cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

TIKVAH-ETHIOPA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ

Ko'proq ko'rsatish
EfiopiyaAmxarToif belgilanmagan
Reklama postlari
227
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Follow me 👈
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
I am @christ_4901 on TikTok. To download the app and watch more videos, tap: https://m.tiktok.com/invitef/download?username=muser&platform=telegram

TikTok

Selam
Hammasini ko'rsatish...
Join meAnonymous voting
  • Please join me
  • Please join me
0 votes
Waama diggoona hechitotee
Hammasini ko'rsatish...
🔥 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ለስፔሻሊቲ ስልጠና ፈተና ያለፉ ሰልጣኞች ቅሬታ ምንድነው ? በ2016 ዓ/ም አዲስ የህክምና ስፔሻሊቲ ሀኪም ሰልጣኞች ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ባወጡት የማስፈፀሚያ መመሪያ የተሰጠው ፈተና አልፈን እና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተመደብን በኋላ " የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና  (GAT) ትወስዳላችሁ " በሚል ወደኋላ ተጎትተናል ሲሉ ቅሬታቸዉን አቅርበዋል። ፈተናዉን ያለፉ አንድ ሽህ ስድስት መቶ ገደማ የህክምና ባለሙያዎች በጤና ሚኒስትርና በትምህርት ሚኒስትር ስምምነትና በተማሪዎች መብትና ግዴታዎች መካከል ያልሰፈረ  ያሉትና አሁን ላይ የትምህርት ሚኒስቴር " ወደኋላ ተመልሸ እፈትናችኋለን " የሚለው የድህረ ምረቃ መግቢያ (GAT) ፈተና አግባብ ያልሆነና ከዲፓርትመንት ፈተና ቀድሞ ሊሰጥ የሚገባዉ ነው ሲሉ ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ከሁለት ወር በፊት ከተወዳደሩት ሶስት ሽህ ዶክተሮች መካከል አንድ ሽህ ስድስት መቶዎች ማለፋችን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ሲጀምሩ ከየስራቦታችን ክሊራንስ ጨርሰንና ቤተሰባችን ይዘን በየተመደብንበት አካባቢ ቤት ሁሉ በመከራየት ዝግጁ ብንሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ድንገት " የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና መውሰድ አለባችሁ " አለን የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች አሁን ላይ ጥሪ አድርገዉ የነበሩት ሀሮማያና አምቦ ዩኒቨርሲቲዎች እንደገና በአዲስ ማስታወቂያ ጥሪዉን ማራዘማቸዉን ገልጸዋል ብለዋል። በዚህ ወቅት ሁሉም ሰልጣኝ ከስራ፤ ትምህርትም ተስጓግሎ የመንግስትን ውሳኔ እየጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል። የሚመለከተዉ አካል በትምህርት ሚኒስቴርና በጤና ሚኒስትር የመጀመሪያ ስምምነትና ተማሪዉ በደረሰዉ መብትና ግዴታ መሰረት ሁኔታዎች እንዲመሩ ያድርግልን ሲሉ ጠይቀዋል። " ያ ካልሆነ ግን ስራ መልቀቃችንና የፈተና ውጤት አላግባብ ከመሰጠቱ በላይ ውጤቱ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር የሚፈጥር በመሆኑ በሰላማዊ ሰልፍ ሀሳባችን የምንገልጽ መሆኑ ይታወቅልን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል። መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የኤዶን ቀበሌ የታጠቁ አካላት ተቆጣጥረዋት ሰንብተዋል " - የወረዳው የጸጥታ ሀላፊ ከሰሞኑ በወንዶ ገነት ፣ ኤዶ ቀበሌ የተቀሰቀሰዉ ረብሻ በአካባቢዉ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቦታዉን ከጥር ሰላሳ ጀምሮ ለቀዉ መውጣታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል። ለአመታት በሲዳማና ኦሮሚያ አዋሳኝ በሆነችዉ የኤዶ ቀበሌ ያለዉን ውጥረት ለማርገብ በሚል መቀመጫቸውን በቀበሌዋ አድርገው የቆዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቦታዉን መልቀቃቸውን ተከትሎ ችግሮች መከሰታቸውን የወንዶገነት ወረዳ የጸጥታ ሀላፊ አቶ ሀማሮ ሀይሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። " የፌዴራል ፖሊስ አባላት ቦታዉን ሲለቁ የመጡ የታጠቁ አካላት የፌደራል ፖሊስ አባላት ትተው የሄዱትን የደንብ ልብስ በመልበስ በአካባቢዉ መንቀሳቀስ ጀመሩ " የሚሉት አቶ ሀማሮ ፤ ምሽት ላይም ከሰራ ወደቤቱ የሚመለሰዉን ሰዉ በማስቆም ገንዘብ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። ትላንት ጠዋት ይህዉ ሰውን መዝረፍና ማሰቃየት ቀጥሎ መንገድ ከመዝጋት ባለፈ አንድን ልጅ ተኩሰዉ አቁስለዋል ብለዋል ኃላፊው። ይህን ተከትሎ ወደአካባቢዉ ያመራዉ የመከላከያ ሀይል ትራንስፖርት አስጀምሮ ያአካባቢዉን እንቅስቃሴ ማስቀጠሉን ገልጸዋል። " አሁን ላይ የመከላከያ ሀይሉ መውጣቱን ተከትሎ ሸሽተዉ የወጡት ጸረሰላም ሀይሎች ተመልሰዉ ሊገቡ ይችላሉ " የሚሉት ኃላፊዉ ጉዳዩን በሽምግልናም ሆነ በህግ ከስሩ መፍታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። መረጃውን የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው። ፎቶ፦ በወንዶ ገነት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል (ፋይል) @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በፈንጂ እና በድማሚት ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም " - የከበሩ ማዕድናት አምራች ማህበር ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል። ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ፈንጂ ቢጠቀምም፤ ሙከራው እንዳልተሳካ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳደር ገልጿል። የመከላከያ ሠራዊት መሀንዲሶች በአካባቢው ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፤ ዋሻው የሚገኝበትን ቦታ ተመልክተው " ፈንጂ እና ድማሚት " በመጠቀም የዋሻው የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካም ተብሏል። የተንጠለጠውን ገደል ለመናድ አልተቻለም። ይህ ሙከራ ከከሸፈ በኋላ እንዲወገድ የሚፈለገውን የዋሻ ክፍል " በታንክ የመምታት " ሀሳብ ከመሀንዲሶቹ በኩል መቅረቡን የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ገልጿል። ያቺ ቦታ ብትመታ እና ብትናድ ሰዎቹን ቆፍሮ የማውጣት እድል እንደሚኖር ማህበሩ ገልጿል። ይሁንና " በታንክ መምታት " የሚለው ሀሳብን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ተነግሯል። የመከላከያ ሠራዊት አባላት መውጫ ያጡትን የማዕድን ቆፋሪዎች ለማውጣት አሁንም በአካባቢው እንደሚገኙ ተገልጿል። በዋሻው ውስጥ መውጫ ካጡ 12 ቀናት ያስቆጠሩት የማዕድን አውጪዎች ያለ ምግብ " እስካሁን መቆየት ይችላሉ ? " ለሚለው ጥያቄ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር አሁንም ተስፋ እንዳለ አመልክቷል። " ይኖራሉ። እስከ 15 ቀን ድረስ የመቆየት እድል አላቸው። ዋሻው ውስጥ ውሃ ስላለ፤ አፈር በሉ ምንም አሉ ዞሮ ዞሮ የመቆየት እድላቸው አለ " በማለት ግለሰቦቹ በህይወት ይገኛሉ የሚል ተስፋ እንዳለው ማህበሩ ገልጿል። መረጃው የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው። ፎቶ፦ የደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #የተማሪዎችምገባ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፤ የውሃና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚከናወነው የምገባ ሥርዓት ፈተና መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው የነበረው በአ/አ ት/ት ቢሮ የተማሪዎች ምገባ ባለሙያ አቶ አለሙ ሀይሉ ፥ የምገባ ሥርዓቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቁ አጋዥ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል። የሥርዓቱ በት/ቤቶች መኖር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን በዚህ ሂደት አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል። ምንም እንኳን ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር ሲታይ በርካታ ለውጦች ቢኖሩም  #የውሃ_አቅርቦት ችግር ተግዳሮት መሆኑን  አመልክተዋል። በተለይ ምገባ ላይ ብዙ ውሃ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ አለሙ ፤ " 5 የምገባ ቀናቶች አሉ (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በእነዚህ ቀናት መካከል የውሃ አቅርቦቱ እንደተፈለገ የማይሆንበት ጊዜ አለ " ብለዋል። ችግሩን ለመቅረፍም አማራጮች እየተወሰዱ መሆኑና ተጨማሪ የውሃ ታንከር ጥቅም ላይ እንደሚውል አስረድተዋል። አንዳንድ ት/ቤቶችን በተባለው ቀንም አድሬስ ከማድረግ አኳያ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው " ከዚያ አኳያ ውሃ ነው መታገዝ ያለበት " ሲሉ አሳስበዋል። ሌላው በመንግሥት እንዲሁም በዓለም ባንክ የተሰሩ የምገባ አዳራሾች የመብራት አቅርቦት እንዲኖራቸው ከማድረግ ጋር ተያይዞ በተወሰነ ደረጃ ተግዳሮት እንዳለ አመልክተዋል። ምንም እንኳን የምገባ አዳራሾች ቢኖሩም ምግብ ለማብሰያ የሚሆን #የመብራት_ኃይል አቅርቦት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጸዋል። በሌላ በኩል በት/ቤቶች ምገባ ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰዎች በተለይ #ከኑሮ_ውድነቱ አኳያ ሲታይ የሚከፈላቸው ክፍያ " በጣም አነስተኛ ነው " በማለት ሲያማርሩ ይደመጣሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንኑ ምሬታቸውን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል። አቶ አለሙ ፤ " ከምገባ ክፍያ ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለው በየጊዜው እንደዬ ኑሮ ሁኔታው እየታዬ ይሻሻላል። " ብለዋል። " ለምሳሌ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥናት በማድረግ ወደ #23 ብር በተማሪ (በነፍስ ወከፍ) እንዲያድግ ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል። " በዚህ ዓመት ለምገባ ፕሮግራሙ መጠቀም ያለባቸው ተብሎ የተመደበው ወደ 3.2 ቢሊዮን ብር ነው " ሲሉ አክለዋል። " በዚያ ደረጃ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይኬዳል ማለት ነው። ሲጀመር (የምገባው ፕሮግራሙ) በ14 ብር ነበር አሁን #23 ብር የደረሰበት ሁኔታ አለ። ለቀጣይ ደግሞ ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ እየተጠና የሚሻሻልበት አሰራሮች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የምግብና ሥርዓተ ምግባ ቅንጅታዊ አሰራርን አስመልክቶ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ጥያቄ አቅርቦ ነው። መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው " - አቶ ከበደ አሰፋ የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ፣ በመቐለ ዙሪያ ስለሚስተዋለው፦ * የመሬት ሊዝ ሁኔታ፣ * ስለወልቃይትና ራያ ተፈናቃዮች፣ * ስለፕሪቶሪያው ስምምነት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። አቶ ከበደ በመቐለ ዙሪያ የመሬት ጉዳይ ምን አሉ? ➡ 70 እንደርታ ውስጥ፣ እንደ አጠቃላይ መቐለና ዙሪያው ያለውን የመሬት ወረራ በልዩ ሁኔታ እንቃወማለን። ይሄ የመሬት ፓሊሲ አርሶአደሩን የሚያደኸይ ነው። ይሄም በተጨባጭ እየታዩ ነው። ➡ የስርዓቱ ሰዎች ከአርሶ አደሩ መሬቱን በጉልበት ይቀማሉ። ለሚፈልጉት ባለሃብት ያቀርባሉ። ከባለሃብቱ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የመሬት ፓሊሲ የኪራይ ስብሳቢነት፣ የሙስና ምንጭ ነው። ➡ በሊዝ ስም መሬት በካሬ በ85,000 ብር ይገዛሉ። ይህን 20፣ 30 ፐርሰንት እየከፈሉ ይወስዳሉ። ይሄ ገንዘብ ከሕዝቡ በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደ ነው። የሕዝብ ሀብት ዘረፉ፣ መልሰው የድሃውን መሬት በመግዛት ሕጋዊ እያደረጉ ነው ያሉት። ምንጩ ግን ሕገ ወጥ ነው። ጭቆናው ድርብ ነው። ➡ ባለን መረጀ መሠረት 1867 አካባቢ መሬት የመጀመሪያው ሊዝ ተዘጋጅቷል፣ በመቐለ ዙሪያ ለምሳሌ ስራዋት፣ እግረወንበር…ብዙ ናቸው።  ➡ ያካተቷቸው አንሷቸው ተጨማሪ 13 ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ መቐለ አካተው፣ የእንደርታ ህዝብን መሬት ሸጠው ለመበልጸግ ዝግጅት ላይ ናቸው። ስለተፈናቃዮች ምን አሉ ? ☑ የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከምንም ነገር በላይ ለወልቃይትም ሆነ ለራያ ሕዝብም መታሰብ አለበት። ማዶና ማዶ ባሉ ሊህቃን ምክነያት ይህን ሕዝብ የጦር ሜዳ እየሆነ ነው። እየተፈናቀለ፣ የገፈቱ ቀማሽ እየሆነ ያለው ይሄ ሕዝብ ነው። ስለኘሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ? - ትግራይ ውስጥ እስቲል #ታጣቂዎች ትጥቃቸውን #አልፈቱም። እኛ መፍታት አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለን። ለምን ዓላማ ነው ከነመሳሪያቸው እስካሁን የሚቆዩት ? ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም። - ኢትዮጵያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መከላከያ ሠራዊት ነው። ከዛ በመለስ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ይፍቱ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አንዱ ይህ ነው።  - ለምን እንደተቀመጡ አናውቅም ስጋት አለን። መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.