Telegram 🧲 Best Tips 🇪🇹
Kanalga Telegram’da o‘tish
እንኳን ደህና መጣችሁ። በቴሌግራም ከመፃፃፍ እና ዳታ ከመላላክ በተጨማሪ በርከት ያሉ ሥራዎችን መስራት ይቻላል። 📜 በዚህ ቻናሌ ትክክለኛ የቴሌግራም አሪፍ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል 🔞 በኃላፊነት መረጃዎችን እንጠቀም ለሌሎችም እናጋራ 🤝 ስልካችንን ከመደዋወል እና ከማህበራዊ ሚድያ መከታተያነት ይልቅ ለራሳችን እንጠቀምበት
Ko'proq ko'rsatish1 563
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-137 kun
-5230 kun
Postlar arxiv
የቴሌግራም አካውንታችሁን ከጠላፊዎች ጠብቁ፣ ያገኛችሁትን Link ከመንካት ተቆጠቡ፣ አጓጊ እና ቀልብ ከሚስቡ ማስፈንጠሪያዎች ተጠንቀቁ።
8⃣ Telegram ask you regularly for two-step /
ቴሌግራም ከመንታፊዎች እራሳችሁን ጠብቁ ይላል
ከላይ ቴሌግራማችሁን በፓስኮድ መዝጋት ጠቃሚ መሆኑን ሳነሳ፣ ለዘላለም ትጠበቁ ዘንድ ደግሞ የጀርባውን ተጨማሪ two-step verification ይለፍ ቃል ማስገባቱ ግዴታ መሆኑን ከላይ አስርሜበታለሁኝ። እናም ቴሌግራም ደስ የሚለው ንቁ እንድትሆኑ በየተወሰነ ጊዜ የጀርባ በር ይለፍ አስገብታችኋል ብሎ ያስታውሳችኋል። ይህ ከአደጋ ተከላካይ ማስታወሻ በመሆኑ በጣም ይመቸኛል፣ ብሎም ይለፍ ቃሉን እንዳልረሳ ያስታውሰኛል።
Staying secure on Telegram is super important! 🛡️ One personal tip? Always enable the passcode lock. It’s saved me from unintended snoopers on my phone! 🔒 And don’t forget to check the Privacy settings regularly. Keep your chats safe and sound! 💬 #TelegramTips #PrivacyFirst
7⃣ Two-step verification is your Telegram Survival/
የጀርባ የዘላለም ይለፍ ቃል ካለ ቴሌግራማችሁ የናንተ ነው
ከላይ ቴሌግራም የራሱ የሆነ ፓስኮድ (ይለፍ ቃል) እንዳለው ያወራነው እንዳለ ሆኖ ይህንን ማጠንከሪያ እና ስልካቹ እንኳን ቢጠፋ ወይም አጋጣሚ ፓስኮዱ ሌላ ሰው እጅ ቢገባ መልሳችሁ በእጃችሁ ለማድረግ two-step verification የሚባለውን ጠንካራ ሌላ የጀርባ የይለፍ ቃል ማስገባት ግድ ይላችኋል። ይህ የኋላ ደጀን የቴሌግራማችሁ አለኝታ እና የዘላለም ህልውና ነው። ግን ይለፍ ቃሉ መረሳት የለበትም።
🔒 Staying safe on Telegram is easier than you think! Always enable two-step verification for extra security. Remember to check privacy settings; control who can see your info. Lastly, be cautious about sharing personal details in chats. Let's keep our conversations secure and private! 😊 #TelegramTips #StaySafe
6⃣ The pin option for your important infos /
በጣም አንገብጋቢ መረጃዎችን ሁሌም ከፊት
ቴሌግራም ስትጠቀሙ በርካታ አንገብጋቢ መረጃዎችን ከቻቶች ውስጥ የት እንዳሉ በመፈለግ ጊዚያችሁ ተቃጥሎ ይሆን? እንግዲያውስ ከቻቶች መካከል ቀላሉ መለያ የፈለጋችሁትን መረጃ ጫን በማለት ፒን ስታደርጉት ከላይ ሁሌም ቁጭ ይላል፣ በቃ ከዚያ ውስጥ ፈለግ ፈለግ ማድረግ ብቻ 😎
✨ Have you ever struggled with organizing your chats? I totally get it! One little trick I love is using pinned messages to keep important info at the top. It’s super handy! What’s your favorite Telegram tip? Let’s share ideas! #TelegramTips #ChatOrganization
5⃣ Monthly new updates & amazing features /
በየወሩ አዳዲስ ገፅታዎችና አስገራሚ ይዘቶች
እንደ ቴሌግራም ምርጥ አፕ አይቼ አላውቅም ስላችሁ በምክንያት ነው፣ እጅግ በጣም ለአጠቃቀም ቀላል ከመሆኑ ባሻገር በየወሩ የሚለቃቸው ማሻሻያዎች የቱን ይዤ የቱን ልልቀቀው ያስብላል። እናም ቴሌግራምን አብልጬ እንድወደው የሚያደርገኝ አንዱ ማንነቱ ይህ ነውና ግዴለም ትክክለኛ ቦታ ነው ያላችሁትና ቴሌግራም መጠቀሙን ቀጥሉበት።
Ever struggled with Telegram’s endless features? I get it! From using multiple accounts for your work-life balance to keeping chats private with passcodes, it’s all about tailoring it to your needs. What’s your go-to Telegram tip? 🤔✨ #TelegramTips #StayConnected
4️⃣ Use Multiple Accounts /
በትንሹ በ3 ስልክ ቁጥራችን 3 አካውንት እንከፍታለን
ቴሌግራም ከሌሎች አፖች ወሳኙ መለያው በአንድ ስልካችን ላይ ከከፈትነው ቴሌግራም አካውንት በተጨማሪ ቢያንስ 2 ተጨማሪ አካውንቶችን በተለያዩ ቁጥሮቻችን ለተለያየ ዓላማ አካውንቶችን መክፈት ያስችለናል። ይህም የተለያዩ ሥራዎችን ለይተን ለምሳሌ የግል፣ የሥራ እና የንግድ ብለን ከፋፍለን በቀላሉ በመቀያየር ለመጠቀም ያስችለናል።
Telegram allows you to manage multiple accounts in one app without logging in and out repeatedly. You can keep personal, business, and work conversations separate while using the same device. This saves time, improves organization, and makes communication faster, easier, and more professional every day.
3️⃣ Protect with Passcode Lock /
ቴሌግራም የራሱ ፓስዎርድ ስላለው እፎይ ነው
የቴሌግራም ወዳጅ ያደረገኝ 3ኛው ሀቅ ከሌሎች አፖች በተለየ ሁኔታ ወደ ቴሌግራማችን ከእኛ ፈቃድ ውጪ ማንም ሰው ገብቶ መረጃዎቻችንን እንዳይመዘብር ፓስዎርድ ማድረግ አስችሎናል። ስለዚህ ስልካችን ቢጠፋ ወይም ሰው እጅ ቢገባ ቴሌግራማችንን ከፍቶ ማየት አይቻልም። Local Passcode ያላስገባችሁ ካላችሁ ፍጠኑ ፓስዎርድ አስገቡ።
Telegram allows you to secure your app with a passcode lock, fingerprint, or face unlock. This prevents unauthorized access to your private chats, files, and channels. Even if someone holds your phone, they cannot open Telegram without your permission, giving stronger personal privacy and security.
2️⃣ Telegram Multi-Device Connectivity /
ቴሌግራም ፍላሽ ዲስክን እንድረሳው አድርጎኛል
ቴሌግራምን እጅግ በጣም እንድወደው ያደረገኝ 2ኛው ምክንያቴ ፋይል ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ ፍላሽን ስላስረሳኝ ነው። ለምሳሌ ከሞባይሌ ወደ ኮምፒዩተሬ ፋይል ለማስተላለፍ በፍላሽ ዲስክ ቫይረስ ያደርስብኝ የነበረውን ስቃይ እርግፍ አድርጎ ስላስቀረልኝ ነው። በአንዴ ያሉኝ ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ እና ታብሌት ላይ ይህንን አፕ በተመሳሳይ ጊዜ በመጠቀም የላኩትን ፋይል ሁሉም ቦታ ማግኘት በመቻሌ እፎይ ካልኩኝ ቆየሁኝ።
Telegram works smoothly across phones, tablets, and desktop computers at the same time. You can instantly access messages, photos, videos, and documents from any device without needing USB flash disks. Its cloud storage makes file transfer faster, easier, and more convenient for daily personal and business use.
1️⃣ Telegram Privacy & Freedom of Speech /
ቴሌግራም ለሰው ልጆች በነፃነት መተንፈሻ ትጥቅ ነው
ቴሌግራም ለሰው ልጆች የራሳቸውን ግላዊ ነፃ ንግግሮች እና ፅሁፎች ያለማንም ከልካይነት እና ክትትል በነፃነት መግለፅ ይችሉ ዘንድ ቴሌግራም መስራቹ ፓቬል ዱሮቭ የሚመራው ልዩ አፕ ነው። ከሌሎቹ የመልዕክት መላላኪያ አፖች ቴሌግራም ከየትኛውም መንግስታት እና ተፅእኖ ፈጣሪ አካላት ተገዢነት ነፃ ሲሆን ተጠቃሚዎች ያለ ገደብ እና ቁጥጥር 100% በነፃነት ያለስጋት ይህንን አፕ እንዲጠቀሙ አስችሏል።
Telegram is trusted for strong privacy and freedom of communication. It offers Secret Chats with end-to-end encryption, self-destruct messages, and strong account protection. Unlike many platforms, Telegram protects user independence, supports free expression, and gives users more control over their conversations, data, and digital privacy.
ቴሌግራም የዓለማችን ምርጡ የመልዕክት መለዋወጫ App ሲሆን፣ በ2026 ደግሞ በርካታ አዳዲስ ገፅታዎችን በመጨመር በተለይ የAI የጽሑፍ አርትዖትን አካቶ ከፍ ብሏል።
በተጨማሪም ሀይለኛ የሕዝብ አስተያየት መስጫዎች፣ የቀጥታ ፎቶዎች ስርጭት፣ የተጠበቀ/የተቆለፈ ይዘት እና ጠንካራ የቻናል መሳሪያዎችን በማካተት ተፅእኖ ፈጣሪነቱን ጨምሯል።
ለእኔ ቴሌግራምን ለምን በጣም እንድወደው ያደረጉኝን በቀጣይ 30 አስደማሚ እውነታዎችን አጋራችኋለሁ፣ አብራችሁኝ ቆዩ።
+1
ቴሌግራም በኮምፒውተር እየተጠቀሙ አማርኛ አላነብ ብሎታል ?
ከሰሞኑ የቴሌግራም መተግበሪያ የዊንዶው ቨርዥን አማርኛ ጹሑፎችን ለማንበብ ሲቸገር ተስተውሏል።
ቴሌግራም በኮምፒውተር የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻችን ከታዩን ቅደም ተከተል በመጠቀም አማርኛ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
Setting > Chat Setting > Font Family > ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን የአማርኛ ፎንት ይምረጡ (ለምሳሌ፦ Ebrima, Nyala , Noto sans . . .) > Save > Restart
አማርኛ ፎንት በአማራጭ ውስጥ የማያገኙ ከሆነ የሚፈልጉትን ፎንት ቀጥታ ካወረዳችሁ በኋላ ቴሌግራማችሁን እንደ አዲስ በመክፈት መምረጥና ማስተካከል ይችላሉ።
ለአብነትም፥ Noto sans የተሰኘውን ፎንት https://fonts.google.com/noto/specimen/Noto+Sans+Ethiopic ላይ ማውረድ ይችላሉ።
አማርኛ ፎንት ስለመረጡ አማርኛ ብቻ ነው የሚያነበው ማለት አይደለም የላቲን ፊደላትንም ማንበብ ያስችላችኋል።
✅TADE TG TIPS-260925-1✅
እንደሚታወቀው ከላይ እንደ ማሳያ የተቀመጡትን አይነት የአማርኛ የተለያዩ የሚያምሩ ፎንቶችን ወይም መልከ ፊደሎችን ከጥቂት አመታት በፊት ማግኘት አዳጋች ነበር። ምክንያቱም የእኛ ሀገር ባለሙያዎች በኮምፒዩተሮቻችን እንጠቀምበት ዘንድ ስላልሰሩልን ነበር። አሁን ግን ምስጋና ለሀገሬ ልጆች ይሁንና እጅግ በጣም አስደማሚ የሆኑ ፎንቶችን ወይም መልከ ፊደሎችን ወጣቶቻችን እያሳዩን ነው።
ከላይ በZipped Folder ውስጥ ያስቀመጥኩላችሁ ከ100 በላይ የአማርኛ ፎንቶች ወይም መልከ ፊደሎች እጅግ እንደሚጠቅሟችሁ እርግጠኛ ነኝ። እያንዳንዱን ኮምፒዩተሮቻችሁ እና ላፕቶፓችሁ ላይ Install በማድረግ/ በመጫን እንደ እንግሊዝኛው አማርኛውንም ተራቀቁበት።
መልካም በዓል!
ውድ የቻናሌ የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለደመራው እና ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
መልካም በዓል ይሆንላችሁ ይሆንልን ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው።
✅TADE TG TIPS-240925-1✅
ይህ Application ሁሉንም የስልክ መረጃ አበጥሮ ስለሚያስቀምጥ በተለይ ስልክ ከሰው ለመግዛት ስታስቡ ይህንን ጭናችሁ ጠቃሚ ነጥቦችን ብታውቁ ለውሳኔ ይረዳችኋል።
የገዛችሁትን አዲስ ስልክ ውስጡ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ተቸግራችኋል?
ወይም ደግሞ
ከሰው ለመግዛት ያሰባችሁት ስልክ ውስጡ ምን እንደሚመስል ለማወቅ አዳጋች ሆኖባችኋል?
እንግዲያውስ ልክ ከላይ ለምሳሌ በScreenshot እንዳሉት ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት እነሆ እኔ ተጠቅሜበት ስለ ስልኮቼ በዝርዝር ያስረዳኝን Application ላስተዋውቃችሁ
+1
አሁን ግን የቻናሉ አባላት ከ4ሺ ወደ 2ሺ እያሽቆለቆለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቴሌግራምን በተመለከተ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ለምን ወደ እናንተ አላቀርብም ብዬ ስሙን ቀይሬ ተመልሻለሁ። ስለዚህ ለእናንተ በቀን ተቀን ሥራችሁ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናቸው የምላቸውን እኔ ተገልግዬ የጠቀሙኝን የTelegeram Best Tips በተከታታይ ወደ እናንተ ማድረሴን እጀምራለሁ። በቤተሰብነት አብረን እንቆይ። ለሌሎችም አጋሯቸው። የለቀቁት አባላትም ተመልሰው ይቀላቀሉናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
አመሰግናለሁ።
ውድ የቻናሌ አባላት
እንደምን አላችሁ? እንደምንስ ከረማችሁ? እንደምንስ ሰነበታችሁ?
እኔ እግዚአብሔር ይመስገን እጅግ በጣም ደህና ነኝ።
እንደሚታወቀው የቴልግራም ክሪፕቶ ዓለም ከአመት በፊት እጅግ መነቃቃትን ፈጥሮ በርካቶቻችን በተስፋ ከመደበኛ ሥራችን ጎን ለጎን ተፍ ተፍ ስንል ነበር።
በተለይ የሞባይል ስክሪናችንን ታብ ታብ በማድረግ ያላጎረጎድን የለንም 🫣😜😂
ሆኖም ያሰብነውን ያክል ማግኘት ካለመቻላችን በላይ ይበልጥ ተጠቃሚ የሆኑት በርካታ አባላትን ያፈሩ ባለቻናሎች ሆኑና በርካቶቻችን የበይ ተመልካች ሆነናል።
ከዚያም በተረፈ ደግሞ የክሪፕቶ ዓለም የሚተነበይበት ካለመሆኑ ጋር ተዳምሮ ሲስተሙን ተረድቶ የመግዣ እና የመሸጫ ወቅት በትክክል መከተል ከባድ ነበር። በዚህና መሰል ኹነቶች የተነሳ እኔም ወደ መደበኛ ስራዬ በማተኮሬ በቴሌግራም ክሪፕቶ ላይ እንደ ቀድሞ እምብዛም ተሳታፊ መሆን አልቻልኩም።
ግን ቢያንስ በድምሩ የአንድ ሞባይል ወጪን መሸፈን መቻሌ ይሁና ብዬ ባልፈውም፣ ነገር ግን ካጠፋሁት ጊዜ እና የአዕምሮ ድካም ጋር ምንም አይስተካከልም ነበር። ይሁና ምን ይደረጋል፣ መቼም ስለ Crypto ይበልጥ ማወቅ ችለናል ብዬ አምናለሁ። ወደፊት የተሻለ መንገድ ካለ እንመለስበት ይሆናል።
+4
🤖 5-Nov-2024
🔔🔠🅰️🔠🔠🔠🅰️🔠 ❤️ Code
⭐️ Total 4M, but 2M Added to Balance
🎟 🔠🔠🔠🔠🔠 ➖ 5️⃣3️⃣
All in one
ለእያንዳንዱ 10 ደቂቃ መጠበቅ ግድ ነው።🤖 🔤🔤🔤🔤🔤 በቀላሉ ለመጫወት 🛡 START 🛡
