፣ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ እና ማንቆርቆሪያ/አንስላል ቀበሌ የጭነት እና የህዝብ መኪኖችን ሹፊሮችን ተሳፋሪዎችን በማስቆም ለግል ጥቅማቸው እየዘረፉ የሚገኙ ግለሰቦችን በ64ኛ ክፍለ ጦር ህግ ማስከበር ዘመቻ በቁጥጥር ስር እያወሉ ይገኛሉ። ከእነዚህ የአፈንጋጭ ኃይሎች ውስጥ:- 1ኛ. ዘራፊ መልካሙ አየለ 2ኛ. ዘራፊ ማስተዋል አሠፋ 3ኛ. ዘራፊ ታዴ ዳምጤ የተባሉ ግለሰቦች በእነማይ ወረዳ ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ሲዘርፉ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ➛በእነማይ ወረዳ እድገት በአንድነት ቀበሌ ልዩ ቦታው የዳጓት ለአፈንጋጭ ኃይሉ መረጃ ይሰጥ የነበረ ግለሰቦች እና አፈንጋጮች በ64ኛ ክፍለ ጦር የህግ ማስከበር ዘመቻ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ውሏል ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ገብሬ ካሰቸው 2ኛ. ሸገው ላቃቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል። ➛በ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላትን የውሸት ትርክት በመስበክ የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ እና የተለያዩ ምክንያቶች በማስመልከት ወደ አፈንጋጩ ቡድን ገብተው የነበሩ ግለሰቦች ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ይሁን ጤነው እና 2ኛ. ፋኖ ሀብታሙ እንደግ አፈንጋጮችን በመታኮስ 64ኛ ክፍለ ጦር ጥሪ ተቀብሎ በሰላም እጅ ሰጥቷል። በ64ኛ ክፍለ ጦር የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ከጠላት ተልኮ በመቀበል የሚሰሩ ግለሰቦች በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍል አስገድደው ገንዘብ እንዲያግዝ በማድእግ እና አንዳንድ የፋኖ አባላት ቤተሰብ ለመጠየቅ እንደተንቀሳቀሱ የፋኖ አባላትን በአፈሙዝ በመደብደብ እና በማስገደድ የአፈንጋጭ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ጌቴ አሻግሬ 2ኛ. ፋኖ ከባዱ ሰናይ 3ኛ. ፋኖ ትዋቸው ዳኜ ሲሆኑ ትዋቸው ዳኜ የ64ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበር ቢሆንም እጁን በጥይት በመምታት ህክምና እንዳያገኝ አድርገውት በህክምና እጦት ምክንያት በአፈንጋጭ ቡድኑ እየተሰቃየ ይገኛል። ➛በሌላ መረጃ ከ64ኛ ክፍለ ጦር ከጠላት ተልዕኮ በመቀበል በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ መቀመጫቸው አርገው የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲያሰቃዩ ከነበሩት አፈንጋጮች ውስጥ:- 1ኛ. አብረሀም ፍቃዱ የተባለ ግለሰብ የአገዛዙን ተልኮ ተቀብለው በ64ኛ ክፍለ ጦሩ የቆዩ ቢሆንም የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ ምክኛት በማድርግ ከክፍለ ጦሩ በማፈገጥ ቆሰቆስ ከሚገኘው የአፈጋጭ ኃይል ጋር በመሆን የአገዛዙን ተልኮ ተቀብሎ ሲሰራ የቆዩ ቢሆንም ተልኮውን ጨርሶ የትመን 01 ቀበሌ ከሚገኘው የጠላት ኃይል መግባቱ ተረጋግጦል። ➛ከጠላት ተልኮ ተቀብለው በዝርፊያ የተሰማሩ በእነማይ ወረዳ ስር እየሱስ፣ የትመን፣ ዘብች እና አካባቢው ቀበሌ የአካባቢው ማህበረሰብ የሚዘርፍ ማህበረሰቡን የሚያንጋጥጡ ጋጥ ወጥ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና በቁጥጥር ስር የማዋል ዘመቻዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም

በምኒልክ ዕዝ እና በላይ ዕዝ ጥምረት 197 የአገዛዙ ሰራዊት የተደመሰሰበትና ከ85 በላይ የቆሰለበት እንዲሁም ሁለት ብሬን እና 43 ክላሽ የተማረከበት ድል ተጎናፀፉ:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በአርበኛ አምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ የሚመራው ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ እንዲሁም አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር የተውጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ አብዛሀኛው የጠላት ኃይል የተደመሰሰበትና ይዞት የመጣው የጦር መሳሪያ ምርኮ የሆነበት ፋኖዎች ታላቅ ድል ያስመዘገቡበት አውደ ውጊያ ተካሂዷል። ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል በሻምበል ጫላ የሚመራው 61ኛ ክፍለ ጦር መነሻውን ከቡግና ወረዳ አይና ከተማ ሀሙሲት አድርጎ ብርኮ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በዓል በሚከበርበት በአራት አቅጣጫ ማለትም በብርኮ ገብርኤል አቅጣጫ፣በጤና ጣቢያው አቅጣጫ፣በጭቃው አቅጣጫ እና በብርኮ ኪዳነ ምህረት አቅጣጫ ለማጥቃት አስቦ ተኩስ የጀመረው የአገዛዙ ኃይል ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር በመጣበት ላይመለስ ተደምስሷል። በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት በሜካናይዝድ የታገዘ አንድ ዙ-23፣ሁለት ሞርታር፣ሦስት ዲሽቃና ብዛት ያለው ብሬንና ስናይፐር ታግዞ የገጠመ ሲሆን የጦር ጠበብቶቹ ጠላትን በመጣበት ቋንቋ አናግረው ጄኔራል አስታጥቄ የላከውን ተረካክበው ከንፍሮ ጥሬ እንዲሉ የተረፈው ወደ መጣበት እየተዝረከረከ ተመልሷል። ጠላት በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደ ሲሆን 197 ጠላት የ61ኛ ክፍለ ጦር የሰው ኃይልን ጨምሮ ሲደመሰስ፣85 ቁስለኛ እና ሰባት ተማርኳል፤ በተጨማሪም ሁለት ብሬን፣43 ክላሽ፣84 ወታደራዊ ሻንጣ፣2850 የብሬን ተተኳሽ፣2200 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል። ለአማራ ህዝብና ለንፁሃን የማይጨነቀውና የጦር ወንጀል እየሰራ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በየ ዓመቱ ታህሳስ 29 የሚከበረውን የቅዱስ ላሊበላ የልደት ቀንና የገና በዓል ንግስን ለማክበር እየተጓዙ የነበሩ 12 ንፁሃንን፣በሞርታር ቅንቡላ ሁለት ንፁሃንን፣ቤት ለቤት በመዞር የፋኖ መረጃ ናችሁ በሚል ሁለት እናቶችን ሲረሽን፣ ዘጠኝ ንፁሃንን አቁስሏል፤ ብርኮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመድፍ ቅምቡላ አፍርሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም

⚫️#ከአፋብኃ_የተሰጠ_የሀዘን_መግለጫ‼️ "አንተ ወጥተህ ወርደህ ያስጀመርከውን የአንድነት ትልም በተግባር በመጨረስ ራዕይህን እውን እናደርጋለን" ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ የሀዘን መግለጫ! ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም በሸዋ ክፍለ-ሀገር ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ልዩ ስሙ ራሳ በተባለ አካባቢ አገዛዙ በሰነዘረው የድሮን ጥቃት አማራን አንድ ለማድረግ በሸዋ ፣በጎጃም ፣በወሎ እና በጎንደር እድሜ ሳይገድባቸውና ሳይታክቱ ፤ሲንከራተቱና ሲደክሙ የነበሩትን አርበኛ ተስፋዬ መካሻን ጨምሮ ሌሎች ንፁሀን አማሮች ለህልፈት ዳርጓል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "አማራው አንድ ይሆናል' በሚል ከፍተኛ ሽብር ውስጥ የገባው አሸባሪው የብልፅግና ስብስብ "አንድነቱን ያደናቅፍልኛል'' በሚል የዲጅታል ሚድያ መንጋውን ቢያሰማራም እቅዱ በተደጋጋሚ እየከሸፈ ይገኛል። በዚህና መሰል ክስተት መደናገጥ ውስጥ የገባው ይህ ሀገር አውዳሚ ስብስብ የዘፈቀደ የድሮን ጥቃት በመሰንዘር እና የተለያየ አጀንዳ በመስጠት ልዩነቱን ለማስፈት እየጣረ ቢሆንም የተፈፀመውን ልብ ሰባሪ ድርጊት እንደተጨማሪ እድል በመጠቀም አርበኛ ተስፋዬ መካሻ የጀመረውን የአንድነት ውጥን በማሳካት ራዕዩን እውን በማድረግ የምንክሰው ይሆናል። አርበኛ ተስፋዬ መካሻ ሀብተወልድ አርበኛ ብቻ ሳይሆኑ አባት፣ አስታራቂ የአንድነት መንገድም አንድነትም ናቸው፡፡ የእኛ አባቶች ባስቀመጡልን ታሪክ ብቻ ሳይሆን በኖሩት ታሪክ ያቆዩዋትን ሐገር ዳግም ከገባችበት የቁልቁለት ጉዞ አቅንተን በልዕልና እንድትኖር በርካታ ወንድሞቻችን አጥተን ህልውናችንን ከአለት በጠነከረ መሰረት ላይ እንገነባዋለን። የጀመርከው አንድነት መሠረት ተመስርቶ አይተኸዋል፤ እንገነባዋለን። ጠላት ሺህ ጊዜ ቢለፋ፤ ሺህ ጊዜ ቢጥር ታሪካችሁ የትም ወድቆ አይቀርም። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ©የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም 20/ዐ4/2018 ዓም

በጀግው ፋኖ የተማረከውን የመከላከያ አባላትና ወንጀለኛ እስረኞችን ያነጣጠረ የድሮን ድብደባ ማድረጉን ተያይዞታል ። ፋኖ የሚማርከውን የመከላከያ አባላት አለም አቀፍ ህግን በጠበቀ መልኩ ምርኮኛ አድር
+3
በጀግው ፋኖ የተማረከውን የመከላከያ አባላትና ወንጀለኛ እስረኞችን ያነጣጠረ የድሮን ድብደባ ማድረጉን ተያይዞታል ። ፋኖ የሚማርከውን የመከላከያ አባላት አለም አቀፍ ህግን በጠበቀ መልኩ ምርኮኛ አድርጎ ሲንከባከብ የቆየ ቢሆንም አገዛዙ ምርኮኛ የለብኝም ለማለት ይመቸው ዘንድ በአራቱም ግዛቶች ምርኮኞቹን በድሮን ሲ*ጨ*ፈጭ*ፍ ከርሟል !! ዛሬም የሆነው ይህ ነው የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የብልፅግናው ጦር በሸዋ እራሳ ከ25 በላይ ምርኮኞችንና እስረኞችን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎችን በርካታ ንፁኃንን 4 ጊዜ በጣለው የድሮን ቅንቡላ ጨፍጭፏል ። የአማራ ፋኖ በሁሉም ግንባሮች እራሱን ጠብቆ አውደ ውጊያውን እያደረገ ቢሆንም ፋኖን በድሮን ለመ*ጨ*ፍጨ*ፍ ምቹ ሁኔታን ማግኘት ያልቻለው የአብይ አህመድ መንግስት ያገኘውን ንፁሃንና ተቋማትን በድሮን እያወደመ ይገኛል ።

🔥#ደህንነቱ_በቁጥጥር_ስር_ዋለ‼️ የስርዓቱ ታማኝ ዘብ ከሆነው መከላከያ በመረጃና ደህንነት ስራ የተሰማራው ደህንነት በፋኖ ቁጥጥር ስር ዋለ‼️ አበበ አዛናው የተባለው የ74ኛ ክ/ጦር አባሉ  በመረጃነት ልዩ ስልጠና ተሰጥቶት በተለያዩ ቦታዎች ሲሰራ የቆየ ሲሆን በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ በመቄት የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እና በደቡብ ጎንደር ጋይንት ጨጨሆ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች ቅንጅት በደብረዘቢጥ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል።  የመረጃ አቅሙ እያደገ የመጣው የቀጠናው የፋኖ ኃይል በክትትል ይዞ ባደረገው ማጣራት ባንዳው የመከላከያ መረጃና ደህንነት ሰው የሆነው አበበ አዛናው ፋኖን እና የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ስራ መሰማራቱን ገልጾ ስርዓቱ በአማራ ሕዝብ ላይ ለሚያደርሰው ሁለተናዊ ግፍ  ተባባሪ ነበርኩም ብሏል። በሌላ በኩል በእጃችን በርካታ የአገዛዙ  ወንበር አስጠባቂ አካላትን ይዘናል ያለው በቀጠናው የተቋቋመው የጋራ ግብረኃይል  የኦሮሙማውን ስርዓት ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት በብቁ ቁመና ላይ እንገኛለን ያለ ሲሆን አሁንም በባንዳነት የተሰማራችሁ የአገዛዙ ፈረሶች ልብ ግዙ ሲል አሳስቧል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 20/ዐ4/2018 ዓ.ም

ዛቻ እና ማስፈራራት '' እርዳታ ለከለከለው አበቦክር ወይስ እርዳታ ላሰባሰበው ታኩር'' ስራ መስራት አልቻልኩም ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብኝ ነው ቲክቶከር ታኩር የላከው አሳዛኝ መልዕክት የደሴው ቲክቶከር ታኩር ሰሞኑን አግማስ ኢትዮጵያ (Agmas Ethiopia Charity organization) በሚል ለደብረ ብረሃን ተፈናቃዮች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች የገቢ ማሰባሰብ እና የለግሱ ጥሪ ሲያስተላልፍ የነበረ ሲሆን የሚታወስ ነው። እናም ታኩር በመልዕክቱ ምንም በማላውቀው ለተቸገሩ ወገኖች እንድረስ በሚል ከሰዎች ጋር በጋራ በመሆን ተፈናቃዮች ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ የሰበአዊ ድጋፍ ለማድረግ እና የበኩሌን ለመወጣም በሞከርኩ ይህን በጎ ተግባር ብየ ያሰብኩትን ስራ ወደ ፓለቲካ ወስደው ስራ ባታየ ድረስ በመምጣት ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረሱብኝ ነው እና ህዝብ ይወቅልኝ ዛቻው በወርቁ አይተነው በኩል ያለው ነው፣ በማላውቀው እና ባልዋልኩበት ከሱ ጋር እንደት ግንኙነት ኖሮህ ነው ይህን ያክል ገንዘብ ሊረዳ እና ለግልህ ጭምር ስጦታ ሊሰጥህ ቻላ በማለት ብዙ መልዕክቶች እና ማስፈራሪያዎች መተውብኛል፤ በዚህ ከቀጠለም ለህይወቴም ስለሚያሰጋኝ ስራ ቦታየን ለቅቄ ወደ ትውልድ ቦታየ ወሎ ደሴ ለመሄድም እያሰብኩ ነው በማለት የሚያሳዝን መልዕክት አስተላልፏል። ይህን ህፃን ልጅ በማያውቀው ፓለቲካ ውስጥ ባትከቱት እና ድሃ እናቱን ሰርቶ ቢረዳ የሚመለከተው አካል ቢረዳው እና ይህን አይነት ፀያፍ ተገባር የሚያደርጉትም ከድርጊታቸው ቢቆጠቡ እንላለን።

ትዉስታ ፀፀት⁉️

የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ እርስ በረዕሱ በመታኮስ ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል። ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ እና ሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱውኃ ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚ
+1
የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ እርስ በረዕሱ በመታኮስ ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል። ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ እና ሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱውኃ ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ የ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ ከባላት ቢቸና ከተማ ሰረገው ገብተዋል በሚል ፍረሀት እና ቅዥት ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም እርስ በእርሱ ሲታኮስ አድሯል። በእርስ በረስ ተኩሱ:- 1ኛ. ባንዳ እግዜሩ የጎንቻ ተወላጅ የሚኒሻ ስምሪት ኃላፊ ተወግዷል 2ኛ. ቢተዉ ጌታነህ ቢቸና ከተማ 02 ቀበሌ ፖሊስ 3ኛ. ሚሊሻ ተሬ ጋሪ የሚገፋ 4ኛ. ሚሊሻ አያልሰው ደሱ ሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ በእርስ በረስ ውጊያ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

#ትግል #በማብቃት #ይጠራል! በትግል #ዑደት አዳዲስ አሰራሮች ይወለዳሉ፣ ይተገበራሉም። #ኃይል ይበቃል፤ ሲበቃ ይጠራል። #ለውጥን ለመቀበል ዝግጁ ያልሆነው ይሾልካል። ለበርካታ ዓመታት ዋጋ የተከፈለበት ትግል #በሾለኩት #ግለሰቦች ሳይሆን #በተሸከሙት #majorities ይወሰናል። ማብቃት #በአስተሳሰብ ለውጥ፤ ማብቃት #በመርሐዊ ጉዞ፤ ማብቃት #በሳይንሳዊና #አካባቢያዊ ግንዛቤዎች ይገለፃል። በዚህ ትውልድ ውስጥ #የአማራ ፋኖ ሊገመት የማይችል ፈጣን የአደረጃጀት ዕድገት ያመጣ ቢሆንም ቅሉ ወደ አንድ ለመሸከፍና ተቋማዊ ለማድረግ ጊዜያትን እንደወሰደ ይታወቃል። ይህ ደግሞ ልክ እንዳለፈው ታሪካችን የድል-አጥቢያ አርበኞች የህዝባችንን ትግል እንዳይነጥቁን ማስተዋል እና እርጋታ የተሞላበት መስዋዕትነት ተብሎ ቢመዘገብ ስህተት አይኖረውም። ወደ ጹሑፌ ዋና ነጥብ ልመለስና #የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና/ በላይ ዘለቀ ዕዝ በጥልቅ #ማብቃት፤ የማጥራት ዘመቻው ለህዝባችን በርካታ አዳዲስ ለውጦችን ይዞ መጥቷል። ከእነዚህም ውስጥ #ወንበዴና #ዘራፊን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ጥልቅ ማብቃትና ማጥራት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! ወደ ፊት ብቻ! @የአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ የጥናት እና ምርምር መምሪያ አላፊ አርበኛ እና ደራሲ Anteneh Dires !!

፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ "ህዝቤን ለሚጨፈጭፈው ሰራዊት አባል ሁኘ የወገኔን እልቂት ማየት አሞኛል" ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም በመከላከያ ሰራዊት የሪፐብሊካን ኃይል ሜንቴናስ  መምሪያ ቡድን መሪ እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ automotive engineering የድግሪ ምሩቅ፣ በወታደራዊ ክፍል የ25ኛ ክ/ጦር አባልና በውትድርና አለም ለ14 ዓመት በማገልገል የእረጅም አመት ልምድ ያለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅሏል። የአረመኔው ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አውጆ ከተንቀሳቀሰ ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከጀነራል  እስከ ተራ እግረኛ ወታደር ድረስ በእየጊዜው እየከዱ ትግሉን የተቀላቀሉ ሲሆን ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ ከሪፐብሊካን ኃይል ሜንቴናስ መምሪያ በመውጣት ለአማራ ህዝብ ነፃነት የሚዋደቀውን የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅሏል። የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት ሀገራዊ ተልዕኮ በተቃራኒው በእራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት ኢትዮጵያን ለመበታተን ቆርጦ ተነስቷል ያለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ ሰራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ይልቅ በመላ ሀገሪቱ ሰፈር ለሰፈር እየዞረ ህዝብን መጨፍጨፍና መግደል ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎታል ሲል ተናግሯል። ከተራ አባል እስከ ከፍተኛ የጦር አመራሮች በአንድ ብሔር የበላይነት የተቋቋመው የመከላከያ ሰራዊት ለግለሰቦች ስልጣን እና የብልፅግና ዘብ ሁኖ ከመቆም ያለፈ አላማውን የዘነጋ የኢትዮጽያን ህዝብ ባገኘበት ሁሉ የሚገድል የሚያሳድና የሚዘርፍ ወንበዴ ቡድን እየሆነ መምጣቱን አክሎ ገልጿል። ከ5 አመታት በፊት የነበረው የሰራዊቱ አሰላለፍ ተቀይሮ በየ ሰፈሩ ምሽግ ቆፍሮ ውሎ የሚያድረው የሰራዊት አባላቱ በግዳጅ እየታፈሰ ሰልጥኖ የተመረቀና የተሰለፈለትን አላማ ጠንቅቆ የማያውቅ በመሆኑ በህዝብ ላይ እያደረ ያለው እልቂት በኢትዮጽያ ታሪክ ተፈፅሞ የማያውቅ ነው ሲል ሰራዊቱ ህዝብ ጠል እንዲሆ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አመላክቷል። የአማራን ህዝብ በኃይል ለማንበርከክና መንግስታዊ የዘ ፍጅትን ተቀብሎ በሙሉ ኃይሉ ጭፍጨፋ እያደረገ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሙሉ ሰራዊቱን በክልሉ አስገብቶ ከድሮን እስከ እግረኛ ሰራዊት እያደረሰ ያለው የዘር ጭፍጨፋ በወገኔ ላይ ከፍተኛ እልቂት ተፈፅሟል ያለ ሲሆን ህዝቤን ለሚገድለው ሰራዊት አባል ሁኘ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እረፍት ስለነሳኝ ከወንድሞቸ ጋር ለመታገል 206ኛ ኮርን ከአዲስ አበባ መጥቸ ተቀላቅያለሁ ብሏል። "ከራስ በፊት ለህዝብ" የሚለው የተቋሙ እሴት ተንዶ ሰራዊቱ ህፃናትን፣ሴቶችንና እናቶችን በመድፈር፣ንፁሀንን በመግደል እና በመረሸን፣የወንድን ልጅ ብልት፣የሴትን ልጅ ጡት በመቁረጥ የራሱን ህዝብ በማዋረድ እጅግ አረመኒያዊ ተግባሩን ያለ እርህራሔ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል። የአማራ ህዝብ በፋኖነት ተደራጅቶ ሊያጠፋው የመጣውን ኃይል መታገል ፍትሐዊ ነው የሚለው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የመከላከያ ሰራዊት በሁሉም የኢትዮጽያ ህዝብ የተጠላ ህዝባዊ ድጋፍ የሌለው ከህዝብ የተነጠለ ኃይል መሆኑን በአይኔ ተመልክቻለው ያለ ሲሆን የአማራ ህዝብ ለመከላከያ አይደለም ድጋፍ ለመስጠት ይቅርና የሰራዊቱን ዩኒፎርም ማየት እንደሚጠየፍ ጠቁሟል። በመጨረሻም ትግሉን ከተቀላቀለ ቀናትን ያሳለፈው ፻ አለቃ ደስ ይበለው ገድፍ የፋኖ ሰራዊት በአጭር ጊዚያት ያስመዘገበው ድል ፣ የአላማ ጥናት፣ የትጥቅ ሁኔታ ፣ ጠንካራ አደረጃጀትና የማይቋረጥ የህዝብ ድጋፍ ያለው መሆኑ እንዳስደነቀው ጠቁሞ የመከላከያ ሰራዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በሻለቃ ሊኖረው የሚገባ 480 ያላነሰ የሰው ኃይል በሚደርስበት ምት እና የሰራዊት ኩብለላ ወደ 180 የሰው ኃይል በማሽቆልቆል እየተበታተነ መምጣቱን አክሎ ገልጿል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት