es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Telegram 🧲 Best Tips 🇪🇹

Telegram 🧲 Best Tips 🇪🇹

Ir al canal en Telegram

እንኳን ደህና መጣችሁ። በቴሌግራም ከመፃፃፍ እና ዳታ ከመላላክ በተጨማሪ በርከት ያሉ ሥራዎችን መስራት ይቻላል። 📜 በዚህ ቻናሌ ትክክለኛ የቴሌግራም አሪፍ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል 🔞 በኃላፊነት መረጃዎችን እንጠቀም ለሌሎችም እናጋራ 🤝 ስልካችንን ከመደዋወል እና ከማህበራዊ ሚድያ መከታተያነት ይልቅ ለራሳችን እንጠቀምበት

Mostrar más
1 496
Suscriptores
-224 horas
-97 días
-1930 días
Archivo de publicaciones
📌 ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ላይ Sleep፣ Hibernate እና Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው❓ ኮምፒውተራችን እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትና ለረጅም ጊዜ ሲሰራ ከተለመደው ፍጥነቱ ይዘገያል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ ኮምፒውተራችንን ተገቢውን እረፍት መስጠት ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ኮምፒውተርን ለማሳረፍ Sleep፣ Hibernate ወይስ Shutdown ማድረጉ ይሻላል? የ3ቱን አማራጮች ልዩነትና ጥቅሞች ከዚህ በታች በዝርዝር እንመልከት፡ 1. 💤 Sleep Mode (ለአጭር ጊዜ እረፍት)
ኮምፒውተርዎን Sleep ሲያደርጉት ስክሪኑና ፕሮሰሰሩ ይዘጋሉ፤ ነገር ግን እስከዚያ ያከናወኗቸው ስራዎች በሙሉ በRAM ላይ ተከዝነው ይቆያሉ። እንዴት ይሰራል? ከRAM በስተቀር ወደ ሁሉም ክፍሎች የሚሄደው የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል። RAM መረጃውን እንዳይረሳ አነስተኛ የባትሪ ኃይል ይጠቀማል። ጥቅሙ፡ መልሰው ሲከፍቱት በሰከንዶች ውስጥ በፍጥነት ስራ ወደነበሩበት ይመለሳል። መቼ እንጠቀመው? ለጥቂት ደቂቃዎች ወይም ሰዓታት ከኮምፒውተራችን ራቅ ስንል (ለምሳሌ ለምሳ ወይም ለአጭር እረፍት)። ጉዳቱ፡ ባትሪው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ያልተቀመጡ (Unsaved) ፋይሎች ሊጠፉ ይችላሉ።
2. 🐻 Hibernate Mode (ለመካከለኛ ጊዜ እረፍት)
ይህ አማራጭ በSleep እና በShutdown መካከል የሚገኝ ነው። እንዴት ይሰራል? ኮምፒውተሩ ከመጥፋቱ በፊት በRAM ላይ ያሉትን መረጃዎች (ያልተቀመጡ ፋይሎች፣ ክፍት የብራውዘር ታቦችና አፕሊኬሽኖች) በሙሉ ወደ Hard Drive/SSD ያስቀምጣቸዋል። ጥቅሙ፡ የላፕቶፑ ባትሪ ቢ አልቅ ወይም ባትሪው ቢወልቅ እንኳ መረጃዎች ሃርድ ድራይቭ ላይ ስለሚቀመጡ ምንም ነገር አይጠፋም። ኮምፒውተሩ በምንም አይነት መንገድ ኃይል አይጠቀምም። መቼ እንጠቀመው? ስራችንን ሳንዘጋ ለብዙ ሰዓታት ወይም ለቀናት ኮምፒውተራችንን ማስቀመጥ ስንፈልግና ባትሪ እንዳይበላብን ስንፈልግ።
3. 🔌 Shutdown (ሙሉ በሙሉ ማጥፋት)
ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ የሚዘጋና የነበሩትን ሂደቶች የሚያቆም አማራጭ ነው። እንዴት ይሰራል? ሁሉም የተከፈቱ ፕሮግራሞች ይዘጋሉ፤ በRAM ላይ ያለው መረጃ ይጸዳል፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙም ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። ጥቅሙ፡ ኮምፒውተሩ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ኃይል አይጠቀምም። በተጨማሪም ጊዜያዊ ፋይሎችን (RAM Temp Files) ስለሚያጸዳ ኮምፒውተሩ ሲነሳ ትኩስና የተቀላጠፈ እንዲሆን ይረዳል። መቼ እንጠቀመው? ኮምፒውተሩን ለረጅም ጊዜ (ለምሳሌ ለቀናት/ሳምንታት) የማንጠቀመው ከሆነ ወይም ሲስተሙ እንዲታደስ (Reset እንዲሆን) ስንፈልግ።
💡 ባጭሩ ለመወሰን፡ ለአጭር እረፍት (1-2 ሰዓት): ➡️ Sleep ስራ ሳይዘጋ ለረጅም ሰዓት/ለማደር: ➡️ Hibernate ስራ ጨርሶ ሙሉ በሙሉ ለማሳረፍ: ➡️ Shutdown

የኤአይ (AI) ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመጣ ቁጥር፣ በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት የምንመለከታቸው ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እንዲሁም ድምፆች በሰው ልጅ የተሰሩ ይሁኑ ወይም በኤአይ የተፈጠሩ
የኤአይ (AI) ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመጣ ቁጥር፣ በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት የምንመለከታቸው ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እንዲሁም ድምፆች በሰው ልጅ የተሰሩ ይሁኑ ወይም በኤአይ የተፈጠሩ መለየቱ ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል። ይህንን ችግር ለመፍታት Google ይዘቶች በኤአይ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚሰጥ SynthID የተሰኘ ፕላትፎርም አስተዋውቋል። በዚህ ፕላትፎርም አማካኝነት በGoogle AI የተፈጠሩ ይዘቶችን ብቻ ሳይሆን የOpenAI፣ NVIDIA፣ Kakao እና በቅርቡ ደግሞ የApple AI ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሰሩ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችንና ድምፆችን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።
አጠቃቀም፡ 1. https://synthid.com/ ድህረ ገጽ ላይ በመግባት በGoogle አካውንታችሁ Login አድርጉ። 2. ማረጋገጥ የምትፈልጉትን ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም የድምፅ ፋይል በማስገባት በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።

+2
በሩሲያ ሳራቶቭ ከተማ በሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ “Syoma” የተባለ ሮቦት አንድ ደንበኛን ለማጥቃት ሲሞክር የሚያሳይ የደህንነት ካሜራ ቪዲዮ ከሰሞኑ ተሰራጭቶ መነጋገሪያ ሆኗል። ቪዲዮው ላይ ደንበኛው ሮቦቱን ከገፋው በኋላ፣ ሮቦቱ ወደ እሱ በመሄድ በእግሩ ለመርገጥና ለመደባደብ ሲሞክር ይታያል። ደንበኛው በፍጥነት ከቦታው ሲሸሽ የሱቁ ሰራተኞች ሮቦቱን አስቁመዋል። በኋላም ሮቦቱ እንደገና እንዲነሳ (reboot) ተደርጓል። በሩሲያው ክስተት ላይ ሮቦቱ ለምን በዚህ መንገድ ምላሽ እንደሰጠ የቴክኒክ ስህተት፣ የስርዓት ችግር፣ የቁጥጥር ችግር ወይም ሌላ ምክንያት በግልጽ አልታወቀም። ተመሳሳይ የሚመስል ክስተት በቻይና ዜጂያንግ ግዛትም ተመዝግቧል። የደህንነት ካሜራ ቪዲዮ እንደሚያሳየው፣ አንድ ሮቦት የሰራውን መሐንዲስ ሊያጠቃ ሲሞክር ታይቷል። በቪዲዮው ላይ ሮቦቱ መሬት ላይ ተንበርክኮ ወደነበረው መሐንዲስ በመሄድ፣ በእጁ የያዘውን የርቀት መቆጣጠሪያ በእግሩ መትቶ ሲጥለው ይታያል። ሮቦቱ ያደረገው ድንገተኛ እንቅስቃሴ ምን እንዳስከተለው ግን ጥያቄ አስነስቷል። በሌላኛው የቢሮ ካሜራ የተጋራው ቪድዮ እንደሚያሳየው ደግሞ ከቁጥጥር ውጪ የሆነውን ሮቦት ሠራተኞች ሊያረጋጉት ሲታገሉ ነገር ግን አሻፈረኝ ብሎ ሲረግጣቸው ይታያል። ሶስቱ ክስተቶች የAIና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂዎች የበለጠ ራሳቸውን ችለው እየሰሩ በሚሄዱበት ወቅት፣ ሮቦቶች ባልተጠበቀ መንገድ እርምጃ ቢወስዱና ጉዳት ቢያደርሱ ለዚያ ድርጊት ተጠያቂው ማን ይሆናል? የሚል ጥያቄ አስነስተዋል።
ታድያ እስኪ አስቡትና በቀጣይ ጊዜያት እናንተ ከሮቦት ጋር ቢሮ ውስጥ እየሰራችሁ ከሰው ትዕዛዝ አልፎ እንዲህ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ በሮቦት ብትደበደቡ ምን ይሰማችኋል? ምንስ ታደርጋላችሁ?

Telegram is introducing Gram Wallet for everyday payments, transfers and purchases inside the app, aimed at its one billion u
Telegram is introducing Gram Wallet for everyday payments, transfers and purchases inside the app, aimed at its one billion users. The old "Wallet in Telegram" is now Walt, a separate app for trading, investing and earning yield. Existing Walt users keep their accounts and funds, and the rebrand took effect on September 28. Gram Wallet is rolling out in stages. ቴሌግራም ለዕለታዊ ክፍያዎች፣ ዝውውሮችና ግዢዎች የሚያገለግል "ግራም ዋሌት" (Gram Wallet) አስተዋውቋል፤ ለ1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችም ደረጃ በደረጃ ይዳረሳል። የቀድሞው "Wallet in Telegram" ደግሞ "Walt" ተብሎ ስሙ ተቀይሯል፤ ለግብይት፣ ለኢንቨስትመንትና ለትርፍ ማግኛ አገልግሎቶች ያገለግላል። ነባር ተጠቃሚዎች መለያቸውንና ገንዘባቸውን ሳይቀይሩ መጠቀም ይችላሉ።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ ! መልካም በዓል !
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ ! መልካም በዓል !

መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይሁንላችሁ ! መልካም በዓል !
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይሁንላችሁ ! መልካም በዓል !

የቴሌግራም አካውንታችሁን ከጠላፊዎች ጠብቁ፣ ያገኛችሁትን Link ከመንካት ተቆጠቡ፣ አጓጊ እና ቀልብ ከሚስቡ ማስፈንጠሪያዎች ተጠንቀቁ።
የቴሌግራም አካውንታችሁን ከጠላፊዎች ጠብቁ፣ ያገኛችሁትን Link ከመንካት ተቆጠቡ፣ አጓጊ እና ቀልብ ከሚስቡ ማስፈንጠሪያዎች ተጠንቀቁ።

8⃣ Telegram ask you regularly for two-step / ቴሌግራም ከመንታፊዎች እራሳችሁን ጠብቁ ይላል ከላይ ቴሌግራማችሁን በፓስኮድ መዝጋት ጠቃሚ መሆኑን ሳነሳ፣ ለዘላለም ትጠበቁ ዘን
8⃣ Telegram ask you regularly for two-step / ቴሌግራም ከመንታፊዎች እራሳችሁን ጠብቁ ይላል ከላይ ቴሌግራማችሁን በፓስኮድ መዝጋት ጠቃሚ መሆኑን ሳነሳ፣ ለዘላለም ትጠበቁ ዘንድ ደግሞ የጀርባውን ተጨማሪ two-step verification ይለፍ ቃል ማስገባቱ ግዴታ መሆኑን ከላይ አስርሜበታለሁኝ። እናም ቴሌግራም ደስ የሚለው ንቁ እንድትሆኑ በየተወሰነ ጊዜ የጀርባ በር ይለፍ አስገብታችኋል ብሎ ያስታውሳችኋል። ይህ ከአደጋ ተከላካይ ማስታወሻ በመሆኑ በጣም ይመቸኛል፣ ብሎም ይለፍ ቃሉን እንዳልረሳ ያስታውሰኛል።
Staying secure on Telegram is super important! 🛡️ One personal tip? Always enable the passcode lock. It’s saved me from unintended snoopers on my phone! 🔒 And don’t forget to check the Privacy settings regularly. Keep your chats safe and sound! 💬 #TelegramTips #PrivacyFirst

7⃣ Two-step verification is your Telegram Survival/ የጀርባ የዘላለም ይለፍ ቃል ካለ ቴሌግራማችሁ የናንተ ነው ከላይ ቴሌግራም የራሱ የሆነ ፓስኮድ (ይለፍ ቃል) እንዳለ
7⃣ Two-step verification is your Telegram Survival/ የጀርባ የዘላለም ይለፍ ቃል ካለ ቴሌግራማችሁ የናንተ ነው ከላይ ቴሌግራም የራሱ የሆነ ፓስኮድ (ይለፍ ቃል) እንዳለው ያወራነው እንዳለ ሆኖ ይህንን ማጠንከሪያ እና ስልካቹ እንኳን ቢጠፋ ወይም አጋጣሚ ፓስኮዱ ሌላ ሰው እጅ ቢገባ መልሳችሁ በእጃችሁ ለማድረግ two-step verification የሚባለውን ጠንካራ ሌላ የጀርባ የይለፍ ቃል ማስገባት ግድ ይላችኋል። ይህ የኋላ ደጀን የቴሌግራማችሁ አለኝታ እና የዘላለም ህልውና ነው። ግን ይለፍ ቃሉ መረሳት የለበትም።
🔒 Staying safe on Telegram is easier than you think! Always enable two-step verification for extra security. Remember to check privacy settings; control who can see your info. Lastly, be cautious about sharing personal details in chats. Let's keep our conversations secure and private! 😊 #TelegramTips #StaySafe

6⃣ The pin option for your important infos / በጣም አንገብጋቢ መረጃዎችን ሁሌም ከፊት ቴሌግራም ስትጠቀሙ በርካታ አንገብጋቢ መረጃዎችን ከቻቶች ውስጥ የት እንዳሉ በመፈለግ
6⃣ The pin option for your important infos / በጣም አንገብጋቢ መረጃዎችን ሁሌም ከፊት ቴሌግራም ስትጠቀሙ በርካታ አንገብጋቢ መረጃዎችን ከቻቶች ውስጥ የት እንዳሉ በመፈለግ ጊዚያችሁ ተቃጥሎ ይሆን? እንግዲያውስ ከቻቶች መካከል ቀላሉ መለያ የፈለጋችሁትን መረጃ ጫን በማለት ፒን ስታደርጉት ከላይ ሁሌም ቁጭ ይላል፣ በቃ ከዚያ ውስጥ ፈለግ ፈለግ ማድረግ ብቻ 😎
✨ Have you ever struggled with organizing your chats? I totally get it! One little trick I love is using pinned messages to keep important info at the top. It’s super handy! What’s your favorite Telegram tip? Let’s share ideas! #TelegramTips #ChatOrganization

5⃣ Monthly new updates & amazing features / በየወሩ አዳዲስ ገፅታዎችና አስገራሚ ይዘቶች እንደ ቴሌግራም ምርጥ አፕ አይቼ አላውቅም ስላችሁ በምክንያት ነው፣ እጅግ በጣም ለአ
5⃣ Monthly new updates & amazing features / በየወሩ አዳዲስ ገፅታዎችና አስገራሚ ይዘቶች እንደ ቴሌግራም ምርጥ አፕ አይቼ አላውቅም ስላችሁ በምክንያት ነው፣ እጅግ በጣም ለአጠቃቀም ቀላል ከመሆኑ ባሻገር በየወሩ የሚለቃቸው ማሻሻያዎች የቱን ይዤ የቱን ልልቀቀው ያስብላል። እናም ቴሌግራምን አብልጬ እንድወደው የሚያደርገኝ አንዱ ማንነቱ ይህ ነውና ግዴለም ትክክለኛ ቦታ ነው ያላችሁትና ቴሌግራም መጠቀሙን ቀጥሉበት።
Ever struggled with Telegram’s endless features? I get it! From using multiple accounts for your work-life balance to keeping chats private with passcodes, it’s all about tailoring it to your needs. What’s your go-to Telegram tip? 🤔✨ #TelegramTips #StayConnected

4️⃣ Use Multiple Accounts / በትንሹ በ3 ስልክ ቁጥራችን 3 አካውንት እንከፍታለን ቴሌግራም ከሌሎች አፖች ወሳኙ መለያው በአንድ ስልካችን ላይ ከከፈትነው ቴሌግራም አካውንት በተጨማሪ
4️⃣ Use Multiple Accounts / በትንሹ በ3 ስልክ ቁጥራችን 3 አካውንት እንከፍታለን ቴሌግራም ከሌሎች አፖች ወሳኙ መለያው በአንድ ስልካችን ላይ ከከፈትነው ቴሌግራም አካውንት በተጨማሪ ቢያንስ 2 ተጨማሪ አካውንቶችን በተለያዩ ቁጥሮቻችን ለተለያየ ዓላማ አካውንቶችን መክፈት ያስችለናል። ይህም የተለያዩ ሥራዎችን ለይተን ለምሳሌ የግል፣ የሥራ እና የንግድ ብለን ከፋፍለን በቀላሉ በመቀያየር ለመጠቀም ያስችለናል።
Telegram allows you to manage multiple accounts in one app without logging in and out repeatedly. You can keep personal, business, and work conversations separate while using the same device. This saves time, improves organization, and makes communication faster, easier, and more professional every day.

3️⃣ Protect with Passcode Lock / ቴሌግራም የራሱ ፓስዎርድ ስላለው እፎይ ነው የቴሌግራም ወዳጅ ያደረገኝ 3ኛው ሀቅ ከሌሎች አፖች በተለየ ሁኔታ ወደ ቴሌግራማችን ከእኛ ፈቃድ ውጪ
3️⃣ Protect with Passcode Lock / ቴሌግራም የራሱ ፓስዎርድ ስላለው እፎይ ነው የቴሌግራም ወዳጅ ያደረገኝ 3ኛው ሀቅ ከሌሎች አፖች በተለየ ሁኔታ ወደ ቴሌግራማችን ከእኛ ፈቃድ ውጪ ማንም ሰው ገብቶ መረጃዎቻችንን እንዳይመዘብር ፓስዎርድ ማድረግ አስችሎናል። ስለዚህ ስልካችን ቢጠፋ ወይም ሰው እጅ ቢገባ ቴሌግራማችንን ከፍቶ ማየት አይቻልም። Local Passcode ያላስገባችሁ ካላችሁ ፍጠኑ ፓስዎርድ አስገቡ።
Telegram allows you to secure your app with a passcode lock, fingerprint, or face unlock. This prevents unauthorized access to your private chats, files, and channels. Even if someone holds your phone, they cannot open Telegram without your permission, giving stronger personal privacy and security.

2️⃣ Telegram Multi-Device Connectivity / ቴሌግራም ፍላሽ ዲስክን እንድረሳው አድርጎኛል ቴሌግራምን እጅግ በጣም እንድወደው ያደረገኝ 2ኛው ምክንያቴ ፋይል ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ
2️⃣ Telegram Multi-Device Connectivity / ቴሌግራም ፍላሽ ዲስክን እንድረሳው አድርጎኛል ቴሌግራምን እጅግ በጣም እንድወደው ያደረገኝ 2ኛው ምክንያቴ ፋይል ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ ፍላሽን ስላስረሳኝ ነው። ለምሳሌ ከሞባይሌ ወደ ኮምፒዩተሬ ፋይል ለማስተላለፍ በፍላሽ ዲስክ ቫይረስ ያደርስብኝ የነበረውን ስቃይ እርግፍ አድርጎ ስላስቀረልኝ ነው። በአንዴ ያሉኝ ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ እና ታብሌት ላይ ይህንን አፕ በተመሳሳይ ጊዜ በመጠቀም የላኩትን ፋይል ሁሉም ቦታ ማግኘት በመቻሌ እፎይ ካልኩኝ ቆየሁኝ።
Telegram works smoothly across phones, tablets, and desktop computers at the same time. You can instantly access messages, photos, videos, and documents from any device without needing USB flash disks. Its cloud storage makes file transfer faster, easier, and more convenient for daily personal and business use.

1️⃣ Telegram Privacy & Freedom of Speech / ቴሌግራም ለሰው ልጆች በነፃነት መተንፈሻ ትጥቅ ነው ቴሌግራም ለሰው ልጆች የራሳቸውን ግላዊ ነፃ ንግግሮች እና ፅሁፎች ያለማንም ከ
1️⃣ Telegram Privacy & Freedom of Speech / ቴሌግራም ለሰው ልጆች በነፃነት መተንፈሻ ትጥቅ ነው ቴሌግራም ለሰው ልጆች የራሳቸውን ግላዊ ነፃ ንግግሮች እና ፅሁፎች ያለማንም ከልካይነት እና ክትትል በነፃነት መግለፅ ይችሉ ዘንድ ቴሌግራም መስራቹ ፓቬል ዱሮቭ የሚመራው ልዩ አፕ ነው። ከሌሎቹ የመልዕክት መላላኪያ አፖች ቴሌግራም ከየትኛውም መንግስታት እና ተፅእኖ ፈጣሪ አካላት ተገዢነት ነፃ ሲሆን ተጠቃሚዎች ያለ ገደብ እና ቁጥጥር 100% በነፃነት ያለስጋት ይህንን አፕ እንዲጠቀሙ አስችሏል።
Telegram is trusted for strong privacy and freedom of communication. It offers Secret Chats with end-to-end encryption, self-destruct messages, and strong account protection. Unlike many platforms, Telegram protects user independence, supports free expression, and gives users more control over their conversations, data, and digital privacy.

ቴሌግራም የዓለማችን ምርጡ የመልዕክት መለዋወጫ App ሲሆን፣ በ2026 ደግሞ በርካታ አዳዲስ ገፅታዎችን በመጨመር በተለይ የAI የጽሑፍ አርትዖትን አካቶ ከፍ ብሏል። በተጨማሪም ሀይለኛ የሕዝብ አስተ
ቴሌግራም የዓለማችን ምርጡ የመልዕክት መለዋወጫ App ሲሆን፣ በ2026 ደግሞ በርካታ አዳዲስ ገፅታዎችን በመጨመር በተለይ የAI የጽሑፍ አርትዖትን አካቶ ከፍ ብሏል። በተጨማሪም ሀይለኛ የሕዝብ አስተያየት መስጫዎች፣ የቀጥታ ፎቶዎች ስርጭት፣ የተጠበቀ/የተቆለፈ ይዘት እና ጠንካራ የቻናል መሳሪያዎችን በማካተት ተፅእኖ ፈጣሪነቱን ጨምሯል። ለእኔ ቴሌግራምን ለምን በጣም እንድወደው ያደረጉኝን በቀጣይ 30 አስደማሚ እውነታዎችን አጋራችኋለሁ፣ አብራችሁኝ ቆዩ።

ቴሌግራም በኮምፒውተር እየተጠቀሙ አማርኛ አላነብ ብሎታል ? ከሰሞኑ የቴሌግራም መተግበሪያ የዊንዶው ቨርዥን አማርኛ ጹሑፎችን ለማንበብ ሲቸገር ተስተውሏል። ቴሌግራም በኮምፒውተር የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻች
+1
ቴሌግራም በኮምፒውተር እየተጠቀሙ አማርኛ አላነብ ብሎታል ? ከሰሞኑ የቴሌግራም መተግበሪያ የዊንዶው ቨርዥን አማርኛ ጹሑፎችን ለማንበብ ሲቸገር ተስተውሏል። ቴሌግራም በኮምፒውተር የምትጠቀሙ ቤተሰቦቻችን ከታዩን ቅደም ተከተል በመጠቀም አማርኛ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። Setting > Chat Setting > Font Family > ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን የአማርኛ ፎንት ይምረጡ (ለምሳሌ፦ Ebrima, Nyala , Noto sans . . .) > Save > Restart አማርኛ ፎንት በአማራጭ ውስጥ የማያገኙ ከሆነ የሚፈልጉትን ፎንት ቀጥታ ካወረዳችሁ በኋላ ቴሌግራማችሁን እንደ አዲስ በመክፈት መምረጥና ማስተካከል ይችላሉ። ለአብነትም፥ Noto sans የተሰኘውን ፎንት https://fonts.google.com/noto/specimen/Noto+Sans+Ethiopic ላይ ማውረድ ይችላሉ።  አማርኛ ፎንት ስለመረጡ አማርኛ ብቻ ነው የሚያነበው ማለት አይደለም የላቲን ፊደላትንም ማንበብ ያስችላችኋል።