Eth-cryptopia
Kanalga Telegram’da o‘tish
✔️Future millionaire Welcome to Eth-Cryptopia🔥 በዚ ቻናል የተለያዩ Airdrops ከብዙ እውቀት ጋር አብረን የምንሰራበት ቤት ነው። ለማንኛውን ጥያቄ ወይም ውይይት ግሩፓችንን መቀላቀል ትችላላቹ @EthCryptopia_Group Buy ads: https://telega.io/c/EthCryptopia
Ko'proq ko'rsatish4 892
Obunachilar
-624 soatlar
-247 kun
-2630 kun
Postlar arxiv
4 892
✔️I saw a post from someone trying to get Satoshi Wallet seed phrase👀
Imagine if he gets it 👀
4 892
#USIRN
✔️I do not trust them 🙌🏽Every time when market is closed they try to manipulate with this kind of things
4 892
🔔Social Media
✔️በሃገራችንም ሆነ በሌሎች ሃገራት የ Social Media አጠቃቀም አንጻር ከፍተኛ የሆነ በአለማወቅ ወይንም ደግሞ ሆን ተብሎ የሚደረገ ነገር አለ።ይሄም የሆነ ሰውን ከመሬት ተነስቶ ቡሊ ማድረግ ነው። ከሰሞኑን ቲክቶክ ላይ በተሰጣት ኮሜንቶች ተሰምቷት ራሷን ያጠፋች ልጅ እንዳለች የተለያየ ቦታ አየው እና ይሄ ነገር ደግሞ የመጀመርያ አለመሆኑ የሆነ ነገር እንድል አደረገኝ።ሃገራችን ላይ ካለው አጠቃቀም ስንነሳ በመጀመርያ ደረጃ ደረጃ የሰውን ሃሳብ አክብሮ አግባብነት ባለው መንገድ ሃሳባ መስጠት የማይታሰብ ነው ቀጥታ ያንን ግለሰብ አጥቅቶ ወይ ሃሳቡን ለማስቀየር መሞከር ካልሆነም ቡሊ ማድረግ የተለመደ ነገር ሆኗል።
✔️ሰውን በተደጋጋሚ ቡሊ የሚያደርጉ ሰዎች ከውስጣቸው ያልተፈቱ ችግሮች፣ ቁጣ፣ ዝቅተኛ ራስ-መተማመን፣ ወይም የራሳቸው የስነ-ልቦና ጫና ወይም ደግሞ ቅናት ሊኖርባቸው ይችላል።ከስነ-ልቦና አንጻር ሲታይ
—አንዳንዶች የራሳቸውን ብስጭት በሌሎች ላይ ያወጣሉ
—አንዳንዶች ትኩረት ለማግኘት ይሞክራሉ
—ሌሎች ደግሞ ከዚህ በፊት ራሳቸው ተጎድተው ሊሆን ይችላል
—አንዳንዶች የ empathy (የሌላን ሰው ስሜት መረዳት) እጥረት ሊኖርባቸው ይችላል
✔️ሰዎችን ቡሊ የሚያደርጉ ሰዎች (አካላዊ ጥቃት) እነዚ ሰዎች በህክምናው bullying disorder የሚል ስያሜ ሲኖረው Social Media ላይ የሚደረግ ቡሊ ደግሞ Cyberbullying ይባላል አብዛኛው ሰው በ Social media ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች bullying disorder አለባቸው ብለው ባያምኑም እኔ በግሌ ግን የዚ ነገር ተጠቂ ይመስሉኛል በምንም አይነት መልኩ ሰውን በማጥቃት የሚደሰት ሰው ለኔ አካላዊ ጥቃት ከማድረግ ጋር አንድ ነው!
✔️Bullying Disorder ያለባቸው ሰዎች ከሚያሳዩት ባህሪዎች መካከል
— Aggressive behavior — ጠበኛ ባህሪ
— Antisocial traits — የሌሎችን መብት እና ስሜት አለመከበር
— Narcissistic traits — ከፍተኛ ራስ የሆነ ቦታ ላይ ሰቅሎ ሌሎችን ዝቅ ማድረግ
— Low empathy — የሌላን ሰው ስሜት ያለመረዳት
— Toxic behavior patterns — ሌሎችን በስሜት የሚጎዱ የተደጋጋሚ ባህሪያት
✔️ከሞላ ጎደል social media ላይ ያሉ ሰዎች እነዚን ባህሪዎች ያሳዩአቸዋል ሶ የ Bullying Disorder አለባቸው ማለት ይቻላል።
✔️social media ላይ ሰውን መሳደብ፣ ማዋረድ ወይም በተደጋጋሚ አሉታዊ ኮሜንት መጻፍ በሰው የአእምሮ ጤና ላይ ከባድ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
— ጭንቀት (Stress)
— ድብርት (Depression)
— ፍርሃት እና ጭንቀት (Anxiety)
— ራስን ዝቅ አድርጎ ማየት
— ሰዎችን መሸሽ
— ከፍተኛ ሁኔታ ላይ እራስን ለመጉዳት ሀሳብ (ሰሞኑን እንደሰማነው አይነት ራስን እስከማጥፋት የሚደርስ)
✔️በተለይ “online bullying” ወይም “cyberbullying” ተብሎ የሚጠራው ነገር ብዙ ሰዎች በዝምታ የሚያልፉት ችግር ነው ነገር ግን ከባድ ችግር ይዞ የሚመጣ ነገር ነው።
✔️Social media ላይ ያለው ሃሳብ በሙሉ ልክ ነው እያልኩኝ አይደለም ነገር ግን ዱላ ቀረሽ ስድብ የሚያወርዱ ሰዎችን ከማየት ነው ይሄንን ነገር ለማምጣት የወስንኩት።
✔️አንድ ወደ Social media እንደ Tiktok አይነት ያሉ መተግብርያዎች ላይ ሲመጣ ለሚመጣበት ማንኛውም ነገር ተዘጋጅቶ መሆን አለበት አለበለዝያ መጨረሳው መሰበር ነው የሚሆነው። የሰው ልጅ ምላስ ምንም የሰብራል የሚባል ነገር አለ ለማንኛውም Stay Safe😊
4 892
+1
🔥Hagere TV
✔️ይሄ ቻነል ከዚ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የትኛውም የግል የቴሌቪዥን ጣብያ አድርጎት የማያውቀውን ነገር እያደረገ ነው ከሳምንት በፊት በዚ አመት የሚደረገውን የ አለም ዋንጫ የማስተላልፍ መብት ተቀብሎ ነበር አሁን ደግሞ እስከ 2021 ድረስ የትም ሀገር የሚካሄድ የአለም አትሌቲክር ውድድርን የማስተላለፍ ፍቃድ አግኝቷል።ይሄ ለ ሀገሬ ቲቪ ትልቅ ነገር ሲሆን እንደ ሀገር ያለውን የሜድያ ኳሊት ከፍ አድርጎባቸው ለልሎቹ።
✔️የዛሬ 4 አመት EBC ሁሉንም ጨዋታ የማስተላለፍ መብት አግኝቻለው ካለ በኋላ ከ Yacine TV Stream ሲያደርግ የሚያስታውስ👀
4 892
✔️Another option
✔️You can use Binance Marketplace for some payments. You can Use it for Mobile services like topup Mobile card for your or anyone's Number , Mobile packages.....
✔️You can even Book flight and Hotel rooms
✔️You can find it on Binance app Go to Home page and Drag Down from the top
✔️Just make money there is always a way✌️🏽
4 892
+2
✔️Btw you can use this option for direct bank transfer. But the problem is high transfer fee you have to pay $25 per transaction for any amount
4 892
Repost from Watcher Guru
JUST IN: 🇺🇸 Jerome Powell officially delivers his final FOMC press conference as Federal Reserve Chair.
End of an era.
@WatcherGuru
4 892
🚀 PJD Capital Crypto Contract Strategy Community 🚀
(Free real-time buy and sell signals provided by the channel)
💎 Cryptocurrency: Free alerts
📈 Entry Point: Free alerts
🔝 Take Profit Price: Free alerts
⛔️ Stop Loss Price: Free alerts
👥 Follow the official PJD Capital channel: @UKPJDVIP
👥 Get real-time trading quotes: @UKPJD
PJD Capital website: www.UKPJD.com
The channel provides trading prices and real-time market dynamics strategies, long/short strategy references, and entry/exit price ranges!
4 892
Repost from Watcher Guru
JUST IN: 🇺🇸 Trump family's World Liberty Financial partnered with crypto project linked to alleged scam-ring operators sanctioned by the US, WSJ reports.
@WatcherGuru
4 892
🔔የነዳጅ ነገር
✔️ሃገራችን ላይ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት ተከስቶ ብዙ ሚልየነሮች እየመጡ ነው። ከተማው ላይ የምታዩት የነዳጅ ሰልፍ ከ ትላልቅ መኪና እስከ ትናንሽ የነዳጅ ሽያጭ ላይ የተሰማራ ነው ሁሉም ባይሆንም አብዛኛው 2 ቀንም አንድ ቀንም ተሰልፎ የሚያገኘውን ነዳጅ መልሶ እነሱ ከገዙበት 4 እና 5 እጥፍ እያተረፉ እየሸቱት ይገኛሉ።በጣም የሚያሳዝነው በዚ መካከል እየተጎዳ ያለው ህዝብ እና ህዝብ በቻ ነው።ናፍጣ ተጠቃሚ የ ትራንስፖርት ሰጪዎች ይሄንን እንደ ስራ ይዘውት ከሳምንት እስከሳምንት ማደያ ላይ ሰልፍ ይዘው ነው የምናያቸው። አንድ የቢት መኪና ያን ያህል እንቅስቃሴ የማያደርግ ወይ የ ትራንስፖርት አገልግሎት ውስጥ የሌለ ቢያንስ በሳምንት 3 ግዜ ለነዳጅ ተሰልፎ ታያላቹ በጣም የሚያስቀው ነዳጁን እየጨረሰ ሳይሆን አውጥቶ እየሸጠ መሆኑ ነው ።
✔️ትንሽ የምትሏቸው መኪኖች ከ 40 እስከ 50 ሊትር ነዳጅ መያዝ ይችላሉ።አንድ 50 ሊትር መያዝ የሚችል መኪና 3 ቀን ተሰልፎ ነዳጅ በ 163 ብር ሂሳብ ይቀዳል 50*163 = 8,200 ብር + 1500 - 2000(ጉቦ ለ......) 10,200 በአጠቃላይ ያወጣል ከዛ በኋላ ራሱን ነዳጅ ተረካቢ ስላለው ከ 500 እስከ 1000 ብር በ ሊትር ይሸጠዋል።ከቀዳው 45 ሊትር የሚያክለውን እንኳን በትንሹ በ 500 ብር ቢሸጠው ያወጣውን እጥፍ ያገኛል 45*500 = 22,500 (አስቡት ይሄ በትንሹ በ 500ብር አንዱን ሊትር ቢሸጠው ነው እስከ 1000 ብር ነው እየተሸጠያለው ብላክ ላይ)። ይሄ በሳምንት 3ግዜ ምናምን ሊያደርገው ይችላል እንደሚያገኙት ነዳጅ ይወሰናል በሳምንት 3 ግዜ መቅዳት ከቻሉ ቀን ሙሉ ሳይመላለሱ በሳምንት እስከ 67,000 ብር ኪሳቸው የገባል ከዚ ላይ የነዳጁን ብናነሳ ደግሞ ሶስት ግዜ የሚቀዱበት 10,200 * 3 = 30,600 (67,000 - 30,600 = 31,000 ብር ትርፍ)😊
✔️ይሄንን ነገር የሚያደርጉት ትላልቅ ተሽከርካሪዎችም ጭምር ናቸው እነሱ ደሞ የመኪናው ሳልባትዮ በጣም ትልቅ ነው አብዛኞቹ የ ደርሶ መልስ ስለሚቀዱ ከ 300 ሊትር በላይ ነው የሚይዘው አንደ ሳልባትዮ አይነት ይወሰናል።በቃ ሂሳቡን ለ እናንተ ትቼዋለው አስቡት)
✔️ይሄ ነገር ከተፈጠረ የነዳጅ እጥረት ጋር ተደማምሮ ተጨማሪ እጥረት እንዲፈጠር እና የሃገሪቱ Economy ገደል እንዲገባ የሚያደርገው ነገር ነው።ይሄ ነገር አሁን ላይ በግልጽ ነው የሚከናወነው ገና ነዳጅ ማደያ ጀምሮ ይታወቃል እዚ ቼይን ላይ እዛው የማደያው ባለቤቶች፣ በውስጥ ያሉ ሰራተኞች ፣ የጸጥታ አካላት ተብለው የሚመደቡ አካላት ሁላ አሉበት ብር ተቀብለው ብዙ መኪና ያስገባሉ በ ሃላል።የትኛውን ይሄንን ነገር መቆጣጠር የሚችል አካል ይሄ ነገር እንደሚደረግ ያውቃሉ ግን ማንም እርምጃ ለመውሰድ ፍቃደኛ አደለም ሁሉም የ ቼይኑ አካል ስለሆነ!
✔️ይሄን ነግር ረስቼው ነበር ከ 2 ቀን በፊት አልጃዚራ እዚ ስላለው የነዳጅ እጥረት የሰራው ዘገባ ሳየው ትዝ ብሎኝ ነው።
ለማንኛውም የተለመደ ነገር ነው የሆነ ነገርን ተጠቅሞ በ አቋራጭ ማደግ እኛ ሃገር ግን ምን ለማለት መሰላቹ ይሄ ህዝብ ነው ከዚ የወጣ ሰው ነው ወደፊት መንግስት ሆኖ ሃገር የሚመራው ሁሉም በ እጁ ሲሆን ምን ሊያደርግ እንደሚችል አስቡት😊 ከመንግስት አካላት ጀምሮ እስከ ህዝብ ሁሉም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ነው ለማደግ የሚፈልገው።የነዳጅ እጥረቱ በዚው የሚቀጥል ከሆነና ይሄንን ሌብነት የሚያስቆመው ከሌላ በ ቀን አንድ ግዜ መብላት የምይቻልበት ደረጃ እንደሚደረስ አትጠራተሩ አብዛኛው ስራም እንደሚቋረጥ እመኑ🙌🏽
