uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Kanalga Telegram’da o‘tish

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

Ko'proq ko'rsatish
4 436
Obunachilar
-324 soatlar
-357 kun
-8630 kun
Postlar arxiv
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ወንድምና እህቶቻችን፦ በቅድሚያ ለዚህ ላበቃችሁ አምላካችን አላህ ምስጋና ሁሉ ይገባው ፤  እኛን በመቀላቀላችሁ እጅግ ደስተኞች ነን።  ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አዲስ እህትና ወንድሞቻችንን ለመቀበል ዝግጅታችንን እያደረግን እናንተን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፤ ማንኛውንም information ለማግኘት እነዚን የጀመዓ አባላት ያነጋግሩ::   1.አሕማድ       ☎️ 0917579730             0717579730   2.ዑማር ጀማል       ☎️ 0923893759   3.መንሱር አወል       ☎️ 0943590777         ወይም በ Telegram @wkumuslimsbot አዲስ የምትገቡ እህቶች የሴት ተወካዮችን በነዚህ ወንድሞች በኩል ማግኘት ትችላላቹ ! ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ https://t.me/EHEMSU

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በ2018 ዓ.ል አዲስ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2017 ዓ.ል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ስንድቱን ጨርሶ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው:: ስትመጡ የሚቀበሏቹ ወንድሞች እና እህቶች ማንኛውንም አይነት ትብብር የሚያደርጉላችሁ ይሆናል:: በምትመጡ ሰዓት ከዚህ በታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል የሚያስፍልጋቹን ትብብሮች  ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን:: • ፉርቃን ጀሚል  - 0968278025 • ሰለሃዲን ሙዘሚል-0983048814 • ጀማል አህመድ - 0909282436 • ፉአድ ከድር - 0921053417 • ኢብራሂም ጀማል-0976710967 🔴የእህቶችን ስልክ ለማግኘት ወንድሞች ጋር በዚህ 👉 0968278025 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ :: © DDUMSJ https://t.me/EHEMSU

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 2018 አመት አዲስ ገቢ  እና በሪሜዲያል ፕሮግራም ለተመደባቹሁ ሙስሊም  ተማሪዎች  በሙሉ ወደ ዩንቨርስቲ ስትመጡ  በሚዛን ቴፒ  ሙስሊም ተማሪዎች  ጀመዓ አቀባበል ስለሚደረግላችሁ፣ ስለዚህ ለማንኛውም እርዳታ እነዚህን ስልኮች መደወል ትችላላችሁ። Mizan-Tepi University 2018 Freshman and Remedial program for all Muslim students who have been assigned to the university — you will be welcomed by the Mizan-Tepi University Muslim Students Jama’a, so you can call these phone numbers for any help you need. 📞 +251 941 400 147 – Muhammad Asrar 📞 092 263 8097 – Abdurahmen 📞 096 390 6763- Masud Mizan-Tepi University Muslim Students Jama’a https://t.me/EHEMSU

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ወንድምና እህቶቻችን፦ በቅድሚያ ለዚህ ላበቃችሁ አምላካችን አላህ ምስጋና ሁሉ ለሱ የተገባ ይሁን እያልን፤  እኛን በመቀላቀላችሁ እጅግ ደስተኞች ነን።  ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመአ (JUMJ) አዲስ እህትና ወንድሞቻችንን ለመቀበል ዝግጅታችንን ጨርሰን እናንተን በመጠበቅ ላይ እንገኛለን፤ ማንኛውንም information ለማግኘት እነዚህን የተመደቡ የጀመአ አባላቶችን Contact ማድረግ ትችላላችሁ:: ዋናው ግቢ (Main Campus) 1. ሙሐመድአሚን አማኖ     ☎️ +251961973861 2. ኢምራን ሙደሲር     ☎️ +251913335647 ቴክኖሎጂ ካምፓስ (JIT) 1. ሰይድ መሐመድ     ☎️ 0994103863 2. ሙባረክ ሁሴን     ☎️ +251976558719 ግብርና ካምፓስ (Agri-Campus) 1. ረመዳን     ☎️ 0977235953 2. ዐብዱረዛቅ     ☎️ +251970248251 3. ሽኩሪ     ☎️ 0948573198 አዲስ የምትገቡ እህቶች የሴት ተወካዮችን በነዚህ ወንድሞች በኩል ማግኘት ትችላላቹ ! ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመአህ (JUMJ) https://t.me/EHEMSU

አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለደረሳችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች:- የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች በኢስላማዊ እህት ወንድማማችነት አቅፎ እና ደግፎ ለ
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለደረሳችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች:- የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች በኢስላማዊ እህት ወንድማማችነት አቅፎ እና ደግፎ ለመቀበል ዝግጅቱን ጨርሷል:: ከመረጃዎች ጀምሮ የሚያስፈልጋችሁን ማንኛውም ነገሮች ከላይ በምስሉ ላይ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች መጠየቅ ትችላላችሁ

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በትላንትናው እለት የጁምዓ ሰላት ሰዓት እንዲስተካከል ለዩኒቨርሲቲው አሳሰበ ። ደብዳቤው በዋናነት ለዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረ
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በትላንትናው እለት የጁምዓ ሰላት ሰዓት እንዲስተካከል ለዩኒቨርሲቲው አሳሰበ ።   ደብዳቤው  በዋናነት ለዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፤ በግልባጭ ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ለተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ባስገባው ደብዳቤ የሐገራችን መንግስት ሙስሊም ሰራተኞች የጁምአ ሰላትን እንዲሳተፉ ለማድረግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አርብ ከ 05፡30 እስከ 07፡30 እንዲዘጉ መመሪያ ያወጣና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የዩንቨርስቲው አመራሮች ለመመሪያው መተግበር ቁርጠኛ መሆናቸው የገለጹ ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በውጤታማነት አለመተግበሩን ጠቅሷል።    የትምህርት ዘመኑ እየተጀመረ በመሆኑ የተማሪዎች ህብረት እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉም የአካዳሚክ መርሃ ግብሮች የጁሙዓ የሰላት ጊዜን በሚመለከት የመንግስት  መመሪያዎች መተግበራቸውን እንዲከታተሉና ስህተቶችንም እንዲያርሙ አጥብቆ አሳስቧል። የህብረቱ ተወካዮች ከተማሪዎች ህብረት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የተማሪዎች ህብረትም ጥያቄው ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ አፈጻጸሙን እንድሚከታተል ገልጿል። ዩኒቨርሲቲውም በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ከሳምንት በኋላ ውሳኔ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሙስሊም ተማሪዎች:-   የASTU ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ መረጃ ከመስጠት ጀምሮ በአግባቡ የሚቀበሏችሁንና የሚያስተናግዷችሁን ሙስሊም እህት ወንድሞቻችሁን አዘጋጅቷል::    ♢ 0979509258 ••• ሰለሐዲን አብደላህ    ♢ 0941232826 ••• ሙሐመድአሚን ጀማል ለእህቶች:- +251965164385 እህቶች ከላይ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮችም ጭምር በእህቶች በኩል ያሉ የጀመዓው አስተባባሪዎችን አድራሻ ማግኘት እንደምትችሉ ጀመዓው አሳውቋል:: https://t.me/EHEMSU

ለAASTU (አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች:-   በመጀመሪያ ለዚህ ያበቃችሁን አምላካችንን አላህ እያመሰገንን በሚከተሉት አድራሻዎች ስለ ዩኒቨርሲቲው: ጀመዓው እና አጠቃላይ ሁኔታዎች መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን::      ♢ አብዱሰላም ሁሴን ---  0979037273      ♢ ፋሩቅ ባህሩ --- 0928988230      ♢ አይመን ሁሴን --- 0938807462      ♢ ሳሊም አሕመድ --- 0986164265 :- በእህቶች በኩል ያሉ የጀመዓውን ተወካዮች ስልክ ቁጥር ከላይ ከተጠቀሱት ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ:: አላህ ፍሬያማ እና ራሳችሁን ጠቅማችሁ ኡማውን የምታገለግሉበትን የዩኒቨርሲቲ ሕይዎት ይወፍቃችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው:: https://t.me/EHEMSU

ለአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:- በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን :: የ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን : 👉AMU Muslim students union         📞 0950805051 👉 Main campus      📞Amir :-0963764285 Andurazaq.   shamsu     📞V. Amir:-0967348340  Osama Ali 👉Chamo campus     📞Amir :-  0940020497 abdela ferej     📞V. Amir:-0907568300 Awol mohammed 👉 Sawla campus 📞Amir :- 0988401854 Umar Mokriya 👉Abaya campus     📞Amir:- 0963638759 Mohammed sa'id... 👉 Kulfo campus      📞Amir :-0944450840.  Hayatu.... 👉Nechsar campus         📞 Amir :- 0915273321 Mohammed Adem ወደ ግቢ የምትቀላቀሉ እህቶች የሴት ተወካዮችን በነዚህ ወንድሞች በኩል ማግኘት ትችላላቹ አርባምንጭ ዩንቨርስቲ የሞሉ  ተማሪዎች  ቀድመው መረጃ እንዲያገዩ በተለያዩ ግሩፖች ሼር እናድርግ https://t.me/amumsu1

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:- በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን :: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::      ☎️ AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252 Main and FBE Campus ☎️ አብዱረሂም አሚን           ስልክ ፦ +251995477358 ☎️ አሊፍ ሀጂ        ስልክ ፦ 0955942642 CTBE (AAiT)  (5 Kilo) Campus ☎️ማህፉዝ ነጋሽ - 5 kilo - 0996220264 4 Kilo Campus ☎️ ዘይድ ሳዲቅ - 4kilo - +251992546811 ☎️ መስዑድ አሊ -4 kilo  +251968645684 Sefere Selam Campus ☎️ አብዱረህማን ወሊዩ -sefere selam +251925025478 ☎️Bedhaso -sefere selam +251988358715 Ldeta Campus ☎️ Yusuf Hamid           ስልክ ፦ 0907645390 ☎️ Dawud Sultan        ስልክ ፦ 0951023812 ወደ ግቢ የምትቀላቀሉ እህቶች የሴት ተወካዮችን በነዚህ ወንድሞች በኩል ማግኘት እንደምትችሉ ለማሳወቅ  እንወዳለን። https://t.me/aaumsu

ከጁምዓ ቀን የስራ ሰዓት ጋር ተያይዞ ያለው አዋጅ በዚህ ዶክመንት ውስጥ ይገኛል:: በዶክመንቱ ገፅ 86 እና 87 ላይ እንደተቀመጠው አዋጁ ጁምዓ ቀን የስራ ሰዓት ከጧት እስከ 5:30 ከሰዓት ደግሞ ከ8:00 ጀምሮ እንደሆነ ይደነግጋል:: @MohammadamminKassaw

ከAAUMSU ይህንን እንደ ሞዴል ተጠቀሙ:: ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ሆናችሁ ካምፓሶች or ት/ቤቶች ከጁምዓ ቀን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ጋር ተያይዞ ያለውን የሰዓት ስህተት አስተካክሉ:: በሕጉ መሠረት
ከAAUMSU ይህንን እንደ ሞዴል ተጠቀሙ:: ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ሆናችሁ ካምፓሶች or ት/ቤቶች ከጁምዓ ቀን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ጋር ተያይዞ ያለውን የሰዓት ስህተት አስተካክሉ:: በሕጉ መሠረት ጁምዓ ቀን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ከጧት እስከ 5:30 ከሰዓት ደግሞ ከ8:00 ጀምሮ ነው:: ከ5:30 እስከ 8:00 ባለው ውስጥ ትምህርት የሚሰጡት ከሕግ እና መመሪያ ውጪ ነው:: ይህንን ማስተካከል ደግሞ የራስን መብት ከማስከበር ነው:: :- ይህ ደግሞ መሆን ያለበት ነገሩ ሁሉ ካለፈ ቡሃላ ሳይሆን ከአሁኑ ትምህርት ሳይጀመር ነው:: @MohammadamminKassaw

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዩኒቨርሲቲው በነጭ ሳር ካምፓስ ኒቃቢስት ተማሪዎችን "ኒቃብ ለብሳችሁ ግቢ መግባትም ሆነ ዶርሚተሪ መያዝ አትችሉም!" ማለቱን ተከትሎ ለዩኒቨርሲቲው ፕ
+1
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዩኒቨርሲቲው በነጭ ሳር ካምፓስ ኒቃቢስት ተማሪዎችን "ኒቃብ ለብሳችሁ ግቢ መግባትም ሆነ ዶርሚተሪ መያዝ አትችሉም!" ማለቱን ተከትሎ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ጥያቄውን አቅርቧል:: መሠል የመብት ጥሰት የሚፈፅሙ አካላትም ተጠያቂ እንዲደረጉ ጠይቋል::

አላህ አላህ! አይመን ኸይረዲን ••• 579 ከ600ው ••• ከአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት ! አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! ! እንኳን ደስ ያለው ! እንኳን ደስ አለን ! ! @Moha
+1
አላህ አላህ! አይመን ኸይረዲን ••• 579 ከ600ው ••• ከአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት ! አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! ! እንኳን ደስ ያለው ! እንኳን ደስ አለን ! ! @MohammadamminKassaw

ሌላ ጀግና ሌላ ሰቃይ - 585 ከ600ው! ሁንዳኦል አባስ ቱሬ - የኻሊድ ጓደኛ ! እርሱም የዶዶላ ልጅ ነው ሰዎች:: ምን አይነት ተዓምር ነው በረቢ? ምን አይነት ጀግኖች ናቸው በአላህ?! አላህ ይ
ሌላ ጀግና ሌላ ሰቃይ - 585 ከ600ው! ሁንዳኦል አባስ ቱሬ - የኻሊድ ጓደኛ ! እርሱም የዶዶላ ልጅ ነው ሰዎች:: ምን አይነት ተዓምር ነው በረቢ? ምን አይነት ጀግኖች ናቸው በአላህ?! አላህ ይጨምርላቸው! ደስ አሰኙን --- ደስ ያሰኛቸውና !! @MohammadamminKassaw

ኒቃብ ••• በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ካምፓስ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሶ መግባትን ተከለከሉ! አዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅዳሜ ጀምሮ መግባት የጀመሩ ሲሆን ኒቃቢስት ተማሪዎችን
ኒቃብ ••• በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ካምፓስ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሶ መግባትን ተከለከሉ!    አዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅዳሜ ጀምሮ መግባት የጀመሩ ሲሆን ኒቃቢስት ተማሪዎችን ኒቃብ ካላወለቃችሁ አትገቡም ዶርሚተሪ አትሰጡም እንደተባሉ ጀመዓው አሳውቋል:: የተማሪዎችንም የመብት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እስከመጨረሻው እንደሚታገል ገልፇል:: :- ዩኒቨርሲቲዎች ካለፉት አመታት የመብት ጥያቄዎች መማር አለባቸው:: መሠል ስህተት የሚፈፅሙ የዩኒቨርሲቲ አመራሮችም ተጠያቂ መሆን አለባቸው:: @MohammadamminKassaw

ጥቂት ስለ ትንታጉ ተማሪ ኻሊድ በሺር! ቁርዓን ሐፊዝም ነው ጎበዝ! በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና ከ600ው 591 ያመጣው ኻሊድ በሺር ውልደቱ ቡኖ በደሌ ዞን ውስጥ በምትገኘው ጋቺ ወረዳ
ጥቂት ስለ ትንታጉ ተማሪ ኻሊድ በሺር! ቁርዓን ሐፊዝም ነው ጎበዝ! በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና ከ600ው 591 ያመጣው ኻሊድ በሺር ውልደቱ ቡኖ በደሌ ዞን ውስጥ በምትገኘው ጋቺ ወረዳ ነው:: እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ እዚያው ተምሯል:: ቁርዓንን ሸይኽ ዘይኑ ላይ አክትሟል ሀፍዟል:: አባቱ መምህር ናቸው:: በስራም ምክንያት ወደ አርሲ ተዛውረው አሁን እዚያ ናቸው:: @MohammadamminKassaw

እንኳን ደስ አለው ! እንኳን ደስ አለን ! ! ወንድማችን ኻሊድ በሺር ከሁሉም የኢትዮጵያ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ600 ••• 591 በማምጣት ሰቃይ ሆኗል:: ስለ ስኬቱ ደስ ብሎናል ! አላህ ይባርክ
እንኳን ደስ አለው ! እንኳን ደስ አለን ! ! ወንድማችን ኻሊድ በሺር ከሁሉም የኢትዮጵያ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ600 ••• 591 በማምጣት ሰቃይ ሆኗል:: ስለ ስኬቱ ደስ ብሎናል ! አላህ ይባርክለት ! !

ሶላተል- ጀመዓ በቤተ- መንግስት ! አዲሶቹ የመጅሊስ አመራሮች በቤተ- መንግስት የጀመዓ ሶላት ሲሰግዱ የሚያሳይ ፎቶ ነው ••• ይህ እንግዲህ ዛሬ የሆነ ነው ! ትምህርት ቤት የሚከለክሉትስ? ትምህር
+1
ሶላተል- ጀመዓ በቤተ- መንግስት ! አዲሶቹ የመጅሊስ አመራሮች በቤተ- መንግስት የጀመዓ ሶላት ሲሰግዱ የሚያሳይ ፎቶ ነው ••• ይህ እንግዲህ ዛሬ የሆነ ነው ! ትምህርት ቤት የሚከለክሉትስ? ትምህርት ቤት እንከለከላለን ብለው የማይከተሉትስ? ልጆች ሆይ:- አባቶቻችሁን ምሳሌ አድርጋችሁ ስገዱ ••• መብታችሁ ነውና ት/ቤቶች ሆይ:- ቤተ- መንግስቱን ምሳሌ አድርጋችሁ ተማሪዎች ሲሰግዱ ለመከልከል አትሞክሩ ••• መብታቸውን ማክበር ግዴታችሁ ነውና @MohammadamminKassaw

ስራ --- አካውንቲንግ ፍሬሽ ተመራቂ! ቦታ:- አዲስ አበባ CVያችሁን @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ:: @MohammadamminKassaw