uz
Feedback
Abenezer kidus (abini)

Abenezer kidus (abini)

Kanalga Telegram’da o‘tish

For paid promotions @abenezerkidus

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Abenezer kidus (abini) analitikasi

Abenezer kidus (abini) (@newsfromab2016) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 331 obunachidan iborat bo'lib, Taʼlim toifasida 12 210-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 109-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 331 obunachiga ega bo‘ldi.

02 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -350 ga, so‘nggi 24 soatda esa -25 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 23.06% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 12.99% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 767 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 122 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 6 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“For paid promotions @abenezerkidus”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 03 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Taʼlim toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 331
Obunachilar
-2524 soatlar
-1327 kun
-35030 kun
Postlar arxiv
+2
YacineTV__V3.1.apk8.40 MB

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ያከናወነውን
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ያከናወነውን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደት አጠናቆ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ምደባው የተማሪዎችን የብሔራዊ ፈተና ውጤት፣ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ የክልልና የዞን ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛንን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችም በምርጫቸው መሠረት ቅድሚያ እንዲያገኙ ተደርጓል። በተጨማሪም 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተወለዱበት ወይም ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ 30 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በራሳቸው ክልል ወይም ዞን ውስጥ እንዲመደቡ ታሳቢ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ደግሞ ለከፍተኛ ውጤታቸው ልዩ ታሳቢ ተደርጎላቸው በመጀመሪያ ምርጫቸው ወደጠቀሱት ዩኒቨርሲቲ እንዲመደቡ መደረጉ ተገልጿል። ዓይነ ስውራንና የመስማት ችግር ያለባቸውም አስፈላጊውን የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ልዩ ታሳቢ ተደርጓል። ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ። በምደባው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎችም የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታቸውን ማቅረብ ሲችሉ፣ የቅሬታ ማቅረቢያው የምደባ ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ብቻ ክፍት እንደሚሆን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

ማስታወቂያ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደት አጠናቆ የምደባ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። የተማሪዎች ምደባ ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል። 1. የምደባው ዋና መስፈርቶች 1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። 1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል። 1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት የዩኒቨርሲቲዎችን ብሔራዊ ስብጥር ለማጠናከር እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦ • 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተወለዱበት ወይም ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤ • 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በራሳቸው ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ታሳቢ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። 1.4. የፆታ ሚዛን በዩኒቨርሲቲዎች የሴትና የወንድ ተማሪዎች ተወካይነት ሚዛናዊ እንዲሆን የፆታ ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። 2. ልዩ ምደባ ከመደበኛው የምደባ መስፈርት በተጨማሪ ልዩ ታሳቢነት የሚያስፈልጋቸው እና የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሚከተለው መሠረት ልዩ የምደባ ታሳቢነት ተደርጎላቸዋል። 2.1. የዓይነ ስውራን እና የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች የዓይነ ስውራን እና የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ልዩ ታሳቢ ተደርጓል። 2.2. 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ላስመዘገቡት የላቀ የአካዳሚክ ውጤት ልዩ ታሳቢነት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ባስቀመጡት ዩኒቨርሲቲ እንዲመደቡ ተደርጓል። ይህ ልዩ የምደባ አሠራር ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተናው ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው። 3. የምደባ ውጤትን ስለመመልከት ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት ይችላሉ። የምደባ ውጤት ማየቻ ማስፈንጠሪያ፦ [https://student.ethernet.edu.et/view-placement] 4. ቅሬታ ስለማቅረብ በምደባ ውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታ ማቅረቢያው የምደባ ውጤቱ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ብቻ ክፍት ይሆናል። ተማሪዎች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታቸውን ከአስፈላጊው መረጃና ማስረጃ ጋር በማያያዝ በሥርዓቱ በኩል እንዲያቀርቡ እናሳስባለን። የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ እናሳውቃለን። 5. ማሳሰቢያ ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው። በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ ይችላል። በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በእውነተኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ብቻ በመመሥረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን። የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። የትምህርት ሚኒስቴር

photo content
+1

የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር ተማሪዎች ወ
+1
የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ የመቁረጫ ነጥቡ የተማሪዎች ውጤት፣ የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም እና የሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህን መሰረት በማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

ዉጤት ማየት ተጀምሯል!!

ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ መረጃ👇 https://t.me/+szBcUvcvedQzNGFk

" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news

photo content
+1

የአፋር ብ/ክ/መ/ት/ቢሮ የ2018 የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ Afar Education Bureau Grade 6th_Result_released ሀምሌ 29/2018 (ትምህርት ቢሮ) ማንኛ
የአፋር ብ/ክ/መ/ት/ቢሮ የ2018 የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ Afar Education Bureau Grade 6th_Result_released ሀምሌ 29/2018 (ትምህርት ቢሮ) ማንኛውም ተፈታኝ ከዚህ በታች በተገለጸው ዌብሳይት https://afar6.ministry.et/#/result በመግባት ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ (form) ላይ የመለያ ቁጥር (Registration number) በማስገባትና ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ ውጤቱን ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ማየት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የማለፊያ ነጥብ (አማካይ ውጤት) በቀጣይ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ትምህርት ቢሮ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ ቢሮው ውጤቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ፤ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ክልላዊ 50 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 እና በላይ ማለፊያ ነጥብ ተቆርጦለታል ብለዋል። በዚህ መሠረት 8ኛ ክፍል መደበኛ፣ የግል፣ ማታ እና ርቀት ተብሎ ተከፍሎ ውጤቱ መቀመጡን ሀላፊው በመግለጫቸው አብራርተዋል። በመሆኑ አጠቃላይ 8ኛ ክፍል የተመዘገቡ 86 ሺህ 502 ሲሆኑ የተፈተኑ 78 ሺህ 203 ከእነዚህ ውስጥ 50ና በላይ እንዲሁም 48 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡና ቀጣይ ክፍል ያለፉ 47 ሺህ 307 ናቸው ብለዋል አቶ አብዮት። በዚህ መሠረት ክልላዊ ውጤት ከመቶ ሲታይ 60 ነጥብ 4 ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ 126 ሺህ 224 ሲሆኑ ፈተና የወሰዱ ደግሞ 110 ሺህ 566 ከእነዚህ ደግሞ ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበው ወደ ቀጣይ 7ኛ ክፍል የተዛወሩ 70 ሺህ 584 ናቸው ሲሉም የቢሮ ሀላፊ አብራርተዋል። በዚህም ክልላዊ ውጤት በመቶ ሲገለፅ 63 ነጥብ 8 እንደሆነ ተገልጿል። የ8ኛ ክፍል በትምህርት ቤት ደረጃ ሲገለፅ 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተመሪዎችን ማሳፍ ሲችሉ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳየታቸውን አቶ አብዮት ገልፀዋል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲያሳልፉ 81 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል ሀላፊው። አጠቃላይ ክልላዊ ውጤቱ ከአምና የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ8ኛ ክፍል 3 በመቶ በማነስ ተመዝግቧል ሲሉም የቢሮ ሀላፊ ተናግረዋል። ይህ አምና ክልላዊ ውጤት በመቶ 63 በመቶ እንደነበር ተገልጿል። በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል አምና ክልላዊ ውጤት 56 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2018 ደግሞ 63 ነጥብ 84 እንደሆነም ተገልጿል። ተማሪዎችም በዚህ ሊንክ ገብተው ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል። https://se.ministry.et/#/result https://se6.ministry.et/#/result

photo content

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ***** ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 194374 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 165342(85.06%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ3% ብልጫ አሳይቷል። ተማሪዎች በሁለት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ ሲሆን :- ➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት 3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ ❷ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን ለመጀመሪያ 1) start የሚለውን ይጫኑ! 2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ 3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ 4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ ➌ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) 1) ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት 3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን 4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ 5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

photo content
+1

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ ውጤት ከ2017ዓ.ም ከተመዘገበው ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ20% ጭማሪ(እድገት) ተመዝግቧል። ተማሪዎችም ውጤታቸውን በሁለት አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:- ➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት 3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ ❷ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ 1) start የሚለውን ይጫኑ! 2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ 3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ 4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ ➌ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት 3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን 4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ 5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ 👉 2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

photo content

Qabxiin Qormaata Kutaa 6ffaa Bara 2018 Ibsame. ---------------- BBO - Adoolessa 24/2018 Naannoo Oromiyaatti Qormaatni Naannoo
+1
Qabxiin Qormaata Kutaa 6ffaa Bara 2018 Ibsame. ---------------- BBO - Adoolessa 24/2018 Naannoo Oromiyaatti Qormaatni Naannoo Xumura Barnoota Sad. 1ffaa Kutaa 6ffaa Bara 2018 Waxabajjii 08- 09/2018 kennamee tura har'a qabxiin barattootaa ifoomeera. Qabxiin darbiinsaas 50%fi ol ta'uun murtaa'eera. Qormaata kan fudhatan barattoota dhiira 267,307 dubara 249,902 #walitti :517,209 ta'an keessaa qabxii darbiinsaa (50%fi ol) galmeessisuun gara kutaa itti aanuutti kan darban dhiira - 243,827 (91.2%) dubara -221,012 (88.4%) #walitti - 464,839 (89.9%) ta'uun beekameera. Haaluma kanaan qabxii ilaallachuuf #Liinkii asii gaditti dhihaate banuun; #Lakkoofsa Galmee keessan/Registration Number/ galchuun #Itti aansuun Maqaa keessan kan jalqabaa galchuun qabxii keessan ilaallachuu ni dandeessu. Liinkii:- https://oromia6.ministry.et

🔗 የውጤት መመልከቻ ሊንክ: ce6.ministry.et
🔗 የውጤት መመልከቻ ሊንክ: ce6.ministry.et

በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት፦ የ6ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት👇 https://sidama6.ministry.et/#/result የ8ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት
በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት፦ የ6ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት👇 https://sidama6.ministry.et/#/result የ8ኛ ክፍል ውጤት ለመመልከት 👇 https://sidama.ministry.et

photo content

Abenezer kidus (abini) - Telegram kanali @newsfromab2016 statistikasi va tahlili