cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 735
Obunachilar
-224 soatlar
-77 kunlar
-1430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Repost from አባወራ
ክርስትናን ያልጮች ያደረገ ክርስትና ===================== ሳተናው! አንድ ወንድምህ በፈተና ተንጦ፣ በንባብ ረግቶ፣ በልምድም በስሎ ያገኛቸውን መራር ሐቆች በምክር መልክ አቅርቦልሃል፤ አንተ ግን በወደድከው ኑር! በዓለም ሳለ ውጊያ እንዳለበት ለጦርነትም ታጥቆና ሠልጥኖ መኖር እንዲገባው በአባቱ የተነገረው ክርስትያን ዘወትር ፍርሃትንና ብሶትን በሚግቱ አስመሳይ ሰባኪያንና ዘማሪያን ሲሸበር ይኖራል። እነርሱ ለሆዳቸው ለብዝበዛቸውና ከዓለም መንግሥታት ጋርም ተሻርከው ትውልዱ ለባርነት የተመቸ ይኾን ዘንድ ለሀገራችን ለቤተክርስትያናችንም ባዕድ የኾነ የብሶት፣ የሮሮ፣ የምሬት፣ የድካም፣ የባይተዋርነት፣ የሽንፈት፣ ያልጫ "ትምህርት" ይግቱታል። ይህንኑም በተለይ ዘወትር ታቦት ቢያነግሱ ደስ በሚላችው፣ በአፍኣ በኾነ ጩኸት በለቅሶና ዋይታ በማላዘንም በተሞላው "መዝሙራቸው"፣ ትውልድ ከተማረው ከተሰበከው አንጻር በፍርሃት እንዲኖር በሚያደርገው ጩኸታቸው ትውልዱን ፍዝ ያደርጉታል። ታናሼ! ዛሬ እኔና አንተ የምንኖርበት ክርስትና ያ አባቶቻችን በጀግንነት ሀገር፣ ድንበር ጠብቀው ትውልድ ያስቀጠሉበት፣ ሲሻቸው ዐለምን ትተው ቤት ለይተው፣ ከዓለም ተድላ ደስታ ርቀው በቅድስና የኖሩበት ሲያልፍም የመነኑበት በፍጹም አይደለም። እስኪ ራስክን ታዘብ! ምንህ በታሪክ የሰማሃቸውን ጀግኖች፣ በገድላቸው ጠበል ጠዲቅ የቀመስክላቸውን ወገኖችህን ይመስላል። ቁምና ሰውነትክን በብርጭቆው ፣ ልብህንም በአባትህ ቃል መስተዋትነት መርምር! ስለ እውነት ትቆማለህ? ራሱ እውነት የኾነ፣ የእውነት ምንጩ፣ እውነተኛው አምላክ "አባቴ ነው" ብለህ አንተ እኮ ዛሬም ማት ገጽ ላይ ድድ ከማስጣት ባላፊ ባግዳሚው ልጥፍም ላይ አስተያየት ሲጪ (commentator) ከመኾን ያለፈ አላደግክም። ወንድምዓለም! አሁን እኔና አንተ ክርስትናን የምንኖርበት መንገድ የእውነት ትጥቅ ከመታጠቁ፣ ያባቱን ቃል ከመጠበቁ፣ ያባቶቹን ፈለግ ከመከተሉ የተነሳ፦ 💪 ደፋር፣ 💪 ኃይለኛና 💪 ሥልጡን ሊኾን ሲገባ አልጫ፣ ሰነፍ፣ ሰበበኛ፣ ስሜታዊ ኾኖ ማማረር፣ ማላዘን፣ መነፋረቅ እንጂ ራሱ ላይ፦መጨከን፣ መሠልጠን፣ መጠንከር፣ መተባበር፣ መተጋገዝ፣ መደጋገፍ የራቀው ትውልድ በማፍራት ክርስትናችንን ያልጮች መመሸጊያ የሆዳደሮች መፋነኛ አድርጎታል። ይህም ደግሞ ካናት እንዳየለብን ማስተዋል ይቻላል። እስኪ ራስክን ታዘብ! እንኳን ለሀገርና ለትውልዷ በይፋ ለሚኾነው አይደለም፤ በቤትህ ትዳርህን በመምራት ልጆችህን ለምታንጽበት ሥርዓት መዋቅር ትቆማለህን? በትንሿ ቤትህ፣ ያንተ ብቻ በኾነችው ቤተመንግሥትህ በድፍረትና ጥንካሬ በራስህ ላይ ሠልጥነህም በእውነት ስለእውነት መቆም ካቃተህ የትም ለማንም በእውነት መቆም አትችልም። ዐለም በክፋት እንድትሞላ ያደረጋት እርሷ ከእውነት ይልቅ ኃይለኛና ጥበበኛ ኾና እንዳይመስልህ ይልቁንስ እርሷን ሊሽራትና ሊደመስሳት የሚችለውን እውነት፦ 👉 ታጥቀው መኖር ያልፈቀዱ፣ 👉 የሚፈሩ፣ 👉 ክፋትን፣ ነውርን፣ ኃጢአትን የሚታገሱ ከዚህ እጅግ የሚከፋውና የሚብሰው ደግሞ ✨ እንዲህ መኖሩ ራሱ ክርስትና በሚመስላቸው ሰዎች ዝምታ ነው። ከዚህም የተነሳ አባታችን ካስተማረን፣ አባቶቻችንም ከኖሩት ጋር ፍጹም የማይነጻጸር፣ የማይመሳስል ያልጮች የኾነ፣ ሆዳደሮችን የሚያፈራ፣ ትውልዱን ለባርነት ያደላደለ፣ ለጠላት የተመቸ "ክርስትና" እየኖርን ክፋት በዓለምም ኾነ በሀገራችን እንዲሠለጥን ኾኗል። የአባትህን ቃል አስታውስ፣ በልብህም አስተውለው እንዲህም ይላል፦ በዓለም ሳላችሁ.... አታንቀላፋ! አትነፋረቅ! አታላዝን! ይልቁንስ አባትክን፣ ፈለጉን የተከተሉ የቀደሙ አባቶችክንም ምሰል እንጂ! . . ...ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
🙏 16👍 7👎 1 1
ልዩ ቆይታ!
Hammasini ko'rsatish...
👍 15
እውነቱ ይህ ነው አናድምጠው
Hammasini ko'rsatish...
👍 29 8 1
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ በብልጽግና እና በአብይ አሕመድ የተከፈተው ጥቃት እና ሂደቱን አስመልክቶ የተዘጋጀው ጥናት ( ሊያደምጡት የሚገባ )
Hammasini ko'rsatish...
12👍 4
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን። የትንሣኤው ብርሃን ኃይለ መቃብርን ድል እንደነሳልን የድህነት፣ የድንቁርና፣ የዘረኝነት፣ የቂመኝነት፣ የትዕብት፣ የስስት፣ የአፍቅሮ ነዋይ . . . በአጠቃላይ የክፋት መቃብርን ድል እንነሣ ዘንድ ይርዳን።
Hammasini ko'rsatish...
35👍 3🙏 3
ትንሣኤው የአሸናፊነታችን መሠረት ነው! ትንሣኤው በመከራ ውስጥ ላሉት ሁሉ በደስታ የምንናገረው ከሁሉ በላይ አጽናኝ እና አስደሳች ብስራታችን ነው! ለዓለሙ ሁሉ የምንመሰክረው ሥጦታችን ነው! ለሰው ልጆች ሁሉ ከዚህ የላቀ ብስራት የለም! ክርስቶስ ተነሥቷል! ደስ ይበላችሁ! ይሄንን ለሁሉ ንገሩ! በመክራ ውስጥ ላሉ ወገኖቻችን ሁሉ ነገሩ! እነሆ ይሄ በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ ላለን ሁሉ ትልቁ መጽናኛ ነው! ክርስቶስ ተነስቷል! የትንሣኤያችን በር ተከፍቷል!
Hammasini ko'rsatish...
30👍 4🙏 2👏 1
ቀዳም ሥዑር (ቅዳሜ ሽር) የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው። ይኽች ቀን ቀዳሚት ሰንበት እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ያረፈባት ቀን ናት። ቀጥሎም ጌታ ስኩብ በመቃብር ሆኖ ያደረባት ቀን ናት።  ቅዳሜን ሥዑር የተባለችበትን ሦስት ምክንያት መጥቀስ ይቻላል።  አንደኛው:- ጌታ በዕለት ዓርብ ተሰቅሎ ሞትን ሽሮ በሥጋው ወደ መቃብር በነፍሱ ወደ ሲኦል ሄዶ ነፍሳትን አውጥቷል። ቅዳሜም ነፍሳት ከሲኦል እየወጡ ነበር። የመጀመሪያው አዳም ከገነት ዓርብ ጌታ ሲኦልን እንደ ከፈተ ወጣ ልጆቹ ተከታትለው ወጡ የመጨረሻው ነፍስ የወጣው እሑድ ጌታ ሊነሣ ሲል ነው። ነፍሳት ከሲኦል ወደ ገነት ተጓዘው የተፈጸሙት በሦስት ቀን ነው። ስለሆነም ሞት ተሽሮባታልና ቀዳም ስዑር ተብላለች።  ኹለተኛው ምክንያት:- በብሉይ ሰውን ማዳን ያልቻለችው ሕገ ኦሪት በሐዲስ ኪዳን የፍቅር ሕግ የተተካችው በክርስቶስ ሞት ነው። ሰንበትን የሻረ ይገደለ የምትል ኦሪት ነበረች። “ ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰውም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፥ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ” ዘጸ.31:14 ስለሆነም ቀዳሚት ሰንበት ሰው ታስገድል ነበር። ስለሻራት ሰውን መግደሏ በክርስቶስ ሞት ስለቀረ (ስለተሻረባት) ቀዳሚት ሥዑር ተባለች። ሰውን የምታድነው ሰንበት ተተካች። ዘኁ.15:33-35 ሦስተኛው ምክንያት:- ስለ ጾም በታዘዘበት የፍትሐ ነገሥት አንቀጽ "ወኢይደሉ ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ወትረ እስመ እግዚአብሔር አዕረፈ ቦቱ እምኵሉ ግብሩ አላ ይደሉ ከመ ይጹሙ በዝንቱ ሰንበት ባሕቲቱ እስመ ፈጣሬ ፍጥረታት ኮነ ቦቱ ስኩበ ውስተ መቃብር" "በቅዳሜ ሰንበት ቀየሳምንቱ ሊጾሙ አይገባም እግዚአብሔር የሥነ ፍጥረት ሥራውን ፈጽሞ ዐርፎበታልና ነገር ግን ጌታ በመቃብር ስኩብ ኾኖ በዋለበት ቅዳሜ ብቻ ሊጾሙ ይገባል"  "ወእመቦ ዘተረክበ እምካህናት እንዘ ይጸውም በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበት (ቀዳሚትን ነው) ዘእንበለ ሰንበት ዐባይ ባሕቲታ ዘድኅረ ሕማማት ይትመተር" "ከካህናት ወገን ከሰሙነ ሕማማት በኋላ ካለች ተላቅ ሰንበት ቀዳሚት በቀር እሑድ ወይም ቅዳሜ ሲጾም ቢገኝ ከሹመቱ ይሻር" ብለዋል። ስለኾነም ከሁሉም ቀናት ቀዳሚት በዚኽ ቀን በጾም ተሽራለች።  ሠለስቱ ምዕት ሃይማኖተ አበው ይኽንን ሲገልጹ “በሰንበት፡ ቀኖችም ፡ እንደሌሎች ፡ ቀኖች  አትጹም፤ ጌታችን ፡ ኢየሱስ  ክርስቶስ ስኩብ ፡ በመቃብር' ሆኖ ፡ ከነበረባት፤ ድኅነት ፡ በተደረገባት፡ ከፋሲካ፡ ዋዜማ ፡ ካለች ፡ ከአንዲት ፡ ቅዳሜ ፡ ቀን (ቀዳም ሥዑር) ፡ በቀር” ይላል። ሃይ.አበ ሠለስቱ ምዕት ምዕ.20:27 መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Hammasini ko'rsatish...
👍 14 6